Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ @akakikaltycom Channel on Telegram

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

@akakikaltycom


ይህ የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን የቴሌግራም ገፅ ነው!

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ (Amharic)

አቃቂ ቃሊቲ የአዲስ አበባ ከተማው ኮሙኒኬሽን የቴሌግራም ገፅ ነው። አቃቂ ቃሊቲ ከታላቁ ከተማ Akaki Kality እና ሐረር ከተማ የተለያዩ ሰላምታ እና ትንሽ ገጽና ዜናዎችን እንዲሁም ለፍቅራት ከፈለጉት በበቃ መብራት ድምፅ ይሆናል። ማንኛውም ሰው በአቃቂ ቃሊቲ ይፈልገዋል። ለምሳሌ በአቃቂ ቃሊቲ ካለው በድምብ ሰላም ላይ ለትንሽ ምኞት ይሆንበታል። ሰላምታውን በማመልከት አሰልጣኝ ፣ ማስታወቂያ ወደ ይዘቱ ያድምጡ እና አጥቓላ ጮኼ የሆነውን መረጃ እንማማርት ያድምጡ።

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

21 Nov, 17:52


#የሀሳብ_ልዕልና_ለሁለንተናዊ_ብልፅግና!
የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ አመት ምስረታ በዓል በማስመልከት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አመራሮች ከሸገር ክ/ከተማ ጋር የወዳጅነት ስፖርታዊ ዉድድር

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

21 Nov, 08:14


የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!!!

"ቆሻሻን ማቃጠል ይብቃ፤ ቆሻሻን በማቃጠል አካባቢዬን አልበክልም " በሚል መሪ ቃል ታላቅ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

ህዳር 12/2017 ዓ.ም ( አቃቂ ሊቲ )

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ "ቆሻሻን ማቃጠል ይብቃ " በሚል መሪ ቃል ታላቅ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ልዩ ቦታዉ ማሰልጠኛ አደባባይ አካባቢ አካሂዷል።

በጽዳት ዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ፣ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ፣ የክ/ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ለገሰ ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የተለያዩ ተቋማት ሀላፊዎች ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ የፀጥታ አካላትን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ ከለውጡ በፊት ከተማዋ ደረጃዋን የማይመጥን ሁኔታ ዉስጥ የነበረች ቢሆንም ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ ብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱና በከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ላይ በሰራው የሰዉ ተኮር የልማት ስራዎች ከተማዋ እንደ ስምዋ ውብና ፅዱ የዲፕሎማሲ መናሀሪያ እየሆነች እንደምትገኝ ጠቅሰው ማህበረሰቡ ቆሻሻን በአግባቡ በመሰብሰብና መልሶ በመጠቀም አካባቢን ንፁህ ማድረግ እንደሚገባው ተናግረዋል ።

የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 5 ዓመታት ሀገሪቱ ገብታበት ከነበረችው የችግር አረንቋ ስቦ በማውጣት በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ዘርፎች በርካታ የሚታዩ ስራዎችን በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠና ወደ ብልፅግና ማማ ከፍ እያደረገ እንደሚገኝና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ያሉ ሲሆን በኮሪደር ልማትና ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ከተማዋን ውብ ፣ ፅዱ ፣ለነዋሪዎችዋ ምቹና ተወዳዳሪ ለማድረግ እያከናወነ በሚገኘው የልማት ስራ ማህበረሰቡ በፅዳት ስራ ላይ ንቁ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በአስተዳደሩ ወረዳ 8 የሚገኘዉ በፅዳትና ዉበት በነዋሪዎች ፅዱና ዉብ የሆነች ጃቴ ሞዴል ብሎክ 1 ተጎብኝቷል።

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

12 Nov, 18:40


የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸማችንን ድክመት እና ጥንካሬዎቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው በመለየት ገምግመናል።

የስራ ባህላችን ወጪ ቆጣቢ ፣ጥራትና ባጠረ ጊዜ ውስጥ የሰራናቸው ስራዎች ከተማችንን ለነዋሪው ምቹ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ እና የሀገራችንን ገፅታ ለመገንባት የሰራናቸው የኮሪደር ልማትና ከተማዋን መልሶ የማደስ ስራዎቻችን ዉጤታማ ሆነዉ ከተማችን በሩብ አመቱ ብቻ 20 የተለያዩ አህጉርና አለምአቀፍ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ ችላለች።

