𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤 @jannah_islamic_tube Channel on Telegram

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

@jannah_islamic_tube


cross @izzyqueen_zxz

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤 (English)

Welcome to 𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤, a Telegram channel dedicated to providing a platform for sharing Islamic knowledge and inspiration. Led by the username @jannah_islamic_tube, this channel aims to spread the message of peace, love, and spirituality through various content and discussions. Whether you are looking for daily reminders, motivational quotes, or informative videos, this channel has something for everyone seeking to strengthen their faith and connection with Islam. Join the discussions, engage with like-minded individuals, and deepen your understanding of Islamic teachings. With cross collaborations with @izzyqueen_zxz, you can expect a diverse range of content that will enrich your spiritual journey. Follow 𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤 today and be part of a community dedicated to spreading positivity and knowledge. Embrace the beauty of Islam and nurture your soul with the wisdom shared on this channel.

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Feb, 11:55


በእዘነቱ ነው እንጂ በሲትሩ ታጅበን
እንደኛማ ቢሆን እንደ ወንጀላችን
እንኳን ልንወደድ ማንስ ሊዘይረን...

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Feb, 19:02


ፀጉር ሸፍኖ ሱሪ መልበስ ኪታብ ቀርቶ እንዳለመሞጠል ነው...

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Feb, 18:57


አዋጅ ሰዎች ሆይ ንቁ!!
ኢማናችሁን ጀድዱ። አካላችሁን በስፖርት መንፈሳችሁን በዒባዳ አንፁ። ማንነታችሁን በዚክር ገንቡ። መጪው ጊዜ ከባድ የዕልቂት ዓመት ነው። በኢማን ብርሃን ጨለማውን የሚሰነጥቁ ሰዎች ብቻ ነጃ የሚወጡበት ዘመን!! አላህ ለጦርነት የፈጠራቸው ሙጃሂዶች እንጂ የማይድኑበት ወቅት

አዋጅ ሰዎች ሆይ ንቁ!!
ምድርና ሰማያት የተመሰረቱባትን ቃል አጥብቃችሁ ያዙ። ፍጥረታት ወደዚህ ምድር የመጡባት፣ ይቅጣጩበት ዘንድ ቂብላ የተተከለባት፣ የጂሃድ ሰይፎች የተመዘዙባት፣ የአላህ መብት በባሪያው ላይ ሁሉ የተደነገገባት ቃል!! ላኢላሀ ኢለላህ!! በእርሷ መንገድ ኑሩ በእርሷ መንገድ እንደፀናችሁም ሙቱ። ራሳችሁን ለመጪው ጊዜ አዘጋጁ።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Feb, 18:47


➤ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም


“ከወንጀል ሁሉ ድንበር ከማለፍ (ከበደል) እና ዝምድናን ከመቁረጥ የበለጠ አላህ ለባለቤቱ በአኼራ ከሚያቆይለት ቅጣት ጋር ቅጣቱን በዱንያ ሊያፋጥንለት ተገቢ የሆነ የለም።”

📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 918


ረመዳን 18 ቀን ይቀሩታል አላህ ያድርሰን 🤲

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

10 Feb, 15:42


ልብህ ላይ የአላህን ፍራቻ
መለኪያው ሶላት ነው ❤️‍🩹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

01 Feb, 17:50


❤️‍🩹ለረመዳን ቆንጆ ቆንጆ ፕሮፋይል እና ወልፔፐር ፒክቸር ከፈለጋቹ ተቀላቀሉን👇👇
@remedan_picture

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

01 Feb, 17:49


ቀድር እንዲህ የሚያረጋጋ መልዕክት አለው .....

ያለፈህ ነገር አልተፃፈልህም
የተፈጠረልህ ነገር ፈፅሞ አያልፍህም!❤️‍🩹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

01 Feb, 17:30


አላህ አያረፍድም :-

📌 ዩሱፍ ላይ እንዳላረፈደው
📌 ያዕቆብን እንዲሁ እንዳልተወው
📌ዩኑስ ላይ እንዳልጨከነው.....

እኛም ላይ አያረፍድም🫶

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

30 Jan, 15:45


በራእ ቢን ዓዚብ ከነቢዩﷺ የሰሙትን እንዲህ በማለት አስተላለፉ፦ ለአላህﷻ ከፍተኛው ጀነት ላይ ሚያስገባቸው የተመረጡ ሰዎች አሉት እነርሱም ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ አስተዋይ ናቸው… አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከሰዎች ሁሉ አስተዋይ እንዴት ሆኑ አልናቸው

እርሳቸውም፦ ወደጌታቸው በመሽቀዳደምና ወደሚያስደሳው በመቻኮል ላይ ባለወኔ ስለሆኑ ነው ፣ የዱንያ እላፊዎቿ፣ ሹመቶቿና ፀጋዎቿን ችላ ያሉና ተዋርዳ የታየቻቸው ነበሩ ትንሽን ታገሱ........ ረዥምን አረፉ

كتاب حلية الأولياء وطبقات الأصفياء

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

27 Jan, 12:26


🦋ቀደሮችህ እንደ ሁኔታው ይሄዳሉ
አንተ ደስተኛ ሁነህባቸው እንዲሄዱ አድርግ
ምናልባት የመውደድህ ምንዳ ደስ ሊያደርግህ ይችላል😊💜

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

25 Jan, 14:20


ጅብሪልም ወደ ነብዩ ﷺ ዘንድ መጣና፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ ይህች ኸዲጃ ናት ምግብ ይዛ ወደ አንተ እየመጣች ነውና ወደ አንተ ስትመጣ ከጌታዋና ከእኔ የሆነን ሰላምታ አድርስላት። በጀነት ውስጥ ከዕንቁ የተሠራን ቤትን አብስራት።❤️
እናታችን ኸዲጃ ከጌታዋና ከታማኙ መልዕክተኛ የሆነን ሰላምታ በደረሳት ጊዜ ምን ተስምቷት ይሆን?

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

24 Jan, 12:58


አላሁ የውመል ቂያማ እነደዚህ ይላል…
የአደም ልጅ ሆይ…  ታምሜ ለምንድን ነው ያልጠየከኝ…  የአለማቱ ጌታ ሆነህ እንዴት ይላል … ባሪያዬ ታሞ አልጠየከውም ብትጠይቀው ኖሮ እሱ ዘንድ እኔን ተገኘኝ እንደነበር አታውቅም እንዴ

ርቦኝ ለምንድን ነው ያላበላኽኝ…  የአለማቱ ጌታ ሆነህ እንዴት አበላሀለሁ ይላል … ባሪያዬ ርቦት ምግብ ጠይቆህ አላበላኸውም ብታበላው ኖሮ እሱ ዘንድ እኔን ተገኘኝ እንደነበር አታውቅም እንዴ

ውሀ ለምንድን ነው ያላጠጣኸኝ …  የአለማቱ ጌታ ሆነህ እንዴት አጠጣሀለሁ ይላል … ባሪያዬ ጠምቶት አላጠጣኸውም ብታጠጣው ኖሮ እሱ ዘንድ እኔን ተገኘኝ እንደነበር አታውቅም እንዴ

አላህ እጃችንን ሁሌ ሰጪ ያርግልን
ልባችንንም ቸር ያርግልን

💚ዱንያ ላይ ያለ ነገር በሙሉ ቀሪ አይደለም 💚ጠቃሚው ነገር ከጠፊዋ ለዘላቂዋ ሀገሬ መስራት ነው

صلُّوا على خير العباد وسلِّـموا
    فصلاتنا ذُخـــــرٌ لنا ووسَـــامُ
    يا ربُّ صَـلِّ على النَّبيِّ محـمَّدٍ
    مَــا لاحَ برقٌ وأسـتهلَّ غَمـــامُ

    اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمدﷺ
ለዘላቂው ሀገር የምንሰራበት ፣በሀቢባችን ላይ የበዛ ሰለዋት የምናወርድበት በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚
መልካም ጁምዐ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

23 Jan, 19:07


🦋❝በዱንያ ህይወት ከምትይዛቸው ነገሮች ሁሉ በጣም ውዱ እና አሏህ ለባሮቹ ከለገሰው ግዙፉ ነገር ⎧ኢማን⎫ ነው .. ስለዚህ ጥበቃ አድርግለት ተጠባበቀውም ፣ ትርጓሜውንም በመልካም ስራዎች አሳምረው ... ሙዕሚንኮ ሀፍረተኛ ነው ፣ ሙዕሚን ለአሏህﷻ ባሮች ርህሩህ እና አዛኝ ነው❞🦋


🩵 الحبيب عمر بن حفيظ🩵

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

23 Jan, 15:53


🦋በየትኛውም ቦታ የውመል ቂያማ (በትንሳኤው ቀን) ለኔ ቅርቡ በዱንያ ሳለ በኔ ላይ አብዝቶ ሶለዋት ያወረደው ነው🦋

ሰይደልዉጁድ ﷺ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

23 Jan, 14:24


ምናልባት ከአላህ ሪዝቅ
ያንተ ድርሻ የርሱ ውዴታ ቢሆንስ !?🥰🧡
اللهم حبك وحب حبيبك🧡🤲

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

21 Jan, 17:10


ወዳጄ!
ሁላችንም ወደ አላህ እየሄድን ነው፡፡ ቀጥ ብሎ በሙሉ ኢማን እና ዒባዳ ወደ አላህ የሚሄድሰው ግን የለም፡፡ ሁሉም እያነከሠ ነው የሚሄደው፡፡ ሁሉም የጎደለው ነው፡፡ ሁሉም ደካማ ነው፡፡ ግማሽ ሶላት፣ ግማሽ ፆም፣ ግማሽ ዚክር፣ ግማሽ ቁርኣን… ይዘን ነው የምንሄደው፡፡ የደከመ፣ የሰነፈ፣ የሰባበረ የቂን ነው ያለን።

ባይደርስ እንኳን ወደርሱ የሚሄድን አላህ ባርያ አይመልስም፡፡ እንሄዳለን፡፡አላህ ይርዳን ።…

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

21 Jan, 06:02


channel mezgzat meflg 📥 inbox

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

20 Jan, 15:43


የመጨረሻችን በሚመስሉ ቀናትም ሂወት አላበቃም

.አሁንም ህይወት ይቀጥላል ቀደራችን እስኪደርስ
በየትኛውም ከባድ ችግር ውስጥ ከሆናችሁ ታገሱ።

አላህ ከታጋሾች ነውና😊

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

20 Jan, 15:25


«🦋....የእያንዳንዱ ቀን ንጋት አሏህ ጨለማዎችን እንደሚገፍ ማሳያ ነው ፣ አስተውሉ....! 🦋»

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

19 Jan, 18:15


አላህ🫀

ልመናህን መቀበል ባይፈልግ ኖሮ ዱዐውን አያገራልህም ነበር....

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Jan, 16:13


ተወዳጁ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«በተምር ቁራጭ ቢሆንም እንኳን እሳትን ተጠንቀቁ።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
:
ኢማም ኢብኑል‐ቀዪም [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐
«ሶደቃ ሰውየውን ከአላህ ቅጣት ይታደጋል። ወንጀሉና ኃጢኣቱ ጥፋት ሲፈርድበት። ሶደቃ ይመጣና ከቅጣት ያድነዋል። ከጥፋት ያላቀዋል።»
#በተምር ቁራጭም ቢሆን ነፍሳችሁን ከእሳት ጠብቁ!…

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

12 Jan, 14:29


ወዳንተ መምጣት እየፈለኩ
የዱንያ ጣጣዎች መንገድ ላይ አስቀሩኝ....
ካንተ ለመድረስ አስቤ በተነሳው ቁጥር
ነፍሲያና ሸይጣን ከጉዞዬ አገዱኝ።
ቁጣህ አይኑርብኝ እንጂ ሌላው ሁሉ ምንም ነው።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

12 Jan, 09:40


🦋ውድቅ ንግግርን በብዛት ማዳመጥ ቀልብን ያደርቃል ቀልብን ዚክር ማብዛት እና ሶላት አለ-ነቢይ ማብዛት እንጂ ሌላ ምንም አያለሰልሰውም🦋

الحبيب عمر بن حفيظ💚

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Jan, 17:45


ስስታም በዱንያ ላይ እንደ ድሆች ይኖራል በቀጣዩ አለም እንደ ሀብታሞች ይገመገማል!!

📕አሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Jan, 16:23


ይህ ለራሴ ለኔ ነው፦
ንቃ አንተ ዝንጉ መሀይም ሆይ! በቃ ስለራስህ ምን የምታውቀው የሚያሳስብህ ነገር የለም? በቃ ስትራብ መብላት፣ ስትጠግብ መተኛት፣ ስትናደድ መጨቃጨቅ መቆጣት...በቃ ይህ ነው የምታውቀው? ታድያ ከእንስሳዎች በምን ተለየህ!!!
#አህሉል_ዊርዲ 📿

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

07 Jan, 17:46


ይህ ለራሴ ለኔ ነው፦
ንቃ አንተ ዝንጉ መሀይም ሆይ! በቃ ስለራስህ ምን የምታውቀው የሚያሳስብህ ነገር የለም? በቃ ስትራብ መብላት፣ ስትጠግብ መተኛት፣ ስትናደድ መጨቃጨቅ መቆጣት...በቃ ይህ ነው የምታውቀው? ታድያ ከእንስሳዎች በምን ተለየህ!!!
#አህሉል_ዊርዲ 📿

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

06 Jan, 18:54


«አልወለደም፤ አልተወለደምም

«ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም☝️

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

04 Jan, 18:44


የመሬት መንቀጥቀጥ የትንሳዔ መቅረብ ምልክት ነው። ቢሆንም ነገሩ ሲከሰት ወደ አላህ በተውበት (በንስሃ) መመለስ እንዳለብን ዑለማዎች ይመክራሉ። በተረፈ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ከባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ከማድመጥ ባለፈ፤ ያገኙትን ሁሉ ከሚያወሩ የሶሻል ሚዲያ ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች ልንረበሽ አይገባም!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036



©: ቡኻሪና ሙስሊም በአማርኛ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

04 Jan, 13:23


ቀን ቀን የደከምንለት ሌት ሌቱን የቃዠንለት  ሃብትና ንብረት አመድ መሆኑ አይቀሬ ነው! ! እንኳን ተሰብሳቢው ሰብሳቢውም አይቀርለት!! 
كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍۢ👐
በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

04 Jan, 13:23


በ Alarm ቀርቶ በመሬት መንቀጥቀጥ መነሳት 😔

ኡመር ረድየላሁ አንሁ

أيها الناس ما كانت هذه الزلزلة إلا عند شيء أحدثتموه والذي نفسي بيده إن عادت لا أساكنكم فيها أبدا

ሰዎች ሆይ፣ ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው እናንተ በምታደርጉት ነገር ነው፣ ነፍሴም በእጁ በሆነው እምላለሁ ከተመለሰች፣ ከናንተ ጋር በውስጧ አልኖርም።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

03 Jan, 18:36


🦋የዛሬዋ ለይል- ለይለቱ ረጛኢብ🦋

የረጀብን የመጀመሪያ ኸሚስ እና ጁሙዐ የአሏህ ደጋግ ባሮች በስስት ከሚጠብቋቸው ለይሎች አንዷ ናት።
🌹ሠይደልዉጁድﷺ የተፀነሡበት ድንቅ ለይል🌹
አሏህ በእኛ ፍላጎት እና ሂማ ሳይሆን  በራህመቱ  ይወፍቀንና የአሏህ ደጋግ ባሮች የሚያደርጉትን

🩵ኢስቲጝፋር 
 🩵ያ ሃዩ ያ ቀዩም
🩵 ያ  ሃፊይ
🩵ሱረቱል ሙናፊቁንን እናብዛ!...... 

    اَعُوْذُ بِاللهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيْمِ
بِسْمِ اللهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيْم

اَلَّلهُمَ اِنِّيْ أَسْتَغْفِرُكَ مِنْ كُلِّ مَا تُبْتُ عَنْهُ اِلَيْكَ ثُمَّ عُدْتُ فِيْهِ، وَأَسْتَغْفِرُكَ مِنْ كُلِّ مَا أَرَدْتُ بِهْ وَجْهَكَ فَخَالَطَنِيْ فِيْهِ مَا لَيْسَ فِيهْ رِضَائُكَ. وَأَسْتَغْفِرُكَ لِلنِّعَمِ الَّتِي تَقَوَّيْتُ بِهَا عَلَى مَعْصِيَّتِكَ، وَأَسْتَغْفِرُكَ مِنَ الذُّنُوْبِ اَلَّتِيْ لَا يَعْلَمُهَا غَيْرُكَ وَلَا يَطَّلِعُ عَلَيْهَا أَحَدٌ سِوَاكَ، وَلَا تَسَعُهَا اِلَا رَحْمَتِكَ، وَلَا تُنْجِيْ مِنْهَا اِلَا مَغْفِرَتُكَ وَحِلْمُكَ. لَا اِلَهَ اِلَا أَنْتَ سُبْحَانَكَ، اِنِيْ كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينْ.

اَلَّلهُمَ اِنِّيْ أَسْتَغْفِرُكَ مِنْ كُلِّ ظُلْمٍ ظَلَمْتُ بِهِ عِبَادِكَ، فَأَيَّمَا عَبْدٍ مِنْ عِبَادِكَ أَوْ أَمَةٍ مِنْ إِمَائِكَ، ظَلَمْتُ فِيْ بَدَنِهِ أَوْ عِرْضِهِ أَوْ مَالِهِ، فَأعْطِهِ مِنْ خَزَائِنِكَ الَّتِيْ لَا تَنْقُصْ. وَأَسْأَلُكَ اَنْ تُكْرِمَنِيْ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيِءٍ. وَلَا تُهِيْنَنِيْ بِعَذَابِكَ وَتُعْطِيَّنِيْ مَا أَسْأَلُكَ فَاِنِيْ حَقِيْقٌ بِرَحْمَتِكَ يَا أَرْحَمَ الرَّاحِمِينْ. وَصَلَّى اللهُ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ و عَلَى َآلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينْ. وَلَا حَوْلَه وَلَا قُوَّةَ إِلَا بِاللهِ الْعَلِيِ الْعَظِيْم.     

   አሏህ ለይሉን ከሚጠቀሙበት ያድርገንማ🤲

#አህሉል_ዊርዲ 📿

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

03 Jan, 17:19


አላህ 😊

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

29 Dec, 16:56


🦋ብትቀማመጣቸው ማትነደምባቸው ሰዎች 🦋

«በዱንያም ሆነ በአኺራ ደስታን ማግኘት የከጀለ ሰው ነፍሱን በእነዛ የአሏህ ደጋግ ባሮች ቀልብ ውስጥ ያስገኝ...አሉ።

“እንዴት?”ቢባሉ..ውደዳቸው ይወዱሀል ቀልባቸው አሏህን የሚመለከቱበት ስፍራ ነውና..🌹»

🦋ኢማም አል-ገዛሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ 🦋

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

29 Dec, 14:16


ለቻናላችን ቤተሰቦች  በሙሉ ። ኪስን የማይጎዳ ምንም አይነት Side Effect የሌለው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ የሰውነት ለውጥ የሚያሳያችሁን ኦርጅናል የየመን ማር ይዘንላችሁ መተናል። እዘዙን ያላቺሁበት እናመጣለን!!

በተፈጥሮአዊ መንገድ በአጭር ቀናት ለመወፈር የሚረዳ ንፁህ ማር ለወንድም ለሴትም የተዘጋጀ ይዘዙን...በየክፍለሀገሩም እናደርሳለን ።

በብዛት ለሚፈልግ  በቅናሽ እናስረክባለን 

ስልክ ፦0986703904

ቴሌግራም፦ @Jentit1
ነፃ delivriy

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

29 Dec, 08:55


ማንም ላይ ተማምነሽ
በሙሉ ልብሽ አትደገፊ
ዞር ሲሉብሽ ልትወድቂ ትቺያለሽ❤️‍🩹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

29 Dec, 08:49


ረጀብ በአላህ ዘንድ ከተከበሩና ከተውደዱት ወሮች መካከል ነው። በዚህ ወር ኢስቲግፋር ማብዛት ይወደዳል! ጥሞና ይፈልጋል! ... ወደ ረመዳን እየተጠጋን ውሏችንንና ሁኔታችንን የተሻለ ለማድረግ ካልሞከርን ብሎም ነፍሶቻችንን የምንበድል ከሆነ እንከስራለን!

ልክ እንደ ጀሰዳችን ሩሓችንም ምግብ ይፈልጋል። ቁርኣን እንድትቀራለት ይፈልጋል።...በተለያዩ ዚክሮች የተራበውን ልቡን እንድንሞላለት ይፈልጋል! ውስጣዊ ሰላሙን ከሚያሳጡት ነገሮች በሙሉ እንድታርቀው ይፈልጋል። 💛

ሰውነታችንን በአካል እንቅስቃሴና Diet እንደምንንከባከበው ሩሕም እንክብካቤያችንን ይሻል! ቆሻሻ መልበስ እንደማንፈልገው ሁሉ ነፍሳችንን የሚያቆሽሹ ጉዳዬችንም መጥላት ይኖርብናል! ... እኛ ግን በእንቶ ፈንቶ ሀሳቦች፤ ጥላቻና በመጥፎ እይታዎች ሩሓችንን እናደክመዋለን! አላህ ቁርኣኑ ላይ እንዲህ ይላል፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا عَلَيْكُمْ أَنفُسَكُمْ ۖ لَا يَضُرُّكُم مَّن ضَلَّ إِذَا اهْتَدَيْتُمْ ۚ إِلَى اللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ፤ (ጠብቁ)፡፡ በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም፡፡ የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡" [ሱረቱል ማዒዳ:105]

አሁን ላይ አለመረጋጋት በሰፊው ይስተዋልብናል! ውስጣችንን ረብሸን ሌላውንም እንረብሻለን። ስክነት ይጎድለናል! ወሬዎቻችን ፈጣንና ተለዋዋጭ ናቸው! መስማትም ማየትም የምንፈልገው የሚያስደነግጥ፥ የሚያበጣብጥ አጀንዳ ነው! ለጊዜው ስቀን አልፈን ሊሆን ይችላል ነፍሳችንን ግን በከባዱ እየበደልነው ነው! ከመንፈሳዊ ምግቦች እያስራብነው ነው! የ Depression እና የጭንቀት ተጠቂ የመሆናችን አንድ ምክንያት ይህ ነው።

ለነፍሳችን ሰኪና የሚሰጡ ምግቦችን መመገብ ራስን የመውደድና የመንከባከብ ጥግ ነው! ቁርዓን፤ ሰለዋት፤ ዚክር፤ ሰላት፤ ፆም፤ ሰደቃ፤ መልካም ንግግር፤ ፈገግታ እና ሌሎችም ለልባችን እርካታ የሚሰጡ የነፍስ ምግቦች ናቸው። ከጫጫታዎች፤ ከመጥፎ ንግግሮችና ሀሜቶች እራሳችንን የምንከላከለው በመንፈሳዊ ተግባሮች ብቻ ነው። ... በየጊዜው ገለል ብለን ኸልዋ ገብተን ከነፍሳችን ጋር የምንተሳሰብበትን ጊዜ ካልፈለግን እና የጥሞና ጊዜ ከሌለን ውስጣችን መረበሹ አይቀርምና! ... አላህ ይሁነና 😊

አላህ የውስጥ ሰላምን ይወፍቀን! 💛....መጪውን የረጀብ ወር ከሚጠቀሙት፤ የረመዳን ወር'ንም ከሚደርሱ ባሮች ያድርገን!

#የረጀብ_ሐሳቦች 💛

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

27 Dec, 17:45


ጂብሪል መጥቶ አበሰረኝ 😊...አሏህ እንዲህ በል ብሎኛል በማለት ነገረኝ፦

❝ባንተ ላይ ሶለዋት ያወረደ እኔም በርሱ ላይ ሶለዋት አወርዳለሁ...ባንተ ላይ ሰላም ያወረደ በርሱ ላይ ሰላም አወርዳለሁ።❞😊

❤️ወለላዬ የኔው ነብይ ﷺ ❤️

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

26 Dec, 15:56


🦋ከአንደሉስ ሙስሊሞች ባህል መካከል አንድ ቤት ውስጥ የአላህን ቃል የሀፈዘች ሴት ካለች ቤቱ ፊለፊት የሚበራ ፋኖስ ይደረጋል..🦋

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

22 Dec, 18:01


ምኞትሽ የሰው ልጅ ውዴታን ለማግኘት
አታድርጊ የሰው ልጅ ልብ ተገለባባጭ ናት
ዛሬ ወዶሽ ነገ ይጠላሻል:: ምኞትሽ
አላህ በወደደኝ ብለሽ ተመኚ እሱ ከወደደሽ
ሁሉም ነገር ይወድሻል አላህ ከሚወዳቸው ያድርገን አሚን


.❤️‍🩹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

22 Dec, 17:05


"ከምድር በላይ ሆኖ ከአላህ ጋር አደብ ያለደረገ ሰው ፣ ከምድር በታች አላህ አደብ ያስይዘዋል።"

    (ሀሰኑል በስሪ (ረሂመሁላህ))

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

22 Dec, 05:35


አላህ እኮ ቸር ነው
አንድን ወስዶ እልፍ መስጠትን
ያውቅበታል الحمدلله❤️‍🩹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

19 Dec, 15:35


ህይወት ምንም ያህል ብትከብድ
እወቅ الله ነፍስን ከአቅሟ በላይ
አይጭንባትም::

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

19 Dec, 15:34


ሐኪም ዘንድ እያንዳንዱን ህመምህን
በዝርዝር መናገር ግድ ይልሃል !!


ነገር ግን አላህ ዘንድ ያ ኢላሂ… 🤲
ማለቱ ብቻ ይበቃሃል።
الحمدلله

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

19 Dec, 15:34


ደስተኛ ለመሆን
ብቸኛው  መንገድ ወደ አሏህ
መቅረብ ነው።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

17 Dec, 18:17


🦋هل تعلم أن لك رزقين؟🦋
ታውቃለህን ላንተ ሁለት ሪዝቅ እንዳለህ⁉️

🦋ሪዝቅ ሁለት ነው..ግዚያዊ እና ቋሚ ሪዝቅ
🌹 ጊዚያዊ ሪዝቅ ምንለው አሁን ያለህ ግና አሏህ በማንኛውም ሠዐት ሊወስድብህ ይችላል። ማለትም ጤና፣ ልጅ፣ገንዘብ፣ደስታ፣ስኬት፣ ጓደኛ፣ስራ እና ሌሎች ..ሁሉም ዐለማዊ ሪዝቅ ናቸው።

🌹ቋሚ ሪዝቅ ግን እስከ ቂያማ ቀን ድረስ ቋሚ ሆኖ ሚቆይ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዐለም የሚጠቅመን ሪዝቅ ነው።ማለትማ...

🌟ሠዎች በተኙበት ወቅት ተነስተህ ሁለት ረከዐ ሠግደህ ጌታህን መገናኘትህ ..ሪዝቅ ነው።
🌟ሶላተ ዱሃ መስገድህ..ሪዝቅ ነው።
🌟ወላጆችህን መኸደምህ..ሪዝቅ ነው።
🌟በሶላት ውስጥ ያለህ ኹሹዕ..ሪዝቅ ነው።
🌟ያማረ ስነምግባርህ ..ሪዝቅ ነው።
🌟አሏህን ዚክር ማድረግህ..ሪዝቅ ነው።
🌟ቅንነትህ ..ሪዝቅ ነው።
🌟ዝምድና መቀጠልህ ..ሪዝቅ ነው።

🦋ጊዚያዊ ሪዝቅ.. ከቋሚው ሪዝቅ እንዲያዘናጋን አንፍቀድ..የሀቂቃ ሪዝቅ ዒባዳን መወፈቅ ነው.. ምክንያቱም የሀቂቃ ሀያትህ እርሱ ነውና።

🌹ያ ረብ..የተዘጉብንን የኸይር በሮች ክፈትልን ባርክልንም🌹

#አህሉል_ዊርዲ 📿

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

17 Dec, 13:59


መርዛማ ሰዎችን ማጣት ድል ነው ::

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

17 Dec, 13:59


ሲጋራ ብታጨስም ሙስሊም ነህ!
አልኮል ብጠጣም ሙስሊም ነህ!
ዘፈን ብታዳምጥም ሙስሊም ነህ!
ዚና ብትሰራም ሙስሚም ነህ!
ግን ሁሌም ቢሆን አስታውስ ሰላት እስካልሰገድክ ሙስሊም አይደለህም!።
አንድ ሙስሊም ከካፊር የሚለየው ነገር በሰላቱ ነው ምናልባት በቀን 100 ጊዜ
(لا اله لا اله الا الله)
ልትል ፣ ፆም ልትፆም ትችላለህ ግን አዝካርህ ፆምህ ምንም ኸይር ስራህ ያለ ሰላትህ ጥቅም የለውም
ለዛም ነው
ሰላትን አደራ
ሰላትን አደራ
ሰላትን አደራ
ብሎ ሶስት ጊዜ የመጨረሻ ንግግራቸው ያደረጉት ።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Dec, 18:13


ማስታወሻ
ሰውን መበደል ከባድ ወንጀል ነው። የዙልምን ክፍያ አላህ እንደበፊቱ እያዘገየ አይደለም ። ምላሹን ነገሩ ሳይቆይ አየር ላይ እንደቴሌ ብር እየከፈለ ነው። አለኝ አንድ ወዳጄ።

ከበደል ተጠንቀቁ ። የቂያማ ቀን ድርብርብ ጨለማ ሆኖ ይጠብቃችኋልና።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Dec, 17:20


ሙገሳው ጌጥ ወቀሳው ደግሞ ነውር የሆነው አላህ ብቻ ነውና ከአፈር በላይ ላለ አፈር ሙገሳ ብለህ ስራህን አታበላሽ❗️

ኢኽላስ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Dec, 05:50


🦋አል ኢማም አሽ-ሺብሊይ አንድ ጎረቤታቸው ካረፈ በኋላ በህልም አየሁት አሉ....
"አሏህ ምን አደረገክ?" አልኩት።
እሱም " ያ! ሺብሊይ... ትላልቅ አስደንጋጭ ክስተቶች አለፉብኝ😥፡፡ ከነሱ ዉሰጥ ሁለት መላኢካዎች መተው ቀብር ዉስጥ ሲጠይቁኝ ከድንጋጤ የተነሳ አፌ ተቆላለፈ..መመለስም አቃተኝ..በምን ምክንያት ነው ይሄ የገጠመኝ? በእስልምና ሞቼ አይደል እንዴ? አልኩ ለራሴ....

ተጣሪ በሚሰማ ድምፅ ተጣራ.." ይሄ ምላስህን ችላ በማለትህና ባለመጠበቅህ ያጋጠመህ ቅጣት ነው" አለኝ። መላይካዎች ሊቀጡኝ እና ሊይዙኝ ሲመጡ እንደ ድንገት አንድ ቆንጆ መልክና ጥሩ ጠረን ያለው በእኔና በነሱ መሀከል ሆኖ ከለከላቸው …ከዛ የጥያቄውን መልስ እያስታወሰኝ አስባለኝና መለስኩላቸው።

እጅጉን አጀበኝና "አሏህ ይዘንልህና አንተ ማነህ?" ብዬ ጠየቅኩት።
እሱም "እኔ ሰይደልዉጁድ ላይ ሶለዋት በማብዛትህ ምክንያት የተፈጠርኩ ፍጡር ነኝ! 😍 በተጨነክና በተጠበብክ ግዜ እንድረዳህ ታዝዣለው" አለኝ !!!
ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
"ኢዝን ተክፊ ሐመክ ወየግፊር ዘንበክ"
እንደዛውም
"💚 የክፊ ሐመክ ወየቅዷ ጘመክ" ብለዋል። ከጭንቀት ሁሉ እንደሚገላግል እና ወንጀልን እንደሚያስምር ያወሱበት ሀዲሳቸው ነው🦋

መቲኑ በሀቁ ያግባን አሚይን🤲

#አህሉል_ዊርዲ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

12 Dec, 17:52


የተሰበረች ልብ የታመመች ነፍስ
የዛለች አካል ሰብር ያጣች ሁሉ ካንተ
ውጭ ማን ጠጋኝ አለው ኢላሂ
በዝነትህ🥹🙏

🤍

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

12 Dec, 17:02


🦋አል ኢማም አሽ-ሺብሊይ አንድ ጎረቤታቸው ካረፈ በኋላ በህልም አየሁት አሉ....
"አሏህ ምን አደረገክ?" አልኩት።
እሱም " ያ! ሺብሊይ... ትላልቅ አስደንጋጭ ክስተቶች አለፉብኝ😥፡፡ ከነሱ ዉሰጥ ሁለት መላኢካዎች መተው ቀብር ዉስጥ ሲጠይቁኝ ከድንጋጤ የተነሳ አፌ ተቆላለፈ..መመለስም አቃተኝ..በምን ምክንያት ነው ይሄ የገጠመኝ? በእስልምና ሞቼ አይደል እንዴ? አልኩ ለራሴ....

ተጣሪ በሚሰማ ድምፅ ተጣራ.." ይሄ ምላስህን ችላ በማለትህና ባለመጠበቅህ ያጋጠመህ ቅጣት ነው" አለኝ። መላይካዎች ሊቀጡኝ እና ሊይዙኝ ሲመጡ እንደ ድንገት አንድ ቆንጆ መልክና ጥሩ ጠረን ያለው በእኔና በነሱ መሀከል ሆኖ ከለከላቸው …ከዛ የጥያቄውን መልስ እያስታወሰኝ አስባለኝና መለስኩላቸው።

እጅጉን አጀበኝና "አሏህ ይዘንልህና አንተ ማነህ?" ብዬ ጠየቅኩት።
እሱም "እኔ ሰይደልዉጁድ ላይ ሶለዋት በማብዛትህ ምክንያት የተፈጠርኩ ፍጡር ነኝ! 😍 በተጨነክና በተጠበብክ ግዜ እንድረዳህ ታዝዣለው" አለኝ !!!
ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
"ኢዝን ተክፊ ሐመክ ወየግፊር ዘንበክ"
እንደዛውም
"💚 የክፊ ሐመክ ወየቅዷ ጘመክ" ብለዋል። ከጭንቀት ሁሉ እንደሚገላግል እና ወንጀልን እንደሚያስምር ያወሱበት ሀዲሳቸው ነው🦋

መቲኑ በሀቁ ያግባን አሚይን🤲

#አህሉል_ዊርዲ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

12 Dec, 16:46


አላህ በምንወደው ነገር በቅርብ
ያስደስተን ይሆናል!
ኢንሻ አላህ 🖤

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Dec, 19:14


💔 በዝምታ ልብን ከሚበላ ሀዘን
አላህ ይጠብቃችሁ 😓

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Dec, 18:04


🌹ነገ ኸሚስነው ኢንሻአሏህ የቻልን እንፁም 🤗
ለሌሎችም ሊላሂ ተዓላ አንስታውሳቸው
አሏህ ካገራላቸው ያድርገን🤲

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

05 Dec, 15:47


ያጀባር በሚሰብረኝ ሰው ላይ አንታጠለጥለኝ..
ያቃዲር በማንም ልብ ላይከባድ ሸክም አታድርገኝ..
ያቀሪብ እንድርቀው ከሚመኝ ሰው አርቀኝ
አሏሁማ ሶሊ🤲❤️

ሙሂቦቹ😍❤️
በغይብ ዱዓቹ አስታውሱኝ🤲
አሏህዬ አሚን ቢያለው እንተም በሯህመትህ ተቀበላቸው🤲❤️

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

16 Nov, 17:22


.🥀

ይሰምራል ሃሳቡ ይሽራል ህመሙ
ያያቸው እንደሆን ነብዩን በሕልሙ

صلى الله عليه وسلم💚

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

08 Nov, 13:02


صلِّ الله عليك يا سيدي يا رسول الله ﷺ

|   ጁምዓኩም ሙባረክ🖤 በሶለዋት የደመቀ ይሁን!      |

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

02 Nov, 11:34


ጭንቀት እና ጉም አንድ ናቸው የፈለጉትን አክል ቢገዝፉ ጨለማው ምንም አክል ድቅድቅ ቢል ጉም ነውና ብትን ይላል ጭንቀትም ሀከዛ በተለይ የጭንቀት መበተኛ የሀሳብ መድረሻ የነገራት መክፈቻ 🔑 ሰለዋትን ከያዝክ ጭንቀት ትካዜ መገቢያ ያጣሉ ሰይዱል ውጁድ ሲጠሩ ።ሰሉ አለይሂ ወሰሊሙ ተስሊማ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

02 Nov, 11:26


አንድ ዐሊም እንዲህ ይላሉ ❝🦋አስተዋይ ማለት መልካምና እና መጥፎን ያወቀ ሰው አይደለም።እነሆ አስተዋይ ማለት መልካምን ባየ ግዜ የተከተለና መጥፎን ባየ ግዜ ደግሞ የራቀው ማለት ነው🩵❞ አሉ

  🦋    🦋

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

29 Oct, 16:20


" በአላህ ሲትር ውስጥ መቆየት
ካሻህ አላህ በሌላው ላይ የጣለውን
ሲትር አታንሳ..!"

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

28 Oct, 15:45


🦋የዋሻው ወዳጃቸውም የዐለሙ ዘይኑ የኔ ሠይደልዉጁድﷺ ውሃን ተጠምተው ባሉበት ሃለት አንዲት ኩባያ ወተት ያገኛሉ

ሲዲቁ ❝የወለደችኝ እናቴ ፊዳ ትሁንልዎ❞ እያሉ ጥማቸውን ከጥማቸው አስቀድመው እፊታቸው ተቀምጠው ሲጎነጩ ይመለከቱ ያዙ

ወተቱ የሠይደልዉጁድንﷺጉሮሮ አርጥቦ  ጥማቸውን ሲያረካላቸው ሲመለከቱ.. ፍቅርን በፈጠረው በአህመድ ጌታ እምላለሁ የእርሳቸውም ጥማት ተወገደ..❤️
🌹❞ الحبيب يشرب والمحب يرحى❝
🌹ተፈቃሪው ይጎነጫል አፍቃሪም ይረካል🌹   

እንደዛው ነውስ           

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

24 Oct, 18:34


🦋አቡ ጣሊብ...🦋

🩵ሰይደልዉጁድንﷺ ከ8 አመታቸው ጀምሮ ያሳደገ...ከልጆቹ የበለጠ ይሳሳላቸው ነበር...ለኑቡዋ ከተላኩ በኋላም ድጋፉ አልተለያቸውም ...ኢስላምን ባይቀበልም ህይወቱ እስካለፈበት ወቅት ድረስ ከጠላት ይከላከልላቸው ፣ ይንከባከባቸው ነበር።...ሰይደልዉጁድﷺ በሐዲሳቸው እንዳሉት በጀሐነም ትንሹን ቅጣት የሚቀጣው እሱ ነው...በምንም ሳይሆን ለሳቸው በነበረው መሐባ ነበር...
اللهــم صلِّ على سيِّدنا محمَّدٍ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

24 Oct, 18:34


🤎ሰለዋት አብዙ!
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም💚💚💚

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

23 Oct, 06:05


ክሪምቱን ከኡስታዝ ያሲን ኑሩ ምክሮች እና ዳዕዋዎች አጫጭር ምክሮች ጋር አዲስ በአይነቱ ልዩ ኘሮግራም ለመከታተል ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ ይሃው ለማግኘት ቻናላችንን JOIN ያድርጉ!!! ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

23 Oct, 05:31


30 ሰከንድ ነው ያላቹ ፍጠኑ መልሱ !

🎓 ቀላል ጥያቄ ☑️ 2 🏆

2.ሁሉም ነብያት ለአከባቢያቸውብቻ
ይላኩ ነበር አንድ ነብይ ብቻ ስቀር ይህ
ለአለማት የተላከው ነብይ ማነው⁉️

         ቀላል ጥያቄ ነው ሁላችሁም ተሳተፉ
ከመለሱ ልዩ ቻናል ይጋበዛሉ!

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

23 Oct, 05:15


🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞ጀናዛ ላይ ዝሙት የፈፀመው ወጣት

ሱብሀነላህ በጣም ልብ የሚነካ እውነተኛ ታሪክ አላህ ይጠብቀን እባካችሁን ከ18 አመት በታች ለሆናችሁ እንድታዳምጡት አይፈቀድም ❗️‼️

ሙሉ ታሪኩን ለማድመጥ አሁኑኑ ከስር full audio የሚለውን ነክተው ጆይን በማለት ታሪኩን ያገኛሉ

🔑ማሳሰቢያ
ወላሂ የእውሸት ❗️ውሸት ሀራም ነው❗️
ማስታወቂያ አይደለም pin message ላይ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

20 Oct, 13:56


ላንተ የተከለከልክ ቢመስልህም...እውነታው ግን

......ታዝኖልህ ነው

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

19 Oct, 17:33


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

🦋አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ ❣️

[ሱረቱል-አሕዛብ - 56]

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

19 Oct, 16:14


🦋ለአንበሳው ሠግተውለት🦋

🦋በአንድ ወቅት ሰይዲ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ  አናታቸው ላይ አማኢማቸውን እንደለበሱ ከተፋፋመው ማዕረካ ላይ ይዘልቃሉ። ሞቅ ካለው የሰይፍ ፍጭት መሀል   የሰይድ ኻሊድ አማኢማ ከከሃዲያኖቹ እግር ሥር  ተንከባለለች።
ጥምጣሟን ፍለጋ ሰይድ ኻሊድ ብቻቸውን ሆነው  ወደ ከሃዲያኑ ተርታ ሲገሰግሱ ሶሃቦች በድፍረታቸው እየደነገጡ ኻሊድ ሆይ! በገዛ እጆቻችሁ  ወደ ጥፋት አታምሩ ተብሏል ምነው? እያሉ  ተጯጯሁ....ለአንበሳው ሰግተውለት።

ሰይዲ ኻሊድ ጦር ግድሙን አተራመሱት “ምነው ለአንዲት ጥምጣም ተብሎ ኸልቁን ማስጨነቁ” ያስብላል.... ጥምጣማቸውን ከወደቀችበት አንስተው ተመለሱና ለሷሂቦቻቸው እንዲህ ሲሉ አስረዱ
“ስሙኝማ ጓዶች ይህች አማኢማ ተራ ጨርቅ  አትምሰላችሁ...የአህመድ የጸጉር ዘለላ የተቋጠረባት ናት!

 የዐለሙ ራህመት በሓጅ ወቅት ላይ ፀጉራቸውን ተልጨው ነበር... ከጸጉራቸው ላይ እየዘገኑ  ለአስኋቡ ሁላ እንዲከፋፈልም አዘዙ....ሰይድ ጦልሃ ካከፋፈለው የጸጉር ዘለላ ላይ የአንድ ጉንጉን ባለዕጣ ሆንኩኝ...ግዜ ሳላጠፋ የአህመዱን ጉንጉን  ከጦር ፈረሴ ግንባር ላይ አንጠለጠልኳት....ከዚያማ       አንድንም ዘመቻ አልተሳተፍኩም በጸጉሩ በረካ  የጠላትን መንደር ድባቅ የመታሁ ብሆን እንጂ” አሉ
🦋🦋🦋🦋🦋

#khemis💚💚

🤍اللهم صل🤍 وسلم على🤍 سيدنا ونبينا 🤍وحبيبنا وشفيعنا🤍وقرة عيوننا 🤍محمد صلاةً🤍 تشرح🤍 بها صدورنا🤍

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

12 Oct, 17:14


🩸🩸

ተውበት ከወንጀል መዝገባችን
ሊያጠፋልን ይችላል
ከ ህሊናችን ላይ ሚያጠፋልንስ ምን ይሆን?

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Oct, 11:20


♦️ሰይዲና ዐሊይ كرم الله وجهه ተጠየቁ ❞«ከሞት  የበለጠ ከባድ ነገር አለን?»

   🌹«አዎን የወደዱትን መለየት ከሞትም ይብሳል»
   
እንደርሳቸውስ ያጣ ማን አለ? የህይወት አባታቸውን የዐለሙን ራህመት እና የዘይነልዉጁድን ልጂት የሃሰነይኖቹን እናት ዛህራዬ ማጣት ይከብዳል!  
                               
ሶላት እና ሰላም  በአህመድ በኑር አበባው   በቤተሰቡም ላይ ይስፈን🌹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

11 Oct, 11:19


ወደኔ
ከተመለሱ እኔ ወዳጃቸው ነኝ
እምቢ ካሉ እኔ ሀኪማቸው ነኝ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

06 Oct, 21:49


እያደግን ስንሄድ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)ለምን ይህች አለም ለአማኝ እስር ቤት ናት እንዳሉ እንገነዘባለን

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

05 Oct, 16:06


🦋እኔ የዐለሙ ራህመት ሙሀመድ ነኝ🦋

❝ወደ አሏህ ቤት ዚያራ ጉዞ ወጣሁ ይላሉ አንድ የአሏህ ባሪያ..።በመንገድ ላይ አንድን ሰው ተወዳጀሁ ታዲያ ይህ ሠው አይቀመጥም አይቆምም አይበላም  አይጠጣም አይሄድም አይመጣም በሠይደልዉጁድﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ ብቻ።
ብዛት ሶለዋት የሚያወርድበትን ምክንያት ጠየቅሁት እና እንዲህ አለኝ❞ ይላሉ

      ❝ከአባቴ ጋር ወደ መካ ጉዞ ጀመርን።በመሃል መንገድ አንድ ማረፊያ ቦታ ላይረፍት አረግን።ቦታው ላይ ተኝተን በነበርንበት በህልሜ አንድ ተጣሪ ጠርቶኝ ❝አንተ ሰው ንቃ!  አሏህ አባትህን ገድሎታል ፊቱንም ማጥቆርን አጥቁሮታል❞  ሲለኝ ሰማሁ በድንጋጤ ከእንቅልፌ  ነቃሁ።በፍጥነት ተሸፋፍኖ  የተኛውን አባቴን ፊት ስገልጥ  አባቴን እንደተባለው  ፊቱ ጠቁሮ ተኮራምቶ ሞቶ አገኘሁት። ልቤ ተሰበረች የበረታ ሐዘን ውስጥ ባለሁበት በድጋሚ እንቅልፍ አሸነፈኝ።
               አንድን ህልም በድጋሚ አየሁኝ። ከአባቴ ራስ እና እግር በኩል 4  4  ጥቋቁር አስፈሪ ፍጥረታት አባቴን ለመቅጣት እየተቻኮሉ  ነበልባልማ  ቁልምም ብረቶችን ይዘው አየኋቸው። በዚሁ አስፈሪ ሁኔታ ላይ  አንድ የፊቱ ወገግታ  ከጥጥ ፍልቃቂ የነጣ  ውብ ሰው አስፈሪዎቹን ፍጥረታቶች  ❝ከዚህ ሰው ራቁ❞ እያለ በብርሃኑ ሃይል አባረራቸው። የአባቴንም ፊት ገልጦ በኑር ፈገግታ ሞላው።

    ባለግርማው ሰው  ወደ እኔ ተጠግተው ❝አሏህ የአባትህን ፊት አብርቶለታል❞ አሉኝ።    ❝ማናችሁ ለአባቴስ ይህንን ለምን አደረጉለት❞ብዬ ስጠይቃቸው

          ❝እኔ የዐለሙ ራህመት ሙሀመድ ነኝ። አባትህ ነፍሱን በወንጀል ያጨማለቀ ድንበር አላፊ ነበር።ግና እኔ ላይ ሶለዋት ከማውረድ ቦዝኖ አያውቅም።  ❝🦋وأنا غياث لمن صلى علي🦋❞ በእኔ ላይ ሶለዋትን ለሚያበዛም የክፉ ቀን  ደራሽ እሆንለታልሁ!

የኔ ሠይደልዉጁድﷺ🩵

📜ከሠይድ ጀማሉዲን መውዒዛቸው ላይ የተገኘ

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

04 Oct, 17:55


🦋ሞኝ አወራ ብለህ አትመልስ አንተ ሰው,
ዝምታህ ይሻላል ምላሽ ከምትሰጠው...
ካናገርከውማ ደስታውን አገኘ ፍላጎቱም ሞላ,
ዝም ያልከው ጊዜ ግን,
በቁጭት ይሞታል ጥፍሩን እየበላ...🦋

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

27 Sep, 09:59


ጁምዓ.....

ሰይዲ ረሱሉላህ ﷺ እንዲህ ብለውናል :

" ጁምዐ ቀን እኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ ..
የኡመቴ ሰለዋት ሁሌ ጁምዐ ቀን ይቀርብልኛል..
እኔ ላይ ያወረደው ሰለዋቱ የበዛ የበለጠ ወደኔ ቅርብ ይሆናል "
" أَكْثِرُوا عليَّ مِنَ الصَّلاةِ في يومِ الجمعةِ ؛ فإنَّ صَلاةَ أُمَّتي تُعْرَضُ عليَّ في كلِّ يومِ جُمُعَةٍ ، فمَنْ كان أكثرَهُمْ عليَّ صَلاةً ؛ كان أَقْرَبَهُمْ مِنِّي مَنْزِلَةً ."
رواه البيهقي

ሰሉ አለ ነቢ
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

21 Sep, 20:12


S֮t֮r֮o֮n֮g֮ I֮m֮a֮n֮:
Report
Report
Report
   ቁርአንን ልክ እንደ ሙዚቃ አንቋሽሿል
እንዴት ቁርአንን እንዳረከሰው በሊንኩ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ

ሁላቸውም YouTube እና ቴሌግራም channal ገብታችሁ ሪቦርት አርጉ።

Because they got alot of report on the above channal they proceed to this new one. We will not stop reporting untill they stop mocking by our Quran‼️‼️‼️

Report their YouTube channel ⚠️

https://youtube.com/@officialquranicsongs?si=et-vaE3gi_LD1-yE

And here their telegram channal👇

https://t.me/QuranicSongs

Share

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

21 Sep, 06:50


💙የወደድከውን ባታገኝ እንኳን ያገኘኸውን ውደድ
💙ላንተ መልካም ቢሆን ኖሮ #አሏህ የወደድከውን ላንተ ባደረገልህ ነበር!!!

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

18 Sep, 16:54


"I pray to ﷲ that every person in this world obtains his full right to live the life he desires, to achieve what he wants whenever he wants and for his own reasons and not others, to live a dignified life in which he does not have to compromise for any reason."

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Sep, 12:34


🤍 ስንቱ ስላንቱ ገጠመ ሀቢቢ 🥹 ግና መቼ የእርሶስ ነገር ገባን እና ...... በዚህች ብርቅዬ ማዓዛ ባላት...ጠረኗ ተፈልጎ ባልተገኘ ሌሊት ... የእርሶ ኡመት አደረገ እና በብዙ አበሰረን ☺️
😊 ያ አሏህ መታደል 🥰

ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ሀቢቢ ያ ረሱለሏህ 🤍🤍

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

15 Sep, 09:20


☞ ኢብኑ ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦

አንድ የአላህ ባርያ ሰወች ዘንድ ትልቅ ደረጃ ያለው ሆኖ አላህ ጋር ግን ያነሰ የተዋረደ እንዳይሆን ከአላህ ጥበቃ ሊሻና ሊጠነቀቅ ይገባል።

📚[ ﺟﻼﺀ ﺍﻷﻓﻬﺎﻡ ﺹ٢٦٨ ]

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

13 Sep, 18:24


💜 ስለ እድል ከጠየቁህ
እድል ማለት ከ4300 እምነቶች መካከል
ሙስሊም ሆኖ መወለድ ነው በላቸው::
❤️

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

09 Sep, 19:39


"🤍በዚች ምድር ላይ እንደ ረሱል ﷺ ያፈቀረ እንደሳቸውም የተፈቀረ የለም። ወደፊትም አይኖርም!
          ሰሉ አለ ነቢ አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድﷺ🌹

🌹اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد ﷺ 🌹

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

08 Sep, 18:19


የሰው ልጅን ክፋት ስታይ አሏህ ለምን ጀሐነምን
እንደፈጠረ ትረዳለህ ።

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

06 Sep, 17:37


ስለፍትህ ከጠየቁህ ኡመር ሞቷል በላቸው....

ፍትህ ሚለውን ቃል ካሁን ቡኋላ ባንጠቀመው ባይ ነኝ....

ያላጠባች ጡት ምነኛ አድለኛ ናት ያስብላል....💔
አላህ ነጃ ያውጣን

𝔍𝖊𝖓𝖊𝖙 ᴛ𝔲𝔟𝔢🖤

03 Sep, 18:11


ከአላህ ያልመጣ ቢሄድ ምን ይገርማል

2,013

subscribers

272

photos

79

videos