ልጅ ወርቅነህ... ✍ ( lij werkneh ) @lij_werkneh_gitm Channel on Telegram

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

@lij_werkneh_gitm


➣ የቻናሉ አጋፋሪ (ወርቅነህ አስፋው) እና የእውቅ ገጣምያን ስራዎች በፅሁፍ እና በድምፅ ይቀርባሉ።

➣ የመጻህፍት ቅምሻ እና ጥቆማ ይደረጋል።

➣ የኪነ ጥበብ ምሽት ኘሮግራሞች ጥቆማ

➣ ከምስል ጋር የተቀናበሩ ግጥሞች በስፋት ይቀርቡበታል።

➢ ለማንኛውም አስተያየት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን
አስተያየትዎን ያስቀምጡ
👇👇👇👇👇
@Lijwerkneh
@Lijwerkneh
@Lijwerkneh

ልጅ ወርቅነህ... (Amharic)

ልጅ ወርቅነህ ከዚህ በታችና ከቦታዎች ላይ ፊት ከሚገኝበት የᛊቻናሉ አጋፋሪ አንዱ ይበልጣል። በወርቅነህ እና እውቅ ገጣምያን ስራዎች ላይ በፅሁፍና በድምፅ ይቀርባሉ። የመጻህፍት ቅምሻ እና ጥቆማ ለመመገብ ይደረጋል። የኪነ ጥበብ ምሽት ኘሮግራሞች ጥቆማ፣ ከምስል ጋር የተቀናበሩ ግጥሞች ለትክክለኛው እና ለማንኛውም አስተያየት ከታች ይወሳል። በሥልጣን ከእናንተዎ ኦጋሎንጎ ላይ እና ከእናንተ መሆን የመጣል። ይህ አጭር ጨንወት ለማንኛውም ተደርግረህ የተሞክረህ ወርቅነህ አዝናኝ ታሪክ ነው።

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

21 Oct, 16:22


ልትቀብረኝ በመጣህ
እኔም ባገኘሁህ
ለቀብር ለሰልስት በማታ በካርታ
በመክበብ ጨዋታ
በምሽት በወጉ
ድንኳን ስጠብቁ
ደግሞ ተደጋግሞ ለአርባ ሰማንያ
ከእኔ እንዳትጠፋ
ለተስካር ሙት አመት
ለሰባት ለአስራ ሁለት
ምነው በገደለኝ
ናፍቆት ሞት ቢሆነኝ
ሁሌ ሁሌ እንድታባብለኝ
ናፍቆት በገደለኝ
               ረድኤት ተረፈ


ጆይን /😍👇👇/
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

09 Oct, 18:50


ልዩ የኪነ - ጥበብ ምሽት ጥቆማ
👇👇👇👇👇👇👇👇

ዝክረ ጥበባት ፪

‘’ሳቅ ተከሽኖ’’

መቼ 👉 የፊታችን አርብ ጥቅምት 01 ቀን 2017 ዓ.ም 

ከ 11:00  ጀምሮ በግዮን ሆቴል


join/ጆይን😍
   👇👇👇👇
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

23 Aug, 20:34


እሺ በቃ እወድሻለሁ "አላት የሞት ሞቱን።ቃላቱ አልወጣ ብለው ተናንቀውት ነበር፡፡ "እወድሻለሁ ማለት መሸነፍ የሚመስላችሁ ለምንድን ነው?'' አለች ሰብለ። ደስታ የሰማውን አላመነም ''አልሰማሽም እንዴ፤እወድሻለሁ ነው እኮ ያልኩት ''አለ። 'እሱንማ ሰምቼዋለሁ፡፡የጠየቁህ ግን ያንን ለማለት የፈጀብህን ጊዜ እና ሂደት ከግምት ውስጥ በማስገባት "እወድሻለሁ"ብሎ ደፍሮ ፊት ለፊት መናገር ለምን ይከብዳቸዋል ብዬ ነው አለች።''ትልቅ መሸነፍ ነው የሚሆንባችሁ"አለችው

ከሱ መልስ ሳትጠብቅ። "መሸነፍማ ነው አላት፡፡ "ምን?ምን አልክ?"አለች እሷም

በተራዋ የሰማችውን ባለማመን፡፡

"አዎን መሸነፍ ነው ።ፍቅር መሸነፍ ነው፡፡ፍቅር መያዝ ነው፡፡ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነው።ፍቅር ከምክንያት ውጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነው፡፡ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ውጪ መሆን ነው" ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነው፡፡ያስፈራል ፍቅር ፣የማይታከሙት ህመም፣የማይጠገን ቁስል፣የማያባራ እንባና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል።

የሚያስፈራው ያፈቀርሽው ሰው ሳይሆን ፤ማፍቀር ራሱ ነው"ካፈቀርሽ በኋላ"እኔ የምትይው ሁሉ ይጠፋል።ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ፡፡በፈቃደኝነት ከራስሽ የምታስቀድሚውና የምታስበልጪው ሌላ ሰው ይኖራል ማለት ነው፡፡" ፍቅር ያለ ውጊያ መማረክ ነው፣እጅ መስጠት፣ወዶ መግባት ፣ከራስ መነጠል፣መጥፋት ፣በማያውቁት ሰው ዓለም ውስጥ ገብቶ መሰደድ ።አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል ::"

ወንድ ወይንም ሴት ስለሆንን ግን አይደለም ፍቅርን የምንፈራው፡፡ሰው ስለሆንን ነው፡፡ማናችንም ብንሆን የህይወታችንን መንገድ መቆጣጠር ባንችል እንኳን ማቀድና መምራት እንፈልጋለን ።አንቺን ወደድኩሽ ስል ይህን ሁሉ መተው ማለት ነው፡፡አንቺን በመውደዴ ከዚህ ቀደም የኖርኩት፣ ያቀድኩትና እያሰብኩት ሁሉ ተጠራርጎ ገደል ይገባል። ምን እንደሚሆን፣ምን እንደሚመጣ፣ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ምክንያቱም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ነው"

አለማወቅ ደግሞ ያስፈራል።ራሴን እንኳን እየተቆጣጠርኩ ባለሁበት ሁኔታ፣ስለ ህይወቴ አካሄድ የማውቀው ጥቂት ነው፡፡ግን የማውቅ ስለሚመስለኝ ስራዬ፣ዕውቀቴ፣ ጓደኞቼ ወዘተ የምላቸው የኑሮ ማስመስያዎች በሙሉ ትርጉም

በሰላም እኖራለሁ "ፍቅር ግን መምሰልን ያጠፋል፡፡ከፊት ለፊቴ የተቀመጠው ያጣሉ።ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ምን እንደሚያስፈራ ታውቂያለሽ ?አላት፡፡ ምን ? አለችው፡፡ አፏን ከፍታ ስታዳምጠው ስለነበር ጥያቄውን ያነሳችው እሷ ራሷ መሆኗ ሁሉ ጠፍቶባት ነበር::

"ፍቅር መተወን አይችልም

በመሆኑም ከልቡ የወደደና ያፈቀረ ሰው ማፍቀሩን ማወጅ ቢያስፈራው አይደንቅም፡፡በቀላሉ እወድሻለሁ የሚል ሰው መውደዱን ገና ያላወቀ ወይንም አስመሳይ ነው" አላት፡፡

#አለመኖር
#ዶክተር ዳዊት ወንድምአገኝ

@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

24 Jul, 09:29


ምን ተሰማው ቀዬው...?
እናት ምን ተሰማት፣ ምን አለ ሀገሩ
ሰው እንደ እህል ዘር፣ ሲዘራ ከአፈሩ።

/ ልጅ_ወርቅነህ... /

😢🙏😢🙏😢🙏😢

1000511561276 👉 የጎፋ ዞን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ ፈንድ ።

🙏🙏 ማገዝ በቻልነው አቅም እናግዝ 🙏🙏

😢🙏😢🙏😢🙏

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

03 Jul, 20:04


እሳት ወይ አበባ
....................

ይቅር ብቻ አንናገርም፥
እኔና አንቺ አንወያይም፥
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም.....ዝም፡፡
አበባ አንሆን ወይም እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን ባጫረው መአት
እድሜአችንን እንዳማጥናት....
እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ -እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን ፥ እየቃተትን ስናነባ፡፡......
ፈራን፤ አዎን ፍቅር ፈራን፥
የነፍስን አንደበት ዘጋን፥
የእድሜ ጠብታችንን ምጥ፥ የጣር ፅንሳችንን ልሣን፥
ልጅነት የለገሠንን
በመለኮት የቀባንን
በእሳቱ ያጠመቀንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ፥ በሥልጣን ያላበሰንን
ፈራን፥ አዎን እውነት ፈራን
የስሜት እስትንፋስ ነሳን፡፡ ....

       ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
        

ጆይን / share /
😍👇👇😍
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
   

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

12 Jun, 18:03


#ያንቺው_ሰማይ....
""""""""""""""""""""""""
ሰማዩ ሲዳምን...
ለመዝነብ ነሽጦት፣ ደርሶ ሲያስገመግም
ትውስ ትይኝና...
ብዕሬን አንስቼ፣ እፅፋለሁ ግጥም

አየሽ አይደል፣ ትውስታ አለኝ ከክረምቱ
ልቤ ያጉረመርማል፣ ይጨምራል ምቱ

ክረምት እየሸኘሁ፣ የምቀበል እኔ
ከአጠገቤ እርቀሽ፣ ቢቆጠር ዘመኔ

እኔ ግን...
እግዜር እንዳፀናው፣ ዘርግቶ ከበላይ
እኔም በቦታዬ...
ይኸው ፀንቼ አለው፣ የምድር ላይ ሰማይ

ለዛም መሰል....
የበላዩ ሰማይ፣ ድንገት ሆድ ሲብሰው
ዶፍ ዝናብ ዕንባውን፣ ለምድር ሲልከው
ደስታ አይሉት ሀዘን፣ አንዳች ይወረኛል
አጉረምርሞም አልቅሶበት፣ ሲወጣለት ደስ ይለኛል።

እኔ ያንቺው ሰማይ....
ምንም እንኳ በውብ ቃላት፣ ባጉረመርም በግጥሜ
እንደ ሰማይ አይለቀኝም፣ አይወጣልኝ የዕንባ ጥሜ

ብቻ ግን.....እጠብቃለሁ
እንደምትመጪም አውቃለሁ
በሰማይ እኔነቴ ላይ፣ ኮከብነትሽ  ያበራል
መፅናቴ ተስፋው ለምልሞ፣ በወቅቱ ፍሬን ያፈራል

እስከዛው ግን....

አመሌ ነውና....
በዘነበ ቁጥር የሰማዩን ስሜት በቶሎ  እጋራለሁ
ያው እንደነገርኩሽ....
በምድር የፀናሁ፣ ሰማይም አይደለሁ ?

                   / ልጅ_ወርቅነህ /


     

      ጆይን/ share/
      😍👇👇😍
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

20 May, 20:26


" #ንድፍ"

ሀገር ያውቅ የለም ወይ
የፈጣሪን ስሌት
ወንድን የማነፁን
አስቀድሞ ከሴት
የኔ ኃላ  መሆን
ያንተ ፊት መፋጠር
ምኑ ነው የሚያስደንቅ
የታል አዲስ ነገር?
እኔን በዋናነት
ሲሰራኝ አልሞ
አንተን ንድፍ አ´ረገህ
ጫረህ አስቀድሞ ።

#ሜሮን_ጌትነት



ጆይኝ /share/
😍👇👇😍
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

03 May, 18:45


ያለ ሳዶር ያለ ዳናት...
በኃጢአት ናዳ፣ እረኛዬን ክጄ እየቸነከርኩት
ዛሬም በኔ ዘመን....
በበደል መስቀል ላይ፣ ዳግመኛ ሰቀልኩት ።

/ ልጅ_ወርቅነህ../



ጆይን/share
😍👇👇😍
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

21 Apr, 18:32


✞ #ኒቆዲሞስ ✞
"""""""""""""""""""""""
ጨለማን ገርስሶ፣ እንደ ኮከብ የሚያበራ
ከአይሁድ ሰማይ ስር፣ ግርማው የተፈራ
በምድር ላይ፣ ሀብት ዕውቀትን፣ ሁሉን ሰንዶ የያዘ
የእስራኤል ረቡኒ፣ በአብርሆት የተጓዘ

እርሱ ማለት...
የሊቆች ሊቅ ሆኖ ሳለ፣ ዕውቀት አይኑን ያልጋረደው
ከፈጣሪው ከእግሮቹ ስር፣ ቁጭ ብሎ የተማረው

እርሱ ማለት...ኒቆዲሞስ
እርሱ ማለት...የወርቅ አትሮንስ

በብርሀን የተገኘው...
ክብር ዝናው እሳት ሆኖ፣ ሲፈትነው ወርቅነቱን
በጨለማ ተሸሽጎ...
ከንፎ ሄደ ክርስቶስ ጋር፣ ሊመረምር ምስጢራቱን

ገሰገሱ ወደ አምላክ፣ የታደሉት ውብ እግሮቹ
በጨለማ ክርትት አሉ፣ የናፈቁት ወብ አይኖቹ
ኒቆዲሞስ በንፁህ ልብ፣ ጥልቅ ዕውቀትን ስለሻተ
ክርስቶስም ልቡን አይቶ፣ ከእርሱ ጋራ ተቀመጠ

