Nursing covet @nsgcovet Channel on Telegram

Nursing covet

@nsgcovet


Welcome!

You will find here health related events, Scholarship to study aboard, research grants, vacancies and health & health related news.

Aim high,Study hard, live your dream.
Thank you.

Nursing covet (English)

Are you a nursing student or a healthcare professional looking to advance your career? Look no further than Nursing covet! This Telegram channel is dedicated to providing you with valuable information on health-related events, scholarships to study abroad, research grants, job vacancies, and the latest news in the healthcare industry. Whether you are a student aspiring to study abroad or a professional looking for career opportunities, Nursing covet has got you covered. Stay updated on the latest trends in healthcare, discover job openings that match your skills and qualifications, and explore exciting opportunities to further your education with scholarships and research grants. Our aim is to help you reach your full potential in the healthcare field. By staying connected with Nursing covet, you can aim high, study hard, and live your dream. We believe that with the right resources and information at your fingertips, you can achieve your goals and make a positive impact in the world of healthcare. Join us on Nursing covet and take the first step towards a successful and fulfilling career in nursing or healthcare. Thank you for choosing us as your trusted source of information and support. We look forward to helping you achieve greatness in your professional journey. Remember, the future of healthcare is in your hands!

Nursing covet

16 Nov, 08:04


#ጥቆማ

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

Nursing covet

03 Nov, 19:35


Last chance to join Major Airdrop!

https://t.me/major/start?startapp=350274628

Nursing covet

03 Nov, 18:39


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ የተመዛኞች መረጃ ወይም COC ዉጤት online ማድረጊያ ሲስተም ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

ዛሬ ቅዳሜ 23/02/2017 ዓ.ም የክልሉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ የተመዛኞች መረጃ ወይም COC ዉጤት online ማድረጊያ ሲስተም ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።

መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽ ለማድረግ ታልሞ ይህ የተሰራ ሲሰተም ከዚህ በፈት የሠራተኞችና የአዲስ ተቀጣሪዎች የCOC መረጃ ለማጣራት እስከ ኤጀንሲ ድረስ በመምጣት ሲያባክኑ የነበረውን የጊዜና ውጪ ብክነት የሚያስቀር ነው።

ተመዛኞች ወይም ተቋማት የ COC ዉጤት ለማየትም ሆነ ሠርትፊከት ለማረጋገጥ https://www.southwestcoc.gov.et/ ላይ በመግባት የሠርትፍኬት መለያ ቁጥር በማስገባት ሠርትፍኬቱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ የምችሉ መሆኑን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Nursing covet

27 Oct, 07:28


የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎች ነፃ የስልክ መሥመር ይጠቀሙ!

ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ  በውጭ ሀገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ላይ እንዲሰማሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዲስ ሥርዓት ዘርግቶ እየሠራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪትን በተመለከተ ያለዎትን ማንኛውንም ጥያቄ ወደ ☎️9138 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን!

ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 17፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

Nursing covet

25 Oct, 09:01


#ጤናባለሙያዎች

" ቀን ፣ ምሽት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ ነው " - ጤና ባለሙያዎች

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዲዩቲ ክፍያ አልተከፈለንም ያሉ ከ 80 በላይ የጤና ባለሞያዎች ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን ፤ አንጋጫ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች የ6 ወር የዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ) ስላልተከፈላቸው ከማክሰኞ 12/02/17 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ማቆማቸው ተሰምቷል።

በአመት ከ120 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ በቁጥር ከ80 በላይ ይሆናሉ የተባሉት የጤና ባለሞያዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ስራ ያቆሙ ሲሆን የሆስፒታሉ አስተዳደር በበኩሉ እስከ ትላንት ድረስ ወደ ስራቸው ካልተመለሱ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድባቸው በደብዳቤ አሳውቋቸዋል።

ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ወደስራ ገበታው የተመለሰ ባለሞያ አለመኖሩን ሰምተናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው በሆስፒታሉ የሚሰሩ ባለሞያዎች " ከዚህ በፊትም በስራ ላይ ሆናችሁ ጥያቄያችሁን አቅርቡ ተብለን ተስማምተን ጀምረን ተታለናል ሳይከፈለን የመጀመር ፍላጎት የለንም " ሲሉ ገልጸዋል።

ክፍያው ያልተከፈለው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ወር የ2016 ዓም የመስከረም፣ ጥቅምት፣ ጥር እና የነሀሴ ወር የ2017 ዓ/ም የመስከረም ወር በአጠቃላይ የ6 ወር የዲዩቲ ክፍያ ነው።

" ከዚህ በፊት የ4 ወር ክፍያ ባልተከፈለን ወቅት በወረቀት በዞን እና በክልል ደረጃ ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቀን ነበር ነገር ግን ችግራችን አልተፈታም ከዚህ በላይ በትዕግስት መጠበቅ አልቻልንም ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች እየተዳረግን ነው " ብለዋል።

አክለው " ቀን ፣ምሽት ፣ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓል ወቅት ጭምር እየገባን ሰርተን ክፈሉን ስንል የሚሰጠን ምላሽ ማስፈራሪያ በመሆኑ እና ' እየሰራችሁ ጠይቁ እንጂ ሥራ ማቆም አትችሉም ' በማለት እንዲሁም የሚያስተባብሩትን አካላት ' በህግ እንጠይቃለን ' የሚል ማስፈራሪያ ከወረዳ አስተዳዳሪዎች እየደረሰን ነው " ብለዋል።

ባለሙያዎቹ " አምና ጥር ወር ላይ በተመሳሳይ ስራ አቁመን የነበረ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ጭምር አመልክተው ' እናንተ በስራ ላይ ተገኙ እንጂ እንዲከፈል እንነግራለን ' በማለታቸእ ወደ ስራ ተመልሰን ነበር ፤ ምንም ምላሽ ሳይሰጠን ቆይቶ በኋላ የአንድ ወር እንዲከፈለን ተደርጓል ፤ ከዚያ በኋላ ግን በተለመደው መቆራረጥ ነው የቀጠለው " ሲሉ ገልጸዋል።

ክፍያው እየተቆራረጠ ነው የሚገባው ወደ ኋላ ተመልሶ ያልተከፈለንን ክፍያ የመክፈል ምንም ፍላጎት የለም ነው ያሉት።

" የፊቱን እንከፍላለን ወደ ኋላ ተመልሶ ለመክፈል ግን ዞኑ በጀት የሌለው በመሆኑ በጀት ሲለቀቅልን ነው የምንከፍለው " የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ ዝግ ሆኖ በቆየባቸው ቀናት ሁለት ነብሰ ጡር እናቶች ምጥ ይዟቸው ወደ ሆስፒታል መጥተው የነበረ ሲሆን ባለሞያ በሆስፒታሉ ባለመኖሩ ወደሌላ ሆስፒታል በግል ትራንስፖርት በሚጓዙበት ወቅት የህፃናቱ ህይወት እንዳለፈ አክለዋል።

ሀኪሞች ሥራ በማቆማቸው ታካሚዎችም ከሆስፒታል በር እየተመለሱ መሆኑም ተነግሯል።

ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ በተመሳሳይ የስራ ማቆም አድማ ባደረጉበት ወቅት ሆስፒታሉ የወሰደው እርምጃ ያለምንም የቅጥር ማስታወቂያ 17 ሰዎችን መቅጠሩን የተናገሩት ጤና ባለሙያዎቹ " አሁንም ችግራችንን ከመፍታት ይልቅ ከሌሎች ቦታዎች ባለሞያ አምጥተን እንቀጥራለን በሚል እያስፈራሩ ነው " ብለዋል።

" ' ባለሞያ እንቀጥራለን እንደለቀቃቹ ቁጠሩት መጥታቹ ቁልፍ አስረክቡ ንብረት ላይ ቆልፋቹሃል ' በሚል ከፖሊስ ማዘዣ በማውጣት ማስፈራሪያ እየተደረገ ነው ፤ እኛ ሥራ እንለቃለን እላልንም እንሰራለን ግን ክፈሉን ነው ያልነው ተርበናል፣ ገንዘብ አጥተናል፣ ልጆቻችንን ማስተማር አልቻልንም የወተት እና የቤት ኪራይ መክፈል ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ የባለሞያዎቹን ቅሬታ ይዞ የሆስፒታሉን ሥራ አስኪያጅ አቶ ተሰማ አበራን ትላንት ቢያነጋግርም ስብሰባ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ለጊዜው ምላሽ አልሰጡም።

ምላሻቸውን እንዳገኘን የምናካትት ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Nursing covet

23 Oct, 13:33


🌏በውጪ ሃገር ስራ ስምሪት የህጋዊ ኤጀንሲዎችን ዝርዝር ለምትፈልጉ በሙሉ!

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የውጪ ሃገር ስራ ስምሪት ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ እየተሰማሩ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህ ህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ በሚገኝ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሄዳችሁ የባዩሜትሪክስ መረጃ ሰጥታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ በሞያ ዘርፋችሁ የአጭር ግዜ ሥልጠና በመውሰድ የብቃት ማረጋገጫ (COC) ካገኛችሁ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት እድሉን ለመጠቀም ከዚህ በታች ስማቸው የተዘረዘረውን ህጋዊ ኤጀንሲዎች በማግኘት ፕሮሰሱን መጀመር ትችላላችሁ!

በዚህ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ከፓስፓርት፣ ሜዲካል ምርመራና የሥልጠና ክፍያ ውጪ ምንም አይነት ክፍያ የማይከፈል ነፃ መሆኑን አውቃችሁ ተጨማሪ ክፍያ የሚጠይቋቹ ኤጀንሲዎች ካጋጠሟቹ pfs.mols.gov ላይ ወይም በ9138 ነፃ የሥልክ መስመር ጥቆማ መስጠት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Nursing covet

18 Oct, 00:28


X Empire ተጠናቋል ። ቶክናችሁ ነገ ማታ ሁለት ሰዓት የሚሰጣችሁ ይሆናል ።።

Nursing covet

15 Oct, 23:49


"ወደፊት ለምታስቡት እና ለምትመኙት
አላማ በየቀኑ የምታደርጉት ጥቃቅን
ልማዶች ትልቅ ተጽኖ አላቸው!"

"Unlock the potential of your future through the power of consistent daily actions. Each routine lays a brick in the foundation of your success. Embrace the daily grind!"

Nursing covet

12 Oct, 16:02


ጠቃሚ መረጃዎች

CPD Trusted e-Course Sites
https://cpd.moh.gov.et/cpd/course
https://elearning.moh.gov.et
Ethiopian midwife assosation: https://emwa-elearning.com/
Ethiopian medical assosation: https://www.ethiopianmedicalass.org/ema-e-learning-cpd-portal/
Ethiopian public health assosation: - https://www.etpha.org/epha-cpd/courses.html
The Ethiopian assosation of anesthetiss (EAA);
https://eaacpd.com/course/index.php?categoryid=I
amerf health Africa: https://leap.amref.org/
https:/cpd.moh.gov.et
https://engagement.wcea.education/ena
https://engagement.wcea.education/ema
https://engagement.wcea.education/emwa
https://engagement.wcea.education/eaa

Nursing covet

12 Oct, 09:18


የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያች በሙሉ
____

በMedicine, Nursing, Public Health, Pharmacy, Anesthesia, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Surgical Nursing, ሙያዎች ተመርቃችሁ በመስከረም 8 - 10/2017 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን ብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከጥቅምት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 952/0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል [email protected] ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር(Registration No) እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Nursing covet

12 Oct, 09:09


X empire point መሰብሰብ October 17 ማለትም ከ5 ቀን በኋላ ይጠናቀቃል። 👋

Listing Date: October 24/2024

Nursing covet

12 Oct, 08:06


🚩 End of Chill Phase

Frens, mark the date for the end of the Chill Phase!

October 17, 18:00 UTC

There's only a little time left to level up your Empire.

Be sure to connect your wallet in the Airdrop section if you haven't done so yet.

Enjoy these final days of gameplay! Soon, we'll reminisce together...

P.S. The Claim option will be available the day after the Chill Phase ends.

Nursing covet

11 Oct, 14:59


Chill phase (x EMPIRE season 2) የዛሬ ሳምንት ይጠናቀቃል !

X Empire በአጠቃላይ የዛሬ ሁለት ሳምንት ከ 13 ቀን ቡሃላ ሊስት ይደረጋል !

690,000,000,000 $X + 34.5 ቢሊየን ለህዝብ ይከፋፈላል

Nursing covet

11 Oct, 14:58


ሰበር

X empire October 24 ሊስት ይደረጋል🤗🥳

Nursing covet

09 Oct, 03:54


ደስታ ቢራቢሮ ሲሆን፤ ለመያዝ ብንሞክር የማይጨበጥ....ነገር ግን ፀጥ ብለን ስንቀመጥ ከአጠገባችን ብልጭ የሚል ነው።

🦋ለደስተኝነት አንድ መንገድ ነው ያለው። እሱም ከምኞታችን አቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ መጨነቅን ማቆም ነው።  እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም። በበርሃ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም። የፍላጎት ስሌትህን ወደ ጎን አርገውና፣ ስለ ንጋት ፀሀይዋ መሞቅ ፣ ስለ ቀኑ ብራነት፣ በነፃ ስለምትተነፍሰው ውድ አየር፣ ደክሞህ እንኳ ሰለማይደክማት ልብህ፣ በዙሪያህ ስላሉት ወገኖች፣ ይህንን ማንበብ  እንኳ ስላስቻለህ አይንህ ስታስብ ...
.
.
.
በደንብ ስታጤን ... በእርግጥ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ብዙ እንደሆነ ትረዳለህ ፡፡ ያኔ እድለኝነት ይሰማሀል፡፡ ያኔ እንዳልጎደልክ ይገባሀል .... ያኔ አመሰጋኝ ትሆናለህ....

💎 የራስህ አመለካከት ሲጠራ ደስታህና መልክህ እንደፀሓይ ያበራል። በቁስ ያልተደገፈ ደስታ ውስጥህን ይሞላዋል፡፡ ነገ ራሱ የብዙ ዛሬዎች ድምር ነውና ለደስታህ ቀጠሮ አትያዝለት ...
የደስታህ ጊዜ አሁን ነው።


            https://t.me/Nsgcovet ❤️