ሰላም ዶክተር ልጄ እድሜው 3 አመቱ ነው። ሆዱ በቀኝ ጎን ያበጠ ነገር አለው። ሆስፒታል ሳሳየው የኩላሊት እጢ ነው አሉኝ። በጣም ስለጨነቀኝ በህፃናት ላይ ይከሰታል ወይ? ህክምናውስ?( የወላጅ ጥያቄ)
🩺 ውድ ጠያቂያችን እንደርሶ አገላለፅ አብዛኛውን ጊዜ በልጆች ላይ የሚከሰተው የኩላሊት እጢ ወይም ካንሰር ሲሆን በሕክምና አጠራሩ ዊልምስ እጢ(Wilms Tumor) ይባላል።
🩺ይህም እጢ በልጆች ከሚከሰቱቱ የኩላሊት እጢዎች ቁጥር አንድ ሲሆን በአጠቃላይ በህፃናት ከሚከሰቱት የሆድ ውስጥ እጢዎች በሁለተኛ ደረጃ ይገኛል።
✍ ጥያቄ 1: ዊልምስ ዕጢ ምንድን ነው?👉የኩላሊት እጢ (Wilms tumor ወይም nephroblastoma) ተብሎ የሚጠራው ከኩላሊት ህዋሳት የሚነሳ አደገኛ (ካንሰር) ዕጢ ነው።
👉በልጆች ላይ በጣም የተለመደው የኩላሊት ካንሰር ሲሆን ከጠቅላላው የልጅነት የካንሰር በሽታዎች 6 በመቶውን ይይዛል።
👉 እንደማንኛውም ካንሰር የመዳን እና የረዥም ጊዜ ህልውና ከልጅ ወደ ልጅ በእጅጉ ሊለያይ ቢችልም
👉ነገር ግን አብዛኛው የዊልምስ እጢ ያለባቸው ህጻናት በትክክል ከታከሙ ከበሽታው ሙሉ በሙሉ የመዳን እድል አላቸው።
👉ይህ ዕጢ ከአዋቂዎች የኩላሊት ካንሰር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
👉 እብጠቱ ብዙውን ጊዜ አንድ ኩላሊትን ያጠቃል፣
👉ነገር ግን በግምት ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ይህ እጢ ካለባቸው ልጆች ሁለቱ ኩላሊቶች ላይ የመከሰት እድል አለው።
✍ጥያቄ 2: ይህ እጢ የሚያጠቃው እነማንን ነው?👉የዊልምስ እጢ እስከ 8 ዓመት አካባቢ ባሉ ህጻናት ላይ የመከሰት እድል አለው።
👉75 በመቶ የሚሆኑት ከ5 አመት በፊት ይከሰታል ።
👉በአጠቃላይ በዊልምስ እጢ የተያዙ ህጻናት አማካይ እድሜ ከ2 እስከ 3 አመት የእድሜ ክልል ነው።
👉 ባልታወቁ ምክንያቶች ይህ እጢ ከፈረንጅ ልጆች ይልቅ ብዙ ጥቁር ዝርያ ያለባቸውን ልጆችን ያጠቃል።
👉በአጠቃላይ አማካይ ዕድሜ አንድ ኩላሊት ወይም ሁለቱም ኩላሊቶች ላይ በመከሰቱ ሊለያይ ይችላል።
🌡🌡አንድ ኩላሊት ከተጎዳ (unilateral) ከሆነ አብዛኛውን ጊዜ ከ3 አመት አካባቢ ሲሆን
🌡🌡ሁለቱም ኩላሊቶች ከተጎዱ (bilateral) አብዛኛውን ጊዜ ከ30-33 ወራት ውስጥ ይገኛል።
👉አብዛኛውን ጊዜ ይህ እጢ በአጋጣሚ (Sporadic) ይከሰታሉ።
👉ብዙውን ጊዜ ከተወለዱ በኋላ በኩላሊት ውስጥ በሴሎች ውስጥ የሚውቴሽን ውጤቶች ናቸው።
👉በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን የጄኔቲክ ጉድለት የዊልምስ እጢ አደጋን ይጨምራል።
✍ጥያቄ 3: ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?👉አብዛኛውን ጊዜ ምልክት አይኖረውም።
👉ወላጆች ልጆቻቸውን በሚያጥቡበት ጊዜ ድንገት ሆድ ውስጥ እብጠት ሊያስተውሉ ይችላሉ።
👉ለማንኛውም ዊልምስ እጢ በሚከተሉት ምልክቶች ይታወቃል:
👉👉የሆድ እብጠት ብዙውን ጊዜ ወደ አንድ ጎን በኩል
👉👉 የሆድ ህመም
👉👉አልፎ አልፎ ትኩሳት
👉👉ሆድ ድርቀት
👉👉ከፍተኛ የደም ግፊት (High blood pressure)
👉👉በሽንት ውስጥ ደም መቀላቀል (hematuria)
👉👉ድካም
👉👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉👉 ክብደት መቀነስ
👉👉በተደጋጋሚ የሽንት ኢንፌክሽን
✍ጥያቄ 4: የዊልምስ ዕጢ ምርመራ ምን ይመስላል?👉የተሟላ የህክምና መረጃ ከተወሰደ እና የልጅዎን አካላዊ ምርመራ ከተደረገ በኋላ፣
👉ካንሰሩ ባህሪውን፣ መጠኑን እና መስፋፋቱን እና አለመስፋፋቱን (metastasized) ለማወቅ የሚከተሉትን ምርመራዎች ሊታዘዙ ይችላሉ።
🩺 1) የሆድ አልትራሳውንድ(Abdominal ultrasound)
🩺 2) የሆድ ሲቲ ስካን(Abdominal CT scan)
🩺 3) የደረት ራጅ(Chest x ray) ወይም የደረት ሲቲ ስካን(Chest CT scan) እና ሌሎች ምራመራዎች ሊታዘዙ ይችላሉ።
✍ ጥያቄ 5: ሕክምናው ምን ይመስላል?👉የተለያዩ የህክምና አማራጮች ሲኖሩት እንደ እጢ ደረጃ እና መጠን ይለያያል!
1) በመድኃኒት(chemotherapy)
2) ቀዶ ጥገና (Surgery)
3) ጨረር( Radiotherapy)
✍ጥያቄ 6: ታክሞ የመዳን እድሉ ምን ያህል ነው?👉የዊልምስ እጢ አጠቃላይ የፈውስ መጠን(ሙሉ በሙሉ የመዳን እድሉ) ከፍተኛ ሲሆን ይህም ከመቶ 85% ነው።
👉እንደማንኛውም ካንሰር ግን ትንበያ እና የረጅም ጊዜ የመኖር እድሉ ከልጅ ልጅ በእጅጉ ሊለያይ ይችላል።
👉አፋጣኝ የሕክምና ክትትል ካገኘ የመዳን እድሉ ከፍተኛ ነው።
👉ቀጣይነት ያለው ክትትል እና የሚደረግለት እንክብካቤ በጣም አስፈላጊ ነው ።
👉ምክንያቱም የጨረር እና የኬሞቴራፒ ህክምናዎች እንዳስፈላጊነቱ ወሳኝ ነገር ስለሆኑ ነው።
✍ጥያቄ 7: ምን አይነት ቀዶ ሕክምና ነው የሚደረግላቸው?👉የተጎዳው ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ወይም አንዳንድ ጊዜ በከፊል በቀዶ ጥገና ሊወገድ ይችላል።
👉ኩላሊቱ በሙሉ ሲወገድ ይህም Radical Nephrectomy ይባላል።
👉በአንዳንድ ሁኔታዎች በከፊል የኩላሊት ቀዶ ጥገና Partial Nephrectomy በመባልም ይታወቃል።
👉 ይህም ማለት እጢው ያለበት የኩላሊት ክፍል ብቻ ይወገዳል።
👉አብዛውኛውን ጊዜ የተለመደው ቀዶ ጥገና ኩላሊቱን ከእጢው ጋር ሙሉ በሙሉ የማውጣት ቀዶ ጥገና ነው።
👉ቀዶ ህክምናው ልምድ ባላቸው እና በዚህ ዘርፍ ስፔሻላይዝድ ባደረጉ የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች ቢሆን ይመረጣል።
👉ከቀዶ ጥገና በኋላ የተለመደው ማገገም በሆስፒታል ውስጥ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት የሚቆይ ቆይታን ያጠቃልላል።
👉 ከቀዶ ጥገና በኋላ የህመም ማስታገሻ በመውሰድ ቀደም ብለው የእግር ጉዞን እናበረታታለን እና
👉ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዎች ይመለሳል ብለን እንጠብቃለን።
👉እንደ እጢው ደረጃ እና ተስፋፊነት መሠረት ቀጣይ ለሚሰጡ ህክምናዎች ክትትል ያስፈልጋል።
ለምሳሌ : ከቀዶ ጥገና በኋላ ኬሞቴራፒ ወይም ጨረር ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ለመወሰን ከህክምና ቡድኑ ጋር ክትትል ያስፈልጋል።
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን።
አዘጋጅ: ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:
የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር
Dr. Saleamlak Tigabie:
MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at DCSH) , Assist. Proff. @WU, Dessie, Ethiopia
🩺አድራሻ:
🌡ባቲ ጠቅላላ ሆስፒታል (ደሴ ዳውዶ ፔፕሲ አጠገብ)👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት :
📱0911441651
👉Gmail:
[email protected]Telegram:
👉(https://t.me/DrSaleamlakT)
👉https://t.me/DrSaleamlakPediSurgeon (በግል ለማናገር እና ምስሎችን ለመላክ)
TikTok(https://www.tiktok.com/@drsaleamlakpedisurgeon?_t=8p5K11aLB4f&_r=1)
YouTube(https://www.Youtube.com/@Doctortube69)
Facebook(https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/)