UNIVERSITY INFO @university_info2 Channel on Telegram

UNIVERSITY INFO

@university_info2


UNIVERSITY INFO (English)

Welcome to UNIVERSITY INFO, your ultimate destination for all things related to universities around the world! Whether you're a high school student exploring potential colleges or a current university student looking for resources and support, this Telegram channel is the perfect place for you. Who is it? UNIVERSITY INFO is a channel dedicated to providing valuable information about universities, including admissions processes, scholarship opportunities, campus life, and more. It is a one-stop-shop for anyone interested in furthering their education and making informed decisions about their academic future. What is it? UNIVERSITY INFO offers a wide range of resources and updates to help users navigate the complex world of higher education. From tips on writing a standout college essay to guides on choosing the right major, this channel covers all aspects of the university experience. Members can also engage in discussions, ask questions, and connect with like-minded individuals who share their academic goals. Join UNIVERSITY INFO today to stay informed, inspired, and empowered on your educational journey. Whether you're dreaming of studying abroad, pursuing a career in academia, or simply want to expand your knowledge, this channel is here to support you every step of the way. Don't miss out on the latest updates and insights from the world of universities - subscribe to UNIVERSITY INFO now!

UNIVERSITY INFO

07 Dec, 18:43


#Update

" የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " - የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል

" ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ኃይል ወደነበረበት እየተመለሰ ነው " ሲል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው የሲስተሙን ቮልቴጅ በማረጋጋት የተቋረጠውን ኃይል ደረጃ በደረጃ ለመመለስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲሁም በክልል ከተሞች የተቋረጠው ኃይል ወደነበረበት መመለሰ መጀመሩን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ አልተፈታም።

ችግሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈታ ድረስ በትዕግስት ተጠባበቁ ተብሏል።

UNIVERSITY INFO

03 Dec, 10:36


ክለቡ ባወጣው መግለጫ ምልክቱን ያላደረገው " በሃይማኖቱ ምክንያት ነው ፤ ውሳኔውን እናከብራለን " ብሏል።

ክለቡ አክሎም ፤ የግብረሰዶማውያኑን ምልክት የሚያሳየውን የአምበሎች መለያ በኩራት እንደሚደግፍ ፤ ከግብረሰዶማውያን ማኅበረሰብ ጋር አብሮ እንደሚቆም ፤ እኩልነት እና ተቀባይነት እንዲንሰራፋ እንደሚሰራ ገልጿል።

ከሳም ሞርሲ በስተቀር ሌሎች የፕሪሚዬር ሊጉ አምበሎች የግብረሰዶማውያንን ባንዲራ አጥልቀው ሲጫወቱ ነበር።

#SamMorsy #PremierLeague #Muslim

@university_info2

UNIVERSITY INFO

03 Dec, 10:36


" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም !! "

" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም ! " ያለው የእግር ኳስ ተጫዋች ግብረሰዶማውያን ለመደገፍ ሲባል ክንድ ላይ የሚጠለቀውን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፍልሚያ አፍቃሪያን እንዳሉ ይታወቃል።

ከየትኛውም ሀገራት በላይ ደግሞ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱት ፍልሚያዎች እጅግ ብዙ ተመልካች ያላቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከፉክክር ጋር ያጣመሩ ናቸው።

በተለይም የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ በሀገራችን ኢትዮጵያ ሳይቀር እጅግ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለውና ብዙ ተመልካች ያለው ነው።

ከህጻን እስከ አዋቂ፣ አዛውንቶች ሳይቀሩ ነው ፍልሚያውን የሚከታተሉት።

ነገር ግን በየዓመቱ ይህ የእግር ኳስ ፍልሚያ የሚደራበት ወር በተለይም ሃይማኖተኛ የሆኑ የእግር ኳስ ተመልካቾችን የሚያስቀይም ነው።

ሰዎቹ " እኩልነትን ለማምጣት " ይበሉት እንጂ በበርካታ ሃይማኖተኛ እግር ኳስ ተመልካቾች እና ተጫዋቾች ዘንድ የሚወገዝ ተግባር ነው የሚፈጽሙት።

የፕሪሚዬር ሊግ ክለቦች ለግበረሰዶማውያን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት አምበሎቻቸው የግብረሰዶማውያኑን መለያ ምልክት ክንዳቸው ላይ እንዲያጠልቁ ያደርጋሉ።

ይህን ዘመቻ የሚያደርጉትም እኤአ ከኅዳር 29 እስከ ታኅሣሥ 5 ነው።

ከቀናት በፊት በነበረ አንድ ጨዋታ ላይ ግን የአንድ ክለብ አምበል " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ምልክቱን ሳያድረግ ቀርቷል።

የተጨዋቹ ስም ሳም ሞርሲ ይባላል ፤ ኢፕስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል ነው።

በእምነቱም የእስላም እምነት ተከታይ ሲሆን የግብፅ ዜጋ ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ቡድኑ ኖቲንግሃም ፎረስት ከተባለው ቡድን ጋር በተጫወተበት ወቅት ክንዱ ላይ ምልክቱን " አላጠልቅም " ብሎ ጨዋታውን ያካሄደው።

UNIVERSITY INFO

11 Sep, 13:55


🏵️ 2017\_ያንተ\_አመት\_ነው 🏵️

👉 ምክንያቱም ቲቪ ላይ ተጥደህ አትውልም
👉 ሶሻል ሚዲያም ትቀንሳለለህ
👉 ንባብ ታበዛለህ
👉 አማራጭ ቢዝነስ ታያለህ
👉 ራስህን ታስተምራለህ
👉 የሚያሳድጉህ ጓደኞች ታፈራለህ
👉 በእምነት ትንቀሳቀሳለህ

= ስኬት ያንተ ይሆናል።

መልካም አዲስ አመት

😴 እንቅልፋም ሳይሆን ንቁ
🗣 የሚያወራ ሳይሆን የሚተገብር
🚫 ሰበበኛ ሳይሆን ተአምረኛ የምንሆንበት አመት ያርገው 💫"

UNIVERSITY INFO

09 Sep, 17:29


ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለቴክኒክ እና ሞያ ትምህርት ቤቶች፡

🗣"አምና ከዩንቨርስቲ ውጪ ያሉ የቴክኒክ እና ሞያ ትምህርት ቤቶች እስከ ስድስት መቶ ሺህ ተማሪዎችን ለመቀበል እንደሚችሉ አሳውቀው ነበር።"

"ነገር ግን የተመዘገበው ተማሪ ከሁለት መቶ አርባ ሺህ አይበልጥም ነበር።"

"ተማሪዎች ዩንቨርስቲ ካልገባን በስተቀር ቴክኒክና ሞያ አንገባም ማለት የለባቸውም። በሌሎች ሃገራት ብዙ ገንዘብ የሚያስገኙ ሞያዎች እነኚህ የቴክኒክና ሞያ ትምህርቶች ናቸው። ሃገራችንም የምትፈልገው እነኚህን ነው በስፋት።"

"ቴክኒክና ሞያ መግባት አልፈልግም ብሎ ጠመንጃ ከጨበጠ የተሳሳተ ምርጫ ወስኗል ማለት ነው።"

@university_info2

UNIVERSITY INFO

09 Sep, 17:26


የክልሎች መረጃ


1️⃣አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 21%(ከ10ሺ በላይ) ተማሪዎችን አሳልፏል።

2️⃣ሀረሪ 13.3% (337)

3️⃣ኦሮሚያ 3.5%(8520)

ሁሉም ክልሎች ከአምናው የተሻለ ተማሪ አሳልፈዋል።

💥በአጠቃላይ 1663 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

ሀረሪ ውስጥ ሁሉም አሳልፈዋል።💥

አዲስ አበባ 4 ትምህርት ቤቶች ምንም አላሳለፉም።



@university_info2

UNIVERSITY INFO

09 Sep, 11:40


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች 5.4% ብቻ ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል ። 🤯

@university_info2

UNIVERSITY INFO

09 Sep, 10:31


Loading ...................

ዝግጁ ናችሁ??

@university_info2

UNIVERSITY INFO

09 Sep, 10:28


ውጤት ወደ ማታ ይለቀቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዓት መግለጫ ይሰጣል። ስለ ፈተናው ሁኔታ፣ ምን ያክል ተማሪ 50 እና ከዛ በላይ አመጣ የሚለውን ከሰዓት እንሰማለን ።

ዘንድሮ የተፈታኞች ቁጥር 684,205 ተማሪዎች ነው። ከነዚህ ውስጥ 29,718 ተማሪዎች በ #Online ተፈትኗል።

Remedial ይቀር ይሆን? ስንት ተማሪ ያልፋል ? ካለፈው ሁለቱ አመት የተለየ ያርግልን።

ውጤት ወደ ማታ ላይ ከ 12 ሰዓት ቡሃላ ይለቀቃል።

በሀገሪቱ ያለው ሰው ሁሉ ማለት በሚቻል መልኩ ሙከራ ያደርጋል። ስለዚህ ሳተዩ እስከ ነገ ልቆይባችሁ ይችላል ። Network ይጨናነቃል።


መልካም አዲስ አመት
መልካም ውጤት

🔥ለሁሉም ውጤት ጠባቂዎች Share ይደረግ



@university_info2

UNIVERSITY INFO

09 Sep, 04:20


ውጤት ዛሬ ይፋ የሆናል።

የ 2016 የ 12ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ ጳጉሜ 4, 2016 ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።

የተማሪዎች ውጤት እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ሲስተም ገብቶ አላለቀም። እና ዛሬም ቀኑን ሙሉ እየሰሩ እንደኘበር መረጃዎች ደርሰውናል።

የፈተናው ውጤት ዛሬ ሰኞ እስከ ምሽት 6:00 ይፋ ልሆን ይችላል። የፈተናው ውጤት ዛሬ ማይለቀቅም ከሆነ መች እና ስንት ሰዓት እንደሚለቀቅ ይፋ ይደረጋል።

ውጤት ሲለቀቅ ኔትወርክ ይጨናነቃል።

@university_info2

UNIVERSITY INFO

08 Sep, 04:33


" የመመዝገቢያ ቀናት ከጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ ነው " - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አንጋፋዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ /ም  ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ለመቀበል መዘጋጀቱን አሳውቆናል።

ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ገልጾልናል።

ከማክሰኞ ጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም እስከ መስከረም 8/2017 ዓ.ም የመመዝገቢያ ቀናት እንደሆኑ ይፋ አድርጓል።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ወደፊት በራሱ በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ ይገለጸል።

www.aau.edu.et


@university_info2

UNIVERSITY INFO

31 Aug, 09:26


የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል?

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ እንደሚደረግ የሚጠይቁ በርካታ መልዕክቶች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡

የመልቀቂያ ፈተናው ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል ስንል አንድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል፡፡

"የፈተናው እርማት በጥንቃቄ እየተከናወነ እንደሆነ" የገለፁት ኃላፊው፤ እርማቱ እንደተጠናቀቀ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

"እርማቱ በጥንቃቄ እና በፍጥነት እየተሠራ መሆኑንና በቅርቡም ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ" ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

@university_info2

UNIVERSITY INFO

06 Aug, 09:01


ክፍት የስራ ማስታወቂያ

Ethio telecom is seeking to hire young, energetic, and customer-focused professionals with zero years of experience for the position of Contact Center Advisor proficient in:
⚡️Amharic
⚡️Afaan Oromoo
⚡️Af-Somali and
⚡️Tigrigna

Qualified individuals who meet the requirements are encouraged to apply through the Ethio telecom website before August 11, 2024.

➡️Click here to apply: bit.ly/3AchAM4
📹Watch how to apply: youtu.be/6h-78lnmft8


@university_info2

UNIVERSITY INFO

01 Aug, 16:37


#DirredawaUniversity

ማስታወቂያ 🙏
ለድህረ - ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

@university_info2

UNIVERSITY INFO

29 Jul, 09:50


#National_GAT

ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተፈታኞችን ለ3ኛው ዙር አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ለማዘጋጀት ቲቶሪያል እየሰጡ ይገኛሉ።

የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመቀጠል "ወጥ የሆነ" ፈተና በትምህርት ሚኒስቴር እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ተማሪዎቹ ለመማር የሚያመለክቱበት የትምህርት ክፍል የተለያዩ በመሆናቸው ወጥ ፈተና መሰጠቱ አግባብነት የለውም የሚሉ ባለሙያዎች አሉ፡፡

ተፈታኞች "የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተናው ከባድ ነው፣ የማለፊያ ነጥቡም በጣም ተሰቅሏል" ሲሉ ይደመጣሉ።

ምሁራን በበኩላቸው "ፈተናውን ማቅለል ይቻላል፣ ይህ ግን መፍትሔ አይደለም" ይላሉ። ይልቁንም "ሌሎች አገራት እንደሚያደርጉት የመግቢያ ነጥቡን ቀነስ ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ" ምሁራኑ ይመክራሉ፡፡


@university_info2

UNIVERSITY INFO

10 Jul, 11:59


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መሰጠት ጀምሯል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተናው በመዲናዋ በወረቀት እና በኦላይን በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው የፈተና ጣቢያዎች፦

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6 ኪሎ፣ 5 ኪሎ፣ 4 ኪሎ እና ኤፍቢኢ ግቢዎች)
 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት
 አብሮህት ቤተ-መጻሕፍት
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ

@university_info2

UNIVERSITY INFO

10 Jul, 06:41


በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ይጀመራል።

በአማራ ክልል ውስጥ የተፈታኞች ቁጥር ከታቀደው በግማሽ እንደሚያንስ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

ቢሮው በዚህ ዓመት ከ200 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀመጡ አቅዶ ነበር።

ነገር ግን አሁን ፈተና ላይ ይቀመጣሉ የተባሉት  96 ሺህ 408 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ቀሪ 106 ሺህ ያክል ተማሪዎች ፈተና አይወስዱም።

አሁን ላይ ፈተናውን የማይወስዱ ተማሪዎች  ተምረው በመስከረም 2017 ዓ/ም በሁለተኛ ዙር ለመፈተን እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

በነገ ዕለት ፈተና የሚጀምሩት ተማሪዎች ለፈተናው መቀመጥ የሚያስችላቸውን ትምህርት የተከታተሉ እንደሆኑ ቢሮው አሳውቋል።

UNIVERSITY INFO

10 Jul, 06:39


#National_Exam

አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡

ፈተናው በሁለት ዙር ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ በዛሬው የመጀመሪያ ቀን ፈተና መርሐግብር የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ፈተናዎች ይሰጣሉ፡፡

ዘንድሮ 700,000 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን እና በወረቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።