የኮሚኒስትን ፓሊስ በሚቀርፀዉ ኮሚቴ (politeburo) ስብሰባ ላይ በህይወት ያለችን ዶሮ ይዞ ወደ ስብሰባ ይገባል።በተሰብሳቢዎቹ ፊት በመቆም ሙሉ በሙሉ ቆዳዎ እስከሚታይ ድረስና ደም በደም እስክትሆን ድረስ የዶሮዎን ላባ በጨካኔ ይነቃቅለዋል።ዶሮዎም በስቃይ ውስጥ ሆና ብትጮህም፣ስታሊን ከምንም ነገር ሳይቆጥር አንድም ላባ ሳይቀር ባዶ እስክትሆን ድረስ ይነቃቅለዋል።ላባዎንም ነቅሎ ከጨረሰ በኋላ ከኪሱ ጥሬ በማዉጣት ለዶሮዋ ይሰጣታል።ሚስኪኗ ዶሮም በስቃይም ዉስጥ ሆና ስታሊን እየተከተለች፣ እግሩ ስር የበተነላትን ጥሬ መለቃቀም ጀመረች።
ሰታሊንም ወደ ተሰበሰበዉ የፓለቲካ አመራር አየተመለከተ "ይቺ ዶሮ ህዝቡን ነዉ የምትወክለዉ።ህዝቡን ልትደበድቡት፣ልታሰቃዩት፣ሀይሉን ልታሳጡት ይገባል።ይህን ካደረጋችሁ በኋላ ፣ኪሳችሁ ገብታችሁ የሚበላዉን ነገር ትወረዉሩለታላችሁ።ያኔ ይህ ህዝብ በምትሄዱበት ሁሉ ይከተላችኋል፣ያመልካችኋል።መጨቆኑን ረስቶ ለዘላለም ጀግና ያደርጋችኋል።"በማለት ነበር ታዳሚያን የተናገረዉ።
@WENDETUTORIAL