ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄 @semetnbegtm Channel on Telegram

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

@semetnbegtm


እንኳን ደህና መጡ ወደዚህ ቻናል
የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥምና ስነፅሁፎች ከእራሳችንና ከገጣምያን ተሰብስበው የምናደርስበት ስሜታችንን የምንገልፅበት አውድ ነው።
ግጥማቹን ሌላ ችሎታቹን ለማጋራት የምትፈልጉ ላኩልን✍️

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄 (Amharic)

የስሜትን በግጥም ቻናል ለመመልከት እና ለመረጃ አለብን። ይህ ቻናል የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥምና ስነፅሁፎችን ለአውድ ሰፋ የምንገልፅበት ነው። እናስከብካቸው እራሳችንና ገጣምያን ተሰብስበው ለማጋራት ግጥማቹን ሌላ ችሎታቹን ለማጋራት የምትፈልጉ ላኩልን። በእንዴት ፣ በእንቁልቁል አስተማሪ ግጥም እንዳያከብሩ እናነበራቸው የስሜታችንን ታሪካዊ አምስት ድርጊት ለማስገባት እንስከክላቸው።

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

23 Nov, 04:44


...እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር። "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ።
ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ።

የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት። "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም በተራዋ የሰማችውን ባለማመን።

"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው።ፍቅር መያዝ ነው።ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው።ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው።ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ :: ሊሆን ይችላል።

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ።በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው።"
ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ

መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::''

ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው።ሰው ስለሆንን ነው።

ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው።አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"
አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።

ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው።ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል።ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት። ምን ? አለችው።

አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::
"ፍቅር መተወን አይችልም

በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም።በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት።

አለመኖር 📚


#ከእንማር የተገኘ
https://t.me/semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

22 Nov, 14:55


ፍንዳታ
.
.
መቃብር ባልገባም፤
በለቅሶ በዋይታ፤
እርግጥ ነዉ ሞቻለሁ፤
የፈነዳሁ ለታ።

@topazionnn
@topazionnn
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

22 Nov, 03:16


ደህና ናት ምክንያቱም አሁንም ተስፋ አላት።

ዛሬ የሀዘን እንባን ያነባው አይኗ ነገ የደስታ እንባን እንደሚያወርድ ተስፋ ታደርጋለች ዛሬ የጎደለው ማጀት የጎደለው ኑሮ ነገ እንደሚሞላ ተስፋ ታደርጋለች የከዷት ጥለዋት የሄዱ የኔ ያለቻቸው ሰዎች የእሷ እንዳልነበሩ ተረድታለች ስለዚህ የተሻሉና የሷ የሆኑትን ፈጣሪ እንደሚሰጣት ተስፋ ታደርጋለች ቀኑ አልቆ ሲመሽ መንጋቱን በተስፋ እንደምትጠብቀው ሁላ የተዳፈነው ህይወቷም እንደሚያበራ ተስፋ ታደርጋለች በፈተና ውስጥ መሰራት በችግር ውስጥ መገንባት እንዳለ ታወቃለች ለዛም እያመሰገነች ለድካሟ ብቻ ከሰው ተሰውራ ጥቂት ታነባለች አዎ ታለቅሳለች ውስጧን ታማለች ሚደግፍ ሰው አጥታ በራሷ ትፍገመገማለች ግን ደና ናት ሁሉ ሚቻለውን ታሪክ ቀያሪውን እሱን ታምነዋለች ጋሻ መከታዋ መነሻ ምርኩዟ እሱን ይዛዋለች ስለዚህ ደና ናት ሁሉን አሳልፎ ጨለማውን ገፎ የሰራዊት ጌታ ሁሉን ቻዩ አምላክ እንደሚያነሳት እምነትና ተስፋን ሰንቃለች እናም በጣም ደህና ናት ።


ከተስፋና እምነት በላይ ምን ደህና ያደርጋል??

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
https://t.me/semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

21 Nov, 15:18


ሚካኤል ቅዱሱ
.......................................ሴናዬ✍️
የሞቴን ደብዳቤ ባይቀይረው ዛሬ
የሞት ሞቴን ሽሯል እንዳልጠፋ ኖሬ
ያን ጊዜ ነበረ ታምረኛው ስሬ
ትናቴም እሱ ነው ለዛሬ መኖሬ
   ሩሩ መሀሪ አዳኝ በመሆኑ
ዛሬም ትናንትናም ፀዐዳ ነው ቀኑ
ቀኑ መች ይመራል
ሌቱስ መች ያስፈራል
ምሽቱም ይነጋል በክርስቶስ ግርማ
ሚካኤል ሲመጣ ይጠፋል ጨለማ
በላኪው አምላኩ መልክተኛው ደርሶ
  አቃናው መንገዴን መንዱን አፍርሶ

አማላጅነቱ ሀያል ብርቱነቱ
የመላክት አለቃ ፀጋ በረከቱ
ያኖረን..ያኖረኝ ምልጃ መልእክቱ
ያዳነን..ያዳነኝ ሀይልና ጉልበቱ
ሚካኤል መልአክ ሚካኤል ቅዱሱ
ነብሴን በመንፈስ ስጋዬን በነብስህ ጠብቃት ከርኩሱ !
        ሚካኤል ንጉሱ
        ሚካኤል ቅዱሱ

     የሴቷ ልጅ

https://t.me/semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

21 Nov, 06:41


@semetnbegtm
ኦ ሚካኤል...
ፍፁም ትሁት ቢሆን ተሠጠው ልዕልና
ተርበው ለጠሩት የሚመግብ መና
ሞግዚት ነው በዓለም ለሌላቸው ወላጅ፣
ለታመኑት አባት ጠላትን አሳዳጅ
..
ነገድ ብሔር አይለይ ሲቀበል አደራ
ልጆች አሳዳጊ ከፊት እየመራ
ቦታ አይወስነው ጊዜ አይወስነው
ልጆቹን ሲጠብቅ፣
ስሙ ግርማ ያለው ጠላት የሚያስጨንቅ
የማይሰለች አባት ፍቅሩ የሚጨምር
የሞትን ደብዳቤ በህይወት የሚቀይር
..
ልዑል እምልዑላን ስልጣኑ ከፍ ያለ
ሠልፉን እየመራ ዘንዶውን የጣለ
እሱ ያልረዳው ሠው አይገኝ በዓለሙ
ለአህዛብ አደለም ክርስቲያኖች ስሙ
..
ዓለም ጥበበኛ ያውቅበታል ሴራ
ቆላ ደጋ ብሎ ቢደግስ መከራ
ስጋችሁ አይራድ ፍፁም አትደንግጡ
ሠልፋችሁን ይምራ ልክ እንደ አፎምያ
ለሚካኤል ስጡ፣
የዓለምን ሴራ የገንዘብን ድግስ
በእምነት ብለጡ፣
የሚካኤል ልጆች አትፍሩ ቀኑ
ቢጨልምም
እንኳን የአዳም ዘር ዘንዶው አልቻለውም!!
ኤርሚ ግርማ
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

21 Nov, 02:50


ህዳር 12 ቀን ታላቁ
መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ
አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው
ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡

የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለታላቁ ለሊቀ መላእክት
ለቅዱስ ሚካኤል
አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ምልጃው አይለየን አሜን 🙏🙏🙏

    
   መልካም በዓል🥰

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

20 Nov, 03:23


አለ ማፍቀር

ራቅ ብለው ፤በአይን እያዩ
ስሜት በግልፅ፤ ሳያሳዩ
ከተወዳጁ ፤እያወጉ
ቀርቦ ጠረን ፤እየማጉ
በመከተል፤ እንደ ጥላ
በመገስገስ ፤ከእሱ ሗላ
ቃል እያጡ፤ ለመናገር
በዛ ሰው ፊት ፤መደናገር
በሙሉ ቀልብ ፤እያመኑ
የቅርብ እሩቅ ፤እየሆኑ
ሳይገለፅ፤ የልብ እውነት
የሰው ደስታን፤ ላለማጥፋት
ለራስ የከጀሉት ፤ሌላ እቅፍ እያዩት
በዝምታ ፤ታጥረው
ምኞትን፤ ተነጥቀው
እንዲህም፤ አለ ማፍቀር
....
ተስፋ በሌለበት፤ ተስፋ እየቀጠሉ
ለፍቅር እየኖሩ ፤እራስን እየጣሉ
ላልተሰጠ ነገር ፤ዋጋ እየከፈሉ
ማማረርን ይዘው፤ ከአምላክ ከተጣሉ
ሙሉነትን ትቶ ፤ባዶ ሆኖ ከመጥፋት
ከምድር ከሰማዩ ፤ጠልቶ ከመለየት
ለነፃዋ ህይወት ፤ደስታን ማሰንበቻ
ማጣፈጫው ቅመም ፤አለማፍቀር ብቻ።

✍️የተክልዬዋ
#repost

https://t.me/semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

19 Nov, 19:21


@semetnbegtm
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

19 Nov, 05:18


የስነ ፅሁፍ ወዳጆች እድሉ አያምልጣችሁ👆


@semetnbegtm
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

19 Nov, 02:03


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

18 Nov, 16:19


ስሙኝማ…
ልጅነትን ስሸኝ በሀሳብ አድጌ
ከብቸኝነት ጋር ልላቀቅ ፈልጌ

ትዳር ለመወጠን ካሰብኩኝ በኋላ
ያየሁት እሸት ሁል ሆነ 'ማይበላ

የሆነ ቀን ለታ
አንድ አለኸኝ ብላ
ቃል የገባች እንስት
አንድ አለሽኝ ብየ
ቃል የሰጠኋት ሴት
ከብዙ ሁካታ ከጨዋታ መሀል
ከእኔ አስበልጠህ
ሴት አትወድም አይደል?
ብላ ስትጠይቀኝ መሳቄን አቁሜ
በንዴት በግኜ ደግሞም ተገርሜ
"አትሳሳች ውዴ
ካንች እጥፍ ድርብ ውለታ የዋለች
ለእኔ ደስታ ብላ ደስታዋን የሸጠች
እኔ እንደምወድህ ውደደኝ ያላለች
ካንች በበለጠ
ፍፁም ምወዳት ገራሚ ሴት አለች"
ብየ ቃል ሳወጣ
ገደል ግባ ብላ ገፍታ ጥላኝ ሄደች

በዚህ ቃል ተናዳ ከፊቴ ላይ ሳጣት
ፍቅሯን አራግፌ ከልቤ አወጣኋት

ደግሞ ትናንትና
አንድ አለችኝ ያልኋት
የህይወት አጋሬ
"መውደድህ እንዴት ነው
የት ድረስ ነው ፍቅሬ?
አንዴ ቃል አውጣና
በል ንገረኝ ዛሬ"
ብላ ስትጠይቀኝ
በኔ ልብ አዋዋል በፍቅር አደራደር
ከመውደድ ዙፋኔ ከልኬት ማህደር
ቦታ አደላድየ ላሞግሳት ስጥር
የሚከተሉትን ቃላት ብወረውር
"ዚች አለም ስኖር ካገኘኋቸው ሴት
ደስታ ካቋደሱኝ ካለበሱኝ ሀሴት
ደረጃ ሰጠሁሽ በሁለተኛነት"
ብየ ስናገራት
ከእኔ የበለጠ የምትወዳት ካለች
ከርሷ ጋር አብረህ ኑር
ብላ ጥላኝ ሄደች
የምር ጉደኛ ነች😢
ይህን ስትናገር በፍቅር አኩርፋ
ለእርሷ ያለኝ ፍቅር ከእኔ በኖ ጠፋ

እናም
ነገ የማገኝሽ የትዳር አጋሬ
መኖርሽ የምሆን የምትሆኝ መኖሬ
ቀደም አስቢበት በይ ልንገርሽ ዛሬ

ከመንገስሽ በፊት ከልቤ ዙፋን ላይ
ሁለተኛነትሽን በይ አምነሽ ተቀበይ
ወይም
ብቻየን ወድቄ
ሳልቀምሰው ይቅር እንጂ
የትዳርን አለም
አንደኛነትንስ
ከእናቴ አስበልጬ
የምሰጠው የለም

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

@poem_by_poem

@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

18 Nov, 11:43


አንዳንድ ሁኔታዎች ሲያሰለቹኝ መጃጃል ወደ ሚመስሉት የልጅነት እምነቶቼ መመለስና ደግሞ ማመን ያምረኛል ትዝ ይለኛል ድሮ የጠፋ እቃን ማግኘት ሲያቅተኝ መዳፎቼ ላይ እንትፍ ብዬ በእጆቼ መዳፌን እመታና ምራቁ ወደ ሄደበት አቅጣጫ የጠፋው እቃ እንዳለ አምኜ እቃውን እፈልጋለሁ ሁልጊዜም ባይሆን አንዳንዴ በዛ ምሬት የፈለኩትን አገኝ ነበር አሁን ላይ ሳስበው ምናለ እንደዛኔው ሁሉንም ነገር በቀላሉ የሚቀበል ልብ ቢኖረኝና የጠፉ ብዙ ነገሮቼን እንደዚህ ፈልጌ ባገኘሁ እላለሁ ። ምናለ የጠፋኝ መንገዴን ፣የጠፉ ሀሳቦቼን፣ የተሰናከሉ ህልሞቼን ና ደስታና ስኬቴን እንትፍ ብዬ መዳፌ ላይ ምታርፈው ምራቅ እንደድሮ ባምናትና ብትመራኝ በየት በኩል እንደተደበቁ ብጠቁመኝ እላለሁ። እንጃ ብቻ🤯


✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ስሜትን በግጥም(፳፬)😘😢😄

17 Nov, 03:12


ያለ ግጣም መግጠም
ሲቆይ ላያጣጥም
ጥቂት ግን ያስጉዛል
ትዝታና ፀፀት በደርዘን ያስይዛል
ልኩ የራቀው አካል ልኩ የራቀው ነፍስ
ሳይሰበር እንዲው መቼም ላይመለስ
ላይ ላዩን እያበራ ውስጡ እየዳመነ
ስንቱ ልብ በቁጭት ከስቶ መነመነ
ያለ ፍቅር ጥምረት የራስን ሰው ጥሎ
እራስን መቅጣት ነው ከናፍቆት ተዳብሎ
አዲስ ግንኙነት እንዲሁ ሰው ይዞ
ምክንያትን ያጣ መድረሻ ቢስ ጉዞ
አይን ወዲ ብሎ ልብ ወዲያ ካለ
ዋጋ የሚያስከፍል ትልቅ ጥፋት አለ

✍️የተክልዬዋ


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm