የኛ ግጥም 😍😄❤🥰🥺 @ethiopianye Channel on Telegram

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

@ethiopianye


እንኳን ደና መጡ🙏
በዚህ ቻናል
#ግጥሞች
#ቀልዶች
እንዲሁም ሀገርኛ ወጎችን አዝናኝ መረጃዎችን በለዛ እናገኛለን
ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ስራዎን ማቅረብ ከፈለጉ ወይም cross ከፈለጉ
በዚህ ያናግሩኝ 👉 @berii34
እዚህ ለይ ደሞ👇
@ethiopianye👈join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

for any comment👉 @berii34

የኛ ግጥም 😍😄❤🥰🥺 (Amharic)

እንኳን ደና መጡ! ስለዚህ ቻናል የኛ ግጥም 😍😄❤🥰🥺 በዚህ ቻናል ላይ የሚገኙበት የማህበረሰብ የግጥም መረጃዎችን በትክክል ማግኘት እና ስለሚሻር ያናገሩ። ለማንኛውም አስተያየት እና ስራዎን ማቅረብ/ማስተካከል ለማለፍ እና cross ለማስተላለፍ ህይወት እፈልጋለን። እባኮት ከዚህቻናል ደሞ @berii34 እንዴት ሊደርስ ይችላል ማድረግን ይቀንሱ። በዚህ ቻናል ከፈለጉ @ethiopianye አገባብቀለት። ከዚህ ለይ ደሞ @ethiopianye እንዴት ሊክትኩ ይችላል join ለመፅሓፍ በማድረግ ቤተሰብዎን ይሁኑ። ለጠቃሚዎች ስናንት @berii34 ላይ ጨምሮ እንዲሁም ጽሁፎችን ይመልከቱ።

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

24 Nov, 14:13


የዝናብ ላይ እንባ

የማይድን በሽታ የማይታይ ህመም
ሊሽር የማይገደው ያመረቀዘ ደም
ሀኪም የማይገታው ቃል የማይመልሰው
የችግር ክራሬ አይሰማም ለሰው
የማንነቴ ካብ የጭንቄም መሰረት
ልቤና አይምሮዬ ሙግት የገቡለት
እንባ ይገበራል እንደ ችግር ስለት
እንደ ቀን መወጫ መሻገሪያም🪜 ሆኖ
ቁስሌን ያባብሳል ከሰው ተሸፍኖ
ተከልሎ በጉም
አልታየህም ተብሎ አይያዝበት ቂም
ተረቱስ አይደል ካለቀሱ እንባ አይገድም
የኔ እንባ ግን ዳባ ለብሶ
ከችግር ስቃዬ ከበደሌ ብሶ
ህመሜን የማይሽር ሆድ የማያባባ
ከሆነ ሰንብቷል የዝናብ ላይ እንባ💧

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

24 Nov, 13:42


አንዳንዴ
በዕውቀቱ ስዩም

    ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮ በአቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ ፤

እስከመቼ ድረስ
ዳርዳሩን መራመድ፤በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ሞክረው በቅሌት

ሰው ቅፅር አይደለም፤በእሾህ የታጠረ
እንድንጥሰው ነው ፤ ህግ የተፈጠረ።

አይሰለችህም ወይ
መኖር በመጠንቀቅ
     አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ፤በግንባርህ ውደቅ
     አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
     ርካብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ወድቆ ከመነሳት !

በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጓሙን ልቀቀው !

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

24 Nov, 13:40


ሸጋ ቅዳሜ ተመኘን !!

#Mahmoud_Ahmed

ሰላም አልማዝዬ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

21 Nov, 07:23


የሳቅሽን አቦል ድምቀት
ለዘመናት ሞቄ ሞቄ
እንድታለቅሽ አልፈልግም
ስለ እምባሽ መች አውቄ
የምትስቂው ሙሉ ብርሃን
የተስፋ ቃል ፍንጣቂ
እምባሽ ግና ጽልመት ወሳጅ
ሞት እና ህይወት አስታራቂ
ብደምቅበት በዓለም ሁሉ
ሳቅሽን በገፍ እየቀዳው
ስታለቅሺ ባይ ለአንዴ
እምባሽ ሊሆን
አይኔን ዳዳው

ለዘመናት ያልተሻረ
ህመም ስቃይ ነበረብኝ
ጠብ አድርጎ ቁስሌን ሻረው
ከሳቅ እምባሽ በለጠብኝ

ለዘላለም ብጸልይም
ከሀዘን ችግር እንዳትገቢ
ግና ለቅሶሽ ይናፍቃል
ያምርብሻል ስታነቢ 💧

#mikiyas_feyisa

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

21 Nov, 07:15


ሳቄን አትመኑት ፥ በእንባ ነው የነጣው
ከሰው መሀል ሆኜ ፥ ሰውነት ከመጣው ።

#አብርሃም_ተክሉ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

20 Nov, 18:14


ለካ ሁሉ ነገር አይወጣም ከሚዛን
ከፍ ዝቅ አይልም ፥ ምንም ዳኛው ቢካን
ሁለት ስህተት ፥ ሁለት እውነት ፥ ለአንድ ቦታ
ያለ አጥፊ የሚከሰት ግድፈት አለ
  ከላይ ሲታጭ ለይሁንታ ።

ሲጠቋቆሙ ቢውሉ ፥ የማይፈታ ከስሩ
ችሎቱ ማይደመደም ፥ ማንንም እማኝ ቢጠሩ ።
 
          #ምሕረት_ዘነበ
@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

20 Nov, 16:52


(ዝም የዋጠው ፍቅር)

ረጭ እንዳለ ባሕር
በሚጮህ እርጋታ እንደተንጣለለ
አደብ እንደያዘ
ከዝምታ እልፍኝ እንደተንጋለለ
በውስጡ ግን
አዕላፍት ነፍሳቶች እንዲርመሰመሱ
ቃል አልባ ትርምስ ይዘው እንዲያምሱ
እንደዛ ይመስላል የኔና' አንቺ ነገር
ከባህር ገፄ ውስጥ ጠልቆ ያንቺ ሃገር
የሙት ባህር ያህል ዝም ከወረሰው
ነፍስ የዘራው ፍቅርሽ የሚርመሰመሰው።


#እንግዳዬ_ዘሪቱ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

20 Nov, 16:44


#Ms_ጊዜ✍️

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

19 Nov, 11:26


አይ አንቺ
ያኔ ባንች አሻራ ሰው ሳይተካበት፤
ያንቺን ውበት ወስዶ ዘመን ሳይደምቅበት
ውብ ነበርሽ ሎጋ የጎመራች ፍሬ፤
እድሜ ሳይከልልሽ ሳይሸፍንሽ ዛሬ፤
አይ አንቺ
ቁመና ና ውበት ቋሚ መስሎሽ ነበር ፤
ጊዜ የማይሽረው ወድቆ ማይሰበር፤
አወየው መሸወድ ውበት ሲያታልልሽ፤
በፈራሹ ገላሽ ሲሸነጋግርሽ፤
የነገን ሳያሳይ ዛሬ ላይ ሲክብሽ፤
እውነትም(2x) አንቺዬ ሞኝ ነሽ፤
''ማነሽ የኔ ቆንጆ የኔ ማር ወለላ፤
ከሞት ያስነሳኛል ማየት ያንቺን ገላ፤
ካይኔም ስር አይጠፋ የፊትሽ ፀዳሉ፤
ውብ አርጎ ፈጥሮሻል ፈጣሪ ባምሳሉ''፤
ያሉሽ ሰዎች ሁሉ እንደ ጉም በነኑ፤
ተነኑ እንደዘበት፤
ከዛ ቁንጅናሽ ላይ ጠባይን ቢያጡበት፤
ያንን ግርማ ሞገስ በዜሮ አበዙት፤
እና የቃላቴ ውሉ ልልሽ የፈለኩት፤
የፊትሽ ገፅታ የገላሽ ማማሩ፤
ሁሉ ተሰብስበው ባንድ ቢደመሩ፤
የጠባይሽን ጫፍ ቅንጣት እያክሉም፤

#ከነዓን_ዮሴፍ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

18 Nov, 16:44


........መፍራቴን ደፍሬ
ነውርኩ መፍራቴ ላይ ደፈርኩት በጭካኔ
በሰቀቀን እየናወዝኩ እየኖርኩ ቀርቶኝ መቅኔ
ጢሻ ጫካ መኃል ከሚኖርበት አውሬ
በሰው ተከሰስኩኝ መፍራቴን ደፍሬ

#አቤል(ያኖስ)

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

17 Nov, 16:30


እጁ አለበት

አወይ ፀሀይ ንዳድ፤🌞
የስው ልጅ ጉልበት እንደዘበት ማራድ፤😥
ተንገብግቦ መኖር እንደ ሰማ ምጣድ፤
በጠራራ ጠዋት ፍጥረት ባልነቃበት፤
ሰው እንኳን ተነስቶ ባልተራወጠበት🛌
ምን ይሉታል እስኪ፤
የፀሀይ መቸኮል ተሯሩጦ 🏃መውጣት፤
ድሮኮ ስናውቃት፤
የጠዋቷን ፀሀይ vitamin ነበረ
ብለው የሚጠሯት፤
ያሁኗ ፀሀይ ግን ፈጣሪም ሲሰራት
አቃጣይ ነገር ናት🔥
ኸረ ሞትን ሰዎች ሙቀቱ ገደለን፤
ገና በጠዋቱ በላብ ተዘፈቅን፤
እንደ ረጋ ዘይት እንደፈረደበት፤
አንዴ በሞቀ ውሀ እምቢ ካለ በእሳት፤
በፀሀይ መቀቀል ስራ እንደሆነበት፤
እኛም ተሰቃየን ፍዳችንን አየን🙉
ሽቶ ተቀብተን ፍየል ፍየል ገማን🐐
ገና ነጋ ብለን ከቤት ስንወጣ፤
ፀሀይ ካናት ወጥታ መደናገር መጣ፤
ኸረ እስኪ ቆይ ዛፎች ወዴት ደረሳችሁ፤
ምግብ ማዘጋጀት በቃ አቆማችሁ፤
እናንተም እንደ ሰው ተንገበገባችሁ፤
እስኪ እንደው ንገሩን ውዴት ፈለሳችሁ፤
እንዲህ ስንቃጠል እንዴት አስቻላችሁ፤
ነው ወይስ ስንተክል ነቃይ መጣባችሁ፤
ሙስና በሏችሁ🫣
ታዲያ እስኪ ምን ልበል፤
ቆሜ እየሄድኩኝ አከላቴ ሲቀልጥ😓
እግሬና ብብቴ ለ ሽታ ሲጋለጥ፤
እንዴት አልማረር እኔ ግን ሲመስለኝ ፤
አምላክ በሰዎች ላይ
እንዲህ አይጨክንም፤
ፍጥረቱን ለማጥፋት አሁን አልወሰነም፤
ታዲያ ለዚህ በደል ለክፋቷ ብዛት፤
እኔ ስጠረጥር መንግስት እጁ እለበት

#ከነዓን_ዮሴፍ

#ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

17 Nov, 11:09


የመዳፍ ትንቢት

ደላይ ዛጎልጣት መዳፍን አንብቦ
ነገን አሳይቶን ዛሬአችንን ገልቦ
አባ ንፋው በተስፋ  አባ ዘባሪቆ
ትንቢታችንን ቢነግረንም ወይ አደንግዞ
                           አልያም አድምቆ

ይቅርብን የልምዣት አቅል የሚያስት
ለሁሉም አንድ ነው የመዳፍ ትንቢት
ካሻከሩት ከጋሩበት መስነፍ ካልቀለለው
ልስልስ ውበት
ልስልስል ኑሮ
                      መዳፍ ላይ ነው።

#አቤል_(ያኖስ)

#ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

17 Nov, 05:14


ህዝቤ ጠይም ሳለ ሩህሩህ ነበረ
ቀለም ገባው መስል ይቀ'ላ ጀመረ

#አማኑኤል_ሀብታሙ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

16 Nov, 18:01


📎

በዓለም
አንድ አንቺ
አጥብቀሽ ወድደሽኝ ፤

በዓለም
አንድ አንቺ
በሙሉ ዐይን አይተሽኝ ፤

በዓለም
አንድ አንቺ
እሾህ የሌለበት ~
አበባ አድርገሽኝ ፤

ከሰው መደበቂያ
ከሰው መኗኗሪያ
ጭንብሌን አስጣልሽኝ ።

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

16 Nov, 16:51


ማርፈድ
ታውቃለህ አውቃለሁ፤
ተግባብተናል ተዋውቀናል፤
ሀዘን ደስታን ተጋርተናል፤
ከሰው በላይ ተላምደናል፤
ካልተያየን ቅር ይለናል ፤
በልባችን ዘር ዘርተናል፤
ማጨዱ ግን ያው ከብዶናል፤
ልባችን❤️ ፍቅር እያለው፤
አፋችን ምን ለጎመው፤
ምን ከበደው ለመናገር፤
ቃል አውጥቶ ለመመስከር፤
የተሸለምነውን ፍቅር፤
ካምላክ የተሰጠን የመዋደድን ቃል፤
እስኪ እናውጣው እንናገር🗣
ከልባችን አንታገል፤
አንሽሸው ይህን ደስታ፤
እናጅበው በትዝታ፤
እንሞሽረው በእልልታ
                 ቃል አውጥተን ለአንድ አፍታ፤
አንተም ሁነኝ አባወራ፤
እኔም ልሁን እማወራህ፤
ቃል አውጥተን እንግባባ፤
ጎተራችን ማሳው ይሙላ፤
ቤታችን ይሁን ተድላ፤
አንዳችን ላንዳችን እንሁን ከለላ፤
ትንሽ ከዘገየን ማርፈድም አለና።
                      #ከነዓን_ዮሴፍ

@ethiopianye
@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

16 Nov, 05:15


ጨለማው

ጨለማ ነው ህይወቴ
ክፋት ነው ሀብቴ
ክህደት ነው እምነቴ
የለም ቀርቷል ሰውነቴ
በጣም እርቆኛል ድህነቴ
የሰው ደም ነው ሀብቴ
ክፋት ነኝ እኔ ጨለማው ነው ቤቴ
አታሳዩኝ ብረሃን ወጋገን ያመኛል
ተው አትነካኩኝ ፅልመት ይሻለኛል
የነካካቹኝ እንደሆን ብላቹ ይቀየራል
እረፉ ብያለው ጨለማዬ ያሰምጣቹሀል

                                #ማያዬ_አብዮት
@ethiopianye
@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

15 Nov, 16:21


ተዘጋጃችሁ............ ተመስጦ ያስፈልጋል ➢
ገጣሚና አቅራቢ ኤፍሬም ስዩም

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

14 Nov, 03:52


#ማያዬ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

13 Nov, 19:25


ወይ አለመታደል
እኔ እና አንቺ እኮ.....
መፋቀር ታድለን መለየት ወደድ፤
ይሀው ሳንጋባ  ሰማንያ ቀደድ።
@አሀድ

@ethiopianye

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

13 Nov, 17:29


ለምን ፈጠርህ?

እልፍ አዕላፍ ዘመናት  ወደ ኋላ ዞሬ
መኖሬን ሳልጨርስ ባለመኖር ኖሬ
እንደ ኤፍሬም ስዩም
ለምን አልፈጠርም አልልህም ዛሬ

ያለው ያነሰበት ፍስሀ የራቀው
አለም ጠባብ ሆና
                   ልቡን የጨነቀው
ፍጡር ያነሰው ነው
ለምን አልፈጠርህም
                ብሎ የሚጠይቀው

ያውም ወደ ትናንት የኋሊት ተጉዤ
   ፍጡር የሌለበት ቀናትን መዝዤ
ወደ አንተ አልመጣም
ለምን አልፈጠርህም?
                   የሚል ሙግት ይዤ

ሁሉን የምታደርግ
                      የአለማት ንጉስ
ለምን አልፈጠርህም
                  የተባልህ ክርስቶስ
አንዴ ልጠይቅህ
                   ጥያቄየን መል'ስ

ለምን ፈጠርህ?

ለሰው ነፃ ፈቃድ
                    ከሰጠህ በኋላ
ለምን እባብ ፈጠርህ
                    ካንተ የሚያጣላ

ለምን ፈጠርህ?

የተገኘን ሁሉ
ከየመንገዱ ላይ እየበላን ስንኖር
ብርድ ሳይደቁሰን ልብስ ሳንቸገር
በለስን የፈጠርህ
                    ለምን ጥቅም ነበር

የሚበላ ሞልቶ
በለስን የበላን እኛ ሆዳም ፍጡር
አትስሩ ያልከንን በመስራት ስንሽር
ሞት ሲፈረድብን የባርነት ቀንበር
ለምን አንተ ሞተህ
               ፈጠርህ አዲስ መኖር

ደግሞስ
ሞታችንን በሞት
             በገደልከው ማግስት
ልቡን እያወቅኧው
            ይህን የአዳም ፍጥረት
አመንዝራ ፈጥረህ
ለምን ትደግማለህ ስተትን በስተት

አንተ የአለም ገዢ
             ሁሉን ማድረግ ስትችል
ለምን ትፈጥራለህ
            ቃል ማክበር የማይችል
ለምን?
        ለምን?
አስርቱ ትዕዛዝህን ጠንቅቆ ፈፃሚ
ለክብርህ አጎብዳጅ ሰጋጅና ጿሚ
አለምን ዘንግቶ ከማህሌት ቋሚ
በሁሉ ስራዎች አንተን የሚከተል
እንዲህ አይነት ፍጡር
        መርጠህ መፍጠር ስትችል
ለምን ትፈጥራለህ
                    ቃልህን ሚያቃልል

ለምን ፈጠርህ?

የአንተን ግሩም ስራ
                   ፍጥረትህን የሚንቅ
አውቃለሁ ባይ ፍጥረት
                  በፍፁም የማያውቅ
አንተን ሊገዳደር
ከትልቁ ባህር
                 በማንኪያ የሚጠልቅ
የእጆችህን ስራ
ለምን ፈጠርህ ብሎ
                        ደፍሮ የሚጠይቅ
ለምን ትፈጥራለህ
                     የእኔ አይነቱን ደረቅ

እኮ ለምን?

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI


@ethiopianye