ETHIO NEWS @ethio_news1 Channel on Telegram

ETHIO NEWS

@ethio_news1


በየእለቱ ትኩስ እና አዳዲስ የሀገር ውስጥ የአለም ዜናዎችን በፍጥነት ሰብስበን ወደናንተ እናደርሳለን ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ

ለእውነተኛ ለትክክለኛ መረጃ ብቻ እንሰራለን።

ETHIO NEWS (Amharic)

ኢትዮ ዜማን ከሚደረገው አትክልት ለመርዳት በግእዝ ለማንበብ የተሳለንነው 'ETHIO NEWS' በውስጥ እንደናንተ የተከለከለ የመረጃ ታሪክን ስለተከታተል እና አዲስ መረጃዎችን በመግባት ውስጥ በነበሩበት በፍጥነት ሰብስበን። አሁንም ዘንድ ሚናና ጠቃሚ እንዲሆን ይረዳል። ETHIO NEWS ለኢትዮጵያ ዜሮች የምንሆን የአለም ዜናዎችን በማስተዋወቅ ከእኛ ለማወቅ የትኩስ ዝግጅት እንችላለን። ማነቃቻውን የሚያሳይ ማህበራዊ ደንበኞች የስራውን ስራዎች ስኬትን እና መረጃዎችን ስለማድረግ እናመሰግናለን።

ETHIO NEWS

06 Nov, 16:47


https://www.tiktok.com/t/ZTFcth2WQ/

ETHIO NEWS

04 Nov, 18:19


"እኔ ከተመረጥኩ ከምሰራው ዝርዝር ጋር ትራምፕ ከተመረጠ ከጠላቶቹ ዝርዝር ጋር ወደ ፕሬዚዳንት ቢሮ ይገባል" ካማላ ሃሪስ እጩ ፕሬዚዳንት

የዓለማችን ልእለ ኃያሏ አሜሪካ እጩ ተወዳዳሪ ካሚላ ሀሪስ በቀጣዩ ሳምንት በሚጠናቀቀውና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በመከናወን ላይ በሚገኘው ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ሰንብተዋል።

ይህ ምርጫ በሁለት ፓርቲዎች ወይም በሁለት እጩዎች መካከል የሚካሄድ አይደለም። ምርጫው በአንድነትና ነጻነት እንዲሁም በመከብለዋል።

በቀውስ መካከል የሚደረግ ነው ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ የመዝጊያ ንግግር በዋሽንግተን ዲሲ ፕሬዚዴንሻል ጋርደን ከነጩ ቤተመንግስት ጀርባ አድርገዋል።

ከ40 ሺ በላይ ደጋፊዎች በተገኙበት አደባባይ ባሰሙት የቅስቀሳ ንግግር በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩት እጩ ፕሬዝዳንቷ ፤ ትራምፕ ከፋፋይና ህዝቦች እርስ በርሳቸው አንዱ ሌላውን እንዲጠራጠር ቀስቅሷል ሲሉ ከሰዋቸዋል።

ትራምፕ በርካታ ክሶች የተከፈቱበትና በፍርድ ቤት በመታየት ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው ያሉት ካሚላ ሃሪስ፤ የፈጸሟቸው ወንጀሎችን ያጣሩ፣ የመረመሩና ለህግ ያቀረቡትን ለመበቀል "ጠላቶች " ያሏቸውን ስም ዝርዝር በእጃቸው መያዛቸውንና ገልጸው ፤ የፕሬዳንቱን ቢሮ አሸንፈው ከወሰዱ ከፍተኛ በቀል ሊያደርሱ እንደሚችሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል ።

እኔ ህገወጥነትን ስከላከልና ለተጎዱት ጥብቅና ስቆም ነበር ያሉት ሀሪስ፤ ከመረጣችሁኝ እዳምጣችኋላሁ፤ መግባባትንም ለመፍጠር በቁርጠኝነት እሰራለሁ። እናንተ ብቻ እድሉን ስጡኝ ሲሉ መራጮችን ተማጽነዋል።

ትራምፕ ቢመረጥ ለሃብታሞቹ ጓደኞቹ ታክስ በመቀነስ በመካከለኛ ገቢ በሚኖሩ ላይ ጫና ያበረታል፤ ካሉ በኋላ በአነሰተኛ ገቢ ለሚተዳደሩት ኑሮን ለመደጎምና የጤናን መድህን ዋስትና ለማረጋገጥ ከልብ እሰራለሁ ብለዋል።

ETHIO NEWS

08 May, 21:16


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን😘❤️👍🙏

ETHIO NEWS

08 May, 21:16


በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በአጎዋና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የአሜሪካ የኮንግረስ አባልና በኮንግረሱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ አባል ሺላ ቼርፊለስ-ማኮርሚክ ጋር ኢትዮጵያን ከአጎዋ ማግለሉ የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ቀውስን አንስተዋል፡፡

ሲያብራሩም አጎዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባሉ ዜጎች ላይ ተጽዕኖው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

በአሜሪዊያን ባለሃብቶች ገበያ ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ቀላል እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ግጭቶች፣ የአንዳንድ ቡድኖች ስርዓት አልበኝነት መረጋጋትና እድገት ላይ ተጽዕኖው እያሳደረ መሆኑንም ለኮንግረስ አባሏ ገልጸዋል፡፡

ከኮንግረስ አባል አሚ በራ ጋር ባደረጉት ውይይትም የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ማፅደቅ፣ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙና ለስደተኞች የሚሰጠውን ሰብዓዊ ድጋፍ፣ ስለአጎዋ ለኢትዮጵያና አሜሪካ የንግድ ግንኙነት አስፈላጊነት፣ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካና የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነትን ተግባራዊነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አምባሳደሩ ውይይታቸውን በመቀጠል ለኮንግረስ አባል ጆን ጋራመንዲ በአጎዋ፣ በኢትዮጵያ ሊፈጠር የሚችለው አጋርነት እና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ የሰብአዊ ድጋፍ እና የምግብ አቅርቦት፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ስለሚታዩ ግጭቶች መንስኤና ምክንያቶችም ለማብራራት እድል አግኝተዋል፡፡

ጆን ጋራመንዲ እና ባለቤታቸው ፓትሪሺያ ከፈረንጆቹ 1966 እስከ 1968 በኢትዮጵያ የሰላም ጓድ ውስጥ ያገለገሉ ሲሆን፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ሀገሪቱን በተደጋጋሚ ይጎበኙ እንደነበርም ነው ያስታወሱት።

ጥንዶቹ ችግሮችንና እድሎች ጨምሮ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ ማህበረሰብና ባህል ጥልቅ ግንዛቤ እንዳላቸው አሳውቀዋል።

ETHIO NEWS

09 Jan, 06:46


ይህን ያውቁ ኖረዋል..🇪🇹🇸🇴

ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ግጭት ከገባች ምን ይፈጠርባታል!

በሶማሊያ ያለው 20,000 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሶማሊያን ለቆ ከወጣ የአልሸባብ ሃይል ሶማሊያን ከ72 ሰአት በነሰ ጊዜ ይቆጣጠራታል።ምክንያቱም ሶማሊያ ሶማሊያ በጣም ደካማ ከአልሸባብ ራሷን መከላከል የማትችል ደካማ ሀገር ናት። በዚህም ከአለም ደካማ የሚሊተሪ ሃይል ካላቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፋለች። የሶማሊያ በ2023 የሚሊተሪ ሃይል መረጃዋ ከዚህ በታች አስቀምጣለሁ።

➠የሰራዊት ብዛት.... 17,000
➠ተጠባባቂ ሃይል.... 00
➠ ጀነራል መድፍ ..... 40
➠ሮኬት ፕሮጀክት......00
➠ ተዋጊ ጀት ..........  00
➠ተዋጊ ሄሊኮፕተር .....00
➠ባህር ሃይል .............00
➠ የውጊያ ታንክ...........15 ብቻ ያላት ሀገር ናት።
ለዚህም ነው በጀግና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምትጠበቀው።

አይበለውና አልሸባብ ድጋሚ ሞቃዲሾን ከተቆጣጠረ
በአሜሪካ መሪነት ሃያላኑ ሶማሊያ ላይ ቁጥር ስፍር የሌለው የሰብዓዊ እርዳታን ጨምሮ ከፍተኛ ማዕቀቦች ይጣላሉ።ብዙ ሀገራት ከሶማሊያ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ግንኙነት ያቋርጣሉ። አሸባሪው የአልሸባብ ሃይል የሶማሊያ ህዝብ ላይ የበቀል ሰይፋቸውን መዘው የሶማሊያን ህዝብ ቁምስቅል ያሳያቸዋል ወ.ዘ.ተ ክፉኛ ችግር ይገጥማታል።

ስለዚህ ሶማሊያ ይሄ ሁሉ ኪሳራ ከሚመጣባት ኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ድንፋታና ፉከራ ብትቀንስ ይሻላታል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ የሶማሊያ የመኖር ያለመኖር ዋስትና ናት። መረጃው ከተለያዩ ዌብሳይቶች ያሰባሰብኳቸው ናቸው። Ahmed

ETHIO NEWS

04 Jan, 05:25


ሰበር ሰበር ሰበር


የወንድም ጅቡቲ ህዝብና መንግስት ለሶማሊላንድ ሪፑብሊክ እውቅና ሰጥቷል። የእኛም ይቀጥላል!!

ኢትዮጵያ — የጥቁር ህዝቦች የነጻነት መንፈስ !!

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777

ETHIO NEWS

03 Jan, 19:24


የጃፓን አየርመንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ዛሬ በቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳረፈ #በእሳት ተያይዟል።

12 የበረራ ቡድን አባላትን ጨምሮ 379 ሰዎችን ያሳፈረው አውሮፕላን በእሳት ቢያያዝም አንድም ሰው ህይወቱ ሳያልፍ ከእሳት አደጋው ማትረፍ ተችሏል።

367 መንገደኞችን ያሳፈረው የጃፓን አየርመንገድ አውሮፕላን መነሻው በሆካይዶ ደሴት ሺን ቺቶሴ ከተባለ አካባቢ እንደነበር ተገልጿል።

አውሮፕላኑ 6 ሰዎችን አሳፍሮ ከነበረ ሌላ  የጃፓን ባህር ዘብ ትንሽ አውሮፕላን ጋር መጋጨቱ ተነግሯል። ከ6ቱ አምስቱ ሲሞቱ ፓይለቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በህይወት ተርፏል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ግን የአደጋውን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን አቋቁመዋል።

የመረጃ ምንጭ፦ ሮይተርስ፣ አልአይን፣ ዶቼቨለ ናቸው።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777

ETHIO NEWS

03 Jan, 19:24


መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ሶማሊ ላንድ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሠነድ በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበበ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ አባላት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማብራሪያው ላይ እንደገለጹት÷ አዲስ የተፈረመው የመግባቢያ ሠነድ ለኢትዮጵያ የባሕር በር እና የወደብ አማራጮችን ያሰፋል፡፡

ሠነዱ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ከማስጠበቅ አንጻር ትልቅ ሚና አለው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የመግባቢያ ሠነዱ ለኢትዮጵያ የባሕር በር እና ወደብ ከማስገኘቱ ባሻገር በተፈራረሙት ሀገራት መካከል የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ግብርና እና ቱሪዝም ትብብርና አጋርነትን ስለማካተቱ አብራርተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚንስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር እና የወደብ ባለቤት መሆን እንደሚቻል አሳይታለች ብለዋል።

ETHIO NEWS

03 Nov, 11:51


ከአንታርክቲካ ድረስ እየመጡ ባለበት ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን መፈለጓ እንደ ስህተት መቆጠር የለበትም- የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዛሬው መግለጫ ላይ የተነሳው ጉዳይ የኢትዮጵያ የወደብ ጉዳይ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጠቅላይ ሚንስትሩ ያነሱት የቀይ ባህር ወደብ ጉዳይ ዙሪያ ያለው አመለካከት ምንድን ነው? በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ተነስቷል።

ቃል አቀባዩ በምላሻቸውም "ጠቅላይ ሚንስትሩ የሀገሪቱ የመጀመሪያው ውጪ ጉዳይ ግንኙነት የሚመለከታቸው መሪ ናቸው ነገር ግን በወደብ ጉዳይ ያደረጉት ንግግር በስህተት ተተርጉሟል" ብለዋል።ኢትዮጵያ ከዚህ በፊትም አማራጭ ወደብ እንዲኖራት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስትሰራ ነበር የአሁኑ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ንግግርም ለጋራ ጥቅም በትብብር እንስራ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል።

"ከአንታርክቲካ ድረስ ወደ ቀይ ባህር የመጡ አካላት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያ አጠገቧ ያለው ቀይ ባህርን መፈለጓ ስህተት ሊሆን አይችልም" ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ETHIO NEWS

04 Oct, 23:47


አሜሪካ የDV-2025 አመልካቾችን መቀበል ጀመረች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመታዊውን የዲይቨርሲቲ ቪዛ (#ዲቪ) ፕሮግራም / " ግሪን ካርድ ሎተሪ " በመባል የሚታወቀውን በአሜሪካ ለመኖር እና ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ዛሬ ክፍት አድርጓል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ መርሃ ግብሩ ዛሬ ሩቡዕ ጥቅምት 4 ተጀምሮ ማክሰኞ ህዳር 7 ቀን 2023 ይጠናቀቃል።

አሜሪካ አሁን ባለው ፕሮግራም 55000 ለሚደርሱ የውጭ ዜጎች የግሪን ካርድ እድል ትሰጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዲቪ ፕሮግራም ለመመዝገብ / ለማመልከት ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው አሳውቋል።

ነገር ግን ወደፊት ለቃለ መጠይቅ ቀጠሮ የተያዙ ተመራጮች መደበኛ የቪዛ ማመልከቻ ከማቅረባቸው በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ። እነዚህ ተመራጮች በቆንስላ ኦፊሰር አማካኝነት ለቪዛ ብቁ መሆን አለመሆናቸውን የሚወሰንላቸው ናቸው።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዲቪ ለመሙላት ብቁ ከሆኑ በርካታ ሀገራት 55,000 አመልካቾች በዘፈቀደ በውስጥ ስርዓት ይመረጣሉ።

አስፈላጊ #መመሪያዎችን ፣ መስፈርቶችን እንዲሁም ለማመልከት ይህን ትክክለኛ ድረገፅ ይከተሉ፦ https://dvprogram.state.gov/

አመልካቾች ዲቪ ለማመልከት #ክፍያ_የማያስፈልግ ስለሆነ ከአጨባርባሪዎች እንዲጠነቀቁ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳስቧል።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777

ETHIO NEWS

27 Sep, 13:14


ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በአዳማ ከተማ ከመስከረም 03 2016 ዓ፣ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየውን የከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ፓርቲው፣ በስልጠናው ማብቂያ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርቲው ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሥራ መመሪያና ስምሪት መስጠታቸውን ገልጧል።

የአመራር አባላቱ ሥልጠና፣ በአገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ፈጥሯል ተብሏል በሥልጠናው ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ኹለት ሺህ የፓርቲው አመራሮች መሳተፋቸው ተመላክቷል። ፓርቲው፣ ተመሳሳይ ሥልጠና በየደረጃው ለሚገኙ የፓርቲው አመራሮች በቀጣይነት እንደሚሰጥም ገልጧል።

https://t.me/Skyline7777
https://t.me/Skyline7777

ETHIO NEWS

12 Sep, 02:25


መልካም አዲስ ዓመት 2016

ETHIO NEWS

07 Sep, 14:51


https://youtu.be/RtEZU5C7Dck?si=QvQr_jGUF_kamaEf

ETHIO NEWS

06 Jul, 00:06


https://vm.tiktok.com/ZM2ugVBw8/

ETHIO NEWS

05 Jul, 20:08


የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ፦

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት በሙሉ ድምፅ አጸድቋል።

ይህም ማለት በኢትዮጵያ 12ኛው ክልል እንዲደራጃ ይሁንታ ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት ፦

ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ በደቡብ ክልል ሥር ሲተዳደሩ የቆዩት ፦
👉 የዎላይታ ፣
👉 የጋሞ ፣
👉 የጎፋ ፤
👉 የኮንሶ ፣
👉 የደቡብ ኦሞ ፣
👉 የጌዲኦ ዞኖች እንዲሁም
👉 የአማሮ ፣
👉 የቡርጂ ፣
👉 የደራሼ ፣
👉 የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ ክልል ሆነው " ደቡብ ኢትዮጵያ " በሚል እንዲደራጁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በሌላ በኩል ፦
👉 የሃድያ ፣
👉 የከንባታ ጠንባሮ ፣
👉 የሀላባ ፣
👉 የሥልጤ ፣
👉 የጉራጌ ዞኖችና እና የየም ልዩ ወረዳ ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት #በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል።