*********************
👉የጅግጅጋ ጉምሩክ/ቅ/ጽ/ቤት እና የገቢዎች ሚነስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከተመረጡ 08 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተዉጣጡ የታክስና ጉምሩክ ክበብ አባላት በጉምሩክ ህጎች እና አሰራር እንዲሁም በአገር ዉስጥ ታክስ ዙሪያ በጋራ በመሆን የካቲት 08 ቀን 2017 ዓ.ም በጅግጅጋ ቅዱስ ዮሰፍ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት የትምህርት ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ።
👉የስልጠና መድረኩን የከፈቱት የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ የስራ ሂደት አቶ ሲሳይ ጥላሁን ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የሰልጠናው ዓላማ አዲሱ ትዉልድ በቀረጥና ታክስ ላይ ያለዉን ግንዛቤ በማስፋት ታማኝ እና አገር ወዳድ ትዉልድ ለማፍራት የሚያግዝ መሆኑን እና በክላስተር 06 በጉምሩክ እና ታክስ ህጎች እና አሰራሮች ዙሪያ እየተሰጠ ያለዉ ስልጠና ቀጣይነት ያለዉ መሆኑን አመላክተዋል።
👉በ2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ 3ኛ የወጣችው ተማሪ ሲና አበራ ለተሳታፊ ተማራዎች የልምድ ልውውጥ እና መዘጋጀት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አሰተያየት በመሰጠት ለተወዳዳሪ ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፋለች።
👉ስልጠናዉን በአገር ዉስጥ ታክስን በሚመለከት ከገቢዎች ሚኒስትር የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ክፋዮች ትምህርት ክፍል አቶ ሚሊዮን ኢያሱ እና በጉምሩክ ህጎች እና አሰራሮች ዙሪያ ደግሞ ከቅ/ጽ/ቤቱ በአቶ ሲሳይ ጥላሁን በጋራ በመሆን ስለታክስ ምንነት፣ የታክስ ዓይነቶች፣ ስለጉምሩክ ምንነት እና የጉምሩክ ሥነ-ስረዓት አፈፃፀም እንዲሁም ኮንትሮባንድና የታክስ ማጭበርበር ወንጀሎች በሀገር ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት በተመለከተ ግንዛቤ በመፈጠር የሰልጠናው መድረክ ተጠናቋል።
************************
************************
በደንበኞች ትምህርት ቡድን የተዘጋጀ
የካቲት 10/ 2017 ዓ.ም
ጅግጅጋ, ኢትዮጵያ
**************