#ብስራት ሚዲያ፦ ዶክተር ዳንኤል ገለታ እና ዶክተር ሕይወት ብርሃኑ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት በቅርቡ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት አቅርበው ተመርቀዋል ።
ዶክተር ዳንኤል ገለታ በሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ ትሮፒካልና ተላላፊ በሽታዎች የመመረቂያ ፅሁፉን ያቀረበ ሲሆን ባለቤቱ ዶክተር ሕይወት ብርሃኑ ደግሞ በባዮሜዲካል ሳይንስ ሜዲካል ፊዚዮሎጂ አጠናቃለች።
ስኬታማ የሕይወት ጉዞ ያላቸው ባለትዳሮቹ የፍቅር ትውውቃቸውን በተመለከተ ሲገልፁ ዶክተር ሕይወት ብርሃኑ በጅማ ከተማ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ በጨቅላ ሕፃናትና በልጆች ላይ የሚሰራ ድርጅት ለመስራት በመጣችበት ወቅትና ዶክተር ዳንኤል ለተቋሙ ስልጠና ለመስጠትም በሄደበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል።
ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም በተመሳሳይ ቀን የተመረቁ ሲሆን የ3ኛ ዲግሪያቸውንም በአንድ ቀን ማጠናቀቅ ችለዋል። ከፍተኛ ጥረት የተሞላበት ስኬታማ የሕይወት ጉዧቸውን ከ Netser Media ጋር ያደረጉትን ቆይታ በዩቲዩብ ቻናል ቀርቧል።
Gizatu Amare