እንኳን በሰላም ለዛሬዋ ቀን አበቃችሁ!
እስቲ የዛሬዋን ቀን አርፋችሁ ጀምሯት!
ቀንን አርፎ መጀመር ማለት እረፍትና እርካታ ፍለጋ ምንም ነገር ለማድረግ ከመታገል መረጋጋት ማለት ነው፡፡
ውስጣችሁ እርፍ እንዲል ማንም ሰው ሊቀባለችሁ አይገባም፣ ማንንም ሰው ማስደሰትም የለባችሁም፡፡ ስላረፋችሁ ግን ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሚዛነዊ አድርጋችሁ የመያዝ መረጋጋት ታገኛላችሁ፡፡
ውስጣችሁ እርፍ እንዲል የትኛውም ስራ ስኬታማ መሆን የለበትም፡፡ ውስጣችሁን አሳርፋችሁና አረጋግታችሁ የምትሰሩት ስራ ራሱ መነሻው ስኬታማነት መሆኑን አስታውሱ፡፡
ከእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ተነስቼ ከጀመርላችሁ ሌሎቹን እናንተው አስቧቸው፡፡
ምንም ነገር ስታደርጉ፣ የውስጣችሁን እረፍት ነገሩ እስከሚሳካ አታዘግዩት፡፡
መጀመሪያውኑ ፈጣሪ በሰጣችሁ ማንነት፣ ባላችሁ የሕይወት ራእይና አጠገባችሁ ካለምንም ቅድ-ሁኔታ በሚወዷችሁ ሰዎች እርፍ በሉ፡፡
ከዚህ አይነቱ ሁኔታ ስትነሱና ስትጀምሩ ሰዎችም ሆኑ ሁኔታዎች የእናንተን ስሜት እንደፈለጉ አያደርጉትም፡፡
Dreyob