Mega Projects Construction Office @megaprojectsconstructionoffice Channel on Telegram

Mega Projects Construction Office

@megaprojectsconstructionoffice


ይህ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ መረጃ እና መልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

Mega Projects Construction Office (Amharic)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ መረጃ እና መልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። የተለያዩት ስልጠናዎችን በሚከተለው ማበርካት ውስጥ በየቤታችን እንገልፃለን። የህዝብ እቃዎችን እና ኢንተርናሽናል አባላትን እና ልማት ዘርፉን በሚፈጠሩ ንብረቶች በአድራሻችን ለማዘጋጀት ይገኛሉ። እናቶችን እና ዕርዳታዊ ምክርን እና በብሄራዊ ክፍል ለመመገብ ይከታተሉን። በእውነት አስተዳደሩ በተጠቀሰው ጊዜ በአርበኞች መካከል ሊተባብሩላት ነው ብለን ማለት ነው።

Mega Projects Construction Office

15 Nov, 06:28


ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡን እና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፦ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ህዳር 6 ቀን 2017 ዓም አዲስ አበባ
ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡን እና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካዛንቺስ አካባቢ ካሉ ባለሀብቶች ጋር አካባቢውን በትብብር መልሶ ማልማት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::
በውይይቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ እንደ መጀመሪያው ሁሉ የሁለተኛውንም የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡን እና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል::
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የካዛንቺስ አካባቢ ባለሀብቶች በበኩላቸው በኮሪደር ልማት እና በመልሶ ማልማት ስራው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን የከተማው ጽዳትና ውበት ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ በመሆኑ በሚችሉት ሁሉ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም አካባቢውን እንደሚያለሙ ቃል በመግባት እንዲሁም ያላቸውን የልማት ጥያቄዎች በማቅረብ ለመልሶ ማልማት ስራው በቀረበላቸው ጥሪ ደስተኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Mega Projects Construction Office

13 Nov, 11:02


ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል።
ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል።
አሁን በሶስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል። በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው።
. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Mega Projects Construction Office

13 Nov, 09:44


ፕሮጀክት ፅ/ቤቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት እንዲመሩ የተመደቡት የስራ ሃላፊ ከሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ።
ህዳር 4 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የተመደቡት ዋና ስራ አስኪያጅ ዘለቀ ዋኬኔ (ኢ/ር) ከፕሮጀክት ፅ/ቤቱ መካከለኛ አመራሮችና አጠቀላይ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን፣ ፕሮጀክት ፅ/ቤቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ጉልህ አበርክቶ ያደረገ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፤ በሥራ የተገኙትን ውጤቶች ይበልጥ በማጠናከር ሁሉም ሰራተኛ የተጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የግንባታ ጊዜ እና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።
አያይዘውም የተጀመረውን ከተማ አቀፍ የልማት ጉዞ ይበልጥ ለማፋጠን እና ውጤታማ ለማድረግ፤በየደረጃው ያለው አመራርና ሰራተኛ ከምን ጊዜውም በበለጠ ተግቶ በመስራት ተገቢውን ውጤት ማምጣት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስቀምጠዋል።
በመድረኩም የተለያዩ አመራሮች ዳይረክተሮች እና ሰራተኞች የእንኳን ደህና መጣህ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ በተቋሙ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በስኬት እንደሚወጡ ተናግረዋል።

Mega Projects Construction Office

12 Nov, 08:04


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማከናወን ጀመረ።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብረት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በግምገማችን እቅዳችንን የከወንበትን መንገድ በመገምገም ጥንካሬዎቻችንን እያስቀጠልን በድክመት የተለዩ ስራዎችን ደግሞ በትኩረት መገምገም ተገቢ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ያሳሰቡ ሲሆን በስራዎቻችን ላይ የሚታዩ ድክመቶችን ሳንሸፋፍን መገምገማችን አንዱ የጥንካሬያችን ምንጭ በመሆኑ ብልሹ አሰራር፣ ሌብነት፣ ጉቦኝነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት በመቅረፍ ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር እንዴት አቅደን ሰራን ሰራየን እንዲሁም ሀላፊነቴን እንዴት ተወጣሁ ብሎ መገምገም ይገባል ብለዋል::