ከውሀና ከመንፈስ፣ ዳግም ስለመወለድ
በጥምቀት ልጅ ሆኖ፣ ከእግዜር ስለመዛመድ
በጥቂት ክርክር፣ በብዙ አውቆ ተረዳ
አለማወቁን አወቀ፣ አምሽቶ ከእውቀት ጓዳ

ኒቆዲሞስ የታደለ....
አንደ ንብ እየታተረ፣ ሁሉን ከጌታው ቀሰመ
ለትውልድ ምስክር ሊሆን...
እንደ ማር የጣፈጠውን፣ ወንጌልን በልቡ አተመ።

ተወዳጀ ከክርስቶስ፣ ሁሉን ናቀ4ና እርሱን መረጠው
እስከ ስቅለቱም ሄዶ ፣ለጌታው ፍቅሩን አሳየው

ያኔማ... በመስቀል...
ክርስቶስ ቤዛችን ሊሆን፣ ሲፈፀም የማዳን ግብሩ
ከዮሐንስም በቀር...
ከክርስቶስ ጋር  የነበሩ፣ በድንገት ፈርተው ሲቀሩ

ኒቆዲሞስ ግን ከዮሴፍ ጋራ ...
ከመስቀል ስጋውን ወስዶ፣ በእንባ ጌታን ገነዘ
አልሸሸም መከራን ፈርቶ...
ወትሮም ሞትን አይፈራም፣ በልቡ ጌታን የያዘ

ታመነለት ተገዛለት፣ ከእውነት ጋር ተካከለ
መምህር ሆኖ ተማሪ፣ ያንተ አይነት ከወዴት አለ?

አልማር ብለን ነው እንጂ....
አወቅን መጠቅን ላልነው፣ ህይወትህ ብዙ ያስተምራል
ህይወትክን ህይወት ላረጉ፣ ለኃጥአን ነፍስን ያስምራል

እኛ ግን በኃጢአት ሞት...
በቁም ሞተናልና፣ እባክህ መጥተህ ገንዘን
ወይ ደግሞ...
በጥበብ መርተህ፣ ለቅፅበት ከሞት ቀስቅሰን።

                  / ልጅ_ወርቅነህ.... /


ጆይን/ share/
😍👇👇😍
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

26 Mar, 19:57


አይደለም ምኞቴ
ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ

ከንፈርሽን ማለብ
ቀሚስሽን መግለብ
ከገላሽ ቆርሼ :ገላየን መቀለብ
ደረትሽን ማለም
ጡትሽን መሳለም
በቁንጅናሽ ጅረት : ገነቴን ማለምለም
አላማየ አይደለም::

ምኞቴን ልንገርሽ?

ካለሺበት ቦታ: ቀልቤን ማሰማራት
ወትሮ ካንቺ ጋራ: ቡና መጠራራት
ሰላም መገባበዝ: ትዝታ መጋራት

የጨለመ ፊቴን : ባይንሽ ጮራ ማድመቅ
በቃላትሽ መስከን: በሳቅሽ መጠመቅ
በጎ መንፈስሽን :ካይንሽ ላይ መሻማት
ርጋታሽን ማጥመድ : ዝምታሽን መስማት።

/ ✍️በእውቀቱ ስዩም /



ጆይን & share
👇👇😍😍👇👇
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

11 Feb, 17:43


#አሽሙረ_ዝናብ
"""""""""""""""""""""""""""""""
አሽሙረኛው ዝናብ....
በጥርሶችሽ ንጣት፣ ቀንቶ ሲያሸሙር
ከደጃፌ ደርሶ...
በሬን ይዘጋዋል፣ በበረዶ ክምር

እኔማ

አልተወው ነገር፣ ደጃፌን ዘግቷል
አልጠርገው ነገር...
የፈገግታሽን በር፣ ጥርስሽን ይመስላል

ነፍሴ ተሸበረ...
ጠላሁኝ በረዶ፣ ወደድኩኝ በረዶ
ልቤ ቀልቡን አጣ...
ብርድና ሙቀቱን፣ በአንድ'ዜ ተላምዶ

እየቀዘቀዘ...
ደግሞ በታቃርኖ፣ ሀሴት እየቸረኝ
በዝናብ ታጅቦ...
ጎጆዬን ወረሰ ፣ ጥርስሽ እያሞቀኝ።

          /  ልጅ ወርቅነህ.. /

  
    ጆይን/join/
   👇👇👇👇
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

04 Feb, 09:26


#ድንግልና እና ምልክቱ.......🙈
አስደናቂው የሰርግ ገጠመኜን እንካችሁ👇👇

የመልስ ሽርጉዳችን እንደቀጠለ ነው። መቼም ወግ ነውና ለእድምተኛው የተዘጋጀውን በግ አርዶ እና ጠብሶ የማብላት ስራ በኛ በሚዜዎቹ ጫንቃ ላይ አርፏል ብቻ ሳይሆን ተከምሯል ማለቱ ሳይቀል አይቀርም። ሁላችንም በየፊናችን መራወጣችንን ተያያዝነው።

ግማሹ ከጉልቻው፤ ግማሹ ደግሞ፤ ከበጉ ጋር ትግል ገጥሟል። በመጨረሻም ግን ትግላችን ፍሬ አፍርቶ በልጅነታችን ያየነውን የሻሞላ ፊልም በበጉ ላይ ተውነን ካበቃን በኋላ.....በጉን ስናርድ እና ስንገፍ ቆማ ስትመለከት የነበረች አንድ የሙሽሪት ጎረቤት ከአጠገባችን ጠጋ በማለት እንዲህ አለችን " ንፁህ ነው?...ማለቴ ድንግል ነው? " አለች ወደ በጉ እየተመለከተች። የጉድ ቀን ይሉሀል ይሄ ነው እንግዲህ! እኔም ግራ በመገባቴ ምክንያት ፣ከመናገር ተቆጥቤ በውስጤ ነገሩን በማሰላሰል ተጠምጃለሁ ።

ቀጥዬም ግን አላስቻለኝምና ዝምታዬ እንዲህ ስል ሰበርኩ " ቆይ የበግ ድንግልና ደሞ ምን ያደርጋል?? እኛ ከበጉ ጋር ግጦሽ አልወረድን የበጉን ድንግልና በምን እናውቃለን? " አልኩኝ ብሶትና ቀልድን በቀላቀለው ንግግሬ..... ከዚያም ንግግሬን በጥሞና ስትሰማ የነበረችው ልጅ የንግግሬን መጨረስ ተከትላ ወዲያውኑ ድመጿን ከፍ አድርጋ ክት ክት ብላ ሳቀች። በሁኔታው የተገረምን ሁላችንም ሚዜዎች ግራ በመጋባት እርስ በእርስ ተያየን።

የኛንም ግራ መጋባት ያስተዋለችው ይህች ሳቂታ ሴት " አይደለም!...አይደለም! " አለች።ያልገባንን ነገር ግልፅ ለማድረግ ሁሉ ነገሯ እየተንሰፈሰፈ። እንዲህ ስትልም ነገሩን ማብራራት ቀጠለች " ይኽውላችሁ ይሄ ባህላዊ ጉዳይ ነው ወጉ እንዳይቀር ላስታውሳችሁ ብዬ ነው። እኔኮ የጠየኩት የበጉን ሳይሆን የሙሽራውን ድንግልና ነው...ሙሽራው ድንግል ከሆነ ያረዳቹትን በግ የኋላ እግሩን በመለየት ምልክት እንዲሆን ለቤተሰቡ እና ለታዳሚው ማሳየት እና የበጉን የኋላ እግሮች ለቤተሰብ ማስረከብ ይኖርባችኋል። አለች! ሰምተን የማናውቀው አስገራሚ ባህል በመሆኑ ሁላችንም በአግራሞት ከሰማናት በኋላ ያለችንን ሁሉ አንድ በአንድ ለማድረግ ወሰንን።

ለዚህም ጉዳይ እኔ በመመረጤ የድንግልና ምልክት የሆነውን የበጉን የኋላ እግር ለታዳሚው በማሳየት እና ለሙሽራዋ እናትም እነሆ ልጃችን ንፁህ ነው በማለት የበጉን የኋላ እግር በክብር አስረክቤ ወደ ተቀረው ስጋ እና ወደ ተቀረው ስራዬ አመራሁ። መቼም ታድያ በፎቶው ላይ የሚታየው ፈገግታዬን ያየ ሰው '' የሙሽራውን ሳይሆን የራስህን ድንግልና የምታስመሰክር እኮ ነው የምትመስለው'' እያለ ሳያማኝ ይቀራል.?!....😁😂😂

አበቃሁ........👋

/ ልጅ_ወርቅነህ... /

@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

10 Dec, 18:58


እየመጡ....
"""""""""""""""""""
ሀገሬ ስምሽን ለጠሩ...
አንቺን ላሞካሹልኝ፣ እያጨበጨብኩ ከርሜ
ድንገት የከዱሽ ጊዜ...
ተስፋሽን ሲያጨላልሙት፣ ስለወጣልኝ እርሜ

ዛሬ ማንም ተነስቶ...
እየመጣሁ ነው ቢለኝ፣ ፈፅሞ እኔ አይደንቀኝም
ለመጣ ለሄደው ሁሉ፣ ሳዳምቅ እኔ አልገኝም

ምክንያቱም...
መጡልን ያልናቸው ሁሉ፣ በአንቺ ሲመጡ ስላየን
ፅልመት ገፈፉ ስንል ፣ ፅልመት ሲያለብሱሽ ስላየን

ቢመጣም ቢሄድም...
ቢመጣም ለራሱ ሲል ነው፣ ቢሄድም ጠግቦ ሲያበቃ
ላንቺማ እግዜሩ ይምጣልሽ፣ እርሱ ነው ያንቺ ጠበቃ

እናም ከእግዜሩ በቀር...
እየመጣው ነው ላለኝ፣ ደጅ ላይ ቆሜ አልጠብቅም
በአፉ የጠራሽ ሁሉ፣ ሲጠቅምሽ አይቼ አላውቅም።

                    / ልጅ ወርቅነህ.../


@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

26 Nov, 20:15


የሳቅሽን አቦል ድምቀት
ለዘመናት ሞቄ ሞቄ
እንድታለቅሽ አልፈልግም
ስለ እምባሽ መች አውቄ
የምትስቂው ሙሉ ብርሃን
የተስፋ ቃል ፍንጣቂ
እምባሽ ግና ጽልመት ወሳጅ
ሞት እና ህይወት አስታራቂ
ብደምቅበት በዓለም ሁሉ
ሳቅሽን በገፍ እየቀዳው
ስታለቅሺ ባይ ለአንዴ
እምባሽ ሊሆን
አይኔን ዳዳው

ለዘመናት ያልተሻረ
ህመም ስቃይ ነበረብኝ
ጠብ አድርጎ ቁስሌን ሻረው
ከሳቅ እምባሽ በለጠብኝ

ለዘላለም ብጸልይም
ከሀዘን ችግር እንዳትገቢ
ግና ለቅሶሽ ይናፍቃል
ያምርብሻል ስታነቢ ።




# ሚኪ

@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm

ልጅ ወርቅነህ... ( lij werkneh )

14 Nov, 20:08


ኤልያስ_ሽታኹን
"ወንበሩ ሰው አለው?"
*    *    *     *     *     *    *
እሷ
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እኔ
"ነበረው"
(የለም የለም ውሸቴን ነው)
እመጣለሁ ካለች
ዘመን ያስቆጠረች፡፡
ደርሻለሁ ብላኝ
መጠበቅ የበላኝ
አይሃለሁ ያለች
ልክ ነሽ ሰው አለች፡፡
(ነበረች)
እሷ
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እኔ
"ነበረው"  እንዳልል
"አለውም" እንዳልል
ቁጭ በይ እንዳልል
ያንገበግበኛል ቃሏን እንደመጣስ
ግራ ገባኝ እኮ ግን ደሞ ብትመጣስ
ግን ደግሞ የለችም
መጣለሁ በላኝ ይኸው አልመጣችም....
ወንበሩ ሰው አለው
እንጃ
ቀርታለች እላለው
እንጃ
መንገድ ሰነከላት
እንጃ
ወይ ሌላ ከጀላት
እንጃ
መስከረሟ ጠባ
እንጃ
እግዜር መሀል ገባ
እንጃ
ብቻ ወንበሩ ሰው...አለው
ብቻ ወንበሩ ሰው...የለው፡፡
መቀመጥ
ያውም ወንበር ይዞ
ትመጣለች ብሎ
ሽንት እንኳ ቀዝቅዞ

መናፈቅ
ሳቅን ሲጠብቁ ስትቀር መነፍረቅ
መጎለት
ለመጣ ሰው ሁሉ ትመጣለች ማለት
መጠበቅ
እንደድሮ ፅሁፍ ላይታዩ መድመቅ
ነብዝዞ
ደብዝዞ
መገኘት
ሰውን ለመቀበል ራስን መሸኘት...
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እንጃ...


ጆይን /join/
👇👇👇👇👇👇👇
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm