በሶሞኑ የሓራና ሀሮ ጉዞዬ በጣም የሚገርምና በሐዘንና የአድናቆት የተደበላለቀ ስሜት የእንባ ቧንቧ የሚከፍት እውነተኛ ታሪክ ሰምቼ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ ። ታሪኩንም እንደሚከተለው አቀርብላችኋለሁ : –
ክስተቱ በወሎ ዞንተንታ በምትባለው የሀገራችን ክፍል የተከሰተ ነው ። እንደሚታወቀው ሀገራችን ውስጥ በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ የሽርክ አይነቶች ይሰራሉ ። ሽርክ ደግሞ ደረካቱ ይለያያል ። የሽርክ አይነቶች ሁሉ እኩል አይደሉም ። በጣም አሰከፊ የሽርክ አይነት ከሚካሄድባቸው አካባቢዮች አንዱ የወሎ ዞን ነው ። ወሎ አካባቢ የሽርክ ኮተትና ግሳንግስ ሲሆን የሚሰሩ የሽርክ አይነቶች የህፃናት ፀጉር የሚያሸብቱ ናቸው ። ሽርክ መሰራቱ ብቻ ቢሆን ባልከፋ ነበር ነገር ግን እነዚህ የሽርክ ተግባር የሚሰሩ አካላት ከእነርሱ ጋር አብሮ ያልሰራን ወሀብይ በሚል የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ባይተዋር እንዲሆን ማእቀብ በመጣል ራሱን እንዲጠላ ያደርጋሉ ።
የዘህ ግፍና በደል ገፈት ቀማሽ ከሚሆኑት የአላህ ባሮች ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ደቡብ ወሎ ተንታ በምትባለዋ መንደር ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ሸይኽ አሕመድ ዐ/ወሀብ አንዱ ናቸው ። እኝህ ሸይኽ ሽርክን በአይነቱ አውግዘው አድባር ቆሌ አልገዛም ፣ የሙታንን መንፈስ አልለማመንም ፣ ፍጡርን ድረሱልኝ ብዬ ከጌታዬ ደጃፍ መባረር አልመርጥም ፣ በቂዬ አላህ ነው እሱን ብቻ ነው የማመልከው ፣ የምከጅለውና የምለምነው ፣ ከጭንቅ አውጣኝ ፣ ተምኪን ፈልጌያለሁ ብዬ እጄን ምዘረጋው ወደርሱ ብቻ ነው በማለታቸው ከአካባቢ ማህበረሰብ እንዲገለሉ ተደረጉ ። በዚህ አላበቃም ማእቀቡ ቢታመሙም ቢታመምባቸውም እንዳይጠየቁ ፣ ቤተሰባቸውም ሆነ እሳቸውም ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ፣ ቢሞቱ እንዳይቀበሩ ፣ ቢሞትባቸውም እንዳይቀበርላቸው ፣ ምንም አይነት ችግር ቢገጥማቸው ማንም እንዳይረዳቸው ተወሰነባቸው ።
ይሁን እንጂ እኚህ ሸይኽ ከማህበሰቡ የተጣለውን ማእቀብ ከቁብ ሳይቆጥሩ ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን ይዘው በማህበረሰቡ የተወገዙና የተረገሙ እየተባሉ አላህ በቂያችን ነው ብለው የህይወትን ጉዞ ጀመሩ ። ይህ ሲሆን የሱና ሰዎችን ለማግኘት ደርሶ መልስ የ6 ሳአት መንገድ የሚሆን ቦታ ሄደው እየመጡ የባይተዋርነት ስሜታቸውን እያቀጨጩ ነበር ።
እኚህ ጉደኛ ሸይኽ አላህ ይህን ፅናታቸውን የሚፈታተን ፈተና እንዲገጥማቸው ፈለገ ። ልቻቸው በጠና ታመመ ። ልጃቸውን ሐኪም ቤት አስገብተው ያለ ጠያቂና ያለ ተተኪ ሲያስታምሙ ቆዩ ። የአላህ ውሳኔ ሆነና ልጃቸው ወደ አኼራ ሄደ ። ቤታቸው ከሐኪም ቤቱ በእግር የ3 ሳአት መንገድ ያስኬዳል ። መኪና ለመከራየት አቅም አልነበራቸውም ። አብሽር ብሎ የሚያፅናና ቤተሰብም ሆነ ጎረቤት አጠገባቸው የለም ። የልጃቸውን ጀናዛ ተሸክመው የሶስት ሳአት መንገድ ተጉዘው ቤታቸው ደረሱ ። እናትና አባት የልጃቸውን ጀናዛ አጥበው ከፍነው ተሸክመው ወስደው ቀበሩ ።‼ሱብሓነ ላህ ለስሙ በሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ ነው ያሉት ነገር ግን አላህ በቂያችን ነው እንዴት ትላላችሁ ተብለው በዚህ መልኩ ታሪክ የማይረሳው አላህ ፊት አሳፋሪ የሆነ ተግባር ተፈፀባቸው ።
እኚህ ጉደኛ አባትና እናት ልጃቸውን ቀብረው ተመልሰው አላህ በቂያችን ነው ይህ ለተውሒድ ከሚከፈል ዋጋ አንፃር ኢምንት ነው አሉ ። አላህ የፈለገውን ይሰራል ልጃችንን እኛ ቀብረነዋል ሁላችንም ሞተን ሬሳችን አውሬ ቢበላውም አላህን ከማምለክ ሊያግደን የሚችል አይኖርም ይላሉ ።
ከዚህ መራራ ፈተና በኋላ ግን ሶብራቸውና ፅናታቸው ፍሬ አፍርቶ ትላልቅ መሻኢኾች እንደነ ሸይኽ ኢስማኢል ፣ ሸይኽ ዐ/ ሰመድ ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ሓያትና ሌሎችም ወደ ተውሒድ ተመልሰው በአሁነ ሳአት ተንታ አካባቢ በሸይኽ ኢስማኢል አማካይነት የተውሒድና ሱና ዳዕዋ እየተስፋፋ ነው ። ኪታቦች ይቀራሉ ፣ ሙሓደራዎች ይደረጋሉ ፣ ልጆች ተውሒድና ሱና ይማራሉ ፣ ባጠቃላይ የሰለፍያ ዳዕዋ ችግኝ እያበበ ነው ።
ይህ የሆነው በተጣለባቸው የግፍ ማእቀብ ለ30 አመት አካባቢ በፅናት የታገሉት ሸይኽ አሕመድ ዐ/ወሃብ በህይወት እያሉ ነው ። በአሁኑ የሓሮ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እንደሚመጡ ሸይኽ ሙሐመድ ሓያት ደውለው ከነገሯቸው በኋላ ጉዳይ ገጥሟቸው መጥተው ለማየት ሳንታደል ቀርተናል ። እስኪ ይህን ታሪክ የምናነብ ወደራሳችን እንመልከት እኛ ለነብዩ ዲን ምን የከፈልነው ዋጋ አለ ? አላህ ይዘንልን ።
https://t.me/bahruteka