ፋብሪካዉ ታሪክ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የተመረተው አንዴ ብቻ ሲሆን በወቅቱም የአገዳ መትከያ መሬት ስፋት 12 ሺህ ሄክታር ነበር፤ አሁን አንድ ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት ያለው የመሬት ስፋት ዘጠኝ ሺህ ሄክታር መሆኑ ተጠቁሟል ።
ኢፕድ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አማን ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው በ2016 ዓም 300 ሺ ኩንታል ስኳር አምርቷል፤ በተያዘው የበጀት ዓመት አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ለማምረት ዝግጅት ተደርጓል።
አሁን ላይ አመራሩ ሰባቱንም ቀን ተከፋፍሎ፣ አገዳ አስገብቶ ስኳር አውጥቶ ነው የሚውለው፤ በእኔ ቀን ፋብሪካው የተሻለ ማምረት አለበት ብሎ እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን እስካሁን በቀን ሰባት ሺ ኩንታል ስኳር ይመረታልም መባሉን ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል።