Best kerim @bestkerim Channel on Telegram

Best kerim

@bestkerim


اهدنا الصراط المستقيم ،
فلقد تعبنا من الطرق الملتوية

#شمس التبريزي

+251938704306

Best kerim (Arabic)

في قناة 'Best kerim' ستجد الإلهام والإرشاد نحو الصراط المستقيم. يعتبر هذه القناة مكانًا للتفكير والتأمل، حيث يتم نشر اقتباسات وحكم من العديد من المصادر، بما في ذلك #شمس التبريزي. استمتع بالمحتوى الملهم والمفيد وتعرف على طرق تحقيق الهدف النبيل في الحياة. انضم إلينا على هذه الرحلة الروحية وتعلم كيف تسلك الطريق الصحيح نحو النجاح والسعادة. للانضمام، اتصل على الرقم +251938704306 واستعد لتحول إيجابي في حياتك!

Best kerim

14 Feb, 18:53


አንድ ልጨምር

(ከቀደሙት ልጥፎች የቀጠለ ...)

ቀደምት ዐሊሞቻችን ፉቀሐዎቹ፣ የመዝሐብ ሊቃውንቶች ኹሉ ከጌታቸው በሚያገኙት የኢጅቲሀድ (ምርምር) ሥጦታ በተጨማሪም እንደ ከሽፋና ከራማቸውን ኹሉ አፍነው ይዘው፤ ሰው እንዳያቅባቸው ተደብቀው እንደ ተርታ ኾነው ነው የኖሩት። እርግጥ ኪታቦቻቸው የሚለው ዒልም በተርቢያ ይታከማል ፥ ከአላህ የሚመጡ መንፈሳዊ ሽልማቶች እንደ ከራማ የመሰሉ ደግሞ በሸሪዓ ልጓም ይያዛል የሚለውን ነው።

ከርሱ በባሰ መልኩ ደግሞ ከራማቸውን ልክ ሴት ልጅ ውበቷን የምትደብቀውን ያህል ደብቀው ነበር የኖሩት። (ፈተና አለውና) ከፍ ሲልም ከራማ ማለት በሐቅና ሸሪዓ ላይ ጽኑ መኾን ነው አሉ። ዒልማቸውንም ኾነ ይህን ታላቅ የጌታ ስጦታ በዚህ ልክ ጠበቁት ሕዝባቸውን ለማዳን ብቻ ሲሉ ይጠቀሙበት ነበር። ለሆዳቸው ኾነ ለዱንያቸው የጌታቸውን ይህን ጸጋ ሳይጠቀሙበት ብዙዎቹ አመለጡን። ዛሬም በአይኔ ያየኋቸው ከባባድ ሰዎች አሉ። (አላህ ንጽሕናቸውን ይባርክልን)

በተቃራኒው ... ዛሬ ዛሬ ....

የኾነ ቲዩብ ከፍቶ ሺህ ቪዲዮ ከኾነ ሰው ከቃረመ እንደአደገኛ ዐሊም እራሱን ይሰቅላል። ትንሽ የአድናቆትና ጭብጨባ ማአት ሲጎርፍለት እንደአደገኛ ባለከራማ ጉዳይ ካልፈታሁ ይላል። በዚህ አያቆምም ሆዱንም ይሞላበታል፣ ይነግድበታል። የሰው ኢማንና ልብ አድርቆ ሰዎች ትክክለኛ ዓሊሞች ጋር እንዳይገናኙ ሽፍታ ይኾናል። ባለ መዝሐቦቹን፣ ፉቀሀዎቹን፣ ሱፍይ ዐሪፎቹን እንደ ተራ ጓደኞቹ ይወዳደራቸዋል። ልካቸውን ሳይረዳ፣ ከሰንሰለታቸው ሳይቋደስ በአቋራጭ ይነግድባቸዋል።

በእስልምና ስም ከእስልምና ከሚያወጡ ሰዎች አላህ ይጠብቀና!

አሚይንንን

Best kerim

14 Feb, 13:44


የግለሰብ እስልምና (ሸሪዓ) የለም፤ ካለም የሚኖረው የግለሰብ ኢማን (እምነት) ነው። እንደምታውቁት ከአላህ እምነት (ዲን) መንገድ ውጭ ያሉ ብዙ "እምነቶች" ሸሪዓ (የአላህ መመሪያ) ስለሌላቸው እንጂ እንደ መንፈስ ጥሩ የሚባሉ ልምምዶች ፈጥረው ነበር። መመሪያ (ሸሪዓ)(ልጓም)(ፊቂህ) ስለሌላቸው በቀላሉ ኮራፕት ያደርጋሉ። ብዙ ጊዜ እስልምና ውስጥም ብዙ ይፈጠራሉ፤ ግለሰቦች ሲኾኑ ያሻቸውን ሐዋ ተከትለው ሸሪዓ ለመመስረት ይሞክራሉ። እነዚህ ግለሰቦች መዝሀቦቹ የሰሩትን እኛም እንሰራለን በሚል የኢንተለኬት ሎጂክ ተነስተው ይህን ይሞክራሉ። አንዳንዶቹ መዝሀብ ማፍረስም ሐሳብ ነበራቸው፣ አንዳንድ ጀምዓዎች ከመዝሀቦች የመብለጥም ዓላማ ነበራቸው፣ በቅርቡ ሳዑዲ ላይ አምስተኛ መዝሐብ የመስራት ዓላማ የነበረውም አንድ የዋህ "ዑለማ" አይተናል። እነዚህ ሰዎች መዝሐብ እንዴት እንደተደራጀ ያወቁት በንባብ ሐይል ነው። በአዕምሮ ሚዛን ብቻ የምትመሩ ሲኾን፣ የዑለሞችን የረባኒያ ሰንሰለት የማታጤኑ ከሆነ በርካታ ደጃላዊ ሐረካቶች በየፊናው በዑለማ ስም ሊያምታታችሁ ስለሚችል የምትመሩበትን ዓሊም መምረጥ ድርሻችሁ ነው። ወደ መንፈሳዊ ማንነት የማያሳድጓችሁን በጌጣጌጥና ፖለቲካ የሚጠምዷችሁን ቁሳዊ ሰባኪዎች ማወቅና መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው።

አላህ ከመሰል ፈተና ይጠብቀና፣ ያስረዳንም

Best kerim

14 Feb, 11:49


በነገራችን ላይ ቅብ አንሁን። በተለይ 30ዎቹን እያለፍን የምንገኝ፣ በተለይም ኢስላማዊ ትምሕርቶችን የምናስተምር ሰዎች!!

ቅብ ምንድነው? በወጣቶች ቋንቋ "ሳክስ" የምንለው መሰለኝ። አንዳንዱ ተቀባብቶ ይመጣል፤ በተለይ እኔ በማላቀው በቲክቶክ መንደር። ከዚያም እንደከባድ "ሙጅተሒድ" "ተመራማሪ" ይሰራራዋል።

ከሆነ የቲዩብ ሸይኹ ይቃርምና፣ ለተርታውና ለምስኪኑ ምንም የማይመለከተውን ነገር እያወራ ዝናውንና እንጀራውን ይጋግርበታል። እርግጥ በዚህ ዘመን እንደሚቀባቡ ሰዎች ተከታይ ያለውም የለም። ቁርኣንን አንተ አንብበህ የማትረዳ ያህል እኔ ብቻ ስለ ቁርኣን ላውራ ይሉሃል፣ ኢስላምን በፈለጉት የዩቱብ ሸይኽ ለቃቅመው በሚፈልጉት መንገድ ሊያውም በአጫጭሩ ያለ የሌለውን ያቀርቡልሃል። ዳዕዋ ሲያደርጉ ተቀባብተው ነው። ዐዲስ ልብስ ገዝተው ወይም ተከራይተው፣ ጸጉራቸውንና ፊታቸውን ተሰርተው፣ ብራንድ ነገር መጠቀማቸውን እያሳበቁ እየተንበላጠጡ ኢስላምን ከእነርሱ ባላይ ማንም እንዳልተረዳው በሚያሳብቅ የቅብ ሥነልቡና ተሞልተው ይሰክሳሉ!!

ለዘመናት የምናቃቸውን መሠረታዊ አስተምህሮቶች መጋጨት ደስታቸው ነው። ፉቀሐዎችንና ሱፍዮችን እንደ ኋላ ቀር በማሰብ "ዘመናዊ ኢስላም" እንነርሱ ጋር እንዳለ ይወተውታሉ። እነዚህ ቅቦች በአጠቃላይ የፈተና ተጣሪዎች እንዳይኾኑ ያሰጋኛል። ድሮ ድሮ የሚያሰጋኝ ዳዕዋ አክ**ራሪና ጽንፈኞች ብቻ ነበሩ። ዛሬ ግን ከዚያው መንደር ያመለጡ የሚድያ ቅቦች ተበራክተዋል። ይህ አጀንዳ ያሳሰባቸው ሰዎች ብዙ ቪዲዮዎች ቢልኩልኝም ትኩረት አትስጧቸው የሚል መልስ ብቻ ነው የነበረኝ። ዛሬ ግን በዚህ መስመር ያመጣሁት፤ ይህ ራሱን የቻለ በሽታ መኾኑን ለማሳወቅ ሲኾን የታማሙ ሰዎች ስለማይታወቃቸው ቅርብ ቤተሰብ ያላቸው እንዲያሳክሟቸው ለመጠየቅ ሲኾን፤ እኛም ከእነዚህ ቅብ አካሄዶች ራሳችንን መጠበቅ እንደሚገባን ለማስገንዘብ ነው።

ወላሁ አዕለም

Best kerim

14 Feb, 06:27


ጠዋት ከፈጅር በኋላ ልጄ እንደነቃች ምን ብትለኝ ጥሩ ነው? ባባ ሰማዩ ምንድነው? ዒድ ነው እንዴ ዛሬ?! ማታ ዒድ ይመስላል ስንል የሰማችን አይመስልም?!!

ለመልካም ተፋኡላችሁ ማረጋገጫ ነው 😍😄

ጁምዓ ሙባረክ

Best kerim

13 Feb, 19:37


ቁርኣን ምርጡ ጓደኛ ነው። የዛለ የደከመ ውስጥህን ሳትደብቅ የምትነግረው፣ የፈለግከውን ስሜት የምትነግረው፣ ስሜትህን ሳትነገርው የሚያነብህ፣ የውስጥህን ሐጃ ሳትነግረው የሚያወጣልህ፣ ብትሸሸው የማይሸሽህ፣ ትንሽ ስትቀርብ ብዙ የሚሰጥህ ውቡ የውስጥ ኃይል ነው። በተለይም በእነዚህ በተመረጡ ለሊቶች ውስጥ ከመደበኛ ዊርድህ በተጨማሪ የተመረጡ አንቀጾችን ብናነብ ይመከራል። ለዚህ ለሊት ከተመረጡ አንቀጾች ውስጥ አንዱ “የዱኻን ምዕራፍ” ነው። ከመኝታ በፊት እናንብበው ብዙ ጉዶች በውስጡ ይዟል። ቁርኣንን ለመቅረብ የልብ ዝግጁነት ካለ በቅርበታችን እጥፍ እርሱ እኛን ያቀርበናል።

ቁርኣንን ቀርቦ ያፈረ ሰው የለም!

ውብ ለሊት ይኹንልና

Best kerim

13 Feb, 18:13


በማይረቡ ነገሮች መጨቃጨቅ እምነትን ይገድላል። ተግባር የገራለት ሰው እምነቱን ሐይ ያደርገዋል። ለዘመናት በጭቅጭቅ ከሰለዋትና ከሕብረት የዚክር ሐድራዎች ለተዘናጋንበት ጊዜ ቀዷ (ማካካሻ) ያስፈልገናል።

ሐያ

Best kerim

13 Feb, 18:06


ቅርብ ሰአት ልክ የዒድ ለሊት የሚመስል ስሜት ውስጤ ላይ አነበብሁ። ከዚያም አንድ ወንድም ተመሳሳይ ሐሳብ አስተያየት መስጪያ ላይ ጻፈልኝ። ለሊቱ የምር "የዒድ ለሊት" ስሜት ካለበት የኾነ የሚያስመረቅን ነገር አለው ማለት ነው!

ሰለዋት ጨምሩበታ

Best kerim

13 Feb, 17:49


የሕብረት ሰለዋትና ዚክር ላይ በርቱ በየመስጂዱና ሙሰላው ላይ ኹሉ የሰለዋትና የዱዓ ሐድራዎችን አቋቁሙ የኡመቱ ክብር ሐይ ኾኖ መመለሱን ማንም የሚያግደው የለም። ሰዎች ተሰባስበው ሲዘክሩ፣ ሰለዋትና ዚክር ማድረግ የገራለትም ያልገራለትም ከእነርሱ ጋር እስካለ ድረስ አብሮ ከምንዳውም ከመንፈሱም ይቆራኛል። ይህን በረከት በትነው "ሩሕ" የሌለው ዳዕዋ በግለሰቦች ዘንድ አሰራጩ። ይህ የገባው ሰው በ "ዘመናዊ" ስም በሚደረግ ዳዕዋ አይወናበድም።

ወደ ክብራችን የምንመለሰው አባቶቻችን በሄዱበት መንገድ ነው!

ለሸይኾቻችን ኹሉ #አልፋቲሓ

Best kerim

13 Feb, 17:25


ለሊቱ የጁምዓ ለሊት ነው ደግሞ ወዲህ የሸዕባን አጋማሽ ለሊት ነው። ዱዓ ሙስተጃብ የሚኾንባቸው ሁለት ለሊቶች ተጋጠሙ ይህ ለሊት ለመላእክቶች ዒድ ነውም ይሉታል። በዚህ ለሊት ሐጃችንን ሳይኾን የሐጃውን ባለቤት አላህን እንገናኝ። ሐጃችን ላይ ብቻ ወይም ሰበብ ላይ ብቻ አንልፋ። ይህን ኹሉ ስለሚያስተናብረው አላህ በማሰብ ልባችን ይህን የሚያስተናግድ መንፈሳዊ ማንነት የሚያድግበትን ነገር ኹሉ ከእርሱ እንለምንበት።

አላህ ልባችንን ሐይ ያድርግልን

ሰለዋት ጨምረን ጨማምረን እንበል

Best kerim

13 Feb, 17:13


አልሐምዱሊላህ በጣም መስጂዶቻችን ላይ ጥሩ የሰለዋት፣ የዚክር፣ የዱዓ ሊቃዎች እየተደረጉ ነው።

መፍትሔው ይህ ብቻ ነው፤
ወደ ዋሻው መመለስ ብቻ!!

ኒስፈ ሸዕባን እንዴት እያሳለፋችሁት ነው?

Best kerim

13 Feb, 16:25


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

13 Feb, 08:52


https://t.me/Noor_Musela/6335?single

Best kerim

12 Feb, 19:20


ቁርኣንን ማንበብ ከዚክር ኹሉ በላጭ ዚክር ሲኾን ከአምልኮ ኹሉ ብልጫ ያለው መቃረቢያም ነው። ቁርኣኑን ጥንቅቅ አድርጎ የሚቀራ ሳሊክ ተጨማሪ ዊርዶች ይጠቅሙታል። መንገዱን ይጠግኑለታል። ይህ ቁርኣን በጽሞና ስናነብ የብዙ ዓለማትን በራፎች እየከፈተ ያሳየናል። በጥሩ ድምጽ ስንቀራው በሐሳብና በስልቹነት የተቆራረጠ ድምጽን ያስተካክልልናል። በብዛት ስናነበው ከውስጣች ብዙ የተቃጠሉ አየሮችን ያስወጣልናል። ይህ ሸዕባን ሳይወጣ በጥቂት ገጾች ይለማመዱት። እናት አባቶች ልጆቻችሁ ፊት ድምጾትን ከፍ አድርገው በመቅራት ቤቱን ያስውቡ። ለቤቱ በረከትና መላእክት ይጥሩ፣ ሸረኛውንና ሐሲዱን በዚህ መንፈስ ሐይል ያስወጡ!!

ሞክሮ ያጣ የለም!!

ሐያ

አላህ ይረዝቀና

Best kerim

12 Feb, 14:10


#ሸዕባን_አጋማሽ_ምን እንስራ?

የሸዕባን አጋማሽ ለሊት የሚውለው ሐሙስ ለጁምዓ ለሊት ነው። በዚህ ለሊት አላህ ፍጡራኑንን ኹሉ በጅምላ የሚምርበት ለሊት ነው። ከሁለት ሰዎች ሲቀር አንደኛው፦

* አላህ ላይ የሚያጋራና
* በልቡናው ውስጥ ቂም የሚቋጥር ሰው

አላህ ላይ ማጋራት ሲባል ይህ በየሜዳው በኾነው ባልኾነው አጋርተኻል እንደሚባለው ሰበካ ሳይኾን። የፈጣሪን ችሎታ ለፍጡር፣ ቁስና፣ ሰበብ መስጠት ኹሉ የአጋሪዎች ተግባር ላይ ሊገኝ ይችላል።

ሁለተኛው የጥላቻና ቂምን በተመለከተ ሁላችንም የምንፈተንበት አጀንዳ ነው።

በዚህ ለሊት የተለየ የሚሰራ የተደነገገ አምልኮ የለም። ለዚህ ለሊት የሚያስፈልገው ከተጠቀሱት ሁለት ተግባራት የጸዳ ልብ ማዘጋጀት ነው።

ይህን ንጹሕ ልብ ማዘጋጀት ከባድ ስለኾነ መማጸኑ ይሻላል ብለው ይመስለኛል ዑለሞቹ ምሽቱን በሙጥለቅ አምልኮዎች ያሳልፉታል። ሙጠለቅ አምልኮ ማለት በየትኛውም ቦታና ጊዜ ማድረግ የሚቻል የአምልኮዎች አይነት ናቸው። ለምሳሌ ቁርኣን፣ ዱዓ፣ ሰለዋት በየትኛውም ሁኔታ ቢሰሩ ክልከላ የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው። በዚህም በ 15ኛ የሸዕባን ለሊት ዑለሞቹ የያሲንን ምዕራፍ ከዱዓዎች ጋር ያከናውናሉ። ይህ የግዴታ አምልኮ ሳይኾን ከዕውቅ ዑለሞች የተገኘ ተጅሩባ ነው። በምሽቱ የሚደረገው ይህ የዱዓ መርሀግብር የአላህን በዚህ ለሊት ያዘጋጀውን ልዩ ሽልማት ለመጎናጸፍ የሚደረግ ተማጽኖ ነው።

አላህ ይወፍቀን

ልባችንን ያጽዳልን

Best kerim

12 Feb, 06:48


#ከዘመን_ጣኦት_መጠንቀቅ

“ ለሁሉም ሕዝብ የሚያመልከው ላም ጥጃ አለው፤ የእኔ ሕዝብ ጥጃ ዲናርና ዲርሐም ናቸው።”

[ደይለሚ ከሑዘይፋ ይዘው የዘገቡት ሐዲስ ነው። ከንዝ 2/223]

በሰይድና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘመን በሳሚሪይ አማካኝነት የተሰራችው የወርቅ ጥጃ የብዙሀኑን እምነት የፈተነ ተግባር ነበር። ሳሚሪይም የነበረው ዕውቀትና አስገራሚ ነገሮች ወደ አሉታዊ መንፈስ ተቀይሮበት በወርቅ ጥጃ በመስራት ያፈዘዛቸውን ሕዝቦች "እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ" ነበር ያላቸው። ከዚህ አስገራሚ ቁርኣናዊ ተረክ ብዙ እንማራለን። ሰይዳችን (ዐለይሂ ሰላም) የሕዝቦቻቸውን ፈተና የኾነውን "ገንዘብ" የት ድረስ እንደሚደርስ ነግረውናል። በዘመናችን እንደ ትላንቱ ጥጃ ወይም የኾነን አካል ጠፍጥፎ የሚያመልክ ሰው ላናገኝ እንችላለን። ግና የደጃል ሰራዊት ገንዘብን በሰዎች ውስጥ በማንገስ ሊመለክ የሚችል ሐይል እንዳለው ብዙ የሚጠቁሙ ነገሮች ይታያሉ።

የእኔ ሕዝብ ጥጃ ዲናርና ዲርሐም ነው!

ይህን ከባድና አስደንጋጭ እውነታን ዛሬ ላይ ፍንትው አድርጎ የሚያሳኝ ትንግርት ነው። ሁሉም ነገር ወደ ገንዘብና ጥቅም በሚዞርበት በዛሬ ጊዜ ወደ ቀደመው የሱና መንገድ መመለስ እጅግ ፈታኝ ነው። የእምነት ጽንሰሐሳቦች ኾነ ግለሰቦች በገንዘብ የተለወሱበት የዱንያና የገንዘብ ዓሊሞች በተበራከቱበት በትክክል የእውነት ጥሪን ከሐሰተኛ ጥሪ ጋር ለመለየት ሰይድና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ኸድር በማግኘት የተገለጠላቸውን እውነት ያህል መረዳት ያስፈልጋል። ሁሉ ነገር በተደበላለቀበት ጊዜ፣ ገንዘብ የፈለገውን በሚያደርግበት ዘመን ከገነኑት ጋር መግነን፣ ቦግ ካሉት ጋር አብሮ ከመቅለጥ በዝምታ መረዳትን ማስቀደም ያስፈልጋል።

አላህ ከከባዱ ፈተና ይሰውረን፤ ብዙ ቢያስወራም ሐዲሱ ላይ እንቆይ!

አላህ ያስረዳን

Best kerim

11 Feb, 18:29


ቁርኣንን ለማንበብ ስንቀመጥ እንቅልፍ ቢያስቸግረን፤ አለፍ ሲል የኾኖ የማይታወቁ ንግግሮች ከአንደበት መውጣት ከጀመሩ ቁርኣኑን ከመቅራት ማቆምና ዊርድን በሌላ የተሻለ ሁኔታና መልካም የውስጥ እረፍት በመውሰድ ማካካስ ይመከራል። ምክንያቱም ቁርኣን ውስጥ ሙሉ ትኩረት ካልተገኘ ማስተንተን ካልታከለበት ጥቅም የሌለው ንባብ ይኾናልና።

ቁርኣንና ሰላት በቂ በራሳቸው ማረፊያ ቢኾኑም ከምንም ነገር የጸዳ ውስጣዊ ዝግጁነት ያስፈልጋቸዋል።

በሸዕባን ወር የቁርኣንን አቀራር በደንብ ለነፍሳችን የምናድስበት ወር ነው።

አላህ ወደ ቁርኣን መቅረቡን አይከልክለን

Best kerim

11 Feb, 12:56


۩اللّٰه۩

አላህ የሚለው ከሊማ የራሱ የኾነ መሸሸጊያ ሲኾን ቃሉ ሙሉ ደህንነት እንዲሰማህ ያደርጋል።

"في لفظِها أمنٌ نلوذُ بهِ
طوبىٰ لمَن أنتَ يا مَولايَ مَولاهُ!"🤍
لِأَنكَ اللهُﷻ ♡゙

ማንም ሰው አላህ ጋር የማውራት ነጻነቱን ማንም ሰው ሊነፍገው አይችልም። አላህን ያለምንም ደላላ ማግኘት ይቻላል። ስሙን ደጋግሞ በመጥራት፣ ስሙን የሚያስታውሰንን ነገር መስራት ኹሉ ዚክር ነው። ከስሙ የሚያርቀን ነገር ኹሉ ጘፍላ ነው።

ከሚወረድ በላእ፣ ከተጻፈ በላእ ኹሉ አላህ ነጃ ይበለን

Best kerim

11 Feb, 08:13


በሰዎች ውስጥ የመታየት፣ የመደመጥና አጀንዳ የመኾን የፍላጎት መጠን የት እንደረሰ እያየን ነው። ሰዎች ከፍተኛ በጀት መድበው የመታየትና የመደመጥ ስሜታቸውን ያረካሉ። ትርፉ ምንድር ነው? "ሰው" ማለት እኮ ጀግና ተብሎ ዛሬ መሞትን የሚመርጥ ኢጎ ያለው ፍጡር ነው። ይህ ስብዕና እያደር እንዳመጣ በበሽታው መጠቃት እንዳይከሰት፤ በመንፈስ መቀረጽና መታረም ያስፈልጋል። ይህ ዝና እና ገንዘብ የሚያመጣው በሽታ ሳይኾን ነፍስ ውስጥ ተደብቆ በዝና እና ገንዘብ ሰበብ የሚገለጥ ችግር ነው።

አላህ ያስረዳና

Best kerim

10 Feb, 19:27


ዛሬ ሚዲያ ላይ የወጡ ጽሑፎችን አንብበህ አስተያየት ጽፈሀል። ዜናዎችን አንብበህ አስተንትነሀል፣ በርካታ በእጅ ስልክ ላይ የመጡ መልእክቶችን በጥንቃቄ አንብበህ መልሰኻል። በዕለትህ የጌታህን ቁርኣን (ሰማያዊ መልእክትስ) ከድርሻህ ከፍተህ አንብበህ መልስ ሰጥተኻል?!

ያ ዐብደላህ! ይህ ቁርኣን የጌታህ መልእክት ነው። በዐቅምህ ልክ ከፍተኸው የድርሻህን ለመውሰድ መጣርህን ሳታረጋግጥ አትተኛ። ለሕይወትጅህ የማይቋረጥ በረከት የሚለግስህ ውድ ሙስሐፍ ነው።

አላህ ይረዝቀና

Best kerim

10 Feb, 17:59


የኡስታዝ ናስርን ቃለምልልስ ካደመጥኩ በኋላ ስለ ሐሳብ ሜንስትሪም (ማዕከል) እያሰብኩ ዋልሁ። ማሕበር፣ ቡድን፣ ተቋም፣ ግለሰብ ሜንስትሪም ሲኾን መጨረሻው በሽታ ነው። የሐሳብ ልዕልና ከፍ ሲል ግለሰቦች ተደብቀውና ደብዝዘው ኡመት (ማሕበረሰብ) መሥራት ይችላሉ። በቃለ ምልልሱ ወቅት አልፎ አልፎ ስለ ሙረቢው ሐጂ ኪኪያን (ራሕመቱላህ) የሕይወት ዘይቤ ሲነግረን በትክክለኛ ሸይኽ የመታነጽን ዋጋ መረዳት እንችላለን። የሕይወት ዘይቤውን የምታውቅለት እያንዳንዱ እንቅስቃሴውን የምትቃኝለት ሸይኽ አለህ ማለት ዕጣህ ያማረ ነው ማለት ነው። 4 ሺህ መጽሐፍ አንብበዋል አለን እኮ ድንቅ መተዋወቅ

በነገራችን ላይ ሐጂ ሙሳ (ራሕመቱላህ) በጣም ድብቅና የሽይኸነት ሚናቸውን በማደብዘዝ ሕዝብን ሲያገለግሉ የነበሩ ጥበበኛ ድንቅ ሰው ነበሩ። የየትኛውም እምነት ተከታይ፣ የየትኛውም የእስልምና ቡድን በእርሳቸው ያልተጠቀመ የለም። እርሳቸውን በሚገባ አይቶና ተኗኑሮ ችሎ የሚቃወማቸው ሰው አይገኝም። ይህ እንግዲህ ከአላህ የሚሰጥ ጥበብ ነው። ሸይኹ የሰው ልብ ውስጥ ለመግባት የደበቁት አቋም ኾነ በይፋ የመጋለጥ ማስታወቂያ አልሰሩም። ያደረጉት ነገር ቢኖር መኖርን ማስቀደም ብቻ ነው። ይህ የሚገባህ የእርሳቸውን ተርቢያ ያገኙ ሰዎችን ልብ ስትመለከት ነው።

ኢስላም ሲኖርበት ፣ ተርቢያ የምር ከዕውቀት ጋር ሲጣመር አማኞች ከልዩነታቸው ጋር የልብ መዋሀድን ይፈጥራሉ። በዘመቻ፣ በፖለቲካ ልፍያ የአማኞች ልብ አንድ አይኾንም።

በ "ተዓሊም" እና "ተዓሊብ" መካከል ያለው ልዩነት ግልጽ ነውና

#አልፋቲሓ

Best kerim

10 Feb, 08:22


ኡስታዝ ናስር ዲኖን መሪ ፖድካድት ላይ የነበረውን ጭውውት ከተመለከቱ በኋላ ዘምዘም ባንክ ሒሳብ ለመክፈትና ሦስት ቀን ዳዕዋ መውጣት አማረኝ። :-D :-D ( ይህን ያልሁት አንድም ቦታ ሰዎች ባንኩን እንዲጠቀሙ ሳይወተውት በመጨረሱ ነው። )

በፖድካስቱ ላይ ...

ትምሕርትና ዕውቀት፣ ከሥነምግባርና መንፈሥ ጋር ሲዋሐድ የሚፈጠረውን የሥነልቡና ሙሉዕነት፣ የዳዕዋ ውበትና የተግባቦት ዐቅም ምን እንደኾነ የተማርኩበት ውብ ቆይታ ነው።

ሐጂ ሙሳ ኪያያን (ቀደሰላሁ ሲረሁ) " My Mentor" ብሎ ሲጠራቸው ውስጤ ተቁነጠነጠ። ሐጂዬ ፖለቲከኞ ያልነበሩ፣ በዕውቀትና በመንፈስ ምርጡ ሰው ነበሩ ብሎ የልቤን አውርቶኛል። በንግድ እንቅስቃሴያቸውም የሚገርም ቤተሰብ እንደነበራቸው አያይዞ በአስገራሚ ገለጻ ሰኞዬን አበራልኝ።

ኡስታዝ በሕይወቴ የተማርኩት ትልቁ ጥበብ [ዝምታ] ነው ይላሉ፤ ትልቁ የኢንቨስትመንት ጊዜዬው ደግሞ ከሐጂ ሙሳ ኪያያንን ጋር ያሳለፉት እያንዳንዷ ደቂቃ እንደኾነ ነገሩን። ዝም ብለህ ጉድ አትልም!!

