" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር" @uznesswzchristjesus Channel on Telegram

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

@uznesswzchristjesus


የተለያዩ መንፈሳዊ ህይወትዎን የምያሳድጉ ምክርን ያገኙበታል፡፡ ሐሳብ ለመስጠት @YeshuaJoshua

ሕይወት ከክርስቶስ ጋር (Amharic)

የህይወት ከክርስቶስ ጋር በትራስ የተወሰነ እና በስለራት ድምፅ ነው፡፡ የተለያዩ መንፈሳዊ ህይወትዎን የምያሳድጉ ምክርን ያገኙበታል፡፡ የአእምንት ስለስነ ዲሞክራሲ መጻሕፍት አንድ ሆኖ እንዲለዋወጡ፣ መንግስት እና አገልግሎታቸውን በየአቅጣጫ የአቀረብ እንዲሆኑ ወደ ትምህርትና ከተማው ያገኙበታል፡፡

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

05 Jan, 12:57


ማብራርያው የምያተኩሬው በሉቃስ ወንገል 1:26-38 ባለው ክፍል ላይ ነው፡፡

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

05 Jan, 12:55


«ይህ እንዴት ይሆናል?» የሚለው የማርያም ምላሽ፥ ከዘካርያስ ጥርጣሬ ጋር ተመሳሳይ ነው። ነገር ግን መልአኩ ዘካርያስን የቀጣው ሲሆን፣ ማርያምን ግን አልቀጣትም። ለምን? ምናልባትም ከጥርጣሬያቸው በስተ ጀርባ የተለያዩ አመለካከቶች ሊኖሯቸው ይችላሉ። የዘካርያስ አቀራረብ ልጅ ለመውለድ እንደማይችል በማሰብ እግዚአብሔርን እንደ ተጠራጠረ የሚያመለክት ይሆናል። የማርያም አቀራረብ ግን እግዚአብሔር የሚሠራበትን መንገድ ለማወቅ የጠየቀች ይመስላል። ያላገባች ልጃገረድ እንደ መሆኗ ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አድርጋ አታውቅም። እስክታገባ ድረስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ እንደማትችል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስተምራል። በታሪክ ደግሞ ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሳታደርግ ያረገዘች ሴት ኖራ አታውቅም። እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጅ በማርያም ማሕፀን ውስጥ ሊፀነስ የሚችለው እንዴት ነው? የመልአኩ መልስ ለማርያም ትርጉም የሚሰጥ አይመስልም። መንፈስ ቅዱስ በሰውነቷ ውስጥ ተአምር በመሥራት ከወንድ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሳታደርግ የምትፀንስበትን ተግባር እንደሚፈጽም ነበር የገለጸላት።

ማርያም ገና ወጣት ብትሆንም፣ «እኔ የጌታ ባሪያ ነኝ። እነሆም፥ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ» በማለት የሚያስገርም መንፈሳዊ ብስለት አሳይታለች። በእዚህም ማርያም ከቤተሰቧ ለመፈናቀል ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች። ምክንያቱም በዚያን ዘመን ከጋብቻ ውጭ ያረገዘች ሴት ልጅ ለቤተሰቡ ትልቅ ሐፍረት እንደምትሆን ይታመን ነበር። ከጋብቻ በፊት የወለደች ሴት የሚያገባ ሰው ስለማይኖር፣ ያለ ጋብቻ ለመኖር ወስናም ነበር። በመላው ሰዎች ሊሰድብዋት ከፈለጉ ሳይከፋት በገሊላ የዲቃላ እናት ተብላ ለመጠራት ዝግጁ ነበረች። ለዚህም ምክንያቱ ለእግዚአብሔር ያላት ፍቅርና ታዛዥነት ነበር። እግዚአብሔር ነገሮችን እንዴት እንደሚሠራ ባታውቅም፣ ስለ እግዚአብሔር መነቀፍን መርጣለች።

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

05 Jan, 12:54


ገብርኤል ለማርያም ያስተላለፈው መልእክት በጣም ግልጽ ነበር። እግዚአብሔር በዓለም ታሪክ ውስጥ ልዩ ለሆነ ዓላማ መርጧታል። ልጅ ትወልዳለች። የልጁም ስም ኢየሱስ ይባላል። ይህም ኢያሱ ከሚለው የዕብራይስጡ ስም ጋር ተመሳሳይ ስያሜ ነው። የሁለቱም ስሞች ፍች፥ “እግዚአብሔር ያድናል» ወይም «እግዚአብሔር ደኅንነት ነው» የሚል ነው። ይህም የኢየሱስ ትልቁ አገልግሎት ለሰው ልጆች ደኅንነትን ማስገኘት እንደሆነ ያመለክታል። ኢየሱስ «የልዑል ልጅ» እንደሚባል ገብርኤል ለማርያም ገልጾላታል። አብዛኞቹ አይሁዶች «እግዚአብሔር» የሚለውን ቃል ለመጥራት ስለማይደፍሩ ይህ «የእግዚአብሔር ልጅ» ለሚለው አገላለጽ ሌላው አማራጭ ነበር። ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠው መሢሕና በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀውጥ ንጉሥ ነበር። ከዳዊት በተለየ አኳኋን የኢየሱስ አገዛዝና መንግሥት ዘላለማዊ ነው።
ሉቃስ ማርያም ከሌሎች ሴቶች ሁሉ በላይ ቅድስት መሆኗን አይነግረንም። ይልቁንም እግዚአብሔር ትምህርትን፣ ዘርን፥ ሀብትን መሠረት ሳያደርግ ሰዎችን ለዓላማው እንደሚመርጥ የሚያመለክት ምሳሌ ነው። ከሰው አስተሳሰብ አንጻር እግዚአብሔር የተማረችውንና ከልዩ ዘር የተወለደችውን ሀብታም ሴት ይመርጣል ብለን እናስብ ይሆናል። የገጠር ገበሬ ልጅ እንደ መሆኗ፣ ማርያም ከእነዚህ መስፈርቶች አንዱንም አታሟላም ነበር። ስለ ማርያም የምናውቀው ነገር ቢኖር እግዚአብሔርን የምትወድ ሴት መሆኗ ነበር። ይህ ታሪክ ባለን ስጦታ ተመክተን እንዳንታበይ ያስጠነቅቀናል። የመዝሙር ስጦታ ቢኖረን ይህ የሆነው በራሳችን ችሎታ ሳይሆን ከእዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ነው። ቁሳዊ በረከት፣ ጥሩ ቤተሰብ፣ ልዩ ችሎታ፣ ውበትና መልካም ገላ ቢኖረን፣ ይህንን ሁሉ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት እንደሌለ መገንዘብ ይኖርብናል። ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፤ ትምክህት እንዳይገዛንና ከእኛ የተሻሉ ናቸው ብለን በምናስባቸው ሰዎች እንዳንቀና ይህንን ማስታወስ አለብን። ይህ የእግዚአብሔር ምርጫና ስጦታ እንጂ የእኛ እንዳልሆነ መገንዘብ አለብን።

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

05 Jan, 12:20


ምንጭ፦ ቲም ፌሎስ የአ/ክ ማብራሪያ

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

05 Jan, 12:19


ሊድያ የአንድ ዕውቅ ወንጌላዊ ልጅ ነበረች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ካጠናቀቀች በኋላ የጸሐፊነት ሥልጠና እንድታገኝ እግዚአብሔር ረዳት። ከዚያም ለአንድ ነጋዴ ተቀጥራ ለመሥራት አሰበች። አንድ ቀን አንድ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ የመጣ ወንጌላዊ ለጋብቻ ጠየቃት። የወንጌላዊው ጥያቄ ሊድያን አስከፋት። ሰውዬው የገጠር ወንጌላዊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፥ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ያጠናቀቀው በቅርቡ ነበር፡ ደመወዙም ትንሽ ስለሆነ ይጠቅሙኛል ብላ የምታስባቸውና የወርቅና የብር ስጦታዎች ሊያቀርብላት እንደማይችል ተገንዝባለች። ብሔሩም ቢሆን እርሷ ከምታከብራቸው ብሔሮች መካከል አልነበረም። ከሰውዬው ሁኔታ የሚስባት ምንም ነገር ስላልነበረ በፍጥነት አሉታዊ ምላሿን ሰጠችው። ውሎ ሲያድር ግን እግዚአብሔር በልቧ ውስጥ መሥራት ጀመረ። «ከእኔ በላይ ምቹ ሕይወት ትፈልጊያለሽ? ከትምህርትሽ በላይ እኔን ትወጅኛለሽ? ከክብርሽ በላይ እኔን ትወጅኛለሽ? ይህን ወንጌላዊ እንድታገቢው እፈልጋለሁ። ፈቃደኛ ነሽ?» ሲል እግዚአብሔር አፋጠጣት። ጓደኞቿን ስታማክር፣ «ድሃ ወንጌላዊ ለማግባት ማሰብሽ ራሱ ዕብደት ነው» ሲሉ መለሱላት። መጫወቻም አደረጓት። ወላጆቿም የማይመጥናትን ሰው ልታገባ ነው ብለው ስለተበሳጩ፥ ሁኔታው በጣም አናጋት፡፡

ጥያቄ፡- ሀ) ሊድያ ምን ማድረግ ያለባት ይመስልሃል? ለ) ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልጋቸው ነገሮች የተሻለ ደረጃ፣ ክብርና የተሻለ የሕይወት መንገድ ያመጡልናል ብለን የምናስበው እንዴት ነው?
አብዛኛውን ጊዜ ለራሳችንና ለልጆቻችን ውሳኔ የምንሰጠው ራስ ወዳድና ዓለማዊ መመዘኛዎችን መሠረት አድርገን ነው። ስለዚህ የልባችንን መሻት ለመግለጽ ለልጆቻችን መልካሙን ሁሉ እንመኛለን። ስለዚህ ልጆቻችን ጥሩ ትምህርትና ጥሩ ሥራ እንዲያገኙ፣ ከሀብታም ወይም ከዝነኛ ቤተሰብ ጋር እንዲጋቡ እንፈልጋለን? ወይስ ትልቁ ፍላጎታችን ልጆቻችን በጌታ መንገድ ሲመላለሱ፣ ሲታዘዙትና የዓለምን ምቾት መጣል በሚያስፈልግበት ሁኔታ እንኳን እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ማየት ነው? የቤተ ክርስቲያን መሪ ልጆች አነስተኛ ደመወዝ በሚያስገኝ የወንጌላዊነት ሥራ ላይ ተሰማርተው እግዚአብሔርን የማያገለግሉት ለምንድን ነው?

ዛሬ እግዚአብሔር አንዲት ወጣት እጅግ ከባድ ውሳኔ እንድታደርግ እንዴት እንዳደረገ እንመለከታለን። ይኸውም በሰብአዊ ባሕል ባል ሳታገባ የእርሱን ልጅ በማሕፀኗ ውስጥ እንድትሸከም አድርጓል። ይህች ወጣት የጓደኞቿን ሽሙጥ ታግሣ ፅንሱን በማሕፀንዋ ውስጥ ትሸከማለች? የወላጆቿን ቁጣም ለመታገሥ ፈቃደኛ ነበረች? እጮኛዋ መተጫጨታቸውን እንዲያፈርስ ፈቅዳለች? ከአምልኮ ቦታዋ ለመባረር ፈቃደኛ ሆናለች? ማርያም እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ስለ መረጠችና የዓለምን ውርደት ለመቀበል ስለ ፈቀደች እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።

ይህች ወጣት በዓለም ሁሉ የታወቀች ለመሆን በቅታለች። እግዚአብሔርን ለመታዘዝና እርሱ በሚፈልገው መንገድ ለመኖር ስንወስን፣ ዓለም ልትስቅብን፣ ወላጆቻችን አሳባችንን ላይረዱት፣ እኛም መልካሙን ስማችንንና ሕይወታችንን ልናጣ ብንችልም፣ በሰማይ ስማችን የከበረ ይሆናል። እግዚአብሔርም የሚገባንን ዋጋ ይሰጠናል፡፡

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

23 Nov, 19:37


አንዳንዴ እኛ ላናውቀው እንችላለን እንችላለን እንጅ ጌታ እየሱስ ነፍሳችን ልያጠፋ እንደዝህ አፉን ከፍቶ ጠላት እየጠበቀ እያለ ነው ያዳነን፣ የምያድነንም፡፡ እስት ስለጥበቃው አሁን ግዜ ውሰዱና እየሱስን አመስጊኑት!

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

11 Nov, 04:06


Greatest man in history, Had no degree, yet they called him Teacher. Had no medicines, yet they called him Healer. He had no army, yet kings feared Him. He won no military battles, yet He conquered the world. He committed no crime, yet they crucified Him. He was buried in a tomb, yet He lives today. His name is Jesus. ❤️

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

24 Oct, 16:31


ታሪክን የቀየረው የማርቲን ሉተር አንድ ቀን

"በስተመጨረሻም በእግዚአብሔር ምሕረት ከብዙ ቀንና ለሊት ማሰላሰል በኋላ “ጻድቅ በእምነት ሕይወትን ያገኛል ተብሎ ተጽፎአል፤ የእግዚአብሔር ጽድቅም በሥራ ስለ ታየ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ሰው የሚጸድቀው በእምነት ነው።” የሚለው አረፍተ-ነገር አውድ ላይ አተኮርኩ። ከዛም የእግዚአብሔር ፅድቅ ማለትም ፃድቅ ከእግዚአብሔር በሆነ ስጦታ የሚኖርበት ፅድቅ በእምነት መሆኑን መረዳት ጀመርኩ። የክፍሉ ትርጉም ይኼ ነው ፣ የእግዚአብሔር ፅድቅ በወንጌል ተገልጧል፤ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደተጻፈ መሀሪ እግዚአብሔር በእምነት አፅድቆ ምንም ሳንሰራ የምንቀበለውን ፅድቅ ይሰጠናል። ይህን ባወቅሁ ግዜ ዳግመኛ እንደተወለድኩና በተከፈተ በር መንግስተ ሰማይ እንደገባሁ ተሰማኝ። ከዛም ፈጽሞ አዲስ የሆነ የሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ገጽታ ተከፈተልኝ።"

ማርቲን ሉተር ፣ 1545 እንደጻፈው

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

23 Oct, 19:40


“ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።”
መዝ 119፥18

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

21 Oct, 19:14


“አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”
— ፊልጵስዩስ 4፥7

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

16 Oct, 05:26


"የምያሳፍሬውን ስውሪ ነገር ጥለሀል"?

“ነገር ግን # የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን።” 2ኛ ቆሮ 4፥2

መዝሙር 19
¹² ስሕተትን ማን ያስተውላታል? # ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
¹³ #የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
¹⁴ አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

14 Oct, 05:25


“... ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤”
ምሳሌ 23፥17

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

11 Oct, 07:27


እየሱስን ትወደዋለህ/ሽ? አዎ ከሆኔ መልስህ የምሪህን ትወደዋለህ?

ይህን ጥያቄ ማንም ብጠይቀን መልሳችን አዎ ዕወደዋለሁ እንደምንል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ያውም ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ብለን በፍጥነት ነው የምንመልሰው! ቀጣዩ ጥያቄ ደግሞ እንደምትወደው እንዴት ታውቃለህ? ስትባል ነው አሀሀሀ... ብለን ትንሽ ለማሰብ ግዜ የምትወስደው አይደል? ብቻ ምንም ይሁን ምን እንደምትወደው የምታውቅበትን አንዱን መንገድ እንይ!

የምርህን እንደምትወደው የምታውቅበት መንገድ ስትታዘዘው ብቻ ነው፡፡ ፍቅር በተግባር ይገለጣል ይባል የለ? ስለዝህ በንግግር የምገለፅ ፍቅር የለም ማለት ነው፡፡ መቼም የወለዱህ ወላጆችህን የምትወዳቸውና የምታከብራቸው ከሆኔ እንደምትታዘዝላቸው ግልፅ ነው፤ መቼም ያዘዙህንን ሳትፈጽመው ማሚ ዕወድሻለሁ፤ ዳዲ ዕወዳሀለሁ አከብርሀለሁ ብትል ምንም ትርጉም የለለው ንግግር እየተናገርክ እንደሆኔና አንቴም እንደዛ እንደማትል ግልፅ እንደሆኔ ታውቃለህ ብዬ አስባለሁ፡፡ ከመታዘዝ ውጭ ማክበርህንና መውደድህን ልትገልፅላቸው አትችልም፡፡ ለጌታ እየሱስም ያለህን ፍቅር በትዕዛዙ ስትመላለስ ብቻ ትገልጸዋለህ፡፡ ጌታ እየሱስ በጌቴሰማን ለደቀመዛሙርቱ እንድህ ብሏቸው ነበር፦

“#ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።..."
— ዮሐንስ 14፥15-16

“#እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ #ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።”
— ዮሐንስ 15፥10

ጌታ እየሱስ ትወደኛለህ? እያለ በየቀኑ፣ ቀንህን በጠዋት ስትጀምር ብጠይቅህ መልስህ ምን ይሁን? ቀኑን ሙሉ እኔን በፍቅር በመፍራትና በመታዘዝ ዋል እያለህ ነው፡፡ ተባርካቿዋል፡፡ መልካም ቀን፡፡

https://t.me/UznesswzChristJesus

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

10 Oct, 15:27


ሽህ ግዜ ከማወቅ፣ አንድ ግዜ መታዘዝ ይበልጣል፡፡ ጌታን አወቅኩኝ የምትለው ብዙ በማወቅህ ሳይሆን ብዙ በመታዘዝህ ነው፡፡ ብዙ የማታውቀውን ዕዉነት ለማወቅ ከመጓጓትህ በፍት እስከአሁን የምታውቀውን ለመታዘዝ ጀምሪ፡፡

ጌታ መታዘዝን ያብዛልን፡፡

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

10 Oct, 09:29


ዕብራውያን 4 (Hebrews)
12፤ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤
13፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

08 Oct, 04:31


“እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፥”
  — ኢሳይያስ 66፥13

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

06 Oct, 04:57


❤️❤️❤️👇👇👇


ክርስቶስን ከተውከው ከቀንህ ላይ ፀሀይን
እንደማውጣት፤ከለሊትህም ላይ ጨረቃን እንደማንሳት፤ከባህር ውስጥ ውሃን እንደማጥፋት፤ከወንዝ ውስጥም ጓርፍን እንደመተው፤ከእርሻህ ላይ ሰብልን እንዳለመሰብሰብ፤ከስጋ ውስጥ ነፍስን እንደማውጣት፤ከመንግስተ ሰማያት ውስጥ ሃሴትን እንደማጣት፤ሁሉን ተዘርፎ እንደማጣት ነው።
ቻርለስ ስፐርጅን

     

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

05 Oct, 13:36


“እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥”
ኤፌ 5፥1

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

02 Oct, 15:31


“ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።”
  — ኢሳይያስ 55፥7

" ሕይወት ከክርስቶስ ጋር"

29 Sep, 02:56


Channel photo updated