ታኅሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም፣ (ሀገሬ ቴቪ)፥ በመጪው ክረምት ነጻ ወኪል የሚሆነው እንግሊዛዊው የሊቨርፑል ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በልጅነት ክለቡ ሊቨርፑል ይቆያል ወይስ ወደ ስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያልማድሪድ ያቀናል የሚለው ጉዳይ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል፡፡
እኤአ ከ2016 ጀምሮ ለዋናው የሊቨርፑል ቡድን መሰለፍ የጀመረው እና ከተከላካይ መስመር እየተነሳ ከፍተኛ የግብ እድሎችን በመፍጠር የሚታወቀው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ምርጥ የሚባል የውድድር አመትን በማሳለፍ ላይ ይገኛል፡፡
በአዲሱ አሰልጣኝ አርነ ስሎት ቀዳሚ ተመራጭ የሆነው አሌክሳንደር አርኖልድ በመጪው ክረምት በአንፊልድ ያለው የውል ስምምነት የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ ቀጣይ ቆይታው በተመለከተ ዘገባዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ፡፡
ከዋክብቶችን በማስኮበለል የሚታወቀው የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያልማድሪድ አርኖልድን በጥሩ የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ለሊቨርፑል ይፋዊ ጥያቄ ቢያቀርብም ውድቅ ተደርጎበታል፡፡
ሊቨርፑል ወሳኝ ተጨዋቹን በነጻ ላለማጣትና በቀጣይ አመታት በአንፊልድ ለማቆየት ንግግር የጀመረ ሲሆን በቀጣይ ጊዝያት የተጨዋቹ ውሳኔ እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡
የቀኝ ተከላካይ ክፍተታቸውን ለመሙላት ሎስብንላኮቹ አርኖልድን ቀዳሚ ኢላማቸውን ማድረጋቸው የተዘገበ ሲሆን ለተጨዋቹ የአራት አመት የውል ስምምነት እንደሁም ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝለትን ስምምነት አቅርብውለታል፡፡
አርኖልድ በልጅነት ክለቡ ሊቨርፑል ይቆያል ወይስ ወደ ስፔን በማምራት ማድሪድን ይቀላቀላል የሚለው ጉዳይ በቅርብ ቀናት እንደሚታወቅ ይጠበቃል፡፡
በማሕበራዊ መገናኛዎቻችን መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/hagerietv
ትዊተር: https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: https://www.t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: https://www.hagerie.tv