መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1 @menaharia_fm Channel on Telegram

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

@menaharia_fm


ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1 (Amharic)

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1 የወንጌለች ፕሮግራሚናል ስብሰባችን እና ሁሉንም በዚህ ቻንሌ በአማርኛ ይኖራል። እኛ የሚያስፈልገን ሪፖርት ፈቃድ እና ቼት ያግኙን በጣም በአማርኛ የምልማል ፕሮግራም እንቅስቃሴ ተጠናቋል። ለማስገንባ በሚስተናገዱ ወንጌል ቻንቃሊንሲም መለኮታችንን ማስገንባት በሚፈልጉ አገራት መካከል እናወን። እንደገና በሰላም ያግቡ።

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 16:26


https://youtu.be/Schdgqjywjk?si=LBc5pRU4BVjn11Qd

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 13:35


#ፓርላማ

ምክር ቤቱ ነገ 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

ጥር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በ17ኛ  መደበኛ ስብሰባው የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 13:17


በአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

ጥር 21 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

አውሮፕላኑ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ እየበረረ በነበረተ ወቅት መከስከሱን የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል ገልጸዋል።
__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 12:18


የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የመሬት መንቀጥቀጥን (ንዝረትን) አስመልክቶ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ይፋ አድርጓል

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት  👉
📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲  
https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 10:29


በኢትዮጵያ ያለው የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተለያዩ ሃገራትን ያሳተፈ ሊሆን ይገባል ተባለ

ጥር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ሃገር ከውስን ሃገራት ጋር ብቻ ሁሉን አቅፍ የሆነ ግንኙነት ላይ ትኩረት ማደርግ  ስጋት የሚፈጥር በመሆኑ በተለይም በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የሚደርጉ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ይተለያዩ ሃገራትን የማሳተፍ አቅጣጫ መጠቀም እንደሚገባ ምሁራን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል።

ሃገርን ለተሻለ ምርታማነት እና ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር በኢኮኖሚ ዘርፍ የምንከትላቸው ከውጪ የቀጥታ ኢንቨስትመንት ፖሊሲዎች በውስን ሃገራት ላይ መወሰኑ በዲፕሎማሲው ምህዳር ላይ ባለው ተለዋዋጭነት ገፈት ቀማሽ ላለመሆን የተለያዩ ሃገራትን ያሳተፈ የኢንቨስትመንት አማራጭ መከተል እንደሚገባ በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የዲፕሎማሲ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ አበራ ሄጲሶ ተናግረዋል፡፡ 

በተለያዩ ሃገራት ኢትዮጵያን ወክለዉ ያሉ አባሳደሮች የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ማመቻቸት እና የማሳሳመን ስራ ላይ  ከፍተኛ ክፍተት እንዳለባቸዉና ይሁን የሚቀረፍ ኢኮኖሚ-ድፕሎማሲ ስራ ሊሰሩ እንደሚገባቸዉ አስገንዝበዋል፡፡
                        
የምጣኔ ሃብት ባለሙያ  ዶክተር ቆስጠንጥንዮስ በርኸተስፋ እንድሚገልጹት በኢትዮጵያ ያለው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ ሃገራት መካከል ከግማሽ በመቶ በላይ በቻይና መሆኑና ቻይና በአፍሪካ ብሎም በአለም አቀፍ ደርጃ ከምታንቀሳቅሰው ኢኮኖሚ  እንዲሁም  በሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ በምትከተለው የኢኮኖሚ- ዲፕሎማሲ አካሄድ እንደሃገር ስጋት የሚፈጥረበት ሁኔታ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል።
                         
በፖለቲካ አለም ብሎም በዲፕሎማሲው ሰፊ ምህዳር ላይ ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት አቅም እና አማራጮች ለመጠቀም  ጠንካራ አቋም ያላቸው ዲፕሎማቶች በሁሉን አቀፍ ግንኙነት ላይ መፈተሽ እና ማጠናከር እንደሚገባ ምሁራኑ አመላክተዋል።

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 09:00


በመዲናዋ የግብር ከፋዮችን መረጃ እስከ ጥር 26 ድረስ የማጣራት ስራ እንደሚሰራ ተገለጸ

ጥር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ ያለውን የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለማዘመን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

አሁንም የግብር አሰባሰብ ስርዓት አለመዘመን እና በጥናት ያለመደገፍ ችግር መኖሩን የሚገልፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ይህንን የማጥራት ስራ ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

በከተማዋ እስካሁን በደረጃ ሀ፣ ለ እና ሐ ወደ 450 ሺህ የሚደርሱ ግብር ከፋዮች ቢኖሩም ነገር ግን በየደረጃዎቹ ምን ያህል ግብር ከፋዮች አሉ የሚለው እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግን የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገልፀዋል፡፡

ይህ በተቋሙ እቅድ፤ አፈፃፀም እና በከተማዋ በሚሰሩ የልማት እቅዶች ላይ ክፍተት እንደሚፈጥር ነው ያስረዱት፡፡
                        
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም በተቋሙ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በሁሉም የግብር ክፍያ ደረጃዎች ስር የሚገኙ የግብር ከፋዮችን መረጃ የማጣራቱ ስራ ጥር 8 በይፋ መጀመሩን እና እስከ ጥር 26 በተደራጀ መልኩ መረጃዎችን አጣርቶ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
                          
የግብር ከፋዮችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ማጣራት መቻሉ የሚገኘውን የግብር ገቢ በተገቢው መንገድ ለልማት ስራ እንዲውል እቅድ ለማውጣት እና የግብር አከፋፈል ሁኔታውን ምን ላይ እንደሚገኝ በማስረጃ ለማስደገፍ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 08:35


ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ቅፅበታዊ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለው ገለጸ

ጥር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሀገሪቱ ቅጽበታዊ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች በክምችት ደረጃ እንዳለው ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡

በተለያዩ  አካባቢዎች ቅፅበታዊ ያልሆኑ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ክልሎቹ በራሳቸው አቅም ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነር ዶክተር ሽፈራው ተ/ማርያም  በፀጥታ ችግር እና በሌሎች ምክንያቶች ክልሎቹ  ከአቅማቸው በላይ ሲሆን በኮሚሽኑ ድጋፉ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ድጋፍ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ አሁን ላይ ቅፅበታዊ አደጋዎች ሲያጋጥሙ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም እንዳለ አመላክተዋል፡፡

ክምችቱ ለታለመለት አላማ እንዲውል ክትትል እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ በተለይም የፀጥታ ችግር ባሉባቸው አካበቢዎች ድጋፉ በፍትሃዊነት እንዲሰራጭ በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች በኩል እንዲደርስ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቅፅበታዊ ሳይሆን በጊዜ ሂደት ለሚፈጠሩ ችግሮች ከመንግስት ባሻገር ህብረተሰቡ በራሱ ድጋፍ የሚያደርግበትን ተሳትፎ ማስቀጠል እንደሚገባ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም ገልፀዋል፡፡

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 08:26


በሃረሪ ክልል እየተሰራጨ ያለው ነዳጅ ካለዉ ፍላጎት አንጻር ተመጣጣኝ አይደለም ተባለ

ጥር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀረሪ ክልል እየተሰራጨ ያለው የነዳጅ መጠን ተመጣጣኝ አለመሆኑን ለመናኸሪያ ሬዲዮ የገለጹት የክልሉ ንግድ ቢሮ የክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ጽጌ ናቸው ።

በክልሉ ያሉ ነዳጅ ማደያዎች ውስን መሆናቸውንና አሁን ላይ በትክክል እየሰሩ ያሉት 15ቱ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡ 

ምንም እንኳን ናፍጣ በበቂ ሁኔታ ወደ ክልሉ እየደረሰው ቢሆንም ነዳጅ ግን ከክልሉ ካለው ፍላጎት አንጻር በጣም አነስተኛ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በዚህ የተነሳም በክልሉ ኮንትሮባንድ እና የህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት እንዲስፋፋና ተጋላጭ እንዲሆን ምክንያት እየሆነ ነው ሲሉ ገልጸው ፤ የክልሉ ንግድ ቢሮ በህገ-ወጥ ነዳጅ ንግዱ ላይ የተሰማሩትን ነጋዴዎች በትኩረት እየተቆጣጠረ ቢሆንም ፤ ማደያዎቹ ነዳጅ ሲጨርሱ በሰዓቱ አለመቅረቡና ባለመድረሱ ምክንያት የቁጥጥሩን ስራ እንዳከበደዉ ተናግረዋል፡፡
             
በጉዳዩ ላይ መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ በቀለች ኩማ እንደገለጹት፤ ማንኛውም ክልል የቤንዚን እጥረት ሊያጋጥመው የሚችል ነው ምክንያቱም የነዳጅ ምርቱ በራሱ ለኮንትሮባንድና ለህገ-ወጥ ንግድ ተጋላጭ በመሆኑ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እንደ ተቋሙ በስርጭትና ግብይት ላይ በምናደርገው ቁጥጥር እንደ ሌላው ክልል ሁሉ በሃረሪ ክልልም በተሰጣቸው ኮታ ልክ እየቀረበ ይገኛል ፤ አሁን ላይ የቤንዚንም ሆነ የናፍጣ ጋዝ እጥረት አለ ብሎ ሪፖርት ያቀረበልን አንድም የክልል ንግድ ቢሮ የለም ሲሉ ገልጸዋል።

የነዳጅ እጥረት ሲኖር ሲስተም ላይ ማየት የሚቻል በመሆኑ አይተን ምላሽ እንሰጣለን ከሃረሪ ክልል ግን እጥረቱን አስመልክቶ የደረሰን መረጃ የለም ብለዋል፡፡
                     
በቅርቡ በሃረሪ ክልል ከ13ሺህ ሊትር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጹ የሚታወቅ ነው ።

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

29 Jan, 07:40


የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተለምዶው "ሿሿ" የተባለውን ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተጠርጣሪዎቹ  ብዛታቸው 4 ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው በቁጥጥር ስር  የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አካባቢ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

የግል ተበዳይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቄራ  እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሄደው የጤና ምርመራ ለማድረግ ዘነበወርቅ አደባባይ ትራንስፖርት እየጠበቁ ነበር።

ግለሰቦቹም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 B-13788 አ.አ በሆነ የቤት መኪና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለውና የግል ተበዳይን ተሽከርካሪው ውስጥ ካስገቧቸው በኃላ ቄራ ድረስ ከምትሄጂ እዚሁ ቅርብ ቦታ የጤና ምርመራ ማድረግ ትችያለሽ፤ እናሳይሻለን በማለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ታቦት ማደሪያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ ቅያስ ውስጥ በማስገባት በእጅ ቦርሳ ውስጥ የነበረ 7900 ጥሬ ገንዘብ ይዘው ለመሰወር ሙከራ ሲያደርጉ በአየር ጤና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ግለሰቦቹ ወንጀሉን ፈፅመው በተሽከርካሪ ለማምለጥ በሚሞክሩበት ሰዓትም  አንድ ግለሰብ ላይ አደጋ ማድረሳቸውን መረጃው ይጠቁማል።

ከተያዙት 4 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አንዷ ሴት ስትሆን አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ፖሊስ መምሪያው ግለሰቦቹ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ወንጀል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፓስተር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደነበርና ደጋጋሚ ወንጀል ፈፃሚዎች መሆናቸውን ጅምር የምርመራ መዝገቡ እንደሚያመላክት ተገልጿል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለውና የተለያዩ ማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን በህግ ለማስቀጣት ህብረተሰቡ የራሱን ጥንቃቄ ከማድረግ ጀምሮ ጥቆማ በመስጠት የተለመደውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።
__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 - Menahria Radio 99.1

28 Jan, 19:44


የአርሰናል ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቷል

ጥር 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አወዛጋቢ የነበረው ይህ የቀይ ካርድ ጉዳይ በጣም የወዳጁ ሊግ መጥፎ ገፆታ የታወቀው ሊጉን የማይመጥኑ ዳኞች የተሰገሰጉበት ሊግ እንደሆነ በድጋሜ የተንፀባረቀበት አጋጣሚ እንደነበር አይዘነጋም።

በሞሌኒው ጨዋታ ዎልቭሶች በሜዳቸው አርሰናልን አስተናግደው 1-0 በሆነ ውጤት በተሸነፉበት ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ወጣቱ ማይልስ ልዊስ ስኬሊ የዎልቭሱ ተከተላካይ ማት ዶኸርቲ ላይ ግልፆ ኳስ የሚቋረጥ እርምጃ ቢወስድም ጨዋታውን በዳኝነት ሲመራ የነበረው ማይክል ኢሊቨር ቢጫ ሳይሆን ቀጥታ ቀይ ካርድ መምዘዛቸው በስፋት ሲያነጋግር ቆይቷል።

ምንም የቪድዮ ምልከታ ዳኝነትን ሳይጠይቁ ኳስ ለማቋረጥ የሄደን ተጫዋች አደገኛ የአጨዋወት መንገድን ተከትሏል በሚል በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲሸኝ የወሰኑበት መንገድ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እስካሁን መነጋገሪያው ርዕሰ ጉዳይ ነው።

የጨዋታው አልቢትር ማይክል ኦሊቨር በዳኝነት ሙያቸው የአርሰናል ተጫዋችን በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ሲያሰናብቱ የትላንቱ ለ8ኛ ጊዜ ያደርገዋል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ተጠባቂ በነበረው የኤቲሀዱ ጨዋታ አርሰናል ሲቲን 1-0 እየመራ በነበረበት ሰአት ሊያንድሮ ትሮሳርድ ፊሸሽካ ከተነፋ በኋላ ካስ መተሀል በሚል ይኸው አልቢትር ማይክል ኦሊቨር ተጫዋቹን በቀይ ካርድ ከሜዳ ማሰናበታቸው አይዘነጋም።

የአርሰናል ደጋፊዎች በፕሪሚየር ሊጉ አጀንዳ ተይዞብናል ብለው እስኪያስቡ ድረስ የደረሰው ይህ ጉዳይ ዋና አልቢትሩ ማይክል ኦሊቨር እና ቤተሰቦቹ ላይ የማስፈራሪያ እያ የግድያ ዛቻዎች እንዲደርሱ አድርጓል።

የእንግሊዝ የዳኞች ማህበር የኦቨርን ውሳኔ እንደሚያከብሩ እና ትክክል ውሳኔ እንደወሰኑ ቢናገሩም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ወዲዪውኑ በመቀበል የተጫዋቱ ቀይ ካርድ መነሳቱን አሳውቀዋል።

በዚህም መሰረት በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረገው ተጠባቂው የኤቲሀዱ ፍጥጫን ጨምሮ ፤ በካራባኦ ካፕ ከኒውካስል ዩናይትድ ጊር የሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ እና በፕሪሚየር ሊጉ ከሌስተር ሲቲ ጋር የሚያከናውኑት ጨዋታ ላይ ተስፈኛው ወጣት ተሰልፎ የሚጫወት ይሆናል።

__

ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን

መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1

ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ

👉011-639-28-52
👉
011-639-37-63

የቀጥታ ስርጭት 
👉 📻 radio 99.1

https://t.me/menaharia_fm

https://x.com/MenahriaFm99_1

ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲   https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-