ማስታወሻ🍀🍀🍀
ልጆቼን ስታድጉ ምን መሆን ነው የምትፈልጉት እላቸዋለው
ሴትዋ ልጄ ሳይንቲስት ትላለች ወንዱ ልጄ ደግሞ አንዳንዴ አባት ይለኛል አንዳንዴ ደሞ ፓይለት ይለኛል
አንድ ቀን ግን ይሄ ጥያቄ በጣም ክፍተት እንዳለው ተረዳው
እኛ በልጅነታችን ምን መሆን ነው የምትፈልገው እየተባልን ዶክተር፣ፓይለት፣አስተማሪ፣ወታደር፣ሹፌር አረ ብዙ ስራዎችን ጠርተናል
የሚገርመው ግን እኛ ማለት ስራችንን ማለት ነን እንዴ???
እንዴት እኛነታችንበስራ ብቻ ለመግለፅ ይሞከራል???
ያም ይመስለኛል ብዙዎቻችን ከተማርንበት ትምህርት ውጭ ሞት የሚሆንብን???
እና እኔ ልጆቼን ሳይንቲስት እና ፓይለት ሲሉኝ እሱ የምትሰሩት ስራ ነው እላቸዋለው ምን ዓይነት ሰው ነው መሆን የምትፈልጉት እላቸዋለው።ይሄ መልስ ልቤን እርክት ያረግልኛል
ፍቅር፣ሰላም፣ደስታ፣ሰው አክባሪ፣ፈሪሀ እ/ር ያለው፣ታማኝ፣ራሱን የገዛ ይሉኛል።
ተመስገን እንዲህ አይነት ማንነት ካላቸው ምንም አይነት ፕሮፌሽን ላይ ቢገቡ ስኬታማ እንደሚሆኑ አውቃለው።
ልጆችን ከፕሮፌሽን በላይ ሰውነትን እናስተምራቸው
መልካም ቀን♥