ብርሃን ይኹን💡 @lettherebelightofficial Channel on Telegram

ብርሃን ይኹን💡

@lettherebelightofficial


ብርሃን ይኹን
መጽሐፍ ቅዱስን በተለያዩ መንገዶች በማድረስ ሰዎችን ኹሉ ክርስቶስን ወደ መምሰል ሕይወት እንዲጠጉ የሚያግዝ ክርስቲያናዊ አገልግሎት ነው።

Facebook page link

https://www.facebook.com/berhanyihunofficial/

Instagram link

https://www.instagram.com/berhan_yihun/

ብርሃን ይሁን💡 (Amharic)

ብርሃን ይሁን💡 ከማመን ጋር የተኮረበ ተለያዩ መሳሪያዎችን እና አስተማሪ ጥያቄዎችን እንዴት እንደሚቀላቀል ለመስራት የሚያሳዝን ነው። የብርሃን ይሁን💡 ቢሮ በተለያዩ አስተካክሎ መጠበቅ ይቻላል። እንደዚህ ነገር በታላቅ ውጤቱ ብርሃን ይሁን💡 ደግሞ ስለ መንግስት እና በግልጽፍ ግን ገና በተለያዩ ድምፅ እንደሚታይ ነው። በተጨማሪም ብርሃን ይሁን💡 ከይሁዳና ከሌሎች ቦታዎች ጋር ለማረጋገጥና ለመተግበር እንዲሁም ከተነሱ ታሪክና ኮሜዲያል ቦንስንት ይመልከቱ።

ብርሃን ይኹን💡

06 Jan, 05:38


ዮሐንስ 1:14

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።

ብርሃን ይኹን💡

03 Jan, 13:45


ሰው ከመጀመሪያ የወደቀው ከእረኛው ይልቅ ክፉን ሰምቶ ነው ። አሁን ሰው የሚድነው እረኛውን ሲሰማ ነው ።

መዝሙር 1:2፤

ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።

እግዚአብሔርን የሚሰማ ይድናል።

ብርሃን ይኹን💡

02 Jan, 19:19


ኤርምያስ 29:11

ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።

ብርሃን ይኹን💡

02 Jan, 06:00


ገላትያ 6:7

አትሳቱ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና፤

ብርሃን ይኹን💡

30 Dec, 14:35


እግዚአብሔር ትዕግሥተኛ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ “ንጹሕ ነህ፡” አይልም፤ እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።

ናሆም 1:3

ብርሃን ይኹን💡

28 Dec, 08:53


ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤

ዮሐንስ 1:12

ብርሃን ይኹን💡

26 Dec, 22:08


ልጁን ስሙት።

ብርሃን ይኹን💡

25 Dec, 12:31


ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ

ብርሃን ይኹን💡

24 Dec, 18:17


“ከመመሪያህ ማስተዋልን አገኘሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ።”
መዝሙር 119:104

ብርሃን ይኹን💡

23 Dec, 09:04


The ancient temptations Jesus experienced in the wilderness have morphed into toxic cultures of
celebrity. Rich Villodas

ብርሃን ይኹን💡

18 Dec, 06:37


“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የተፈተነ ድንጋይ፣ የመሠረት ድንጋይ፣ ለጽኑ መሠረት የሚሆን የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አስቀምጣለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም።”
ኢሳይያስ 28 : 16

ብርሃን ይኹን💡

17 Dec, 07:42


ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።

መዝሙር 1:1-2

ብርሃን ይኹን💡

15 Dec, 16:13


“ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፤” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።

ብርሃን ይኹን💡

10 Dec, 21:22


1 ሳሙኤል 3:10፤ እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል፡ ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር፡ አለው።

ብርሃን ይኹን💡

06 Dec, 20:47


“ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ “ረቢ” ማለት መምህር ማለት ነው። እርሱም፣ “ኑና እዩ” አላቸው። ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ በዚያም ዕለት አብረውት ዋሉ፤ ከቀኑም ዐሥር ሰዓት ያህል ነበር።”
ዮሐንስ 1 : 38 - 39

ኑና እዩ

ብርሃን ይኹን💡

05 Dec, 06:43


በማግስቱም፣ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ! የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበር ከእኔ ይልቃል’ ያልሁት እርሱ ነው፤ እኔ ራሴ አላወቅሁትም ነበር፤ በውሃ እያጠመቅሁ የመጣሁትም እርሱ በእስራኤል ዘንድ እንዲገለጥ ነው።

