Abdu Book Center @abdubook Channel on Telegram

Abdu Book Center

@abdubook


በመጻሕፍት መደብራችን ፡
የታሪክ መጻሕፍት
የትምህርት አጋዥ እና መማሪያ መጻሕፍት
የተለያዩ ልበ-ወለድ እና መንፈሳዊ መጻሕፍት
ቆየት ያሉና አዳዲስ መጻሕፍት ሌሎችም..
አድራሻችን=አዲስ አበባ ፒያሳ የምኒልክ ሀዉልት ፊቱ ባዞረበት በኩል ፊት ለፊቱ ባስ እስቴሽኑ 50ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በ0929574133 ደዉልሉን
@Abduseller

Abdu Book Center (Amharic)

አብዱ መጻሕፍት ቦክ ሌሎችን መደብራችን ሰዎችን ለመቀበል የሚገኝ ነው። በዚህ መሰረት እንደነበሩ እና እንደሚገኙ ነገሮች እና ምንም አገልግሎት የለውጤ እንዲሆን፣ መድረስ አብዱ መጻሕፍት ቦክ ነው። ስለሆነ ለማንኛውም ሰው በሚቀጥል የትምህርት መጻሕፍት ውስጥ ያለውን መጻሕፍት እና መማሪያ መጻሕፍት ይምረጡ። ይሄ መልእተኛ ግን እንዲህ በመሆኑ፣ እንደተለያዩ መጻሕፍት ለሚጠቀም በባዶ ዘመን ከፍተኛለሁ። ትምህርት አጋዥ እና መማሪያ መጻሕፍት ላይ የተገኘው , ማንኛውም ሰው የመጠበቅን መጻሕፍት ለሚረዳት በዚህ መጻሕፍት ላይ መንገድ ያለበት ልበ-ወለድ እና መንፈሳዊ መጻሕፍት እናቶች ተመልእቶ በመቀበል የሚገኝ እንደሆነ እንዲሆን አብዱ መጻሕፍት ቦክ በሚገኙበት በበቃዎች ላይ እናቶችን ለመቅበል ስልኩን በሰጥተን እናመልከታለን።

Abdu Book Center

23 Nov, 10:13


የሕይወት ተፈራ አዲስ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዉሏል።

አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ  "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።

በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

14 Nov, 17:12


ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።
በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

14 Nov, 17:11


የሰዉ ልጅ በተፈጥሮዉ ብልህ አስተዋይ ራሱን በራሱ መምራት የሚችል ቢሆንም ዳሩ ግን የብቃትና የአስተዉሎት ደረጃዉ አንዱ ከአንዱ በአስገራሚ ሁኔታ ይለያያል።የዚህ ዋና ምክንያት ደግሞ ሁለት ነዉ።አንዱና ዋንኛዉ የኃያሉ ፈጣሪ ስጦታ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የዕዉቀት ሁኔታና የራስ ጥረት ነዉ።ይህን አስመልክተዉ እዉቁ ምሁር ሑጅጀተል ኢሥላም ኢማም አልገዛሊ የሰዉ ልጅ የእዉቀትና የአስተዉሎት ደረጃ ልዩነቱን እንደሚከተለዉ በምሳሌ አስደግፈዉ ገልጸዉታል«የሰዉ ልጅ አእምሮ ልክ እንደምድር አካል ሁሉ የተለያየ ደረጃ አለዉ።ከፊሉ የምድር አካል ማንም ሰዉ ሳይነካዉ በተፈጥሮዉ በብዛት(ዉሃዉ) ይፈሰዋል።ከፊሉ በራሱ ሃይል ትንሽ ትንሽ ያመነጫል።ከፊሉ ደግሞ ሲቆፍሩት በቅርብና በቀላል ልፋት ይገኛል።ከፊሉ በብዙ ድካምና ርቀት እንጅ አይገኝም።

«መሃይምነት ኢብሊስ ወደሰዎች የሚገባበት ሰፊ በርነዉ።ኢብሊስ(ሳጥናኤል) ወደመሃይሞች በሰላማዊ መንገድ ይገባል።እዉቀት ወዳለዉ ሰዉ ግን በሌብነት መልክ እንጅ መግባት አይችልም።ኢብሊስ ያለ እዉቀት አምልኮ ብቻ በሚያበዙ አቢዶች ላይ በመሃይምነታቸዉ ሳቢያ እዉነትን ከሀሰት አደባልቆባቸዋል።ብዙሃኑ በቂ እዉቀት ሳይኖራቸዉ በዒባዳ ላይ ይተጋሉ።ኢብሊስ ከእዉቀት የሚፈለገዉ ተግባር(ብቻ) እንደሆነ አሳያቸዉ።ከተግባር ደግሞ የዉጫዊ የአካል ተግባርን ብቻ እንጅ ሌላን አይገነዘቡም።እዉቀት የቀልብ ተግባር እንደሆነና የቀልብ ክንዋኔ ደግሞ ከአካል ክንዋኔ እንደሚበልጥ አያዉቁም»

#የእዉቀት_ኃይል_በኢሥላም
    ክፍል፦አንድ
አዘጋጅ ሙሐመድ ዑመር አደም

Abdu Book Center

08 Nov, 15:11


ፍቅር ን ሳታዉቁት ፍቅርም ሳያዉቃችሁ
ከግብሩ ርቃችሁ ስም ምትዳፈሩ
ፍቅር ን ባታፍሩት ለይላን እንኳ እፈሩ
ተወዳጁ መጅኑን ለይላ
በወንድም ሷሊሕ አስታጥቄ

በጥሩ ብዕር የተሰደረ

በብዛትም ሆነ በፍሬ ስትፈልጉ በ09-29-57-41-33 ደዉሉልን።
አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ  "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።
በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

25 Oct, 14:03


ሐዲስ ከቁርዓን ቀጥሎ የእስልምና መሰረታዊ ምንጭ፤የዚህን ዲን ዝርዝር አፈፃፀም አጠቃልሎ የያዘ የሰዉ ልጆች ትልቅ ሐብት ነዉ።ዓለም በዉስጧ ከያዘቻቸዉ ቅርሶች መካከል እንደ ቁርዓንና እንደ ሐዲስ ዉድ ቅርስ የለም።የሰዉ ልጅ ቁርዓንን ካጠገቡ ስላለ፤ሐዲስ በጥንቃቄ ተመዝግቦና ተጠብቆ ስለተላለፈለት ታድሏል።

ይህ ቅርስ በእስልምና ያለዉ ደረጃ ምን ያህል ነዉ?እንዴት ተሰበሰበ?በእንዴት ዓይነት ስልት ተመዝግቦና ተጠብቆ እኛ ዘንድ ሊደርስ ቻለ?ሐዲስን በማስተላለፍ ለሰዉ ልጅ ይህን ታላቅ ዉለታ የዋሉ ስብዕናዎች እነማን ናቸዉ?ይህች መጽሐፍ ለእነዚህና ተያያዥ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ትሰጣለች ተብሎ ይታመናል።

      አምባሳደር ዑስታዝ ሐሰን ታጁ

አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ  "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።
በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

13 Oct, 12:56


ከ1-12 ክፍል ላሉ ተማሪዎች እንዲኾኑ ታስበዉ የተሰናዱ ማጣቀሻ(አጋዥ) መጽሐፍት በመደብራችን ከ20-30% ቅናሽ ይሸምቱ።
#Extreme_Book_series
#New_edition
#ለተጠቃሚዎች
#ለነጋዴዎች

ድርጅታችን ላለፉት 11 ዓመታት የExtreme Books ወኪል አከፋፋይ ሆኖ መቆየቱ ልብ ይለዋል።

አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።

በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

08 Oct, 07:46


በሙስሊም ግዛቷ አንደሉስ(በአሁኗ ስፔን) የትምሕርት ተቋማት ዉስጥ ይማሩ የነበሩ አዉሮፓዊያን ተማሪዎች ስፊቅህና ስለሸሪዐ(ስለ እስልምና ሕግጋት) ተግባራዊ አፈፃፀም የሚያትቱ የሙስሊም ሥነ-ጽሑፎችን ተርጉመዋል።በዚህ ጊዜ አዉሮፓ የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓትም ሆነ በእኩልነትና በፍትሕ ላይ የተመሰረተ ሕግ አልነበሩዋትም።ናፖሊዮን ግብፅን በወረራ በያዘበት ወቅት 1798-1801 በማሊኪይ ትምሕርት ቤት(መዝሀብ) የታወቁት የፊቅህ ህግጋት ወደ ፈረንሳይኛ ተተረጎሙ።ቀጥሎም ለፈረንሳይ ሕግ በእርሾነት ያገለገሉ "ኪታብ አል_ኸሊል"ተተረጎመ።በዚያን ጊዜ የነበረዉ የፈረንሳይ ሕግ በአብዛኛዉ ከማሊኪ ትምሕርት ቤት ፊቅህ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ እናገኘዋለን።

አዉሮፓ ከግሪክ ፍልስፍና ጋር የተዋወቀችዉ በሙስሊሙ ኅትመቶችና የትርጉም ሥራዎች አማካኝነት ነበር።ለዚህም ነዉ የኢሥላሙ አለም ቢያንስ ለሦስት ክፍለ ዘመናት ያክል በሳይንስ ዘርፍም የአዉሮፓ መምህራን እንደነበረ በርካታ የአዉሮፓዊያን ጸሐፍት የሚመሰክሩት....

