ሰሚነሽ ኪዳነምህረት @semineshkidanemihret16 Channel on Telegram

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

@semineshkidanemihret16


"በኪዳነምህረት ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል"

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት (Amharic)

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት በኪዳነምህረት ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል! እሱ ማንኛውም ተጽእኖ ለሁሉንም የኦሮሞ ቋንቋ እና ልማት እንደሚሆን, የባለአደራ ቡድኖችን እና ተዛሪሞችን ሌላው ቤተ-ሰዎችን ስኪን አድርጓል። በአማርኛ ከፍተኛ ቋንቋ በተገኘ ምርጥ አዝናኝ እና ፍላጎት ይማሩ። ይህ ቤተ-ሰዎ ከተለምነው ቋንቋዊ ባቀረበው በተገናኘ የፍላጎት ሂደት እንዳለ ይሆናል።

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

21 Nov, 17:08


የሰሚነሽ ኪዳነምሕረት አስተዳዳሪ
👉 መጋቢ ሰናያት ቀሲስ ሐይለማርያም ማለደ

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

20 Nov, 22:40


✝️ ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ
🌸 ሚ-መኑ
🌸 ካ-ከመ
🌸 ኤል- አምላክ
ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ
🌹መኑ ከመ አምላክ (እንደ
እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት
ነው፡፡💐
👉ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ
ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር
ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት
አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው
መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን
የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ
እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ
ሹሞታል፡፡

በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና
መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ።
ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር
ተዋጋ፥አልቻላቸውምም።
✝️የዮሐንስ ራእይ 12፥7❤️
💐የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

14 Nov, 06:04


+ #አባቶቻችን_እንዲህ_አሉ +

"ለምድር የሕይወት ዘመንህን ሁሉ ብትሠጣት በመጨረሻ የምትሠጥህ መቃብር ብቻ ነው:: ለሰማይ ግን ራስህን ብትሠጥ በመጨረሻ የምትሠጥህ ዙፋንን ነው"
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

"እግዚአብሔር ከኃጢአተኛ ይርቃል ብሎ ማሰብ ፀሐይ ከዓይነ ሥውር [ስላላያት] ትርቀዋለች ብሎ እንደማሰብ ነው"
#ቅዱስ_እንጦንስ

"እግዚአብሔር ለአንተ ሲል ራስህን ዝቅ አደረገ:: አንተ ግን ለራስህ እንኳን ስትል ራስህን ዝቅ ማድረግ እንዴት ያቅትሃል?"
#ቅዱስ_መቃርስ

"ለሰውነትህ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ከሠጠኸው ሰውነትህ የማትፈልገውን ነገር ሁሉ ይሠጥሃል:: ሰውነትህን ሠልጥንበት እንጂ አንተ ለሰውነትህ አትገዛ"
#አቡነ_ካራስ

"ሰይጣን ሊያስመስለው የማይችለው ተግባር ትሕትና ብቻ ነው"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሰዋስው

"ሰሎሞን 'ዝም ለማለት ጊዜ አለው ለመናገርም ጊዜ አለው' አለ:: ዝምታን ያስቀደመው በዝምታችን ወቅት የመናገርን ጥበብ ስለምንማር ነው"
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

"ቁጣ በሕይወት እስካለች ድረስ የብዙ ደስታ አልባ ልጆች እናት ሆና ትቀጥላለች"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሰዋስው

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

11 Nov, 05:09


https://youtube.com/channel/UCMc9DM8FLryno5W8SB_NI3w?si=6Qzvh_T1VG_2pPRk

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

06 Nov, 06:09


🌸 ጥቅምት 27💐
✝️መድሐንያለም ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ
መድኃኔዓለም (በዓለ ስቅለት)

ጥቅምት ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

🌹የአምላካችን የመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥባቆት ከሁላችን ጋር ይሁን

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

02 Nov, 08:42


መፅሐፉን የምታገኙ አንብቡት

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

16 Oct, 18:39


🕯️🕯️ነፍስ ይማር💔💔
👉አባ መፍቀሬ ሰብእ ወመፍቀሬ አምላክ

የደሴ ማኅቶት ፤ የላሊበላው መብራት ፤ የግሸኑ ድምቀት

እንኳን ለሰው ይቅርና ለዕፅዋትም አባት መሆን የቻሉ ዋርካ

የቅጽረ ቤተ ክርስቲያን አበቦችን በፍቅር የሚንከባከቡት እኚህ መናኝ በዘመነ ጽጌ (በአበባ ወራት) ወደሰማያዊው ቤታቸው ተጠርተዋል::

ሳር ቅጠሉ የሚያከብራቸው ሃይማኖታቸውን ባይከተል እንኳን አባትነታቸውን የሚወድላቸው የምናኔ ምሳሌ የብሕትውና ጥግ በረከታቸው ይደርብን:: ለአባ መፍቀሬ ሰብእ በሕይወታቸው ሳሉ የሚገባቸውን ክብር ለሠጣችሁ የደሴ ምእመናን እግዚአብሔር ያጽናችሁ::

አባ ጸሊ በእንቲኣነ

"መፍቀሬ ነግድ፣ ዘሠናይ ምግባሩ ዘአንጽሐ ርእሶ ጻድቅ፣ ወኄር፣ ወየዋህ፣ ወመስተዓግሥ" ቲቶ 1:8

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

15 Oct, 09:20


🌸ጥቅምት 5💐

✝️የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) የዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ ቀን ነው

🌷አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ።
🌷አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው።
🌷የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

🌷አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል!!

🌷የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት ፀንቶ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

09 Oct, 05:52


🌸መስከረም 29🌹
✝️እናታችን ቅድስት አርሴማ ሰማዕትነት የተቀበለችበት ቀን ነው

"ውበት ሐሰት ነው፤ ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች" ምሳሌ 30፥31

"ቅድስት አርሴማ"እግዚአብሔርን የምትፈራ በቅዱሳን ሰማዕታት ማህበርና በገነት በሮች የሕይወት ፍሬ ያፈራች ሰማዕት ናት
"በነቢይ ስም ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል በጻድቅ ስም ጻድቅን የሚቀበል የጻዲቁን ዋጋ ያገኛል፤ በስሜና በደቀመዝሙሬ ስም ከታናናሾች ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኅ ያጠጣ እውነት እላችኃለሁ በሰማያት ዋጋውን አያጣም" ብሏልና። (ማቴ 10፥40-42)። የእናታችን ቅድስት አርሴማ በረከቷ ይደርብን
👉እንኳን ለሰማዕቷ ለቅድስት አርሴማ አመታዊ ክብረ በአል አደረሰን አደረሳችሁ 💐💐
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏💐🌹💐🌹

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

06 Oct, 20:00


👉መሬት መንቀጥቀጡን ሳይሆን መሬቱን ያንቀጠቀጠውን እንፍራ!!!
#አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ እንደበደላችን ሳይሆን እነደቸርነትህ ይቅር በለን
#አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ እንደበደላችን ሳይሆን እነደቸርነትህ ይቅር በለን
#አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ እንደበደላችን ሳይሆን እነደቸርነትህ ይቅር በለን

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

06 Oct, 13:51


🌸መስከረም 26💐

✝️ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የተሰነፀበት ቀን

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከም መስከረም ሃያ ስድስት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ወደ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ልኮት መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ስለ መወለዱ አበሠረው

ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር ። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና ።

ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው ።

👉የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሀንስ ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏

ሰሚነሽ ኪዳነምህረት

05 Oct, 04:31


💔ተውን በቃን🙏

✝️ይህችን ቅደስት ቤተ ክርስቲያን ካሰባችሁላት ተዋት
#ለልጆቻችሁም ካሰባችሁ ተውን!
👉ይህ ሕዝብ በጦርነት ዜና፣ በኑሮ ውድነት በሌላም ብዙ ጭንቀት አለበት። እንደአባትነታችሁ ሰላምን ባትሰጡት እንኳ ሌላ ወከባ አትጨምሩበት።
👉እንደፖለቲከኛ የያዛችሁት ሽኩቻ ሰልችቶናል።
👉ተናግራችሁና ሠርታችሁ አርአያ መሆን ካልቻላችሁ ዝም በማለት አርአያ ሁኑን!
👉ይህ ምእመን ቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ሁሉ ዝም ያላችሁ ከላይ እስከታች ስላላጠፋችሁ አልነበረም።
👉አሳልፈው የሰጡት አባቶች ከመካከል እንደነበሩ ጠፍቶትም አይደለም። ግን ስለማእተቡና ስለቀደሙት አባቶቹ የደም ሰማእትነት ሲል ብዙ እየተደረገ በብዙ ዝም አለ።
👉እናንተ የተቋም መሪዎቻችን እንጂ ሃይማኖታችን አይደላችሁምና መሠረቱን ክርስቶስን አስቦ ታገሰ!
👉እናንተ ግን ተጸፅታችሁ ወደ አንድ መጥታችሁ ከውጫዊ ጥቃት ልትጠብቁት ይቅርና እያደረ አዲስ የውስጥ ፈተና ትጠራላችሁ።
👉ሙስናው፣ መልካም አስተዳደር ችግርና ውጫዊ ፈተናችን ብዙ ነው አይካድም።
👉የእናንተ የአደባባይ ንተርክ ግን እውነት ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ አስባችሁ ነው? ወይስ ለክብራችሁ? ወይስ ስልጣናችሁን ለማጽናት?
👉ራሳችሁን በጾም በጸሎት የወሰናችሁ ብፁዓን አባቶችስ እስከመቼ ጥግ ይዛችሁ ታያላችሁ? ጸሎት ከሁሉም የበለጠ ኃይል እንደሆነ ብናምንም ተስፋ እንዳንቆርጥ ተግሳጻችሁን እንመኛለን!
👉👉እናም ጽሑፉ የሚመለከታችሁ ብፁዓን አባቶች የአደባባይ መዘላለፉን ትታችሁ በውስጥ ተሟገቱ። የውጭ ፈተናችን ይበቃናል። እንደተከታታይ ድራማ እናንተን መከታተል ደክሞናል።
👉👉እንዳው በልጅነት የምጠይቃችሁ ድፍረት አይሁንብኝና ከቻላችሁ ወደ ገዳም ገብታችሁ አረፍ በሉ። የጥሞና ጊዜ ጥሩ ነው ብላችሁ አስተምራችሁን የለ?
እስኪ እኛም ካለእናንተ እንየው
#መስከረም ጌታቸው ፃፈቺው

2,529

subscribers

737

photos

8

videos