Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ @ethiolawtips Channel on Telegram

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

@ethiolawtips


@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️
Youtube👇
https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg
Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1
Facebook 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law 🥇ኢትዮ ሕግ (English)

Are you looking for legal tips and advice in Ethiopia? Look no further! Lawyer_Henok's Telegram channel, Ethio Law, is here to provide you with valuable insights and information regarding Ethiopian laws and regulations. Led by lawyer Henok Taye, who holds an LL.B and LL.M, this channel offers a wealth of knowledge on various legal topics

Whether you are a law student, legal professional, or simply someone interested in learning more about Ethiopian law, Ethio Law is the perfect channel for you. From tips on navigating the legal system to updates on recent legal developments, you'll find everything you need to stay informed and empowered

In addition to the valuable content shared on the channel, you can also connect with lawyer Henok Taye directly. Reach out to him at 0953758395 for personalized legal advice and support

Don't miss out on this opportunity to expand your legal knowledge and stay up-to-date with the latest legal trends in Ethiopia. Join Ethio Law today and become a part of a thriving legal community dedicated to promoting justice and legal literacy. Follow Lawyer_Henok on Youtube and Tiktok for even more insightful content, and connect with him on Facebook to stay connected with the legal community. Don't wait, join Ethio Law now!

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

20 Jan, 08:33


ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ የመንደር ውል ህጋዊ የሚሆንባቸው 5/አምስት/ ሁኔታዎች 👉(Abraham Yohanes)

የማንይቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በ ፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካልተደረገ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ከተወሰኑ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች በመነሳት የመንደር ውል ህጋዊ ተብለው የሚቆጠሩበት ሁኔታዎች አሉ። እነዚህ 5 ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

❶ኛ የሽያጭ ውል መኖሩ ከታመነ ወይም ካልተካደ

ገዢ ውል እንዲፈፀምለት ክስ አቅርቦ ከሳሽ መከላከያ መልሱ ላይ በመካከላቸው ውል መኖሩን ካመነ ወይም ካልካደና በሌሎች ነጥቦች ላይ መልስ ከሰጠ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት አልተደረገም ብሎ ውድቅ ሊያደርገው አይችልም።

❷ኛ በማህበር በመደራጀት የተሰራ ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ (ሰ/መ/ቁጥር 36294 ቅፅ 8)

በማህበር በመደራጀት እየተሰራ ያለ ቤት ቤቱ ተጠናቆ ካርታ እስኪወጣለት ድረስ የማህበሩ አባል የሆነ ሰው ይህን ቤት ቢያስተላልፍ ቤት የመስራት መብቱን ወይም እጣውን እንዳስተላለፈ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረትን እንዳስተላለፈ አይቆጠርም። የማህበሩ አባል በስሙ ካርታና የባለቤትነት ማስረጃ እስካልተሰጠው ድረስ ቤቱ ወይም እየተሰራ ያለው ቤት በማህበሩ አጠቃላይ ይዞታ ስር የሚገኝ በመሆኑ የማህበሩ አባል ለ 3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ የሚችለው እጣውን ወይም ጥቅሙን እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት አይደለም። እንዲህ አይነት ውሎች የግድ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ሊረጋገጡ አይገባም።

❸ኛ ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (ሰ/መ/ቁጥር 32222 ቅፅ 7)

ብዙን ግዜ እንዲህ አይነት ውል ከ Real Estate ቤቶች ግንባታ ጋር የተያያ ነው። ምንም እንኳን ውላቸው ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ቢሉም ዉሉ በሚደረግበት ግዜ ቤቱ ያልነበረ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ከአንዱ ወደ ሌላው ተላልፏል ሊባል አይችልም። ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል የግንባታ ውል እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ሊባል የሚችል ባለመሆኑ ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መረጋገጥ አይኖርበትም።

❹ኛ አዋዋይ ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች ለተወሰነ ግዜ ሳይፈፀምበት የቆየ የመንደር ውል (የሰ/መ/ቁጥር 36740 ቅጽ 8)

ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ መሠረት በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው የመንደር ውል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች የተሟሉት የተወሰነ ግዜ ከቆየ በኋላ ቢሆንም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰው አካል ፊት ያልተደረገ ነው በሚል ውድቅ ሊደረግ አይገባም የሚል ነው።

ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ እንዳለው ቤቱን የሚመለከቱ እዳና እገዳ ለማጣራትና ክፍያ ለመፈፀም የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በውል ላይ ማህተም ሣያሣርፍበትና የፕሮቶኮል ቁጥር ሰጥቶ ሣያረጋግጥበት የተወሰነ ጊዜ ያለፈ ቢሆንም እነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እስኪከናወኑ ድረስ በውል ላይ ማህተም ሣያርፍበት መቆየቱ ወይም የፕሮቶኮል ቁጥር ሣይሰጠው መዘግየቱ ውል እንዳልተደረገ የሚያስቆጥረው ነው ለማለት አያስችልም፡፡

❺ኛ የሊዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (የሰ/መ/ቁጥር 191095 & 225796)

በሊዝ የተገኘ ይዞታ ላይ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ወይም ተጀምሮ በግማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብት ዘመኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቦተው የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ ይቻላል። ነገር ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ ግማሽ ግንባታ ከተከናወነ በኋላ ከሆነ በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ ከተሰራው ህንፃ ጭምር በመሆኑ የሊዝ መብት ማስተላለፍ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደ ማስተላለፍ ይቆጠራል። ስለዚህ ሁለት ነገር መታየት ይኖርበታል። የመጀመሪያው አንድ ሰው መሬት በሊዝ ወስዶ ምንም አይነት ግንባታ ካልፈፀመበት ወይም ግንባታ ጀምሮ በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብቱን በመንደር ውል ማስተላለፍ ይችላል። ሁለተኛው የግንባታው ደረጃ ግማሽና ከዛ በላይ የደረሰ ከሆነ ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ የተገነባውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ጭምር በመሆኑ ውሉ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ መረጋገጥ ይኖርበታል።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

19 Jan, 13:35


~የሰበር መዝ/ቁ 249348~
ታህሳስ 28 ቀን2017 ዓ.ም
የሌላን ሰው መሬት አጥር አጥሮ በመያዝ ቤት ሳይሰሩ ባለቤቱ ሳይቃወመኝ ነው የሰራሁት በማለት የፍ/ህ/ቁ 1179 በመጥቀስ መከራከር አይቻልም።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

14 Jan, 15:54


ምክር ቤቱ በሙስና የተጠረጠሩ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን አሰናበተ
----
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው የሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የስንብት ውሳኔን አጽድቋል፡፡

የስንብት ውሳኔውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸ-ገነት መንግስቱ አቅርበዋል፡፡

ዳኛ አዱኛ ነጋሳ እና ዳኛ አክሊሉ ዘሪሁን የተጣለባቸውን ሕዝባዊ ኃላፊነት ባለመወጣት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸውን ወ/ሮ እጸ-ገነት አብራርተዋል፡፡

የተሰጣቸውን ሹመት አላግባብ በመጠቀም፣ ዳኛ አዱኛ ነጋሳ ገንዘብ እና ቼክ በመቀበል ፤ ዳኛ አክሊሉ ዘሪሁን የአስር ሚሊዮን ብር ቼክ በመቀበል ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት መፈጸማቸውን ሰብሳቢዋ ጠቅሰዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ቋሚ ኮሚቴው ከፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጋር በጥልቀት እንደመከረበት ወ/ሮ እጸ-ገነት ተናግረው ፣ ውሳኔውን ምክር ቤቱ እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፡፡

ውሳኔውን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን፣ “ቅጣቱ አስተማሪ አይደለም፤ አስተማሪ የሕግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ፤ ወደ መረጠን ሕዝብ ስንሄድ አገልግሎት እና ፍትህ የምናገኘው በገንዘብ ነው ስለሚሉን ውሳኔው ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡

በአንጻሩ፣ “ቋሚ ኮሚቴው ዳኞቹ ከመሰናበታቸው አስቀድሞ የፌዴራሉን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማዳመጥ ይገባዋል፤ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ውሳኔ እንደ ምስክር ተጠቅሞ ዳኞችን ከስራ ማሰናበት የዳኞቹን መብት ይጋፋል” የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

በተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ ውሳኔው ውሳኔው ውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 5/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡(ፓርላማ)

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

13 Jan, 04:55


ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ፦

ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

12 Jan, 11:13


በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ተገቢውን የቅጥር ስርዓት ሳይከተል የተፈፀመ የሰራተኛ ቅጥር ሲኖር ህጉ ምን ይላል ?
==================================
✍️አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሰረት ተወዳድሮ አሸናፊነቱ ተረጋግጦ ቅጥር የፈፀመ ሰራተኛ ቅጥሩ የቅጥር ስርዓት ለመግዛት የወጣው ህግን ባልተከተለ መንገድ የተፈፀመ መሆኑ ከተረጋገጠ ስህተቱ የቀጣሪው መንግስት መስሪያ ቤት ቢሆን እንኳን ቅጥሩ ፀንቶ የሚቆይበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የአዲስስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ 56/2010 አንቀፅ 94መሠረት በማድረግ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 165886የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ/ም በቅፅ 24 ላይ አስገዳጅ ትርጉም ተሰጥቶበታል።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

12 Jan, 05:59


ሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን ያገባ እንደሆነ እና ጋብቻው በሞት ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት የፈረሰ እንደሆነ እና ከሁለቱ ሚስቶች አንደኛዋ ንብረቶቹን በማፍራት ሂደት የተለየ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ያረጋገጠች እንደሆነ ከተፈራው ንብረት ግማሽ ድርሻ የሚገባት ሲሆን፣ የሌላኛዋ ተጋቢ ከባል ጋር ግማሹን ትካፈላለች።

በእርግጥ ሟች ሁለት ሚስቶች ኖረውት የሞተ እንደሆነ ሁለቱ ሚስቶች የንብረቱን ድርሻ ግማሹን ለሁለት ሊካፈሉ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅሊይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁጥር 24625 ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁጥር 45548 ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመው) አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ያሉት እንደሆነ ንብረቶቹን በማፍራት ረገድ ከሚስቶቹ አንደኛዋ ሚስት ከሌላኛዋ የተሻለ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ባደረገችው አስተዋጽኦ ልክ ልትካፈል ትችላለች የሚል ሃሳብ መነሻ በማድረግ ባል ንብረቱን በሚያፈራበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በትዳር የነበረች ሚስት ንብረቱን በማፍራት ረገድ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳደረገች ግምት ተወስዶ ከንብረቱ ግማሹን ድርሻ የማግኘት መብት እንዳላት እና በአንፃሩ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያላደረገች ሚስት ከባል ድርሻ ግማሹን የማግኘት መብት ብቻ ያላት ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በሰ/መ/ቁጥር 50489 (ቅጽ 11 እንደታተመው) ጨምሮ በሌልች በርካታ መዛግብት ላይም ይህንኑ የሚያጠናክር ውሳኔ ሰጥቷል።Join👇
https://t.me/ethiolawtips
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

11 Jan, 20:11


የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ-መንግስት ትርጉም የሰጠባቸውን የተጠቃለሉ ሰላሳ ዘጠኝ መዝገቦች የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።👇

https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

11 Jan, 08:02


አዲሱ የትራፊክ ቅጣት

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

09 Jan, 17:41


የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ በወንጀል የሚያስጠይቁ ድርጊቶች!!

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

09 Jan, 11:38


ዕለታዊ🔔
-------------
⚖️📚በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት📚⚖️
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
📚⚖️በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ማለት ዋጋን በመክፈል የአንድ ንብረት ሀብትነት ወይም የአላባ ጥቅም ተቀባይነትን በአንዳንድ ምክንያቶች የሚገዛውን ሦስተኛ ወገን ለማስለቀቅ ለአንዱ ሰው የተሰጠ መብት ነው የፍ/ሕ/ቁ 1386 ።
📚⚖️ቀዳሚ የመግዛት መብት ያላቸው እነማን ናቸው?
በፍ/ሕ/ቁ 1388 ላይ እንደተገለፀው በቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ከጋራው ንብረት ውስጥ ለሚሸጠው አንድ ክፍል ለጋራ ባለሀብቶቹ በሕግ መሠረት አላቸው።በባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ወቅት የጋራ የሆነውን ንብረት ሸጠው ለመካፈል የወሰኑ ከሆነና አንደኛው ተጋቢ ንብረቱን በግዢ ለማስቀረት ከፈለገ ቅድሚያ የመግዛት መብት ይሰጠዋል ማለት ነው ይህም በአንቀፅ 1388(2) ሰፍሯል ።
📚⚖️ይሁንና የጋራ ባለሀብቶች የሆኑት ከመካከላቸው አንዱ ወይም ብዙዋች ቅድሚያ የመግዛት መብታቸውን የተው እንደሆነ ሌሎቹ በተተው ንብረቶች ሁሉ በቀዳሚነት ይገባኛል በማለት መብታቸውን ይሰሩበታል አንቀፅ 1388(3)።
📚⚖️ የዘመዶች ቅድሚያ የመግዛት መብት የሚያገኙት መቼ ነው?
በፍ/ሕ/ቁ 1389 መሠረት አንድ ሰው ከዘመዶቹ ከአንደኛው በውርስ ያገኘውን ርስት የሸጠ እንደ ሆነ የሻጩ ዘመዶች በቅድሚያ የመግዛት መብት በሕግ መሠረት አላቸው። ይህ የግዥ ሁኔታ በምን መልኩ ይፈፀማል ለሚለው አንቀፅ 1390 በዝምድና ደረጃ አገማመት እንደሚፈፀም አስቀምጧል ።
📚⚖️አንድ በአንድ ለማየት ያህል በአንቀፅ 1390(1) ስር እንደሰፈረው ሻጩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው በአባቱ የዝምድና መስመር ከሆነው ከአንዱ ዘመዱ እንደ ሆነ በቀደምትነት ለመግዛት በተሰጠው መብት ሊጠቀሙ የሚችሉት በሻጩ የአባት ወገን የዝምድና መሥመር ውስጥ የሚገኙት ዘመዶቹ ብቻ ናቸው።
📚⚖️እንዲሁም ደግሞ ሻጩ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት ያገኘው በእናቱ የዝምድና መሥመር ከሆነ ከአንዱ ዘመዱ እንደሆነ በቀደምትነት በተሰጠው መብት ሊጠቀሙ የሚችሉት በሻጩ የእናት መሥመር ውስጥ የሚገኙ ዘመዶች ብቻ ናቸው የፍ/ሕ/ቁ 1390(2)።
📚⚖️አንዳንድ ጊዜ የቤተ ዘመድ የይገባኛል ቀዳሚነት ተራ የሚወስነው ኑዛዜ በሌለ ጊዜ የውርስ ንብረት የሚከፋፈልበትን አኳኋን በሚመለከተው ስለ ውርስ በተፃፈው አንቀፅ መሠረት የሚታይ ይሆናል።
📚⚖️ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሠረት በይገባኛል መብታቸው ሊጠቀሙ የሚችሉ ብዙ ሰዎች ያሉ እንደ ሆነ ደግሞ የቀዳሚነቱ ምርጫ የሚሰጠው በሚሸጠው መሬት ላይ ለሚኖሩት ወይም ራሳቸው እየሰሩ በዚሁ መሬት ለሚጠቀሙት ቤት ዘመዶች ነው የፍ/ሕ/ቁ 1392።
⚖️📚ብዙ ባለመብቶች የእኩልነት ቀዳሚ ገዢ መብት ካላቸው እንዴት መብቱ ተለይቶ ይሰጣል?
እንዲህ በሚሆን ጊዜ በአንድ የተራ ደረጃ ውስጥ በቀዳሚነት ይገባናል በማለት በእኩልነት ያላቸው ብዙዎች ሰዎች ያሉ እንደ ሆነ መብቱን በኅብረት ይሠሩበታል በመሬቱም ትክክል በሆነ ድርሻ የጋራ ባለሀብቶች ይሆናሉ በማለት የፍ/ሕ/ቁ 1393(1) አስፍሯል።

📚⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️📚⚖️⚖️
🛑

https://t.me/EthioLawtips
📚📚⚖️📚join☝️☝️☝️

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

09 Jan, 11:30


በወንጀልና በሙስና የተፈራ ንብረት የማስመለስ አዋጅ ጸደቀ

******



ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

አዋጁ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈራን ንብረት ማስመለስ የሚያስችሉና የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተጨመሩ አንቀጾችን አስመልክተው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በአዋጁ ላይ በአስረጅ፣ በህዝብና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት እንደሰበሰበ ገልጸዋል።

የንብረት ማስመለስ አዋጅ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ አስረድተዋል።

አዋጁ ዜጎች በላባቸውና በወዛቸው ንብረት እንዲያፈሩ የሚያበረታታ፣ በወንጀል ንብረት የሚያፈሩትን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ የአገርን ዕድገት የሚያሳልጥ እንደሆነ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ በመሆኑ በተፈጻሚነቱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና አስፈጻሚ አካላትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ እና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት እንዳይጋፋ መታየት አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በአዋጁ ሃብት የማፍራትና የማውረስ ሕገ-መንግስታዊ መብትን የሚቃረን ድንጋጌ አለመካተቱንም አብራርተዋል።

የጸረ-ሙስና ትግል እንዲጠናከር የሚያደርግ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘና የተመዘበረ የአገር ሃብትን ለማስመለስ የሚያስችልና ሕገ-ወጥነትን የሚያስቆም አዋጅ እንደሆነም ጨምረዋል።

ምክር ቤቱ በአዋጁ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ ዝርዝር ውይይት በማድረግ በ ሶሰት ተቃውሞ እና በአራት ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

09 Jan, 11:30


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ አዋጅ

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

09 Jan, 11:30


በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የታየዘ ግለሰብ ነዳጁ ተወርሶ በእስራት እና በገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ የሚያደርገው አዋጅ ጸደቀ‼️
***

ምክር ቤቱ  6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ  እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባዔው፤ የነዳጅ ውጤቶችን  ግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት በመመርመር አጽድቋል፡፡

በዚህም  ነዳጅ ውጤቶችን ግብይት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በሁለት ተቃውሞ   በአንድ ድምጽ ተአቅቦ ጸድቋል፡፡
አዋጁ ከያዘቸው ጉዳዮች መካከል፤

መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል  ከ3 ዓመት እስከ 5 አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም  ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺ  ብር ቅጣት ይጥላል፡፡

የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣  በዚህም   ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 350 ሺህ እስከ 500  ሺህ ብር   የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል የሚሉ ነጥቦች ይገኙበታል፡፡

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

08 Jan, 16:46


ጋብቻ፤ፍቺና የንብረት ክፍፍል በኢትዮጵያ(የፌደራልና የክልል የቤተሰብ ሕጎች ማብራሪያ )መፅሐፋን የት ማግኘት እንችላለን ብላቹ ለጠየቃቹ በዚህ ቁጥር ደውላቹ ማግኘት ትችላላቹ👇

የን+251927120453

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

08 Jan, 12:10


የውል ይርጋ
---------------
1)የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810(2) ላይ የተመለከተው የይርጋ ገደብ ተፈፃሚ የሚሆነው ውል በፈቃድ ጉድለት ወይም በችሎታ ማጣት የተነሳ እንዲፈርስ ጥያቄ የቀረበ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህቁ 1810 የሰ/መ/ቁ 48012 ቅፅ 12
2)በውል ግንኑነት ውስጥ የራስን ግዴታ ሳይወጡ ሌላው ወገን ግዴታውን አልተወጣም በሚል የሚቀርብ ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1757 በሰ/መ/ቁ 39568 በቅፅ 12
3)የማይንቀሳቀስ ንብረት ሻጭ በዉሉ መሠረት የመፈፀም ፍላጎት የሌለው መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ለገዢ ያላሳወቀ እንደሆነ ገዥ ውሉ እንዲፈፀምለት የመጠየቅ መብቱ በ10  ዓመት ይርጋ የሚታገድበት ስለመሆኑ 1845;1789:1731:1732 የሰ/መ/ቁ 38935 ቅፅ 12
4)የፍትሐብሄር ጉዳዮች የ ይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ጊዜ ጀምሮ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1846 የሰ/መ/ቁ 36756 ቅፅ 12
5)የፀና የውል ግዴታ የገባ ሰው ውሉ በፍርድ እንዲሰረዝ ለመጠየቅ የሚችለው ሌላኛው ተዋዋይ ወገን ግዴታውን በአግባቡ ያልፈፀመ(ያልተወጣ) እንደሆነ ወይም የፈፀመው ፍፁም ባልሆነ አኳኃን ከሆነ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1784;1785(2).(1)"የሰ/መ/ቁ 66935 ቅፅ 13 ላይ ሰፍሯል።
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

08 Jan, 12:07


ውል መሰረዝ፤ ማፍረስ እና በስምምነት ማቋረጥ
ውል መሰረዝ
ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደኛው እንደ ውሉ ባለመፈጸሙና የውሉን ግዴታ በመጣሱ በተዋዋዩ ወይም በፍርድ ቤት ውሉን ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች ቀሪ ማድረግ
ውል የሚሰረዘው ከመሠረቱ ግድፈት ስላለው አይደለም፡፡ ይልቁንም የውል መሠረዝ ምክንያት ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታን ከመፈፀምና ካለመፈፀም ጋር ተያይዞ የሚከሠት ነው፡፡ የውል መሠረዝ ሥርዓትም የራሱ የሆነ አካሄድ አለው፡፡ ይኸውም ውሉን የመሠረዝ ፍላጐት ያለውን ወገን የውሉ ግዴታ ባለመፈፀሙ የተነሳ ከህግ ወይም ከውሉ ከራሱ ባገኘው መብት ተጠቅሞ ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆንበት አጋጣሚም ግዴታው ባለመፈፀሙ የተነሳ የደረሰውን ጉዳት ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ጥያቄ አቅራቢው ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም፡፡ በመሆኑም የውል ይሰረዝልኝና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በህጉ አግባብ የሚስተናገዱ ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁ. 1784 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በተናጠል መሰረዝ
አንደኛው ተዋዋይ ወገን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን መሠረት በማድረግ ውልን በተናጠል ለመሠረዝ የሚችለው ከሚከተለት ሶስት ሁኔታዎች አንደኛው የተሟላ መሆኑን ለማስረዳት ሲችል ነው፡፡
• የመጀመሪያው ባለዕዳው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት የውሉን ግዴታ የሚፈፅምበት ቁርጠኛ ጊዜ በውሉ ላይ በግልፅ ተመልክቶ እንደሆነና በውሉ ላይ የተገለፀው ቁርጥ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውሉን ለመሰረዝ የሚችል መሆኑን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1775(ለ) ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሁለተኛው ምክንያት ባለዕዳው ውሉን ያልፈፀመበትን ምክንያትና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዳኞች ባለዕዳው ውሉን የሚፈፅምበት የችሮታ ጊዜ ከሰጡት በኋላ ባለእዳው በዳኛ ውሣኔ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1770 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሶስተኛው ባለገንዘቡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 በተደነገገው መሠረት ሌላኛው ተዋዋይ (ባለዕዳው) በውል የገባውን ግዴታ የሚፈፅምበትን ጊዜ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆንና በማስጠንቀቂያው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈፅም ሲቀር መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ሌላኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ መሠረት እንዲፈፅም ለመጠየቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የሚችለው በመጀመሪያ እሱ የበኩሉን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የተዘጋጀ ሲሆን እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1857 በግልፅ ይደነግጋል፡፡
ስለሆነም ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማና ግብ እንደዚሁም የድንጋጌውን የተፈፃሚነት ወሰን ለመረዳት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመዝነው አንደኛው ተዋዋይ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 ሌላኛው ተዋዋይ ውሉን እንዲፈፅምለት ለመጠየቅ፤ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 ድንጋጌዎች መሠረት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና በፍትሐብሔር ቁጥር 1787 በተደነገገው መሠረት ውሉን በተናጠል ለመሠረዝ በመጀመሪያ በእሱ በኩል በውል የተጣለበትን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ በማስረጃ ለማረጋገጥ የቻለ መሆን እንዳለበት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎችን ይዘትና መሠረታዊ ግብ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሕግ አውጭው በውል ለገባው ግዴታ ተገዥ በመሆን በእሱ በኩል ያለውን ግዴታ ያልፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያልቻለ አንድ ተዋዋይ ወገን ሌላኛውን ተዋዋይ ወገን ቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን በተናጠል እንዲሰርዝ በማሰብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን አውጇል ተብሎ አይገመትም፡፡ አንድ ተዋዋይ የውሉን መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ በመግለጽ ለሌላኛው ወገን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውል በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በመጀመሪያ እሱ በውሉ የገባውን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57280 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 1770፣ 1771፣ 1774፣ 1757፣ 1787
ውል ማፍረስ
በህጉ የተቀመጡት የውል አመሰራረት መስፈርቶችን ያለሟላና ግድፈት ያለበት በመሆኑ የተነሳ የውሉ ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች መቅረት
ውል ማፍረስና ውል መሠረዝ በውል የተቋቋሙት ግዴታዎች ከሚቀሩባቸው መንገዶች ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም ምክንያታቸውና ውጤታቸው የተለያዩ ነው፡፡ የውል ማፍረስ ከውል አመሠራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ሲሆነ
ውሉ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዳይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በስምምነት ማቋረጥ /ቀሪ ማድረግ/
ተዋዋይ ወገኖች በውል አቋቁመውት የነበረውን ግዴታ በፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት በስምምነት ቀሪ ሲያደርጉ የተለየ ፎርም መከተል እንዳለባቸው የሚደነግግ አስገዳጅ ድንጋጌ የለም፡፡ የውለታ በተዋዋዮች ስምምነት መቋረጥ (terminate) መደረግ ከውል መፍረስ ወይም ከውል መሠረዝ የተለየ ባህሪና ውጤት ያለው መሆኑን አግባብነት ያላቸውን የፍታብሔር ድንጋጌዎች ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም ውል በስምምነት ቀሪ ማድረግ (termination of contract) ውልን ከማሻሻል (ውል ከመለወጥ) (variation of contract) እና ውል ከመተካት (Novation of contract) የተለየ ባህሪ፣ ይዘትና ውጤት ያለው መሆኑን፣ የፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን፣ የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1722 እና የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1826 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
የውሉ በተዋዋዮቹ ፈቃድና ስምምነት መቋረጥ (ቀሪ) መሆን የተዋዋይ ወገኖች የወደፊት የውል የመፈፀም ግዴታ የሚያስቀር መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል፡፡ እንደዚሁም የውሉ መቋረጥ /ቀሪ/ መሆን ያለፈውን ሁኔታ የማይነካ መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 3 ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የውል ቀሪ መሆን (termination of contract) ተዋዋዮቹ በውል አቋቋመውት የነበረውን መብትና ግዴታ ቀሪ የማድረግ ውጤት የሚኖረው መሆኑን ከፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1807 /ለ/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 63063 ቅጽ 14፣ ፍ/ህ/ቁ. 1682-84፣ 1722
በአብላጫ ድምፅ የተሰጠ
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

08 Jan, 11:55


ነገር ግን በ አንቀጽ 1788 ላይ ያለው የውሉ የማይቻል መሆን/impossibility of the contract/ የሚለው ሀሳብ ውሉ ሲመሰረት የሚቻል ነው። ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አፈፃፀሙ የማይቻል /performance impossibel/ ሲሆን ነው። ውሉ ከተመሰረተ በኋላ ከመፈፀሙ በፊት የማይቻል ከሆነ  መፍትሄው መሠረዝ /cancellation/ ነው። እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም ባለመብቱ ውሉን በራሱ የመሠረዝ መብት አለው። ለምሳሌ የባለዕዳው መሞት፣ መታሰር ፣ መጥፋት ወይም መታመም የተነሳ እሱን ተክቶ ውሉን የሚፈፅም ሰው ከጠፋ የውሉን መፈፀም የማይቻል ስለሚያደርገው ባለመብት ውሉን በራሱ የመሠረዝ መብት አለው። እንዲሁም ባለዕዳው አንድ ልዩ የሆነ ዕቃ ለማስረከብ ቢስማማና ባለዕዳው ዕቃውን ከማቅረቡ በፊት ሊጠገን በማይችል መልኩ ቢበላሽ/ቢወድም ባለዕዳው ግዴታውን ለመወጣት የማይቻል ይሆንበታል። ስለዚህ ለባለመብቱ ህጉ ያስቀመጠው መፍትሄ ውሉን በአንድ ወገን መሠረዝ ነው።

(3) የጉዳት ኪሳራ /Damage/ (1771/2/ እና 1790-1805)


ውሉን ለፍርድ ቤት በማመልከት እንዲሠረዝለት የሚጠይቀውም ሆነ በራሱ የመሠረዝ መብት ያለው ተዋዋይ ወገን በተጨማሪ ኪሳራ/loss/ ደርሶበት እንደሆነ ይህን ኪሳራ የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው። ምን ግዜም ቢሆን ኪሳራ ውሉ በተፈለገው ግዜና አኳኋን ተፈፅሞ ቢሆን ኖሮ ባለገንዘቡ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ጥቅም የሚያካክስ ሊሆን ይገባል።

አሁን በቀጥታ ወዳነሳነው ጥያቄ ስንሄድ.......

ከግራ ቀኙ የሽያጭ ውል እንደምንረዳው ጎሴ ቤቱን በ 5 ሚሊዮን ብር ለመግዛት ተስማምቷል። ነገር ግን በውሉ መሠረት 4 ሚሊዮን 900 ሺ ብር ቅድሚያ ክፍያ በመስጠት ቤቱን ከተረከበ በኋላ የሚቀርበትን 100 ሺ ብር ለቦሴ አልከፈላትም። ይህ የሚያሳየው ጎሴ እንደውሉ ያለመፈፀሙን ነው። ነገር ግን ቦሴ አብዛኛው ክፍያ ተከፍሏት ሳለ ጎሴ 100 ሺ ብር ብቻ ስላልከፈላት ውሉ ተሠርዞ ወደነበሩበት እንዲመለሱ መጠየቋ ተገቢ አደለም። ምክንያቱም ከላይ ለማብራራት እንደሞከርነው መሠረታዊ ባልሆኑ /non fundamental/ ጥቃቅን ምክንቶች የውል ይሠረዝ ጥያቄን ዳኞች መቀበል እንደሌለባቸው በ ቁጥር 1784 &1785 ተመላክቷል።

ስለዚህ ገዥ /ጎሴ/ በውሉ መሠረት አብዛኛውን ክፍያ ለ ሻጭ /ቦሴ/ ከፍሎ ቤቱን መረከቡ የውሉ አብዛኛው ክፍል መፈፀሙን የሚያሳይ ነው። ከ ቅን ልቦና አንፃርም ቦሴ አብዛኛው ክፍያ ተፈፅሞላት ሳለ ቀሪው አነስተኛ ክፍያ እንዲከፈላት ወይም እንዲፈፀምላት በመጠየቅ ውሉ ውጤት እንዲኖረው ማድረግ እየቻለች ውሉ እንዲሠረዝ መጠየቋ ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ

➡️ ቦሴ ቀሪው ክፍያ እንዲፈፀምላት /specific performance/ መጠየቅ ስትችል እንዲሰረዝ መጠየቋ ተገቢ አደለም።

➡️ ጎሴ አብዛኛውን የውሉን ክፍል ፈፅሞ ሳለ ውሉ እንዲሠረዝ መጠየቁ ተገቢ ያለመሆኑን እና ውሉ ቢሰረዝ ከ ሻጯ ይልቅ እሱ ላይ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ማስረዳት አለበት።
https://t.me/legal_affairs
@ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

08 Jan, 11:52


በመሠረቱ ተዋዋዮች ያቋቋሙት ውል በመካከላቸው ሕግ ሆኖ ያገለግላል። ይህ እንደ ሕግ ሆኖ የሚቆጠረው ውል ተከበረ የሚባለው ደግሞ ተዋዋዮች የየራሳቸውን በውሉ የተመለከተውን ግዴታቸውን በአግባቡ  ሲፈፅሙ ነው። ነገር ግን ከተዋዋዮች አንዱ ውሉን ለመፈፀም የማይችልበት ወይም የማይፈልግበት ምክንያት ሊፈጠር ይችላል።  እንዲህ በሆነ ግዜ ውሉን ላከበረው ወገን ሕጉ አማራጭ መፍትሔዎችን አሰቀምጧል። ከተዋዋዮች አንዱ ግዴታውን በውሉ መሠረት ሳይፈፅም የቀረ እንደሆነ ውሉን ያከበረው ወገን የሚከተሉትን ሕጉ ያስቀመጠውን አማራጮች መጠቀም ይችላል።

(1) ውሉን በግዴታ እንዲፈፅም መጠየቅ /forced or specific performance/ የፍ.ሕ.ቁ 1776

በዚህ አማራጭ መሠረት ባለዕዳው ውሉን ላከበረው ወገን በውሉ ላይ የተቀመጠውን ግዴታ እንዲፈፅም ወይም ንብረት እንዲያስረክብ ወይም ገንዘብ እንዲከፍል ወይም ማድረግ የማይገባው አድርጎ እንደሆነ የሰራውን ስራ እንዲያፈርስ የሚገደድበት አማረጭ ነው።  ነገር ግን ባለገንዘቡ የውሉ መፈፀም የተለየ ጥቅም የሚሰጠው መሆኑንና በጉዳት ኪሣራ መልክ ሊካስ የማይችል መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። እንዲሁም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር ባለመብቱ ውሉን ባለዕዳውን በማስገደድ ለማስፈፅም አይችልም። በርግጥ ይህ አማራጭ ሁል ግዜ የተሳካ አይሆንም። ውሉን ለማስፈፀም የማያስችሉ ብዙ ምክንያቶች ይኖራሉ። እንዲሁም ይህ አማራጭ የባለዕዳውን ነፃነት /Liberty/ የሚጋፋ ከሆነ ተመራጭነት የለውም። የውሉ መፈፀም የባለዕዳውን ነፃነት የሚጋፋ ከሆነ ባለመብቱ  ውሉን ሰርዞ የደረሰበትን ጉዳት በማሳየት ኪሳራ /damage/ ከመጠየቅ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም።

(2) ውልን መሠረዝ /cancellation/

ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ወይም አንደኛው በውሉ መሰረት ማድረግ የሚገባውን ካላደረገ ወይም ግዴታውን ባግባቡ ያልፈፀመ እንደሆነ ሌላው ተዋዋይ ወገን ለፍርድ ቤት በማመልከት ወይም በራሱ ውሉን መሰረዝ የሚችልበት ስርዓት ሕጉ ዘርግቷል።

ይህን አማራጭ እንደሚከተለው በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን

➡️ ውልን በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሠረዝ ማድረግ/judicial cancellation/ (1784 እና 1785)

➡️ ፍርድ ቤት ሳይኬድ ውልን በአንድ ወገን መሠረዝ /Unilateral Cancellation/ (1786 - 1789)

(A) ውልን በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ እንዲሠረዝ ማድረግ

ውል በፍ/ቤት እንዲሠረዝ አቤቱታ በቀረበ ግዜ ፍርድ ቤቱ በዋናነት ማጣራት ያለበት ውሉ በአግባቡ አለመፈፀሙን ወይም አጥጋቢ ባልሆነ ሁኔታ መፈፀሙን ነው። ነገር ግን መሰረታዊ ባልሆነ ወይም በረባ በልረባው ምክንያት ውል እንዲሠረዝ አይደረግም። ውል እንዲሠረዝ ጥያቄ በቀረበ ግዜ በተለይ መታየት ያለባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች 1ኛ፦ የውሉ መሰረዝ ግራቀኙ ላይ የሚያመጣው ጉዳት 2ኛ፦ በውሉ የተመለከውና ሳይፈፀም የቀረው ተግባር ወይም ግዴታ መሰረታዊ የውል ጥሰት /Fundamental breach of contract/ መሆን ያለመሆኑን 3ኛ፦ ውሉ እንዲሰረዝ የጠየቀው ተዋዋይ ወገን ቅን ልቦና /Good Faith/ የሚሉት ናቸው። እነዚህን መሰረታዊ ነጥቦች ፍርድ ቤቱ ካጣራ በኋላ ውሉ እንዲሠረዝ ወይም የውሉ መሠረዝ አስፈላጊ ካልሆነ ጥያቄውን  ላቀረበው ሰው ተገቢውን ካሰ ወስኖ ውሉ እንዲፀና ማድረግ ይችላል። ሳይፈፀም የቀረው ተግባር/ግዴታ መሠረተዊ የውል ጥሰት /Fundamental breach of contrcat/ ካልሆነ ውል አይሠረዝም። እንዲሁም ውሉ እንዲፈርስ ጥያቄ ያቀረው ወገን በቅን ልቦና /Good faith/ ሳይሆን ወይም ስለተጎዳ ሳይሆን ጥያቄውን ያቀረበው ተንኮል በማሰብ ወይ ሌላ ድብቅ አላማ በማሰብ የሆነ እንደሆነ ውሉ ሊሠረዝ አይገባም። ነገር ግን እዚጋ ልብ ማለት ያለብን ጉዳይ ሰይፈፀም የቀረው ተግባር መሠረታው የውል ጥሰት ባለመሆኑ ውሉ ሳይዘረት የቀረ ቢሆንም የደረሰ ኪሳራ ወይም ጉድለት ካለ ጉዳት የደረሰበት ወገን ሊካስ ወይም ጉድለቱ ሊታረም ይገባል።

(B) ፍርድ ቤት ሳይኬድ ውልን በአንድ ወገን መሰረዝ /Unilateral Cancellation/

ውሉ ባግባቡ ባለመፈፀሙ ተጎድቻለው የሚል ተዋዋይ ወገን ፍርድ ቤት መሄድ ሳያስፈልገው በራሱ ውሉን የሚሰርዝበትን በ 4/አራት/ ከፍለን ማየት እንችላለን፦

1⃣ የመሰረዣ አንቀፅ/ቃል /Cancellation clause (ቁ.1786)

ተዋዋይ ወገኖች አንዱ ወገን የውል ግዴታውን ባለመፈፀሙ የተነሳ ተጎድቻለው የሚለው ሌላኛው ተዋዋይ ወገን ፍርድ ቤት መሄድ ሳይጠበቅበት ውሉን በራሱ መሰረዝ የሚችልበት አንቀጽ በውላቸው ውስጥ ለማካተት ሙሉ ነፃነት አላቸው። ተዋዋዮች በውላቸው ውስጥ እንዲህ አይነት መብት በማካተታቸው ፍርድ ቤት በመሄድ የሚያጠፉት ገንዘብ፣ ግዜ እና ጉልበት አይኖርም። ነገር ግን እዚህ ጋር ልብ ማለት ያለብን ጉዳይ ውሉ የተሰረዘበት ሌላኛው ተዋዋይ ወገን የውሉን መሰረዝ በመቃወም ፍርድ ቤት ማመልከት እንደሚችል ነው። ፍርድ ቤቱም ውሉ ተከብሯል አልተከበረም? ጉዳት ደርሷል አልደረሰም? የሚሉትን ጭብጦቶቾ አከራክሮ ይወሰናል ማለት።

2⃣ ባለዕዳው የተወሰኑ የጊዜ ገደቦችን ማክበር ባለመቻሉ ምክንያት ሌላኛው ተዋዋይ ውሉን በራሱ የሚሠርዝበት ሁኔታ(ቁ.1787)

በተወሰኑ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ሁሉንም የግዜ ገደቦች አለማክበር ውልን በራስ የመሠረዝ መብት አያጎናፅፍም።
➡️ ፍርድ ቤት ጉዳት አድርሷል ወይም እንደውሉ አልፈፀመም ለተባለው ተዋዋይ ወገን እንደውሉ መፈፀም እንዲችል የተወሰነ ግዜ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን የሚያምንበት ከሆነ ከ 6 ወር የማይበልጥ የችሮታ ግዜ /grace period/ መስጠት ይችላል። ነገር ግን በዚህ ግዜ ውስጥ ባለዕዳው ግዴታውን አለመወጣቱ ከተረጋገጠ ባለመብቱ ውሉን ለመሰረዝ ፍርድ ቤት መሄድ አይጠበቅበትም (1787 & 1770)።
➡️ ባለዕውዳው ውሉን አለማክበሩ ወይም እንደውሉ ለመፈፀም ፍቃደኛ አለመሆኑ የሚረጋገጠው ባለገንዘቡ በሚሰው ማሰጠንቀቂያ ግዜ ውስጥ የሚሰጠው ምላሽ ነው። ለባለዕዳው ተገቢው የማስጠንቀቂያ ጊዜ ተሰቶት በዚህ ግዜ ውስጥ ያልፈፀመ እንደሆነ ውሉን ለማክበር ፍላጎት የሌለው መሆኑን በመረዳት ባለገንዘቡ ውሉን በራሱ መሠረዝ እንዲችል ሕጉ መብት ሰቶታል (1787 & 1774)።
➡️ እንዲሁም ባለዕዳው እንደ ውሉ ሳይፈፅም በውሉ ላይ በቁርጠኝነት የተመለከተው የውል መፈፀሚያ ግዜ ካለፈ ባለመብቱ ውሉን በራሱ ለመሰረዝ መብት አለው(1787 & 1775(b))።
3⃣ ባለዕዳው ውሉን የማይፈፅም መሆኑን ሲያስታውቅ/1789/
ባለዕዳው ውሉን የማፈፅም መሆኑን ከገለፀ ባለመብቱ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ለመሠረዝ መብት አለው። እንዲሁም ባለዕዳው ውሉን የመይፈፅም መሆኑን በግልፅ ካስታወቀው ደግሞ ባለመብቱ ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳይጠበቅበት ውሉን የመሰረዝ መብት አለው።
4⃣ ውሉ ከተደረገ በኋላ አፈፃፀም የማይቻል ሲሆን /Performance impossible (ቁ.1788)
ይህ ሀሳብ በ ፍ/ሕ/ቁ 1715 ላይ ከተመለከተው ሀሳብ ይለያል። በአንቀጽ 1715 ላይ ያለው የውሉ የማይቻል መሆን /impossibility of the contrct/ ውሉ ከጅምሩ ሲመሰረት የማይቻል በመሆኑ ነው። ውሉ ከጥንስሱ የማይቻል ከሆነ የውሉን ትክክለኛነት /validity of the contract / ስለሚነካ መፍትሔው በ ፍ/ሕ/ቁ 1808(2) መሰረት መፍረስ /invalidation/ ነው።Join👇
@ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

06 Jan, 17:23


የቀብድ ህጋዊ ውጤት
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

1 ቀብድ ሻጭና ገዥ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ ውል መፈፀማቸውን እርግጠኛ ሲሆኑ የሚቀባበሉት ገንዘብ በመሆኑ ይህን ማድረጋቸው ገንዘቡን ለመቀባበላቸው ብቻ ሳይሆን ውሉን ለመዋዋላቸውም ማስተባበያ የማይቀርብበት ማስረጃ መሆኑን የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1883 ይደነግጋል።

ገዥና ሻጭ አንድን ቤት ሲሻሻጡ በፍትሀ ብሄር ህግ 1723(1) ስር የተመለከተውን ፎርም ባያሟሉም ሻጭ ለዚሁ የሽያጭ ውል ማስፈፀሚያ ቀብድ መቀበሉ ከተረጋገጠ በማያከራክር ሁኔታ ውሉ መደረጉን ያረጋግጣል። አንድ ውል የህጉን ፎርም ካላሟላ በህግ ፊት የማይፀና ይሆናል ነገር ግን  በልዩ ሁኔታ የቀብድ ገንዘብ ክፍያ ካለ ውሉ የህጉን ፎርም ያላሟላ ቢሆንም የቤት ሽያጭ ውል ስለመኖሩ የማያከራክር ማረጋገጫ ስለሆነ ውሉ የፀና ይሆናል።

(የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ መዝገብ/ቁ 56794 ቅፅ 12)

የተከፈለው ክፍያ ግን ቀብድ መሆኑ በውሉ ላይ ካልተገለፀ በቀር ቀብድ ነው ተብሎ ሻጭ አጠፌታውን እንዲከፍል የማያስገድድ ከመሆኑ በላይ ውሉ መኖሩንም ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም።

2 የቀብድ ክፍያ መኖሩ የውሉን መኖር የሚያረጋግጥ ብቁ ማስረጃ ቢሆንም ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ለማፍረስ ተቃራኒ ስምምነት ካላደረጉ በቀር ቀብድ ተቀባዩ የተቀበለውን ገንዘብ እጥፍ አድርጎ በመመለስ፥ ቀብድ ሰጪው ደግሞ ይህንኑ የሰጠውን ገንዘብ ለተቀባዩ በመልቀቅ ያለሌላ ተጨማሪ ሁኔታ ውሉን የማፍረስና በመካከላቸው የተመሰረተውን ግዴታ ለማስቀረት መብት አላቸው። ይህም አሰራር በቀብድ የታሰረ ውል ከሌሎች ውሎች የሚለይበት ልዩ ባህሪ ነው። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1885)

ፍርድ ቤቶችም በተዋዋይ ወገኖች መካከል ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር ሻጩ የቀብዱን አጠፌታ ከፍሎ ውሉን በማፍረስ የሸጠው ቤት እንዲመለስለት ከጠየቀ መወሰን የሚገባቸውና ተገዶ እንዲፈፅምም ማድረግ የሌለባቸው መሆኑ ግልፅ ነው።

የተደረገው ውል ሊፈፀም የማይችል (impossible)፣ ወደ ገዥ ሊተላለፍ የማይችል እና ህገ ወጥ (unlawful) ከሆነ ግን ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ከሚመላለሱ በቀር ሻጭም እጥፉን እንዲመልስና ገዢም የከፈለውን እንዲለቅ የሚጣልባቸው ግዴታ የለም።

3 ውሉ በአግባቡ ከተፈፀመ እና ለ ቀብዱ ገንዘብ ዕጣ ፋንታ በተዋዋዬቹ መሀል የተደረገ ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ የቃብድ ሂሳቡ ከጠቅላላው የሽያጭ ዋጋ ላይ የሚታሰብ ወይም እንዲመለስ የሚደረግ ይሆናል። (የፍትሀ ብሄር ህግ ቁ 1884)
Join 👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

06 Jan, 17:01


ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፍትሕ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት በክልሉ ሥር በሚገኙ ወረዳዎች ዳኛ ወይም ዐቃቤ-ሕግ ሆኖ ለመሥራት ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሥራ ውድድር ማስታወቂያ አውጥቷል።

ብዛት፡- 300

የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ከታኅሳስ 30 እስከ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

ስለዚህ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ዝርዝር መረጀ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ።👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

05 Jan, 15:43


#ትክክለኛ_ፍርድ_ለመስጠት_ወይም_ውሳኔ_ለመወሰን_የሚረዱ_ጠቃሚ_እና_ቀዳሚ_ነገሮች፦
1. የሕግ ዕውቀት (Legal knowledge)
ሥራንና ባለሙያን ማገናኘት (Training or Specialization) እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፦ ለሕክምና ሐኪም፣ ለሕንጻና ግንባታ መሐንዲስ እንደሚያስፈልግ ለዳኝነትም (ለፍትሕ ስራ) የሕግ ባለሙያ ያስፈልጋል፡፡ የሚሰየመው ችሎት ከሚካሔደው ሙግት ወይም ክርክር ጋር የተገናኘ ሰፊ ዕውቀትና ልምድ ያለውና ስለጉዳዩ ማብራሪያ እና አስተያየት መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡

2. የዳኝነት ነፃነት (Judicial independence)
የዳኝነት ነፃነት ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ የማዕዘን ራስ መሆኑ በተግባር የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ መሠረታዊ ተልዕኮውም በፍርድ ሥራ ወይም በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ጥላቻና ፍራቻ፣ ስሜትና ግፊት ቦታ እንዳይኖራቸው ማድረግ ነው፡፡

ይህም ዳኛው ሕጉን ዐይቶ ክርክሩን ስምቶ በሕጉ መሠረት ውሳኔ እንዲሰጥ ለማስቻል ነው፡፡ ዳኛው በቁንጽል አመለካከት ወይም በዕውቀት እጥረት የሰጠው ፍርድ/ውሳኔ በይግባኝ ተመዝኖ የሚለወጥ ወይም የሚሻሻል ቢሆን የዳኝነት ሥርዐት የሚያጠናክር እንጂ የሚያስነቅፍ አይሆንም፡፡ በሌላ በኩል ፍርዱ በግፊት ወይም በስሜት፤ በጥላቻ ወይም በፍራቻ የተሰጠ ሆኖ በይግባኝ ሳይታረም የጸና ሆኖ ቢቀር በሁለት በኩል ለነቀፋ የተጋለጠ ይሆናል፡፡ ይኸውም በአንድ በኩል ተጽዕኖው ከውስጥም ይምጣ ከውጪ በራሱ ሕገ ወጥ መሆኑ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግም ፍርዱ ወይም ውሳኔው በሕግ መሠረት ያልተሰጠ በመሆኑ ከራሱ አልፎ ሥርዓቱን ጭምር ለሥጋትና ሐሜት በመዳረግ አመኔታውን ስለሚያቃውስበት ነው፡፡ ይህም የዳኝነት ነፃነት የጥበቃ አድማስ ዳኚውንም ተዳኚውንም እንደሚያካትት ያመለክታል፡፡ ሁለቱም ካልተጠበቁ ለአደጋ የሚጋለጠው ዳኛው የሚተረጉመው፣ ተከራካሪው የሚማጸነው ሕግ ነው፡፡ ሕግ ሥርዓት ስለሆነ ለሥጋት ከተጋለጠ አመኔታ ስለሚያጣ ነፀብራቁ ከዚያ አልፎ ኅብረተሰቡን የሚያውክ ይሆናል፡፡

ስለዚህ የዳኝነት ነጻነት በቁንጽል ከተወሰነ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሳይሆን ሰፋ ብሎ ከኅብረተሰቡ የፍትሕ አስተዳደር ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ነው፡፡

3. ነገርን በግልጽ ማየት (Clarity of the case or suit)
ክስን/ክርክርን ወይም ሙግትን በግልጽ መስማት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መብት ነው፡፡ ምስጢራዊነትን ስለሚያስወግድ በተከሳሹ ላይ የቀረበውን ክስ ከሳሹ እንዲያስረዳ ይገፋፋል፤ ተከሳሽም መከላከያውን ያለፍርሃትና ሥጋት ለማቅረብ ያስችለዋል፡፡ ዳኞችም በፍርሃት፣ በሥጋት ወይም በስሜት እንዳይፈርዱ የሕዝብ አስተያየት በታዛቢነት ይመለከታቸዋል፡፡ የግልጽ ችሎት ጽንሰ-ሃሳብ እየዳበረና የሕግ ጥበቃ እያገኘም የመጣው በዚህ ምክንያት ነው፡፡

4. ስርዓት (Following the legal procedures)
ክርክር/ሙግት የጨረባ ድግስ እንዳይሆን ሥርዓት እንዲከተል ማድረግ የተገባ ነገር ነው፡፡ ክስ እንዴት እንደሚቀርብ፣ መልስ እንዴት እንደሚሰጥ፣ ማስረጃ እንዴት እንደሚቀርብና እንዴትም እንደሚመዘን፣ ማን አስቀድሞ እንደሚናገር፣ ማን መልስ እንደሚሰጥ፣ ጥያቄ እንዴት እንደሚቀርብ፣ ወዘተ…ሥርዓት ካልተበጀ እውነትን የያዘው ተጎድቶ አፍ ያለው ረትቶ ሊሔድ ይችላል፡፡

5. ጭብጥ (Determining fact in issue or legal issue)
ጭብጥ የሙግት ልብ ወይም እምብርት ነው፡፡ ጭብጥ ተለይቶ መውጣቱ ለግራ ቀኙና ለዳኛም እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ ነው፡፡ ሙግት ለማገዶ እንደሚሰበሰብ ፍልጥ ቢታሰብ ጭብጡ እንደማሠሪው ልጥ ሊመሰል ይችላል፡፡ ‹‹ለሺህ ፍልጥ ማሰሪው ልጥ›› ነውና ጭብጥ የሙግት መሰብሰቢያና ማሰሪያ ነው፡፡

ማሰሪያ የሌለው ፍልጥ እንደሚበታተንና ለአያያዝ እንደሚያስቸግር ሁሉ በጭብጥ ያልተያዘ ሙግትም ወደ ጭፍጫፊ ነጥቦች እየተሰነጣጠረና እየተሰበጣጠረ ስለሚሔድ መያዣ መጨበጫ የሌለው ይሆናል፡፡

በመሆኑም ጭብጥ የሙግት/ክርክር ዳር ድንበርና ይዘት ጭምር ወሳኝ ነው፡፡ ግራ ቀኙ የተለያዩበትን ሥረ ነገርና ሕጋዊ መሠረቱን አጥርቶ ያመለክታል፡፡ ተከራካሪዎቹ ጭብጣቸውን እንዲያስረዱ፣ በጭብጣቸው እንዲረጉ፣ ፈራጅም በጭብጡ ተወስኖ ማስረጃውን መዝኖ ክርክሩን አዳምጦ ሕጉን አገላብጦ ሙግትን እንዲቆርጥ ውሳኔውን እንዲሰጥ ያስችለዋል፡፡

6. ማስረጃ (Evidence, may be eyewitness, documentary, demonstrative, or expert opinion if any)
ፍርድን በማስረጃ ላይ የተመሠረተ መሆን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ አስተያየት የሚቀረጸው በማስረጃ ላይ በመመሥረት ነው፡፡ ማስረጃ በሁለት ወገን የሚቀርብና አልፎ አልፎም ዕውቅ ነገር ሲያጋጥም ከፈራጅ ግንዛቤ (judicial notice) የሚፈልቅ ነው፡፡ በእነዚህ ላይ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ጠቃሚ ነው የሚትሉትን ነገሮች መጨመር ትችላላችሁ. እስራኤል ዶሳ..✍️

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

05 Jan, 14:46


አንድ ሰው አስቦ ወደ ሌላ ሰው ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ ካስተላለፈ በስህተት ወይም ተጭበርብሮ መሆኑን ካላስረዳ ገንዘቡ እንዲመለስ የመጠየቅ መብት የሌለው መሆኑን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
Join👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

05 Jan, 13:16


የሠ/መ/ቁ 193894
(ያልታተመ)
🍁🍁🍁
አቅመ ደካማ ሆነው ጧሪ ፍለጋ ቀበሌያቸውን የለቀቁ የገጠር መሬት ባለይዞታዎች መሬታቸውን ሊነጠቁ የማይገባ ስለመሆኑ
(የትግራይ ክልል የገጠር መሬት አዋጅ 239/2006)

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

05 Jan, 13:16


ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅጽ 19 መ.ቁ. 110549 ላይ የገጠር የእርሻ መሬትን መሸጥ ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ በይርጋ ሳይገደብ በማንኛውም ጊዜ ሊፈርስ የሚችል ውል ነው ተብሎ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሠጥቷል።

የገጠር የእርሻ (ባዶ) መሬት ከገዛ በኊላ ይዞታው ወደ ከተማ ክልል ገብቶ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ገዥ የይዞታው ማረጋገጫ ሰንድ ቢወስድም ይዞታው ወደ ገዢው የገባበት የገጠር መሬት ሽያጭ ውል ከመነሻውም ህጋዊ ባለመሆኑና በህግ አግባብ ባልተገኘ ይዞታ ላይ የሚሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ስልጣን ባለው አካል በመሰጠቱ ብቻ ህጋዊ ሊሆን የሚችልበት አግባብ የሌለ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 እና 1196 ጣምራ ንባብ አንፃር ተቀባይነት የሚያገኝ አይደለም።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

05 Jan, 05:43


@ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

03 Jan, 19:07


ባልና ሚስት በጋብቻ መካከል የሚያደርጉት የስጦታ ውል ተቀባይነት አለው?

በጋብቻ መካከል በየትኛውም ንብረት ላይ ባልና ሚስት እርስ በራስ የሚያደርጉት የስጦታ ውል ፍ/ቤት ቀርቦ ካልፀደቀ በቀር  በህግ ፊት ተቀባይነት የለውም።ሲል የፌደራል ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት በሰ.መ.ቁ. 158292 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
Telegram 🔥👇
https://t.me/ethiolawtips
Business law tips
@henoktayelawoffice

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

02 Jan, 20:03


ፀደቀ‼️በኢትዮጵያ #የወንድ_የዘር_ፈሳሽ ልገሳ፣ የሰውነት አካል መለገስ እና በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል። አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው። ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል። ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅን አጸደቀ
**

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ (ዶ/ር)፥ የአዋጁን አስፈላጊነት እና በአዋጁ የተካተቱ ድንጋጌዎችን አስመልክተው ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል።

በተለያዩ ሕጎች በተበታተነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የሚገኙ የጤና አገልግሎቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በአንድ ማእቀፍ ሕግ እንዲወጣ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት እና ከነዚሁ ድንጋጌዎች በተጨማሪም አሁን ወቅቱ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ ደረጃ የተጣጠመ አዳዲስ የጤና አገልግሎት ድንጋጌዎችን በማካተት እና በስራ ላይ የነበሩት ድንጋጌዎችን በማሻሻል ወጥ የሆነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የሕግ ማእቀፍ በማስፈለጉ የተዘገጀ ረቂቅ አዋጅ ነው ።

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

02 Jan, 18:06


#የፌዴሬሺን_ምክር_ቤት_ውሳኔ_በዐይነ_ስውራን_ጉዳይ
ፌ/ም/መ/ቁ. 019/08

"የዳኝነት ሥራ ተፈጥሯዊ ባሕርይ  ማየት የተሳናቸው ሰዎችም ተመጣጣኝ ማመቻቸት ከተደረገላቸው ሊሠሩ የሚችሉት ሙያ ስለሆነ  'ማየት የተሳናቸው ሰዎች የዳኝነት ሥራን መሥራት አይችሉም' የሚል ልማዳዊ አሠራርን በመከተል ከዳኝነት ዕጣ ድልድል ውጭ በማድረግ በዐቃቤ ሕግነት የመመደብ ውሳኔ ማየት የተሳናቸው ሰዎች በመረጡት ሙያ የመሰማራት እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ የእኩልነት መብታቸውን የሚጋፋ ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 41(2)፣ 25 እና 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም።" -የፌደሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

02 Jan, 08:40


ዋስትና ድጋሚ መነሳት የሚችል እና የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 74 በሰፊው የተተረጎመበት እና ለክስ መመስረቻ 15 ቀን ከተሰጠ በኋላ በዚህ ጊዜ ውስጥ ክስ ካልተመሰረተ አዲስ ነገር በመሆኑ የዋስትና ጥያቄ ማንሳት እንደሚቻል ትርጉም የተሰጠበት የሰበር ውሳኔ👇
Join https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

12 Nov, 00:41


Legal job vacancy
0 experience
@ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

11 Nov, 07:53


ስለ ውርስ ይርጋ የተሰጠ ውሳኔ አግባብነት /የሕግ ጉዳይ/

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 243973 ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአመልካች እነ ወ/ሮ ጠይባ መሐመድ እና በተጠሪ አብዱልዋሀብ መሐመድ መካከል በሰጠው ውሳኔ ወራሽነት ማስረጃ ይዞ ወይም አሳውጆ ነገር ግን ውርሱ ሳይጣራ ወይም ንብረቱን በእጁ ሳያስገባ ሦስት ዓመት ካለፈ ውርስ የመካፈል መብቱ ያልፍበታል ወይም በይርጋ ቀሪ ይሆናል ሲል ወስኗል። ይህ ውሳኔ ምን ያህል ተገቢ ነው?

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ሲጽፍ በትንታኔው መጨረሻ ላይ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000 /1/ መሠረት የወራሽነት ክስ በሦስት ዓመት ውስጥ ካልቀረበ ተቀባይነት እንደሌለው አስቀምጧል። ሦስት ዓመቱ የሚቆጠረው ከመቼ ጀምሮ ነው ለሚለው ጥያቄ ከሳሹ ሁለት ነገሮችን ባወቀ በሦስት ዓመት ውስጥ መክሰስ አለበት ብሏል። እነኚህም 1ኛ/. እሱ እራሱ የወራሽነት መብት ያለው መሆኑን እና 2ኛ/. ንብረቱ በሌላ ሰው ማለትም በተከሳሹ መያዙን ናቸው። እነኚህን ባወቀ በሦስት ዓመት መክሰስ አለበት ብሏል። በዚህ መሠረት ውርስ ሳይጣራ ወራሽነት መብቱን አሳውጆ ብቻ ንብረቱን በእጁ ያላስገባ ሰው ከሦስት ዓመት በኋላ አካፍሉኝ ብሎ መጠየቅ አይችልም የሚል ውሳኔ ሰጥቷል።

ይህንን በሚመለከት የፍትሐብሔር ሕጉ በቁጥር 999 የወራሽነት ጥያቄ ክስ ምን እንደሆነ ትርጉም ይሰጠዋል። የወራሽነት ጥያቄ ክስ ማለት እውነተኛው ወራሽ በሌላ ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ባደረገ ሰው ላይ ወራሽነቱ እንዲታወቅለትና ንብረቶቹን እንዲመልስ የሚያቀርብበት ክስ ነው። የወራሽነት ጥያቄ ክስን በሚመለከት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 998 /1/ እንዲህ ዓይነት ክስ በቀረበላቸው ጊዜ ዳኞች ያላግባብ የተሰጠውን የወራሽነት ምሥክር ወረቀት ሊሠርዙት እንደሚችሉ ይደነግጋል። ስለዚህ ሁለቱን አንቀጾች አንድ ላይ ስናገናዝብ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ማለት ያለ አግባብ ወራሽነቱን አሳውጆ የውርስ ሀብት የያዘ ሰው የምሥክር ወረቀቱ እንዲሠረዝበትና ንብረቱን እንዲመልስ እውነተኛው ወራሽ የሚያቀርበው ክስ ብቻ ነው እንጂ ማንኛውም የውርስ ልካፈል ጥያቄ አይደለም። ሰበር ፍርድ ቤቱ ግን ማንኛውንም የውርስ አካፍሉኝ ጥያቄን የወራሽነት ጥያቄ ክስ አድርጎ መውሰዱ ትክክለኛ አይደለም። ውርስ ሳይጣራ የሚቀርብ ማናቸውም የውርስ ልካፈል ጥያቄ በሦስት ዓመት ውስጥ መቅረብ አለበት የተባለው የተሳሳተ ነው።

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ የጀርመንን ሕግ መሠረት በማድረግ የተቀረጸ መሆኑን ካተተ በኋላ የኢትዮጵያ ሕግ የሚዛመደው ከእንግሊዝ ሕግ ጋር ነው በማለት የደረሰበት ድምዳሜም አሳማኝ አይደለም። በዓለም ላይ ሦስት ዓይነት የውርስ ማስተላለፊያ መንገዶች መኖራቸውን አትቶ እነኚህም 1ኛ/. ሞትን ተከትሎ በቀጥታ ለወራሾች የሚተላለፍበት፣ 2ኛ/. የወራሾች ፈቃደኝነት ተረጋግጦ የሚተላለፍበት እና 3ኛ/. ውርሱ እስኪጣራ ድረስ ንብረቱ በሌላ ሰው እጅ ቆይቶ የማጣራቱ ሂደት ካለቀ በኋላ ለወራሾቹ የሚዘዋወርበት መሆኑን ገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ የጀርመኑ የሚከተለው ሞትን ተከትሎ ወዲያውኑ ለወራሾች የሚተላለፍበትን የመጀመሪያውን ሥርዓት ነው ሲል አስቀምጧል። በመቀጠልም የኢትዮጵያ ግን የሚዛመደው ከሦስተኛው ዓይነት የእንግሊዝ ሕግ ጽንሰ ሀሳብ ጋር ነው ብሏል። ለዚህም ሰፋ ያለ ትንታኔ አቅርቧል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ የጀርመንን መሠረት በማድረግ የተቀረጸ ሆኖ ሳለ ከዚያ የተለየ ሊሆን የሚችልበት ምክንያት አሳማኝ አይደለም። እንዲያውም የፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 826 /1/ አንድ ሰው የሞተ እንደሆነ በሞተበት ጊዜ ዋናው መኖሪያ ስፍራው በሆነ ቦታ የሟቹ ውርስ እንደሚከፈት ይደነግጋል። ከዚህ የምንረዳው በኢትዮጵያ ውርስ የሚከፈተው በሌላ የሽግግር ሥርዓት ሳይሆን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሟች እንደሞተ ወዲያውኑ በሚኖርበት ቤት መሆኑን ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ የውርስ ሕግ የሚቀራረበው ከዛው ከተወሰዱበት ከጀርመን እንጂ ከእንግሊዝ ሕግ ጋር ሊሆን አይችልም። ከዚህ ጋር በተጣጣመ የፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1124 /1/ ውርስ ከተከፈተ በኋላ አንድ ወራሽ በውርስ የሚያገኘውን መብት በከፊል ወይም በሙሉ ለሌላ አሳልፎ መስጠት ይችላል ይላል። አንቀጽ 826 እና 1124 /1/ አንድ ላይ ስናናብባቸው አንድ ሰው ሲሞት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውርሱ እንደሚከፈት፣ ወራሹም ወዲያውኑ (ከማሳወጁም በፊት) በውርስ መብት እንደሚያገኝ እና ይህንንም ለሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደሚችል ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ሕግ ውርሱ ለወራሾች የሚተላለፈው ሞትን ተከትሎ በቀጥታ ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ማንኛውም ወራሽ በሦስት ዓመት ውስጥ ካልጠየቀ መብቱን ያጣል የሚለው አተረጓጎም ትክክል አይደለም። በሕግ የተገኘ መብት ለሌላ እስካልተላለፈ ድረስ እንዲሁ ሊጠፋ የሚችል ነገርም አይደለም። ይህ ዓይነቱ አተረጓጎም ድጋሚ በደንብ እየታየ ሊስተካከል ይገባል።

እንዲህ ዓይነት አተረጓጎም በሀገር ላይ እና በሕብረተሰቡ አኗኗርና ባህል ላይ የከፋ ውጤት ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ሊስተዋል ይገባል። ልጆች ከወላጆቻቸው መካከል አንዳቸው ሲሞቱ የቀረውን አስቀምጦ በመጦር ፈንታ ሦስት ዓመት ሳያልፍ መብቴን ልጠየቅ በሚል ወላጆቻቸውን በስተእርጅና እንዲከሱ፣ ንብረት እንዲካፈሉ፣ ለእንግልት እንዲዳርጉ ያደርጋል። በቤተሰብ መካከል መተማመንን የሚያጠፋም ነው። ንፁሀንን የሚጎዳና የውርስ ሀብት አላካፍልም ብለው ለሚክዱና በሸፍጥ ለሚከራከሩ የተሻለ ዕድል የሚሰጥም ነው። ስለዚህ አሁን ሰበሩ ፍርድ ቤት በዚህ ጥያቄ ላይ ያለውን ጉራማይሌ አተረጓጎም አንድ ወጥ ለማድረግ መሥራቱ ጥሩ ጅምር ቢሆንም ይህንን አተረጓጎሙን በቶሎ ሊያስተካክለውና ሊያዳብረው ይገባል። ዩኒቨርስቲዎችና የሕግ ሙያ ማኅበራትም የተለያየ ዐውደ ጥናቶችንና ኮንፍረንሶችን ከፍርድ ቤቱ ጥናትና ምርምር ክፍል ጋር በመተባበር ሊያዘጋጁና ሊያግዙ ይገባል።
በጠበቃ ታምራት ኪዳነማርያም
Join👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

04 Nov, 14:04


በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በውርስ ሀብት ክፍፍል ላይ ከሰባት ባላነሱ ዳኞች የተሰጠው አዲስ የሰበር ሰሚ ውሳኔ ግልባጭ
JOIN👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

01 Nov, 07:33


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ አደርገ

The National Bank of Ethiopia Announces the Launch of an Online Inter-Bank Money Market Platform

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

27 Oct, 14:34


#የሰበር መዝ/ቁ 240242
~ግንቦት 29/2016ዓ.ም~
`````````````````````
የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የ አደራ ውል የግድ በፅሁፍ ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ እና አንዲህ አይነት ዉል (ይዞታ ላይ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የ አደራ ዉል) ንብረቱን ሌላ ሰው ለግዜው አንዲጠብቅ አንጂ የማስተላለፍ ዉጤት ያለው ባለመሆኑ ዉሉ የ ፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1723(1) በሚደግገው መሰረት በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት የግድ መደረግ የሌለበት ስለመሆኑ የፌደራል ጠ/ፍ/ቤ/ሰበር ሰሚ ችሎታ በመዝገብ ቁጥር - 240242 (ያልታተመ) ላይ በ ቀን - 29/09/2016 አ.ም አስገዳጅ ትርጉም ሰጥቷል::

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

24 Oct, 13:50


ABOUT-LAW is a premier e-legal service platform established in October 2020. Whether you need legal advice, legal documents, , or any other legal assistance, we are here to help.

Join us Now!

Link- https://t.me/ethiolawblog

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

22 Oct, 15:19


ወራሽነት ማረጋገጫ የያዘ ሰው በማናቸውም ጊዜ ንብረት መካፈል ይችላል የሚለው ውሳኔ ተሽሯል።
የፌደራል የሰበር ሰሚ ችሎት ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የወራሽነት የምስክር ወረቀት የያዘ ሰው በማንኛውም ጊዜ የውርስ ንብረት ጥያቄ ማንሳት ይችላል ተብሎ ከዚህ ቀደም በሰበር በመ/ቁ 205248፣ መ/ቁ 44237፣ 38533 የተሰጡ ውሳኔዎችን አሻሽሏል። በሌላ ልዩ ሕግ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የወራሽነት ጥያቄ በፍ/ሕ/ቁ 1000 በተመለከተው የጊዜ ገደብ በይርጋ ይታገዳል። የውርስ ማጣራት ተጠናቆ ንብረቱ የጋራ ባልሆነበት ሁኔታ የወራሽነት ምስክር ወረቀት በመያዝ ብቻ የፍ/ሕ/ቁ 1062 መሠረት በማድረግ ያለጊዜ ገደብ የክፍፍል ጥያቄ ሊነሳ አይችለም የሚል የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል።
የውሳኔውን ይዘት ከዚህ ይመልከቱ


https://www.abyssinialaw.com/know-your-rights/case243973-inheritance-claim-timing-revoked
Join👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

22 Oct, 15:18


በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም የተሰጡ ሁለት ውሳኔዎች
👇👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

21 Oct, 11:36


Legal Job Vacancy
position - Junior attorney position
👉Oromia Bank Share Company

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

20 Oct, 14:52


የሚኒስሮቹ አሿሿም የህጋዊነት ጥያቄ አስነሳ!

በትላንትናው ዕለት ማለትም ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሦስት ሚኒስትሮችን መሾማቸው ዋነኛ ዜና ሆኖ ውሏል። ከዛም ባሻገር ህጋዊነቱ ላይ ጥያቄ ተነስቶበታል፣ በመሆኑም ጉዳዩ አከራካሪ ሆኗል። ይህን ሁኔታ ተከትሎም የህግ ምሁራን የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሙያዊ አስተያየትና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

በዚህም ምክንያት በርካታ ጥያቄዎች መነሳት ጀምረዋል፣ ከእነዚህም መካከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችን በቀጥታ መሾም ይችላልን? በአንድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ ባልና ሚስትን መሾምስ የጥቅም ግጭት/Conflict of Interest አያስከትልምን? በሀገሪቱ ብቃት ያለው ሰው ጠፍቶ ነው ወይ የአንድ ቤተሰብ አባላትን በካቢኔያቸው ውስጥ ለመሾም የተገደዱት? ወዘተ. የሚሉት ይገኙበታል።

እኔም የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎች መሠረት በማድረግ እንደ አንድ የህግ ባለሞያ ሀሳቤን እንደሚከተለው ለመግለጽ ወደድሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችን በዕጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያጸድቃል እንጂ በቀጥታ የመሾም ስልጣን የላቸውም። አይደለምና የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል የሚሆኑ ሚኒስትሮችን ቀርቶ የሚኒስትሮች ም/ቤት አባል የማይሆኑ ኮምሽነሮችን መሾም አይችልም።

ለምን የተባለ እንደሆነ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 74(2) ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ም/ቤት አባሎችን ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ወይም ለስራው ብቃት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች መካከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት አቅርቦ ሹመታቸውን ያስጸድቃል በማለት ይደንግጋል እንጂ ሚኒስሮችን ራሱ እንዲሾም ስልጣን አልሰጠም።

ህገ መንግስቱ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በአንቀጽ 55(13) ላይ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግስት ፍርድ ቤት ዳኞችን፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን፣ የኮምሽነሮችን፣ የዋና ኦዲተርን እንዲሁም የሌሎች ሹመታቸው በምክር ቤት መጽደቅ ያለበትን ባለስልጣኖች ሹመት ያጸድቃል ስለሚል ከእነዚህ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች አንጻር ካየነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው ሹመት ህጋዊ መሆኑ ላይ ጥያቄ ያስነሳል።

በሌላ በኩል በአገሪቱ ያን ያህል ሰው የጠፋ ይመስል የተወሰኑ ሰዎችን ከአንዱ መስሪያ ቤት ወደ ሌላኛው መስሪያ ቤት እያዘዋወሩ መሾሙስ ተገቢ ነውን ለሚለው ጥያቄም መልሴ በፍጹም አይደለም የሚል ይሆናል። በተለይም የአንድ ቤተሰብ አባላት በአንድ ካቢኔ ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወስኑ ማድረግ የጥቅም ግጭት የሚያስከትል መሆኑ አይቀርም።

ከሁሉም በላይ ግን ባል ሚኒስትር ሆኖ የሰራበትን መስሪያ ቤት ሚስት ሚኒስትር ሆና ስትሄድ በመ/ቤቱ ሰራተኛ ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ጫና እና ምናልባትም የቀድሞው ሚኒስትር በስራ ሒደት የፈጠረው ችግር ቢኖር ወይም ያለአግባብ ያስከፋቸው የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ቢኖሩ አዲሷ ሚኒስትር የእሳቸውን ገበና በድፍረት በማጋለጥ የማስተካከል ዕድላቸው ጠባብ ነው የሚሆነው።

ለማንኛውም የሚኒስትር መስሪያ ቤቶቹ ሠራተኞች በየመስሪያ ቤቶቹ የፌስ ቡክ ገጻቸው ላይ የተሰማቸውን 'ደስታ' የገለጹ ሲሆን በእነሱ አተያይ ሹመታቸውም ያለቀለት ይመስላል። ለመሆኑ የሚኒስትሮቹ ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ሲቀርብ ተቀባይነት ሳያገኝ ቢቀርስ ውጤቱ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? እስቲ ተወያዩበት!
sisay m. Addisu

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

19 Oct, 09:49


መደብ- የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሬጅስትራር
ብዛት -30
ልምድ -2
ደመወዝ -11000+2000
@ethiolawtips

Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

19 Oct, 09:28


የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

16 Oct, 12:14


https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

14 Oct, 11:45


https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

14 Oct, 11:24


መደቡ- የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ
ብዛት-7
ደመወዝ - 23,117+5500+400
ልምድ-7&6
Join👇
@ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

14 Oct, 11:15


ልምድ -6 ዓመት
ደመወዝ -10,150
መደቡ-የሕግ ባለሙያ

የፕላንና ልማት ሚንስቴር

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

11 Oct, 11:13


የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት
ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ አጭር ማብራሪያ

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

11 Oct, 11:00


Share የደቡብ ኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁ.docx
@ethiolawtips
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

08 Oct, 07:02


To: All final year (5th year) law students at law schools in Ethiopia

RE: Application for Externship Position

Mehrteab & Getu Advocates LLP (MLA) is considering to host up to four graduating class law students during first semester of 2024/25 academic year. Accordingly law students who are eligible for Externship during this semester can apply for the position.

Eligibility Criteria for application

1. Being a final year (5th year) law student at any law school in Ethiopia;
2. Having a minimum CGPA of 3.5 at the time of application; and
3. One page motivation letter and up to date CV.

Date of application – up to Wednesday 09 October 2024
Mode of application – by email addressed to the Firm’s Manager Sophia Bellete at [email protected]

Selection Criteria

CGPA (50%), participation in extra curriculum activities and trainings (30%) and motivation letter (20%).

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

06 Oct, 05:36


ከህግ ትምህርት ቤት መሠረታዊ ትሩፋቶች ጥቂቶቹ
*********
ምንጭ ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ Tiblet Bushra
**********
የህግ ትምህርት ቤት በአንድ ወገን ብቻ የተነገረ ታሪክ ወይም ፍሬ ነገር ሁሌም ጎዶሎ እንደሆነ ያስተምርሀል፡፡ በምንም ጉዳይ አቋም ከመውሰድህ፣ ከመፍረድህ፣ አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ሙሉ ታሪኩን ማወቅ በመርህ ደረጃ እንደቅድመ ሁኔታ ያስቀምጥብሀል ”There is always the other side of a story” ብለህ እንድታስብ ያስገድድሀል፡፡ ከዛ ውጪ የሚደረስ ድምዳሜ ትክክለኛ ያልሆነ ወይም የተዛባ፣ ያዳለ፣ ፍትሀዊነት የጎደለው ነው፡፡ ይህ አይነት አስተሳሰብ እንዲኖርህ የሚጠበቀው ደግሞ እጅህ ላይ በመጡ የህግ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆን በአገራዊ ጉዳዮች፣ በግለሰቦች ጉዳዮች በምትሰማቸው ከአንድ ወገን የሚነገሩ ታሪኮች፣ ውሳኔዎችም ጭምር ነው፡፡

የህግ ትምህርት ቤት ለሀሳቦች ክፍት መሆንን (Open mindedness) ያስተምርሀል፡፡ እውነት ወይም ሀሰት ፈተና ቀርቦልህ ለአንድ ጥያቄ እውነትም ብለህ 10/10 ሀሰትም ብለህ 10/10 ልታገኝ ትችላለህ ልታጣም ትችላለህ፡፡ ለመልስህ እንዳቀረብከው የክርክር ነጥብ ጥንካሬ እና ምክኒያታዊነት፡፡ በዚህ አንተ ከያዝከው ሀሳብ የተለየ ሀሳብ ይዞ አሳማኝ ምክኒያት ለሚያቀርብልህ እጅ መስጠት እና የራስን ሀሳብ በምክኒያት መተው ሽንፈት እንዳልሆነ ያስተምርሀል፡፡

የህግ ትምህርት ቤት የሀሳብ ነጻነት ጠቀሜታን፣ የሀሳብ ነጻነት ማክበርን ወይም ለሌሎች እይታ ዋጋ መስጠትን ያስተምርሀል፡፡ በአንድ አከራካሪ ጉዳይ ላይ አስተማሪህ የያዘውን አቋም እያወክ ይህን ጉዳይ በፈተና መልክ ሲያመጣው ካስተማሪው የተለየው የራስህን አቋም በምክኒያት አስደግፈህ ካቀረብክ ከኔ አቋም ውጪ አቋም ኖረው ብሎ ዜሮ አይሰጥህም፡፡ ካንተ ጋር ባይስማማም እንደ መከራከሪያ ነጥቦችህ ጥንካሬ እና ምኪኒያታዊነት ከፍ ያለ ማርክ ሊሰጥህም ይችላል፡፡ ይህን ሲያረግ ከኔ ብትለይም ያንተን ሀሳብ አከብራለሁ፣ ዋጋ እሰጠዋለሁ፣ አቋሜን እያወክ የራስህን አቋም ማስቀመጥህን እንደንቀት አላየውም እንደጥንካሬ፣ እንደ እሴት ጭማሪ አየዋለሁ እንጂ የሚል ትምህርት ያስተምርሀል፡፡

የህግ ትምህርት ቤት ስለ “ጥርጣሬ ተጠቃሚ” “benefit of doubt” ጽንሰ ሀሳብ ሲያስተምርህ ይህን ጽንሰ ሀሳብ ከወንጀል ጉዳዮች በዘለለ በሌሎች ጉዳዮችም እንድትተገብረው ጥበብን (wisdom) ያስተምርሀል፡፡ ስለሆነ ሰው ወይም ጉዳይ የማትገምተው አይነት ነገር ስትሰማ “እውነት ላይሆን ይችላል” “ከሚመስለው ውጪ ሊሆን ይችላል እውነቱ” “ምናልባት ይሄን እንዲያደርግ ያስቻለው አስገዳጅ ሁኔታ ሊኖር እኮ ይችላል” እና የመሳሰሉ ሌላ ከሚኖሩ አጠራጣሪ ነገሮች ለመጠቀም የሚያስችለው ሁኔታዎችን ከግምት ማስገባትን ሊጨምር ይችላል፡፡

የህግ ትምህርት ቤት በመርህ ደረጃ በጭፍን መታዘዝ (blind obedience) ልክ አለመሆኑን ያስተምራል፡፡ ለአለቃ መታዘዝ አንደኛው የስነ-ምግባር ግዴታ ቢሆንም ህገ-ወጥ የሆነ ትእዛዝን አለመቀበል መብትህ ሳይሆን ግዴታህ አርጎ ያስተምርሀል፡፡ ይህ ትምህርት እና አመክኒዮው ደሞ ለሌሎች ጉዳዮችም እንድትጠቀመው ትምህርት ይሆንሀል፡፡

የህግ ትምህርት ቤት ስለሰው ልጆች ክቡርነት፣ እኩልነት፣ ነጻነት… እያስተማረህ ትህትናን/ humility፣ በምንም ሁኔታ ላይ ብትሆን አንተ ከማንም እንደማታንስ ከማንም እንደማትበልጥም ያስተምርሀል ወይ ደግሞ ያስታውስሀል።

የህግ ትምህርት ቤት ባህል፣ ወግ፣ ሀይማኖት፣ ማንነት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ወይም በግለሰቦች ውስጥ ያለውን ቦታ ያንን ችላ ያለ ምንም ነገር ዘለቄታ እንደማይኖረው ያስተምራል፡፡ በዛው ልክ ጎጂ የሆኑ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመቀየር ወይም አዲስ ባህልን ለመፍጠር (to set Norm or standards) ሕግ ያለውን ኃይል ያሳይሀል

የህግ ትምህርት ቤት የህግ የበላይነትን መጠበቅ ወይም ማስጠበቅ ለሁላችንም የጋራ ሰላም፣ ደህንነት እና ጥቅም፣ ዋስትና መሆኑን ፈትፍቶ ያስተምርሀል፡፡

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

04 Oct, 13:58


በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ተጠናቆ ለህትመት በቃ!!
የፌዴራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ እና ከጄስቲስ ፎር ኦል ፒ.ኤፍ. ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዐውደ ጥበባዊ የሕግ መዝገበ ቃላት (Encyclopedic Law Dictionary) ምረቃ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ጀምሮ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችና የፍትሕ ዘርፉ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል፡፡

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

30 Sep, 11:28


የቤት ሽያጭ ውሎችን በሚመለከት በሰበር ችሎት የተሰጡ ውሳኔዎች
Join👇
@ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

30 Sep, 06:48


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው ውሳኔ አንድ ሰው አስቦ ወደ ሌላ ሰው ሂሳብ ቁጥር ገንዘብ ካስተላለፈ በስህተት ወይም ተጭበርብሮ መሆኑን ካላስረዳ ገንዘቡ እንዲመለስ የመጠየቅ መብት የሌለው መሆኑን አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
Join👇
@ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

28 Sep, 09:26


የስራ መደቡ የህግ ባለሙያ 3
ልምድ 4
ደመወዝ 7071
ልምድ 6
ደመወዝ 9056
Join👇
@ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

26 Sep, 09:06


ማስታወቂያ

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥብቅና ፈቃድ በፈተና ለማግኘት በአዋጅ ቁጥር 1249/2ዐ13 የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ/የምታሟላ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ/ት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

25 Sep, 13:46


ክፍት የስራ ማስታወቂያ
@ethiolawtips
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ባለው ክፍት የስራ ቦታ በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸውን በዜሮ አመት የስራ ልምድ እና ከአምስት አመት በላይ የስራ ልምድ ያላቸውን ሙያተኞች አወዳድሮ መቅጠር ስለሚፈልግ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
መመዝገቢያ መስፈርቶች
1ኛ ኢትዮጵያዊ የሆነች/የሆነ በኢትዮጵያ የሚኖር
2ኛ ለህገመንግስቱና ለህግ የበላይነት ተገዥ  የሆነ
3ኛ የየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ች  እና ወንጀል ቅጣት የሌለበት፡፡
4ኛ በታታሪነቱ/ቷ/ በስነምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች/ ማስረጃ  ማቅረብ  የሚችል/የምትችል/
5ኛ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የተመረቀ/ች
6ኛ የስራ ልምድ ዜሮ አመት በ2015 እና በ2016 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ሆነው የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ለወንዶች የመመረቂያ ነጥባቸው 3.5 እና ከዚያ በላይ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች 3.25 እና ከዚያ በላይ
7ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት /15/ አስራ አምስት
8ኛ ከአምስት ዓመት በላይ የስራ ልምድ ላላቸው በአቃቢ ህግነት፣ በዳኝነት ፣ በህግ ምርምር ፣ በመምህርነት እና በተመራማሪነት ያገለገለ/ች/ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
9ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት ከአምስት ዓመት በላይ ላገለገሉ 10/አስር
10ኛ ደመወዝ በተቋሙ ስኬል መሰረት
11ኛ የስራ ቦታ ቢሮው በሚሰጠው ምደባ ቦታ፣
ተመዝጋቢዎች /ተወዳዳሪዎች/ ለምዝገባ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶች   ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ፓስፖርት የትምህርት ማስረጃቸውን ዋና ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ከምትኖሩበት አካባቢ አግባብነት ካለው አካላት የተፃፈ የስነምግባር ማስረጃ፣
የምዝገባ ቦታ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ መስከረም 12ቀን 2017ዓ.ም በሚለው እትም ወጥቷል።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0115159550 /  0115159548
        የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ
@ethiolawtips
Join Join👇👇
https://t.me/ethiolawtips

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

23 Sep, 18:20


ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚላኩ የፍ/ብሔር ይግባኞች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
🖼️ yohannes Hailu

12,395

subscribers

1,121

photos

7

videos