ዮሐንስ 1:29-31

ብርሃን ይኹን💡

04 Dec, 09:48


ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በእርሱ ላይ ዐትሟልና።” ዮሐንስ 6:27

ብርሃን ይኹን💡

03 Dec, 19:22


“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤”
ማቴዎስ 11:25

ብርሃን ይኹን💡

01 Dec, 16:55


““ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤ ልቤ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች።”
መዝሙር 27 : 8

ብርሃን ይኹን💡

30 Nov, 04:08


ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

ማርቆስ 8:34

ብርሃን ይኹን💡

29 Nov, 13:47


ፊልጵስዩስ 3:8-9፤ አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤

ብርሃን ይኹን💡

28 Nov, 16:47


ቀላል ነው  መንገዱ
በአቋራጭ ሲኼዱ
እዚያም እዚህም ካሉ እንዲያው ሲፋንኑ
ልፋት አይጠይቅም ለሐሰት ከወገኑ
ልጓም የለበትም ሰፊ ነው መንገዱ
ፍጻሜው ያስፈራል መዘዙ ነው ጉዱ                                                                                   
ከባድ ነው መንገዱ
ታምነው ለሚኼዱ
ወለም ዘለም ሳይሉ መስቀሉን ከያዙ
ዋጋ ያስከፍላል ከእውነት ጋራ ሲጓዙ
መቼ የዋዛ ነው በዝቶበት ጥምዝምዝ
ፍጻሜው ግን ያምራል የለበትም መዘዝ

- ኢየሩሳሌም ነጊያ

ብርሃን ይኹን💡

28 Nov, 05:13


ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።

ዮሐንስ 15:15

ብርሃን ይኹን💡

27 Nov, 13:06


መልካም ወዳጅ ስጠኝ ብለን እንደምንጸልይ እንዲሁ መልካም ወዳጅ አድርገኝ ብሎ መጸለይም ተገቢ ነው። ከመቀበል ይልቅ መስጠትን ከክርስቶስ እንማራለንና።

ብርሃን ይኹን💡

26 Nov, 04:23


“ስለዚህ ርኩሰትንና ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ክፋትን አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን፣ በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።”
ያዕቆብ 1:21

ብርሃን ይኹን💡

25 Nov, 14:14


እግዚአብሔር ከክርስቶስ ውጪ ለኾኑት ያዘጋጀውን ቁጣ እና የፍርድ መጠን ልንረዳው እንደማንችል እንዲሁ በክርስቶስ ላሉት አኹን ያበዛውን የምሕረቱን ታላቅነት በሙላት ልንረዳው አንችልም ።

ብርሃን ይኹን💡

24 Nov, 17:29


እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋራ ትልቅ ትርፍ ነው ።

ብርሃን ይኹን💡

23 Nov, 07:53


የእግዚአብሔር ፈቃድ ርሱም በጎና ደስ የሚያሠኝ ፍጹምም የኾነው ነገር ምን እንደ ኾነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
ሮሜ 12፥2

ብርሃን ይኹን💡

21 Nov, 14:01


የአማኝ ሕይወት ከእግዚአብሔር ባነሰ በየትኛውም ነገር ሊረካና ሊሞላ አይችልም። ሕይወታችን ሙሉ ትርጕም ያገኘው ከእግዚአብሔር ጋራ በልጁ ታርቀን በመንፈስ ቅዱስ ከርሱ በተወለድን ቅጽበት ነው። የገዛ ሕይወቱን አንዴ ሰጥቶናል ከራሱ የሚበልጥ የሚሰጠን ገና ተስፋ የምናደርገው ምንም ነገር የለውም። ይልቅ የሰጠንን ሕይወት ዐውቀን እናጣጥመው ዘንድ ኹሉን እየተውን ለእኛ ረብ የነበረውን ኹሉ እንደ ጕድፍ እየቈጠርን ወደ ርሱ እንፈጥናለን። በርሱ ለመገኘት ርሱን ለማወቅ በክርስቶስ የላቀውን የእግዚአብሔርን የመጥራት ዋጋ ለማግኘት በርሱ እንኖራለን በርሱ እንታወቃለን።

ብርሃን ይኹን💡

21 Nov, 04:54


“ክርስቶስ ስለ እኛ የሞተው በሕይወት ብንኾን ወይም ብንሞት ከርሱ ጋራ እንድንኖር ነው።”
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5÷10

ብርሃን ይኹን💡

20 Nov, 08:04


ክርስቶስን ምሳሌ አድርገን ከመከተላችን በፊት ለድነት የተሰጠን የእግዚአብሔር ስጦታ አድርገን መቀበል አለብን።

ማርቲን ሉተር

ብርሃን ይኹን💡

19 Nov, 16:22


መልካም እረኛ እኔ ነኝ።
መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።

የዮሐንስ ወንጌል 10÷11

ብርሃን ይኹን💡

18 Nov, 18:03


እግዚአብሔር ፍቅር ነው÷
ምክንያቱም እግዚአብሔር ሥሉስ አሐዱ አምላክ ስለኾነ።

ድሪው ሀንተር

ብርሃን ይኹን💡

17 Nov, 19:38


እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ስለዚህ የጠፋችሁ አይደላችሁም።

ሚልክያ 3:6

ብርሃን ይኹን💡

16 Nov, 16:25


“ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞትና አምልኮተ ጣዖት የሆነው መጐምጀት ናቸው።”
ቈላስይስ 3:5

ብርሃን ይኹን💡

16 Nov, 05:42


ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ “በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ።

ሉቃስ 9:23

ብርሃን ይኹን💡

15 Nov, 11:34


በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ እምነታችን እውነት፣ ተስፋችን ሕያው ኾኗል

ዮሐንስ ወንጌል 11፥26 (ይመልከቱ)

ብርሃን ይኹን💡

14 Nov, 14:51


ከእናንተ መከራን የሚቀበል ማንም ቢኖር እርሱ ይጸልይ

ያዕቆብ 5:13

ብርሃን ይኹን💡

13 Nov, 17:22


ኢየሱስ÷ ለጸሎት ትልቅ ቦታ መስጠቱ ለእኛ ትምህርት ነው። ርሱ ዳናውን እንድንከተል ምሳሌ ሰጥቶናል። ለጸሎት የመረጠው ጊዜም የሚደንቅ ነበር። የመረጠው÷ ሕዝቡ ርሱን የማይረብሹበትን የዝምታ ሰዓት ነበር። ኹሉም ሰው ሥራውን የሚያቆምበትና ምንም እንቅስቃሴ የማይደረግበት ጊዜ ነበር። የመረጠው ሰዓት ሰዎች እንቅልፍ ወስዷቸው ችግራቸውን እንዲረሱና እፎይታ ለማግኘት ወደ ርሱን መመልከታቸውን እንዲያቆሙ የሚያደርግበትን ወቅት ነበር። ሌሎች እንቅልፍ ሲወስድባቸው ርሱ ግን በጸሎት ይነቃቃ ነበረ። በተጨማሪም ለጸሎት የመረጠው ቦታም በጥሩ ኹኔታ የተመረጠ ነው። ማንም ሰው ሊያየው የማይችልበት ቦታ ላይ ለብቻው ይኾን ነበር። በመሆኑም ከፈሪሳውያን እልኸኛነትና ግብዝነት ነጻ ኾነ። እነዚያ ጨለማና ጸጥታ የሰፈነባቸው ኮረብቶች ለእግዚአብሔር ልጅ ተስማሚ የኾኑ የጸሎት ቤቶ ኾነው ነበረ። በእኩለ ሌሊት ጸጥታ ውስጥ ሰማይና ምድር÷ እነዚህ ኹለቱ ዓለማት የተጋጠሙበት የዚህን ምሥጢራዊ አካል ጩኸትና ሲቃ ያደምጡ ነበር።

~ ቻርለስ ስፐርጀን

ብርሃን ይኹን💡

13 Nov, 06:53


የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።

2 ጴጥሮስ 3:10

ብርሃን ይኹን💡

12 Nov, 08:50


ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4 : 5

ብርሃን ይኹን💡

11 Nov, 16:18


ምንም ሆነዋል ።

ብርሃን ይኹን💡

11 Nov, 12:06


ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን አብና መንፈስ ቅዱስ አሉት።

ብርሃን ይኹን💡

09 Nov, 10:09


የሰው ልጅ ከራሱ ጽድቅ በቀር የሚያጠፋው የለም
የሰው ልጅ ከክርስቶስ ጽድቅ በቀር የሚያድነው የለም

ስፐርጀን

ብርሃን ይኹን💡

07 Nov, 16:29


ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤

ሮሜ 5:10

ብርሃን ይኹን💡

05 Nov, 18:36


በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።
1 ቆሮንቶስ 15:19

ብርሃን ይኹን💡

05 Nov, 12:29


"Better a brief warfare and eternal rest, than false peace and everlasting torment."

C.H. Spurgeon

ብርሃን ይኹን💡

04 Nov, 07:54


እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።

ማቴዎስ 11:28

ብርሃን ይኹን💡

01 Nov, 17:26


ሐዋርያትም ጌታን፦ “እምነት ጨምርልን፡” አሉት።
ሉቃስ 17:5

ብርሃን ይኹን💡

30 Oct, 11:38


ፍጹም አምላክ፥ ፍጹም ሰው የኾነውን ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን የሚገኘውን የዘላለም ሕይወት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበሉ።

ብርሃን ይኹን💡

27 Oct, 17:18


የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል።

ብርሃን ይኹን💡

25 Oct, 12:50


ኢየሱስን ትኩር ብለን ካልተመለከትን፥ በማንነቱና በሥራው ዕለት ዕለት ልባችንን ካልሞላን እምነታችን ሊያድግ አይችልም።

ዴቪድ ቲ ጎርዶን

ብርሃን ይኹን💡

22 Oct, 20:43


https://youtu.be/OWsPCU8xKYY?si=jYWtbf83D-R09i1b

ብርሃን ይኹን💡

22 Oct, 14:36


ኢየሱስም ሰምቶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው። የማርቆስ ወንጌል 2:17

ብርሃን ይኹን💡

20 Oct, 17:59


“ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው። እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልእኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም።”
ትንቢተ ኢሳይያስ 55:11

ብርሃን ይኹን💡

19 Oct, 15:36


https://www.facebook.com/share/p/EV9UBZDnA7oCEJfC/?mibextid=WC7FNe

ብርሃን ይኹን💡

17 Oct, 20:54


ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ። መዝሙረ ዳዊት 119: 18

ብርሃን ይኹን💡

15 Oct, 16:11


“..አሁን በመስተዋት እንደምናየው ዐይነት በድንግዝግዝ እናያለን፤ በዚያን ጊዜ ግን በግልጥ እናያለን..”
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:12

ብርሃን ይኹን💡

14 Oct, 16:18


ፍቅሬን በአንደበቴ እንደምገልጠው ኹሉ
ሕይወቴ ማንም የማያየው የልቤም ዐሳብ አንተን ያክብርኽ ።

ብርሃን ይኹን💡

11 Oct, 14:51


ሥጋ ኾኖ በመኻላችን ያደረው ዘላለማዊ ቃል÷ ለቀዳማዊነቱ ጥንት፣ ለደኃራዊነቱ ፍጻሜ የሌለው እኔ ነኝ ያለው እግዚአብሔር ነው።

ብርሃን ይኹን💡

10 Oct, 13:02


“Experience is necessary for the understanding of the Word of God,” which must “be believed and felt.” Craig S. keener

ብርሃን ይኹን💡

05 Oct, 08:04


መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።
መዝሙር 51:16

ብርሃን ይኹን💡

04 Oct, 19:53


https://youtu.be/yK0OBC6FRQs?si=dZyjAaxaiRdu61R9

ብርሃን ይኹን💡

01 Oct, 09:41


እንግዲህ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚሆን ነገር በክርስቶስ ኢየሱስ ትምክህት አለኝ።

ሮሜ 15:17

ብርሃን ይኹን💡

24 Sep, 23:09


“ ለኀጢአት ሞተናል፤ ታዲያ እንዴት አድርገን ከእንግዲህ በእርሱ እንኖራለን?”
ሮሜ 6:2

ብርሃን ይኹን💡

20 Sep, 05:22


ቅዱስ (3x) እግዚአብሔር (2x)

በታላቅ ብርሃን በክብር ያለኸህ
ግርማህ አስፈሪ መሳይ የሌለህ
ፍጥረት በፊትህ ይንቀጠቀጣል
ክብርህን አይቶ ማን ሰው ይቆማል

ቅዱስ (3x) እግዚአብሔር (2x)

በፈቃዴ ደስ እያለኝ ጌታ አመልክሃለሁ (4x)

አምላክ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ክበር ጌታ (4x)
ንጉሥ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ንገሥ ጌታ (4x)

ስለአንተ በየዕለቱ መደነቅ ሞልቶኛል
ዛሬ መንፈስ ቅዱስ አምልኪው ይለኛል
ለምን እንደምኖር ምክኒያቱ ገብቶኛል
አንተን ለማምለክ ነው እኔም ተስማምቶኛል

በመፍራት በመንቀጥቀጥ በፊትህ እቀርባለሁ
ክብር ለሚገባህ ለአንተ ክብርን እሰጣለሁ
አምላኬ ይገባሃል ክብር
አምላኬ ይገባሃል
አምላኬ ይገባሃል ስግደት
አምላኬ ይገባሃል (2x)

አምላክ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ክበር ጌታ (4x)
ንጉሥ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ንገሥ ጌታ (4x)

አምላክ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ክበር ጌታ (4x)
ንጉሥ ስለሆንክ ስለሚገባህ
ንገሥ ጌታ (4x)

ብርሃን ይኹን💡

14 Sep, 20:17


It is hard for people to hear the truth that Jesus is the only way if we speak with an arrogance that suggests that we are the only way. Thomas R. Schreiner