The Federal Supreme Court of Ethiopia @fscethiopiapr Channel on Telegram

The Federal Supreme Court of Ethiopia

@fscethiopiapr


Federal Supreme Court is the highest court in Ethiopia. It is constitutionaly established court. It is also one of the three pillars of the federal state that assures the check and balance in & among.

The Federal Supreme Court of Ethiopia (English)

Are you interested in learning more about the legal system in Ethiopia? Look no further than the Telegram channel 'The Federal Supreme Court of Ethiopia'! This channel, with the username @fscethiopiapr, provides valuable insights into the highest court in the country, the Federal Supreme Court. Established constitutionally, this court plays a crucial role in upholding justice and ensuring the rule of law in Ethiopia. It serves as one of the three pillars of the federal state, providing checks and balances to maintain a fair and just legal system for all citizens. By following this channel, you will have access to updates on key legal decisions, information on the court's functions and responsibilities, as well as educational content on the Ethiopian legal system. Whether you are a law student, legal professional, or simply interested in the judicial system of Ethiopia, this channel is the perfect resource for staying informed. Join the 'The Federal Supreme Court of Ethiopia' Telegram channel today and gain a deeper understanding of the legal landscape in Ethiopia. Stay up-to-date on important court cases, legal reforms, and judicial developments. Don't miss out on this opportunity to expand your knowledge and engage with others who share your interest in the Ethiopian legal system. Subscribe now and become a part of this informative community!

The Federal Supreme Court of Ethiopia

06 Dec, 08:31


የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር

ተ.ቁ መ.ቁ.

1. 3432/10
2. 3644/11
3. 4426/11
4. 4471/11
5. 4771/12
6. 4772/12
7. 4776/12
8. 4777/12
9. 4784/12
10. 4819/12
11. 4899/12
12. 5019/12
13. 5031/12
14. 5119/12
15. 5164/12
16. 5165/12
17. 5171/12
18. 5175/12
19. 5201/12
20. 5266/12
21. 5329/13
22. 5365/13
23. 5375/13
24. 5445/13
25. 5446/13
26. 5481/12
27. 5572/13
28. 5579/13
29. 5585/13
30. 5982/13
31. 5983/13
32. 6103/13
33. 6126/14
34. 6139/14
35. 6203/14
36. 6209/14
37. 6211/14
38. 6220/14
39. 6227/14
40. 6228/14
41. 6231/14
42. 6232/14
43. 6240/14
44. 6385/14
45. 8476/16
46. 8554/16
47. 8701/16
48. 8709/16
49. 8810/16
50. 8888/16
51. 8957/17
52. 9022/17
53. 9192/17

*ማስታወሻ*
1. ቁጥራቸው የቅርብ ጊዜ የሆኑት ጉዳዮች ቀድመው የታዩበት ምክንያት በጉባዔው መመሪያ መሰረት ቅድሚያ አግኝተው ምርመራቸው የተጠናቀቀ (የወንጀል፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአሰሪና ሰራተኛ፣ ከፍ/ቤት ሪፈራል የተላኩ፣ የታገዱ መዝገቦች) መሆናቸውን እየገለፅን ከዚያ ውጭ ያሉት ግን እንደ አመጣጥ ቅደም ተከተላቸው የተስተናገዱ ናቸው፡፡
2. ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች የውሳኔ ግልባጭ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጉባዔው ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

06 Dec, 08:12


ጉባዔው በ60 አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጠ።
----------------------------------------------------------------------
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ህዳር 26 ቀን 2017 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች እና በንዑስ አጣሪ ጉባዔ ደረጃ ተገቢውን ምርመራ እና ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት አቤቱታዎች መካከል 60 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።
ጉባዔው ከተወያዬባቸው 60 የሕገ መንግሥት አቤቱታዎች መካከል 53 የሚሆኑት ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ወስኗል።
በሌላ በኩል በቁጥር 5 በሆኑ የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተጠሪዎች ምላሻቸውን እንዲሰጡባቸው ጉባዔው አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን በመ/ቁ 3537/10 ላይ እየታዬ ያለ መዝገብን በተመለከተ በድጋሚ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም ለመልስ ሰጭው መጥሪያ እንዲደርስ ጉባዔው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ከዚህ በተጨማሪም አንድ መዝገብ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎበት በቀጣይ እንዲቀርብ በጉባዔው ተወስኗል።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

06 Dec, 08:01


ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 5 ክፍል 3
https://www.youtube.com/watch?v=-75Kk64Kioc
በፍርድ ቤቱ ዩቲዩብ ቻናል http://www.youtube.com/@federalsupremecourtethiopi570 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ በመግባት ይከታተሉ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

05 Dec, 14:00


የቻይና ጉዋንግዶንግ ግዛት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ
**********
የቻይና ጉዋንግዶንግ ግዛት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት፣ ዳኞችና እና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ያካተተ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 26/03/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ፈዬራ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የልዑክ ቡድኑ የዳበረ ልምዱን ለማካፈል እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ለመጎብኘት ኢትዮጵያ ድረስ መምጣቱ በፍ/ቤቱ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ለማጠናከር እና የሁለቱን ሀገራት ፍርድ ቤቶች ትብብር ለማሳደግ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የቻይና ጉዋንግዶንግ ግዛት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሚስተር ዋንግ ሃይቂንግ በበኩላቸው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ላደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበው አጋጣሚው ወደፊት በትብብር ለመስራትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እድል የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ዙሪያ በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፍርድ ቤት መር አስማሚነት ዳይሬክተር ወ/ሪት ሉሊት አድነው ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በገለጻውም የኢትዮጵያ ባህላዊ የሙግት መፍቻ ስርዓት እና ሕገ መንግስታዊ ዕውቅና፣ በፍርድ ቤት መር አስማሚነት የሕግና ተቋማዊ ማዕቀፍ፣ የአስማሚነት መርሆዎች እንዲሁም የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ፍትህን ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር ያለው መልካም አጋጣሚዎች ላይ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች መዋቅር እና የዳኝነት ስርአት እና እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ተግባራት፣ የቻይና የፍርድ ቤቶች መዋቅርና አማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓትን ከማጠናከር አንፃር የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

26 Nov, 07:20


የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር


ተ.ቁ መ.ቁ. የአመልካች ስም
1. 3772/11 አቶ ተገኘ ታደሰ
2. 3781/11 አቶ መሃመድ ሁሴን
3. 3793/11 አቶ ሽመልስ ሙሉአለም
4. 3853/11 እነ ዮርዳኖስ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማ
5. 5223/12 አቶ አብዱረዛቅ ሼህ አብራሂም
6. 5237/12 ወ/ሮ ዙፋን ከበደ
7. 5453/13 አቶ ደመላሽ ከበደ
8. 5515/13 እነ አቶ ገዛህኝ ገ/ማሪያም
9. 5623/13 ወ/ሮ አየለች መልካ
10. 5634/13 አቶ ሞላ ፀጋ አለሙ
11. 5638/13 አቶ አሸናፊ ታደሰ
12. 5640/13 እነ ወ/ሮ አባይነሽ አበበ
13. 5927/13 ወ/ሮ ፈንታዩ ሞላ
14. 6107/13 ወ/ሮ ዘይቱና ሱጊ ሙዘይን
15. 6137/14 አቶ ፋሲል ክበበው
16. 6147/14 አቶ ቴዎድሮስ ሞገስ አበበ
17. 6151/14 እነ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት
18. 6152/14 ወ/ሮ ብርሃነሽ እሳቱ
19. 6156/14 እነ ወ/ሮ ባዩሽ አዴሎ
20. 6157/14 እነ ወ/ሮ አስካለ ማሞ
21. 6181/14 አክሊለ ካህሳይ
22. 6182/14 ሰኢድ አህመድ
23. 6183/14 አቶ ከሊሎ ከተራ
24. 6184/14 እነ ወ/ሮ በጋለች ነጋሽ
25. 6187/14 እነ ወ/ሮ ቦጋለች ዳኜ
26. 6188/14 ፀጋዩ ገ/መድህን
27. 6204/14 ወ/ሮ አቦነሽ ዓለሙ
28. 6257/14 አቶ ታምራት ገስፌ
29. 6269/14 አቶ በቀለ ታደሰ
30. 6279/14 ሻምበል ደገፉ ኃይሌ
31. 6402/14 እነ አቶ ቶፊክ አብዱላ
32. 6637/14 ቀሲስ አብርሃም በቀለ
33. 6639/14 አቶ መለሰ ኢፋ ዋቅጅራ
34. 6680/14 አቶ ጸጋዬ ምንዳሁን
35. 6682/14 ጀወይሪያ አብድ የሬ
36. 7310/15 አቶ መስፍን አዱኛ
37. 7937/15 ወ/ሮ ቤቴልሄም ገ/ሚካኤል
38. 8092/15 አቶ አደም ዱሌ
39. 8146/16 አቶ መሊክ መሀመድ አህመድ
40. 8254/16 አቶ ድጋፌ ረታ
41. 8486/16 እነ አቶ አዳነ በርሄ
42. 8497/16 አቶ ዘለቀ አንዳርጌ
43. 8521/16 አቶ ተስፋሁን ተሸመ
44. 8686/16 አቶ ማጆ አጌ
45. 8755/16 የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩም
46. 8821/16 አቶ መገርሳ በዳዳ
47. 8829/16 አቶ ገዙ ደጉ ማሞ
48. 8854/16 ወ/ሮ ሙሉነሽ ማናዬ
49. 8855/16 ወ/ሪትማህሌትገብረመድህን
50. 8877/16 አቶ አብዱ ይማም

*ማስታወሻ*
1. ቁጥራቸው የቅርብ ጊዜ የሆኑት ጉዳዮች ቀድመው የታዩበት ምክንያት በጉባዔው መመሪያ መሰረት ቅድሚያ አግኝተው ምርመራቸው የተጠናቀቀ (የወንጀል፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአሰሪና ሰራተኛ፣ ከፍ/ቤት ሪፈራል የተላኩ፣ የታገዱ መዝገቦች) መሆናቸውን እየገለፅን ከዚያ ውጭ ያሉት ግን እንደ አመጣጥ ቅደም ተከተላቸው የተስተናገዱ ናቸው፡፡
2. ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች የውሳኔ ግልባጭ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጉባዔው ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

26 Nov, 07:18


ጉባዔው በ59 አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔና የውሳኔ ሐሳብ ሰጠ።
---------------------------------------------------------
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት ሐሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በ59 የሕገ መንግሥታዊ የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብና አቅጣጫ ሰጥቷል።
ጉባዔው በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎቾ ተገቢው ማጣራት እና ምርመራ ተደርጎባቸው ከቀረቡለት አቤቱታዎች መካከል 50 የሚሆኑትን ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ወስኗል።
በሌላ በኩል ጉባዕው በዕለቱ ከተወያየባቸው 59 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎቾ መካከል በሦስት ጉዳዮች ላይ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሟል በሚል የውሳኔ ሐሳቡ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ አዟል።
እነዚህ የሕገ መንግሥት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል የተባሉ አቤቱታዎችም በመ/ቁ 2588/10 ከሕገ መንግሥታዊ ንብረት የማፍራት መብት፣ በመ/ቁ 7828/15 እና በመ/ቁ 7939/15 ከሕገ መንግሥታዊ የበላይነት ጋር በተያያዘ የቀረቡ መሆናቸው የተመላከተ ሲሆን የመጨረሻ ውሳኔውም በፌዴሬሽን ም/ቤት የሚሰጥ ይሆናል።
በተጨማሪም በዕለቱ በነበረው የጉባዔው ውይይት ብዛታቸው 2 የሆኑ አቤቱታዎች በአመልካቾች ጥያቄ መሰረት እንዲቋረጡ የተደረጉ ሲሆን በሌሎች 3 አቤቱታዎች ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው በድጋሚ ለውሳኔ እንዲቀርቡ ጉባዔው አቅጣጫ በመስጠት በሌላ 1 አቤቱታ ላይ ተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥ ተብሏል።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

25 Nov, 07:39


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 5 ክፍል 1
https://www.youtube.com/watch?v=fOTSt_Q3mK4
በፍርድ ቤቱ ዩቲዩብ ቻናል http://www.youtube.com/@federalsupremecourtethiopi570 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ በመግባት ይከታተሉ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

22 Nov, 17:32


የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች የስራ እና የዋይድ ኤርያ ፕሮጀክት አፈጻጸምን ጎበኙ
************
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ፣የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም የስራ ኃላፊዎችን የያዘ ልዑክ ቡድን በቀን 13/03/2017 ዓ.ም የፌደራል ፍርድ ቤቶች የስራ እና የዋይድ ኤርያ ፕሮጀክት አፈጻጸምን ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ አላማ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን የፌደራል ፍርድ ቤቶችን በኔትወርክ የማስተሳሰር ስራ ተግባራዊ ለማድረግ የጀመረዉን ፕሮጀክት የደረሰበትን ደረጃ ለመጎብኘትና ቀሪ ስራዎች ላይ ለመወያየት ሲሆን ጉብኝቱ የተደረገው በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ በፌደራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በልደታ፣አራዳ፣ ለሚ ኩራ፣ ቦሌ፣ የካ እና ቂርቆስ ምድብ ችሎቶች ናቸው፡፡

በሁሉም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሮጀክቱ ወደ መጠናቀቅ ምዕራፍ ላይ የደረሰ ሲሆን በሙከራ ደረጃ ከ6 ምድብ ችሎቶች በኔትወርክ የማስተሳሰር ስራው ታይቷል፡፡ የቀሪ ምድብ ችሎቶች እና ስራዎች በቀጣይ በተቻለ ፍጥነት ተጠናቀው ወደ ሙሉ ትግበራ ሊያስገቡ የሚያስችሉ ሌሎች ቀሪ ስራዎች ላይ በመወያየት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

ልዑክ ቡድኑ የፕሮጀክት ስራዉ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ በመደበኛና በተለያዩ ግዜያት ፕሮጀክቱ የደረሰባቸዉን ሂደቶችን ሲከታተል የነበረ ሲሆን የዛሬዉም ጉብኝትም የዚሁ አካል ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

22 Nov, 07:28


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 4
https://www.youtube.com/watch?v=JWxFtOEsuDQ
በፍርድ ቤቱ ዩቲዩብ ቻናል http://www.youtube.com/@federalsupremecourtethiopi570 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ በመግባት ይከታተሉ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

19 Nov, 08:46


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 3- ክፍል 2
https://www.youtube.com/watch?v=7fTRay9ZLjI&t=223s
በፍርድ ቤቱ ዩቲዩብ ቻናል http://www.youtube.com/@federalsupremecourtethiopi570 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ በመግባት ይከታተሉ፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

18 Nov, 12:37


የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር

ተ.ቁ መ.ቁ. የአመልካች ስም
1. 3574/11 አቶ አየለ ይመር
2. 3699/11 አቶ መንግስቴ ጌታነህ
3. 3968/11 ወ/ሮ ትዕግስት ዳኜ
4. 4015/11 አቶ አየለ ቦጋለ
5. 4037/11 ወ/ሮ ማርያም እስማኤል
6. 4268/11 እነ አቶ ተገኔ ዘሪሁን
7. 4304/11 ወ/ሮ ማዕረግ ብዙአየሁ
8. 4325/11 እማሆይ ዋጋዬ ፈንታው
9. 4339/11 ግሎባል ኤልሜክ ኃ/የተ/የግ/ማ
10. 4417/11 አቶ ታዬ ሽፈራው
11. 4446/11 አቶ ተሾመ ጀቢር
12. 4483/11 አቶ ይርጋ አበራ
13. 4535/11 ወ/ሮ ሸሚማ ሁሴን
14. 4612/11 አቶ አርጋው አንለይ
15. 4640/11 ወ/ሮ ምስራቅ ጌታሁን
16. 4697/11 አቶ ሀይሉ ነበረኝ
17. 4767/11 ወ/ሮ ለተስላሴ ታደሰ
18. 4778/12 አቶ ተሰማ ይርሳው
19. 5095/12 ወ/ሮ አበቡ መኮንን
20. 5185/12 አባ ዝናብ አባ ጀበል
21. 5230/12 ወ/ሮ ዘውድነሽ አደሬ
22. 5305/12 ወ/ሮ ሽብሬ ውብሸት
23. 5484/13 ወ/ሮ ፍቅርተ አድነው
24. 5729/13 ወ/ሮ ዘውዲቱ ቱፋ
25. 5825/13 አቶ አባይ አያሌው
26. 5901/13 ወ/ሮ ሄለን አበበ
27. 6190/14 የአቶ አቡበከር አብዱላሂ ወራሾች /5 ሰዎች/
28. 6192/14 አቶ ኃይሉ ሞገስ
29. 6195/14 እነ ወ/ሪት ንጋት ድንቁ
30. 6196/14 እነ አቶ ዘላለም አስጨንቀው
31. 6242/14 እነ አቶ ኑርአህመድ መሀመድ
32. 6245/14 እነ ወ/ሮ የብርጓል በላይነህ
33. 6246/14 አቶ ይሎ ወጋ
34. 6249/14 እነ ዘላለም ወልዴ
35. 6253/14 አቶ ዋለልኝ መኮንን
36. 6261/14 ሐጅ ተሻለ ኬሮ ባርኬ
37. 6389/14 አቶ አስፋው በቀለ
38. 6431/14 ወ/ሮ አልማዝ መሸሻ
39. 6441/14 ወ/ሮ መሰረት ነጋ
40. 6442/14 አበራሽ ሳህሌ
41. 6455/14 አቶ ጉዲሳ ደዎ
42. 6461/14 አቶ አባተ ደምሴ ፈንታ
43. 6538/14 ወ/ሮ ሸቤዛ ሁሴን
44. 6540/14 ወ/ሮ አልማዝ በልዩ
45. 6541/14 ወ/ሮ ያለምወርቅ ሰለሞን
46. 6596/14 እነ ወ/ሪት መሰረት ገብሬ
47. 7211/15 አቶ ቸርነት ድልነሳሁ
48. 7334/15 አቶ ጥላሁን አበበ
49. 8418/16 አቶ ታጁ አህመድ
50. 8520/16 እነ ወ/ሮ ሐረገወይን ታምራት
51. 8591/16 እነ አቶ ደግፌ ሰይፉ
52. 8873/16 ወ/ሮ ኑሪያ ዩሱፍ አብዱላሂ
53. 8889/16 ወ/ሮ ዮዲት ፍቃዱ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

17 Nov, 06:11


በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
******************
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ከፌደራል ፍትህና ህግ ኢኒስቲትዩት እንዲሁም ከኢትዮጵያ አስማሚነትና ግልግል ዳኝነት ማዕከል(EMAC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ያተኮረ ከቀን 05/03/2017-07/03/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ለሶስት ቀናት በቆየው ስልጠና በፍርድ ቤት መር አስማሚነት የአስማሚዎች ሚና እና ክህሎት ምን እንደሆነ፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሂደቶች እንዲሁም የቤተሰብ አስማሚነት ላይ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የተግባር ልምምድ እንዲሁም በስኬት በአስማሚነት የተጠናቀቁ ጉዳዮች ተሞክሮ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ዳኛ አበበ ሰለሞን በመዝጊያ ንግግራቸው በአማራጭ የሙግት መፍቻ ስርዓት መዳኘት የነፃ ፍላጎት ሃሳብን መሰረት በማድረግ ሰው በህሊናው መዳኘት እንዲችል፤ የይቅርባይነት ስሜትን ለማዳበር፤ በራሱ እንዲዳኝ የማድረግ ጥበብን ለመጨመር፤ ጤናማ ግንኙነቶች እንዲቀጥል ለማድረግ እንዲሁም የፍትህ መጓደልን፣ ጊዜና ወጪን የሚቆጥብ በመሆኑ ሕብረተሰቡም ይህንን በአግባቡ እንዲገነዘብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራት እንደሚኖርባቸውና በፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስማሚነት ስራዎችን በሚመለከት እስካሁን የተመዘገቡትን መልካም ውጤቶች በማስቀጠል ከመመሪያው አፈፃፀም አንፃር የታዩ ክፍተቶች በጥናት ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው ገልፀዋል፡፡

አክለውም ስልጠናው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች በፍርድ ቤት ያለባቸውን ኃላፊነት የሚያስገነዝብ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ሁሉም ጥረት በማድረግ አላማውን ማሳካት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

15 Nov, 06:23


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ድምጽ ቅጂ ቅጽ 2
https://www.youtube.com/watch?v=eLKq0dsZc7o

በፍርድ ቤቱ ዩቲዩብ ቻናል http://www.youtube.com/@federalsupremecourtethiopi570 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ በመግባት ይከታተሉ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

14 Nov, 15:33


በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ለፌደራል ፍርድ ቤቶች ረዳት ዳኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል
**********
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ከፌደራል ፍትህና ህግ ኢኒስቲትዩት እንዲሁም ከኢትዮጵያ አስማሚነትና ግልግል ዳኝነት ማዕከል(EMAC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ ያተኮረ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና ከቀን 05/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርዓት ውጤታማነት ለማጠናከር የማስማማት ስራ ለሚያከናውኑ አስማሚ ረዳት ዳኞችን እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል አቅም ማሳደግ ነው፡፡ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ስልጠና የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ላይ የአስማሚዎች ሚና፣ የአስማሚነት ክህሎት፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሂደቶች እንዲሁም የቤተሰብ አስማሚነት ላይ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ፍትህና ህግ እኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በፍታብሄር ጉዳዮች በተናጠል ወገኖች መካካል የሚነሱ አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ጠቀሜታው ሰፊ እንደሆነ ገልፀው በዋነኛነት የፍትህ ሰርአትን ለማጎልበት፣ የባለ ጉዳዮችን ጊዜና ገንዘብ ለመቆጠብ፣ በባለጉዳዮች መካካል በስምምነት ነገሮች አልቀው የነበረው መልካም ግንኙነት ለማስቀጠል ብሎም በማህበረሰብ መካካል የሚኖረውን መልካም መስተጋብር ከመጠበቅ አኳያ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ከስልጠናውም ብዙ ጠቃሚ የትግበራ ዘዴዎችን መቅሰም እንደሚቻል እና ትልቅ አቅም እንደሚሆን አንስተዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ድሪባ ፈዬራ በበኩላቸው በህብረተሰቡ ዘንድ የፍታብሔር ጉዳዮች በመደበኛ ሂደት ውስጥ ካላለፉ ትክክል እንዳልሆነ የማሰብ ባህል መቀየር እና ተገልጋዮች ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡ ጉዳያቸው በስምምነት ማለቅ እንደሚችል ማስተማር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበው ለትግበራወም ተያያዥነት ያላቸው መሰል ስልጠናዎች ትልቅ ሚና ያላቸው በመሆኑ የስልጠናው ውጤት በስራ ሊታይ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናውን የሚሰጡት የኢትዮጵያ አስማሚነትና ግልግል ዳኝነት ማዕከል ዳይሬክተር እና ጠበቃ አቶ ሚካኤል ተሾመ እንዲሁም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ጠበቃ አቶ ሳሙኤል አለማየሁ ናቸው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

13 Nov, 09:14


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሰጠባቸዉን ከቅጽ 1-18 ያሉ በድምጽ ቅጂ መልክ የተዘጋጁ የሰበር ዉሳኔዎች ለኢትዮጵያ ዓይነ ስዉራን ብሄራዊ ማህበር ማበርከቱ ይታወሳል
የድምጽ ቅጂው የተዘጋጀው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ ተደራሽ የሚያደርጋቸውን በሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጡ እና አስገዳጅነት ያላቸዉን ዉሳኔዎች በተለየ ሁኔታ ለአይነስውራን ተደራሽ ለማድረግና አማራጮችን በማስፋት አጠቃላይ ተገልጋዮችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በመሆኑ እነዚህን የድምጽ ቅጂዎችን ተገልጋዮች በፍርድ ቤቱ ዩቲዩብ ቻናል http://www.youtube.com/@federalsupremecourtethiopi570 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ እንዲያገኙት በተከታታይ የሚጫኑ መሆኑን እየገለጽን ፍርድ ቤት መምጣት የምትችሉ ተገልጋዮች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት በመምጣት በማንኛውም ዲጂታል ሚዲያ አማካኝነት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለዛሬ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ቅጽ 1 እነሆ
https://www.youtube.com/watch?v=tHoa1dAl4GQ
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

08 Nov, 14:16


የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ በሚቋቋም ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
****************
ከፌደራል ፍርድ ቤቶች አመራሮች፣ ተጠሪ ዳኞች፣ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስራ ሃላፊዎች የተሳተፉበት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ በሚቋቋም ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከቀን 29/02/2017 እስከ 30/02/2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ስር ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የወንጀል ተጠያቂነት አንዱ ጉዳይ ሲሆን በሚንስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የሽግግር ፍትህ የወንጀል ተጠያቂነት በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ልዩ ችሎት እንደሚደራጅ ደንግጓል፡፡
የመድረኩ አላማም ይህን ተከትሎ ልዩ ችሎቶቹ የሚደራጁት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሆኑ የልዩ ችሎቱን አደረጃጀት እና ነጻነትን በተመለከተ በህግ እንደሚወሰን የሽግግር ፍትህ ፖሊሲው በሚያመላክተው መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህግ አርቃቂ ኮሚቴ አባላትን በማዋቀር አባላቱ ባዘጋጁት የመጀመሪያ ረቂቅ ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከሽግግር ፍትህ ጋር በተያያዘ ችሎት አደረጃጀትንና ሂደቱን የመምራት ሃላፊነት ለፍርድ ቤቶች የተሰጠ በመሆኑ ይህን ልዩ ችሎት ለማቋቋም ረቂቅ አዋጁን በማዳበርና ስራው ላይ ተሳትፎ በማድረግ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁን በማዘጋጀት ክቡር ዳኛ ኑረዲን ከድር (የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ)፣ ክቡር ዳኛ እንዳለ ታደሰ (የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ)፣ ዶ/ር ታደሰ ካሳ (የሽግግር ፍትህ ጉዳዮች የፖሊሲ አማካሪ) ፣ አቶ አስፋው አንሳቦ (የሰብዓዊ መብት ክትትል ቡድን አስተባበሪና የሽግግር ፍትህ ፎካል ፐርሰን)፣ አቶ ጠገነኝ ትርፌ (በህግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክቶሬት ጀነራል የህግ ማርቀቅ ቡድን አስተባባሪ) ተሳትፈውበታል፡፡

በቀጣይ መድረክም የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን እንዲሁም የልዩ ችሎት ማቋቋሚያ አዋጁን በተመለከተ ገለጻ፣ ውይይት እና የግብዓት ማሰባሰብ የሚደረግ ይሆናል፡፡

መድረኩ የተዘጋጀው በዩ.ኤን.ዲ.ፒ (UNDP) ድጋፍ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስተባባሪነት ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

03 Nov, 15:15


በተከታታይ የወንጀል ክስ አሰማም ሂደት ላይ ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ
**********
ከፌደራል እና ክልል ፍርድ ቤቶች ዳኞች፣ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስራ ሃላፊዎች የተሳተፉበት በተከታታይ የወንጀል ክስ አሰማም ሂደት (Continuous Criminal Trial) ላይ ለሁለት ቀናት ከቀን 23/02/2017 እስከ ቀን 24/02/2017 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

በቀን 24/02/2017 ዓ.ም በነበረው መድረክ ተከታታይ የክስ አሰማም በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ምን እንደሚመስል እንዲሁም በተከታታይ የወንጀል ክስ አሰማም ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዚህ ዙሪያ የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶችም ዳሰሳ ተደርጎባቸዋል፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦች ተብለው ከተቀመጡ ነጥቦች መካከል በተቋም ደረጃ የአቅም ግንባታ ስርአት መዘርጋት፣ የህግ ክፍተቶችን በመለየት የማሻሻያ ሃሳቦች ማቅረብ፣ ከፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣ የሰው ሀይል፣ የፋይናንስ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን አቅርቦት ማሻሻል፣ የመዛግበት ክምችና መጨናነቅ መቀነስ የሚሉት ዋነዘኞቹ ናቸው፡፡

በመድረኩ ላይ በመገኘት የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ተክሊት ይመስል በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ተከታታይ የክስ መስማት አለመኖር የፍትህ መጓተትን እንዳያስከትል ዳኞች እና ፍርድ ቤቶች ዋና ተዋናዮች በመሆን ከሌሎች የፍትህ አካላት ጋር የመስራት ሃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡ የዳኞች የግዜ አጠቃቀም፣የክርክር አመራር፣ የምስክርና የክስ አቀራረብ የራሱ የሆነ ተጽእኖ ይኖረዋል ያሉት ክቡር አቶ ተክሊት መድረኩ ላይ የተገኙትን ግብዓቶች በመውሰድ ስራ ላይ ማዋልና ፋይዳው መታየት እንደሚኖርበት ገልጸዋል፡፡

አክለውም የወንጀል ፍትህ አስተዳደር የመጨረሻ ግቡ የህዝቡን ሰላም ማረጋጋት እና የህግ የበላይነት ማረጋገጥ እንደመሆኑ የፍርድ ቤት ስራዎች ውጤታቸው የተረጋጋ ማህበረሰብ መፍጠርና የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

መድረኩ የተዘጋጀው በአውሮፓ ሕብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ፍትህ ስርአት ማሻሻያ ፕሮግራም ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

29 Oct, 15:01


የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ልዑካን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ
**********
የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር እንዲሁም በኢትዮጵያ የቻይና ምክትል አምባሳደርን ያካተተ የልዑክ ቡድን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 19/02/2017 ዓ.ም በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ከዚህ ቀደም በቻይና ለፌደራል ዳኞች ላዘጋጀው የስልጠናና የጉብኝት መርሃ ግብር ምስጋና አቅርበው የልዑክ ቡድኑ የዳበረ ልምዱን ለማካፈል እና ተቋሙን ለመጎብኘት ኢትዮጵያ ድረስ መምጣቱ በፍ/ቤቱ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎችን ለማጠናከርና የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማሳደግ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዋንግ ዚያኦፋንግ በበኩላቸው ጉብኝቱ በቀጣይ በትብብር ለመስራትና የዳኞችን አቅም ከማሳደግ አንጻር የተሸለ እድል የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በቆይታቸውም የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች መዋቅር እና የዳኝነት ስርአት፣ እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ተግባራት እንዲሁም በዳኞች ስልጠና ዙሪያ ሰፊ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ያስገነባውን የስማርት ኮርት ሩሞችና የዋይድ ኤሪያ ዳታ ሴንተርንም ጎብኝተዋል፡፡

የቻይና ናሽናል የዳኞች ኮሌጅ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዋንግ ዚያኦፋንግ በተጨማሪም ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ምክትል ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በነበራቸው የተናጠል ውይይት በቀጣይ ተቋማቱ በትብብር ስለሚሰሯቸው ስራዎች እንዲሁም የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ልዑክ ቡድኑ በቀጣይ ቀናትም የፌደራል ከፍተኛ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትን እንዲሁም የፌደራል ፍትህና ህግ ኢኒስቲትዩትን የሚጎበኙ ይሆናል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

28 Oct, 12:39


ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገልጋዮች
*******
ፍርድ ቤቱ በከፊል ዝግ በሆነበት ጊዜ ለምርመራ ያደሩ መዝገቦች ውሳኔ የመስጠት ስራ በዳኞች የሚሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት በ2016 ነሀሴ ወር የወደፊት ቀጠሮ ያላቸው መዝገቦች ቀጠሮአቸው ተሰብሮ ውሳኔ እንዲያገኙ እና የተቀየረው ቀጠሮ ለተገልጋዮች በኮል ሴንተር በኩል በመልዕክት እና በስልክ የተነገረ ቢሆንም የተወሰኑ ባለጉዳዮች በተለወጠው ቀጠሮ ቀን ተሟልተው እየቀረቡ አለመሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመዝገብ ቁጥሮች ጉዳይ ያላችሁ ባለጉዳዮች ጉዳያችሁ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው የቀጠሮ ቀን ውሳኔ ያገኘ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

The Federal Supreme Court of Ethiopia

25 Oct, 14:54


ጉባዔው በ9 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ።
-----------------------------------------------------------------
የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ተገቢውን ምርመራ እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች መካከል በ9ኙ ላይ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሃሳብና አቅጣጫ አስቀምጧል።
በዚህም ጉባዔው በዕለቱ ከተመለከታቸው አቤቱታዎች መካከል 3ቱ ማለትም (3350/10፣ 4671/11፣ 5238/11) የሕገ መንግሥት ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል ጉባዔው እንዲዘጉ ወስኗል። በሌላ በኩል ሌሎች 3 የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎ እንዲቀርቡ አቅጣጫ የሰጠው ጉባዔው በሌሎች 2 አቤቱታዎች ላይ ተጠሪዎች ምላሽ እንዲሰጡ አዟል።
በዕለቱም በመዝገብ ቁጥር 5691/13 የተመዘገበ አቤቱታ ላይ የሕገ መንግሥት ጥሰት ተፈፅሟል በሚል ለመጨረሻ ውሳኔ ውደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ ጉባዔው የውሳኔ ሐሳብ ሰጥቷል።


የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

23 Oct, 14:25


https://youtu.be/isZmkJ59GcA?si=GMWxCrYS9rfH1eFl

The Federal Supreme Court of Ethiopia

23 Oct, 14:21


የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ መምሪያው የቀለብ ክርክሮችን ወጥ፣ተገማች እንዲሁም ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያግዝ ሲሆን ከስር ባለው ቪድዮ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛና የህፃናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያ አዘጋጅ ክብርት ዳኛ ወ/ሮ እትመት አሰፋ በአባይ ቲቪ ‹‹ፍትህ ለሀገሬ›› ፕሮግራም ላይ ቀርበው ሰፊ ገለጻና ውይይት አድርገዋል፡፡
ይከታተሉት!

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጅያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

23 Oct, 13:53


የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ሰጠ፡፡
፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
ጉባኤው በእለቱ በቀረቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ የተወያየ ሲሆን በዚህም መሰረት በዘጠኝ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች፤በሶስት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች እና በስድስት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በድምሩ በ19 የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ላይ የቀረበባቸው የዲሲፕሊን ክስ አቤቱታ ዳኞቹን የሚያስጠይቅ አይደሉም በማለት ወስኗል፡፡

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ

The Federal Supreme Court of Ethiopia

21 Oct, 15:22


በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 ስር እንደተደነገገው አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠን ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት እንዲታይ እንደሚደረግ እና በዚህ መልኩ የሚሰጠው የህግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማናቸውም ደረጃ ለሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት አስገዳጅ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡

በዚህ መሰረት በ2015ዓ.ም እና 2016 ዓ.ም ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት ውሳኔ የተሰጠባቸውን ጉዳዮች አጭር መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ የውሳኔዎቹን ሙሉ ግልባጭ በፍርድ ቤቱ ዌብሳይት https://www.fsc.gov.et/ ወይም በአማራጭ የቴሌግራም ቻናላችን https://t.me/fscethiopiaPR ላይ በመግባት የውሳኔዎቹን ሙሉ ግልባጭ ማግኘት ይችላሉ፡፡

መልካም ንባብ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሚዩኒኬሽንና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ዳይሬክቶሬት

The Federal Supreme Court of Ethiopia

14 Oct, 11:56


ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን!