ትምህርት ሚኒስቴር @ethio_ministry_education Channel on Telegram

ትምህርት ሚኒስቴር

@ethio_ministry_education


ETHIOPIAN MINISTRY OF EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር (Amharic)

የምድን ኢትዮጵያ ፕሮምናክስ ማኔጅ ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ቀናት የኢትዮጵያ ህዝብ ትምህርትን እና ስነ-ምግባር የሚገባኝ ነው። ይህ ታሪክ በኢትዮጵያ ህዝብ መሆንን ያውቃል። ብዙ ትህነግም ለህዝብ የትምህርት ጥቅም እና መንግስት እንዲለቅ ትህትና እያለ ነው። አሁን ለምን እንደሚታወቅ በአፋባታ እና ምናልባት ስለ ትምህርት የምታደርግም የሚችል ነው? በቅድም በዚህ ታሪክ የህዝብ ትምህርት ለመጠቀም እና በተለያዩ ቦታ ለመከታተል ስለሆኑ ህዝቦች ብትልቀቁ ሆነዋል። ይህ ታሪክ በማንኛውም ቀኝ የተቀናጀ እና አንዴ ነገር ሊደረግባቸው ነው። በእያንዳንዳቸው በእንግሊዝኛ ሰነዶ የተለየ እና ለእንግሊዝኛ እንዲህ በመድረሱ ይጠቀሙታል።

ትምህርት ሚኒስቴር

21 Nov, 09:51


4. ሁለገብ የጥገና ሠራተኛ

° ደረጃ፡-9 
° ደመወዝ፡- 24,435
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በእንጨት ወይም በብረት ሥራ
° የትምህርት ደረጃ፡-  10+2
° የስራ ልምድ ፡- 3 ዓመት 
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

5. የመረጃ ዴስክ ባለሙያ

° ደረጃ፡-11
° ደመወዝ፡- 29,029
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በጆርናሊዝም፣ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ፣ ፖለቲካል ሣይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡-  የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-1/0  ዓመት 
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

ምዝገባ በኦን ላይን https://tinyurl.com/ipdchoexternalvacancy ላይ ነው የሚከናወነው።

ለሥራ መደቡ የሚያስፈልጉ የትምህርት ፤ሥራ ልምድ እና ሌሎች  ማስረጃዎች ወደ ፒዲኤፍ/pdf/ በመቀየር በአንድ ፋይል መያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ማስታወቂያ ትላንት ነው የወጣው ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው።

አመልካቾች ከስራ መደቡ ጋር #ቀጥተኛ_የሆነ የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የተባለ ሲሆን ከግል ድርጅቶች የሚቀርብ ስራ ልምድ ግብር መከፈሉ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት።

ተጨማሪ መረጃ ደግሞ በስልክ ቁጥር 0118 72 24 20 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

መልካም ዕድል !

https://t.me/ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

21 Nov, 09:50


#ጥቆማ

አንድ የስራ ማስታወቂያ እንጠቁማችሁ። ዕድላችሁንም ሞክሩ።

ማስታወቂያውን ያወጣው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ነው።

የስራ መደቦቹ ምን ምን ናቸው ?

1. ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ባለሙያ

° ደረጃ ፡- 14
° ደመወዝ ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ቢዝነስ አስተዳደር፣ኢኮኖሚክስ እና በተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ / ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት


2. ከፍተኛ የማርኬቲንግ ባለሙያ

° ደረጃ ፡- 14
° ደመወዝ ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት ፡- በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ኢኮኖሚክስ እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡- 3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-አይጠይቅም
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

3. ከፍተኛ የብራንዲንግ ባለሙያ

° ደረጃ፡- 14
° ደመወዝ፡- 38,557
° ብዛት ፡- 1
° ተፈላጊ የትምህርት አይነት፡- በማርኬቲንግ ፣ ቢዝነስ አስተዳደር እና ተያያዥ የትምህርት መስኮች
° የትምህርት ደረጃ፡- የመጀመሪያ ዲግሪ/ ሁለተኛ ዲግሪ
° የስራ ልምድ ፡-3/2 ዓመት
° ተጨማሪ መስፈርት ፡-በግራፊክስ ፣ በዲዛይን እና ተዛማች ሰርተፊኬሽን ያለው/ያላት
° የቅጥር ሁኔታ ፡- በቋሚነት
° የስራ ቦታ፡-ዋናው መ/ቤት

ትምህርት ሚኒስቴር

19 Nov, 18:54


የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ፈተና ሊፈተኑ መሆኑ ተሰማ።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘን ፈተና ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም " ብለዋል።

አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

  ምንጭ፡ ሸገር ሬድዮ

@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

13 Sep, 15:07


ለመስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም የተዘዋወረው ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሰባት ማዕከላት ይሰጣል።

ይህ ፈተና የሚሰጠው ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም በተሰጠው የNGAT ፈተና፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደ ፈተና ማዕከል መርጠው ለነበሩ ተፈታኞች መሆኑ ይታወቃል።

ፈተናው የሚሰጥባቸው ሰባት ተቋማት፦

1. በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣
2. በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
3. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
4. በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት፣
5. በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ፣
6. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
7. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፡፡

(የፈተናው ፕሮግራም ከላይ ተያይዟል)


@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 17:30


የ12ኛ ክፍል ውጤትዎን ይመልከቱ!

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦

በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.me/EAESbot

ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማተም እንደምትችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መሔድ ሳያስፈልጋችሁ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ Compliant የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ትችላላችሁ።

አገልግሎቱ በቅሬታችሁ ላይ ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 17:27


የክልሎች መረጃ


1️⃣አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 21%(ከ10ሺ በላይ) ተማሪዎችን አሳልፏል።

2️⃣ሀረሪ 13.3% (337)

3️⃣ኦሮሚያ 3.5%(8520)

ሁሉም ክልሎች ከአምናው የተሻለ ተማሪ አሳልፈዋል።

💥በአጠቃላይ 1663 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

ሀረሪ ውስጥ ሁሉም አሳልፈዋል።💥

አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች ምንም አላሳለፉም።

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 13:27


26.6 % ተማሪዎች ኦንላይ ከተፈተኑት ማለፍ ሲችሉ

4.4% በወረቀት ከተፈተኑት አልፈዋል

@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 11:42


#ውጤት : የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ የፈተናው ውጤት ለሊት 6 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

መግለጫውን ከላይ በቀጥታ ይከታተሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 11:39


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች 5.4% ብቻ ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል ። 🤯

@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 10:27


የ12ተኛ ክፍል ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዓት መግለጫ ይሰጣል። 8:00 ጠብቁን። ትክክለኛው የሚለቀቅበት ሰዓት ይነገራል።

ውጤት የሚለቀቅበት Website እና Telegram ቦት በጊዜው ይነገራል ተብሏል።

ለሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተፈታኞች መልካም እድል🙏

           
@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

09 Sep, 06:31


ውጤት ወደ ማታ ይለቀቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዓት መግለጫ ይሰጣል። ስለ ፈተናው ሁኔታ፣ ምን ያክል ተማሪ 50 እና ከዛ በላይ አመጣ የሚለውን ከሰዓት እንሰማለን ።

ዘንድሮ የተፈታኞች ቁጥር 684,205 ተማሪዎች ነው። ከነዚህ ውስጥ 29,718 ተማሪዎች በ #Online ተፈትኗል።

Remedial ይቀር ይሆን? ስንት ተማሪ ያልፋል ? ካለፈው ሁለቱ አመት የተለየ ያርግልን።

ውጤት ወደ ማታ ላይ ከ 12 ሰዓት ቡሃላ ይለቀቃል።

በሀገሪቱ ያለው ሰው ሁሉ ማለት በሚቻል መልኩ ሙከራ ያደርጋል። ስለዚህ ሳተዩ እስከ ነገ ልቆይባችሁ ይችላል ። Network ይጨናነቃል።


መልካም አዲስ አመት
መልካም ውጤት

🔥ለሁሉም ውጤት ጠባቂዎች Share ይደረግ



@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

31 Aug, 09:27


የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል?

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ የሚጠይቁ በርካታ መልዕክቶች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡

የመልቀቂያ ፈተናው ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል ስንል አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

"የፈተናው እርማት በጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሆነ" የገለፁት ኃላፊው፤ እርማቱ እንደተጠናቀቀ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

"እርማቱ በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየተሠራ መሆኑንና በቅርቡም ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ" ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡


@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

01 Aug, 16:28


በተመሳሳይ መለስተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 8 ኮሌጆች #የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም፦

1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ
2. ዳማት ኮሌጅ ጊዎርጊስ ካምፓስ
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ
5. ቅድስት ሃና ኮሌጅ
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማሪያም ካምፓስ
8. ሀራምቤ ኮሌጅ ሜክሲኮ ካምፓስ

ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍ እና በአካል ሪፖርት ለባለስልጣኑ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡



@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

01 Aug, 16:28


#ETQRA

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በከተማዋ በሚገኙ 59 ኮሌጆች ላይ ያደረገውን ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ተከትሎ 44 ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አሳውቋል፡፡

በዚህም ባለስልጣኑ "ከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ እና የስትራቴጂ ጥሰት" ፈፅመዋል ያላቸውን 18 ኮሌጆች #አግዷል፡፡ እነርሱም፦

1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ
3. ሸገር ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
4. ልቀት ኮሌጅ አራት ኪሎ ካምፓስ
5. ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
6. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ቂሊንጦ ካምፓስ
8. አልፋ ኮሌጅ ላንቻ ካምፓስ
9. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ
10. አረና መልቲ ሚዲያ ኮሌጅ
11. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ
12. ሳትኮም ኮሌጅ
13. ኩዊንስ ኮሌጅ አምስት ኪሎ ካምፓስ
14. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ
15. ኩዊንስ ኮሌጅ መድሀኒዓለም ካምፓስ
16. ሀጌ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ
18. ኩዊንስ ኮሌጅ ዩሀንስ ካምፓስ

የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው ሌሎች 18 ኮሌጆች ደግሞ #የመጨረሻ_የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ በባለስልጣኑ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም፦

1. ግሬት ቡልቡላ ኮሌጅ
2. ቢኤስቲ ኮሌጅ
3. ክቡር ኮሌጅ
4. ፋርማ ኮሌጅ
5. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ
6. ኤግል ኮሌጅ
7. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ
8. ናሽናል ኮሌጅ
9. ሀርቫርድ ኮሌጅ
10. ሰቨን ስታር ኮሌጅ
11. ራዳ ኮሌጅ
12. ሬፍትቫሊ ኮሌጅ ካራሎ ካምፓስ
13. ኬቢ ኮሌጅ
14. ያጨ ኮሌጅ
15. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ
16. ናይል ሳይድ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ አየርጤና ካምፓስ
18. ዊልነስ ኮሌጅ



@ETHIO_MINISTRY_EDUCATION

ትምህርት ሚኒስቴር

10 Jul, 11:57


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀምሯል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተናው በመዲናዋ በወረቀት እና በኦላይን በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች፦

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ፣ 5 ኪሎ፣ 4 ኪሎ እና ኤፍቢኢ ግቢዎች)
 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
 አብሮህት ቤተ-መጻሕፍት
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ

ትምህርት ሚኒስቴር

10 Jul, 06:39


#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

ፈተናው በሁለት ዙር ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና መርሐግብር የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ፈተናዎች ይሰጣሉ፡፡

ዘንድሮ 700,000 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር

05 Jul, 16:55


#NationalExam

" የኦንላይን ፈተናው አልቀረም። የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በበይነ መረብና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።

ሆኖም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የበይነ መረብ ፈተናው እንደቀረ ተደርጎ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ይህ በፍጹም ከእውነት የራቀ ሃሰተኛ መሆኑን አሳውቋል።

ፈተናው በሁለቱም በወረቀት እንዲሁም በኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

ተማሪዎች ይሄን ተገንዝበው ዝግጅታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር " ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራን ነው ለዚህም ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጓል " ብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር

29 Jun, 08:16


#HawassaUniversity

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪ እንዳለፈ ይፋ አደርጓል።

መረጃው ከሀዋሳ የተማሪዎች ህብረት የተገኘ ነው።