የጥበብ - መንገድ ™ @salmakeriem Channel on Telegram

የጥበብ - መንገድ

@salmakeriem


« Art is a step from nature toward the Infinite »
~ Kahlil Gibran 🌸📚


@abawassie ✉️

የጥበብ - መንገድ 📖 (Amharic)

የጥበብ - መንገድ 📖 በእንግሊዝኛ እና አሠሪና ከተማ መጽሀፍ ያግኙ ነው። ይህ መንገድ የጥበብን ወንድምን ወንድሜን እና ወንድሜን ልጅን እንዲሁም የሴቶችን እንስሃሎችን የማስመልከት ያልነበር መጽሀፍያን በነቃነን ፍላጎቴን በማሳደግ ላይ ምክንያት እንዲያስተውሉ ውይይት ያግኙ። የአሮጌ ብክል እና ፕሮፌሰር ልዩ እና ተከታዮች በአዲሱ መጽሀፍ መተሳየታቸውን ተጨማሪ ይሆናል። እናም በእንግሊዝኛ በማንበብ መንገድ በተመሳሳይ አልባ እንዲለያይ ላኩል።

የጥበብ - መንገድ

21 Nov, 17:25


"ህመሜን በትዕግስት ሜዳ ላይ ስተክል የደስታ - ፍሬ ወለደች 🌸።"


ካህሊል ጂብራን
!

የጥበብ - መንገድ

21 Nov, 05:11


ሙላ ናስሩዲን ፍቅር ያዘው።ጨርቅ የሚያስጥል ፍቅር።እናም በፍቅር ያሳበደችውን ሴት ለማግባት ወሰነ።ለእናቱ ነገራቸው። እናት ግን የወደድካት ሴት እምነት ስለሌላት ከሷ ጋር መጋባት አትችልም አሉት።

"ምን ይሻላል ሁለታችንም እኮ እንዋደዳለን" አለ ናስሩዲን።
"ከወደደችህ የምትላትን ትቀበላለች፤ስለ እምነት በደንብ አስረዳት፤አማኝ ትሆናለች" አሉ እናት።ሙላ በዚህ ተስማምቶ ወደ ፍቅረኛው ቤት ሄደ። ሰበካት ስለ ፈጣሪም ነገራት።ስለ እምነት አስረዳት።

ከቀናት በኋላ ናስሩዲን እያለቃቀሰ እናቱ ወዳሉበት ማድቤት ገባ።ክንዳቸውን ተደግፎ እየየውን አስነካው

"ምን ሆንክ ልጄ እቅዳችን አልሰራም?" እናት ጠየቁ።
"መስራት እንኳን ሰርቷል፤ ስለ እምነት ሰበኳት አመነችኝ"አለ።
ታዲያ ምን ተፈጠረ የምታለቅሰው?እናት ጠየቁ።

አያ ሙላ እያለቃቀሰ ምን አለ …
"ልትመንን ነው መነኩሴ ልትሆን ነው

የጥበብ - መንገድ

20 Nov, 16:25


Socrates: - Are you a philosopher? - Nope .. I'm a loser person for asking

Dostoevsky: - You're a novelist - No .. I am writing about the man

what Einstein hates: - You are a genius? - no I mix the desire to know with fantasy -

Van Gogh - you are an artist - no I see beauty in those that seem very ugly to people

Carl Young - you are a great psychologist? - No, I look inside myself, not at the world,

Seoran - Are you a human being? - No, I'm a human being, I'm living my death.

የጥበብ - መንገድ

20 Nov, 05:19


ሕልምን አጥብቀህ ያዝ፤ ምክንያቱም ሕልሞች ከሞቱ፡  ሕይወት መብረር የማትችል ክንፍ ያለው የተሰበረ ወፍ ናትና ።


©ላንግስተን ሂዩዝ

የጥበብ - መንገድ

19 Nov, 15:05


🌸 ስለ ሃይማኖቶች መለያየት !

ሌላ ትልቅ ምርመራ አለ፡፡ ሰዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክል ናቸው፡፡ እርሱም አንድ ህዝብ ለሕይወት አንድ ህዝብ ለሞት አንድም ለምህረት አንድም ለኩነኔ አልፈጠረም፡፡ ይህም አድሎ በስራው ሁሉ ፃድቅ በሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደማይገኝ ልቦናችን ያስተምረናል፡፡ ሙሴ ግን አይሁድን ለብቻቸው እንዲያስተምራቸው ተላከ፡፡ ለሌሎች ሕዝቦች ፍርዱ አልተነገረም፡፡ እግዚአብሔር ስለምን ለአንድ ህዝብ ፍርድ ሲነግር ለሌላው አልነገረም፡፡ በዚህ ጊዜ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ትምህርት ከኛ ጋር ካልሆነ በስተቀር አይገኝም ይላሉ፡፡

አይሁድና እስላም የህንድ ሰዎችም ሌሎችም ሁሉ እንደነሱ ይላሉ፡፡ እንዲሁ ደግሞ ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው አይስማሙም፡፡ ካቶሊኮች እግዚያብሔር ከኛ ጋር ነው ያለ እንጂ ከናንተ ጋር አይደለም ይሉናል፡፡ እኛም እንዲሁ እንላለን፡፡ ሰዎች እንደምንሰማቸው ግን የእግዚአብሔር ትምህርት እጅግ ጥቂቶች ወደሆኑት እንጂ ለብዙዎቹ አልደረሰም፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ደግሞ ወደ ማን እንደደረሰ አናውቅም፡፡ እግዚያብሔር ከፈቀደ ቃሉን በሰው ዘንድ ማፅናት ተስኖት ነውን? ሆነም ግን የእግዚያብሔር ጥበብ በመልካም ምክር ይህ ነገር እውነት እንዳይመስላቸው ሰዎች በሐሰት ሊስማሙ አልተወም፡፡ ሰዎች ሁሉ በአንድ ነገር በተስማሙ ጊዜ ይህ ነገር እውነት ይመስላል፡፡ ሰዎች ሁሉ በሃይማኖታቸው ምንም እንደማይስማሙ በሃሳብም ሊስማሙ አይችሉም፡፡ እስኪ እናስብ ሰዎች ሁሉ ሁሉን የፈጠረ እግዚያብሔር አለ በማለታቸው ስለምን ይስማማሉ? ፍጡር አለ ፈጣሪ ሊገኝ እንደማይችል፤ ስለዚህም ፈጣሪ እንዳለ እውነት ነውና ነው፡፡ ይህ የምናየው ሁሉ ፍጡር እንደሆነ የሰው ሁሉ ልቦና ያውቃል ፡፡ ሰዎች ሁሉ በዚህ ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ያስተማሩትን ሃይማኖት በመረመርን ጊዜ በውስጡ ሐሰት ከእውነት ጋር ተቀላቅሎበታል፡፡ ስለዚህ እርስ በርሱ አይስማማም፡፡ ሰዎች እርስ በርሳቸው አንዱ ይህ እውነት ነው ሲል፡፡ ሁለተኛው አይደለም ሐሰት ነው ሲል ይጣላሉ፡፡ ሁሉም የእግዚያብሔርን ቃል የሰው ቃል እያደረጉ ይዋሻሉ፡፡ እንደገናም የሰው ሃይማኖት ከእግዚያብሔር ብትሆን ክፉዎችን ክፉ እንዲያደርጉ እያስፈራራች መልካም እንዳያደርጉ ትፈቅድላቸው ነበር፡፡ ደጎችንም በትዕግስታቸው ታፀናቸው ነበር፡፡

ሃይማኖት ባሏ ሳያውቅ በምንዝርና
የወለደች ሴትን ትመስለኛለች፡፡ ባሏ ግን ስለመሰለው በሕፃኑ ይደሰታል፡፡ እናቲቱንም ይወዳታል፡፡ በዝሙት እንደወለደችው ባወቀ ጊዜ ግን ያዝናል፡፡ ሚስቱንም ልጅዋንም ያባርራል፡፡
እንዲሁም እኔም ሀይማኖቴን አመንዝራና ዋሾ መሆኑዋን ካወኩ በኋላ ስለርሷ በዝሙት ስለተወለዱ ልጆቿ አዘንኩ ፡፡ እነሱ በጠብ፣ በማሳደድ፣ በመማታት፣ በማሰር፣ በመግደል ወደዚህ ዋሻ ያባረሩኝ ናቸው፡፡ ነገር ግን የክርስቲያን ሃይማኖት እውነት ናት እንዳልል በዘመነ ወንጌል እንደተሰራ ክፉ አልሆነችም፡፡ የምህረትን ሥራ በሙሉ እርስ በርስ መፋቀርን ታዛለች፡፡ በዚህ ዘመን ግን የሀገራችን ሰዎች የወንጌልን ፍቅር ወደ ጠብና ሃይል ወደ ምድራዊ መርዝ ለወጡት፡፡ ሃይማኖታቸውን ከመሰረቱ አመፃ እየሰሩ ከንቱ ያስተምራሉ፡፡ በሐሰትም ክርስቲያኖች ይባላሉ፡፡

© ሐተታ ዘርዓ ያዕቆብ

የጥበብ - መንገድ

19 Nov, 05:16


“Four thousand volumes of metaphysics will not teach us what the soul is.”

–Voltaire 🌸📚

የጥበብ - መንገድ

18 Nov, 05:29


አያ ሙላ ከንግድ ማከል ዕቃ ገዝቶ አሸክሞ እየሄደ ፣ የተሸከመው ሰውዬ በሰዉ መሃል ተሽሎክሉኮ ጠፋበት ፡፡
ከሳምንት በኋላ ሌላ ዕቃ ለመግዛት ከጓደኛው ጋር ወደ ንግድ ማከል የሄደው ሙላ ዕቃውን ይዞበት የጠፋውን ልጅ ከቅርብ ርቀት እንዳየው፣ “ያውልህ ያልኩህ
ልጅ..እቃዬን ይዞ የጠፋዉ...ቶሎ እንደበቅ” አለ !

“ለምንድነው የምንደበቀው - አንቀን ዕቃውን እንቀበለዋለን” እንጅ አለ
ጓደኛዬው

“ሞኝ አትሁን” አለ ሙላ ዓይኑ አፈጥጦ ፣ “እሺ ዕቃውን ሰጠኝ እንበል፡፡ ሳምንት
ሙሉ የተሸከምኩበትን ክፈል ቢለኝስ ? ”

መልካም~ ሰኞ 🙏

የጥበብ - መንገድ

17 Nov, 16:31


<<…ልጅ ሆኜ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ጢቢ፣ ጢቢ ስጫወት ነበር። ጎረምሳ ሆኜ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ሴት ልጅን ሳቅፍ ነበር። ዛሬ አርጅቼ ነብሴን እጅግ ደስ የሚላት ልጄ ስትስቅ ሳይ ነው። አሁን እነዚህን ሶስት እኔዎች ሳስተያያቸው አንድ ሰው ናቸው? እርግጠኛ መሆን ያስችላል። እኔ ሽማግሌውስ አንድም፣ አራትም ብሆን ይኸው እዚህ አለሁ። ያ እኔ የምለው ልጅና ያ እኔ የምለው ጎረምሳ ግን የት ሄዱ? የኔ ትውስታ ውስጥ ከልጅየውም ከጎረምሳውም ከብዙ በጥቂቱ እንደ ፊልም ተቀርፆ ይገኛል እንጂ እነሱ ግን የሉም። እኮ እንዴት እኔ ውስጥ ተቀርፀው ሊገኙ ቻሉ? ያን ጊዜ ልጅየው ሆነ ጎረምሳው ሲኖሩ እኔ እዚያ አልነበርኩም'ኮ። ገና አልመጣሁም ነበራ። ያን ጊዜ ያልነበርኩ ሰውዬ ትውስታ ውስጥ አሁን የሌሉ ያን ጊዜ የነበሩ ሰዎች ተቀርጸው ይገኛሉ። ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የጊዜና የትውስታ ምስጢራዊ ምትሀት ነው። ለመሆኑ ጊዘና ትውስታ ምንና ምን ናቸው?...>>

-- --
ምንጭ ፦ እግረ-መንገድ፣ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ...ገጽ 206-207

የጥበብ - መንገድ

17 Nov, 14:58


"I'll whisper in your ear how much I love you 🌸."


— Franz Kafka

የጥበብ - መንገድ

16 Nov, 16:54


በእግዚአብሔር ሞቷልና በእግዚአብሔር የለም መካከል ያለው ፍልስፍናዊ ልዩነት

ጀርመናዊው ድንቅ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ "the gay science" በሚለው መፅሐፉ ውስጥ ተከተዩን ቃል ይላል:- God is dead. God remains dead. And we have killed him. How shall we, murderers of all murderers, console ourselves? That which was the holiest and mightiest of all that the world has yet possessed has bled to death under our knives. Who will wipe this blood off us? With what water could we purify ourselves? What festivals of atonement, what sacred games shall we need to invent? Is not the greatness of this deed too great for us? Must we not ourselves become gods simply to be worthy of it? There has never been a greater deed; and whosoever shall be born after us - for the sake of this deed he shall be part of a higher history than all history hitherto."

በአጭሩ ኒቼ በ "the gay science" ስራ ውስጥ የሰውልጅ through the rise of rationalism and science ቀድሞ የነበረውን ሀይማኖታዊና እግዚአብሔራዊ ጥገኝነት ገድሎቷል ጥሎታል ይላል.....እግዚአብሔርን ገድለነዋል በሳይንስ እና በአመክንዮ

እንግዲህ god is dead የሚለው ሐረግ ብዙ ሰው እንደሚመስለው(ለፍልስፍና ቤተኛ በሆኑት ወገኖች ዘንድ) existence of god ላይ ያተኮረ ሳይሆን በጊዜ የነበረውን የ moral decay ለማሳየት የተጠቀመው ነው....ሀይማኖት የስነምግባርና የትርጉም ምንጭ መሆኑ ያበቃበትና nihilism የታወጀበት መፈክር ነው....god is dead


እግዚአብሔር የለም'ስ

እግዚአብሔር የለም በatheism የአስተሳሰብ ጎራ ውስጥ የሚቀነቀን ፍልስፍናዊ ሀሳብ ነው....ይህ ነገር ትኩረቱ ከላይ እንዳየነው የ morality ጉዳይ ሳይሆን existence of creator ነው....ማለትም አለም ከየት መጣ?! ማን አስገኘን?! ለምን ተገኘን?! ከሚሉት metaphysical ጥያቄዎች የሚነሳ ነው.....የዘርፉ ፈላስፋዎች እግዚአብሔር የሚባል አካል የሰውልጅ ተፈጥሮ ነግሳበት በነበረ ጊዜ በአእምሮ እንደ አፅናኝ እንደ ጠባቂ የሚያየውን አባታዊ ምስል ፈጥሮ ማምለክ እንደጀመረ ያስረዱናል....መፅሐፈ ክህደት ላይ ኦሪት ዘምልኪ 1÷26 ላይ "ኑ እግዚአብሔርን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር" ብለው የሰውልጆች ሲማከሩ እናነባለን(postmodernism ስልት)

ኢትዮጵያዊ የቅኔ ሊቅ ተዋነይ ይችን ሀሳባችንን በቀጣዩ ቅኔ ያጠናክርልናል

የአምን ወይገኒ
ኵሉ ዓለም በዘፈጠረ ለሊሁ
ብዙኃን እንዘ ይገንዩ ይስግዱ ቅድሜሁ
ለነጽሮ ዝኒ ነገር እሥራኤል ከመይፍርሑ
ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ
ወ ፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ

ትርጉም

ዓለም ኹሉ እርሱ ራሱ በፈጠረው ያምናል፣ ይገዛልም
ብዙዎች በፊቱ እየተገዙ ይሰግዱለት ዘንድ፣
ይኽንን ነገር ለመመልከት እሥራኤላውያን እንዲፈሩ
ሙሴ ፈጣሪውን ፈጠረ፣
ፈጣሪም እርሱን ፈጠረ”


አዩልኝ:- እስራኤላውያን እንዲፈሩ(ስርዓት እንዲገቡ) ሙሴ ፈጣሪ የሚባል ነገር ፈጠረ....እንዲህ የሚል ጂኒየስ የቅኔ ሊቅ እናንት ኢትዮጵያዊያን በጉያቹ ታቅፋቹ አሁንም ሙሴ ለገዛ ህዝቡ የሰራውን እግዚአብሔር የሚባል የውሸት ፈጣሪ ላይ ተቸንክራቹ ታላዝናላቹ ምስኪናት

አዲዮስ


🔯שלום

የጥበብ - መንገድ

16 Nov, 15:15


በህይወት ኑባሬ ፡ ለከፍታ የገነባው ነው ድልድይ አዳልጦን : ከመተታነንስ አረንቋ ራሳችን እናገኘዋለን ፡፡

በመኖር ፍቅር ተጠምደህ ለአዝማናት የገነባኽው የህልም ማማ ቅንጣት በምትመስል ሰበብ ሲናድ ፡ሲፉረከረክ ታገኘዋለህ፡፡

በይሆናል ጅማሮ ፡ በአዕምሮህ የፈተልከው የሀሳብ ዝሐ ፡ ብል በልቶት የመዳረሻህ ፍኖት ብዙ አድካሚ እና አሰልቺ የህይወት ደፋ ቀና ወስዶት ልም ገላህን ድካም ቢገርፍህም ፡ የህይወት መርህ ሻገር ሲልም ውበት ነው፡፡

እ ና ም አንዳንድ መሸነፍ የሚመስሉ ስኬቶችን መቀብል ማመን አለብህ፡ አለመቻልህን ስታውቅ አታስመስል፡ በመንተልህ ጭቃ ገብተህ ፡አትላቁጥ በእልህኝነት ፡ ስካር ለሌላ የድካም ቋት አት ሰናዳ ፡ በስሁት መንገድ ብርሃን አትፈልግ...ለአዕምሮህ ፡ አለመቻልህን እመንለት ፡ ለልብህ የማይበርድ ፡ህመም ለገላህ የማይሽር ቁስል አትሁንባት ፡፡

በተፈጥሮህ ፡ሁሉምን የመሸከም ብቃት
አልተቸረህምና አንዳንዴ ስታውቅ ዋልጌ ሁን ፡ ንቃት ያጀገነው እብድ...

© የአባ ልጅ ነኝ

የጥበብ - መንገድ

15 Nov, 16:18


አሁን የት ነው ያለነው? 'ከታች' ጥሩ ቢያንስ ዳግመኛ አንወድቅም!🌼


© ዶስቶቭስኪ

የጥበብ - መንገድ

15 Nov, 06:08


የማንነት እውነት !



“You’ll never know who you are unless you shed who you pretend to be. ” ― Vironika Tugaleva


⚡️በዙሪያችን ያለው ደመና በውስጣችን ያለውን ጸሐይ ከልሎታል… የየዕለታችን አመድ የመነሻችንን ፍም አዳፍኖታል… የአስተዳደጋችን ቅኝት የዕይታ አድማሳችንን ኮድኩዶታል፣ የአስተምሯችን ስሪት፣ የየቤተእምነታችን መሰረት፣ የአካባቢ፣ የሃገር፣ የሚዲያና የአብሮ ውሎ ሸንጓችን ጨለማ የማንነታችንን ግዝፈት ውጦታል… ትልቁን ምስል ለማየት ስለተሳነን ባየነው ልክ ራሳችንን ሰርተናል… በምልዓት ማየት ስላልጀመርን ለሽንቁር ማንነት ራሳችንን አሳልፈን ሰጥተናል… ነባሩን ዘዬ ስላልፈተሽን አዲስ መንገድ ማየት አቅቶናል… የነገሩንን ስላመንን የሆነውን መጠየቅ ትተናል… አይቻልም ስላሉን አለመደፈሩን ተቀብለናል… እናም ዛሬ ራስዳሽኑ ማንነት በኮረት ጥላ ውስጥ ተጨልሟል…


የማንነትን ጉዳይ… እንደየ ጥናት መስኩ ሃቲት፣ እንደየ መንግስታቱ ውልደት፣ እንደየ ማሕበረሰቡ ነባር ትውፊት፣ እንደየ ሐይማኖታቱ መፃሕፍት እንጂ እንደ ጥልቁ ማንነታችን ምንነት ለመተንተን ሞክረን አናውቅም… ለኛ ማንነት ማለት ብዙዎች የሚያቀነቅኑት ምንነት ነው – ከየልባችን የምንመክረው ዘላለማዊ ወግ አይደለም… ማንነት ለኛ ከመሰሎቻችን የተዋስነው የአደራ ዕቃ ነው – በነፍሳችን ሹክሹክታ ስምረት የሚሰራ ሁሉአዊ መልክ አይደለም… ማንነት ለኛ ከመሆን በኋላ በሆነ ሁነት ውስጥ የሚቀነበብ ወቅታዊ ነው – ከመሆን በፊት በነበረ፣ ባለና በሚኖር ምንጭ ላይ የቆመ ዘላለማዊ አይደለም…

🔆የልኬታችንን ምልዓተ ዓለምነት እንዳናይ አዚም ያደረገብን ማነው?… የምንጫችንን አልፋ እንዳናውቅ ነገር የሰራብን ማነው?… ከጥልቅነታችን የመሰረት ወለል የነቀለን ማነው?… በአንድነት አውድማችን ላይ እልፍነትን ያበራየው ማነው?… በስክነት ጉባኤያችን ውስጥ ጩኸት የዶለው ማነው?… እውነትን ከምናይበት ማማ ላይ ጽልመት የጋረደብን ማነው?…


‘አንተ ማነህ?’ ላለን ሁሉ ማንነት ያልሆነ ማንነት ስንነግር ቆይተናል… ስማችን ያልሆነ ስም፣ ሃገር ያልሆነ ሃገር፣ ቀለም ያልሆነ ቀለም፣ ልክን የማይገልጽ ልኬት፣ ተናጥሎን የሚሰብክ ማንነት፣ ብስለትን የማይገልጽ ዕድሜ፣ ምንምነትን የሚያረቅ ታሪክ፣ … ወዘተ… በቀቀናዊ ኑረት…


⚡️ከመሆን በፊት የሆንከው መሆን ዘላለማዊ፣ ከመሆን በኋላ የሆንከው ሁነት ጊዜያዊ ነው… ዜግነትህ፣ ብሔርህ፣ የትምህርት ደረጃህ፣ ስራህ፣ መደብህ፣ የትውልድ ቦታህ፣ ቤተሰብህ፣ ሐይማኖትህ… ማናቸውም በ ‘እኔ’ ና ‘የኔ’ ቁናነት የሚሰፈሩ ነገሮችህ ማንነትህ አይደሉም… የትኛውም፣ ከእስከ አልባው ሕዋ በተናጥሎ የሚያስቀምጥህ ሃሳባዊውም ሆነ ቁሳዊ ምንትስ ማንነትህ አይደለም… ያንተ ማንነት የሌላውም ማንነት ነው… የእኔ፣ የእርሱ፣ የእነርሱ የሚባል ማንነት የለም… ማንነት አንድና ዘላለማዊ ነው… ዘላለማዊ ማንነት ስላለህ ዘላለምህ ውስጥ ሞት እንኳ የለም…

🌺 በ’እኔታ’ እና ‘አንተታ’ መገለጥ /Subjective manifestation/ ውስጥ እንመላለስ እንጂ የምንጫችን አንድነት /Oneness/ የሁለንተናችን አንድነት ነው… ይህም በሰው፣ በእንስሳ፣ በተክል፣ በፕላኔት፣ በጠፈር፣ በሕዋ… በሚታየውና በማይታየው ዓለም ውስጥ ባሉ መገለጦች ውስጥ ሁሉ ያለ አንድነት ነው… ሕብረት፣ ጋርዮሽ፣ ጥምረት፣ ሕብራዊነት፣ ትብብር አይደለም አነድ-ነት ነው… አንድ ላይ መሆን አይደለም አንድ ብቻ መሆን ነው… Self ውስጥ ቁጥር የለም… በቃ ‘መሆን’ Being ብቻ ነው ያለው…

💫 ራማና ማሀርሺ እንደነገረን “The Self is beyond duality. If there is one there will also be two. Without one there are no other numbers. The truth is neither one nor two. It is as it is.”

🔆 ማንነት አለኝ የምትለው አይደለም – የሆንከው እራሱ ነው… Possession በማንነት ውስጥ ቦታ የለውም… አንተነትህ ከማንነትህ የተነጠለ አይደለም – ማንነትህ ነው አነተነትህ… ማንነትህ ቅርጽ፣ ቀለም፣ መስፈሪያ፣ ድንበር አልያም ጠገግ የለውም – በሁሉ ያለ፣ በሁሉም የሚኖር ነው…

💫“All that we have to do is to give up identifying the Self with the body, with forms and limits, and then we shall know ourselves as the Self that we always are.” Ramana Maharshi

🌼 አንተ ውስጥ ‘ሌላው’ አለ – ‘ሌላው’ ውስጥም አንተ አለህ… “Quantum Physics reveals thus reveals a basic oneness of the universe” – Erwin Schrödinger
💫 አንስታይን በበኩሉ ይህን ይላል … “A human being is part of the whole, called by us ‘Universe’; a part limited in time and space. He experiences himself, his thoughts and feelings as something separated from the rest—a kind of optical delusion of his consciousness. This delusion is a kind of prison for us, restricting us to our personal desires and to affection for a few persons nearest us. Our task must be to free ourselves from this prison.”- Albert Einstein

🔆 ስለማንነትህ እንዲገባህ ማንንም አትጠይቅ… የማንነትህን ልኬት በሌሎች ግንዛቤ ውስጥም አትሻ… ከራስህ ጋር አውጋ! ወደውስጥህ ተመልከት…

⚡️ ከውጭ የምታየው ሁሉ የውስጥያህ ነጸብራቅ ነው… አንተ ሕዋ ውስጥ ሳይሆን ሕዋው ነው አንተ ውስጥ ያለው እንደማለት…

💫“You are not IN the universe; you ARE the universe, an intrinsic part of it. Ultimately you are not a person, but a focal point where the universe is becoming conscious of itself. What an amazing miracle.” ― Eckhart Tolle, ‘A New Earth’

🔆ነፍስህ እስካላዜመችው ማንነት አይገባም… ከአዕምሮ ባርነት እስካልተላቀቅህ መሆን አይገለጽም… ወደ ውስጥ እስካልዘለቅህ ከራስህ ጋር አትገናኝም

ልብህን ጠይቅ ይመለስልሃል!! የማንኛውም ጥያቄህ መልስ ማንነትህ ውስጥ አለ… ማንነትህን የማወቅህ ቅጽበት ውስጥ ደግሞ ደስታ – ዘላለማዊ ደስታ… እ-ፎ-ይ-ታ!!!

መልካም አሁን
©ደምስ ሰይፉ

የጥበብ - መንገድ

15 Nov, 04:30


ከእለታት አንድ ቀን ሙላ ናስሩዲን በሰፈሩ ከሚገኝ ሱቅ በመሄድ ባለሱቁን ፦ " ቆዳ ይኖርሃል?" ሲል ጠየቀው
ባለሱቁም ፦ "አለኝ" አለ
ናስሩዲንም ፦ "ሚስማርስ አለህ?"ሲል ጠየቀ
ባለሱቁም ፦" አዎ አለኝ "ሲል ድጋሜ መለሰ
ናስሩዲንም አሁንም ጠየቀ ፦"ክርስ አለህ?"አለው
ባለሱቁም ፦"ክር አለኝ" አለ
ናስሩዲን ፦"መርፌስ አለህ?" ሲል ጠየቀ
"አዎ አለኝ " አለ ባለሱቁ
ናስሩዲን አንዲህ ሲል ተናገረ ፦ " ታድያ ጫማ እየሠፋህ ለምን አትሸጥም?" በማለት እየሳቀ ጥሎት ሄደ ።


መልካም - ቀን 🌻

የጥበብ - መንገድ

14 Nov, 16:51


' የሞት ~ ሞታችን

አንዳንዴ ያለብርቱ ጉዳይ ተቀጣጥረን
እንተቃቀፍ ፡፡
ከዚህ ቀደም ለሰራናቸው
ላልሰራናቸው ..
ስህተት ~ መዛነፎች
ጥፋት ~ መተላለፎች
« እንባባል! »
ሁሉም ይቅር !
የጥላቻው ደንበር ይፍረስ
ጽዋ እናንሳ በፍቅር እንካስ ፡፡
አሜን ፫

በጥቅሉ...
« መኖር አኳርፎን »
ስሜት አስተዛዝኖን
የቋጠርናቸውን ቂም ርዝራዦች
ስብራት ህመሞች ፡፡
ሁሉንም ጥፋት ፥ አቅለልን ችላ በለን
አውጥተን እናስጣቸው
በአዲስ ፍቅር እንተካቸው፡፡

« በህይወት ፍቅር ተለክፈን!
ልንደሰት..ስንቸኩል ተደናቅፈን
የመታንን እንቅፋት አነሰሳተን
ጥርጊያውን እናሳምር ፡፡
ልቤ ወደ ልብሽ ቅጽር ሲመጣ አይበለው ግር ፡፡
..... ....... .....
« ነይ የኔ ውድ! »
ዳር አትቁሚ
መንገድ ፍኖቱን አሳምሪ
ዝምታሽን ስበሪ ፡፡
ሁሉም ያልፋል
ህመም ድብርቱ
ብስጭቱ..
ብለን የጣልነው ተስፋ
ቢረዝም ቀናቱ ፡፡
ነገ ላይ የምንኮራባቸው
ብርሃናዊ ህልሞች አሉን ና
እንታደስ በተንሳዔው እንደ ገና!
« ነይ የኔ ጀንበር ! »
እንደ ጽሐይ ልሙቅሽ
ገላየ መኸል ንደጅ ና ልፈወስብሽ
ነይ የኔ ሳቅ..
እድሜ የበላው ግንድ ቁጭ ብለን
በልብ ብርሃን እንተያይ
እንሽኮርመም እንጠቃቀስ
እንታደም !
ወንዙ ሲወርድ
ንፋስ ሲነፍ ስ
ልባችን ይበላት ደስ
ከድካም ሸሽጊኝ
ከሞት ጥልማሞት አስቀሪኝ
ብርሃን ሽ ይረፍብኝ
ከማጣት ስካር
አውጥተሽ
አትረፍርፊኝ
ምድረ በዳ ነኝ
..አለምልሚኝ ፡፡
እናም..
የኔ ፍቅር!
« ማታ አመሻሽ ላይ ካፊያ ሲጥል
በደመናው መኸል ቢራቢሮ ስትላጋ
ከጫፍ ጫፍ
ከደንበር ደንበር ስታካልል
በድንግልና አፅም ..
አበቦች ተሞሽረው
ጽጌ ለብሰው
ማህሌት ምስጋና
ሲዘምሩ ..
ሌቱም ይንጋ
ይለፍብን ትዝታን ስናውጋ

..የሞት.. ሞታችን.. እንተቃቀፍ ፤
ከፍለን እንብረር ፡ ምንም ብንሆን መቃብር አፋፍ ፡፡

©የአባ ልጅ (ወረታው) !

የጥበብ - መንገድ

13 Nov, 10:19


« ዋሸራ የመጽሐፍት መደብር ፡ የሚፈልጉትን የፍልስፍና ፡የስነ ልቦና፡ የታሪክ ፡ እንዲሁም የልቦለድ መጽሐፍ እኛ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን ፡፡


አድራሻችን መጎብኘት ብትፈልጉ ፡ አዲስ አበባ ፡ አምስት ኪሎ ከዩንቨርስቲው ፊት ለፊት (ገንዘብ ሚኒስቴር ገባ ብሎ) እንገኛለን ፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡-

📲+251952075233
ይደውሉልን!!
ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን
ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ📚

https://t.me/washerabook

የጥበብ - መንገድ

12 Nov, 13:38


Dostoevsky, the only psychologist from whom I’ve anything to learn.
― Friedrich Nietzsche

Dostoevsky gives me more than any scientist, more than Gauss.
― Albert Einstein

The real nineteenth century prophet was Dostoevsky, not Karl Marx.
― Albert Camus


« ፍላጎቴ የእውነት ውብ የሆነች ን ነፍስ በቃላት መሳል ነው ፡፡ »
...

መልካም ልደት Dostoevsky❤️
💐

የጥበብ - መንገድ

12 Nov, 04:16


_ጥሩ ቀናቶች መሃል

መልካም የአትክልት ስፍራዎች ውስጥ
ለሰዎቻችን
ህይወትን
ኖረናል ብለን እናውራ
ወንዝ ዳር ወርደን
ፈረስ እየጋለብን
ውብ ቆንጃጅቶችን እንጥራ።

እንደባደብ
እንሳደብ
እንጠጣ
እናጭስ
ጮክ ብለን እንናገር
ውሻን በድንጋይ እንልከፍ
እድሜ ሳያልፍብን
ህይወትን ኖረን እንለፍ።

ግጥም እናንብብ
ቡና እንጠጣ
እንተቃቀፍ
ቀን አንደ ቀኑ ይለፍ።
ሎሚ እንምጠጥ
ብርቱካን ጭማቂ እንስራ
ዋሻዎች ውስጥ ራቁታችንን ሆነን
ብዙ ራቁቶችን ወደ ዳንስ እንምራ።

ሴት እንይ
ከንፈር እንሳም
ጥርስ ምላስ ይገጫጩ
ሰዎች ታዝበውን ይንጫጩ
እግዜሩም
ያሻውን የወደደውን ይበል
ሁሉን ሆነን
ኖረናል ብቻ እንበል።

አታልፍምና ህይወት ከተረት
ብቻ ብዙ ተረት እንፍጠር
እጅ ለ እጅ ተያይዘን
ውበት ያለችበት እንብረር።

ብስክሌት እንንዳ
ጥሩ ሲኒማዎች እንሂድ
በድፍረት አንዷን እንልከፋት
ከፈቀደች እጆቿን ተጠግተን እንያዛት።
ብቻ ተረት መፍጠር እንዳናቆም
ቆንጆ ተረት
እውነት የሚመስለውን
ህይወት የሚሸተውን
ኖሬያለሁ የምንለውን...

መንገድ ዳር ሻዪ እንጠጣ
እንገባበዝ ከማናውቀው ጋር
የቡናይቷን ልጅ እናስቃትና
ሲጋራ ለኩሰን ህይወትን ለሳቅ እንዳር።
እንኮልኮል
መንገድ ላይ ወጥተን እንደንስ
ህይወትን መጠየቅ ትተን
ኖረናል ብለን እንተንፍስ።

ፀደይህ ስትስቅ
አፍታ እንዳትወስድ
ቆንጆ መሳምን ጉንጯ ላይ ሳማት
እንብርቷ ስር ውረድና
ውበትን አሪቋን እያት።

ኑራትና ይህችን ህይወት
ኖሬያለሁ በልና ሙታት
ቢራ-ቢሮ ሆነህ ብቻ
አበባ ውስጥ ስመሃት ጥፋት።

ሳቅና ጮክ ብለህ
ሮጠህ እሳት ውስጥ ውደቅ
በልብህ ፀደይ እያየህ
ውበት ውስጥ ተቃጥለህ እለቅ።

ብቻ ቆንጆ ተረት ፍጠር...
ውበት ፣ ነፃነት ፣ ሳቅ ፣ እውነት ... ያለበትን
ኖረህ የምታልፍበትን
ኖሬያለሁ የምትልበትን።

©Nazmi Nahom

የጥበብ - መንገድ

11 Nov, 16:24


የኔዋ ንጋት ኮኮብ ግን ከጎኔ ትጠፋለች ፡፡ወደ እኩለ ሌሊት ክንዴን ተንተርሳ እጉያዬ ላይ እንቅልፍ ሽልብ አድርጓታል ፡እኔ ግን መንፈሴ አልረጋጋ አለ ፡እንቅልፉም ራቀኝ ፡፡በልስላሴ እና በቀስታ ጸጉርዋን ፊትዋን እየዳሰስኩ ፡የኢስክ ኩለን ቀላይ በተመስጦ ፡በአድናቆት ዓይኖቸን ተክዬ አይ ጀመር ፡እንዳይነጋ የለም ፡መሬት ነጋ ፡፡

©የነበረው እንዳልነበረ
ዘመን አይሽሬው
የራሻያ መጽሐፍ ❤️📚

የጥበብ - መንገድ

11 Nov, 13:33


ፍቅር መራር ትዝታዎቹን አስታቅፎህ እብስ ብሎ ይጠፋል…

በፍቅር ዘንድ … ትላንት ወይም ዛሬ፣

ዛሬ ወይም ነገ…እዚህ ወይም እዚያ ብሎ ነገር የለም፡፡

ሁሉም ወቅቶች የፍቅር ወቅቶች ናቸው፡፡ የትኛውም ቦታ ቢሆን ለፍቅር ቤተ መቅደስነት የተገባ ክቡር ነው፡፡

ፍቅርን … ወሰንም ሆነ ዳር ድንበር

ካቴናም ሆነ የተዘጋ በር አይገድበውም፡፡

የትኛውም መሰናክል ጉዞውን ያሰናከለው ፍቅርም በተቀደሰው የፍቅር ስም ለመጠራት ባልተገባው፡፡

ዘወትር፣ ፍቅር ዕውር ነው ብላችሁ ስታወሩ እሰማለሁ፡፡ … አዎን … አፍቃሪ በተፈቃሪው ላይ አንዳችም እንከን አያይም ማለታችሁ ነው፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ … ይሄ ዓይነት አለማየት የማየት ከፍታ ጫፍ ነው፡፡

በምንም ነገር ላይ እንከን አታዩ ዘንድ ምነው ሁሌ በታወራችሁ፡፡


አይይ … የፍቅር ዓይኖችማ … ንፁህ፣ የጠሩና ሰርስረው የሚያዩ ብሌኖች ናቸው፡፡ ስለዚህም ምንም እንከን አያዩም፡፡

አዎን … ፍቅር ዓይናችሁን ሲያበራው … ያኔ … ለፍቅራችሁ ያልተገባ የቱንም እክል አታዩም፡፡ በዕርግጥም፣ ፍቅር አልባ ሸውራራ ዓይን ብቻ ነው በሌሎች ላይ እንከን ፍለጋ የሚተጋ፡፡ የትኛውም የሚያያቸው እንከኖችም … የሌላም ሳይሆን የራሱ ናቸው፡፡


The book of midrad

በሚካዔል ኔይማ

ትርጉም -ግሩም ተበጀ

የጥበብ - መንገድ

10 Nov, 12:54


ድብብቆሽ እንጫወት?! እኔ ልብ ውስጥ ከተደበቅሽ አንቺን ማግኘት አይከብድም ። ከራስሽ ቅርፊት ጀርባ ከተደበቅሽ ግን ማንም አንቺን በመፈለግ አይጠቀምም።

©ካህሊል ጅብራን ❤️

የጥበብ - መንገድ

09 Nov, 15:58


ጥንቆላ፡ አምልኮት እና ስርአት

Based on Philosophical Point of views



በሰውልጅ ቀደመት ታሪክ ውስጥ  ከፍተኛ ድርሻ ይዘው የሚገኙ ሦስት ኃይላተ ሰብ ናቸው ጥንቆላ ፡አምልኮ እና ስርአት[ስርየት]።ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሰው ልጅ ከነበረው አጠቃላይ  የመረዳት ንቃት ማነስ እንዲሁም ለማይታዩ አካላት[መለኮታዊ ለሚላቸው(Superstition)] ከፍተኛ ቦታን ሰጥቷ ሲራቀቅበት እንዲሁም ሲያመልክበት እዚህ ያለንበት ደረጃ ደርሷል።

ብዙ ሰዎች  በትረ ኃይሉን ኃይማኖት የጨበጠ ጊዜ¹ እነዚህ ነገሮች እንደጀመሩ ያስባሉ።እውነታው ግን ይሄ ነው! የሰውልጅ ታሪክ «ሀ» ብሎ የጀመረ ሰአት የጀመሩ ናቸው።እንደውም በተቃራኒው በዘመነ ጽልመት እየተዳከሙ የመጡትንም እንዲሁም የሮማን ካቶሊክ ቸርች አብዛኞቹን በፀረ ክርስትናዊ ምልከታ ግድያ የፈረደችባቸው ጊዜያት ናቸው።

በመጀመሪያ ሀሳቤን ለማስረዳት በእነዚህ ሶስት ተመሳሳይ የሚመስሉን ነገርግን የተለያዩ ቃላት ውቅርን በመፍታት ልጀምር፥

ጥንቆላ[Witch]: ጥቁር አስማት[Black Magic] እና መናፍስት መጥራት[Summoning spirits] ላይ ያተኮረ በሰውልጅ የህይወት ዳራ ውስጥ ጣልቃ ገብነት በመፍጠር ለውጥ ለማምጣት የሚደረግ ነገር።

አምልኮ[occult]: ስለመናፍስት፡የሰውልጅ እውነተኛ መንፈሳዊ ማንነት እንዲሁም ስለተለያዩ ኃይላተ ተፈጥሮ[ነጭ አስማት እና ጥቁር አስማት] የሚያጠና ሳይንስ ነው።ከሜታፊዚክሱ እና ፓራሳይኮሎጂ ጋር ከፍተኛ ተመሳስሎ አለው[በዚህ አጋጣሚ! ዘመናዊው ሳይንስ በራሱ በዚህ ስር የሚመደብ ነው]

ስርአት[Ritual]:ማንኛውም የታቀደ ተግባር ለማንኛውም ነገር ሊደረግ የሚችል በሰዎች መሰባሰብ የሚከውን ነጭ አስማታዊ ስርአት። ባህላዊ፡ ሊሆን አልያ ፖለቲካዊ[የምርጫ ሂደት Ritual ነው!]ወይም ኃይማኖታዊ ሊሆኑ ይችላል በዚህ ይካተታሉ።
እዚህ ላይ እርቅ ከፈጠረን ፍልስፍና በእነዚህ ሶስት ኃይላተ ንቃት ላይ የነበሯት ጉልህ ሚና እንመልከት።



Philosophy And Witch Teaching

በየትኛውም ሰይጣናዊ አምልኮ[Black Magic] ውስጥ ወይም አስተሳሰብ ውስጥ የምናገኘው ነገር እጅግ የተዳከመ የፍልስፍ እንቅስቃሴ ሲሆን አምልኮቱ ካረቀቁት በቀር ተከታዮች ስራቸው በሙሉ ድምፅ ልምምዱን ማፅደቅ ብቻ ነው።በርግጥ ከቀደምት አባቶቻቸው የተማሩን ነገር ነበር እነሱ የሚተገብሩት አንዳንዶቹ ግን ፍልስፍናን እንደመራቀቂያ መሳሪያ በመጠቀም ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብተው ነበር።ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ነገር  የእነቶማስ ሆብስ እና አርስቶትል ፍልስፍና ሀሳብ እና  አንድምታ ከጥንቆላ አስተምህሮ ጋር ንክኪ የነበረው መሆኑ ነው።የፕሌቶን ፍልስፍና[በተለይ Existence of the two worlds] አጥብቀው ይወዱታል።አንዴ ከተነሳ ላይቀር በአለም ላይ እጅግ ተፈላጊ ስለነበረው የሰለሞን ቀለበት(✡️) ማንሳቱ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል። ሰለሞን ከእግዚአብሔር ከተቀበለው ጥበብ መብዛት የተነሳ ሰባ ሁለት[72] ዋና ዋና የመናፍስት ገዢ መሪዎች ላይ ስልጣን  በቀለበቱ በኩል ያገኘ እና ቀለበቱ የመናፍስቱን መሳቢያ ጠልሰም[በእኛ አጠራር መርብበተ-ሰለሞን]  በምልክትነት እንደያዘ ይታመናል።ይሄን ቀለበት ማግኘት ዋንኛ የጥንቆላ Objective Goal ነበር።



Philosophy Science $ Occult

እመኑኝ! ሳይንስ የሚመስጣቹ ሰዎች ይሄኛውን ዘርፍ ትወዱታላቹ።በአይሁድ እምነት ውስጥ በነበረው ሚስጥራዊ ትምርህት ካባላ[Kabbalah]፤በግሪክ:በግብፅ እንዲሁ ሀገራችንን ጨምሮ  አጠቃላይ የአለም እምነቶች ውስጥ የገባው ሄርሜቲዝም [ኢትዮጵያዊው ሄኖክ] እና በስነ-ቅመማው ወይም አልኬሚ [Alchemy] ሚስጥራዊ አስተምሮች በሙሉ በከፍተኛ መልኩ ፍልስፍና የተጠቀሙ ሲሆን በአልኬሚው እንደነዚሞስ በሄርሜቲዝ ሙሉ በሙሉ Philosophical Aspect of Natural Existence  ስለነበረ በሙሉ።
በካባላው ውስጥ የአይሁድ ጠቢባን ፍልስፍና የአፍ መቻቸው ነበረ።ከእነ ዲሞክራተስ:ፕሌቶ:ታለስ:አንክሲማንደር አናክሲማነሳ:ፓራሜንደስ ወደኢል ደግሞ ዜኖ[Zeno of Elie] ከመሳሰሉትን ጋር ከፍተኛ ተመሳሳይ ነጥቦች ነበሯቸው። ዘመናዊ ሳይንስ አብዛኛው ምርምር እና ጥናት የወሰደው ከካባላ ትምህርቶች ነው።
አንደሰ ሁለቱን ለመጥቀስ ያህል፥
   1]Concept of Atom[የአተም ምንነት]
   2]የተፈጥሮ ህግ እና የሰው ልጅ ምንነት[ከሳይንስ አንፃር]
   3]የአንስታይን አንፃራዊ ህግ[Relativity Theory]
   4]የኳንተም ፊዚክስ ምርምሮች

ካባላ[Kabbalah] ወደእኛ ሀገር አስተምህሮቱን ስናመጣው ከ«ባህረ ሀሳብ» ጋር አንድ ነው[ማን ከማን ወሰደ ነጥቤ አይደለም!]


Philosophy Under  Alchemy
ይሄ ዘርፍ ላይ ደግሞ የኬሚካል ቅመማ፣ብረትን ወደ ወርቅ የመቀየር ሂደት ሌሎች የእፀዋት እና የከበሩ ዲንጋዮች ምርምር በዋናነት መርሁ ያደረ ሲሆን በግብፅ መነሻውን አድርጎ  በግሪክ በኩል ቻይና፡ህንድ እና አረብ እንዲሁም ሌሎች ጋር የደረሰ አለምአቀፋዊ ሚስጥራዊ አስተምህሮ ነው።አልኬሚ ብረትን ወደ ወርቅ የመቀየሩ ነገር በቀጥታ የሚፈታ አደለም።ፍልስፍና በሙስሊም ኡለማዎች[Golden Age of Islamic] ዘንድ እና በህንድ መንፈሳዊ እምነቶች[Hinduism,Zen Buddhism]በኩል ሞገስ ያገኘች ሰሞን ነበር አልሜኬ ከፈጣሪ የተበረከተላቸው። አልኬሜ እንደፍልስፍና የተፈጥሮ ንጥረ አካላት እና ሰው እንዴት እንደሚተሳሰሩ ስራዬ ብሎ ያጠናል።ሰው የንቃቱ እና የመረዳቱ ደረጃው ከዴካርት በላይ ያስጨንቀዋል።
በዘመነ ዳግም ውልደት ታዋቂ የነበሩ አልኬሚስቶች ኒውተን እና ተከታዮቹ[Calculase Based Universe] ፣ከአረብ ሒሳብ እና አስትሮኖሚ ምሁራን አቬሴናን እና ጅላል አል-ሩሚ እንዲሁም አቡ ሙሳ፣ ወደ ህንድ በዋናነት ኒታይኒታ ሲድሀ እና ዮጊ ቬማናን  ፣ወደ ቻይና ሰን ፑ-ሂ[Sun Pu-Eh] እና ኮ-ሆንግ[Ko Hong]  ወደ ግብፅ ፈላስፎቹ በሙሉ በዚህ ተጠምደው ነበር ፤ወደ ግሪክ በዋናነት ዞሲሞስ እና አርስቶትል ወደእኛም ሀገር ደግሞ ሙሉበሙሉ በሚባል ደረጃ የነበረ ነገርግን ብረትን ወደ ወርቅ ከመቀየሩ በላይ ዋና ማእከሉ የእፀዋት መሰል ቅመማ ላይ ትኩረቱ ያደረገ ሆነ።



የአብርሃም ኃይማኖቶችን ጨምሮ ሌሎች ጥንታዊው ሆነ ዘመናዊ ኃይማኖት  ነገረ መለኮታ ከእነዚ በመነጨ አስተምህሮ የተቀረፀ ነው።ኒቺ በOn the Genealogy of Morality² መፅሀፉ በኩል አጠቃላይ እነዚህ ዳራ ለመጥቀስ ሞግሯል።የአምልኮ እና  የፍካሬ ከዋክብ ተመራማሪ የሆነው  ማንሊ ፒ.ሆል «The Secret Teaching of All Religion³» መፅሀፉን እንድታነቡ እየጋበዝኩ ሀተታዬን እቋጫለሁ።




___
© ዋቢ መጽሐፍት 📚

¹ Dark Age[When Christianity of Thinking Mainly Dominants]
² On the Genealogy of Morality
Book by Friedrich Nietzsche
³ The secret Teaching of All Religion By Manly P.Hall

© ፍልስፍና

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

05 Nov, 05:12


© የህይወት ትርጉም በተለያዩ ፈላስፎች

1. የበለጠ ለማወቅ ጣር Platonism 📚
2. መልካም ሁን Aristotelianism 🤞
3. ራስህን ቻል cynicism 💪
4. ዛሬ ተደሰት ነገ ለራሱ ይጨነቅ hedonism 🥂
5. ራስህን ከስቃይ አግልል epicureanism 🏖️
6. ምክንያታዊ ሁን መቀየር ማትችለው ነገር አያስጨንቅህ stoicism 🔍
7. የግለሰብ ነጻነትን አክብር classical liberalism 🙋
8. ሌሎች እንዲያደርጉልህ ምትፍለገውን ነገር ለሌሎች አድርግ kantianism

9. የምትፍለገውን ነገር አድርግ ምክንያቱም ህይወት ትርጉም የለውም nihilism

10. ሃሳብህ ላይ ሳይሆን ተግባርህ ላይ ትኩረት አድርግ - pragmatism

11. የፈጣሪህን አላማ ኑር- Theism

12. ያንተ ውስኔ ያንተን ህይወት ይመራል -Existentialism ⚖️

13.የህይወት ትርጉም ምንድነው እያልክ አትፈላሰፍ፣ዝም ብለህ ኑር- Absurdism

14. ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው - humanism

15. ህይወት ትርጉም የለውም አነተ ትርጉም ካልሰጠኸው
-logical positivism 🤹

16. ሰዎችን ሁሉ እኩል ውደድ -Mohsim

17. ከቅንጦት የጸዳ ተራ ህይወት የበለጠ ትርጉም አለው - Confucianism

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

04 Nov, 17:04


በዚህ ዓይነት ሥራውም ቆመ፡፡ ሰውም እሱን ተፀየፈው፡፡ አስፈሪ፣ ቀፋፊ፣ አቅመቢስ ፍጥረት ሆኖ ቀረ፡፡ ቤተሰቡን ድጋሚ መከራ ወረሰው፡፡ መጀመሪያ ድንገት ተመልሶ ሰው ከሆነ፣ ዕቃው አይነካበት ይባል ነበር፡፡ ይጠነቀቁለት ነበር፡፡ የሚፈልገው የበሰበሰ ነገር ነው፡፡ እንደ እርጎ ያለ፣ እንደ ፍርፋሪ ያለ፣ የቆሸሸ ነገር ነው የሚፈልገው፡፡ በበር ሥር አሾልከው ያቀርቡለታል፡፡

ቤተሰቡ በእርሱ የተነሳ ታመመ፡፡ ታወከ፡፡ ሰለቸ፡፡ በኋላ ክፍሉ የቆሸሹ ዕቃዎች መጣያ ሆነ፡፡ ክፍሉንም እርሱንም አቧራ አለበሳቸው፡፡ ቁስል ወረሰው፡፡ አባቱ የወረወረበት የአፕል ፍሬ ጀርባው ላይ ተሰክቶ እዚያው በሰበሰ፡፡ ከሰው ቁጥጥር ውጭ ሆነ፡፡ እህቱም ደከማት፡፡

በመጨረሻ እንደሚናከስ አስቀያሚ አውሬ፣ በር ከፈት አድርጋ በእግሯ የቆሸሸ ምግቧን ትገፋለታለች፡፡ እሱ ግን አሁንም እንደ ሰው ያስባል፡፡ ሁሉንም ያፈቅራቸዋል፡፡ በደረሰበት ነገር ይብሰከሰካል፡፡ እንዴት ብሎ እንደሚያግዛቸው ያስባል፡፡

አንድ ቀን ሊረዳቸው፣ ሊከላከልላቸው ወጣ፡፡ ጭራሽ ቤታቸውን የተከራዩት ሰዎች እግሬ አውጭኝ ብለው ወጡ፡፡ እህቱ በመጨረሻ:-

"ይሄ አውሬ ወንድማችን ግሪጎር አይደለም፡፡ እሱ ቢሆን ኖሮ በደግነቱ፣ በውበቱ፣ በግርማው፣ በመመኪያነቱ እያስታውስነው እንድንኖር ራሱን ከዚህ ያጠፋና ወደሚሄድበት ይሄድ ነበር፡፡ ይሄ ጭራቅ ወንድሜ አይደለም፡፡ እንግደለውና እንገላገል"

አለች፡፡ መረራት፡፡ አልቻለችም፡፡ አባትየውም ሀሳቡን ደገፉ፡፡ እናትየው የሚሉት፣ የሚወስኑት ግራ ገባቸው፡፡

ብዙ ውርደቶችን፣ ብዙ የቤት ውስጥ እስሮችን፣ ብዙ መፀየፎችን፣ ብዙ አለመፈለጎችን፣ ብዙ የነደዱ፣ የከሰሉ፣ የተከፉ ልቦችን ኑሮ፣ በጣሪያው ሥር ካየ በኋላ.. ግሪጎር በመጨረሻ... የአሮጌ ዕቃ መጣያ ወደተደረገው ጉሮኖ ክፍሉ ገብቶ የሚቀርብለትን ትራፊ አልበላም ይላል፡፡ ቀናቶች ቆዩ፡፡ ደንታ የሰጠው አልነበረም፡፡ ሰውነቱ ደከመ፡፡ እና እዚያው መሬቱ ላይ ደርቆ ተገኘ፡፡ ሞተ፡፡

ሲሞት፣ አባትየው ተመስገን ፈጣሪ፣ ስለገላገልከን ብሎ አማተበ፡፡ እናትና እህትየውም አማተቡ፡፡ ፈጣሪን አመሰገኑ፡፡ ከረዥም ጊዜ በኋላ፣ ቤተሰቦቹ ተያይዘው፣ የመጀመሪያውን ሽርሽራቸውን ወጡ፡፡

ትሰማኛለህ ወይ? አለመፈለግ ምንድነው? አስበኸው ታውቃለህ? የግድ ወደ ቅምቡርስነት፣ ወደበረሮነት እስክትቀየር አትጠብቀው፡፡ አስበው፡፡ እና አንዳንዴም ደስ ተሰኝ፡፡ ስለተፈለግክ፡፡ በሰዎች ዘንድ እንደ ሰው ስለተቆጠርክ፡፡ ግን አስበው፡፡ እንዳትረሳው፡፡ በመፈለጎች ሁሉ ውስጥ ልብ የማንለው፣ ያደፈጠ፣ ጊዜን የሚጠብቅ፣ ጊዜ የከለለው፣ ፈጣሪ የከለለው፣ አስቀያሚ አለመፈለግም አለ፡፡

ፍራንዝ ካፍካ፣ ይሄንን ድርሰት በጻፈ በ12 ዓመቱ፣ በዘመኑ ተላላፊ በመሆኑ የተነሳ፣ እና መድኃኒትም ያልተገኘለት በመሆኑ፣ እጅግ አስፈሪ በነበረው የሣንባ ህመም ተቀሰፈ፡፡ እና ወደ ቤተሰቦቹ ቤት ቀኬውን ይዞ ገባ፡፡ ደረቅ ሣል እያሳለ፡፡ የቻሉትን ተንከባከቡት፡፡ ካለ እነርሱ ምን መሄጃ አለው?

ካፍካም እህት አለችው፡፡ ሁለት እህቶች፡፡ ቱበርክሎሲሱ ወደእነሱ እንዳይተላለፍባቸው፣ አፍና አፍንጫቸውን በጨርቅ ግጥም አድርገው ወደ ክፍሉ ሳህን ያቀብሉታል፡፡ ሲጨርስ በተመሳሳይ የኒንጃ ስታይል ሳህኑን ይወስዳሉ፡፡ ብቻውን ተፈርቶ፣ ሰው ተጠንቅቆት፣ በመጨረሻ ምግብ አልበላ ብሎት፣ ጉሮሮው ተዘግቶ፣ እና የእሱም አልበላም፣ አልጠጣም ውሳኔ ተጨምሮበት፣ ይህቺን ምድር፣ በጻፋት መልኩ ተሰናበታት፡፡

ካፍካን አንብበው፡፡ ግን በራስህ ውስጥ እስከዛሬ ያላገኘሃቸውን ነገሮች፣ በዚህች ዓለምና ነዋሪዎቿ እንዲሁም በእግዜርህም ጭምር ላይ ያላገኘሃቸውን ነገሮች የመጋፈጥ ድፍረቱ ካለህ ነው፡፡ ከሌለህ አትቅረበው፡፡ ህይወት ውብ ነች፡፡ ሰዎችም የሚሠሩትን ያውቃሉ፡፡ ደግነትና ክፉነትም የተለያዩ ናቸው፡፡ ብለህ እመን፡፡

አለዚያ ግን እንደ ኒቼ - ከክፋትና ከጥሩነትም በላይ ያለውን ነገር ለማየት ከደፈርክ - ካፍካ ያየውን ለማየት ከፈቀድክ - ራስህም መኖሩን የማታውቀውን፣ ሰዎች ሁሉ ውስጣቸው እንዳለ የማያውቁትን እንግዳ ማንነትና ተፈጥሮ ለመዳሰስ፣ ለማየት ከደፈርክ - ካፍካን ቀረብ ብለህ የሚለውን ስማው - እና ይለይልህ! ይውጣልህ! - እልሃለሁ፡፡ ወዶ እንዲቃጠልለት አልተናዘዘም፡፡ ማወቅ መረገም ነው፡፡


© Assaf Hailu

🔯שלום

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

04 Nov, 17:04


ከፍልስፍና ዓለም :
አለመፈለግ! (በፍራንዝ ካፍካ)

Franz Kafka, «The Metamorphosis» (1912)

በህይወትህ ያለመፈለግ ስሜት ተሰምቶህ ያውቃል? ከሰው የመነጠል፡፡ ፊት የመነሳት ስሜት፡፡ በሰው ፊት መገረፍን ታውቀዋለህ? ከህብረተሰብ መነጠልንስ? በሀገር መረሳትን፣ መገፋትን፣ መተፋትን ቀምሰኸው ታውቃለህ?

አግኝተህ፣ ተከብረህ፣ ተወደህ፣ ሰዎች በመልካም ፊት ጎንበስ ቀና ብለው ተቀብለውህ ያውቃሉ? ከዚያ ደግሞ እነዚያው ሰዎች ወደየት እንሂድ እሱን የማናይበት ብለው ፊታቸውን አጥቁረውብሃል? ሁለመናህ አስቀይሞ፣ መኖርህ ሰዎችን ረብሾ፣ አቅለሽልሾ፣ ከሰዎች ሁሉ ትዕግሥት በላይ ሆነህ፣ የቀረበህን ሁሉ አጥወልውለህ... መፈጠርህን ጠልተህ ታውቃለህ?

ውበትህ ረግፎ፣ ክብርህ ተዋርዶ፣ ከሰውነት ተራ ወርደህ፣ ተዋርደህ፣ ውብ አካልህን አንዳች ቁስል ወርሶት፣ ሰው ከሩቁ ፊቱን የሚያዞርበት ሰው ሆነህ ታውቃለህ? የገዛ ቤተሰብህ ምነው በሞተልንና በተገላገልነው ብለው ተማረውብህ ያውቃሉ? እግዜርም ከሰው ጋር ተባብሮ ፊቱን አዙሮብህ ቀርቶ ያውቃል?

ብዙ የምትመኝላት እህትህ፣ ብዙ ያሰብክለት ወንድምህ፣ ከአቅሙ በላይ ሆነህበት፣ ካንተ ጋር አብሮ በመፈጠሩ መሬት ብትውጠው ተመኝቶ፣ በሰው እንዳትታወቅበት ከሰው ፊት አርቆ ሸሽጎህ ያውቃል? ለገዛ አባትህ ከጥላቻም፣ ከመፀየፍም፣ ከቃላትም በላይ ሆነህበት ታውቃለህ? ለገዛ እናትህ ለማየት የምትዘገንን፣ የፀፀት ምንጭ፣ የእንባ ምንጭ፣ የእርግማን ማስታወሻ የመሆንን ክፉ ዕጣ ፈንታ ቀምሰኸዋል?

እንደ ሰው ያለመቆጠርን፣ ከቆሻሻ ያነስክ ሆነህ የመገኘትን፣ እንደ ትኋን የመጨፍለቅን፣ እንደ በረሮ የመረገጥን፣ እንደ ዝንብ እሽሽሽ የመባልን... አሳፋሪውን የሰውን ልጅ የውዳቂነት ዕጣፈንታ አወራርደኸው ታውቃለህ? ለሰዎች ጌጥ የነበርከው፣ የተወደድከው፣ ብርቅ፣ ድንቅ መመኪያ የነበርከው አንተነትህ ሁሉም ጠፍቶ... ለቤተሰቦችህ እከክ፣ ለወዳጆችህ የተዝለገለግክ ቀንድአውጣ፣ ለቀረበህ ሁሉ የምታስፈራ ጭራቅ ሆነህ ተገኝተህ ታውቃለህ?

አስከፊ ነው፡፡ አስፈሪ ነው፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ያለመፈለግን ሥቃይ የሚገልጽ አቻ ቃል በሰው ልጆች ዘንድ የለም፡፡ እነዚህን ስሜቶች የሚገልጽ ግን አንድ መጽሐፍ አለ፡፡ እነዚህን አስከፊ ያለመፈለግ ሲዖሎች በእውነተኛ ህይወቱም ያስተናገደ፣ ግን ከማስተናገዱም በፊት አስቀድሞ የገዛ ዕጣፈንታውን አስቀድሞ ተንብዮ የጻፈ፣ አንድ ደራሲ አለ፡፡ ፍራንዝ ካፍካ፡፡

ካፍካ በፕራግ፣ በአሁኗ ቼክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ የኖረ፣ ጀርመንኛ ተንጋሪ፣ ጂዊሽ ነው፡፡ በ1924 በእነሱ አቆጣጠር ገና በ40 ዓመቱ የሞተው፡፡ ጠበቃ ነበር፡፡ ዶክተር ነበር፡፡ የጋዜጦችና ጆርናሎች ፀሐፊ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ደራሲ ነበር፡፡ ከጽሁፎቹ 90 በመቶውን በገዛ እጁ እሳት ለኩሶ ያቃጠለ ነው፡፡

ሲሞት ለኑዛዜ አስፈጻሚ ወዳጁ ብሮድ ሁሉንም ሥራዎቼን ለቅመህ አቃጥልልኝ፣ አንድም ሥራዬ ከሞቴ በኋላ በሰው እጅ ገብቶ ስሜ ቢነሳ፣ አጥንቴ ይውጋህ ብሎ በኑዛዜ ረግሞ የሞተ ነው፡፡ ብሮድ ምን አደረገ?

ብሮድ እነዚያን የካፍካን ጽሑፎች ማቃጠል በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን አወቀ፡፡ የስነጽሑፍ ጄኖሳይድ ነው፡፡ የሰው ልጅ ስሜትን አጠቃልሎ መግደል ነው፡፡ እና የሙት አጥንት ይውጋኝ ብሎ ከቃጠሎ የተረፉትን የካፍካን ጽሑፎች፣ ከሞቱ በኋላ አሳተማቸው፡፡ እስከዛሬ የሰው ልጅ ይሄን ኑዛዜ አፍራሽ ሲያመሰግነው ይኖራል፡፡

ይህ በ70 ገጾች የተቀነበበ የዶክተር ፍራንዝ ካፍካ አጭሬ ልብወለድ፣ እስካሁን ድረስ የሰውን ልጅ ማንም የማይደርስበት እጅግ ጥልቅ የስሜት ስፍራ ጠልቆ የነካ ምናልባትም ብቸኛው የጥልቆች ጥልቅ ተረት የመሰለ ታላቅ የዓለም ቅርስ ነው፡፡ የኤግዚስተንሺያሊዝም በለው የሱሪያሊዝም፣ ሄደው ሄደው መሸሸጊያ ዋሻቸው... መድረሻቸው... ይሄ የፍራንዝ ካፍካ የሰውን ልጅ ድንበር የጣሰ ሥራ ነው፡፡

ግሪጎር የሽያጭ ሠራተኛ ነው፡፡ ቤተሰቦቹ ዕድሜያቸውን ሙሉ ኑሮን ለማሸነፍ የተፍጨረጨሩ፣ ግን እንደ ብዙዎች የዚህች ዓለም መከረኞች በትንቅንቁ የተዘረሩ ቤተሰቦች ናቸው፡፡ ግሪጎር ብዙ ጊዜውን በዋል ፈሰስ ኖሮ፣ ድንገት አንድ ቀን ላይ ነቃ፡፡ የአባቱን መሸነፍ አወቀ፡፡ እና ያንን ሽንፈት ለመካስ፣ ባለ በሌለ ኃይሉ ተወነጨፈ፡፡ ህይወት የሰጠውን ሰጠችው፡፡ ስኬት ቀረበችው፡፡

ቤተሰቡን ወደተሻለ ቤት፣ ወደተሻለ ኑሮ፣ በእርጅናቸው ወደ ዕረፍት አስገባቸው፡፡ የ17 ዓመት ታናሽ እህቱን በዝንባሌዋ ጸሐፊነትና ፍሬንች አስተማረ፡፡ ወደፊት ያላቸው፣ የደላቸው ብቻ በሚማሩበት የሙዚቃ ትምህርትቤት ሊያስገባት ዝግጅቱን ሁሉ ጨርሷል፡፡

ግሪጎር፡፡ ሁሉም የሚመኩበት፡፡ ቤተሰቡን የሚያኮራ፣ ካምፓኒውን የሚያስመካ፣ በየሀገሩ ሁሉ እየዞረ ካምፓኒውን እየወከለ ውሎችን የሚፈራረም ቁልፍ የሽያጭ ወኪል ሆኗል፡፡ ብዙ ሰው፡፡ በየሀገሩ ያውቃል፡፡ ይቀርባል፡፡ ያለማቋረጥ ይጓዛል፡፡ ህይወትም ምርቃቷን አበዛችለት፡፡

ግን አንድ ቀን... እንደወትሮው አምሽቶ፣ ደክሞት ቤቱ ሲገባ ተጫጫነው፡፡ ህመም ተሰማው፡፡ ተኛ፡፡ ቁርጥማት ቀረጣጠፈው፡፡ ሲቃዥ፣ አስፈሪ ህልም ሲያይ አደረ፡፡ እና እንቅልፍ ጣለው፡፡ ሲነሳ፡፡ ራሱን ሌላ ፍጡር ሆኖ አገኘው፡፡ ግዙፍ ቁምቡርስ ሆኖ ራሱን አገኘው፡፡ ክንፍ ያለው ቁምቡርስ፡፡ ‹‹ቬርሚን››፡፡ ይሄን ፍጡር አንዳንዶች ‹‹ግዙፍ፣ ቀርፋፋ፣ ቀፋፊ በረሮ›› ብለው ይተረጉሙታል፡፡

ጠዋት ወደ ሥራው እንዲሄድ እናቱ አንኳኩ፡፡ ነቃ፡፡ ግን መነሳት አልቻለም፡፡ እህቱ አንኳኳች፡፡ እሺ ቆይ ብሎ ተኛ፡፡ ቀጥሎ አባቱ በቁጣ የመኝታ ቤቱን ደበደበ፡፡ እንደ እንስሳ የመሰለ እሺ እመጣለሁ የሚል ቃል ብቻ ማውጣት ቻለ፡፡ ጉዳቸውን አልጠረጠሩም፡፡ ግን ባቡሩ የሚነሳበትን ሰዓት አሳለፈ፡፡ ቤተሰቡ ይህን ነገር አይቶ አያውቅም፡፡ የመሥሪያ ቤት አለቃው ቤቱ ድረስ መጣ፡፡

ግሪጎር ግን በአልጋው ላይ እንዳለ፣ እንደ ሌሊት ወፍ የመሰለ፣ ግን ደግሞ እንደ ጉንዳን፣ ራስ፣ ደረትና ሆድ ያለው፡፡ ብዙ እግሮች ያሉት፡፡ ግን ቀጫጭንና ደካማ፡፡ ሆዱ በጣም የተንዘረጠጠና የተከፋፈለ፡፡ ጀርባው ጠንካራ፡፡ በግድግዳ ላይ መሳብ ወደሚችል፡፡ በጣራው ላይ መንጠልጠል ወደሚችል፡፡

በእግሮቹ ጫፍ የረገጠው ነገር የሆነ የሚያጣብቅ ማስቲሽ የመሰለ ዝልግልግ ዳና ይተዋል፡፡ በዚያ ላይ የሰውነቱ ሽታ ጥንባት ሰውን አያስቀርብም፡፡ ችሎ ቀና ብሎ ፊት ለፊት ይህን አስቀያሚ ፍጡር ማየት የሚችል ሰው አልተገኘም፡፡ የአስም በሽተኛዋ እናቱ ገና እንዳየችው ፌንት አደረገች፡፡ ሌላም ጊዜ ደግመው ሸፍነው፣ ጫፉን ብቻ እንድታይ አቀረቧት፡፡ ራሷን ስታ ልትሞት ለጥቂት ተረፈች፡፡

እህቱም እርሱን ማየት በጣም ስለፈራች፣ ራሱን በአግዳሚ ጠረጴዛ ሥር በአንሶላ ተደብቆ ያሳልፋታል፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ ተናወፀ፡፡ ክፍሉ ተዘጋበት፡፡ ተፈራ፡፡ አስፈራ፡፡ አለቃው መጥቶ አንዴ በሩን ከፍቶ አይቶ፣ ዘንዶ እንደቀረበው እየጮኸ፣ የፈጣሪን ስም እየተጣራ ወደመጣበት ሄደ፡፡ የቤት ሠራተኞች ‹‹ምስጢሩን ለማንም አንናገርም፣ ብቻ ሸኙን›› እያሉ አመለጡ፡፡ እህቱ ብቻ ክፍሉ ትገባለች፡፡

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

04 Nov, 06:48


Lord, I Hope This Day Is Good — Don Williams

Lord, I hope this day is good
I'm feelin' empty and misunderstood
I should be thankful, Lord, I know I should
But Lord I hope this day is good

Lord, have you forgotten me
I've been prayin' to you faithfully
I'm not sayin' I'm a righteous man
But Lord I hope you understand

I don't need fortune and I don't need fame
Send down the thunder, Lord, send down the rain
But when you're plannin' just how it will be
Plan a good day for me

Lord, I hope this day is good
I'm feelin' empty and misunderstood
I should be thankful, Lord, I know I should
But Lord I hope this day is good

You've been the King since the dawn of time
All that I'm askin' is a little less crime
It might be hard for the devil to do
But it would be easy for You

Lord, I hope this day is good
I'm feelin' empty and misunderstood
I should be thankful, Lord, I know I should
But Lord I hope this day is good

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

03 Nov, 16:04


« ከሞት በኋላ ባለው የወደፊት ህይወት ታምናለሕ ? ለማንኛውም አለ ብለን እናስብ ና ያ ዓለም የሸረሪቶች ብቻ መኖሪያ ቢሆንስ? ዘላለማዊነት የሚባለው ቀጣይ ህይወት ከህሊናችን በላይ የሆነ ስፋት እንዳለው ያታመናል ፡ ሁኖም ግን በሸረሪት ድር የተሞላች አንዲት ጠባብ ክፍል ብትሆንስ. ?

Fydor Dostoevsky ❤️

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

03 Nov, 10:41


ኢጎ
ኤካሀርት ቶሌ

ኢጎ ከሌሎች የሆነ ነገር ይፈልጋል። የማይቻለው ከሆነ ግን፣ ከሚያስፈልገው ነገር ማለትም ቁስ፣ ስልጣን ፣ ታማኝነት፣ ልዩ ፍላጎቶች ፤አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ እድናቆቶችን ለማግኘት ሲል የሆነ አይነት ሚና ይላበሳል። አብዛኛውን ጊዜ ሠዎች ስለሚላበሷቸው ሚናዎች ማስተዋሉ የላቸውም። ሚናውን ሆነው ቁጭ ይላሉ፡፡ የተወሰኑ ሚናዎች ጉልህ አይደሉም። ሌሎች ደግም ከሚላበሳቸው ሠው በቀር ግልፅ ናቸው። የተወሰኑ ሚናዎች ከሌላው ትኩረትን ለማግኘት ሲባል ብቻ የተቀየሱ ናቸው።

ኢጎ የሚፈልገው ታዲያ ቅርፅ-አልባ (መንፈሳዊ) የሆነውን ትኩረት ወይም ጥልቅ መገኘትን (Presence) ሳይሆን ክብር ማግኘትን፣ መወደስን፣ መደነቅን ወይም በሆነ መልኩ ትኩረት ማግኘትን ወይም ስለመኖሩ መታወቅን የመሳሰሉ ቅርፅ ያላቸውን ትኩረቶች ነው።

የሌሎችን ትኩረት የሚፈራ አይን አፋር ሠው ከኢጎ ነፃ አይደለም። ከሌሎች ትኩረትን የሚፈልግ ደግሞ የሚፈራ ስጉ ኢጎ ባለቤት ነው። ፍራቻው ትኩረት ወይም ተቀባይነት ማጣትን ያስከትልብኛል የሚል ሲሆን፣ ይህም የማንነት ስሜትን ከማጎልበት ይልቅ የሚያኮስስ ስለሚሆን ነው። ስለሆነም የአይን አፋሩ ሠው ትኩረትን የማግኘት ፍራቻ፣ ትኩረት ከማግኘት ፍላጎቱ ያመዝናል። አይናፋርነት የሚመጣው በዋናነት ከአሉታዊ የማንነት ሃሳብ ወይም “ብቁ አይደለሁም” ከሚል እምነት ነው። ወጣም ወረደ፣ የትኛውም ፅንሰ ሃሣባዊ የማንነት ስሜት፣ “እንዲህ ነኝ” ወይም “እንዲያ ነኝ” ማለት፣ አዎንታዊም (እኔ ታላቅ ነኝ) ይሁን አሉታዊ (ብቁ አይደለሁም) ኢጎ ነው።

ከእያንዳንዱ እዎንታዊ የማንነት ፅንሰ ሃሳብ ጀርባ “ጥሩ አይደለሁም” የሚል ድብቅ ፍራቻ አለ። ከእያንዳንዱ አሉታዊ የማንነት ፅንሰ ሃሳብ ጀርባ ደግሞ፣ ከሌላው የተሻለ የመሆን ወይም ታላቅ የመሆን ድብቅ ፍላጎት አለ። የታላቅነት ስሜት ከሚሰማውና በቀጣይነት ያንን ከሚፈልግ ልበ ሙሉ ኢጎ ጀርባ፣ ድብቅ የትንሽነት ፍራቻ አለ። በተቃራኒው አይን አፋር ወይም የትንሽነት ስሜት ከሚሰማው ጎዶሎ ኢጎ ጀርባ፣ ታላቅ የመሆን ጠንካራ ምኞት እለ። ብዙ ሠዎች እንደሚያገኙት ሰውና እንደሚገጥማቸው ሁኔታ፣ በትልቅነትና በትንሽነት ስሜት ውስጥ ሲዋዥቁ ይስተዋላል። ልታውቀው እና በውስጥህ ልትመለከተው የሚገባው ጉዳይ የሚከተለው ነው። ከማንኛውም ሰው አንፃር ትልቅነት ወይም ትንሽነት ከተሰማህ ያ "ኢጎህ" ነው።

ጥቂት ኢጎዎች የሚፈልጉትን ውዳሴና አድናቆት ካላገኙ የተለየ ሚና በመላበስ ሌላ አይነት ትኩረትን ለማግኘት ይሞክራሉ። አዎንታዊ ትኩረትን ካላገኙ በሌላ ሠው ውስጥ አሉታዊ ምላሽን በመቆስቆስ አሉታዊ ትኩረትን ለማግኘት ይጥራሉ።ይህንንም የተወሰኑ ህፃናት ሲያደርጉት ይስተዋላል። ትኩረትን ለማግኘት ሲሉ ረባሽ ይሆናሉ።አሉታዊ ሚናዎችን መላበስ በተለይም የቆየ አካለ-ስቃይ ባላቸው ሠዎች ላይ ጎልቶ ይታያል። ይህም ባለፈው ጊዜያቸው የታወከ ስሜት ያረገዙና ያንንም በበለጠ ስቃይ ማደስ የሚፈልጉ ማለት ነው። ጥቂት ኢጎዎች ዝናን ለመጎናፀፍ ሲሉ ብቻ ወንጀልን ይሰራሉ። በመበጥበጥና ሌሎችን በማውገዝ ትኩረትን ይሻሉ። “እስቲ መፈጠሬን ንገሩኝ፣ የማልረባ እንዳልሆንኩ አሳውቁኝ” ማለት የሚፈልጉ ይመስላሉ። እንዲህ ዓይነት በሽታ የመሰሉ ኢጎዎች፣ የመደበኛ (Normal) ኢጎዎች ፅንፈ-ገፅታ ናቸው።

#የተበዳይነት ሚና በጣም የተለመደ ሚና ሲሆን፣ የሚሻው የትኩረት ቅርፅ ደግሞ በ “እኔ” እና በ “እኔ ታሪክ” የሌሎችን ትኩረት መሳብ፣ ሃዘኔታንና ምፀትን ነው። ማማረር፣ ተነካሁኝ ማለት፣ ቁጣን ማሳየት፣እራስን እንደ ተበዳይ መመልከት እና የመሳሰሉት በብዙ ኢጎአዊ ልማዶች ውስጥ ይገኛል።እራሴን አንደ ተበዳይ የቆጠርኩበት ማንነት ደግሞ ለኢጎ የማንነቱ አካል ስለሆነ ለችግሮቹ መፍትሄ አይፈልግም። ማንም ስለአሳዛኙ ታሪኬ የማያዳምጠኝ ከሆነ ለራሴ መልሼ መላልሼ በመንገር፣ ብሎም ስለራሴ በማዘን፣ በህይወትና በሌሎች ሠዎች እንዲሁም በዕድሌና በፈጣሪ እንኳን ( ቦታ ያልተሰጠኝ ነኝ የሚል ማንነት ለራሴ እሰጣለሁ።ይህ ለራሴ የማንነት ምስል ቅርፅ የሚሰጠኝ እና የሆነ ሠው) የሚያረገኝ ነው። ለኢጎ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ቦታ የሚሰጠው ጉዳይ የለም።

በተለምዶ የልብ ለልብ (የፍቅር) በሚባለው ግንኙነት የመጀመሪያዎቹ ሰሞናት ደስታን ይሰጠናል፣ የተለየ ስሜት እንዲሰማኝ ያደርጋል፤ ፍላጎቴን ያሟላልኛል ተብሎ በኢጎ የሚታለመውን ሠው ለመማረክና የራስ ለማድረግ ሲባል ሚና መላበስ እጅግ የተለመደ ተግባር ነው። አንተ የፈለግከውን ሚና እኔ እላበስልሀለሁ፣ እንተ ደግሞ እኔ የምፈልገውን ሚና ትላበስልኛለህ" የሚለው የማይነገርም የማይስተዋልም ስምምነት ነው። ነገር ግን ሚናን መላበስ እጅግ አድካሚ ከመሆኑ የተነሳ፣ በተለይም አብሮ መኖር ከተጀመረ በኃላ ግንኙነቱ ዘላቂነት አይኖረውም።

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

03 Nov, 08:22


ሙላ ነስሩዲን ትዳር ይይዝና መኖር እንደ ጀመረ ፡ አንድ ጓደኛው ወደሱ በመምጣት..
« ሙላ ነስረዲን ይለዋል አቤት በማለት ሲመልስለት ሰዎች ያሙሀል አለው ።
«ሙላ ነስረዲንም ጉዳዩን ለማጣራት ምን ብለው ነው፡ የሚያሙኝ ሲል ሰውየውን ይጠይቀዋል? »
« ሙላ ነስሩዲን ሚስት ካገባ በኋላ ሀይማኖተኛ ሆኗል እያሉህ ነው »

«ሙላ ነስሩዲንም ልክ እኮ ናቸው ፡ እሷን ካገባው በኃላ ነው በገሀነም መኖር ማመን የጀመርኩት »

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

02 Nov, 11:41


Don Williams 🖤

የጥበብ - መንገድ 📖 °°°

02 Nov, 05:22


"Oh Beloved,
take me•
Liberate my soul•
Fill me with your love and
release me from the two worlds•
If I set my heart on anything but you
let fire burn me from inside•
Oh Beloved,
take away what I want•
Take away what I do•
Take away what I need•
Take away everything
that takes me from you•"
︎~ Rumi

የጥበብ - መንገድ 📖

01 Nov, 17:29


የመኖር ትርጉም ጠፍቶኝ ስጨናበስ
የክዋኔ ጉልበት አጥሮኝ ስልፈሰፈስ
የፍቅር ስሜት ትርጉሙ ሲነፍስ'ሲፈስ

ሞትን በፅኑ ናፈኩ
ያልታጎለ ዝምታን አሰስኩ
የምንምነት መገኛ የት ይሆን ብዬ ፈለኩ
ፈለኩ
ፈለኩ
ፈለኩ
ግና
የህይወት ቋንቋው ይህ ነውና
ምን እላለሁ ዝምብዬ ዝም አልኳ

©ROHHA

የጥበብ - መንገድ 📖

01 Nov, 16:34


« ተማሪው መጥፎ ባህሪ ሲፈጥር ለምን መምህሩን አትገርፉም ? »

© ፈላስፋው ዲዮጋን

የጥበብ - መንገድ 📖

01 Nov, 05:17


የአንተ ክብረ-ወሰን ምንድን ነው?

ፈላስፋው አርተር ሾፐን-አወር ይህን ተናግሯል፡፡ ‹‹ብዙ ሰዎች የራሳቸውን የራእይ ገደብ የዓለም ወሰን አድርገው ይወስዳሉ፡፡ ጥቂቶች ግን እንዲያ አያስቡም፤ ከእነርሱ ጎራ ተሰለፍ፡፡» በጣም ጥልቅ ነጥብ ነው፡፡አሁን የምትኖረውን ሕይወት ባለህ አቅም ልክ እየኖርክ ነው?? ምናልባት ነገሮችን የምትመለከተው በፍርሐት፣ በገደብና በሀሰተኛ ግምት እይታ ይሆናል። የመስኮትህን መስታወት ወልውለህ ወደ ውጭ ስትመለከት አዲስ አማራጮችና እድሎች ይከሰታሉ፡፡

ዓለምን የምንመለከተው እንደሆነው ሳይሆን እኛ እንደሆንነው መሆኑን አስታውስ፡፡ ከአስርት ዓመታት በፊት ደስታ የራቀው ጠበቃ ሆኜ ሕይወቴን የምመራበት የተሻለ መንገድ እየፈለግሁ ሳለ ይህ ሐሳብ ሕይወቴን ለውጦታል፡፡
ከ1954 ዓ.ም. በፊት የአንድ ማይል ርቀትን ከአራት ደቂቃ በታች በሩጫ ሊሽፍን የሚል ሯጭ እንደማይኖር ይታመን ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ሮጀር ባኒስተር ይህን ክብረ ወሰን ከሰበረ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የእርሱን ክብረወሰን በርካታ አትሌቶች ለማሻሻል በቁ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ምን እንደሚቻል ለዓለም እርሱ አሳይቷልና፡፡ ከእርሱ በኋላ የሮጡ አትሌቶች አዲስ ማነፃፀሪያ ነጥብ አግኝተዋል። ያን እምነት ታጥቀውም ሰዎች የማይቻለውን ለማድረግ በቁ፡፡

የአንተ ክብረ-ወሰን ምንድን ነው? ለመሆን እንደማትችል ለማድረግ እንደማትችል፣ ልታገኝ እንደማትችል በማሰብ ስለራስህ የያዝከዉ የውሽት ግምት ምንድን ነው? አስተሳሰብህ እውነታህን ይፈጥራል፡፡ እምነቶችህ ድርጊቶችህን ስለሚመሩ ከአስተሳሰብህ ጋር በሚቃረን መልኩ ፈጽሞ ምንም ነገር አታደርግም፡፡

የሕይወትህ ደረጃ የአስተሳሰብህ ደረጃ ነፀብራቅ ነው። በሕይወትህ አንዳች ነገር ሊከሰት እንደማይችል ካሰብክ ያን ግብ እውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን የምትወስድበት አንዳችም መንገድ አይኖርም፡፡ የ«አይቻልም» አስተሳሰብህ ራሱን እውን ያደርጋል። በራስህ ላይ የምትፈጥረው ገደብ መድረስ ከሚገባህ የታላቅነት ደረጃ እንዳትደርስ ጠልፎ የሚጥልህ ሰንስለት ነው፡፡

© Human_Intelligence

የጥበብ - መንገድ 📖

31 Oct, 15:56


ሰውን “ሰው” የሚያደርገው ምንድነው? ከእኛ ይልቅ የጥንቶቹ ዘመናዊ ነበሩ

ዓለማየሁ ገላጋይ !

ሦስት ታላላቅ ሰዎች በአራስነታቸው በቅርጫት ተደርገው ወደ ወንዝ ተጥለዋል፡፡ ያውም በወላጅ እናቶቻቸው፡፡ (ካማተብን በኋላ ስንቀጥል)
የመጀመሪያው ባለታሪካችን ድንጋይ ላይ ታሪኩ ተቀርፆ የተገኘ ግብፃዊ ነው፡፡ የሴማዊ ሥርወ መንግሥት መስራች የሆነው ንጉስ ሳርጎን (Sargon) ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2ሺህ 360 ላይ በፃፈው የህይወት ታሪኩ እንዲህ ይላል፡፡

“እኔ ንጉስ ሳርጎን፣ ኃይል ያመዘነልኝ የአካድ (AKKAD) ገዢ እናቴ ድንግላዊ የቤተመቅደሱ አገልጋይ ነበረች፡፡ አባቴን አላውቅም፡፡ እናቴ በምስጢር ፀንሳኝ ኖሮ በምስጢር ወለደችኝ፡፡ ትንሽ የቅርጫት ሣጥን አበጅታ እዚያ ከትታኝ ወደ ወንዝ ጣለችኝ፡፡ ብዙ ከተንሣፈፍኩ በኋላ አኪ (AKKI) ሁዳድ ላይ ደረስኩ፡፡ አኪ መስኖ ሲመራ አግኝቶ ከወንዙ አወጣኝ፡፡ እንደ ልጁም አሣደገኝ …” ይላል፡፡

ሁለተኛው ተመሣሣይ ባለታሪካችን የብሉይ ኪዳኑ ሙሴ ነው፡፡ ከክርስቶስ ልደት 1ሺህ 5 መቶ አመት አስቀድሞ፣ በግብፅ ልሳነ ምድር ፈርዖን የእብራውያን ሴቶች ወንድ ልጅ ከወለዱ ወደ ወንዝ እንዲጥሉ ባዘዘበት ጊዜ ሙሴ ተፀነሰ፡፡ ተወለደም፡፡ እናቱ “መልካም እንደሆነ ባየች ጊዜ” ይላል ኦሪት ዘፀአት “ሦስት ወር ሸሸገችው፡፡ ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፡፡ ህፃኑንም አኖረችበት፤ በወንዝ ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው፡፡”ሙሴም በፈርዖን ልጅ ተገኝቶ በቤተመንግስት ውስጥ በልዑልነት አደገ፡፡

ሦስተኛው ባለታሪካችን ደግሞ ፈረንሳዊ ነው፡፡ የሒሳብ ሊቁ ዴ-ላምብርት፡፡ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የኖረው ላምብርት፤ ከትዳር ውጭ በመወለዱ እናቱ የሰው አፍ ፈርታ በቅርጫት አድርጋ ወደ ወንዝ ለቀቀችው፡፡

ወንዝ ዳር ሲንሳፈፍ አንድ “ባለእጅ” አግኝቶ እንደ ልጁ አሣደገው፡፡ አድጐ በጂኦሜትሪ ከዘመኑ አስፈንጥሮ የሚያስብ አስደማሚ ሰው ሆነ፡፡

ወዲያ ወዲህ ሳንል፣ ወደ ፅሁፋችን እንብርት ዘለቅን፡፡ እነዚህን ሰዎች “ሰው” ያደረጋቸው ምንድነው? ምላሹን በማድበስበስ የፅሁፍ ዕድሜ ለመግዛት መጣር ተገቢ አይደለምና “ፍርጥ” እናድርገው፤ “ሰው ነው” ለካ ሰው እንደ ጥንቱ ብሉኮ “እስ - በሱ” ድርና ማግ እየሆነ ነው ምድርን ያለበሳት? (ከተገረምን በኋላ ስንቀጥል)
ሳርጎን፣ ሙሴና ዴ-ላምብርት ከሚንሣፈፉበት ወንዝ ብቻ ሣይሆን ከገጠማቸው መጥፎ ዕጣ-ፈንታ ጭምር ነው በደጋጐቹ እጆች ነፃ የወጡት፡፡ ያ ባይሆንና ዛሬ እኛ እንደምናደርገው የጎዳና ወንዝ ያመጣቸውን ጨቅላዎች ገላምጠን እንደምናልፈው ደጋጐቹ እጆች ቢሰበሰቡስ ኖሮ? (አማተብን) ታላቅ ዛፍ የሚወጣት ዘር መና ሆና ልትቀር፡፡

ሰውን ሰው የሚያደርገው ሰው ነው፡፡ ሰው ያለሰው ”ሰው” ሲሆን የታየው በግሪኮቹ አማልክቶች መለኮታዊ ገድል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ የሮማ ከተማን የቆረቆሩት ወንድማማቾች ሬሙለስና ሬሙስ በህፃንነታቸው የእንጀራ አባታቸው አሙሊዎ ቢጥላቸው፣ የተቀደሰችው ተኩላ ጡት እያጠባች ሞግዝታ አሣደገቻቸው፡፡ ምንም እንኳን ሁለቱ ወንድማማቾች የተኩላ የአደራ ልጅ ቢሆኑም አሳዳጊያቸውን ሳይሆን ዘራቸውን ተከትለው “ሰው” ሆኑ፡፡ ሮማንም ቆረቆሩ፡፡ (ፅሁፋችን እዚህጋ’ኮ ቢገታ “ሰውን ሰው” ያደረገው ተኩላ ነው” ተብሎ ሊቀር ነበር፡፡ ግን እንቀጥላለን የጥቂት አራዊታዊ ተሳትፎዎችን እየዘከርን) አማልከተ አማልክት ዜውስ “አማልቲያ” ከተባለች ፍየል ነው የተገኘው፡፡ ቴዲ ደግሞ ከላም፡፡ ሮማን ከውድቀት የታደጋት ቶክቻው ጐተስ አራዊቶች በደቦ ያሳደጉት የአራዊቶች ሁሉ ጉዲፈቻ ነው … (ነጠብጣቡ አቋረጥነው እንጂ አላበቃም ማለት ነው)
እውነታው ግን እንዲህ አይደለም፡፡

ሰውን ሰው ካላሳደገው “ሰውነቱን” ከየትም አያገኘውም፡፡ ሰው “ሰው” ለመሆን ከሰው መወለድ ብቻ አይበቃውም፡፡ “ሰው” በሚያደርጉ ሰዋዊ ተክህኖዎች በኩል ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡ ሰው ዘሩን ሳይሆን አስተዳደጉን ነው የሚከተለው፡፡ ካስፈለገ አርስቶትልን መጠየቅ ይቻላል፡፡ “የሰው ልጅ ሁለት ልደት አለው” በማለት ምላሽ ይሰጠናል፡፡ በአካል መወለድ እና በባህርይ መወለድ አንድ ልጅ በአካል ከእናት መወለዱ ብቻ “ሰው” አያደርገውም፡፡

በባህርይ ከማህበረሰብ መወለድ ይጠበቅበታል፡እንግዲህ በቅርጫት ወደ ወንዝ ወይም በዱላ ወደ ጐዳና የተጣለ ልጅ ዋነኛ አደጋው “ሁለተኛ ልደቱን” ማጣቱ ነው፡፡ “የመጀመሪያ ልደቱንማ አንዴ አግኝቶታል፡፡ ተኩላም ጡት እያጠባ ያሳድገዋል፡ እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ፡፡

Lucien Malson የተባለ የሥነ-ልቦና ተመራማሪ አንድ አስደናቂ መፅሐፍ ፅፏል፡፡ ርዕሱ “Wolf Children” ይሰኛል፡፡ የሚተርከው በህፃንነታቸው ተጥለው አውሬ ስላሳደጋቸው ልጆች ነው፡፡

ስለ ልጆቹ የቀረቡት አንዳንድ መዛግብት እንደሚጠቀሙት ልጆቹ የአሣዳጊዎቻቸውን የአውሬዎች ባህርይ የሚያንፀባርቁና ከአካላቸው ውጭ ምንም የሰው ጠባይ የማይታይባቸው ናቸው፡፡ በ1799 ዓ.ም መካከለኛ ፈረንሳይ ውስጥ አንድ የ11 ዓመት ልጅ ከተኩላዎች ጋር ተዳብሎ ሲኖር ይገኛል፡፡ ዤን ኢታርድ “ቪክቶር” የሚል ስም ስላወጣለት ስለዚህ ልጅ ባህርይ ተከታታይ ጥናት አድርጓል፡፡ እንዲህ ይላል፡-
“ልጁ በሦስት ስፖርተኞች ከጫካ ተጠምዶ ተያዘ፡፡ ልጁ የቀረበውን ሰው ሁሉ በአውሬ ቁጣ በጥፍሩና በጥርሱ ለማጥቃት ይሞክር ነበር፡፡ ከተኩላዎች ጋር በማደጉ፣ ምግቡ ከውሾች ጋር ሲሰጠው ብቻ በደስታ እየተሻማ አጐንብሶ በአፉ ይመገባል፡፡”

ዤን ኢታርድ 200 ያህል ገፆች በሸፈነ የክትትል ሪፖርቱ ቪክቶር ያሳየውን ለውጥ መዝግቦ ይዟል፡፡ አራት አመት በፈጀ የማረም ጥረት ልጁ በመጠኑም ቢሆን ከአውሬነት ሊላቀቅ ችሏል፡፡
የማልሰን “ዎልፍ ችልድረን” መፅሐፍ ከ1344 እስከ 1961 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ አውሬዎች ያደጉ 54 ልጆችን በሰንጠረዥ ይዟል፡፡ ከተኩላዎች በተጨማሪ ድቦች፣ ዝንጀሮዎች፣ የሜዳ በጐች፣ አቦሸማኔዎች፣ ግሥላዎች … የሰው ልጆችን ከወደቁበት አንስተው አሳድገዋል፡፡ የማልሰን ማጠቃለያ ግን “The fact is that human behavior does not depend on heredity to the same extent as animal behavior.” የሚል ነው፡፡ (የሰው ልጅ እንደ እንስሳት ከወላጆቹ የወረሰው ጠባይ ላይ ተመርኩዞ የሚኖር እንዳልሆነ ነው እውነታው የሚያስገነዝበን እንደ ማለት ነው)
ማልሰን ሰውን “ሰው” የሚያደርገው አውሬ አይደለም፡፡

እያለን ነው፡፡ እርግጥ ሰው የገዛ ልጆቹን ሲጥል ክቡራንና እመ ክቡራት አውሬዎች አንስተው በማሳደጋቸው ሳናመሰግናቸው አናልፍም፡፡ ደግሞም’ኮ አቅቷቸው ጥለዋቸው ባይሆንም ሰርቀን የእነሱን ደቦሎች፣ ቡችሎች፣ ጫጩቶች፣ ግልገሎች … አሳድገናል፡፡ ብቻ ሰው በመሆናችን፣ በማሰብ ልቀታችን፤ እየተመራን ከአውሬዎች በተሻለ ወልደን የመጣል ብቃት አዳብረናል፡፡ (ሳናስበው ልንማረር ነው እንዴ? በሉ፣ “ጐመን በጤና” ወደሚተረትበት ልሣነ ምድር እንዳማረብን)

የጥበብ - መንገድ 📖

31 Oct, 15:56


ምንም እንኳን፤ መገዛትን የማናውቅ ህዝብ ብንሆን፣ ምንም እንኳ “ወንድ ልጅ ከወለዳችሁ ወደ ወንዝ ጣሉ” የሚል ባዕድ የፈርዖን ጌታ ባይኖርብን … አገራችን የልጆች ገነት አልነበረችም፡ ምክንያቱም ጦርነት፣ ረሃብ፣ በሽታ “ሠልስቱ አጋዕዛት” (ሦስቱ ገዢዎች) በሆኑበት ግዛት የህፃናት ገሃነም እንጂ ገነት ሊኖር ስለማይችል ነው፡፡ ይልቅ ግርም የሚለን በዚህ ሁሉ የጦርነት መዓት፣ በዚያ ሁሉ የረሃብ ዶፍ፣ በዚያ ሁሉ የበሽታ መቅሰፍት መካከል ህፃናት እምን ጥግ ተሸጉጠው ጅምር የትውልድ ጉዟቸውን ያጠቃልሉ ይሆን? የሚለው ነው፡፡ (ተአምረ ተአምራት ብለን ስንቀጥል)
በጦርነት፣ በረሃብና በበሽታ መካከል ልጅ የማሣደግ የወላጅነት ፍዳው ብዙ ነው፡፡ ጭንቀቱ ከላይ እስከ ታች ያጠቃለለም ይመስላል፡፡ እስኪ በዚህ ታሪክ ዋቢነት እውነታውን እናረጋግጥ፡-
አንድ ጊዜ ነው አሉ …
… ንጉሥ ምኒልክና ንጉስ ተክለኃይማኖት በስምምነትና በፍቅር ሲኖሩ እንደ ማንኛውም ወራጅ አደራ ቃል ተለዋወጡ፡፡ “እኔ ብሞት የልጆቼን ነገር አደራ” አሉ ንጉስ ተክለ ኃይማኖት፡፡ “እኔም ቀድሜህ ከሞትኩ የልጆቼን ነገር አደራ” አሉ ንጉስ ምኒልክ (የወላጅነት ሥጋቱ የት ድረስ የተንሰራፋ ነው ጃል?) ያም ሆነ ይህ ንጉስ ተክለኃይማኖት በሞት ይቀድማሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ንጉስ ምኒሊክ ንጉሰ ነገሥት ሲሆኑ ቃላቸውን ጠብቀው የንጉሥ ተክለኃይማኖትን ልጅ ራስ ኃይሉ የጐጃም አስተዳደሪ ሆነው በአባታቸው እግር እንዲተኩ አደረጉ፡፡ ሆኖም አዲሱ ተሿሚ በህዝቡ ላይ የአስተዳደር በደል እየፈፀሙ ስላቃቱ፣ አፄ ምኒልክ እንጦጦ ያስጠሩዋቸውና ለሰባት ቀን እንዲታሰሩ ያዛሉ፡፡ ራስ ኃይሉ እስር ላይ እንዳሉ ተረስተው ሰባት ዓመት ደብረ ብርሃን ስለታሰሩ እንዲህ በማለት ለአፄው ላኩባቸው፡፡

“ሟች አደራ ይላል እሺ ይላል ቀሪ፣
መቼም የለ ብሎ ቆሞ ተናጋሪ፤”
ነገሩ አፄ ምኒልክን እጅግ አድርጐ ህሊናቸውን ቆረቆራቸው ይባላል፡፡ “አስኮነነኝ” በሚል ራሱን ፈትተው በቅሎ ከነመጣብሩና ብር ጨምረው ሰጥተው፣ አስደሰተው፣ ከሰው ወደ ጐጃም ላኳቸው፡፡ አደራ ሰጪና ተቀባይ ከምድር በላይ ከፍ ባለው ህሊና በተመዘገበው ውል ይወቃቀሳሉና በሁለቱ መካከል ያለ ልጅ ሁልጊዜም ከለላው አይጓደልም፡፡

ራስ ኃይሉ የአጤ ምኒልክ የአደራ ልጅ ነበሩ ማለት ነው፡፡ በጥንታዊት ኢትዮጵያ በችግር ፅናት ኅብረተሰቡ ህፃናትን ወደ ጎዳና “ፈሰስ” እንዳያደርግና ማህበራዊ ምሥቅልቅሎሽ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከያ ትግግዝ ይደረግ እንደነበር አንዳንድ የባህል ቅሪቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከአደራ ልጅ በተጨማሪ ጉዲፈቻ፣ የጡት ልጅ፣ የክርስትና ልጅ፣ የማደጎ ልጅ፣ የቤት ውልድ ….
እነዚህ ነባር የህፃናት መጠጊያ ባህላዊ “ቤቶች” ህፃናት በህይወት እንዲቆዩ የሚያግዝ ዘዴ ብቻ አይደለም፡፡ ሁለተኛው “ሰው የመሆን” ልደት በተገቢው ሳይጓደል የሚከናወንበት ተቋም ነው፡፡ ለምሳሌ የጉዲፈቻን አፈፃፀም እንይ፡-

አንድ የጥንት ማህበረሰብ ሴት ጉዲፈቻ ወስዳ ህፃን ለማሳደግ ስትወስን ያለባትን የወላጅነት ግዴታ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ በተለይ ልጅዋን ከአራስ ቤት የምትቀበለው ከሆነ እንደወለደችው ሁሉ ለመታረስ ቡሉኮ ትጋርዳለች፡፡ ቅቤ ተቀብታ ሙክት ታርዶላት፣ የገንፎ እህል ተዘጋጅቶላት አርባ ቀን ከቤት ሳትወጣ ትታረሳለች፡፡ ጎረቤት፣ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ እንደወለደች ተቀብሎ የአራስ ጥሪ ይዞ ይመጣል፡፡

የጉዲፈቻ አባትም በበኩሉ እንደ ወላጅ አባት ለጉዲፈቻ አራስ ሚስቱ ሙክት ያርዳል፡፡ ወንድ ከሆነ ጥይት ይተኩሳል፣ እንኳን ደስ ያለህ ይባላል፡፡ ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ ነፍስን ከሥጋ በሚለይ መሃላ አባትነቱ ይረጋገጣል፡፡ “ከልጆቼ ብለየው ይለየኝ፣ ከልጆቼ ብነጥለው ይነጥለኝ፣ ከልጅነት መብቱ ብፍቀው ከሰማይ መዝገብ ይፋቀኝ …” ይላል፡፡

በዚህ መንገድ የባዕድ ወላጆች ጋር የሚያድገው ልጅ ከሌሎች የተለየ አድልኦ አይደረግበትም፡፡ በመሆኑም ጉዲፈቻው ልጅ ከተወለዱት ልጀች እራሱን ነጥሎ ማየት ከመቸገሩ የተነሳ ሲያድግ እውነታውን ለመቀበል ያዳግተዋል፡፡ (ልንጨዋወት ተገናኝተን መማረራችንን ማስቀረት ተስኖን ቆየን) ይሄንን ነባር ባህላዊ “ቤት” ስናፈርስ ነው የዛሬ ልጆች “ወላጅ አልባ” ለመባል የበቁት፡፡

“ወላጅ አልባነት” ወደ “ትውልድ አልባነት” የሚመራ ጅምር ጉዞ መሆኑን የተረዱት የጥንቶቹ ናቸው፡፡ እነርሱ ያበጁትን መከላከያ “ቅጥር” ዋጋ አሳጥተን አፍርሰን ለተንጋጠጠ ማኅበራዊ ቀውስ እራሳችንን አጋልጠናል፡፡

ልጆቹን ከጥቃት የሚከላከል ማህበራዊ አደረጃጀት ያለው ኅብረተሰብ፣ እንደኛ ምንም ከሌለው ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ትውልድ የበለጠ ሥልጡን ነው፡፡ ከአሁኖቹ ከእኛ፣ የጥንቶቹ እነሱ የተሻሉ ዘመናዊ አኗኗር የነበራቸው ዘመናዊዎች ነበሩ ለማለት ነው፡፡

የጥበብ - መንገድ 📖

31 Oct, 12:13


« Self portrait »

Art - Kahlil Gibran ❤️

የጥበብ - መንገድ 📖

31 Oct, 05:37


አራት ዓይነት እብደት...

ብቸኝነት ብርዱ ገላህን ቀዝቅዞ
ከሰው መሀል አንተን ለብቻህ ሰቅዞ
መጠየቅ ስትጀምር ...
ለምን!...እንዴት?...ስትል?
ጥያቄህ በራሱ እብደት ነው የሚባል
ኡፍፍፍ...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!

መጠየቅ ሰልችቶህ ከሕዝቦች ስትርቅ
በራስህ ዓለም ላይ ህሊናህ ሲራቀቅ
አፍህ ዝም ባለ
እብድ መባል አለ።
ኤጭ!...
አቋመ ቢስ መሐል ለብቻችን ነቅተን
አቦ ተሰቃየን!

የሕዝብ ሁሉ ሀሳብ የእብደት ሲመስልህ
ያንተ አሳብ የእውነት....
እውነት እንደሆነ ውስጥህን ሲሰማህ
እብዱ ትባላለህ።
ኤዲያ!...
አውቆ የሚተኛ ሕዝብ መሀል ነቅተን፣
አቦ ተሰቃየን!

ዓለሙም እብድ ነው!
ግና ያለም እብደት ካንተ የሚለየው
አንተ የምታብደው ለዓለም ስትል ነው
ዓለሙ ያበደው አንተን ሊያሳብድ ነው።
ወገን ተሰቃየን!
አውቆ በተኛ አቋመ ቢስ መሐል...
ለብቻችን ነቅተን
አወይ ተሰቃየን!!

ኤፍሬም ስዩም

https://t.me/salmakeriem
https://t.me/salmakeriem

የጥበብ - መንገድ 📖

30 Oct, 15:51


Life Philosophy

የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጀምሮ ኑሮን ለመምራት በሚያደርግበት ግዜ የተለያዩ መሰናክሎች ወይም አንቅፋቶች ያጋጥሙታል። ቁልፉ ግን የህይወትን አላማ ግብ መረዳት ነው። ባጋጠሙት እንቅፋቶች ምክንያት የህይወቱን አላማ ከዳር ሳያደርስ በመንገድ ላይ ሊገታ ይችላል። ስለዚህ ለስኬቱ መዳረስ የሚያራምደው የህይወት አመለካከት ወይም ፍልስፍና ቁልፍ ሚና ይጫወታል። አንዳንዴ ግን የህይወትን ፍልስፍና መያዙ ብቻ በቂ አይደለም። ፍልስፍናውን መከተልና መሆን(ዋነኛው የህይወቱ አካል አድርጎ መኖር) በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።

የህይወታችንን ግብ ከዳር አንዲደርስ ሁለት ግዙፍ የህይወት አመለካከት ግንባሮች አሉ (የሁለቱም ፍልስፍና አራማጆች በየግላቸው ትክክል ነው ብለው ያምናሉ ለምሳሌ ሁለት የእግር ካስ ቡድ አሉ። ሁለቱም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባሉ። ሁለቱም የአጨዋወት ስልት አላቸው። አንዱ የያዘው ስልት ለራሱ ትክክል ነው ለተጋጣሚው ግን ስህተት ነው ሌላውም በተመሳሳይ):-

1) ፕሮታጎኒስት (Protagonist):- የፕሮታጎኒስት አቀንቃኞች የሰው ልጅ እያንዳንዱን ቀን በታላቅ ትጋት መስራት አለባቸው ፣ በቻሉት መጠን ከራሳቸው አልፈው ለሌላው የሚፈይድ አንዳች መልካም ወይም ቀና የሆነ ተግባር መፈፀም አለባቸው። በህይወት ለሚያጋጥማቸው አያንዳንዱ መልካም ሆነ አሳዛኝ ገጠመኝ ሳይበገሩ ወደ ፊት መቀጠል አለባቸው ምክንያቱም ሁሉም የሰው ልጅ በምድር ላይ የተፈጠረበት ትልቁ ምክንያት በህይወት ዘመኑ መልካም ነገር ለመስራት አንጂ ኖሮ ኖሮ ለመሞት በቻ አይደለም ብለው ያምናሉ።

፨ የፕሮታጎኒስቶችን ፍልስፍና ጠቅለል ስናደርገው:-

• የሰው ልጅ የተፈጠረው ለስራና ለስራ በቻ ነው ፣
• ሁሌም ቢሆን መልካም ነገር መስራት ይኖርብናል ፣
• ተስፋ መቁረጥ በምንም ተዓምር የለበትም ፣
• ዛሬን ሳይሆን ነገን ነው መኖር የሚገባን ፣
• ሁሌም ወደ ኋላ ሳይሆን ወደ ፊት ይሉናል።

2) አንታጎኒስት (Antagonist):- አንታጎኒስቶች ያላቸው የህይወት ፍልስፍና የሰው ልጅ ሞትን ማሸነፍ ካልቻለ አልያም የሰው ልጅ መጨረሻው ሞት ከሆነ ህይወት ነገ ሳትሆን ዛሬ በቻ ናት። ስለዚህ የሰው ልጅ መኖር ያለበተደ ዛሬን ብቻ ባሻው መንገድ መሆን አለበት። ስራ ፣ አላማ ፣ ፅናት ፣ ግብ ፣ ራዕይ ... ወዘተ የሚባል ኮተት ሁሉ ከንቱ ስንቅ ነው። አጅግ መናጢ የሆነው ግለሰብና የናጠጠው ሀብታምም መጨረሻው ሞት ነው። ጠ/ሚኒስትሩው ፣ ኩሊው ፣ የተማረው ፣ ያልተማረው ፣ ስኬታማው ፣ ስኬት አልባው ... ሁሉም ይሞታሉ። ታዲያ ሞት የማይቀርል ዕዳ ከሆነ ምን አስለፋን ፣ አስደከመን ...? ሞት የማይቀር ከሆነ የሰው ልጅ ነገን እያሰበ ሳይሆን ዛሬን ብቻ መኖር አለበት ምክንያቱም የሰው ልጅ ምንም ይሁን ምንም መጨረሻው ሞት ነውና የሚል አመለካከት ያራምዳሉ።

፨ የአንታጎኒስቶችን ፍልስፍና ጠቅለል ሲደረግ:-

• የሰው ልጅ ይሞታል ፣
• ዛሬን ብቻ ነው መኖር ያለብን ፣
• የተፈጠርነው ለደስታ በቻ ነው ፣
• ሁሉም ነገር የተፃፈልን ስለሆነ መለወጥ አይቻለንም።

ስለ ህይወት ፍልስፍና አንዳንድ ጥሬ ሀቆች

#በምድር ላይ ካሉት በቢልዬን የሚቆጠር ህዝብ መካከል ሶስት አራተኛው ወይም 75% የአንታጎኒስት አመለካከትን አስበውበት ይሁን ሳያስቡበት ያራምዳሉ። አንድ አራተኛው ወይም 25% የፕሮታጎኒስት አመለካከት ተከታዮች ናቸው።
አኛስ ከየትኞቹ ወገን ነን ...? ሀሳብና ድርጊት በጣም የተለያዩ ጥሬ ሀቆች ናቸው። አንዳንዴ በሀሳብ ደረጃ ተቀብለን በድርጊት ካልገለፅነው ትርጉም የለሽ ይሆናል። ስለዚህ ስንቶቻችን ነን ሀሳብና ድርጊት ሆድና ጀርባ መሆናቸው ቀርቶ መርፌና ክር የሆኑልን?

#ምንጭ:- "ኦያያ ፣ 2000 ከፓሪስ መልስ" *በአዘርግ*

የጥበብ - መንገድ 📖

29 Oct, 16:24


የሕይወትን ችግር በሎጂክ ድራድር ትተበትበዋለህ። ቦቅቧቃነትህን በአይናውጣነት አንቀልባ አዝለህ ፣ የባጥ የቆጡን በመቀባጠርህ ትኩራራለህ። እፍረተ ቢስ ነገር ታወራና፣ ወዲያው በፍርሃትና በሰበብ ትከልሰዋለህ። የምፈራው የለም እያልክ፣ ዞር ብለህ ትለማመጣለህ። በሰቆቃ ጥርሴን አፋጫለሁ ብለኸን፣ ኋላ ደግሞ እየቀለድክ ሳቁልኝ ትለናለህ። ቀልዶችህ ጣዕመ –ቢስ መሆ ናቸውን ስታውቅ ፣ በስነ–ፅሑፋዊ ዋጋቸው ትመፃደቃለህ። መከራ ደርሶብህ ብታውቅም እንኳን ለስቃይህ ቅንጣት እንኳ ዋጋ አትሰጠውም። ከምትቀባጥረው አንዳንዱ እንኳ እውነት ቢሆንም ይሉኝታ ቢስነትህ መጠን የለውም። ከግብዝነትህ የተነሳ ሀቅህን አደባባይ አውጥተህ ታረክሰዋለህ። በእርግጥ ማለት የምትሻው ነገር አለ፣ እቅጩን እንዳትናገር ግን ፍርሃት ጠፍሮ ይዞሃል፣ለመናገር የሚያበቃ ድፍረት አጥሮሃል።

የፈሪ ባለጌ ነህ። በአእምሮህ ንቃት እየተኩራራህ ሳለ ትወላውላለህ። ምክንያቱም አእምሮህ ብሩክ ቢሆንም እንኳን፣ ልብህ በልክስክስነት ፅልመት ተወርሷል። ንፁህ ልቦና በሌለበት ደግሞ ምሉዕ ንቃተ– ህሊና ሊኖር አይችልም።


ወራዳነትህ! አትርሱኝ ባይነትህ !
የመቀላመድህ ገደብ አጤነት! …"

**

ምንጭ :- ''የስርቻው መጣጥፍ'' ተብሎ በቆንጆ መልኩ በፋሲል ይትባረክ ከታተመው

Fyodor Dostoyevsky (Notes From The Underground) መጽሐፍ።

የጥበብ - መንገድ 📖

29 Oct, 15:13


ሴት ነኝ አየሽ፡፡ በትምህርት ነፃ አልወጣም:: እዚህች አገር በትምህርት ነፃ አይወጣም:: በትምህርት ብቻ ነፃ የወጣ የለም:: ሕይወት አሁን ነው: በልጅነት ነው ጨዋታ:: ሴት ሆነሽ ሁለት ነገር፣ ዋና ዋና ነገር ያስፈልግሻል:: ቢቻል ሦስት:: ወሲብ መስጠት፣ ቁንጅና፣ ትምህርት:: በአጭሩ ሸርሙጣ፣ ቆንጆና ምሁር መሆን፡፡ አለበለዚያ የትም አትደርሺም፡፡ ሸርሜነትን ጀማምረሽ አቁመሽዋል፣ ምሁር አይደለሽም፣ ቁንጅናሽ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ይጠፋል:: ይጎልሻል:: አንዱን ብቻ ከሆንሽ ይጎልሻል፡፡ ወንዶች ወይም ገዢዎችሽ እንድትሆኚ የሚፈልጉትን መሆን አለብሽ፡፡ ሴት ለማን ተሰራች? ለወንድ:: ቆንጆ…….ሸርሙጣ….ምሁር፡፡ ሦስቱን በአንዴ አጠቃለሽ መያዝ፡፡ እንደ እኔ መኪና መንዳት ትፈልጊያለሽ? ነጠላ ተከናንበሽ ከሠፈር ሉዘሮች2 ጋር ስትዳሪ ልታረጂ ነው? ነቃ በይ፡፡ ቆንጆ ነሽ፡፡ ሸርሙጣ ነሽ፡፡ በቀላሉ ካናሳ ፖለቲከኛ ጋር አገናኝሻለሁ………ከፈለግሽ፡፡ ይኼ ሁሉ የምታይው ብዙው የማይረባ ሰው ነው:: ይሉኝታ አይያዝሽ፡፡ ኢትዮጵያ ሺት ነገር ሆናለች፡፡ ትዳር ይፈርሳል በየቦታው………እንደ እኔ አይነቶች 'አፍርሱ' የተባልነውን እናፈርሳለን፡፡ ሻል ያለ ፈልጊ……..ጎጆ መውጣት' ምናምን ሲሉ ቃሉ ራሱ አያስቅም? እ? ሂሂሂ 'ቪላ መውጣት' 'መኪና መውጣት' አይሉትም እንዴ?………ሂሂሂሂ… የምትኖሪው አንድ ጊዜ ነው . አስናቀ ምንድነው? የሆነ ባርያ ነገር (ኣውጥታዋለች እኮ)

ወንድ ላሳይሽ? ያለው? የሚያበሉ የሚያጠጡ፣ የሚተኙ፣ የሚያለብሱ፡፡ ማሳደር የሚችሉ:: መኪናቸውን የሚያውሱ:: ሳይቆጥቡ የሚያሰክሩ

አዳም ረታ፡ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ገፅ 92
🔯שלום

የጥበብ - መንገድ 📖

28 Oct, 05:26


ሥነ ህላዌ (Metaphysics)

ከፍልስፍና ቅርንጫፎች ሁሉ ሥነ ህላዌ ‹‹መሰረታዊ›› ነው፡፡ ‹‹ህላዌ›› ስንል ህልውና ያለውን ነገር ሁሉ (ሰው፣ ተፈጥሮ፣ እግዚአብሔር፣ ነፍስ...) ያጠቃልላል፡፡ ስነ ህላዊ ‹‹መሰረታዊ ነው›› የሚያስብለው በሁለት ምክንያቶች ነው፣

የመጀመሪያው፣ ሁሉም ነገር የተመሰረተው ሀላዌ (ህልውና) ላይ በመሆኑና ሜታፊዚክስ ደግሞ መሰረታዊ ስለሆነው ስለ ህልውና አመጣጥና ባህሪ የሚያጠና በመሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ነው አሪስቶትል ሜታፊዚክስን ‹‹First Philosophy›› የሚለው፡፡ ‹‹First Philosophy because it deals with "first causes and the principles of things.

ሁለተኛው ደግሞ፣ ሌሎች የፍልስፍና ቅርንጫፎች የሚመዘዙት ከሥነ ህላዌ (ሜታፊዚክስ) በመሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የፕሌቶ የሥነ ዕውቀት፣ የሥነ ምግባር፣ የኪነ ጥበብና የፖለቲካ ፍልስፍናዎቹ በሙሉ የወጡት ከሥነ ህላዌ (ሜታፊዚክስ) ፍልስፍናው ነው፡፡

‹‹Metaphysics›› የግሪክ ቃል ሲሆን፣ ቃሉን የማርክሲዝም-ሌኒኒዝም መዝገበ ቃላት ‹‹ዲበአካል›› በማለት የግዕዝ ፍቺ ይሰጠዋል፡፡

ዲበአካል ማለት ከቁሳዊ ነገሮች ባሻገር የሚገኙ የረቂቅ ነገሮች ( ስለ እውነት፣ ንቃተ ህሊና፣ ሞትና ዘላለማዊነት፣ ስለ ፈጣሪ፣ ጊዜና ቦታ ...) ጥናት ማለት ነው።

ሜታፊዚክስ የሁለንታን (Universe) ባህርይና በውስጡ ያሉትን ህላዌያት በአጠቃላይ ይመረምራል። በምን ዓይነት ዓለም ውስጥ እየኖርን እንዳለን እና ልዕለተፈጥሮ (Supernatural) የሚባል ነገርስ ከዓለም ወዲያ ሊኖር ይችላል ወይ? ስለሚሉ ጥያቄዎች የሚያብራራ ነው።

‹‹Metaphysics›› የሚለው ቃል ከ‹‹ዲበአካል›› ይልቅ ‹‹ሥነ ህላዌ›› የሚለው ቃል ይበልጥ ይገልፀዋል፡፡ በመሆኑም፣ ሥነ ህላዌ (Metaphysics) ስለ ህላዌ የሚያጠና የፍልስፍና ቅርንጫፍ ነው። ህላዌ ስንል ማንኛውም ህልውና ያለውን ነገር (ሰው፣ ተፈጥሮ፣ እግዚአብሔር፣ መናፍስት...) ሁሉ የሚመለከት ነው። በመሆኑም ሥነ ህላዌ ስንል የማናቸውም ህልውና ያለው ነገር ጥናት ሲሆን በሕዋሶቻችን እርዳታ ልናውቃቸው የማንችላቸውን፣ ነገር ግን በማሰላሰል ላይ በተመሰረተ ትንታኔ ልናውቃቸው የምንችላቸውን ነገሮች የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው።

ለመሆኑ እነዚህ "በሕዋሶቻችን የማናውቃቸው፣ ሆኖም ግን በማሰላሰል የምንደርስባቸው ህላዌን የሚመለከቱ ነገሮች ምንድን ናቸው? የሚከተሉት ፅንሰ ሐሳቦችን ያጠቃልላል፣

፠የህልውና (ሰው፣ ተፈጥሮ፣ እግዚአብሔር፣ ነፍስ፣ መናፍስት... )ምንነትና ባህሪ

፠ሞትና ዘላለማዊነት (Death and Immortality)

፠ጊዜና ቦታ (Time and Space)

፠ አእምሮና አካል (Mind and Body /Matter)

፠መንስኤና ውጤት (Cause and Effect)

፠ንቃተ ህሊና (Consciousness)

፠እውነት፣ ነፃነት (Truth, Freedom)

በመሆኑም፣ በሥነ ህላዌ የምርምር ዘርፍ የሚነሱ ጥያቄዎች እነዚህን ፅንሰ ሐሳቦች የያዙ ናቸው፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፤

★ይሄ ዓለም እንዴት ህልው (Exist ሊያደርግ) ቻለ? ፈጣሪስ አለው?

★ፈጣሪ መኖሩን እንዴት ማወቅ እንችላለን? ማስረጃችን ምንድን ነው? የፈጣሪ ምንነቱና ባህሪው ምንድን ነው? እግዚአብሔር የሞራል ህላዌ (Moral Being የሚያዝን፣ የሚራራ፣ የሚያፈቅር፣ የሚቀጣ፡ የሚሸልም የሚፈርድ) ነው? ወይስ ፈጣሪ (Metaphysical Being) ብቻ ነው? እግዚእብሔር የሞራል ህላዌ ከሆነ በሰው ልጅ ላይ ይሄ ሁሉ አሰቃቂ መከራ ሲደርስበት እንዴት አስችሎት ዝም አለ? ለመሆኑስ ፈጣሪ ከፈጠረው አካል ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ያለ ነው? በዩኒቨርሱ ሥርዓት እና በሰው ህይወት ውስጥስ ጣልቃ ይገባል ወይስ ዩኒቨርሱ እሱ በሰጠው ህግና ሥርዓት እንዲሰራ ትቶታል?

★እውነት ምንድን ነው? እውነት አንድ ነው ወይስ ብዙ? እውነት አንፃራዊ ነው ወይስ በሁሉም ዘመን፣ ባህልና ቦታ የማይለዋወጥ ነገር ነው?

★ነፍስ የሚባል ነገር አለ? ሞት የህይወት የመጨረሻው ምዕራፍ ነው? ወይስ ከሞት በኋላ በሌላ ዓለም ሌላ ህይወት አለ? ይሄንንስ እንዴት ማወቅ እንችላለን?

★ጊዜ ምንድን ነው? በአእምሮ የሚፈጠር ነገር ነው ወይስ ከአእምሮ ውጭ ነዋሪ የሆነ ነገር ነው? ዩኒቨርሱ ከመፈጠሩ በፊት ጊዜ የሚባል ነገር ነበረ?

★ሰው ምንድን ነው? የሰው ምንነት በምንድን ነው የሚገለፀው በአእምሮ፣ በመለኮታዊት ነፍስ፣ በቁሳዊ አካል ወይስ በምን?

★ነፃነት ምንድን ነው? ዕጣ ፋንታ የሚባል ነገር አለ? የሰው ልጅ ዕጣ ፈንታ (መጪው ጊዜ) አስቀድዋ ተወስኗል ወይስ አልተወሰነም? የሰው ሐሳቦችና ስሜቶች ልክ እንደ እንሰሳት መካኒካዊ ናቸው ወይስ አይደሉም?

★የአካል እና የአእምሮ (የሐሳብ/መንፈስ) ግንኙነት ምንድን ነው? ተፈጥሯቸው የተለያዩ ሆነው ሳለ እንዴት ሊዛመዱና መስተጋብር ሊፈጥሩ ቻሉ? ለመሆኑ፣ ከአእምሮ ውጭ የሚኖር ዓለም አለ? ቁስ አካሎች ቀለም (Color) አላቸው? ወይስ ቀለማቸውን አእምሮ ነው የሚሰጣቸው?

★ተአምር የሚባል ነገር አለ? ነው ወይስ ሁሉም ነገር (ሁሉም ክስተት) በመንሰኤ– ውጤት ሰንሰለት የተያያዘ ነው?

ከእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ አንዳንዶቹን ፍልስፍና ከሃይማኖትና ከፊዚክስ ጋር የሚጋራቸው ናቸው፡፡ ለእነዚህ የሥነ ህላዌ ጥያቄዎች በየዘመኑ በሚነሱ ፈላስፋዎች የሚሰጡ መልሶች የተለያዩ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች ጋር በተገናኘ የተፈጠሩት የፍልሰፍና ሥርዓቶች የሚከተሉት ናቸው፣

✿ዕጣ ፋንታን በተመለከተ -Determinism, Existentialism,

✿ከፈጣሪ ህልውናና ባህሪ ጋር በተገናኘ የተፈጠሩት የፍልስፍና ሥርዓቶችና አቀንቃኞቻቸው የሚከተሉት ናቸው፤

1. Theism(አማኝነት- ሁሉም ሃይማኖቶች)

በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ ያሉ ልሂቃንና ፈላስፋዎች

2. Atheism ( ኢአማኝነት)

Democritus,Heraclitus, Epicurians, T. Hobbes, D. Hume, C. Darwin, JS Mill, Nietzsche, B. Russell, K. Marx, R. Dowkins

3. Panteism ( እ/ር እና ተፈጥሮ አንድ ናቸው)

Spinoza, Hegel, Schelling, Goethe, G. Bruno, RW. Emerson, A. Einstein

4. Deism (ፈጣሪ አለ፤ ግን ጣልቃ አይገባም)

Aristotle,Newton, አብዛኞቹ የዘመነ አብርሆት ፈላስፎች (Voltair, J. Locke, Rousseau)

5. Agnosticism (ኢታዋቂነት- ስለ እ/ር ማወቅ አይቻልም)


ምንጭ ፦ የፍልስፍና ትምህርት ቅፅ ፩
አርታኢና አዘጋጅ ፦ ብሩህ አለምነህ

የጥበብ - መንገድ 📖

27 Oct, 12:34


I sometimes forget
that I was created for Joy.

My mind is too busy.
My Heart is too heavy
for me to remember
that I have been
called to dance
the Sacred dance of life.

I was created to smile
To Love
To be lifted up
And to lift others up.

O’ Sacred One
Untangle my feet
from all that ensnares.
Free my soul.
That we might
Dance
and that our dancing
might be contagious.

~ Hafiz

የጥበብ - መንገድ 📖

26 Oct, 05:28


“Art is to console those who are broken by life.”

« ኪነት በህይወት የተሰበረውን ማጽናናት ነው »

― Vincent van Gogh

የጥበብ - መንገድ 📖

24 Oct, 15:01


“Why study philosophy?

Philosophy is to be studied, not for the sake of any definite answers to its questions, since no definite answers can, as a rule, be known to be true, but rather for the sake of the questions themselves; because these questions enlarge our conception of what is possible, enrich our intellectual imagination and diminish the dogmatic assurance which closes the mind against speculation; but above all because, through the greatness of the universe which philosophy contemplates, the mind is also rendered great, and becomes capable of that union with the universe which constitutes its highest good.“

— Bertrand Russell, The Problems of Philosophy (1912), Ch. XV: The Value of Philosophy, p. 127

━━

Background: The Problems of Philosophy (1912) by Bertrand Russell

First published in 1912, Bertrand Russell’s The Problems of Philosophy has never been out of print and is often considered essential reading for philosophy students. Russell, in his trademark usage of clear and concise language, introduces to the reader the key ideas of the great philosophers from Plato to Immanuel Kant, laying the foundation of philosophical inquiry.

Russell considers philosophy as a repeating series of (failed) attempts to answer the same questions:

•Can we prove that there is an external world?

Can we prove cause and effect?

• Can we validate any of our generalizations?

• Can we objectively justify morality?

He asserts that philosophy cannot answer any of these questions and that any value of philosophy must lie elsewhere than in offering proofs to these questions.

“In the following pages I have confined myself in the main to those problems of philosophy in regard to which I thought it possible to say something positive and constructive, since merely negative criticism seemed out of place. For this reason, theory of knowledge occupies a larger space than metaphysics in the present volume, and some topics much discussed by philosophers are treated very briefly, if at all.“

— Bertrand Russell, Preface of The Problems of Philosophy (1912)

የጥበብ - መንገድ 📖

24 Oct, 03:56


ህም...!

«...ፍርድ ያውቅበት የለ?
የህይወትን ትርጉም በአሽሙሩ ሲያራራው፣
ከሞት ያመለጠን ‹ኗሪ› ብሎ ጠራው። »

#ባባ

የጥበብ - መንገድ 📖

23 Oct, 16:21


..ድንገት ልታነብ መጽሐፍ ገልጠህ ፡የተቀዳልህን ቡና ረስተህ ፡ትንኝ ከገባበት ፡ወይም ቀዝቅዞ ከቀረ ፡ የመንገደኛ ጩኸት ሳያናጥብህ ፡አሊያ የኑሮ ጥድፊያ ሳይከትርህ፡በምናብ ዓለም ጭልጥ ብለህ ከነጎድክ ፡ ምናልባት! እያነበብከው ያለ መጽሐፍ የፊዶር ዶስቶቭስኪ ነው ፡፡
በሆነ ታዐምር ፡የዶስቶቭስኪን ገፀ ባህርያት ፡ልታነብ ልትመራመር ተሰልፈህ ፡ሁነኛ ቁምነገር ፈልገህ ስትቀዘመዘም ፡መልሰው የአንተን ነፍስ ያስነብቡሃል ፡ከጦር ሜዳ ሳይሆን ከራስህ ጋር ያነታርኩሃል ፡....የሰውን እድፍ እርቃን ሳይሆን የራስህን ገመና ፡ወለል እያደረጉ ያስነብቡሃል ፡፡
ከመጽሐፉ በጥቂቱ ለቅምሻ ያህል..

"በእርግጥ ሜሪ ቆንጆ ናት" ሁለት ጊዜ ከርቀት ነበር ያየኋት ፡፡እንደዚህ ዓይነት ውበት ነዋ የምታደንቀው "በማለት ሚሽኪንን በድንገት ፡ጠየቀችው
አዎ...ሲል በትግል መለሰላት፡፡
"ለምን ?"
በዚህ ፊት ላይ የሆነ ስቃይ ይታያል..."
አይኖቿ ውብ እና የዋህ ናቸው ፡ፍፁም ዝምተኛ ነበረች ፡እንደ ሌሎች ዝቅ አድርጌ እንደማላያት ነገርኳት ፡በራሷ እንዳትሸማቀቅ ላፅናናት ሞከርኩኝ ፡ይሁንና የተረዳችኝ አይመስለኝም ፡መሬቱን ያየች የሆነ ነገር ብትናገርም ቃላቷን አልሱማሁም ፡፡ተናግሬ ስጨርስ እጄን ሳመችኝ ፡የእርሷን እጅ ልስም ስሞክር ግን ነጠቀችኝ ፡የመንደሯ ትናንሽ ልጆች ያዩኝ በዚህ ቅጽበት ነበር ፡፡
ልጆች ብዙ ነገር ያውቃሉ፡፡ አንዳንዴ ከልጆች የምናገኘው ምክር ፡ከአዋቂወች ምክር ይልቃል ፡፡አንድ ትንሽ ወፍ በደስታ ሲመለከታችሁ ፡የዋህነቱን መካድ ይከብዳል ፡፡ልጆችን ወፎች የምላቸው በዚህ ዓለም ላይ ከአዕዋፍ የሚበልጥ ነገር እንደሌለ ስለማምን ነው ፡፡እውነቱን ለመናገር ከልጆች ጋር መሆን የትኛውንም ነፍስ ያድሳል..፡፡



"እድሜው የገፋ ሰው በድንገተኛ ፍቅር ሲታወር ምንም ሊያደርግ ይደፍራል፡ምክንያታዊነቱን በማጣት የሕፃን ስራ ሊሰራም ይችላል ፡፡"

"የሰው ልጅ ለገንዘብ ፍቅር ሲል ምንም ከማድረግ ወደኋላ እንደ ማይል አሁን ገባኝ ፡፡ስግብግብነት የዘመናችን አዲስ ልክፍት ሁኗል፡፡አንድ ሰው ለገንዘብ ሲል የጓደኛውን አንገት ቆርጦ እንደ በግ የሚያርድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ፡፡"
የገንዘብ መጥፎው ነገር የሕይወት ክህሎት ን ሳይቀር መግዛት መቻሉ ነው ፡፡እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ!

እስኪ ደግሞ...

''የተከበሩ ሆይ -በዚህ ቡድን ውስጥ ኹሉም ሰው ጭዋታ አዋቂ ነው ፡፡እኔ ግን ለዛ ቢስ ነኝ ፡፡ለዛ ቢስነቴን ለማካካስ ግን እውነት ተናጋሪ ነኝ ፡፡በዚያ ላይ ደግሞ በቀለኛ ነኝ ፡በቀለኛ የሆንኩት ምናልባትም ቀልደኛ ባለመሆኔ ይመስለኛል ፡እኔን ያጠቃኝ ሰው በሚዳከምበት ጊዜ ጠብቄ ቂሜን የምወጣበት መሆኑ የተለየ ያደርገኛል ፡፡የሰው ልጅ በእብሪት ተገፋፍቶ ምን እንደሚያደርግ ማወቅ አትችልም ፡፡

በሆነ ምክንያት ኹሉም ሰው የዋህ ፡ሞኝ እና ነሆለል አድርጎ ይመለከተኛል ፡፡ምናልባት በወቅቱ ታምሜ ስለ ነበር ጅል ሳልሆን አልቀርም ፡፡ይሁንና ሌሎች እንደ ጅል እያዩኝ መሆኔን ከተረዳሁ እንዴት ጅል ልሆን እችላለሁ? ወደ ዚህ ሀሳብ ስገባ "እንደ የዋህ እያዩኝ ነው ፡፡አስተዋይና አዋቂ መሆኔን ሊገምቱ አልቻሉም" በማለት ለራሴ ነገርኩት ፡፡ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ሀሳብ በውስጤ ይመላለሳል ፡፡

"ፍላጎቴ የእውነት ውብ የሆነች ን ነፍስ በቃላት መሳል ነው ፡፡"

.....ይቀጥላል!!

ፊይዶር ዴስቶቭስኪ ❤️

የጥበብ - መንገድ 📖

23 Oct, 13:39


አይ መርካቶ !

የከበረ እንደመረዋ ረብጣ አፍኖት ሲያስገመግም
የከሰረ እንደ ፈላስፋ ፥ በቁም ቅዠት ሲያልጎመጉም

©Tsegaye G/medhin

የጥበብ - መንገድ 📖

23 Oct, 09:15


ፍልስፍና፣ ሳይንስ፣ ሀይማኖት

ሁላችንም በአካባቢያችን ህንፃ ሲገነባ ተመልክተናል። ግንባታው ሲጀመር በትላልቅ ድንጋዮች የህንፃው መሰረት ይጣልና ስትራክቸሩ ከመሬት ይወጣል። ግንባታው ከፍ ሲልና ከላይ ያለው የህንፃው አካል ተገንብቶ አልቆ አመታት ሲያልፉ ግን መስታዎቱን እና አልሙንየሙን ብቻ እያየን ከመሬት በታች ያለውን መሰረት እንረሳለን።

እና ምን ለማለት ነው ሳይንስ፣ ሀይማኖትም ሆነ ፖለቲካ የቆሙት ፍልስፍና በሚባል መሰረት ላይ ነው።

ድንገት በምድር ላይ ራሱን ያገኘው የሰው ልጅ ስለ ራሱ እና በዙሪያው
ስለሚገኙ ነገሮች ማሰብ እና ከየት እንደመጡ መጠየቅ/መመርመር የጀመረበት ቅፅበት ነው ፍልስፍና። …ወደ ጥንታዊቷ ግሪክ ተመልሰን ለዛሬ አስተሳሰባችን መሰረት የጣሉ ሁለት ታላላቅ ፈላስፎችን እንመልከት ---- ፕሌቶ እና አርስቶትል

ለፕሌቶ ይህ እኛ ያለንበት ምድር ከፍፅምና የራቀ እና አላፊ ጠፊ በመሆኑ እውነተኛው አለም ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ሌላ አለም አለ። ፍፁም የሆነ ፈጣሪና፣ ዘላለማዊ እና አለም አቀፋዊ የሆኑ (ሀሳቦች) የሚገኙበት በአይናችን የማይታይ ሌላ አለም በሰማይ አለ።

እናም የዛኛው አለም ጥላ የሆነች ምድርን እና በውስጧ የያዘችውን ኮተት በመመልከት እውነተኛ እውቀት ላይ እደርሳለሁ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። የምድር ጥበብና ስልጣኔ ሁሉ በአይናችን እርግብግቢት ፍጥነት እንደ ባቢሎን ግንብ ከመፍረስ አይድንም።

ጠቢብ ምድራዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ግዜውን አያባክንም። በማትሞተው ነፍሱ አማካኝነት ፤ ፍፁም የሆነ ፈጣሪውን እና እውነተኛውን አለም ሊያውቅ ይገባል።

ይህ የፕሌቶ ፍልስፍና ከክርስቶስ አስተምህሮ ጋር ተዋህዶ ለ1500 ዓመታት በአውሮፓ ላይ ነገሰ። በዚህ ሀሳብ መሰረት መጨነቅ ያለብን ስለዛኛው አለም እንጂ ስለ ምድራዊ ህይወት አይደለም። እውቀት የሚገኘው አካባቢያችንን በመመልከት ሳይሆን በምክንያታዊነት
ልቦናችን ውስጥ የተፃፈውን እውነት በመመርመር እና 'በመገለጥ' ነው።
ይህ ዘመን በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ የጨለማው ዘመን በመባል ይታወቃል።

የፕሌቶ ተማሪ ለነበረው አርስቶትል ግን እውነትም ሆነ እውቀት መፈለግ
ያለባቸው እዚሁ ምድር ላይ ነው።
- የእውቀት መነሻ የስሜት ህዋሳቶቻችን ሲሆኑ
- በስሜት ህዋሳቶቻችን የሰበሰብነውን መረጃ ተጠቅመን አንዳች እውቀት ላይ ለመድረስ ከፈለግን ልንከተለው የሚገባ የአስተሳሰብ ስልት አለ። ይህ ስልት ሎጂክ ይባላል ፤ የፈጠረው አርስቶትል ነው።
አሁን የትኛውም ሳይንቲስት ካለ DEDUCTION እና INDUCTION አንዳችም ስራ አይሰራም። Biology , physics, psychology, chemistry ለመሳሰሉት የሳይንስ ዘርፎች መሰረት ጥሏል ፡
ለዚህም ነው አርስቶትል የመጀመሪያው ሳይንቲስት ነው የምንለው።

አውሮፓ ለ1500 አመታት እነ አርስቶትልን ችላ ብላ ‘አንተ ታቃለህ’ እያለች ኖረች፣ ኖረች ኖረችና የጨለማው ህይወት ስልችት ቢላት በፈላስፎቿ መሪነት ሻማ አብርታ ጨለማውን ለመታገል ተዘጋጀች።
ይህ ዘመን በአውሮፓ ታሪክ ውስጥ የአብርሆት ዘመን ENLIGHTENMENT/ እየተባለ ይጠራል። (My favorite thinker ኒቼ፥ ከዘመነ አብርሆት በኋላ አማልክቱ ከእያንዳንዱ ሁነት ጣልቃ ገብነት ውጭ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት “እግዚአብሄር ሞቷል” ሲል ገልፆታል።¹) 1. ይህ አረፍተ ነገር በ'ኔ የተጨመረ።

የዘመናዊው ታሪክ ታላቁ ፈላስፋ ካንት ስለ አብርሆት እንዲህ ይለናል፥ “አብርሆት ማለት ሰው በገዛ ምርጫው ራሱ ላይ ከጫነው ድንቁርና ነፃ
የወጣበት ዘመን ነው።”

እነ ኒውተን የማይለዋወጡ የተፈጥሮ ህጎችን አገኙ። መብረቅ የእግዜር ቁጣ፤ ዝናብ ደግሞ የእግዜር በረከት አይደለም ተፈጥሯዊ ሂደት አለው።
በያመቱ የኮሌራ ወረርሽኝ ህዝባችንን የሚፈጀው እግዜርን ስለምናደድነው ሳይሆን የተበከለ ውሀ እና ምግብ ስለምንበላ ነው። እናም ትንሽ ብንመራመር ሁሉንም ችግር መረዳት እና መፍትሄ ማምጣት እንችላለን ብለው ተነሱ። “ተፈጥሮ የምትመራው በራሷ የተፈጥሮ ቀመር እንጂ በሌላ ውጫዊ ኃይል አይደለም”

ነገር ግን እነ ኒውተን ቋሚ የተፈጥሮ ህግጋትን ማየት ቢችሉም ፈጣሪ የለም ለማለት አልደፈሩም። (ኒውተን በሄደበት ሁሉ መፅሀፍ ቅዱስ ይዞ ነበር የሚዞረው) ምክንያቱም ተፈጥሮን ማን አስጀመረው የሚለው ጥያቄ ያስጨንቃቸው ነበር። መቼም እንዲህ ያለ ውስብስብ እና ድንቅ ተፈጥሮ ካለፈጣሪ አይታሰብም። እናም ተፈጥሮ እንደ ሰአት ናት፤ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ፈጥሯት በራሷ ህግጋት እንድትመራ ትቷት ሄዷል አሉ።

አማኝ የነበረው ካንትም አለ “እዚሁ ምድር ላይ ሁለት አይነት አለም አለ
የመጀመሪያው ይህ በስሜት ህዋሳታችን የምንረዳው ፤ በተፈጥሮ እና በኛ አዕምሮ ትብብር የተፈጠረ፣ በግዜ እና ቦታ የታጠረ ለኛ የሚታየን አለም (THE PHENOMENAL WORLD) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከሰው አንግል ሳይሆን ከፈጣሪ አንግል የሚታይ እውነተኛ አለም ነው። (THE NOMENAL WORLD)

ይህ እኛ የሚታየን አለም የሚመራው በመንስኤ እና ውጤት ስለሆነ የዚህ ምድር ገዢ መሆን ያለበት ምክንያት እና ሳይንስ ነው። ስለዛኛው አለም ያለን እምነት በምድር ህግጋት ውስጥ ጣልቃ አይገባም ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ስለዛኛው አለም እና ፈጣሪ 'እውቀት እና ምክንያት' ምንም ማለት አይችልም።“ “I had to deny knowledge in order to make room for faith.”

ፈረንሳዮች እግዚያብሄር ነው የሾመን እያሉ ሲገዙዋቸው የነበሩትን
ነገስታቶቻቸውን በአደባባይ እስኪያርዱ ድረስ ካንት ያደረገው ክፍፍል እና ይዞት ሊመጣ የሚችለውን ጣጣ የተረዳ አልነበረም።

ዳርዊን ደግሞ መጣና ይህን ፈጣሪ አላስፈላጊ አደረገው። ተፈጥሮ በ
NATURAL SELECTION አማካኝነት በረጅም ግዜ ሂደት ውስጥ እንዴት ራሷን ዲዛይን እያደረገች እንደመጣች የሚያሳይ ቲዮሪ ነደፈ።
ይህ ቲዮሪ በቅሪተ አካሎች እና በDNA ጥናት(?) ተረጋገጠ።

ከካንት በኋላ ፍልስፍና ትኩረቱን እዚሁ ምድር ላይ አድርጎ በሰዎች መሀል ያለ የኢኮኖሚ እና የሀይል ግንኙነት እያጠና ቆይቷል ። ማርክስ የሚባል አንድ ፈላስፋ የፃፈው ሀሳብ የ20ኛውን ክፍለ ዘመን መንግስታት እና ህዝቦች ሁሉ ከኋላ ሆኖ እየጋለበ ሲያፋጀን ኖሯል። አሁንም የማንነት ፖለቲካው ከጀርባ ባሉ የድህረ ዘመናዊ ፈላስፎች እየተመራ ይገኛል።

በኔ እምነት እኛ ኢትዮጵያውያን አሁንም በጨለማው ዘመን ላይ ቆማናል! …በዚህ በ21ኛው ክ/ዘመን ኮሮናን ለማጥፋት ተሰብስበን ካልፀለይን እንላለን፤ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሀዊ መንግስት እንዲመጣ ከመስራት ይልቅ፣ በራዕይ የተነገረለት 'ቴዎድሮስ' እንዲመጣ እንፀልያለን ። በሸሪዓ ህግ ካልተመራሁ እንላለን። (ስልክ፣ መብራት ፣ ውሀ መድሀኒት …) በሳይንስ በረከቶች ላይ ህይወታችንን መስርተን ፤ ሳይንስን እንንቃለን።

እናም እንደሀገር ለሳይንስ እና ለእውቀት በር የሚከፍት ፤መንፈሳዊ መሻታችንን ያልዘነጋ የአብርሆት ፍልስፍና ያስፈልገናል።

የጥበብ - መንገድ 📖

22 Oct, 03:59


ለአፍታ ወደ እሳቤዬ የመጣብኝ ትንታዊ ሃሳብ

(An introspection)

ግን... ይህች ህይወት የምንላት... እያንዳንዳችንን ተነስተን እስክንተኛ ድረስ... ለሆነ ለማናውቀው አንዳች የፈጣሪ ኃይል... በማናውቀው አንዳች መንገድ... ስታስደንሰን፣ ስታወዛውዘን፣ የአምልኮ ቁሳቁሳችንን አስይዛ በየራሳችን የተለየ መንገድ፣ በየራሳችን ልዩ ስልት.. ስናሸበሽብ ውለን እንድናድር የምታደርገን... አንዳች ዓይነት ስልታዊ፣ ምሥጢራዊ፣ ሴረሞኒያዊ የየዕለት አምልኳዊ ሥርዓት ብትሆንስ?

What if life is a kind of ritual of worship to an unknown creator, a God, who is fond of our every move and costume and sacred objects?

What if every step of everyone's life each day is a ritual of worship, a sacred supplication to the ultimate power who designed our every chorus?

እያንዳንዷ የምናደርጋት እንቅስቃሴ፣ የምናነሳትና የምንጥላት ዕቃ፣ የምንራመዳት መንገድ፣ የምንጎርሳት የምንዘራት እያንዳንዷ ነገር፣ የምንስቃት የምናለቅሳት ሁሉ ጠብታ... በሆነ የማናውቀው ታላቅ አምላክ የተፃፈልን የአምልኮ እንቅስቃሴ ቢሆንስ?

ህይወት እያልን የምንጠራው ነገር በሆነ አንዳች ኃይል እንተውነው ዘንድ ተፅፎ በውስጣችን ስንፈጠር ጀምሮ የተገጠመልን የሆነ ዓይነት በመኖር የሚተወን አንዳች ትያትራዊ ተውኔት ቢሆንስ?

የምንናገራት እያንዳንዷ ቃል ከእኛ ውጭ በሆነ አካል ተፅፎ የተሰጠንን አንዳች ዓይነት የሙዚቃ ኖታ የሚከተል ቢሆንስ? በየዕለቱ ወደየምንሄድበት ቦታ የሚመራን አንዳች ዓይነት በየውስጣችን የተገጠመልን ዲዛይን ቢኖርስ?

ሁላችንም እየኖርን ነው የምንለው ሰዎች በማናውቀው መንገድ እያሸበሸብን የምንገኝ የሆነ ሥርዓተ አምልኮ ፈፃሚዎች ብንሆንስ?

ዓለም የትያትር መድረክ፣ እኛ ሰዎቿም ሚና የተሰጠን ተዋንያን ብንሆንስ? የሆነ አምላክ ወይም አማልክት እያነዳንዱን እንቅስቃሴያችንን በማናውቀው ሥፍራ ቆመው ዳይሬክት እያደረጉት ቢሆንስ?

ህይወት የምንለው ከእያንዳንዱ በህዋው ላይ ካለ የከዋክብት ቅንጣት ጋር በጋራ የምናሸበሽብብበት የሆነ ንፍቀ ዓለማዊ ታላቅ የተፈጥሮ ዳንስ ትርዒት አካል ቢሆንስ?

የሚሉ ጥያቄዎችን ያሰቡ አንዳንድ አሰላሳዮችን አውቃለሁ። ድንገት ሃሳባቸው ውል አለብኝ። እውነታቸውን ቢሆንስ? ማን ያውቃል? እንቅስቃሴዎች ሁሉ ቅዳሴ፣ እርምጃዎች ሁሉ ዳንስ፣ ጎንበስ ቀናዎች ሁሉ አምልኮ፣ ቃላት ሁሉ ዝማሬዎች ቢሆኑስ?

ማን አየ? ማንስ አረጋገጠ? መሆኑንስ፣ አለመሆኑንስ?

But surely there's something sacred about our every move. There's something sanctified about our existence. Every form of existence doesn't feel like a simple, a mere, meaningless existence.


©Asefa Hailu

2,095

subscribers

200

photos

2

videos