Exit Exam For All Department @exit_exams Channel on Telegram

Exit Exam For All Department

@exit_exams


@ 2016 GC Exit Exam Batch

Exit Exam For All Department (English)

Are you a recent graduate looking to test your knowledge and skills across various departments? Look no further than the Exit Exam For All Department channel on Telegram! Join us at @exit_exams to challenge yourself and see how you measure up against your peers. The Exit Exam For All Department channel is dedicated to helping recent graduates from the 2016 GC Exit Exam Batch prepare for their future careers. Whether you studied engineering, business, arts, or any other field, this channel offers a comprehensive examination that covers a wide range of topics and competencies. Who is it for? This channel is for recent graduates who want to assess their readiness for the job market and further studies. It is also suitable for professionals looking to brush up on their skills and knowledge in various departments. What is it? The Exit Exam For All Department channel provides a platform for individuals to test their understanding of different subjects, ranging from technical to theoretical. By participating in the exit exams offered here, users can identify their strengths and weaknesses, ultimately helping them make informed decisions about their career paths. Join us today at @exit_exams and start preparing for success in your chosen field! Take the first step towards a bright future with our challenging and insightful exit exams. Good luck!

Exit Exam For All Department

13 Nov, 08:04


የጥሪ ማስታወቂያ


ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ አመት የመደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ በትምህርት ሚኒስተር ለተመደባችሁ እና በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 09 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ ከዚህ በታች የተገለፁትን ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

👉የ12ኛ ክፍል የት/ት ማስረጃ ዋናዉ እና ኮፒው

👉ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናዉ እና ኮፒው

👉የ8ኛ ክፍል የት/ት ማስረጃ ዋናው እና ኮፒው

👉ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ፡-

የትምህርት ማመልከቻ እና ምዝገባ የሚከናወነው በኦንላይን (online system) http://estudent.mwu.edu.et/auth/login ሊንክ በመጠቀም ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሮቤ ካምፓስ በአካል በመገኘት በኦንላይን እንሰድትመዘገቡ እናሳስባለን።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስተር ለተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል።

ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Exit Exam For All Department

09 Nov, 04:40


# አዲስ ማስታወቂያ

ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ አዲስ ለተመደባችሁና የ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ለነበራችሁ እና የማለፊያ ወጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች እስካሁን የመግቢያ ቀን እንዳላሳወቅን ይታወቃል፤ ነገር ግን በቅርቡ ጥሪ እንደምናደርግ አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ. ም

👇👇👇👇
For real and complete information visit  
https://t.me/WCUSU
https://www.facebook.com/wcusu2010                              
https://youtube.com@wcuinfo594
@WCUSTPRb

Exit Exam For All Department

06 Nov, 16:26


#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ማስረጃ፣
- የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ።

Note:

በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ጀምራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድሮዋል በመሙለት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች፥ የሞላችሁትን ቀሪ ፎርም ይዛችሁ መሔድ ይጠበቅባችኋል፡፡

የ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደፊት እንደሚያሳውቅ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Exit Exam For All Department

30 Oct, 17:57


👉ተማሪዎች ቢያንስ ሶስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

👉እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥንም ረቂቅ አዋጁ ይከለክላል


ኢትዮጵያ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅታለች፡፡ ይህ ረቂ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ በትናንትናው ዕለት ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም ይህን ረቂቅ አዋጅ ተጨማሪ ውይይቶች እና ሌሎች ግብዓቶች እንዲታከሉበት በሚል ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

ይህ ረቂቅ አዋጅ እንደሚለው ከሆነ ተማሪዎች ስለ ሚማሯቸው ቋንቋዎች፣ ስርዓት ትምህርት ዝግጅት፣ መምህራን ቅጥር፣ ተማሪዎች ምዘና፣ ትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መንገዶች እና ሌሎችንም ጉዳዮች ይዟል፡፡
ቋንቋዎችን አስመልክቶ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተቀመጠው የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ ብሏል፡፡

እንዲሁም የእንግሊዘኛ ቋንቋን በማስተማሪያነት በግዴታ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ማስተማር ግዴታ ነው የተባለ ሲሆን ክልሎች ግን ከዚያ በፊትም የማስተማሪያ ቋንቋ ማድረግ ከፈለጉ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ተማሪዎች ቢያንስ ሶስት ቋንቋዎችን እንዲማሩ ይደረጋል የተባለ ሲሆን የአፈጻጸም መመሪያ በቀጣይ እንደሚወጣም ረቂቅ አዋጁ ያትታል፡፡
እንዲሁም አንድ ተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቋንቋ ከፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎች መካከል የተማሪን አልያም የወላጅን ምርጫ ታሳቢ በማድረግ ከ3ኛ-10ኛ ክፍል ድረስ እንዲማሩ ይደረጋልም ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ተጨማሪ የውጭ ቋንቋ ክልሎች በሚመርጡት መሰረት ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በአማራጭነት ይሰጣል የተባለ ሲሆን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት አይነት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

የተማሪዎች ምዘናን በሚመለከት ደግሞ እስከ 1ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የሚባለው እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ተማሪዎችን በደረጃ ማስቀመጥን ይከለክላል፡፡
ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወርን በሚመለከት ደግሞ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የሚቻለው ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት አይነቶች 50 ከመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲያመጡ ብቻ ነውም ተብሏል፡፡
ክልላዊ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሁለት ጊዜ በላይ በነጻ ፈተና ላይ መቀመጥ አይችሉም የተባለ ሲሆን ተፈታኞች በግላቸው እንዲፈተኑ ይደረጋል ይላል ረቂቅ አዋጁ፡፡

በዚሁ ረቂቅ አዋጅ ላይም የመምህራንን ትምህርት እና ስልጠና ጉዳዮችን በሚዘረዝርበት አንቀጽ ስር ሴቶች ለመምህርነት ስልጠና በሚወዳደሩበት ጊዜ ለምልመላ የሚያስፈልጉትን አጥጋቢ መስፈርት አሟልተው በውድድር ወቅት ከወንዶች ጋር እኩል ነጥብ በሚያገኙበት ወቅት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ደንግጓል፡፡
እንዲሁም አንድ መምህር በስራ ላይ እያለ በመንግስት ወጪ ደረጃውን የሚሻሽል ስልጠና ከወሰደ ለእያንዳንዱ የስልጠና ዓመት አንድ ዓመት በሙያው ማገልግል አለበት ሲልም ግዴታ ተጥሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ወሲባዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ወንጀሎች መፈጸሙ ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሰው በማንኛውም የትምህርት ተቋም ውስጥ በመምህርነት እንዳይቀጠር አግዷል፡፡
አንድ መምህር የሙያ ፈቃዱን በየሁለት ዓመቱ ከክፍያ ነጻ በሆነ መንገድ ማሳደስ እንዳለበት የደነገገ ሲሆን የስራ ፈቃድ ለማግኘት ከምረቃ በኋላ የ2 ዓመት ልዩ የመምራን ሙያ ስልጠናን መውሰድ እንዳለበትም በረቂ አዋጁ ለይ ተደንግጓል፡፡
የግል ትምህርት ቤትን ማቋቋም ስለ ሚከለከልበት ሁኔታ በሚያትተው አንቀጽ ስር በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ የተሰጠበት ወይም እዳ መክፈል ያልቻለ ሰው፣ ትምህርት ቤቱን ለማቋቋም ፈቃድ ከሚጠይቀው አመልካች ውስጥ ድርሻ ያለው ሰው በወሲባዊ ወንጀል አልያም በህጻናት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ጥፋተኛ መሆናቸው በፍርድ ቤት የተወሰበት ሰው ፈቃድ ማግኘት አይችልም ብሏል፡፡
በመጨረሻም መንግስት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርትን በብቃት እና በጥራት ለማዳረስ ያለበትን ግዴታ ለመወጣት ሀገር አቀፍ የትምህርት ፈንድ እንዲቋቋም አዋጁ ይፈቅዳል ይላል፡፡

Exit Exam For All Department

28 Oct, 08:44


🔈#የመምህራንድምጽ

" መግለጫ እና ወሬ ሳይሆን የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን ፤ እኛ መኖር ከብዶናል !! " - ቃላቸውን የሰጡ መምህራን

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

የማህበሩ ስብሰባ ላይ ፦

መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣

ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል፣

ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ፤ ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት፣

ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣

በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣

የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት፣ የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች ...ወዘተ በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተው ነበር።

በቀረቡት ጥያቄዎች ዙሪያ የትምህርት ሚንስቴር አመራሮች ተገኝተው ምላሽ እንደሰጡ በማህበሩ ተገልጿል።

ስብሰባው የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀው።

ይህንን የማህበሩን ስብሰባ መደረግ የሰሙና ማህበሩም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠውን ቃል ያነበቡ በርካታ መምህራን መልዕክታቸውን ልከዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ መምህራን ፥ " እኛ መግለጫና የማይጨበጥ ወሬና መስማት ሰልችቶናል የተግባር መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

" እኛ መኖር ከብዶናል !! ስብሰባ ከዛ መግለጫ ምን ይሰራልናል ? ምን ያህል ዋጋ እየከፈልን እንዳለን እኛ ነን የምናውቀው ልጅ ማሳደግ ፣ ቤተሰብ ማስተዳደር እጅጉን ፈተና ከሆነብን ሰንብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይህ ማህበር በየጊዜው መግለጫ ነው የሚሰጠን ምንድነው ጠብ የሚል ስራ የተሰራው ? ይሄን ይመልሱልን " ሲሉ ጠይቀዋል።

" መግለጫና ወሬ ምንድነው የሚሰራልን ? ችግራችንን ደጋግሞ መናገር መፍትሄ ከሌለው ጥቁሙ ምን ላይ ነው ? የማይታወቅ ችግር ያለ ይመስል ሁሌ አንድ አይነት ነገር መናገር ያሰለቻል ደክሞናል " ብለዋል።

" መብታቸውን የእንጀራ ጥያቄያቸውን የላባቸውን ደመወዝ ስለጠየቁ ብቻ መምህራን መታሰራቸውን ሰምተናል ይህ ሲሆን እንኳን መፍትሄ እየተሰጠ አይደለም " ሲሉ አማረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ መምህራን ፥" በሚዲያው መግለጫ ሳይሆን ተግባራዊ መሬት ላይ የሚወርድ መፍትሄ ብቻ ነው የምንፈልገው " ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

" ሰራተኛው ኑሮው ቢከድበውና የሚጮኽበት እዲሁም ችግሩን ሰምቶ መፍትሄ የሚሰጠው ቢያጣ ነው ወደሚዲያ የሚቀርበው ስለዚህ እባካችሁ ድምጻችንን ይሰማና መፍትሄ ስጡን " ሲሉ አክለዋል

[ዘገባው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ነው]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Exit Exam For All Department

26 Oct, 17:59


Students' List
From College of Engineering and Technology

15,562

subscribers

1,491

photos

18

videos