📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ @bestletters Channel on Telegram

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

@bestletters


ድርሰት
ደብዳቤ
ግጥም
ወግ
እይታዎች
ዝብርቅርቅ ሐሳቦች
ፖስት ካርድ ስቶሪዎች
ገጠመኞች
ውሎዎች
በዚህ ቻናል ይቀርባሉ።

ወረቀት እና ብዕር የልብ ጓደኞቼ ናቸው።
(የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ )

"I don't write words; i write sentiments."
-®Sofi


@sofimemo

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ (Amharic)

ሶፊ ትህነግና የልብ ጓደኝን የሚገኝ የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል የሚገኙ ሰዎች ውሎችና ገጠመኞችን እይታዎችና ዝብርቅርቅ ሐሳቦችን ስቶሪዎችን እና ፖስት ካርድ ስቶሪዎችን ማግኘት ይችላሉ። ሶፊ ምንኛውንም ቃል አልነበረም፣ በትክክለኛው ችግር እና መረጃ ለማከናወን ይጠቀሙ። በዚህ ቻናል ተጨማሪ የሆኑ ቀናት ሰዎችን ለማስቀመጥ እና መረጃውን ለማሳደግ በሶፊ ትክክለኛ መገለጫን ይቀረጹ።

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

08 Feb, 17:13


ከ ተ ደ ቀ ነ ው ካሜራ
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

04 Feb, 17:38


ዛሬ ላይ የጎዳህ ሁኔታም ይሁን ሰው ፤ ነገም ላይ መጉዳቱ አይቀርም። የባሕርን ጨዋማነት ለማረጋገጥ ባሕሩን ሙሉ መጠጣት አይጠበቅብህም።


የማወራው ስለባሕር አይደለም።
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

02 Feb, 18:40


Sofi dedicate this to you...😃

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

31 Jan, 18:24


ኮስታራ ናት እንኳን ገና ላልቀረበቺው ቀርቶ ለቀረቧትም ፊቷ አይፈታም።ጭምት ናት።ለሰዎች ደግ እና ቁምነገረኛ መሆኗን ግን ብዙ ሰው ይስማማበታል።እኔ ደግሞ ጥሎብኝ ኮስታራ ሰው እወዳለሁ፤ምንም እንኳን ሳቂታ ብሆንም...ለምንም ነገር ሳቅ ይቀድመኛል...ስናደድ እንኳን እስቃለሁ።
"ያለ ሳቅ ህይወት ምንድነው?" ብዬ የማስብ አይነት ሰው ነኝ።

የእሷ ህይወት?
ሳቅ ፈፅሞ የማይታወቅበት ጨለማ ነው ብዬ ደመደምኩ...የማስፈልጋት መስሎ ተሰማኝ...ለጨለመ ህይወቷ ጭላንጭል ብርሃን ልሆን...ፋኖሴን ይዤ ቀረብኳት፥ፈገግታዬን።
አልገርምም?
ማን ነኝ ብዬ ነው የማስበው?

የመጀመሪያ ሰሞን በቀልድ የተከሸኑትን ረጃጅም አረፍተ ነገሮች...በአጭር መልስ ድባቅ መትታ ጨዋታ ታስጠፋብኝ ነበር።እንኳን ለማሳቅ በወጉ ለማውራትም ቃላት እያጠረኝ መጣ...ይቺ ሴት ፋኖሴን፥ፈገግታዬን እፍ ብላ አጥፍታ እኔንም ያለሳቅ ልታስቀረኝ ነው?

እሷን ሳያት "በፌዘኞች ወንበር አትቀመጥ" የሚለውን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አስታውሰዋለው...በተገናኘንባቸው አጋጣሚዎች ላስቃት ስውተረተር፣ቃላት ጠፍቶብኝ ስደናበር...ርቃኝ ልደርስባት ስንጠራራ...በቀልዶቼ ሳይሆን በሁኔታዬ ፈገግ ማለት ጀመረች...ኋላ ላይ ሁኔታዬ አሳዝኗት ነው መሠል እሷው ታስቀኝ ጀመር...

አልፎ አልፎ እንደ ቅመም ጣል የምታደርጋቸው ቀልዶቿ ሆዴን አስይዘው ያስቁኛል...በሳቄ እሷ ትስቃለች...ሳቋ ደስ ይለኛል...ሳቋን ለማየት አንዳንዴ እንዲሁ እገለፍጣለሁ።

አንድ ቀን ብዙ ግርግር በማይበዛበት እሷ ባሳየቺኝ ካፌ ቁጭ ብለን ስንጨዋወት..."ከሳቅ ያኳረፈሽ ምንድነው?" ብዬ ጠየኳት።መልሱን ለመስማት ከመጓጓቴ የተነሳ መላ አካላቴ ጆሮ የሆነ እየመሰለኝ።

ጥያቄን በጥያቄ መለሠች። " ሰው ስለሳቀ ደስተኛ ነው ማለት ነው? " አለቺኝ በአይኖቿ ትኩር ብላ እየተመለከተቺኝ።
"ይመስለኛል...ሳቅ የደስታ መገለጫ አይደል፤እንባ ደግሞ የሐዘን።" አልኳት።
"ሐሴት ምን እንሆነ ታውቃለህ?" አለቺኝ።
"ደስታ አይደል"አልኳት በጥርጣሬ።
"አዎ ነው ግን ምን አይነት ደስታ?" ዝም አልኳት ግራ መጋባቴን አይታ ቀጠለች።
"ውስጣዊ ደስታ!" አለችና እርካታ የተሞላበት ፈገግታ ተጎናፀፈች...ሐሴት አደረገች?
ማብራሪያዋን ቀጥላለች "...ሐሴት ማለት ከትክክለኝነት የሚመነጭ ደስታ ነው...አደርገዋለሁ ያልከውን ስታደርገው ነኝ ያልከውን ስትሆን...ብዙዎቹን የራቀው ደስታ ይሄ ነው...እኔ ደስ እንዲለኝ...በየማዕበራዊ ገፁ የሚያሥቅ ነገር ሳስስ ውዬ አላውቅም...ውጪያዊ ደስታ ውሥጥን አርክቶ አያውቅም፤ይልቅ ባዶነት እንዲሠማህ ያደርጋል አንዳንዴም...ሰዎች ደስታ ውስጣቸው እንዳለ ዘንግተውት ደስታን ፍለጋ አይሆኑ ሲሆኑ ያሳዝኑኛል።እኔ ምንም እንኳን ባልስቅም ውስጤ ባለው ሰላም ሐሴት አደርጋለሁ። "

አለች ፍፁም መረጋጋት እና ስክነት ከሁናቴዋ እያነበብኹ።

ከተለያየን ፤ ከሄደች በኋላ ራሴን ጠየቅኹ...

እውነት ደስተኛ ነኝ?
እንጃ!

እኔም ብሎ ፋኖስ ለኳሽ፤ብርሃን አብሪ

እፍፍፍፍፍ....ፋኖሴን(ፈገግታዬን) አጠፋዋት!

ደግሞ ለፀሐይ የፋኖስ ብርሃን ምኗ ነው?
ለካ ጨለማ የነበረው የእኔ ህይወት ነው።




ከተቀደደው ማስታወሻ
#reposted
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

26 Jan, 18:44


"War is a language we do not want to speak ."
M. Darwish

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

21 Jan, 18:55


ልረሳሽ እየጣርኹ ነው...

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

20 Jan, 18:51


Damn this text.

Pretty artistic 💙

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

19 Jan, 18:22


I love this picture...💙

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

18 Jan, 19:11


?

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

14 Jan, 17:54


Terrific.

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

09 Jan, 19:38


ባለፈው ከስራ እንደወጣው እቃ ልገዛ ወደ ፒያሳ ጎራ አልኹ...የምፈልገው ቤት ጋር ስደርስ ቆምኹ...ቤቱ የለም ፤ በቤቱ ፋንታ ፍርስራሽ ጠበቀኝ ፤ የአድራሻ ለውጥ ማድረጋቸውን የሚገልፅ ፅሁፍ ተንጠልጥሏል። በራሴ ተበሳጨው "ፒያሳ ፈርሷል" እያሉኝ ለማረጋገጥ ይሁን ለምን እንደመጣው አልውቅም ። ካላየው ስለማላምን ይሆን ? አረፍ የሚባልበት ካፌ እንኳ አላስቀሩም ። ፒያሳ ማረፊያ ቦታ የላትም ፤ ደግሞም ያለረፍት እየተቆፈረች ነው...ልሂድ ቢሉም አይቻልም። መጓጓዣም ሆነ መንገድ የለም ።

...ወደ ቤቴ መሄድ ፈለግኹ...ሰማዩ ጠቁሯል። ዝናቡ መጣው እያለ እየፎከረ ነው። አማራጭ ስላልነበረኝ ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ በእግሬ ተያያዝኹት ። ደክሞኛል...መሄድ ሳይሆን ጥቅልል ብሎ መተኛት ነበር ያማረኝ ።ሄድኹ ፤ ብዙ ስሄድ ተበሳጨው፤ስበሳጭ... ይሄን መንገድ ለመስራት ሃሳብ ያመጣውን ሰው ረገምኹ። ሃሳቡን ተቀብሎ መቆፈር የጀመረውን ሰው ረገምኹ...ሀገሬንም ረገምሁ፣ የተወለድኹበትንም ቀን ረገምኹት።

...አራት ኪሎ ጋር ስደርስ እዛም ታክሲ የለም...ባሶቹ ከመሙላት አልፈው ሰው እያንጠባጠቡ ያልፋሉ...ባስ አይሞከርም። ሜትር ታክሲ በስልኬ ጠርቼ ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ አካባቢ ከወዲያ ወዲህ እያልኹ ጠበቅኹ።የመጣም፤የደወለም የለም። እየፎከረ የነበረው ዝናብ በጥቂት በጥቂቱ ማንጠባጠብ ዠምሯል ። ሰው'ው ይተራመሳል። ከግራ ከቀኝ መንገዱ በዶዘር ይታረሳል። የእግረኛውም የመኪናውም መንገድ አንድ ላይ ነው ። የረባ ጃኬት አለበስኹም...በርዶኛል...ደክሞኛል...ግን አማራጭ ስለሌለኝ በእግሬ መሄድ ዠመርኹ...ካፊያው ቀስ ብሎ ወደ ዶፍ ዝናብ ተለወጠ...መንገድ ዳር የነበሩት ቤቶች፣ካፌዎች፣የንግድ ሱቆች ለኮሪደር ልማት ፈርሷል...ከፒያሳ-መገናኛ እየተቆፈረ ነው...በዶፍ ዝናብ ውስጥ እየተራገምኹ መረማመዴን ተያያዝሁት...የለስኹት ሸራ ጫማ የቻለውን ያህል ውሃ አስገብቷል ።(መብራት ነው የቀረው)...ያልበሰበሰ የሰውነት ክፍል የለኝም።

...ስልኬ ጮኽ በረጠበው እጄ፤ስልኬን ዝናብ እንዳይነካው አጎንብሼ ስሙን አነበብኹት እና ክው ብዬ ደነገጥኹ ! ክው አድርጎ ያስደነገጠኝ የደዋዩ ማንነት ሳይሆን Data እስካሁን አለማጥፋቴን ሳይ ነው። የተደወለው በቴሌግራም ነዉ ። Clare ናት የደወለቺው ።

Clare አሜሪካዊት ናት። አንድ አሜሪካ የሚገኝ ጓደኛዬን አዲስ አበባ ኑሮ እጅግ እንደተወደደ በደወለልኝ ቁጥር ስለምነግረው ፤ ብር መላኩ ሲሰለቸው አንድ ስራ አገኘልኝ። ስራው ማዳመጥ ነው።አሁን የኔ ጆሮ የውጪ ምንዛሬ እንደሚያመጣ ማን ሰው ያምናል?
Clare የ28 አመት ጎልማሳ ናት ፤ ጎልማሳ ያሰኛት እድሜዋ ሳይሆን ነገረ ስራዋ ነው። አረ እንደውም አዛውት ናት። ገና ህይወትን በቅጡ ሳታጣጥመው መኖር የደከማት ናት። በወጣት ጉልበቷ አልሮጠችበትም ፤ ቁጭ ብላ ታማርርበታለች። የትም መሄድ አትፈልግም...ሁሉንም ያየች ይመስል ሁሉም ነገር አስጠልቷታል ። ትገርመኛለች ሰው ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት እንዴት ያማራል ? የምትኖርበት ቅንጡ አፓርታማ፣የምትነዳው መኪና፣የምትሰራው ስራ፣ስኬቷ ሰላምን አላመጣላትም ።የምትፈልገው ነገር ግራ ገብቷት ፤ የምትፈልገውን እየፈለገች ነው።

ጓደኛዬ ሲያስቀጥረኝ ስራው የሚጠይቀው መስፈርት "A good listener" መሆን ነው። ገርሞኝ ነበር እዛ ሀገር የሚያዳምጥ የለም ማለት ነው ? አንድም ደስ ብሎኝ ነበር ። ስራ በዶላር በመቀጠሬ...Clare ታወራለች ያለማቋረጥ...የምትደውልልኝ ድባቴ ውስጥ ስትገባ ነው...ከምታወራኝ አብዛኛው ምሬት ነው። በቤተሰቧ ፣ በጓደኞቿ የደረሰባት በደል (አንዳንዴ እኔ ምናገባኝ ! ልላት አስብና መክፈሏ ትዝ ሲለኝ ዝም እላለሁ። ለካ እርቦኝ ጆሮዬን ሸጨዋለሁ ።) ድባቴ ውስጥ ስትገባ Clare ታወራለች ! እየጠጣች... ! አንዳንዴ በ Video ነው የምታወራኝ ። ቅንጡ ሶፋ ላይ በድብርት ተኮራምታ ስለልጅነቷ ታወራለች...የዛኔ ጆሮዬን ብቻ አይደለም...ፊቴንም ትገዛዋለች፤በምትነግረኝ ነገር ያዘንኹ ለመምሰል እየጣርኹ ...የረገበ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ እሰማታለሁ።
Clare አንድ እለት ቆንጆ ስልክ ላከቺልኝ።ከዛም በቪዲዮ ኮል ደውላ ቤቴን በጥራት ብታየው ጊዜ ልቧ በሐዘን ተነካ። ልታወራኝ የነበረውን ነገር ርግፍ አድርጋ ትታ..."i want you to tell me about yourself...your child hood...." በተሰባበረ ኢንጊሊዘኛ አወራት ዠመር። የዛኔ ይመስለኛል ኢንግሊዘኛዬን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማችው ።የዛኔ ይመስለኛል ያወራችውን ልሰማት እንደማልችል የጠረጠረችው...።

ለClare አላነሳሁላትም ጠርቶ ሲጨርስ ዳታዬን አጠፋኹ። ከአራት ኪሎ፣ግንፍሌ፣ቀበና እንዳለፍኹ ወደቤቴ የሚወስደውን ቅያስ ያዝኹ።ቤቴ ስገባ ።መብራት ጠፍቷል።ውሀም የለም።እራትም አልሰራሁም።እጅግ ተበሳጭቼ።ልብሴን ቀያይሬ ጋደም አልኹና ዳታዬን አበራኹ።Clare ደወለች።

Clare: What's wrong Sofi...i have been calling you the whole day...?

Sofi: Come on Clare anything could happen,i live in Ethiopia...no electricity...no water...no food

ልላት አሰብኹና የሀገሬን ገፅታ እንዳላጎድፍ ብዬ

"I was at work the whole day" አልኋት።በባዶ ሆዴ ምሬቷን እንዳልሰማ እየተመኘው ጆሮዬን አዋስኋት። "ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው።"





የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
#reposted
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

08 Jan, 19:08


...

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

04 Jan, 18:48


Deep

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

03 Jan, 18:48


typing...

በቃሌ መሰረት ከተቀደደው ማስታወሻ ላይ አንድ ታሪክ አጋራችኋለኹ። እየፃፍኹት ነው።


አልረሳኹትም ለማለት ነው 😁
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

30 Dec, 17:54


https://vm.tiktok.com/ZMkSBFnAb/

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

26 Dec, 18:07


Please join the challenge 🙏


And share

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

26 Dec, 18:02


💙 !

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

25 Dec, 18:37


5k Families Thank you


Love you guys 💕

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

19 Dec, 18:21


የሐዘንተኛው ሙዚቀኛ ፎቶ በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ በጣም ስሜታዊ ከሆኑ ጊዜዎች አንዱ ሆኖ ተመድቧል። ይህ ፎቶ የተነሳው ብራዚላዊው ልጅ "ዲኢኮ ፍራዛኦ ቶርካቶ" የተሰኘውን ዜማ በመምህሩ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ሲጫወት ነው። ይኖርበት ከነበረው የድህነት እና የወንጀል አካባቢ የታደገው ተወዳጁ የሙዚቃ ስራውም ነው።

በዚህ ፎቶ ውስጥ ሰብአዊነት ጮክ ብሎ ይናገራል። ፅጌረዳ ስጠኝ ፅጌረዳ እሰጥሃለሁ፤ መሳርያ ስጠኝ በመሳርያ እገድልሃለሁ፤ ፍቅር ስጠኝ በፍቅር ከብሃለሁ። ምነግራችሁ ይህን ነው አንድን ህፃን ልጅ የሙዚቃ መሳሪያ እንዲጫወት አታስተምሩምና በመዳፉ ውስጥ በያዘው ቢላ ቆራርጦ ይገድላችዋል!። ምክንያቱም "ዘመን ማለት እናንተ ናችሁና ክፉ ዘመን ማለት ክፉ ትውልድ!" መሆኑን ተገንዘቡ።  ከማንነት ዘር እርቀን ፍቅርን፣ መልካምነትን እና መተሳሰብን መዝራት አስተምሮሃችን ይሁን። በዚህም በጎ እድልን እጨዱ ስልጣኔንም ገንቡ።

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

09 Dec, 17:54


It puts my heart on fire ❤️‍🔥

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

05 Dec, 18:22


ነገን ላየው እጓጓለኹ...

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

02 Dec, 17:45


Life doesn't deserve the amount of worry we give it . እንዲሉ አበው ጭንቀታችንን አደብ እናሲዘዋለን ።የቀረን ግዜ ብዙ እንዳልሆነ ገብቶናል !

ስንወድ አንሰስትም እራሳችን እንከን አልባ አደርገን አንቆጥርም ስናጠፋ ሸብረክ እንላለን ።

በምንወዳቸው ሰዎች ቀልድ አናውቅም ። የኛ ቀን ዛሬ እንደሆነች ዘውተር ላለመርሳት እንምክራለን ። ስንወድቅ ሃዘን አናበዛም ዘጠነኛ ክፍል ሆነን ሳይቀር የሰማናትን ቀልድ አስታውሰን ፈገግ እንላለን ።

መኖር ጥሩ ነው




Adhanom Mitku 🙌

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

01 Dec, 16:56


Deep

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

30 Nov, 19:16


🙌

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

24 Nov, 18:18


አንቺን መውደድ ማለት አምስት ስድስት ሰባት እርምጃ በህይወት ወደኋላ ተራምዶ ልጅነትን እንደ መኖር ነው...

...ጥፋት አጥፍቶ ወይም ክፉ ነገርን ፈርቶ እናት ቀሚስ ስር እንደመሸሸግ...

...ያለ ሐሳብ ያለ ጭንቀት በእናት ጉያ ፤ በእናት እቅፍ ውስጥ በምቾት እንደማረፍ...

...ያለምንም ቅጥፈት ፤ ያለምንም ተንኮል በንፁህ ልብ መውደድ...በንፁህ አዕምሮ ማፍቀር...

ለእኔ አንቺን መውደድ እንደዛ ነው።


ላንቺስ እኔን መውደድ እንደ ምን ያለ ነው?


ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

22 Nov, 19:27


አንዳንድ እስር ቤት የሆኑ ሰዎች አሉ ፤ አብረናቸው እንደፈለግን መሆን የማንችላቸው። ዙሪያችንን በማይታዩ ህጎች ያሰሩን ። ለንግግራችን ፤ ለድርጊታችን የምንጠነቀቅላቸው ፤ እንዲህ ብንል ይቀየሙን ይሆን እያልን የምንሳቀቅባቸው ። መዝናኛ ቦታ ወስደውን እንኳን ስራ የሚሆኑብን የሰው እስር ቤቶች አሉ።

...አንቺን የምወድሽ ፤ አብሬሽ ስሆን ነፃነት ስለሚሰማኝ ነው ። ሰላሙ ያልደፈረሰ ነፃነት ። የክብርሽን ድንበር የማያልፍ ነፃነት ስላለሽ እወድሻለሁ ። በአንቺነትሽ ውስጥ በነፃነት እንደ ወፍ እበራለኹ።

ሰው ለሚወደው ሰው የሚሰጠው ትልቁ ስጦታ ነፃነቱን ነው ፤ ፈጣሪ እንኳን ለሚወደን ፍጥረቶቹ የሰጠን ያን አይደል ?



ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

20 Nov, 18:09


ዛሬ ሚካኤል ነዉ
አደራ እንዳትቀር
ወይ በ እዉኔ በኩል
አልያም በህልሜ በር
አደራ እንዳትቀር

ዛሬ ሚካኤል ነው...
ከልቤ ደብር ላይ
ትዝታ ይነግሳል
የመናፈቅ ዲያቆን
ድንኳኔን ይዞራል
መውደድህ ታቦቱ
መውደድህ ፅላቱ
በፍቅር ካህን ላይ
ተጭኖ ይከብራል

ና እናንግስ ግድየለም
ዉሏ ባልታወቀ በዚች ድብቅ ዓለም
ነገ እንሙት ዛሬ የሚነግረን የለም
እንሳል ግዴለም
ለወሩ እንዲያደርሰን
ፍቅር ሳይጎድልብን
ህይወት ሳትቀንሰን
አንድ አፍታ ብቅ ብለህ
ተመለስ አንግሰህ

እጠብቅሀለዉ ነጭ ጥለት ለብሼ
ቄጠማ ጎዝጉዤ ከደጁ ደርሼ
ወይ በዉን አለሜ አልየም በህልሜ በር
በሚካኤል ብዬህ አደራ እንዳትቀር፡፡
አደራ እንዳትቀር!!!


Elu 🙌

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

14 Nov, 18:25


ተ ፈ ፀ መ !


Enjoy
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

14 Nov, 18:23


@YtbAudioBot

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

14 Nov, 18:11


@YtbAudioBot

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

14 Nov, 17:15


https://t.me/qok_12

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

27 Oct, 18:22


https://t.me/StMichael121212/s/197

I asked my broski to film 📽️ me with the scene i love the most from የእግር እሳት movie and it turned out...😍


Where is a good acting school ?... Now i want to be an actor 😁
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

22 Oct, 21:09


https://t.me/StMichael121212/s/196

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

20 Oct, 18:20


ኑ ችርስ እንበል....


በቀረችን ተስፋ እንጠጣበት...ተስፋችንን ከፍ አድርገን እናጋጭ፤ከችግራችን የሚያይል ሳቅ እንሳቅ፤በአዲስ ህልም እንስከር፤ውድቀታችንን እንርሳው፥እንደሞላለት ሰው ኑ ሐሴት እናድርግ...

ቺርስ!
የትም ተርመጥምጦ ለቀረው ትልቅ ህልማችን።አማራጭ አጥተን ለቆምንበት ያልተገባ ሥፍራ።

ቺርስ!
ተምረን ተመራምረን ችግራንን ድልድይ ሰርተን እንሻገራለን ብለን እንዳላሰብን፤ድልድዮ እኛው ኾነን ችግር ለሚመላለስብን ለእኛ ችርስ እንበል።

ቺርስ!
"የሰናፍጭ ታክል እምነት ቢኖርህ ተራራውን ተነቅለህ ሂድ ብትለው ይሄዳል..."ተብለን ተራራው~ችግር እና ሰናፍጭ~እምነትን አቀያይረን፤ተራራ ችግር ይዘን ሰናፍጭ እምነት ላጣን ለእኛ ቺርስ።

ኑ በውድቀቶቻችን እንሳለቅ፤እልፍ ተስፋን እንሰልቅ፤አዳዲስ ህልሞችን እናልም...ቺርስ!


ከተቀደደው ማስታወሻ
4/13/14
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

18 Oct, 18:17


4444 ተኛ ሜንበራችን እንኳን ተቀላቀልከን 🙌

መፅሐፍ ተሸላሚ ሆነሃል።

User name የለውም ስሙ፡Markos ይባላል።
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

17 Oct, 17:46


በውሽንፍር ውስጥ ነበር ያየኃት...የሆነ ሰቅጣጭ አየር...እየጣደፈች ስትሄድ ነበር...ያለ ጥላ...እኔ እያነከስኩኝ ነበር...ከደረሰብኝ የመኪና አደጋ ላመል ማገገሜ ነበር...ትዝ ይለኛል ተጨማሪ እረፍት ልጠይቅ ወደ መስሪያ ቤት እየሄድኩ ነበር...የመኪናዎቹን ፍጥነት ያላገገመ እግሬ የሚቋቋም አልመሰለኝም...የዜብራ መንገድ ጫፍ ላይ ቆሜ በመኪናዎቹ እየተበሳጨሁ ነበር ያየኃት....'ምን አይነቶቹ ህሊና ቢሶች ናቸው...ዜብራ ላይ መቆሜን እንዴት አያስቡም' እያልኩ በውስጤ ሳጉተመትም ነበር አጠገቤ የቆመችው....'እነዚህ እኮ ካልገቡባቸው አያቆሙም' ብላ አየችኝ....'መፍጠን ስለማልችል ነው የቆምኩት...'...አልኳት ወደ እግሬ እያየሁ....እጄን ያዘችኝ....ከዛ እርምጃዋን በእኔ ልክ ገታች...'እየተጣደፈች አልነበር አሁን ምን ጎተታት' ስል ልቤን ሞገትኩ....'እንጃ' አለኝ ልቤ....'ውሽንፍር አይደል እንዴት አብራኝ ልትበሰብስ ወደደች....'....ጥያቄ ደገምኩ....'እንጃ'....መለሰ ልቤ....

በመጨረሻም ዜብራ መንገድ ላይ አይተው እንዳላየ ያለፉኝን ሹፌሮች አመሰገንኩ..ያጣደፋቸውን ጉዳይ መረቅኩ...ሌላው ሳይቀር የገጨኝን መኪና ወሮታ መክፈል ቃጣኝ....አንዳንዴም ወለምታ ቆንጆ ነው ለካ.....እንኳን አመመኝ....



Shewit




https://t.me/shewitdorka

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

15 Oct, 19:06


4444-ተኛ member-ራችን መፅሐፍ እንደሚሸለም ስገልፅ በደስታ ነው።


ሌሎቻችሁ እስካሁን ሳትሰለቹ አብራቹኝ ስላላችሁ አመሰግናለሁ ።

Much much love for you guys!
©ሶፊ

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

15 Oct, 18:27


አገባኹ ብለህ ስታወራ በዚህ ዘመን 😁🙌

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

14 Oct, 19:40


በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ይሄን ዘፈን አለማዳመጥ እና አንድ የአዶ ኮፊን ማኪያቶ አለመጠጣት የማይቻል ሆኖብኛል ።


By the way ትርጉሙን አላውቀውም የሚያውቀው ሰው comment ላይ ቢተባበረኝ እኔ ደግሞ ቆንጆ ማኪያቶ እጋብዘዋለኹ 😁

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

13 Oct, 17:25


አፍሪካዊቷ ሞሮኮ ፡ የተለያዩ ታላላቅ የመኪና ፋብሪካዎችን በመገንባትና ፡ የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ ፡ መኪና እንደ በቆሎ በማምረት ላይ ነች ።
........
በዚህም ባለፈው በ2023 ብቻ ከግማሽ ሚሊየን በላይ 535,000 የተለያዩ መኪኖችን አምርታ ወደ ውጭ በመላኳ ፡ በአንድ አመት ብቻ 13.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ አግኝታለች ። ይህን ገንዘብ ለማግኘት ኢትዮጵያ ለአስር አመታት ቡና መላክ ይጠበቅባታል ።
....
ግን ምን ዋጋ አለው ሞሮኮ ፡ ይህን መሰል ትላልቅ ኢንደስትሪዎች እንጂ. .. የኮሪደር ልማት የላትም



~Wasihune Bekele ☕️

📖 የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 📖 ©ሶፊ

12 Oct, 19:19


በሌላ ቀን ደግሞ የባለቤቴን ዲያሪ አነበብኩ...

...አንድ ቦታ ስደርስ ትኩረትን የሚስብ እንዲህ የሚል ጽሁፍን ተመለከተኩ "የትዳር አጋር መስፈርት" ይላል። ዝርዝሩ በዛ ያለ ነው። ባለቤቴ የባለቤቷን ባህሪውን ሁላ አቅዳለች፤ግን ፍቅር መስፈርት አለው? በርግጥ ዘው ተብሎ እጮኛ አይኮንም ዘው ተብሎ ትዳር ውስጥም አይገባም።
ጽሁፉ ፈገግ አስባለኝ።ባለቤቴ ለማግባት ያቀደችው መልአክ ነው እንጂ በሰው ዘንድ እንዲህ ሁሉ ተሟልቶ የተሰጠው ሰው አለ ብዬ አላስብም።

አንዱ ቦታ ይበልጥ አሳቀኝ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውስጥ ሁለት አንድ ላይ የማይሄዱ ናቸው። ቁጥብ ይልና ከእርሱ ዝቅ ብሎ ተጫዋች ደግሞ ይላል።እንዴት ነው አንድ ሰው ቁጥብም ተጫዋችም የሚሆነው ? አንዱን መምረጥ ያቃታት ይመስላል።

...ሳስበው ውዷ ባለቤቴ እኔን ያገባችው እነዚህ ሁሉ መስፈርቶቿን ሰርዛ "የተገኘውን" የሚል አዲስ መስፈርት ጽፋ ነው። ምክንያቱም እኔ ከዘረዘረችው ውስጥ አንዱንም አላሟላም ብል ማጋነን አይሆንም።


ሐሳቧን ያስቀየርኋት
እንዴት ብትወደኝ ነው?


Sponsored by Add'o coffee house


ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