ኡስታዝ፣ ዶክተር አላህ ይጠብቅህ

ይህን ፖድካስት በጥሩ ኒያ አድምጡት ልብ ኹላ ያንቀሳቅሳል፣ የዳዕዋ ሰዎች "በያን" የሚሉት ልብ የሚያነቃንቅ ቆይታ አላቸው። ልክ የእርሱ ያህል ዋጋ አለው።

ኡስታዝ ለወጣቶች ሲመክር ከአላህ ጋር ብቻ አትጣሉ ነጻ ሰዎች ናችሁ አለን ሲጠቃለል።

ኢስነይን ሙባረክ

Best kerim

10 Feb, 07:05


https://www.facebook.com/share/15nZY51Zfo/

Best kerim

09 Feb, 20:01


በትንሹም ቢኾን ከቁርኣን የግማሽ ሰዓት በረካ ውሰድ!

ቁርኣን ጋር በየዕለቱ ለመኖር ብንጥር መፈክራችንን ደግሞ ‹‹ቁርኣንን ሳነብ ልረዳና በተጽዕኖው ውስጥ ልኸን!›› የሚለውን ቢሆን፣ በርግጠኝነት ነፍሶቻችን ላይ የሚረጋገጥ ለውጥ እናገኛለን፡፡

ልቦቻችን ከቁርአን ጋር በሚኖር ግንኙነት መስፋት ይችላል፡፡ ከዚያም በሒደት ወደ ውስጣችን ዐዲስ መንፈሥ እየተላበስን እንመጣለን፡፡ ከልብ የሚመነጭም ልዩ ችሎታ ከውስጣችን ይወለዳል፡፡ ይህ ችሎታ ከወንጀል የምንሸሽበትንና መልካም ነገር የምንሠራበትን፣ ዝምድና የምንቀጥልበትን፣ በአላህ መንገድ ላይ የምንለግሥበትንና የምንጣራበትን ዐቅም ይለግሰናል። ሌሎችንም ነገሮች ያንበሻብሸናል።

ለሕይወታችን በሰጠነው የቁርኣን በረካ ልክ ልባችን ላይ ከምንም ነገር በላይ የአላህ ቦታ ገዝፎ መታየት ይጀምራል፡፡ ነፍሳችንና የምንኖርባት ዓለም ደግሞ አንሳንሰን በመመለከት ብዙ ነገሮችን መተውን (ዙህድ) ያስገኝልናል፡፡

በዚህ ግማሽ ሰዓት የኢማንን ትርጉምና እውነተኛን ጥፍጥናን በማግኘት ከአላህ ጋር እንድንሆን በማድረግ ደስታም ይሰጠናል። አላህን ለማግኘትም ከፍተኛ የናፍቆት ስሜት ውስጥ ይከተናል።

ከዚያም የስክነትና መረጋጋት ብሎም በሕይወት መደሰት ይመጣል፡፡ ይህን ጊዜ በሕይወታችን ላይ መደበኛ ካደረግነው በዳዕዋ ሜዳችን ላይ ስኬታማ ያደርገናል፡፡ በተጨማሪ ለረዥም ጊዜ ፈልገን ያጣነውን ከውስጣችን የሚመነጨውን የአዎንታዊነት ባሕርይ ያጎናጽፈናል፡፡

ከፍተኛ ድንዝዜ ውስጥ፣ የሕይወት ትርጉማ ማጣት፣ የነገሮችን ትክክለኛነት አለመረዳት ኹሉ የሚጠረረግል የቁርኣን በረካ ነው። ቅርብ ሰአት ከአንፋል ምዕራፍ መጨረሻ እስከ አልተውባህ አጋማሽ እያነበብኩ ነበር። እነዚህ ምዕራፎች ላይ ስትደርስህ ልብህ ከፍተኛ ግለት ይሰማዋል። አደገኛ የመነቃቃት ዐቅም ይሰጥሀል። ጠላትን ለመርታት የሚያስፈልግህን ስንቅ በሚገባ ይለግስሀል። ያረጀ ልብ ካለን እንዴት በአንዴ ሐይ (ሕያው) እንደሚኾን ገና በንባብህ ላይ ሳለህ ያነሳሳኻል።

ቁርኣን ሐይ ያደርጋል፤ አላህ ማንበቡን ከመረዳት ጋር አይከልክለን!

Best kerim

09 Feb, 16:45


#የልብ_ጥራት

በነገራችን በየቦታው ሞቅ ደመቅ ብለው የሚከናወኑ ኢስላማዊ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞች ከምንግዜውም በላይ ተበራክተው ይታያል። ይህ በእውነቱ ምርጥ ዕድገት ነው። ድሮ የምናቀው የመስጂድ ሙሐደራ ብቻ ነው። በሁለቱ ዓለሞች ውስጥ ግን ጉልህ ልዪነት እንዳለ እየመዘገባችሁ ማለፍ ያስፈልጋል። ድሮ ድሮ ድርጅታዊ ይዘት፣ በፖለቲካዊና ጥቅማዊ ትስስሮሽ የተዋዙ፣ ድርቀት የተላበሱ አልነበሩም። እርግጥ በዘመኑ ትልቁ የሚድያ ሐይል ፌስቡክ ነው ሌላ ነገር የለም። እርሱም ከ 2003 በኃላ ነው በደንብ የታወቀው። በዚያ ዘመን ስራዎችህን ሰው እንዲያይልህና እንዲታደምለህ የምታስተዋውቀው በየመስጂዱ እየሄድክ በመለጠፍ ነው። ልፋት አለው። ፕሮግራም ለማዘጋጀት ዕድል ይኑርህ እንጂ ማንኛውም ሙስሊም አንተ ጋር ሐዲር ነው። ተሳክቶልህ አንድ ሙሐደራ ብትሳተፍ ኢማንህ ይጨምራል። ዳዒው ሰለፊ ይኹን ሱፊ የምታቀው ነገር የለም። ሁልጊዜ በዚህ ሙድ እንቆይ ባይባልም ይህን ስሜት ማጣት ግን እንደ ማሕበረሰብ በጣም ወደ ኋላ የሚያስቀረን ለመኾኑ ሁሌ ይሰማኛል።

ትላንት የሌሉን ብዙ ችግሮቻችን ተቀርፈው ሁሉም ጀምዓ ድርጅትና ሚድያ አቋቁሞ፣ የራሱን መድረክና ሸይኽ ሹሞ ቆም ብዬ ስመለከተው በግለሰብ ደረጃ ሳይኾን እንደማሕበረሰብ ፖለቲካዊና ድርጅታዊ ቁመናችን እንጂ የወንድማማችነትና የኢማን ዕድገት ግን ቁልቁል መውረዱ ያሳዝነኛል። አንድ ሰሞን ሙፍቲ ሐጂ ዑመር (አላህ ይጠብቃቸው) ሲናገሩ አዕምሮዬ ላይ የቀረ አንድ ንግግር ነበራቸው " አንድነት የሚፈጠረው በልብ ነው።" እውነት ነው። ልብ የኢማን ቦታ ነው። በዚህ በተለመደው መንገድ መሄድ የፈለገ አመለካከት ላይ ቢሰራ የሚያድጉት የአመለካከት ዐለቆች፣ ድርጅቶችና ጀምዓዎች እንጂ ኡመት እንደኡመት አያድግም። ሁለቱም ዕድገቶች ቢያስፈልጉም የበለጠ ምርጡን የልብን አንድነት የሚያመጣውን የኢምን ጥራት በውስጣችን ለማሳደግ መሥራት አስፈላጊ ነው።

አላህ ይርዳና

Best kerim

09 Feb, 13:09


https://www.facebook.com/share/p/15Tz1PqmM7/

Best kerim

08 Feb, 20:26


የቁርኣን ተማሪ (ተከታይ) ሆይ! ቁርኣን ስታነብ በእያንዳንዱ አንቀጽ ውስጥ ራስህን ፈልግ፤ አንተን የሚመለከት ነገር በቀጥታ ታገኛለህ። የሚጠቅምህን ነገር በውስጡ ታያለህ፣ ዐቅጣጫም ይጠቁምሀል። በአንቀጾቹ ውስጥ ለበሽታህ መድሐኒት ታገኛለህ። ደስታም በመጎናጸፍ ሐሳብና ጭንቀትንም ታስወግድበታለህ። ይህን ኹሉ የምናገኘው ጥቂት የቁርኣን ገጽን ስንከፍት ተረጋግተን ለማስተንተን ስንታደል ነው። "ማስተንተን የሌለው የቁርኣን ንባብ መልካም ነገር የለውም።" ቁርኣንን ደግሞ በላጩ ዚክርና መቃረቢያ ነው።

ከዕለቱ ድርሻህ ሳትወስድ ወደመኝታ አትሂድ

አላህ ይረዝቀና

Best kerim

07 Feb, 20:03


ወንድሞቼ! ይህ ቁርኣን ልብን ከፋች ነው። በሰጠነው ልክ ይሰጠናል። እንደምንም ታግሰን ሰብሰብ ብለን ወደርሱ ስክን ስንል በምትኩ ከልባችን ማውጣት የቸገረንን ሐጃ ኹሉ ያወጣልናል። የማናቀው የሙድ መቀያየር፣ ስልቹነትና ድባቴ የሚወረው ሰው ታግሶ ቁርኣን ለማንበብ ቢሞክር፣ ወይም ቢያደምጥ፣ አለያ ቢማር የመቀነስ ዐቅሙን ራሱ ማረጋገጥ የሚችለው ነገር። ይህ ቁርኣን በእርግጥም ሕዝቦችን የሚመራ መመሪያ ነው።

ይረዝቀና

Best kerim

07 Feb, 17:30


#የሸዕባን_ሐሳቦች

በዚህ በሸዕባን ወር ታላላቅ ክስተቶች ተከስተው አልፈውበታል፡፡

* በሁለተኛው የሂጅሪያ ዓመት ጾም ተደነገገ።
* ሰለዋትም የተደነገገበት ወር ነው።
* የቀድሞው በይተል መቅዲስ ቂብላ የነበረ ሲሆን በዚህ ወር ወደ መካ የተቀየረበት ወር ነው፡፡ ይህም የሆነው በሁለተኛው ዓመተ ሂጅራ ነው፡፡ (በረጀብም፣ በጀማደል አኺርም ነው ተብሏል፡፡)
*መልእክተኛው በሦስተኛው ሂጅሪያ ሰይደቲ ሐፍሳን ያገቡበት ወር ነው፡፡
* የሙስጠሊቅ ዘመቻ በዚሁ ወር አምስተኛው ሂጅሪያ ተከናውኗል፡፡
* የተቡክ ዘመቻ እንዲሁ በዚህ ወር በዘጠነኛው ሂጅሪያ ተከናውኗል፡፡

ከፍ ያሉት ዑለሞች ደግሞ የቁራእ ወር እያሉ ይጠሩታል። ቁራእ ማለት ቁርኣንን አብዝተው የሚያነቡ ሰዎች ማለት ነው።

አንድ የሻዕባን ሳምንት ሔደ፤
ቀጣዩን ሳምንት አላህ ይባርክልና

Best kerim

06 Feb, 20:32


https://www.facebook.com/share/p/185T35W6ZP/

Best kerim

06 Feb, 17:40


ሁለት ዓይነት ሰደቃ (ምጽዋት) እንዳለ ሸይኽ ዐሊ ጠንጣዊ (ራሕመቱላሂ ተዓላ) አንድ ጽሑፋቸው ላይ ጽፈው አይቻለሁ። አስገራሚ ልምዳቸውንም አካፍለዋል። ልጃቸውን ለማስተማርም በሰሐን ምግብ ይዛ እንድትመጣ አዘዟት ለጥበቃቸው እንድትቃርብላቸው ያስደርጋሉ። ይህ የመጀመሪያው ዓይነት ሲኾን ሰደቃ ቢልማል (በገንዘብ፣ ንብረት የሚደረግ ሰደቃ ነው) ይሏታል። የምግቡን ሰሐን ይዘው ከጥበቃው ጋር አብረው ሄደው ደግሞ በመመገብ ይህ ሰደቃ ቢሽዑር (በስሜት የሚለገስ ሰደቃ) ብለው ያስተምሯታል። ይህን ዓይነቱን ሰደቃ ሲያስተምሯት የሚሰጠው ሰው የተመፅዋችነት ስሜት እንዳይሰማው ያደርጋል። (ረጅም ነው፤ ለአንባቢያን አሳጥሬው ነው)

ምን ለማለት ነው ሰደቃ ሲሰጥ በገንዘብ መሰጠት ጥሩ ኢማን ይጠይቃል የሚያስቀናም ተግባር ነው። የበለጠ ውብ የሚኾነው ግን የሚሰጠው ሰው ተመጽዋችነት ስሜት እንዳይሰማው ማድረግ ግን የበለጠ ጥበብ ነው።

ጥበብ ከጠፋባቸው መሪዎች ኹሉ ይሰውረን

Best kerim

06 Feb, 17:05


ኸሚስ ምሽት ማለት ..

ድሮ በልጅነት ዘመን ከቤተሰቦች የወረስነው ውዱ ምሽት እኮ ነው። እኛ ቤት ቢጠፋ ቢጠፋ ነጭ ሩዝና የቂቤ ቡና አይጠፋም ነበር። ይህን ምሽት በልጅነት አዕምሮ ትዝ ሲለኝ እንናፍቀዋለን። የሰለዋትና የዱዓ ምሽት ነዋ። ይህን ወደ ተርታው ሕዝብ እንደ ሥርዓት የተከሉት የልብ ሥልጡን የነበሩት የሐበሻ ዑለሞቻችን ነበሩ። በሌላ ጉዳይ ሥልጣኔ ሲዛመት የሠለጠንን መስሎን ከእነርሱ የወረስነውን እሴታቸውን አብረን አጠፋነው።

እውነት ነው ሠልጥነናል በቴክኖሎጂ ልቀናል፤ ልባችን ግን ለመድረስ ብዙ ይቀረዋል። ዑለሞቹ በልብ ቀድመውናል። እንመንና ወደነርሱ ዐለም እንመለስ። "ሓዳራ" ማለት ሥልጣኔ ነው። "ሓድራ" ደግሞ መጣድ ማለት ነው። ሓዳራ (ሥልጣኔ) የሐድራ ክፍል ነው ይላሉ የተዘወቁት ሙሒቦች። ስለዚህ ሐድራ ላይ ያልደረሰ መች ሙራዱ ተነካና?! ገና ነው!

ወደ ኸሚሳችን

Best kerim

06 Feb, 16:26


ሐቢቢ ግለሰብ ለመኾን ጣር፣ ለሰው ከማለትህ በፊት ለራስህ ኹን። ራስህን ተሸከም፣ ዙሪያህን ቤተሰብህን ጠብቅ በኋላ ስትዞር ከኾነ ከማታቀው ሕዝብ ጋር ተቀላቅለህ ነው ራስህን የምታገኘው። ለሌሎች መኾን ደግ ነው ምንም ጥርጥር የለውም ለራስህ፣ ለልጆችህ፣ ለባለቤትህ ግን በገንዘብም ብቻ ሳይኾን በተርቢያ፣ በስሜት፣ በፍቅር አብረህ ለመኾን ጣር። ያንተ የኡመቱ ምርጥ መኾን ቤትህን አያድነውም!

ሐያ ቤትህ በጊዜ ግባና ለቤተሰብህ ሰለዋት አስተምር፤ ልክ አባቶቻችን የኸሚስን ዋጋ አስተምረው እንዳሳደጉን!

ሐያ

Best kerim

06 Feb, 15:49


#አላህ_ሊያዘጋጅህ_ነው

« አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከአላህ የጠየቁትን ለመቀበል ዝግጁ አይሆኑም ነገር ግን ባሪያው አላህን በመለመኑ ከጸና የጠየቀውን ለመቀበል በእውነት ዝግጁ እስኪሆን ድረስ ያዘጋጀዋል።»

[ሸይኸና ሐቢብ ዑመር ቢን ሓፊዝ ፤ ተሪም የመን]

እጅህን አንስተህ በጠየቅከው ነገር ድንገት ቢሰጥህ የለመንክበት የውስጥ ዝግጅትና ቁርጠኝነት ወሳኝ መኾኑን አስበህ ታውቃለህ?! ቤተሰብ መመስረት፣ ትልቅ ንግድ ማንቀሳቀስ፣ ሰዎችን መምራት ... ሌሎችም ነገሮች በጠየቅክበት ልክ ዝግጁነት አለህ? አንዳንዴ ከባድ ጸጋ (ኒዕማ) መጥቶልን ውስጣዊ ዝግጁነት ባለመኖር የተነሳ ዕድሉ ከበረከት ይልቅ መርገምት ሊኾንብን ይችላል።

አላህ የጠየቅከውን የሚከለክል ጌታ አይደለም። ግን ደግሞ ለጠየቅከው ነገር ያዘጋጅልሃል፤ አሻፈረኝ ካልክ፣ እርሱ የወደደልህን አልወድ ባይነት ተጠናውጦህ ካማረርክ የፈለግከውን ሰጥቶ ሊፈትንህ ይችላል። ስለዚህ ባለህበት ቦታ ከእርሱ ጋር ማውራትን ካልከለከለህ፣ የማመስገን ጠባይ ካልነፈገህ፣ ታግሰህ ከርሱ መጠበቅ የሚሻልህ ትልቁ በረከትህ ስለኾነ ራስህን ከመኽሉቅ ጋር በማወዳደር የማትወጣበት አዘቅት ውስጥ እንዳትገባ። ይህ በርግጥ ኼሌም የምንፈተንበት ነገር ነው። የሸይኾች ቀውል በረካ አለውና የልቤ ጌጦ ተሪሞች የሚያወሩት ኹሉ በአጭሩ ብዙ መልእክቶች ስጡ ተብለው ተባርከዋል።

ለኸሚሱ ምሽት ይህችን በረከት ያዙልኝ

አላህ የምናነበውን፣ የምንሰማውን፣
የምናወራውን ኹሉ ይባርክልና

Best kerim

03 Feb, 13:37


https://www.facebook.com/share/p/1BX2o4Xx56/

Best kerim

03 Feb, 13:15


አጅርን (ምንዳን) መተሳሰብ ድካምን ይቀንሳል

ከእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ጀርባ ከአላህ ምንዳን የምንተሳሰብበት መንፈስ ከተወገደ ለሕይወት የምናደርገው ልፋትና ድካም ኹሉ በተቃራኒው ሸክሙ ይከብደናል። ለዚህ ሲባል በየትኛውም ድርጊት፣ በንግግሮቻችን፣ በሚገጥሙን አደጋዎችና በምናሳየው ትዕግስት፣ በሚደርሱብን ጉዳቶች ኾነ ሞክረውን ባልደረሱብን ገጠመኞች ላይ ኹሉ ከአላህ ምንዳ መተሳሰብን አንርሳ።

ከዚያም ልባችን እንዲህ ማለት ይጀምራል፦

“ጌታዬ ሆይ! በሙከራዎቼ ኹሉ ከአንተ ዘንድ አለመጥፋቴ ይበቃኛል።”

ሐሳቡ ከመውላና ኢብራሒም ደሱቂይ (ቁዲሰ ሲረሁ) ሐሳቦች የተወሰደ ነው። እነዚህ ሱፍዮች ሕይወትን የተረዱበት ርቀት በጣም አስገራሚ ነው። በሁሉም ነገሮች ላይ ምንዳን የምናስብ ከሆነ እኮ ሕይወታችን አስፈላጊውን ዐቅጣጫ ይይዛል።

ምንዳ ከዘውቅ ጋር ይለግሰና

Best kerim

02 Feb, 19:35


#ከተበ_ረቡኩም_ዓላ_ነፍሲሂ_ራህማ
#አላህ_በራሱ_ላይ_እዝነትን_ጻፈ

አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ለመልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አላቸው፦ [ እነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት (ወደ አንተ) በመጡ ጊዜ

«ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ (አላህ) መሓሪ አዛኝ ነው» በላቸው፡፡]

አል–አንዓም፤54

አዛኙ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንደነገሩን
" ሁሉም የአደም ልጅ ስህተተኛ ነው። ከስህተተኞች ኹሉ በላጮቹ ማለት ደግሞ ወደ አላህ የሚመለሱት ናቸው።"

ይህን ሐዲስ በደንብ ስናስተነትነው ደግግመን በምንሰራቸው ወንጀሎች እንጂ ከቶ ምንም በማናቀውማ ከቶውኑ በአላህ እዝነት ጥላ ስራ መገኘታችንን እንረዳለን።

ጌትዬ እዝነትን በራሱ ላይ ጻፈ! ሰይዳችን አዛኝ ኾነው ተላኩ። ጀነት እኮ እምቢ ያለ ነው የሚገባው አላሉንም?!

እዚህ አንቀጽ ላይ እንቆይ ትንሽ የርሱን እዝነት ማሰብ ብቻ የተውበትን በራፍ ይከፍታል። ተውበት ወንጀል ለሚሰራ ሰው ብቻ የተደነገገ አይደለም፤ ሰይዲ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በቀን ምን ያህል ጊዜ ወደጌታቸው ይመለሳሉ?!

ከ 70 ጊዜ በላይ ....

ተውበት ማለት አሁንም፣ አሁንም፣ አሁንም ወደአላህ መመለስ ማለት ነው። ወደ አላህ የምንመለስበት ሰበብ አለን ማለት ዕድለኞች ነን ማለት ነው።

ወይ ቁርኣን ጉድ ነው

አላህ ያስረዳና ሸዕባን ነው ያ ጀማዓ እንቅራው

ሰላም ለይል

Best kerim

01 Feb, 09:44


ሰው መኖር ያለበት የራሱን ሪዝቅ ነው። የሰዎችን ሪዝቅ ለመኖር መመኘት ወይም የራስን ኑሮ ሌሎች ውስጥ በግድ ለማግኘት መጣር አደገኛ የኾነውን ነፍሲያ (EGO) ያወርሳል። ዙሪያህ/ሽ ያሉ ሰዎች በዘይቤያቸው የራሳቸውን ኑሮ እንዲኖሩ ፍቀድ/ፍቀጂ። ሰዎች እንደኛ እንዲያስቡ፣ እንደኛ እንዲኖሩ ማሰብ በተዘዋዋሪ እኛን ይኹኑ ማለት ነው። ይህ ደግሞ አደገኛ የኾነውን የነፍስ በሽታ ይፈጥራል። በዙሪያችን ያሉ ሰዎች አይደለም ልክ ነው ብለው ያመኑበትንና ያሰቡትን ቀርቶ ስህተት ላይ ቢወድቁ እንኳን የመሳሳት መብታቸውን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። እንደ ፈለጉ ይሳሳቱ ማን ፈራጅ አድርጎን ነው ስለሰዎች የምንደመድመው?!

ልክ ነን ብለን የምናስበው ኹሉ ማን አረጋግጦልን ነው የምንኮፈስበት። ብዙ ጊዜ የሰዎችን ኑሮ እኔ ካልመራሁ የሚሉ ሰዎች ወይም የራሳቸውን ኑሮ በዙሪያቸው ላይ በግድ ካላየሁ የሚሉ ሰዎች "ተሳስቻለሁ" ማለት የሚፈሩ። በፍጹም "ተሳስተው የማያውቁ" "ፍጹም" ግለሰቦች ናቸው። አንድ ሰው በራሱ ነፍሲያ የ "ፍጹምነት" ባህሪይ ከተሰማው በከፍተኛ ደረጃ ሕክምና የሚያስፈልገው ሰው ለመኾኑ ምንም ማረጋገጫ አያስፈልገውም። የትኛውም ሐሳብ ከሆነ ዕውቀት ደረጃ ያደገና የተሻሻለ እንጂ የበቃ አይደለም። ፍጹም የኾኑት የቁርኣንና የሐዲስ ቃሎች ራሱ በዘመን ቋንቋ ሐሳብ እንድንረዳ የምርምር በራፍ ከፋች ናቸው።

በእምነታች ጉዞ ላይ የነፍስን እብሪት የማናሻሽልበት ትሕትናን የማንጨምርበት፣ ስሕተተኛ መኾናችንን የማናረጋግጥ ከሆነ መንገዱ ባርነትን አያወርስም።

አላህ ያስረዳን

Best kerim

01 Feb, 09:05


https://www.facebook.com/share/p/1BRP4dqXdH/

Best kerim

31 Jan, 17:19


#የሸዕባን_ሐሳቦች

ከተሰራጩ የስሕተት አመለካከቶች መካከል ሰዎች የሚከፍሉትን ዘካ በረመዳን ብቻ እንደሚሰጥ አድርገው ማሰብ የተነዛ ምልከታ ነው። ሰዎች በዚህም ምክንያት በረመዳን ወር ብቻ ዘካ እንደሚሰጥና ምንዳውም የላቀ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ይህ ከመሆኑ ጋር ዘካ የሚከፈልበትን ጊዜ ማዘግየት አይቻልም፡፡ ዘካ የሚከፈልብትን ጊዜ ማሳለፍ በድሆች ሐቅ ላይ መተላለፍ ሲሆን እነርሱን መበደልም ነው፡፡ ዘካን ማሳለፍ ድንበር ማለፍና አላህን ማመጽም ስለሚሆን ይህን መጠንቀቅ ያሻል፡፡ በተቃራኒው ዘካን አስቀድሞ መክፈል ግን የተፈቀደ ነው፡፡ ድሆችም ሐቃቸው ቀድሞ መድረሱ ይበረታታል፡፡

በተለይ ባለንበት ጊዜ በረመዳን ምሽቶች ድሆች አምልኮ ትተው በየቦታው ገንዘብ ለመጠየቅ የሚቸገሩበትን ሒደት ለመቀነስ በዚህ ወር ዘካን መስጠት ይወደዳል።

እንግዲህ ዘካ ከፋዮች ሒሳባችሁን በባለሙያ አሰልታችሁ ለባለሐቁ መሰጠቱን ጊዜ ስለሚፈልግ በረመዳን ቢዚ ከመኾን በዚህ ወር ለመጨረስ ሞክሩ!

ዘካ ከሚያወጡት ሰኺዮች ያድርገና

Best kerim

31 Jan, 03:28


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

30 Jan, 19:39


ከተማችን ኸሚስ ምሽት በየመስጂዱ ሰለዋት ሲደምቅ ነው የሚያምርበት፤ ዛሬ ዛሬ ይህን ግርማውን ቢያነሱትም አንዳንድ መስጂዶች ላይ አሁንም ከነክብራቸው አልሉ። የኸሚስ ሰለዋት ያሉባቸው ቦታዎች ኹሉ እመኑኝ በትክክል ሰለዋቱ ይኑር እንጂ ፈሳድ በአከባቢው የመቆየት ብሎም አማኞችን የማዘናጋት ዐቅም የለውም። አንድ ስሙን የማልጠራው መንደር መስጂድ አጠገብ 100 ሜትር ክልል ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ መጠጥ ቤቶችና የሌሎች አምልኮ ቤቶች አይቼ እስካሁን እደነቃለሁ። የሚደረጉ ስብከቶችና የመድረክ ዝግጅቶች ጥሩ ገጽታ ቢፈጥሩም የሰዎችን ልብ የማንቀሳቀስ ሐይላቸው ደካማ ነውና፤ መስጂዶች በየሳምንቱ ለሚደረጉ ሰለዋቶች በራቸውን ክፍት ያድርጉ።

ቅርብ ሰአት ከአንድ አንጋፋ መስጂድ የኸሚስ ሰለዋት ሲላክልኝ ካለሁበት የተሰማኘ ደስታ ወደር አልነበረውም።

አላህ አይውሰድብና

Best kerim

30 Jan, 19:07


https://www.facebook.com/share/v/1HkPjkgdGE/

Best kerim

30 Jan, 15:49


#የሸዕባን_ማነቃቂያዎች

በረመዳን ብዙዎች ጾም፣ የለሊት ስግደትና ቁርአንን ጨርሶ ለመቅራት እንደሚቸገሩ ስሞታ ያቀርባሉ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በረመዳን እንጂ ጾም ሆነ የለሊት ስግደትን ስለማያከናውኑ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በዚህ በሸዕባን ወር ልምምድ ከማድረግ የት ናቸው?! እያሉ ዐዋቂዎች ይመክሩናል።

ነፍስ በምቾትና በእንቅልፍ ላይ ብቻ መደላደልን ከመረጠች ያለምንም ልምምድ የረመዳንን ወር ለመጾም ከሞከረች ድካምና መሰላቸት ውስጥ ለመግባት የተመቸች ትሆናለች፡፡

አቡበከር አልበኽሊይ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ፡

‹‹የረጀብ ወር ዘር የሚዘራበት ነው፡፡ የሸዕባን ወር ለተዘራው ዘር ውሃ የማጠጫ ወቅት ነው፡፡ የረመዳን ወር ሰብል የሚሰበሰብበት ጊዜ ነው፡፡››

‹‹ የረጀብ ወር ምሳሌው እንደነፋስ ነው፤ የሸዕባን ወር ደግሞ እንደጉም ነው፤ የረመዳ ወር እንደ ዝናብ ነው፡፡››

ለጣኢፍ አልማዕሪፍ፤ 121

በረጀብ ወር ያልዘራ በሸዕባን ያላጠጣ እንዴት በረመዳን ማጨድ ይችላል?! ከረመዳን በፊት ለነፍሱ ምንም ኸይር ያላስቀደመ ሰው እንዴትስ የአምልንና የመታዘዝን ጥፍጥና ማጣጣም ይችላል?! ጊዜው ሳያልፍብን በፊት እንሽቀዳደምበት፡፡

ያህያ ቢን ሙዓዝ (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ይላሉ፡ ‹‹ እኔ ለነፍሴ ሞት አላለቅስም የማለቅሰው መልካም አጋጣሚዎች ሲያልፉኝ ነው፡፡››

ሒልየቱል አውሊያእ 10/51 ሲየር 13/15

አላህ ቀላል ያሳዝናል?! ስንት መልካም አጋጣሚዎች አለፉብን ሳንጠቀምባቸው?! ይህ የሸዕባን ወር ግን አያምልጠን!!

አላህ ይረዝቀኝ፤ ይረዝቃችሁ

ሐዬ

Best kerim

30 Jan, 15:49


መልካም አጋጣሚዎች አመጣጣቸው በራሱ ያስታውቃሉ። ሸዕባን ነገ አንድ ብሎ ይጀምራል። ይህ ወር የሰይዳችን ወር ነው። የሰይዳችን ወር በኸሚስ አመሻሽ ሲገባ አንዳች የሚያመረቅን ነገር አለው።

በሰለዋትና መልካም በማሰብ ብንጀምረውስ?!

አላህ የረጀብንና የሸዕባንን ወር ይባርክልን ለረመዳን ወር ያድርