Ethio Mereja @ethiomerejatoday Channel on Telegram

Ethio Mereja

@ethiomerejatoday


Ethio Mereja (English)

Ethio Mereja is a vibrant and engaging Telegram channel that provides the latest news, updates, and insights about Ethiopia. With a focus on current affairs, politics, culture, and more, Ethio Mereja is the go-to source for anyone looking to stay informed and connected with the Ethiopian community. Whether you are a diaspora member wanting to stay in touch with your roots or a local resident wanting to keep up with the latest happenings, Ethio Mereja has got you covered. The channel is run by a team of dedicated journalists and content creators who are passionate about delivering accurate and thought-provoking content to their audience. Join the Ethio Mereja channel today and be a part of the conversation that is shaping the future of Ethiopia!

Ethio Mereja

25 Oct, 18:21


የዋርካው ምሬ ልጆች የከተማ ሰርጅካል ኦፕሬሽን ፈጻሚዎች❤️

Ethio Mereja

14 Oct, 08:39


መረጃ!

ዛሬ ጠዋት ከባሕር ዳር ቅርብ ርቀት የድሮን እና የሄሌኮፍተር ጥቃት ተፈጽሟል። ብልጽግና የሕዝብ ተቋማትን እያወደመ ይገኛል። ጠዋት 2:30 ጀምሮ ሰሜን ጎጃም ደቡብ አቸፈር እና ሰሜን ሜጫ ወረዳ ላይ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ንጹሃን ተጎድተዋል፤ ተቋማት ወድመዋል።
ደቡብ አቸፈር ዝህብስት ቀበሌ ዝህብስት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከኤሌኮፍተር በተጣሉ ቦምቦች ተደብድቧል። በዚያው አካባቢ ያለ የመንገድ ስራ ካምፕ ላይም ቦምቦች ተጥለዋል። እስካሁን አንዲት ህጻንን ጨምሮ ንጹሃን ላይ ጉዳት መድረሱን ምንጮች አረጋግጠዋል።
በሰሜን ሜጫ ብጢ አካባቢ ደግሞ በጠዋት የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ ገበሬዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ አካባቢ ተደጋጋሚ ድሮን ጥቃቶች እየተፈጸሙ ሲሆን፣ ከሲቪሎች ሞት በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች፣ የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎችና የገበሬ ቤቶች ወድመዋል።

Ethio Mereja

09 Oct, 13:00


#ሰበር_ዜና
በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በኤርትራ መንግስት ፈቃድ መከልለከል ምክንያት የቋረጠ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለት ሀገራትን የሚያገናኘው የስልክ መስመርም ተቋርጧል።

Ethio Mereja

08 Oct, 08:47


ሳምንታትን በወሰደ ተደጋጋሚ ተጋድሎ የታዱ አንተነህ ቁዬ ደጋ ዳሞትን ነፃ ማድረግ ተችሏል።

በቀጠናው ጠላት ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው ወረዳወች መካከል አንዷ የሆነቸው ደጋ ዳሞት፥ የፋኖ ተጋድሎ ክስተት የሆነውን ሻለቃ ዝናቡን ያበረከተችልን ደጋ ዳሞት፥ የጮቄ አናት ላይ የምትገኘዋ ፈረስ ቤት ነፃ ሆናለች።

Ethio Mereja

08 Oct, 08:04


ዘመቻ መቶ ተራሮች እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው ዕለትም 5ኛ ክፍለ ጦር ጠላትን በመጥረግ ላይ ይገኛል::

የመከላከያ እና አድማ ብተና አባላት ታሪካዊ ውሳኔ እየወሰኑ ነው:: በቡሬ ቀጠና ህዝብ እንዲጨፈጭፉ ስምሪት ከወሰዱት መካከል 80 ያህክሉ ወገናችንን አንዋጋም ብለው ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የአማራ ፋኖ በጎጃምን ተቀላቅለዋል።

Ethio Mereja

07 Oct, 18:57


ህውሀት መፈንቅለ ስልጣን አደረገብኝ ሲል የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ
=============================
በዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው ህወሓት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 13 የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናትን ከስልጣናቸው እንዲወርዱ መወሰኑን ካሳወቀ በኋላ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር፣ የህወሓቱ ቡድን በግልፅ "መፈንቅለ ስልጣን እንዲደረግብኝ አውጇል" ሲል ዛሬ ማምሻውን ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል። ይህም "ስርዓተ አልበኝነት እንዲሰፍን ፍላጎት እንዳለው ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ሲል በመግለጫው አመልክቷል። «ከዚህ በፊትም የተለያዩ ማደናገርያዎችን እያሰራጨ ቆይቷል ሲልም ህወሃትን ከሷል። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በዚህ «የጥፋት ኃይል» ባለው ቡድን ላይ ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር ፤በዚህ ሰበብም ለሚፈጠር ማንኛውም ጥፋትም ተጠያቂዎቹ ቡድኑ እና አመራሩ ይሆናሉ ብሏል።

Ethio Mereja

05 Oct, 07:28


#እንደምናሸንፍ_እርግጠኞች_ነን
=====================
ዘመቻ መቶ ተራሮች በፋኖ አሸናፊነት
እየተመራ ከተሞችን ከብልፅግና እጅ እየነጠቀ ነው መጨረሻውን ለማየት ከዘመቻው አትራቁ ሲል ጀኔራል ዝናቡ ልንገረው የአማራ ፋኖ በጎጃም ዋና ጦር አዛዥ ተናግሯል።

Ethio Mereja

04 Oct, 04:56


የአማራ ፋኖ በጎጃም የዞን ዋና ከተማ ወደ ሆነችው #ፍኖተ_ሰላም ዘልቀው ገብተዋል።የፋኖ ኃይሎች መከላከያ እና አድማ ብተናን ከከተማዋ አስወጥተው ወደ ካምፕ እንዲገባ አድርገውታል ተብሏል።በዚህም በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ፋኖዎች እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Ethio Mereja

21 Sep, 18:30


#አርማጭሆ_ጎንደር_ታሪክ_ሰራ💚💛
👉የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎቤ ክፍለ ጦር ውስጥ #ክርስቲያን_ታደለ_ብርጌድ ተሰይሟል።በጌምድር አማራነቱን አውርቶ ሳይሆን ተግብሮ ነው የሚሳይ የመይሳው የገብርየ ልጆች ኮርተንባችኃል።

Ethio Mereja

06 Sep, 11:23


የሱዳን ጦር ከፋኖ ታጣቂዎች ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ትጥቅ ማስፈታቱ ተነገረ። እንደ ሱዳን ትሪቢዩን ዘገባ የኢትዮጵያ ወታደሮች የድንበር ከተማ በሆነችው መተማ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የነበረውን ውጊያ ተከትሎ ወደ ሱዳኗ ገላባት ከተማ ሸሽተዋል። የፋኖ ታጣቂዎች መልሰው የያዙትን መተማ ከተማን ሰኞ ዕለት ለአጭር ጊዜ ለቀውት እንደነበር ነው የተገለጸው። መተማ ላይ ውጊያ በሚካሄበት ጊዜም በርካታ የመንግሥት ወታደሮች እና «በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች» ወደ ሱዳን ግዛት ውስጥ በመግባት ተጠልለዋል። የሱዳን ወታደሮችም 77 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ትጥቅ እንዳስፈቱ ዘገባው አመልክቷል። ሱዳንም ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚያሸጋግረውን የድንበሯን አካባቢ በመዝጋት ተጨማሪ ወታደሮቿን ማሰማራቷንም ሱዳን ትሪቢዩን በዘገባው ጠቅሷል። መተማ ላይ በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግሥት ወታደሮች መካከል የሚካከል ጋብ ብሎ የነበረው ተኩስ ትናንት ከቀትር በኋላ 11 ሰዓት ገደማ ዳግም ማገርሸቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሚዲያችን ተናግረዋል።

Ethio Mereja

29 Aug, 17:16


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር) ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ነው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት የነበሩት አንድርያስ እሸቴ (ፕ/ር)÷በፍልስፍና መምህርነት፣ በተመራማሪነትና በአማካሪነት አገልግለዋል፡፡

Ethio Mereja

29 Aug, 12:32


#አማራዎች_ታገቱ
ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ መሀከል አንድ የህዝብ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ከሾፌር ረዳት ጋር በዘራፊ ወንበዴዎች በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።

Ethio Mereja

25 Aug, 09:34


ፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ
****

ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ፦
• ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
• አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
• ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
• ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
• ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
• እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።

Ethio Mereja

18 Aug, 13:20


* እኔም ነገ ልጅ ይኖረኛል
* ታናሽ እህት አለችኝ
* ይህን ለማውገዝ ሰው መሆን በቂ ነው
* ሄቨን የኔም ልጅ ነች

Ethio Mereja

18 Aug, 11:50


ፍትህ

Ethio Mereja

17 Aug, 15:46


ወደ ውጊያ መግባት ነው ያለን አማራጭ👉አቶ ጌታቸው አሰፋ
======================
ህውሀት እያካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ዛሬ ጠዋት ከቡድን ውይይት በኋላ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚከተለውን መናገራቸውን በትግራይ ክልል አክትቪስቶች ዘንድ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል።የፌዴራል መንግስት ተዳክሟል። የትግራይ መስተዳድርም ጠላታችን ሆኗል። ስለዚህ ከእንግዲህ በኋላ ካድሬውን ይዘን ህዝቡንም አነሳስተን ወደ ውግያ መግባት ነው ያለን አማራጭ። በፕሪቶሪያ ምክንያት መንግስታችን ፈርሷል፣አጋዥ ከሆኑ ሀገሮች ከእነ ሻዕቢያ ጥሩ ግንኙነት ተጀምሯል፣ሁሉም አመራር ለመስዋዕትነት ይዘጋጅ ሲሉ ተናግረዋል ተብሏል።