Mega Projects Construction Office

01 Nov, 05:47


የሚዲያ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች የአዲስ አበባን የኮሪደር ልማት ሥራዎች ጎበኙ
የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አመራሮች እና ሠራተኞች በአዲስ አበባ የተከናወኑ እና በሒደት ላይ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።
አመራሮቹ እና ሠራተኞቹ በአራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች በመጀመሪያው ምዕራፍ የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እና በሁለተኛው ምዕራፍ በመሠራት ላይ ያሉትን እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ ልማቶችን ተመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናት ዓለም መለስ የተሠሩትን ሥራዎች እና አጠቃላይ ሒደቱን በተመለከተ ማብራሪያ እና ገለጻ አድርገዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራዎቹ ጥራታቸውን የጠበቁ እና ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግሉ በከፍተኛ ጥናት የተሠሩ እና በመሠራት እንዳሉ ወ/ሮ እናት ዓለም በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።
በተለይ የፍሳሽ አወጋገድ እና የመንገድ ደኅንነት ትኩረት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን እና በአብዛኛው አካባቢዎች ነባር ሕንፃዎች ባሉበት ሆነው የኮሪደር ሥራው እንዲሳለጥ መደረጉን አብራርተዋል።
በዚህም ሰፊ የትራፊክ እንቅስቃሴ ባለባቸው አካባቢዎች ምቹ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ የሚዲያ አመራሮቹ እና ሠራተኞቹ በበኩላቸው፣ በተመለከቱት ነገር በእጅጉ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ፣ “እንደዚህ የዘመነ አኗኗር ለኛ ይገባናል” የሚል አስተሳሰብን ያሰረፀ ሥራ መሠራቱን ተናግረዋል።
ከመንገድ ግንባታው ባሻገር የወንዝ ዳር ልማት መከናወኑ፣ ውብ ግንባታዎች እና አገልግሎት መስጫዎች መካተታቸው ሥራውን ሙሉ እንደሚያደርጉም ጠቅሰዋል።

Mega Projects Construction Office

31 Oct, 07:56


የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የራስ መኮንን ድልድይ ማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት አሁናዊ ገጽታ

Mega Projects Construction Office

30 Oct, 18:17


"በቦሌ መገናኛ ኮሪደር ልማት ወደፊትን ታሳቢ ያደረጉ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ ውለዋል" አቶ ጥራቱ በየነ
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ

በቦሌ መገናኛ ኮሪደር ልማት ወደፊትን ታሳቢ ያደረጉ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እንደዋሉ በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

በቦሌ መገናኛ ኮሪደር የመንገድ ላይ መብራቶች፣ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፣ የደህንነት ካሜራ እና ዘመናዊ መብራቶች ጥቅም ላይ መዋላቸውን የጠቀሱት አቶ ጥራቱ፤ በተጨማሪም ከአንድ ማዕከል መቆጣጠር የሚያስችሉ መሳሪያዎች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች እንዳሉት ገልፀዋል።

በቦሌ መገናኛ ኮሪደር ልማት ከመጀመሩ በፊት ጨለማ፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ የብስክሌትና የእግረኛ መንገድ አለመኖሩን አንስተው፤ ከዚህም በላይ ዝቅተኛ የንግድ እንቅስቃሴ እንደነበር ተናግረዋል።

አሁን ላይ የመንገድ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል ያሉት ኃላፊው፤ የኮሪደር ልማቱ 4 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን አንስተዋል።

ይህም 10 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማሳለፍ የሚችል በመሆኑ የከተማዋ ትልቁ የመንገድ ስፋት ያለው እንደሆነ ገልፀዋል።

መሥመሩ በቦሌ በኩል የሚገቡ ዓለም አቀፍ የእንግዶች መቀበያ መንገድ በመሆኑ ጭምር ደረጃውን ጠብቆ መሠራቱን አብራርተዋል።

የአስፋልቱ ስፋት 68 ሜትር መሆኑን በመግለጽ ለትራፊክ ክፍት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በዚህ የኮሪደር ልማት መገናኛ የሚገኘው የውስጥ ለውስጥ የእግረኛ መንገድ በ45 ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል ብለዋል። አሁን ላይ ስራው ከተጀመረ ሶስተኛ ቀኑን መያዙንም አያይዘው ገልፀዋል።

በዚህም ካፌ፣ ሱቆች፣ መፀዳጃ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ማድረጊያና ሌሎች ተጨማሪ የማኅበረሰብ አቀፍ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የመሠረተ-ልማቶች እንደሚኖሩ ተናግረዋል።
ምንጭ:- ኢ ፕ ድ

Mega Projects Construction Office

30 Oct, 07:01


የቦሌ -መገናኛ ኮሪደር ልማት፤ የምሽት ገጽታ በጥቂቱ
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ

Mega Projects Construction Office

26 Oct, 09:05


ቴውድሮስ አደባባይ የመኪና ማቆሚያ ( Car parking )ግንባታ ፕሮጀክት አፈፃፀም 52 ከመቶ በላይ ደረሰ
ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚያሰራቸው በርካታ የኮሪደር ልማት ሥራዎች መካከል የመኪና ፓርኪንግ ግንባታዎች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ተርሚናሎች ግንባታ ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ ልዩ ቦታው ችርችል ጎዳና አከባቢ የሚሰራው የመኪና ማቆሚያ ግንባታ ፕሮጀክት በ 6641.61 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው እየተካሄደ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የቴውድሮስ አደባባይ ፓርኪንግ ግንባታ ፕሮጀክት አስተባባሪ ማዲያ ባዲ እንደገለፁት የመኪና ማቆሚያ(car parking) የግንባታ ፕሮጀክቱ 570 ተሸከሪካዎችን በአንድ ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ እየተሰራ ሲሆን፤ መመገቢያ እና ካፌ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች እንዲሰጥ ተደርጎ እየታነፀ የሚገኝ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።

አስተባባሪዋ አክለውም በአማካሪነት የኢትዮጲያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንዲሁም በግንባታ ስራው ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን እና ትሬዲንግ እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን፣ የግንባታ ሥራው ፊዚካል አፈፃፀም ከ52 ከመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፤ የግንባታው ሙሉ ወጪ በመንግስት የሚሸፈን ፕሮጀክት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አሁን ላይ በግንባታ ሥራው ላይ ከአንድ መቶ ሰማንያ(180) በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ የእድል የፈጠረ ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጽዋል፡፡

Mega Projects Construction Office

25 Oct, 12:11


#የስራ_ቅጥር_ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ከ60 በላይ ክፍት የስራ መደቦችን የዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2017ዓ.ም እትም በሆነው አዲስ ዘመንጋዜጣ ላይ ስላወጣ፤ይሞክሩ ! ይወዳደሩ! ለሌሎችም መረጃውን ያጋሩ!

ባሉበት ሆነው መረጃዎቻችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100064879894640
Telegram:- https://t.me/MegaProjectsConstructionOffice
Twitter: - @megaprojectsco1
website:- https://www.megaprojectsconstructionoffice.gov.et/ [email protected]

Mega Projects Construction Office

19 Oct, 11:20


#ኮሪደር_ልማት_የሠሩ_እጆች_ድምር_ውጤት
ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ ም አዲስ አበባ

Mega Projects Construction Office

18 Oct, 03:48


አብርሆት ቤተመፃህፍት

አብርሆት የትውልዶችን ልቦና በእውቀት ለማብራት የተቋቋመ ነው። በሕንፃው ምሰሶዎች ጥበብ የሚለው ቃል በ18 የራሳቸው ፊደል ባላቸው ቋንቋዎች ተፅፎ የሚገኘውም ለዚህ ተልዕኮ ያለውን ቁርጠኝነት ለማመላከት ነው።

አብርሆት ቤተመፃህፍት በብልሃት ክህሎት የተጎናፀፉ ወጣቶችን የማብቃት አላማውን በትጋት በመወጣት ላይ ይገኛል። ዛሬ በአብርሆት ያገኘኋቸው ወጣቶች እንደ ሮቦቲክስ እና የፈጠራ ትግበራ ሥራዎች ላይ ተጠምደው ስላገኘኋቸው አድናቆት እና ማበረታቻ ይገባቸዋል።

መጪው ትውልድ ከኢትዮጰያ የልማት ግቦች ጋር በተናበበ ሁኔታ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮዲንግ፣ በሳይበር ሴኩሪቲ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ክህሎታቸውን ማጠናከር መቀጠል ይኖርባቸዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Mega Projects Construction Office

17 Oct, 06:58


የተቋም አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስርዓት ላይ ሰልጠና እየተሰጠ ነው
ጥቅምት 7 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ለመካከለኛ አመራሮቹ እና አጠቃላይ ሰራተኞቹ የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ በመንግስት አገልግሎት ስኬታማነት ማስፈፀሚያ ማኑዋል ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የለውጥ ሥራዎች ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሀይለሚካኤል ሸዋዬ ሰልጠናውን አስመልክተው እንደገለፁት አጠቃላይ የተቋሙን የለውጥ ሥራ በየደረጃው ያለው አመራርና ሰራተኛ እኩል ግንዛቤ ኖሮት ቀጣይ በሚደረገው የስራ እንቅስቃሴ ከሌሎች ጋር አቻ ሆኖ ለመስራትና ተገቢውን የሥራ ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ የሚሰጠው ስልጠና በተቋሙ ያለው የሰው ሃይል፣ ማን በአግባቡ እየሰራ መሆኑን፤ ምን ውጤት እያስመዘገበ እንዳለ በአሰራር ስርኣት በደንብ መለየት እንዲቻል ቀጣይ ለሚዘረጋው የአሰራር ስርዓት ለውጥ ከወዲሁ ምቹ መደላድል መፍጠር አስፈላጊ ስለ ሆነ ነው ሲሉ አቶ ሀይለሚካኤል አክለዋል፡፡

ይህ በሶስት ዙር እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጋር በትብብር የተዘጋጀ ሲሆን እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2017ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።ማት ጋር በትብብር የተዘጋጀ ሲሆን እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2017ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

Mega Projects Construction Office

15 Oct, 11:17


በሪፎርሞ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ጉብኝት መካሄዱ ተገለፀ
ጥቅምት 05 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሪፎርሞ ስራዎችን መጎብኘታቸውን የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።
ጉብኝቱ የተቋሙ የሪፎርም ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በከተማ አስተዳደሩ ሪፎርም ካደረጉ ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አንዱ ሲሆን ሪፎርም ማድረጉን ተከትሎ አሰራሩን በማዘመን የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጁ እንዲታገዝ አድርጓል።
የቢሮውን ሁለተናዊ የሪፎርም ተግባራት በተለያዩ ጊዜያት የጎበኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬም ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፋንታ ደጀንን ጨምሮ ሌሉች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች ጋር በመሆን ተዘዋዉረው ተመልክተዋል።
በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ላይ ገልፃ የተደረገ ሲሆን በቴክኖሎጁ መሠረተ ልማት ግንባታ ፣ ተቋማትን በኔትወርክ ማገናኘት፣ የሲስተም ልማትና የመረጃ ዲጅታላይዜሽን ስራ ማብራሪያ ከተሰጠባቸው ዘርፎች ዋነኛዎቹ ናቸው።
በተቋሙ አደረጃጀት እና ቅንጅታዊ አሰራሮችም በሪፎሙ አመርቂ ውጤት የተመዘገበባቸው ስለመሆናቸው ተብራርቷል።
ጉብኝቱን ተከትሎም ብልሹ አሰራርና የተገልጋይ እንግልት የተንሰራፋበት ተቋም እንደነበር የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በርካታ ውጣ ውረዶች የነበረበት እንደነበርም በዚሁ ወቅት አንስተዋል።
ሪፎምን ተከትሎ የተዘረጋው ቴክኖሎጂ ከተማ አስተዳደሩ ያሉትን ሀብቶች በተገቢው እንዲያስተዳደር የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ሌብነትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ተችሏልም ብለዋል።
ይህም የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና የአመራሩ ቁርጠኝነት ውጤት ነው ሲሉም ገልፀዋል።
ቢሮው በቴክኖሎጁ የታገዘ አሰራር መዘርጋቱ ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ መደላድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ደግሞ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ናቸው።
በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የታዩ ተግባራት ልምድ ተቀምሮባቸው በሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ቢሮዎችም ሊሰራ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አክለው ገልፀዋል።

1,673

subscribers

1,800

photos

78

videos