አማዶን @amadonart Channel on Telegram

አማዶን

@amadonart


አማዶን (Amharic)

አማዶን የቴሌግራም አካባቢ ነው እና በከፍተኛ ታዳጊ የቴሌግራም አካባቢ። ይህ ከአማርኛ ቋንቋ በሚታየው ቴሌግራም ግምት መናገር የሚኖርን ማንበም እና እናንተን ስለ ቴሌግራም አካባቢዎቻችሁ የቴሌግራም እና ትምህርት የሚከተለው ለማስከበር ነው። ስለ ውጤት ሬሽን፣ ሄሳጣን እና እኛም ስለ ቴሌግራም መረጃና መረጃ ያገኛሉ። አማርኛ ብቻ ከመማገን እና ከሚከሩ መሠረቶች መካከል የሚተገበሩት ስራዎችን እንጠቀማለን።

አማዶን

22 Nov, 20:43


ልፅፍ የምወደው
ስለ ፀጉሯ ውበት
ስፅፍ የምገኘው
ስለ ፀጉሯ ሽበት

ሚያሳስበኝ ነገር
የወገቧ መቅጠን
ግጥም የምፅፈው
ስለ ሀዘኗ መጠን

ሀሳብ የሆነብኝ
የእግሮቿ እጣ ፈንታ
መፅሐፌ መጠሪያው
‘የልቧ ከፍታ’

በእጄ ያለችው እሷ
አካል ሰውነቷ
32 ጥርስዋ
እኔ የምፅፈው
ስለ ፈገግታዋ

13|03|17

አማዶን

22 Nov, 20:03


እንዴት ነህ?
ደህና ነኝ!...
አለው ትንሽ ምፀት
ማሳየት ነው ንቀት
ከቁብ አልቆጥራትም
እቺን ትንሽ እብደት።

13|03|17

አማዶን

22 Nov, 17:21


links / via

አማዶን

21 Nov, 17:17


"እንዳለች የቄስ ልጅ ፥ የያዘች ዳዊት
ስማ ቃለ እግዚአብሔር ፥ የምታጫውት

አንቺ ሆዬ ለኔ..."


"የዘመድ የባዳ እጅ ባይዳብሰው
ኑሮን ለመታገል ፥ ይችላል አንድ ሰው?

"እብድ ይሆናል እንጂ ፥ ስቶ ህሊናውን
ስቃይን ይችላል ፥ አንድ ሰው ብቻውን

የዘመድ የባዳ..."


ተሾመ ምትኩ

አማዶን

19 Nov, 17:56


ብቸኝነት ቀስ እያደረገ የሚበላቸው ፥ ሌሊቶች አሉ። ቶሎ አይበላቸውም። ስቃይ ያለበት አሟሟት ነው። እኔን ደግሞ አማልዕክት ፥ ወደውና ፈቅደው የሌሊቱ ጠበቃ አድርገውኛል። እቆረቆራለሁ። ‘አቤት!’ እላለሁ። ዝም ይላሉ። ዝምስ አይሉም። ‘ቆይ እንደውም...’ ይላሉ። ከጠበቃነት ያለፈ ስልጣን ይሰጡኛል። በከፊል ሌሊቱን እንድሆን ያዛሉ። በግማሽ ሌሊቱን እንድሆን ያዛሉ። ሙሉ በሙሉ ሌሊቱን እንድሆን ያዛሉ። አሁን ነው መበላት...

እና አንድ ዘመድ ነበረኝ። በጉን ከማረዱ በፊት ፥ ቆዳውን የገፈፈ። አገጩን(የበጉን) ወደ ላይ ወጥረንለት። እግሮቹን ጠፍንገን ይዘንለት። የበጉ ፊት በአይኔ አለ። የእኔን ፊት ይመስላል። እንግዲህ አማልዕክትም ‘ዘመዶችህ ነን’ ይላሉ።

አማዶን

18 Nov, 19:18


Taxi Driver (1976)

አማዶን

18 Nov, 16:02


ክፍሉን በቻርሟ ስታጥለቅልቅ የነበረች ልጅ ፥ ሊፒስቲክ ያላት፣ መልክ ያልጐደላት፣ ቅጥነትና ውፍረት መሃል ላይ የተገናኙላት፣ አይኗ የሚቅበዘበዝ፣ የትኛውም ወንድ ፕረዘንሷን ኢግኖር ማድረግ እንዳይቻለው የሆነላት፣ አማላይ መሆኗ እየታመነላት የነበረች ሴት... ትጓዛለች። ትቆማለች። ፈገግ ትላለች። እዝን ትላለች። ሁሉም ነገር እየሄደባት ነበር። ቀና እንዳልኩላት ሁሉ ፥ ዝቅ ብዬ የምትሄድበትን እግሯን ሳይ ግን ደነገጥኩ። የቀኝ እግሯ አውራ ጣት ፥ ካልሲዋን በጥሶ ብቅ ብሏል። በስመአብ! ጣፍቶኝ የበላሁት ምግብ ፥ ‘የድመት ስጋ ነው’ ያሉኝ ያህል አቅለሸለሸኝ።

አማዶን

17 Nov, 20:13


መብራቱን አጥፊውና ነይ

ለምን

ምን ማለት ነው ለምን

ቆይ እንጂ እናውራ

እሺ! ምን እናውራ

እኔንጃ... ግን ምን አስቸኮለን

ምን እናውራ

እኔንጃ...

መብራቱን አጥፊው!

ተው እንጂ ተረጋጋ

እሺ ጥፊ ከፊቴ

አማዶን

17 Nov, 17:26


ሕይወት እምሻውን ፌስቡክ ላይ እያነበባችሁ ነው? ከተመለሰች ወዲህ ፥ የፃፈችውና የሚጣል የላትም። በደስታ ነው የኮመኮምኳቸው እኔ።

አማዶን

17 Nov, 08:46


🚫

ደግሞስ አንዳንድ ጊዜ ፥ ፍፁም ፀጥታ አያስፈልግም? ማስፈለግ ሲባል ፥ እንደ ልብስ፣ እንደ ምግብ፣ እንደ መጠለያ። ስለ ሰው ድምፅ፣ ስለ ቴሌቪዥን ድምፅ፣ ስለ ሚያልፍ መኪና ድምፅ፣ ስለ ህፃናት ጫጫታ፣ ስለ ውሾች ማላዘን... ማውራቴ አይደለም። ይሄንን በምፅፍበት ስልኬ እንኳን ፥ ቴክስት ሲገባና ሁለቴ ሲነዝረው መስማት ስላለመቋቋም ማለቴ ነው። መልካም እሁድ 👍🏾

አማዶን

16 Nov, 12:07


Paradox


ታክሲ ውስጥ ሆኜ ፥ መኪናው አጉል ሲንቀዠቀዥ፣ ሹፌሩ እረፍት ሲያጣ እና አንዳንዴም ፍሬን ድንገት ሲይዝ... ምንም አይደንቀኝም። ለህይወቱ የሚጨነቅ ተሳፋሪ “ሾፌር ቀስ በል እንጂ” ሲል ፥ ፀጥ ነው የምለው። ምንም አይመስለኝም። መኪናችን እየበረረ ሄዶ ፥ ሲኖትራክ ጋር ቢሳሳም ፥ ፊቴን ብቻ መለስ አደርጋለሁ እንጂ በመኪኖች ፍቅር ጣልቃ የምገባ አይመስለኝም። ከዚያ ግን እግረኛ ሆኜ አስፓልት ስሻገር ፥ በትክክል ግራና ቀኜን አይቼ ነው። ከርቀት የሚመጣ መኪናም አሳልፋለሁ እንጂ ፥ በጭራሽ ሪስክ አልወስድም። በኔ ጥንቃቄ ጉድለት ፥ መኪና አይገጨኝም። ይህ ለምንድነው?

አሁን በቀደም መሬት ተንቀጠቀጠ። አሁን አሁን እንኳን ፥ የአይን አፋር ተወዛዋዥ ሆኗል። ሶስቴ አልሆነም ከባለፈው ወዲህ? እና ሁለቱን ጊዜ ፥ ሽው ያለብኝ ሃሳብ አለ። ‘ይሄ ነገር ቢለይለትና ፥ እዚህ እንደተቀመጥኩ ድርምስምሱ ቢወጣ እንዴት ነው?’ አልኩ። ይህንንም አልፈራሁም። እንደማይሆን እርግጠኛ ስለነበርኩ ነው ሊባል ይችላል... እርግጠኛ መሆን ሞኝነት ነው። ከዚህ ባለፈም ግን ፥ መሬቱ በደንብ እንዲቀጠቀጥ ሳልመኝ አልቀረሁም። ውጤቱን ባውቅም ፥ ጨዋታ ነው የመሰለኝ። ከዚያ ደግሞ በመንገድ ስጓዝ ፥ በጅምር ህንፃ በኩል አልሄድም። ‘አንድ ብሎኬት ድንገት ቢወድቅብኝስ’ ብዬ እሰጋለሁ። ይህ ለምንድነው?


አንዳንዴ ቁጭ ብዬ እያነበብኩ፣ ወይ ፊልም እያየሁ... የሆነ ሄሊኮፕተር ቆርቆሮውን ንጦት ያልፋል። ፍጥነቱ እና ጩኸቱ ፥ የነገር ይመስላል። ‘ተዋጊ ሄሊኮፕተር ቢሆን’ ብዬ አስባለሁ። ‘በተቀመጥኩበት ቦንብ ጥሎ ቢያልፍ’ እላለሁ። አንዳች የደስታ ንዝረት ይሰማኛል እንጂ አልፈራም። እንዲህ ያለ ዲስትራክሽን አልፈራም። ከዚያ ግን በመንገድ ስሄድ ፥ ክላሸ በያዘ ፖሊስ ጐን ማለፍ አልወድም። ፒካፕ መኪናቸው ጀርባ ፥ ጠመንጃውን ወደ ህዝቡ አዙረው የተቀመጡ ፖሊሶችን ፥ አይናቸውን አላይም። ከአሁን አሁን ተኮሱ ስል ይጨንቀኛል። ይህ ለምንድነው?


