የአዲስ አበባ ነዋሪውና በግብረሰናይ ድርጅት የንብረት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ መስፍን ይመኑ አሰፋ በቆረጡት የትንሳኤ ሎተሪ በ1ኛው ዕጣ የ10,000,000/ አስር ሚሊየን / ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡ አቶ መስፍን ሎተሪ በመሞከር ለረጅም ዓመታት ያህል በደንበኝነት የዘለቁ ሲሆን “የታገሰ ካሰበው ደረሰ “ እንዲሉ በ2016 ትንሳኤ ሎተሪ ህልማቸውን እውን አድርገዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ የመኖሪያ ቤትና ለሥራ መመላለሻ መኪና እንደሚገዙበት በደስታ ስሜት ውስጥ ሆነው ገልጸውልናል ፡፡