Mezmur Lyrics™ @amharic_spiritual_song_lyrics Channel on Telegram

Mezmur Lyrics

@amharic_spiritual_song_lyrics


WE ARE YOUR 1⃣ CHOICE







....እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ....
ቆላ 1:18

Mezmur Lyrics™ (Amharic)

መዝሙር ጽሁፍ™ is a Telegram channel dedicated to sharing the lyrics of Amharic spiritual songs, also known as Mezmur. With the username @amharic_spiritual_song_lyrics, this channel aims to provide a platform for enthusiasts of Ethiopian religious music to connect and engage with the beautiful and uplifting lyrics of Mezmur. Whether you are looking to learn the words of your favorite songs or simply appreciate the poetic nature of Amharic spiritual music, Mezmur Lyrics™ is your go-to choice. Our channel is designed to be a hub for those who seek spiritual enlightenment and inspiration through the power of music. Join us on this journey of discovery and immerse yourself in the rich culture and tradition of Ethiopian Mezmur. Let the words of these songs touch your soul and lift your spirits to new heights. Mezmur Lyrics™ - where the beauty of Amharic spiritual songs comes to life.

Mezmur Lyrics

07 Apr, 16:04


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 20 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.

Mezmur Lyrics

15 May, 13:34


🏵 ውሎህን ቃኝ"! 🏵

አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት፡፡

" ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ?
ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::
አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም፤ እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል፤ ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው፡፡ ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ለንብ ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት

🐝☞ "ውሎሽ የት ነው?"
◽️◼️◽️◼️◽️◼️◽️◼️◽️◼️◽️◼️

☞እንግዲህ እዚህ ጋር ቆም እንበል፣
ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ፤ መቼም ማንም በጤፍ ማሳ ላይ ስንዴን አይጠበቅም።
ስለዚህ ምንጊዜም ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ምክንያቱም ሀሳባችን ስራችንን፤ ስራችን ውጤታችንን፤ ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና፡፡
🏅 ካነበብነው 🏅
🙏 መልካም ጊዜ ተመኘን 🙏

@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

13 May, 18:16


ፓስተር ታምራት ፡ ሃይሌ
#ታሪኬ_የጀመረው

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)


ከወህኒ ከፍርድ እኔኑ ሊያወጣ
ከድንግል ማርያም ሥጋ ለብሶ መጣ
መልክ ውበቱን ተወ የባርያን መልክ ያዘ
እስከ መስቀል ሞት በፍቅር ታዘዘ
ከአደረገው በቀር ኢየሱሴ ምንም ታሪክ የለኝ የእራሴ

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)


በቃሉ እውነተኛ በተግባሩም ደግ
ከፋት የሌለበት የእግዚአብሔር በግ
እኔን ሊያዘምረኝ እርሱ አለቀሰ
እኔን ሊያከብረኝ ወረትን ለበሰ
ከሥም ሁሉ በላይ ሥም አለው
ዛሬም ምሥጋናዬ ለእርሱ ነው

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)


ብዙ የነበረውን እዳዬን ሻረልኝ
ኃጢአቴን ሁሉ ከኋላው ጣለልኝ
በመስቀል ጠርጐ ከእኔ አስወግዶ
ጨካኙን ከሳሼን ባዶ እጁን ሰደደው
እዛጋ ጀመረ ታሪኬ ምሥጋና ይብሳለት አምላኬ

ታሪኬ የጀመረው በቀራኒዮ ነው
በመስቀሉ ግርጌ በአጋጣሚ አይደለም መወለድ ማደጌ
ሠይጣን ሲቀጠቀጥ እራሱን ሲመታ
ባርነቴ ሲሻር ሰንሰለት ሲፈታ
ጠላት ሲመሽበት ለእኔ ግን ሲነጋ
ኢኸው በታሪኬ ተጀመረ እዚያጋ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው ለጌታዬ
ምሥጋናዬ ምሥጋናዬ ይኼው በዜማዬ (፪x)
@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

07 May, 12:16


#ሠርቼ_ሳይሆን_ተቆጥሮልኝ......


❇️ እኔ በራሴ ደካማ ነኝ! #አልችልም! በመልካም ማንነት በጥንቃቄ ብራመድም ለጥቂት ነው እንጂ ፤ ተመልሼ እወድቃለሁ ፤ እንዲሁም እነሳለሁ። እድሜዬን በሙሉ ጠንካራ ሁኜ ያለምንም ስህተት መኖር አልችልም! ህጉንም ሁሉ መጠበቅም አልችልም! ምክንያቱም ፍጹም አይደለሁም።



በዚህ ሁኔታም ፤ ህግን በመጠበቅ እና በመልካም ሥራ የሚጸድቅ ማንነት የለኝም!.... #ብቁ_አይደለሁም ፤ እራሴን አላምንም! ምክንያቱም እጅግ ደካማ ነኝ [በመንፈስም ደሃ ነኝ]። #በሥራዬ_ብጸድቅ ፤ ነገ ደግሞ ስደክም ጽድቄን አጣዋለሁ። በእኔ ኃይል እና በሥራዬ ቢሆን ዛሬ ላይ ባልደረስኩ ነበር። #እንደ_ሥራዬ ቢሆንማ አጠቃላይ ውጤቴ የከፋ ነበር። በሥራዬ ቢሆን ፤ እንኳን በእግዚአብሔር ፊት #ልጸድቅ ይቅርና ፤ በሰዎች ፊት እንኳን ጻድቅ አልባልም ነበር።



አሁን ግን #የምጸድቀው_በሥራዬ_አይደለም! 😁 የምጸድቅበት አዲስ ተስፋ መጥቷል ፤ እርሱም #እምነት ይባላል። ያገኘሁትም #ጽድቅ የራሴ አይደለም! #ተቆጥሮልኝ እንጂ። በራሴ በየትኛውም ሥራ #የእግዚአብሔርን_ጽድቅ ላገኘው ስለማልችል ፤ #እንዲሁ_ተቆጠረልኝ ፤ ያውም የራሱ #የእግዚአብሔር _ጽድቅ። እኔ መሥራት ስላልቻልኩ #ልጁ ሥራዬን ሠራልኝ እና ለእኔ ለደካማው #ተቆጠረልኝ። ልጁ በሠራው እኔ እንዲሁ በእምነት ገባሁ ፤ ልጁ ህጉን በሙሉ መፈጸሙ ለእኔ #ተቆጠረልኝ ፤ ያለ ኃጢአት መመላለሱ ለእኔ #ተቆጠረልኝ።

ሮሜ 3÷28፤ [ #ሰው_ያለ_ሕግ_ሥራ_በእምነት_እንዲጸድቅ >>#እንቆጥራለንና<<። ]

ሮሜ 4 (Romans)
5፤ [ #ነገር_ግን_ለማይሠራ_ኃጢአተኛውንም_በሚያደድቅ_ለሚያምን_ሰው_እምነቱ_ጽድቅ_ሆኖ >>#ይቆጠርለታል<<።

6፤ [ እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር >>#ያለ_ሥራ<< ጽድቅን #ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል። ]
22፤ [ ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ >>#ተቆጠረለት<<።

23፤ ነገር ግን፦ >>#ተቈጠረለት<< የሚለው ቃል #ስለ_እርሱ_ብቻ_የተጻፈ_አይደለም፥ >>#ስለ_እኛም<< ነው እንጂ፤

24-25፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው >>#ለምናምን_ለእኛ >>#ይቈጠርልን_ዘንድ<< አለው። ]

ገላትያ 3 (Galatians)
8፤ [#መጽሐፍም እግዚአብሔር >>#አሕዛብን_በእምነት_እንዲያጸድቅ >>#አስቀድሞ_አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። ]



እግዚአብሔር #በልጁ_ስም በማመኔ ብቻ #የልጁን_ጽድቅ ለእኔ ለኃጢአተኛው እንዲሁ ከቆጠረልኝ ፤ ታዲያ ኃይማኖት የምን #ምቀኝነት ነው? ፤ ለምንድነው "#ለመጽደቅ_መሥራት_አለብህ" የምትለኝ? እህ!!!!!!...... ቆይ መቼም በሥራዬ ፈጽሞ መጽደቅ እንደማልችል ስለሚያውቅ መስሎኝ እግዚአብሔር እንዲሁ #በነጻ ፤ ማመኔን ጽድቅ አድርጎ #የቆጠረልኝ። ወይ ሃሳብህን አስተካክለው ፤ "#ስለጸደክ_መስራት_አለብህ" በለኝ። እንዲህ ስላልከኝም አይደለም ፣ መልካም መስራት የኔ አዲሱ ሰው ማንነት life system ነው።

ሮሜ 8 ÷ 33፤ [ #እግዚአብሔር_የመረጣቸውን_ማን_ይከሳቸዋል? >>#የሚያጸድቅ_እግዚአብሔር_ነው፥ #የሚኰንንስ_ማን_ነው? ]


ሮሜ 10 (Romans)
3፤ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።

እወድሃለሁ አንተ ወንድሜ! ይህ ጽድቅ ለእኔ ብቻ እኮ አይደለም #ላንተም ነው! እመን! #ይቆጠርልሃል! በሥራ ካልክ እውነቱን ልንገርህ መቼም አትጸድቅም! እግዚአብሔር የራሱን ጽድቅ ሊሰጥህ ይፈልጋል ፤ ታዲያ አንተ ለምን የእርሱን ትተህ #የራስህን_ጽድቅ ለማቆም ትጥራለህ? እርሱ እንዲሁ በነፃ ስለሰጠህ?...... የምትድነው እኮ #በራስህ_ጽድቅ ሳይሆን በራሱ #በእግዚአብሔር_ጽድቅ ነው።

Mezmur Lyrics

28 Apr, 01:05


✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟✟✟✟ ✟✟✟✟


✟✟
✟ ✟
✟ ✟
✟ ✟ ✟
✟__✟ ✟


✟✟✟✟✟✟
✟ ✟
✟ ✟



✟✟✟✟✟✟✟✟✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟✟✟✟✟ ✟✟✟


✟✟✟✟

✟✟
✟✟
✟✟
✟✟ ✟ ✟
✟✟ ✟✟
✟✟✟✟✟✟✟
✟✟✟✟✟✟✟
✟✟
✟✟

✟✟
✟✟
✟✟✟✟✟✟
✟✟✟✟✟✟
✟✟ ✟✟
✟✟ ✟✟✟
✟✟ ✟✟✟

✟✟
✟✟✟✟✟✟✟
✟✟✟✟✟✟
✟✟ ✟✟
✟✟
✟✟
እንኳን❖
ለፋሲካ❖
በዓል❖
አደረሰን❖
መልካም የትንሣኤበዓል
ይሁንላችሁ


" ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤"
(1ኛ ቆሮ 5:7)

Mezmur Lyrics

22 Apr, 19:19


Channel photo updated

Mezmur Lyrics

11 Apr, 16:41


. ዋቂኪያ
♻️ ዘማሪ=ዳዊት ቦሩ ♻️
Hሬ ይገዛልህ
✳️ ድንቅ ኦሮምኛ መዝሙር ✳️
Share share share
@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

06 Apr, 14:00


💫"የሕይወትህ መርሆዎች በእነዚህ ላይ የተመሰረቱ
ቢሆኑ⁉️"💫
.
1. የፈለከውን ነገር ሁልጊዜ ላታገኝ ትችላለህ፡፡ ያገኘኸውን
ነገር መውደድን ግን ተለማመድ፡፡ መሻትህ ሁሉ ላይኖርህ
ይችላል ያለህን መንከባከብ ግን አትርሳ፡፡
.
2. ኑሮዬ ይበቃኛል ማለትን ተለማመድ፤ ኑሮዬ ይበቃኛል ማለት ስለ ግብህ ማሰብ አቆምክ ማለት አይደለም፡፡
በዚህ ውሳኔ ማረፍ ቅሬታን ያርቅልሃል እምነት ማጣትን ያስወግድልሃል ተስፋ መቁረጥንና የተዛባ
አመለካከትህንም ያስተካክልልሃል፡፡

3. አሳብህም ልብህም ሰፊ ይሁን፤ አመለካከቶችህ ሁሉ ሁሉንም ነገር በቀናነት በመልካም ጎኑ በመመልከትና በማሰብ ላይ የተመሰረቱ ይሁኑ፡፡
.
4. ሥራህንና ቃልህን ለማዛመድ ትጋ፡፡ ልብህና እጅህ እርስ በእርሳቸው እንዳይጣረሱ ጥረት አድርግ፡፡

5. ወሳኙ ነገር የምትኖርበት ቦታ ሳይሆን አኗኗርህ ነው፡፡ከምታምንበት ነገርም በላይ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባው
ባመንክበት ነገር እንዴት ትኖራለህ የሚለው ነው፡፡


6. ሁላችንም በሕይወት ያለነው ደስተኞች እንድንሆን ነው፡፡ ለዚህም የፈጣሪን ድምጽ አድምጥ፤ ለኑሮህ
ብልጥግና ፍቃዱን ተከተል፤ ስኬታማ ለመሆንም በእውነት ላይ ቁም፡፡

7. እኛ ቀብረን የምናዝነውን ሀዘን ቆመው፣ እኛ ርቦን የምንሰቃየውን ስቃይ ጠግበው፣ እኛ አጥተን የምናነባውን እንባ አግኝተው የሚያነቡት ብዙ ናቸው፡፡ ልዩነቱ እኛ ሁሉን ለእርሱ ክብር ማድረጋችን ነውና ሁኔታዎችህን ሁሉ ለእርሱ ክብር ማድረግን መልመድ ይገባሃል፡፡

8. ማንም ሰው ከጠባቡ ግለኝነት ሕይወት ወደ ሰፊው
ጠቅላላው የሰው ልጅ ምልከታ ከፍ እስኪል ድረስ መኖርን
ተማረ አይባልም፡፡ ማለዳ ማለዳ አዲስ ትርጉም ባለው
መንገድ ለመኖር ራሳችንንን ብቻ መመልከታችን ወደ ፊት
ከመመልከት ጋር ሊዋሐድ ይገባዋል፡፡

9 . ያለህን ስትሰጥ ጥቂት ሰጥተሃል፤ ራስህን ስትሰጥ ግን ያኔ በእውነት ሰጥተሃል እንደሚባለው የእኛን ብቻ ሳይሆን እኛንም ለሌሎች ማካፈል አለብን፡፡
ለምሳሌ፦ ማየት ለተሳነው ሰው መመልከት ቢችል ኖሮ ሊያከናውን የሚችለውን እኛ ብናከናውንለት፣ መራመድ ለማይችል
ቢራመድ ኖሮ ሊሠራው የሚችለውን እኛ በመራመድ ብንሠራለት፣ መናገር ለማይችለው መናገር ቢችል ኖሮ
የሚያስረዳውን አፍ ሆነን ብንናገርለት ይህ ራስን ማካፈል ነው፡፡

10. በፍቅር መግዛት በጥላቻ ከመግዛት፣ ብቸኝነትን ከመንከባከብ ሕይወትን ማጋራት አብዝቶ የተሻለ ነው፡፡በትህትና ልንሠራው የምንችለውን መልካም ነገር በሸካራ ቃላቶች ልናውከው፣ በግለኝነት ልናፍነው አይገባም፡፡

ምንጭ -ከስነ ልቦና ባለሙያዎች የተገኘ
💦💦💦💦💦💦💦💦💦
መልካም ቅዳሜ

Mezmur Lyrics

06 Apr, 08:58


መደምደሚያዬ ነህ የመጨረሻዬ
እየሱሴ ለእኔ እየሱሴ ለእኔ

አገኘሁ ይደግ - መደምደምያዬ ነህ

#TuesdayAmharicNight

@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

06 Apr, 08:58


Our program will start in a couple of minutes.
We will discuss about "the Fruit of the Spirit"

this program is provided with the cooperation of our brother channel @standard_life_love

Share and invite your friends

@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

04 Apr, 15:31


#_የጂሴስ_ፊልም ሰሪው ሮበርት ፖወል ከጋዜጠኛው ያደረጉት #ቃለምልልስ....
ጋዜጠኛው፦ "ለምን እንደ ኢየሱስ ሆነህ ፍልም ሰራህ?"
#ሮበርት፦ "እኔ አንድ ተራ ሰው ነኝ፤ እንደ ማንኛውም ሰው ታሪኩን ተወንኩ፡፡"
ጋዜጠኛው፦ "ስታስብ ኢየሱስ አንተን ይመስላል?
#ሮበርት፦ "ኧሬ በፍጹም!!"
ጋዜጠኛው፦ "አንተ ጂሴስ ፍልም በመስራትህ ሰዎች ለፎቶህ
ይሰግዳሉ ምን ይሰማሃል?
#ሮበርት፦ "ሀዘንና ደስታ ይፈራራቃሉ"
ጋዜጠኛው፦ "ለምን?"
#ሮበርት፦ "አይ ሰዎች ጌታቻውን ትተው ለፎቶዬ ስሰግድና ስማፀኑ ይከፋኛል፡፡ ደስ የሚለኝ ደግሞ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊልም በመስራቴ ሰዎች ጌታን ሲቀበሉ ስመለከት።

🤳Forward to others
👇👇👇👇👇👇

@Amharic_spiritual_song_lyrics
@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

04 Apr, 15:31


@samibt


🇪🇹




🚁 📡
🏡🏦🏥🏠🏤 🏪🏣🏫
/ l \
_🚂🚋🚋/__l__\_🚩_______
👬 🚦/ l \🚦🚶
🌳 / l \ 🌳 🐐
/ l \
🌳 / 🚔 l 🚔 \
/ | \
🌵 / 🚖 l 🚘 🚴
/ l 🚔 \
/ l \
/ l \
/ l \


@samibt
Join us
Invite your friend
@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

02 Apr, 13:25


ለመቼ ነው
🎙ሀና ተክሌ 🎙

ዕውቀት ፡ ስለአንተ ፡ ቢበዛ ፡ ደግ ፡ ነው
እምነት ፡ ያለስራ ፡ ግን ፡ ከንቱ ፡ ነው
እምነቴ ፡ ሲፈተን ፡ በመከራው ፡ ብዛት
ስጨነቅ ፡ በራሴ ፡ ሲውጠኝ ፡ ፍርሃት

ለመቼ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ማለቴ
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ያልኩት ፡ ረዳቴ
ያገባሃል ፡ በእኔ ፡ ሕይወት ፡ እያልኩኝ
በራሴ ፡ ነገሬን ፡ ከጨረስኩኝ

በመልካም ፡ ቀን ፡ አምንሃለሁ ፡ ስልህ
በክፉ ፡ ቀን ፡ አለህ ፡ ሆይ ፡ ሳልልህ
እኔ ፡ እንዳልቀረሁ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ ፡ ጌታ
ቃሌ ፡ አምናለሁ ፡ በስራህ ፡ . (1) .

አምንሃለሁ ፡ ቃሌ ፡ አይበጀኝም
የቃሌ ፡ ብዛት ፡ እኔን ፡ አልሰራኝም???. (2) .
ተግባሩ ፡ እንጂ ፡ ቢበዛም ፡ ሳንኮፉ???. (3) .
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ሁሉን ፡ እያለፉ

ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያርፋል
ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያድራል (፪x)
ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያድራል
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ያርፋል ፡ የታመነ

የሠማይ ፡ ወፎች ፡ አይዘሩም ፡ አያጭዱም
ለነገም ፡ አስበው ፡ ከጐተራም ፡ አይከቱም
እነሱን ፡ ያተገብክ ፡ አንተ ፡ ደግ ፡ አባት ፡ ነህ
እኔማ ፡ ልጅህ ፡ ነኝ ፡ ምልህ ፡ ትሆናለህ

ለመቼ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ማለቴ
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ያልኩት ፡ ረዳቴ
ያገባሃል ፡ በእኔ ፡ ሕይወት ፡ እያልኩኝ
በራሴ ፡ ነገሬን ፡ ከጨረስኩኝ

ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያርፋል
ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያልፋል
ሌት ፡ ይነጋል ፡ ሠማዩም ፡ ይጠራል
የታመነ ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ ያድራል (፪x

🎙ዘማሪት ሀና
@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

02 Apr, 13:22


🎬 Yezema Gize
👤ፅድቅን እንዲያወራ ዝማሬ ዘማሪ ራሄል
@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

29 Mar, 21:15


#ድህነት ማለት የገንዘብ እጦት አይምሰልህ...🖍
አዕምሮህ ሲጠፋብህ ፣ ማሰብ አቅቶህ ጥቅም ልብህን ሲያውረው ሰዎች ደግሞ የአንተን አለመንቃት ተጠቅመው ባሪያ ሲያደርጉህ ያ ነው ድህነት ማለት።

@Amharic_spiritual_song_lyrics

Mezmur Lyrics

29 Mar, 21:14


የተስፋ ፍሬ
****
ገበሬው በእርሻ ላይ
በአንድ እጁ ጭብጥ
እፍኝ ዘር ይዞ
ሁለት ምርጫ ቢመርጥ
(አንድም)
የጨበጠውን ዘር ወይ ጠብሶ ወይ ቆልቶ ወይ ቀቅሎ መብላት
(ወይም)...መሬትን ቆፍሮ ይችን እህል መዝራት
ሁለት ጥንፍ ይዞ ቢቸገር ማማረጥ
ይህን አይቶ ኖሮ
ፈጣሪ አስተማረ የሰውን ተስፋ ጥግ
ፍጥረት ዘርን ጥሎ ዘርን እንዲጠብቅ!
@Amharic_spiritual_song_lyrics
@Amharic_spiritual_song_lyrics
share💯 share💯 share💯
@Amharic_spiritual_song_lyrics
🔺🀄️🀄️ሉን🔺

Mezmur Lyrics

29 Mar, 21:14


. አዲስአለም አሰፋ
. New Spiritual Song
share💯 share💯 share💯
@Amharic_spiritual_song_lyrics
🔺🀄️🀄️ሉን🔺

Mezmur Lyrics

21 Mar, 18:36


Singer Sofia
Amazing song lyrics
🎻🎤🎼🥁🎷🎺🎸🎤🎻🎼🎹🎺🥁
መልካም ነህ ለእኔ አባቴ (፪x)
ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ (፪x)

ይሁንልኝ ብዬ የተሟገትኳቸው
ባለፈው ዘመኔ ኧረ ብዙ ናቸው
ጊዜ ፈጀሁ እንጂ ከወዲህ ከወዲያ
ግን ጥልቅ አስብሎ ደርሶ በአንተ ሞያ

ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ
አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ

መልካም ነህ ለእኔ አባቴ (፪x)
ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ (፪x)

እንደው መጨነቄ ሁሉ ከልኩ አያልፍ
አንዳችም ላልጨምር አንዳችም ላላተርፍ
ባይገቡኝም እንኳን መንገዶቼ ሁሉ
ለአንተ ግን አባቴ ጠርተው ይታያሉ

ከእኔ የምታስበው መልካም ከሆነልኝ
እንዳረከኝ ልሁን የእኔስ ይቅርብኝ

እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ
ስኖር በዚች ዓለም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ
ስኖር በዚች ዓለም (፪x)

እግሮቼን ከወጥመድ ማነው ያወጣቸው
ዓይኖቼ ሁልጊዜ ጌታ ወደ አንተ ናቸው
በመረጥከው መንገድ አስተምረኸኛል
የማያልፈውን ሕይወት መኖር ይሻለኛል
የማያልፈው . (1) . መስማት ይሻለኛል

መልካም ነህ ለእኔ አባቴ (፪x)
ታስብልኝ የለም ዎይ አንተም ልጄን ብለህ
ሁልጊዜ ለእኔ መልካም ነህ (፪x)

እኔ ያልኩት አልሆነም አንተ ያልከው አልቀረም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ
ስኖር በዚች ዓለም
አሁንም የአንተው ነኝ ፈቃድህ ያግኘኝ
ስኖር በዚች ዓለም (፪x)

ትክክል ነህ ጌታ በሥራህ ጻድቅ ነህ
አንተ አትታረምም እንዲህ አድርግ ተብለህ (፪x)
@Amharic_spiritual_song_lyrics