"የኢስላማዊዉ ሥልጣኔ አንፀባራቂ ገጽታዎች"
ዝግጅት፦ዶ/ር ሙስጠፋ አስ-ሲባዒ
ትርጉም፦ረ/ፕሮፌሰር ኢድሪስ ሙሀመድ(በአ አ ዩ የፊሎሎጂ ሙሁር)

አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።


በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።

በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

28 Sep, 12:13


Renaissance

በአዲስ አቀራረብ

በአዲስ ቦታ ስራ ጀምረናል።

አድራሻችን አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ እሳት አደጋዉ ሻገር ብሎ "አባቢያ ራሕመት ታቦር" ሕንፃ ፊትለፊት

ለበለጠ መረጃ በ09-29-57-41-33 ይደዉሉልን።

Abdu Book Center

06 Sep, 19:07


#በምሣሌነት_ማስተማር

የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሠለም)ለማስተማር የሚፈልጉትን በአካላዊ እንቅስቃሴ ሠርተዉ ያሳዩ ነበር።ወደ አላህ እንዴት በፍጹም አክብሮትና ፍርሃት፣ራስን በማስተናነስ፣ጥልቅ በሆነ ስሜት ስግደትን፣በምሽት ወደ አላህ እየተለቀሰ መቃረብን፣እንዴት ማከናወን እንደሚገባ መጀመሪያ ራሳቸዉ ሠርተዉ ከዚያ ለተከታዮቻቸዉ አስተምረዋል።

በመሆኑም ያስተማሩት ሁሉ በመጀመሪያ ቤታቸዉ ባሉ አባላት፣ቀጥሎም በህብረተሰቡ፣ቃላቸዉን ከተግባራቸዉ በመጣጣሙ፣ወዲያዉ ልባቸዉን ነክቶ ተቀባይነት ለማግኘት ችለዋል።ከእርሳቸዉ ህልፈት በኋላም በእርሳቸዉ ት/ቤት በተኮተኮቱና ልቦናቸዉ በፍጹም ጸድቶ ለአላህ አገልግሎት ራሳቸዉን ባሠማሩት ብፁኣን አማካኝነት አስተምህሮቱ በዓለም ተሠራጭቶ፣የአላህ መልዕክተኛ ሰላትና ሰላም ይዝነብባቸዉና በዘረጉት ደረጃ ዲኑን የሚያገለግሉ ሙስሊሞችን ለማየት የሰዉ ልጆች በቅተዋል።

የመልእክተኛዉ ቤት በቋሚነት ለአላህ ራስን የማስተናነስና የመገዛት ስሜት ጎልቶ ይታይ ነበር።የገነት ምስራችና የገሃነም አስደንጋጭ ሁኔታም ይሰማ ነበር።መልዕክተኛዉ ገሀነምን በመፍራትና ገነትን በመመኘት ስሜት ዉስጥ ተዉጠዉ የሚያያቸዉ ሁሉ አላህን የሚያስታዉስበት ሁኔታ ዉስጥ ይገባ ነበር።ኢማም አል-ነሣኢ እንደ ዘገቡት "መልዕክተኛዉ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሠለም እየጸለዩ ባሉበት ወቅት የሚፈላ ዉሃ የሚያሰማዉ ድምጽ ዓይነት ይሰማ ነበር።“ ጸሎታቸዉ ሁሌም በሚቃጠልና በሚያለቅስ ልቦና ነበር የሚያደርሱት።አዒሻ ረዲየሏሁ ዓንሃ ሁልጊዜም ጌታቸዉ ፊት ሲሆኑ እየተንቀጠቀጡ ሲሰግዱ ነበር የምታገኛቸዉ።....

«እነሆ ተምሳሌት»ከገጽ 145-146

መጽሐፉ እዉቁ ቱርካዊ የእስልምና ኃይማኖት ሊቅ ፤የተለያዩ ከ40 በላይ መጽሐፍት አሰናኝ እና ከመቶ በላይ የሚቆጠሩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች አሳታሚ የኾኑት ሙሐመድ ፈትሁሏህ ጉለን «ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ» የሚል ርዕስ ሰጥተዉ ካሳተሙት ዳጎስ ያለ መጽሐፋቸዉ፤ ዋቢ በማድረግ አብዱልዋሲዕ ዩሱፍ ዓሊ መንዲዳ(ኤል ኤል ቢ ኤል ኤል ኤም) ሙክተሶር አድርገዉና የመልእክተኛዉ ስብእና እና ተምሳሌትነት የበለጠ ያጎላልኛል ያሉትን ፓርት ነቅሰዉ በማዉጣት «እነሆ ተምሳሌት» የሚል አርዕስት ሰጥተዉ በተባ ብዕራቸዉ 2009 ዓመተ ልደት ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰዉታል።

Abdu Book Center

04 Sep, 06:41


ማንኛዉንም መጽሐፍት ለማዘዝ ሲሹ በ👉@Abduseller
ይጠቀሙ።

Abdu Book Center

04 Sep, 06:35


#አላህ_ኃጢአተኞችን_በዚህ_ዓለም_የማይቀጣቸዉ_ረስቷቸዉ_አለመሆኑን_አስታዉስ

ሰዎች በዚህች ዓለም ላይ የዓመጽ ሕይወት ሲገፉ እያስተዋለ አላህ ዝም የሚላቸዉ ረስቷቸዉ አይደለም።የመረጡት የጥመት መንገድ መሆኑንና የማመዛዘን ችሎታቸዉን(ሕሊናቸዉን) ሊጠቀሙበት አለመፍቀዳቸዉን ስለሚያዉቅ ንቋቸዉ ነዉ።ይልቁንም በኃጢዓታቸዉ ላይ ዘዉታሪዎች ሆነዉ እያለ አንድ ቀን እንደሚይዛቸዉ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦

"አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤የሚያቆያቸዉ፥ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነዉ።"(ኢብራሒም፡42)

ብዙ ሰዎች በአላህ እዝነት ስፋት ተዘናግተዉ በሃጢዓት ላይ በመዘዉተር እድሜያቸዉን ይገፋሉ።እንዲያዉም ከዚህም አልፈዉ አላህ በሚሰጣቸዉ ምድራዊ ጸጋ ተታልለዉ እንደሚወዳቸዉ ያስባሉ።ይህ ሁኔታም ብዙ የዓለም ሰዎችን ሲያዘናጋቸዉ ይታያል።አላህ እንዲህ ይላል፦

"ገንዘቦቻቸዉንና ልጆቻቸዉም አይድነቁህ፤አላህ የሚሻዉ በቅርቢቱ ሕይወት በነርሱ(በገንዘቦቻቸዉና በልጆቻቸዉ) ሊቀጣቸዉ፥ነፍሶቻቸዉም እነሱ ከሓ*ዲዎች ኾነዉ ሊወጡ ብቻ ነዉ።"(አት-ተዉባህ፡55)

«አስታዉስ»
በአህመድ ሑሰይን(አቡ-ቢላል)
2006 ዓመተ ልደት፥ገጽ 50

አድራሻችን፦
አዲስ አበባ ፒያሳ
ለበለጠ መረጃ በ 0929574133 ይደዉሉልን!

በዚሁ ስልክ ቁጥር በቴሌ ግራም፣ በዋትሳፕ እና በኢሞ ያነጋግሩን!
ክፍለ አገር እና ባሕር ማዶ ላላችሁ የመጻሕፍት ወዳጆች በተመጣጣኝ ዋጋ እና በታማኝነት በያላችሁበት በፍጥነት እንልክላችኋለን።

በቴሌግራም👇👇👇
https://t.me/Abdubook

በtiktok፦👇??👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMjLMx7X9

Abdu Book Center

02 Sep, 10:25


በሐላልና በሐራም አጀንዳ ላይ የኢስላም መሠረታዊ መርሆዎች

- የነገሮችን መሠረታዊ ባሕሪ ሐላልነት ነዉ፣

- ነገሮችን ሐላል ወይም ሐራም በማለት የመወሰን መብት የአላህ ብቻ ነዉ፣

- ሐላሉን ሐራም፥ሐራሙን ሐላል ማለት የሺርክ አካል ነዉ፣

- ሐራምነት ከመጥፎነት እና ከጉዳት ጋር የተያያዘ ነዉ፣

-ፍላጎትን ሊያሟሉ የሚችሉ ነገሮች፥ወደ ሐራም መሄድ ሳያስፈልግ፥ሐላል ዉስጥ ይገኛሉ፣

-ለሐራም የሚያበቃ ነገር ሁሉ ሐራም ነዉ፣

-ለሐራም መዘየድ ሐራም ነዉ፣

- ቅን ሐሳብና መልካም "ኒያ" ሐራምን ሐላል አያደርጉም፣

- አሻሚ ነገሮችን መጠንቀቅ፣

-በሐራም ነገሮች ላይ በሰዎች መካከል ልዩነት የለም፣

-አስገዳጅ ሁኔታዎች ሐራምን(ለጊዜዉ) ለመጠቀም መነሻ ይሆናሉ።

ዝግጅት፦ፕ/ር ኢማም ዩሱፍ አልቀረዳዊ(ራሕመቱላሂ ዓለይህ)

ትርጉም፦አምባሳደር ዑስታዝ ሐሰን ታጁ

1,084

subscribers

632

photos

3

videos