ዛሬ ቀኑ የእብድ ሐሙስ ይባላል። ያለፈው ማክሰኞ ደግሞ የእብድ ማክሰኞ ይባላል። በገጠሩ የሀገራችን ክፍል ወጣቶች የሚጋቡት በዓመት ሁለት ጊዜ (የባለፈው ማክሰኞ እና ዛሬ ሐሙስ) ነበር። በእነዚህ ሁለት ቀን ሙሽራውም፣ ደጋሹም፣ ሚዜውም፣ ሠርገኛውም በመብልና በመጠጥ ይጠግባል፤ በጭፈራም ያሳልፋል። በአጠቃላይ ሕዝቡ እነዚህን ሁለት ቀናት ወደ እብድነት በተጠጋ ጭፈራ ስለሚያሳልፍ የእብድ ማክሰኞና የእብድ ሐሙስ ተብለዋል።
ዛሬ የእብድ ሐሙስ ነውና እብድነቱ ቅርፁን ቀይሯል። የጾሙን መቃረብ ምክንያት በማድረግ የከተሜው ሕዝብ ከበድ ያለ ፈንጠዝያ ላይ ነውና የሐሙስ እብድነቱ በአዲስ አበባም ነግሧል። እብዱ በዝቷልና እያስተዋልን እንበድ። እስከምታብዱ ድረስ አትጠጡ፤ እስከሚያማችሁ ድረስ አትብሉ፤ ኪሳችሁ እስከሚራገፍ ድረስ አትደሰቱ። ሐሙስ ማለፉ አይቀርምና ቀኑን አታሳብዱት።
ቀጣይ እሑድ ጥንብ አንሳ ነው። ለጥንብ አንሳ በሰላም ያድርሰን።
የቴሌግራም ቻናሌን ይወዳጁ።
https://t.me/tadelesi