07|03|17

አማዶን

14 Nov, 18:14


ፊቷ እንኳን የዋህ ነበር። ፈገግታዋ ኃጥያት የሌለበት ነው። አካሄዷ የጨዋ ነው። ጨዋ ማለት ፥ ተንኮል የማያውቅ ማለት ነው። የጉንጮቿ ስርጉዶች የጮሌ አይደሉም። ያልተጋነነው ፍንጭቷ ፥ ሰማያዊ ነው። መላ ሰውነቷ ፥ አንድ አፍታ ሱቅ ተብሎ የተላከ እንጂ ፥ የውጪ አይመስልም። ድንገት ውጪ የተገኘ እንጂ ፥ የውጪ አይመስልም። ነገር ግን ማመን አይቻልም። ይቻላል? ከቤት እስከ ሱቅ ስንት ነገር አለ?

አማዶን

14 Nov, 17:39


ካልጋው ጋር፣ ተጣብቄ
ቃሬዛው ላይ፣ አልቄ
በበሽታ መዓት፣ አካሌ ፈራርሶ
ደዌ በያይነቱ፣ ጨርሶኝ ቀማምሶ
የሞት ሞቴን ብተርፍ፣ ይህን አፈር ልሼ
ማቄን ወዲያ ጥዬ፣
መጎናፀፊያዬን፣ ብለብስም መልሼ
ለመኖር ብዘጋጅ፣ አልፎልኝ ያ ሁሉ
"ታሞ ጨረሰ" እንጂ፣"ድኗል" አትበሉ።
D.T

አማዶን

14 Nov, 09:42


ሰው ታሞ ሲመጣ ፥ በብዙዎቻችን አይን በሽታውን ብቻ ነው። ያ bladder ca patient፣ ያ DKA patient፣ ያቺ cervical patient እንላለን እንጂ ፥ ስማቸው ጉዳያችን አይደለም። ያሳለፉት experience ወይም ያበረከቱት ነገር ብሎ ሃሳብ ፥ ወደ አእምሮአችን አይመጣም። ሰው ሲታመም ወደ በሽታ reduce የመደረግ እጣ ፈንታው ፥ ሊካድ አይችልም።

(እዚህ ጋ ፥ ሐኪሙ ሁሉ እንዲህ ያስባል እያልኩ አይደለም። እኔም ሁሌ እንዲህ አስባለሁ እያልኩ አይደለም። ውንጀላ አይደለም)


የዛሬ ስንት ወር እንደሆነ እንጃ እንጂ ፥ አንድ ኮፍያ የለበሰ ፥ ሽንቱ አልወጣለት ያለው ታካሚ ፥ Urology የተባለ ዋርድ አንድ ቀን ያድራል። የታወቀ bladder cancer patient ሲሆን ፥ ለጊዜው የተደረገለት ነገር ፥ የሽንት ትቦ ማስገባት ብቻ ነበር። ሌላ ምን እንደተደረገለት ትዝ አይለኝም ወይም የለም። አንዳንድ ዋርድ (በተለይ የቀዶ ህክምና ዋርድ) ታካሚው ጉዳዩ ካለቀ ፥ በፍጥነት እንዲወጣ ይደረጋል። መቆየቱ አንድም አልጋ ይይዛል። ሁለት በኢንፌክሽን የመያዙ እድል ይጨምራል። ዋናው ደግሞ በዚህ በዚህ የተነሳ የሚቆጡ ፥ ሲኒየር ሐኪሞች አሉ። ስለዚህ አካልበን ነው ምናስወጣቸው።


እና ይሄ የሽንት ትቦ የተደረገለትን ሰውዬ ፥ በቅዳሜ ጠዋት እንዲወጣ ስነግረው ፥ ቅር ብሎታል። ቆጣ ቆጣም ይል ነበር። አንድ ቀን ተጨማሪ ማደር ይችል እንደሆነ ይለምነኛል። እሱን እሱ እንደማይወስንና እንደማይቻል ነገርኩት። “እንዴት ሽንቴን በፌስታል አድርጌ እሄዳለሁ? ወይ ይውጣልኝና ልውጣ” ይላል። እሱም እንደማይቻል ነገርኩት። አብሮት ያለ ቲቪ ላይ የሚታወቅ ጓደኛ አለው። እሱም ቀስ ብሎ ይለምነኛል። እኔ እንደማልወስንና ታካሚው ካልወጣ ፥ የሚጋተተኝ ሬዚደንት ሐኪም እንዳለ ላስረዳቸው ሞከርኩ። አልፋታ ሲሉኝ እንግዲህ ፥ እኔም ቆጣ ቆጣ አልኩና ተስፋ ቆርጠው ሄዱ። ሰውየው አኩርፎኝ ነው የወጣው ምናምን።


ከስንት ጊዜ በኋላ ሰሞኑን ፥ የእረፍት ዜና ተብሎ ፌስቡክ ላይ ከነስሙ ተለጥፎ ሳየው ትዝ አለኝ። ለካ ሰውየው ታዋቂ የክራር ተጫዋች ኑሯል። በየሬስቶራንቱና የመድረክ ዝግጅቶች ላይ የምንሰማቸው፣ የኢቲቪ መሸጋገሪያ ክላሲካሎች ፥ እነዛ የተቀነባበሩ የክራር ጨዋታዎች ብዙዎቹ የሱ ናቸው አሉ። ምርጥ አልበሞች ያሉት ሰው ነው።


በእርግጥ ይህንን ሁሉ የምለፈልፈው ለምን እንደሆነ እንጃ... ‘ትልቅ ባለሙያም ስለነበር የተለየ መስተንግዶ ሊደርግለት ይገባ ነበር’ ለማለትም አይደለም። ግን እንዲሁ ነገሩ ገርሞኝ ነው። ሰው ሲታመም ፥ በሽታ ብቻ መሆኑ አሳዝኖኝ ነው።


መሰለ አስማማው ይባላል።

አማዶን

14 Nov, 09:42


links / via

አማዶን

12 Nov, 19:13


ትለኛለች... 'ቁምነገር እያወራን ፥ ሽንቴ መጣ ትላለህ እንዴ? ቀድሞውኑ ወንድ ልጅ ሽንቴ መጣ ይላል?'

'እንግዲህ ከመጣ ምን ማድረግ እችላለሁ?' እላታለሁ

ልትይዘው አትችልም ምንድነው? አታስበው።

እሺ። ግን ሸንቼ ብመለስ አይቀለንም?

ሃሳባችን ይበተናል። ሃሳባችን ከተበተነ...

እሺ

እኮ

'ምን እያልን ነበር ታዲያ?' እላታለሁ

ምን አውቃለሁ? ቁምነገር ይዘን ነበር

ነበር?

መሰለኝ...


ትዝ አለኝ! ትዝ አለኝ...

ትዝ አለሽ?

አዎ ትዝ አለኝ

ምን ትዝ አለሽ?

እ? አንተ ግን ለምንድነው ውሃ የምታበዛው? ውሃ አብዛ ይሁን። ምነድነው ሽንት ማብዛት?

አልቻልኩም ግን እባክሽ... ደርሼ ልምጣ እ? ሄጄ ልምጣ?

ሂድ! ሂድ... አልከለክልህም። ልከልክልህ ይከብደኛል።


ሄድኩ። ለረጅም ጊዜ ሄድኩ።

አማዶን

11 Nov, 07:41


I learned at least that I was on the side of the guilty, the accused, only in exactly so far as their crime caused me no harm. Their guilt made me eloquent because I was not its victim. When I was threatened, I became not only a judge in turn but even more: an irascible master who wanted, regardless of all laws, to strike down the offender and get him on his knees. After that, mon cher compatriote, it is very hard to continue seriously believing one has a vocation for justice and is the predestined defender of the widow and orphan.

Albert Camus | The Fall

ጅምላ ገዳዮችንና ደፋሪዎችን፣ ዘራፊዎችንና አቃጣዮችን ወዘተ... Psychologically ለመረዳት፣ ማለትም ህመም የመሆኑን ጉዳይ የሚያስረዱ መላ ምቶችን መፈላለግ አበዛለሁ። ከሁለት ከሶስት አመት በፊት The Fallን ሳነብ ግን ፥ ከላይ ያለው አንቀፅ አብሮኝ ቀረ። እውነት ነው። ወንጀለኛው በሽተኛ ነው የምለው ፥ እኔና አካባቢዬ ላይ እስካልደረሰ ድረስ ብቻ ነው።

አማዶን

10 Nov, 20:46


(M was the ex girlfriend of the man talking)


When I learned of M’s death I felt sure I was the second-loneliest man on the planet. The loneliest man had to be her husband.

I reserve that seat for him. I have no idea what kind of person he is. I don’t
know his name, or the place where he lives. Perhaps he had already lost his name and place. He was, after all, the world’s loneliest man . And I imagine what it means to be the
loneliest man on earth. I already know what it is to be the second-loneliest man on earth. But I still don’t know what it is to be the loneliest. A deep gulf separates the second and the first loneliest on earth.


Men without women | Haruki Murakami

አማዶን

10 Nov, 14:19


የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ስላለኝ ፥ ተራራውን አንቀሳቅሳለሁ። ተራራውን ግን ገፍቼው አላውቅም። የማውቀው ተራራውን ወደ እኔ ማቅረብ ነው። የኔ ችሎታ... መከራን ከደመና ውስጥ መጥራት፣ ከአለት ውስጥ ፈልፍሎ ማውጣት፣ እንዲሁም ከጥልቅ ጉድጓድ ስቦ ማውጣት ነው። ግን ይህም ተዓምር ነውና።

አማዶን

08 Nov, 04:59


Perfection


ፃድቁ ልቤ
ንስሃ ገቢ
ሕጐች አርቃቂው
በፈጣሪ ፊት
ሰው አስታራቂው

ከትራሱ ጋ
ያንጐራጉራል
እንደዚህ ይላል ፦

ከሰራኋት አይቀር
እቺንስ ኃጢያት
ያቺኛዋን ኃጥያት
እንዲህ ባላደርጋት
እንዲህ እንዲህ ባደርጋት...


29|02|17

አማዶን

03 Nov, 16:33


Dostoevsky - To love is to suffer and there can no be love otherwise.

Woody Allen - To love is to suffer. To avoid suffering one must not love. But then one suffers from not loving. Therefore, to love is to suffer; not to love is to suffer; to suffer is to suffer.



Notes from Underground (1864)
Love and Death (1975)

አማዶን

02 Nov, 18:46


ጄምስ ቦንድ ከአድናቂዎቹ ጋ

አማዶን

31 Oct, 19:43


ድሮ ኳስ ስንጫወት ነው፤ አንዱ ልጅ ግርግር አነፍናፊ ነበር። ሰውነቱስ ለጠብ የሚሆን አይመስልም፤ ግን የወንድ ልጅ ልቡ አይታወቅም ብለን መሰለኝ... ንቀነው አናውቅም። ደግሞ ባህሪውን ሁሉም ሰው ስለሚያውቅ ፥ ማንም አይጣላውም።

አንድ ቀን ታዲያ ፥ የሌላ ሰፈር ልጆች ጋር ኃይለኛ ግጥሚያ ተይዞ እያለ ፥ ይሄው የእኛ ልጅ ፥ ከአንድ ትልቅ ልጅ ጋር ነገር ይፈልጋል። በቁመትም በግዝፈትም ትልቅ ነው። ጀግናው ልጃችን ግን ፥ አጓጉል አርጐ ይሰድበዋል። መስደቡ ሳይበቃው ፥ ካልደበደብኩት አለ። ይህ ማለቱም ሳይበቃው ፥ እየፎከረ ወደ ትልቁ ልጅ ሄደ። እና ድብድቡ እውነት ሊሆን ምንም ያህል እንዳልቀረው ሲያይ

ልጃችን ወደፊት እየተራመደና እየተሳደበ ፥
ለእኛ ደግሞ እጆቹን ወደ ኋላ ጣል እያረገ ፥ “እየያዛችሁኝ እንጂ” አለ።

አማዶን

31 Oct, 10:32


"Worshipers or poets can bring drama, passion, tears and worries to women, but never any pleasure. I knew one once. He worshiped his wife. Then he took up worshiping someone else. He didn't like humiliating the one by deceiving her and the other by making her a clandestine mistress. So he confessed everything to his wife, asked her to help him, his wife fell ill, he spent all his time crying, so his mistress finally couldn't stand it anymore and announced she was leaving him.

He lay down on the tracks in front of a streetcar. Unfortunately, the motorman saw him in time, and that worshiper had to pay fifty crowns for impeding traffic."


| Litost | Milan Kundera |

አማዶን

30 Oct, 20:35


ሄይ

ሄይ

ደህና አመሸሽ

ደህና

እስካሁን አልተኛሽም?

አው

ምነው

ምንም

ጠዋት እንቅልፍ አያስቸግርሽም?

አይ

ከእኔ ጋር ተቃራኒ ነን ማለት ነው

ኦኬ..ይ

ቃላቶችሽ አጫጭር ናቸው

ናቸው?

ደስ ይላሉ

🤦‍♂

(ነፍስ ይማር)

አማዶን

29 Oct, 18:44


ከሞት ሁሉ ቅስም ሰባሪው ፥ የልጅ ሞት ይመስለኛል። ከወሎ የፈለቀች ከወዳጄ የሰማሁዋት ፥ አንድ ጨዋታ ትዝ ትለኛለች።

አያ ሙሄ የተባለ ገበሬ ልጁ ሞቶበት ፥ ጎጆው በርንዳ ላይ ኩርትም ብሎ ይቆዝማል ፤ ባለንጀራው አዋ ይመር አጠገቡ ተቀምጧል ፤ አዋ ይመር ወዳጁን በቃል ማጽናናት በቂ ሆኖ አላገኘውም ፤ የወዳጁን ልጅ የቀሰፈውን ፈጣሪ ለመበቀል ስለፈለገ ፥ ጠመንጃውን አነጣጥሮ ወደ ሰማይ ተኮሰ፤

ተኩሱ በረድ ሲል ፥ አዘንተኛው አያ ሙሄ ወዳጁን እያየ እንዲህ አለ፤

“ካገኘከው ገላገልኸን፤ ከሳትኸው ግን አስፈጀኸን”


(Bewketu seyoum)

አማዶን

28 Oct, 20:29


የውሃ ሽታ



ቤትሽ የት ነው? (ትስቃለች)

ቤቴን ማየት ፈለግክ?

ታዲያ

እኔ ግን እኮ ቤት የለኝም

እየቀለድኩ አይደለም

እሺ ግን ቤቴን ባሳይህስ? አባቴ እኮ ሻምበል! ነው

ቢያንስ ከሩቅ እሺ

ይገለኛል ተው...



ሰፈርሽ የት ነው እሺ?

ሰፈሬን ማወቅ ፈለግክ?

ታዲያ

እኔ እኮ ሰፈር የለኝም

እቀየምሻለሁ

ከነገ ወዲያ እወስድሃለሁ

አትነግሪኝም?

አይ እወስድሃለሁ።

እሺ

እሺ

ግን አባትሽስ

ክፍለ ሃገር ይሄዳል...



ስልክሽን አትሰጪኝም?

ስልኬን ልስጥህ? (ትስቃለች)

በዚህ ዘመን ፥ እዚህ ደርሰን... ስልክሽ እንዴት አይኖረኝም?

ስልክ ማውራት እንደምጠላ እያወቅክ

ቢሆንም...

እሺ እሰጥሃለሁ

አሁን ስጪኝ

እሺ ልደውልልህ ቆይ... ውይ ባትሪ ጨርሻለሁ

ማለት በቃልሽ አታውቂውም?

እንዴት በቃሌ አውቀዋለሁ?

እንዴት አታውቂውም!?

ተው እባክህ አታስጨንቀኝ

ህም...

ነገ እሰጥሃለሁ። ነገ...



ሰላም (ፊት ለፊቷ)

ሰላም እንዴት ነህ?

ከጓደኞቼ ጋ ከሩቅ እያየንሽ ነበር።

እሺ (ፈገግ አለች)

ሁላችንም ምራቃችንን እየዋጥን ነበር

እሺ (እየተሽኮረመመች)

ሁሉም ‘ባል ይኖራታል’ ብለው ፈሩ። እኔ ደፍሬ መጣሁ

ባል የለኝም

ና..ይስ

(ፍልቅልቅታ)

ስምሽ ማነው?

የውሃ ሽታ

የውሃ ሽታ?

አዎ የውሃ ሽታ

ቻው እሺ

ቻው...

(ሄድ)

የውሃ ሽታ?

(ዞር) አቤት

እንዳትሆኚ የውሃ ሽታ

አልሆንም...



ግን ሆነች። ቤቷ?... ሰፈሯ?... ስልኳ?... ስሟ።


18|02|17

አማዶን

28 Oct, 11:39


ቢሆንም ግን አላበቃም
ትንሽ ተስፋ ያጃጅላል
በመጠበቅ ደዌነት ላይ
ማደንዘዣ ይወጋጋል

አማዶን

27 Oct, 19:23


አእምሮ ሆይ ፥ አንገቴን የሰጠኹህ እኔ ፥ ወገንተኝነትህ ለማን ነው?

አማዶን

27 Oct, 19:01


Where were you last night?

That's so long ago, I don't remember.

Will I see you tonight?

I never make plans that far ahead.


Casablanca (1942)

አማዶን

26 Oct, 17:38


‘ምንድነው ይህ ሁሉ’ ሳትሉ አጣጥሙ።

አማዶን

26 Oct, 17:38


links / via

አማዶን

26 Oct, 17:09


links / via

አማዶን

25 Oct, 20:09


15|02|17

አማዶን

25 Oct, 20:09


ምንም ነገር ቢያቅተኝ ይኸውልሽ... አንድ ሁለት ቃላት ብዬ ፥ ጥሩ ጥሩ አረፍተ ነገሮች አላጣም። ‘ተስፋ የለውም’ ስትዪ ፥ ተስፋ የሚሰጡ ንግግሮች ማምጣት አውቃለሁ። ‘ቀልብ የለውም’ ስትዪ ፥ ከልብ የሆኑ ጨዋታዎችን መዘርዘር አውቃለሁ። ‘ይህ ጨዋና ዝምተኛ ሰው ፥ ምን ያውቃል?’ ስትዪም  ፥  ከእኔ የማይመስሉ ልብ ወለዶችን መስጠት እችላለሁ። ምንም ነገር ቢያቅተኝ... መፃፍ እችላለሁ። አይመስልሽም?

አማዶን

25 Oct, 20:09


ኑሮዬ ሁሉ ፥ ለሆዴ መሆኑ ያስቆጨኛል። ስለ አላማዬ እያሰብኩ በመሃል ፥ ሆዴ ትንሽ ከተገለባበጠ ፥ ምንም የማያረገኝን ረሃቤን ለማስታገስ  ሁሉንም ትቼ እነሳለሁ። ከሴትዮይቱ ጋር ሆኜ ፥ ስለ ወደፊቱ ህይወታችን እያወራን በመሃል ፥ ሆዴ ከተንጓጓ አምቦ ውሃ ፍለጋ እንከራተታለሁ። ‘ከጨነቀኝ ጨነቀኝ ነው’ እላታለሁ። ከሰው ጋር የለየለት ፀብ ይዤ ካፏሸከኝ ፥ ሁሉን ትቼ እነሳለሁ። ‘ጠላቴ ሆይ መብላት አለብኝ’

ቁርስ ምሳ መክሰስ እራት...

አማዶን

25 Oct, 20:09


አንድ ልብ ወለድ ፥ እንደ ሚላን ኩንዴራ
አንድ ግጥም ፥ እንደ ቡካውስኪ
አንድ ዘፈን ፥ እንደ ተሾመ ምትኩ
አንድ ፊልም ፥ እንደ ዮርጎስ ላንቲሞስ
አንድ የሳይንስ እውቀት ፥ እንደ ሪቻርድ ዳውኪንስ

ግን አንድ ያንሳል

አማዶን

25 Oct, 12:59


"Apathy's a tragedy and boredom is a crime." Bo Burnham

ከዚህ ተጠያቂነት ለማምለጥ ፥ ይህንን ከሰዓት ምን እያደረግኩ ነው?

የሚላን ኩንዴራን Book of laughter and forgetting እኮመኩማለሁ። Background music ላይ ግርማ ይፈራሸዋ አለ። አንዱ Story ሄዶ ሄዶ ፥ ገፁ ሙሉ ቁጥር ላይ ሲደርስ (120 ላይ ሲደርስ) ተንቀዥቅዤ PCዬን ከፈትኩ። አልጠፋም አካልቤ የደገምኩት ፊልም። ደስታን በትንሽ በትንሹ ስለሆነ ፥ ዝግት ንቅል አድርጌ ሞባይሌን ደግሞ አነሳሁ። ያቋረጥኩትን ፖድስካት በ2× ፈፃፀምኩ። በዛው እዚህ አቃጥሬ ልለፍ ብዬ ነው። ወደ መፅሐፌ ልመለስ...

ድብርት ወንጀል ነው።

አማዶን

24 Oct, 17:33


ቢወድቅ ባይነሳ
ተስፋው ቢንኮታኮት
ቅስሙ መቅኔ ቢሆን
ለክፉው ዳረጎት
እየተመጠጠ
ምኑንም ምኑንም
ለቀኑ እየሰጠ...
ባልደግፈው እኔ
ቢያልቅብኝም መልሴ
ምንም አይበግረው
ጠንካራው መንፈሴ።

አማዶን

22 Oct, 18:52


ተረት ተረት...


እድሜው 65 ነበር። አልዛይመር ያለባት ሚስቱ ፥ በአንድ አመት ትበልጠዋለች። እሱም ደግሞ የአፍ ካንሰር አለበት። ለዚህ ቦታ ሳይመርጥ ለወጣ ካንሰር  ኦፕሬሽኖች አድርጓል። የጨረር ህክምና አድርጓል። ጨረሩ መንጋጋውን ይመታዋል። መንጋጋው ካልተደገፈ አይሆንም ከዛ።

ሚስቱ ፥ በቀን ውስጥ ሁለት ሶስት ዳይፐር ያስፈልጋታል። ሲቀይርላት ተፀይፎ አያውቅም። አጣጥቧት ሲጨርስ ፥ ለአፉ ጉዳይ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል። መንዳት ስለማይችል ታክሲ ይጠራል። መናገር ስለማይችል ፥ በእጅ ፅሁፍ የሚሄድበትን ያሳያል።

ሐኪሙ ፥ ተጨማሪ ኦፕሬሽን እንደሚያስፈልገው ይነግረዋል። ከግራ ጉንጩ የተወሰነ፣ ከምላሱም የተወሰነ መነሳት አለበት። እንጂ አደገኛ ነው...

ይህንን ሰምቶ ሲመለስ ፥ የሚስቱን ዳይፐር ቀየረ። እራታቸውን ማሞቂያው ውስጥ ከተተ። የማታ 3:00 ሰዓቱን ዜና አየ። ተነሳ። ተነስቶ ወደ መኝታ ክፍል ሄደ። ተኝታለች። ከመሳቢያው ውስጥ ሽጉጡን አወጣ። ግንባሯ ላይ ደቀነው። ተኮሰ።

በፀጥታ ወደ ሳሎን ሄደ። ሶፋው ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠ። አፈሙዙን አፉ ውስጥ አስገባው። ተኮሰ።

ሁለቱም ተኩስ ጐረቤት አልቀሰቀሰም። ቆየና ግን ማሞቂያ ውስጥ ገብቶ የነበረው እራት ፥ መቃጠል የጀመረው እራት ሰው ጠራ። ሰዎች መጡ። የሆነውን አዩ። ቀጥሎ ፖሊሶች መጡ። የሆነውን አዩ። ብርበራቸውን አደረጉ። የተዘጋ የባንክ ደብተር... 114 ብር የቀረው ሌላ ደብተር... ነበር።

Suicide ነው አሉ።

ከሶስት ሳምንት በኋላ አዲስ ተከራዮች መጡ። አዲስ ባልና ሚስት ናቸው። እሱ የኮምፒውተር ኢንጂነር፣ እሷ ዳንስ የተማረች ናት። እነዚህም ወደ ስኬት እየተጓዙ ያሉ የሚመስሉ ናቸው።



(የCharles Bukowskiን ውብ ግጥም ፥ ዝርው አድርጌ እንደተረጐምኩት)

አማዶን

21 Oct, 11:00


ልክ ካርድ ሞልቼ ፥ ረስቼው የተወሰነ ደቂቃ አልፎ ፥ ስልኬ ዝ ዝ ይልና
810 በአማርኛ “እዳዎ በሙሉ ተከፍሏል” ሲለኝ ድንግጥ እላለሁ። በደንብ አልለመድኩትም።

አማዶን

19 Oct, 16:07


ትወጂኛለሽ?

የመጀመሪያህ ነኝ።

አዎ እሺ...


ትወጂኛለሽ?

ከአንተ ውጭ ማን አለኝ?

አዎ እሺ...


ትወጂኛለሽ?

አንተ እረፍ! ወንድ ልጅ እንዲህ አይጠይቅም።

እሺ...

አማዶን

19 Oct, 16:07


ከዚህች ሴት ጋር ብዙ ቆየሁ ። ቀላል ጊዜ አብረን አላሳለፍንም። ‘ከእንግዲህስ ምን ቀረን’ በማለት ለትዳር ከጀልኳት።

ነገርኳት። ይህንን ብዙ ሴቶች በጉጉት የሚጠብቁትን (ህብረተሰቡ ከሴቶች በአያሌው የሚጠብቀውን) ነገር ፥ ትዳር የሚባለውን ከእሷ ጋር እንዳሰብኩ ነገርኳት። አነጋገሬስ ምንም ሮማንቲክ አልነበረም። ልጅት ግን በጣም ደስ አላት። ፍንድቅድቅ አለችልኝ።

“ግን ግን...” አልኳት

“ግን ምን?”

“አንድ ነገር እንድታረጋግጪልኝ እፈልጋለሁ”

“እሺ”

“በህልሜ ነሽ በእውኔ? አንድ ሁለት ብለሽ ማስረጃዎች ስጪኝ።”

ሳቀች። ኮስተር አልኩ

“አይ አይ... አንዲህ አይነት ቀልድ አይሰራም። ከመሄዴ በፊት ማስረጃ!”

አማዶን

19 Oct, 16:07


በህልሜ ነው

እላታለሁ... “መድረስ አልፈልግ፤ በርትቼ እጓዛለሁ። ማግኘት አልፈልግ፤ አይኔ ይቅበዘበዛል።”

“ችግርህ ሁሉ የቅንጦት ነው” ትለኛለች

“ቆይ አማርኛዬን አስተካክላለሁ”

(በትዝብት ፈገግ ትላለች)

“አማርኛዬን አስተካክዬ እነግርሻለሁ አልኩሽ!”

“አየህ?”

“ምን?”

“ላንተ እንደዚህ ነው። ነገር ሁሉ የቃላት ጨዋታ ነው።”

(ላስተባብል አልኩና አፌን ያዘኝ)

“አየህ? አየህ?” ትለኛለች። ታለቅሳለች? አዎ ታለቅሳለችስ...

(ላባብላት አልኩና አሁንም ያዝ ያዘኝ)

በትዝብት ፈገ..ግ አለች ደግሞ። ነቃሁ ወይ ወደ ሌላ ህልም ገባሁ ከዚያ...

አማዶን

19 Oct, 16:07


የሆነ ነገር ለመፃፍ እነሳና አያታለሁ። “ምን ታየኛለህ?” ትለኛለች

“አትቆጪኛ...”

“መች ተቆጣሁኽ? ለምን ታየኛለህ እንደዚህ”

“የሆነ ነገር ልፅፍ”

“እሺ በል ቶሎ በል” ትለኝና ተረጋግታ መቀመጧን ትቀጥላለች።

ታውቃለች። ልፅፍ ስል አተኩሬ እንደማያት ታውቃለች። ሁሌም ግን ትጠይቀኛለች። ደስ ይላታል።

አማዶን

17 Oct, 18:45


ለግጥም የሚሆን መረጋጋት ማጣት... ያስቆጫል።

አማዶን

14 Oct, 12:10


የፍቅር ጥያቄውን በጨዋ ደንብ አቀረበላት። እዝን አለች። አለች፦

“ታውቃለህ እንዴት እንደማከብርህ። ያንተን ያህል የምቀርበው ሰውም የለኝም። ከአንተ በላይ ምቾቴን የሚሰጠኝ ሰው የለም። የነፍሴ ሰው ነህ። የልቤ ሰው ነህ። ግን ይህንንም ታውቃለህ። የእናቴ ልጅ ማለት ነህ። በሁለታችን መሃል ሌላ ነገር ግን ፥ የኃጥያት ያህል ነው።”

“እሺ” አላት

“ትረዳኛለህ አደል?”

“ደግነቱ... እኔም አንቺም ሁላችንም እንሞታለን። ሁለመናችን አፈር ይለብሳል። አፈር።” ተፍለቀለቀ።

አማዶን

13 Oct, 16:14


ምናልባት የአንዳንድ ሰው የልጅነት ህልም ይሄ ይሆናል። ከመች መች አርጅተው ፥ የባቡር ወንበር ለማስለቀቅ መቁለጭለጭ እንደሚችሉ እና ከመች መች ረጅም የታክሲ ሰልፍ ፥ በነፃነት ሰብረው መግባት እንደሚችሉ እየተመኙ የኖሩ ይመስላሉ። I mean...

አማዶን

13 Oct, 12:23


ሀዘን ያስቀናል ወይ

አማዶን

12 Oct, 06:48


ንዴቴ እንደ ገሞራ ነው፤ ግን አይፈነዳም።
ቁጣዬ የአንበሳ ነው፤ ተሳስቶት ግን አያገሳም።
ኃይሌ የሶስት ጐሽ ጉልበት ነው፤ ነገር ግን አይነሳም።
ሰላም ወዳድ አይደለሁም። የሰላም ባሪያ ነኝ።

አማዶን

11 Oct, 16:29


የሚወዱትን ስራ መስራት መቻል፤ በዚህም በቂ ገንዘብ ማግኘት መቻል... መታደል እንደሆነ እያሰብኩ ነው።

አማዶን

05 Oct, 19:58


ማንያዘዋል እንደሻው ፋና ቲቪ የሰራለት ዶክመንተሪ ላይ ፥ አንዳንዴ እንዴት እውነተኛው አለምና ቴአትር እንደሚምታቱበት ይናገራል። “የሆነ ጊዜ ቤተ መንግስት ለስራ ሄጄ ፥ ግድግዳ ላይ የተሰቀሉ የንጉሱን ከወርቅ የተሰሩ የሆኑ ነገሮች አየሁና ፥ በውስጤ ምናለ እነዚህን ለቴአትር በተጠቀምኳቸው... አልኩ። ለራሴ አይደለም የተመኘኋቸው።” ይላል።

እኔም አንዳንድ ነገሮችን ፥ ከእውኑ ይልቅ ለህልሜ ስመኝ ይገርመኛል።

(ዛሬስ? ምን ይሆን የተደገሰልኝ)

አማዶን

05 Oct, 17:02


links / via

አማዶን

04 Oct, 17:10


“ተው ግን አእምሮ ተው...”