በዚህ ሩብ ዓመት በየተቋማቱ አቅደን ከፈፀምነዉ አንፃር 86 እጅ ዉጤታማ አፈፃፀም የታየበት ሲሆን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን የሰራንበት፣ የአመራር ቅንጅት፣ የስራ ባህላችን መለወጥ እና ከተማችንን የሚመጥን የስማርት ከተማ ግንባታ ስራዎቻችን ስኬት ያገኘንባቸው ናቸው::

በኮሪደር ልማት ምክንያት ለኑሮ ከማይመች ጎስቋላ አካባቢ ያነሳናቸው ነዋሪዎቻችንን ለኑሮ ምቹ የሆነ ንጹህ የመኖሪያ ቤት እና አካባቢ እንዲያገኙ ማድረግ የቻልን ሲሆን ከተማ ብቻ ሳይሆን የሰው ህይወት አብሮ የታደሰበት አፈፃፀም መሆኑንም ገምግመናል::

ፈተናዎችን እየተሻገርን ባሳካናቸው ስኬቶች ሳንረካ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ከህዝባችን ፍላጎትና ካስቀምጥነው ስታዳርድ አኳያ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ያልተሻገርናቸው መሆናቸውን
አምነን ለመከላከል የዘረጋነዉ አሰራር እንዲሁም ነዋሪው የሰጠንን ጥቆማና አስተያየትን መሰረት በማድረግ የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት የጀመሩ ሲሆን አሁንም አፅእኖት ሰጥተን ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በዘላቂነት ለማረም የሚያስችል የአመራር ቁመና ለመፍጠር፣ ግልፅነትን እየጨመርን እና ነዋሪውን እያሳተፍን መስራት የሚያስችል አቅጣጫም አስቀምጠናል::

በተጨማሪም በተቋም ግንባታ፣ የሰው ተኮር ስራዎችን ማጠናከር፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ፣ ገቢ አሰባሰብ ማሻሻል፣ የንግድ ስርአቱን ማጠናከር፣ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ከተማ መገንባት እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በመጨረስ ወደ አገልግሎት ማስገባት እና የ2ተኛ ዙር ኮሪደር ስራን በጥራት እና በፍጥነት ማጠናቀቅ በቀጣይ በልዩ በትኩረት የምንሰራቸው ስራዎች ናቸው::

አገልግሎት አሰጣጣችንን ይበልጥ ቀልጣፋና ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ በማድረግ በትጋትና በታማኝነት በማሳተፍ መስራታችንን አሁንም አጠናክረን እንቀጥላለን::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

11 Nov, 19:25


በዛሬው 4ተኛ አመት 3ተኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባች ሁለተኛ ኮሪደር ስራ ያለበትን በጥልቀት ገምግሟል ።

በግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደረግነው የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ  የ3 አመት የቤት ኪራይ  እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን ፤የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ ተገምግሟል።

በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ ፣ ንፁህ ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል  ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።

ሌሎች ሳይት ላይ አስፈልጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ፤የማህበራዊ  ኑሯቸው ሳይበታተን እድር ፤ ማህበር እና አብሮነታቸው የመሰረቱት ማህበራዊ መስተጋብር እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ን አቃቂ ፤ገላን ጉራ ፤ፉሪ ሃና ፤አራብሳ አምስት እና ስድስት አያት ሶስት፤ ላፍቶ ሃይሌ ጋርመንት እና ለሚኩራ አጠገብ የተሰሩት ሎኮስት ፤አየርጤና ቂርቆስ ለገሃር አካባቢ ፤አራዳ ሰባ ደረጃ አካባቢ በማሃል ከተማ የተገነቡ ቤቶች ላይም የተስተናገዳቸውን እና አፈፃፀሙም ጥሩ  መሆኑን ካቢኔው ገምግሟል።
የመሠረተ ልማት ቅንጅት አካላት ከከተማ እስከ ፌደራል ተቋማት የነበራቸው ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ካቢኔው  በጥንካሬ ገምግሟል ።
በተጨማሪም መሬት እና ካሳ ምትክ እስካሁን ድረስ ብቻ ከ4.6ቢሊየን በላይ መከፈሉን  የሁለት አመት የቤት ኪራይ መከፈሉን እና ቀሪ ተነዴዎችም ቅድመ ዝግጅት ሂደት ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ። በሌላ በኩል በኰሙኒኬሽን ሥራዎችን በደንብ ደጋግሞ ለሕዝብ መረጃን ማድረስ ላይ ከዚህ በላይ ማድረስ እና ተደጋጋሚ የሚዲያ ሽፋን ያላቸው የመረጃ ስርጭት ለህብረተሰቡ መድረስ እንዳለበት ካቢኔው አሳስቧል።  መረጃን  የሚያዛቡ እና ሀገር እንዳትለማ ውዝንብር በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝንባሌዎች የሚያሳዩ የመረጃ ምንጮችን እና አካላት ላይ ህጋዊ ርምጃ በመወሰድ እንዳለበት በአፅንኦት ኣንስተዋል ::
በ2ኛው ዙር ኮሪደር ልማት ስራ 2879 ሄክታር ስፋት ፤ 135ኪሎ ሜትር የኮሪደር ርዝመት ያለው ሲሆን ፤ 240ኪሎ ሜ የአስፋልት መንገድ፣ 237 የእግረኛ መንገድ ፣ 32 የህፃናት መጫዎች ቦታዎች ፣ 79 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ 114የታክሲ እና አውቶቡስ መጫኛ እና ማውረጃ ፣ 58 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች፣ 368 ሄክታር አረንጋዴ ልማት ሽፋን ያላቸው ቦታዎች፣ የ 111 ኪ.ሜ ሳይክል መንገድ ፣ 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ 106 የህዝብ መረዳጃ ቤቶች፣ 121 ኪ.ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ፣ 182 ኪ.ሜ ድሬኔጅ መውረጃ መስመር ፣ 50  የተሸርካሪና እግረኛ መተላለፊያ ፣ 75 ኪ .ሜ ሪቴይኒንግ (የድጋፍ ግንብ) ስራዎችን የሚያካትት ነው ::
ይህንኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክትትል ማሳደግ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የተተገበሩ የ አንደኛ ዙር ኮርድር ልማት ልምዶች ተቀምረው ለ2ተኛው ዙር በተሻለ ብቃት መስራት እንደሚያስፈልግ ፤ ቅንጅታዊ አሰራርም በተጠናከረ መልኩት አሳድጎ በጥንካሬ አሁን ካለው በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካቢኔው አሳስቧል።

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

11 Nov, 19:24


የመተባበርና የመደጋገፍ ዕሴታችን  ለዘላቂ አንድነትና ብልፅግና ጉልህ ሚና አለዉ!!!

አቶ አለማየሁ ሚጀና የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ

በአቃቂ  ቃሊቲ ክ/ከተማ የኮሪደር ልማትን በመደገፍ ወደ ክ/ከተማው ለመጡ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መርሃግብር ተከናወነ።

በመርሃግብሩ የከንቲባ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ፣ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ የክ/ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዮሐንስ የወረዳ 13 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደስታ እና የካቢኔ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የክ/ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ባደረጉት ንግግር እኛ ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ መደጋገፍ መተባበር በዓለም የምንታወቅበት ዕሴት እንደሆነ አስታውሰው ዛሬም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ እየተሰራ ያለዉን የኮሪደር ልማት በመደገፍ ቀድሞ ከሚኖሩበት አካባቢ ወደ ክፍለ ከተማዉ ለመጡ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መደረጉ አብሮነትን ለማጠናከር መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም በዘላቂነት ተጠናክሮ የሚቀጥልና አስተዳደሩ ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች ሲኖሩ ከነዋሪዎቹ ጎን መሆኑን ጠቅሰዋል።

የከንቲባ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ እንደገለፁት "ከተማችን እንድታብብ የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫነቷን እንዲሁም ውብና አረንጓዴ ሆና እንድተሰራ ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ጠቅሰዉ በከተማ አስተዳደሩ ስም በማመስገን፤ ኢትዮጵያውያን ስንደጋገፍ ስንተባበር የተሻለ ሀገር መገንባት እንደምንችል ማሳያ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ሰዉ ተኮር በመሆኑ ልማቱን ደግፈዉ ለተነሱ ነዋሪዎች መኖርያና አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን በሙሉ አሟልቶ ሰጥቷል፤ ለዚህም እናንተ ማሳያ ናችሁ።" ብለዋል።

አክለዉም አስተዳደሩ ዘላቂ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቀጥል ጠቅሰዉ የዛሬዉ   የማዕድ ማጋራት አንዱ መርሃግብርም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው የልማት ተነሺ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ ዛሬም ሆነ ከዚህ ቀደም እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ አመስግነው፤ በተለይም ምንም አይነት የአካባቢ እንግድነት ስሜት እንዳይሰማቸው እየተደረገላቸው ላለው እገዛከተማ እና ክ/ከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል።

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

11 Nov, 19:24


ገበያ ማዕከሉ የዋጋ ንረት ከማረጋጋት ባሻገር የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት እንዳስቻላቸው ተጠቃሚዎች ገለፁ።

ህዳር 02/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ )

የዋጋ ንረትና የምርት አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የተቋቋመው የተለያዩ የምርት አይቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ ለህብረተሰቡ እየሰጠ ይገኛል።

የክ/ከተማው ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 8 የሚገኘውን የሰብልና ጥራጥሬ፣ የአትክልት ፣ ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል በመገኘት በማዕከሉ እየተሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ተመልክቷል።

በምልከታው በገበያ ማዕከሉ የወፍጮ አገልግሎት ስትገለገል ያገኘናት ወ/ሮ ሳምራዊት አባተ እንደምትለው ማዕከሉ የአትክልት ፣ ፍራፍሬ ፣ የሰብልና ጥራጥሬ ምርቶችን በስፋትና በጥራት ከማቅረብ በተጨማሪ የወፍጮ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ሸማቹ በአንድ ቦታ ሁሉንም አገልግሎት ማግኘት መቻሉንና በተጨማሪም እንግልትን የቀነሰ መሆኑን ተናግረዋል።

የገበያ ማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ጫኔ ሸማቹን ከአምራች በቀጥታ በማገናኘት የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ታልሞ የተመሰረተ መሆኑን በመግለፅ በዚህም የተለያዩ የምርት አይነቶችን ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በማስመጣት ከመደበኛው ገበያ ዝቅ ባለ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለማህበረሰቡ እያቀረበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለት ባደረግነው ቅኝት በገበያ ማዕከሉ በኩንታል ነጭ ጤፍ 14,000 ብር፣ ስንዴ 8,000 ብር ፣ በቆሎ 4,100 ብር ፣ አተር ክክ 14,100 ብር ፣ 1 ኪሎ ሽንኩርት 50 ብር ፣ 1 ኪሎ ሙዝ 40 ብር እየተሸጠ ይገኛል።

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

11 Nov, 19:23


በአዲስ አበባ ከተማ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል፡፡

ውዥንብሩ ከየት መጣ የሚለው ሲጣራ በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ ሲሆን በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል::

ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የሚያስቡ አካላት በሚነዟቸው ውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል፡፡

በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ ያለ ስራ ሲሆን ለዚህም የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ ሊሆን ይገባል::

አንዳንድ ያለደረሰኝ በመገበያየት ሕዝብና መንግሥት ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እያሳጡ የራሳቸውን ኪስ የሚሞሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን ይጠበቅባቸዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡ ብልሹ አሠራርን ጨምሮ ደረሰኝ የማቆርጡ እና ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙ አካላትን በ7075 ላይ እንዲጠቁሙ ጥሪውን ያቀርባል::

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

09 Nov, 13:45


#የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ_ለሁለንተናዊ_ብልፅግና"

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

09 Nov, 06:28


ፕረስ ሪሊዝ

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት "የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል እሁድ ህዳር 1/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ልዩ ቦታዉ ቃሊቲ ገብርኤል ፊት ለፊት 40/60 ኮንደሚኒየም ታላቅ የማስ ስፖርት አዘጋጅቷል።

በመሆኑም ከህፃን እስከ አዋቂ ሁሉም የክ/ከተማዉ ነዋሪ እንዲሳተፍ ጽ/ቤቱ ጋብዟል። እንዳያመልጥዎ !!

ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

08 Nov, 13:02


በክ/ከተማው የሚገኙ የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ወደ ህጋዊ ስርዓት በማስገባት ለህብረተሰቡ አገልገሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተገለፀ።

ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም ( አቃቂ ቃሊቲ )

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት በክ/ከተማው የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ባለ ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ እና የህዝብ አስተያየት ቅኝት አድርጓል።

በምልከታው የትራንስፖርት አገልግሎቱ በውስጠ ለውስጥ መንገዶች እየተሰጠ ያለ ቢሆንም በሁሉም አካባቢዎች እየተተገበረ እንዳልሆነ መመልከት የተቻለ ሲሆን አገልግሎቱ በተሟላ መልኩ በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

በአዲ/አ/ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ የአ/ቃ/ክ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ዘውዴ ከዚህ ቀደም የከተማ አስተዳደሩ በከተማው የሚገኙ ባለ ሶስት እግር የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ወደ ህጋዊ ስርዓት ለማስገባት በተደረገ ጥረት አሁን ላይ ወደ አገልግሎት መግባታቸውን ገልፀው በክ/ከተማው አስፈላጊ መስፈርቶችን ያሟሉ 461 ባጃጆች በ8 ማህበራት በተመረጡ 25 መስመሮች በማሰማራት ለነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በክ/ከተማው ወደ ስራ ከገቡት ባጃጆች በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ባጃጆች አስፈላጊውን መስፈርቶች አሟልተው ወደ ስራ ለመግባት በሂደት ላይ እንደሚገኙ በማንሳት ሁሉም የባጃጅ ትራንስፓርቶች በሙሉ ዓቅም ወደ ስራ ሲገቡ ማህበረሰቡ ከትራንስፖርት አቅርቦት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸውን ችግሮች የሚቀርፍ መሆኑን ገልፀዋል ።

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

31 Oct, 08:00


የወጪ ንግድን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ባላፉት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡በዚህ አፈጻጸም ከቀጠልን በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል፡፡ ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ1 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ አለው፡፡ በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡ ይህም የወርቅ ምርት ምን ያህል ለህገ ወጥ ንግድ ተጋልጦ እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ በቡና ምርትም በበጀት ዓመቱ 2 በሊሊዮን ዶላር ገቢ ይጠበቃል፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

31 Oct, 07:59


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ

የኢኮኖሚ ስርዓታችን እጅግ የተዘጋ ነበር፡፡ ይህም በወጪ ንግድ፡ በተኪ ምርቶች፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመት ላይ ኢትዮጵያ መጠቀም ያለባትን ያህል እንዳትጠቀም አድርጓት ቆይቷል፡፡ ከዚህ አኳያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን መሰረት የሚጥል ነው፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

31 Oct, 07:59


የመንግስት ገቢን በተመለከተ

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመንግስት ገቢ በእጅጉን ጨምሯል፡፡ ባላፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የተሻለ እድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ 109 ቢሊዮን ብር ብቻ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት አንጻር አሁንም ዝቅተኛ ገቢ የምትሰበስብ ሀገር ናት፡፡ ይህ በቀጣይ መሻሻል አለበት፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

31 Oct, 07:59


የኢትዮጵያ አየር መንገድን በተመለከተ

በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ ይህ አዲስ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያም በዓመት ከ100 አስከ 130 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተነናግዳል፡፡ አሁን ላይ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለማግዛት አዘናል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡ ይህ ለውጥ በተለይ በአገልግሎት ዘርፍ ለማስመዝገብ የተያዘውን ውስጥ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም የአገልግሎት ዘርፉ 7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

31 Oct, 07:50


ሌማት ትሩፋት

የሌማት ትሩፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ እድገት የተመዘገበበት ዘርፍ ሆኗል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት የሚያስመዘግቡ ሲሆን፡፡ ለአብነትም በወተት ብቻ በዓመቱ 12 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ይጠበቃል፡፡ በዓመቱ 8 ቢሊዮን የዶሮ እንቁላል እንዲሁም 218 ሺህ ቶን ስጋ እና 297 ሺህ ቶን ማር ምርት ለማምረት የሚያስችል አቅም ተፈጥሯል፡፡

#የጠሚሩምላሾች
#PMOEthiopia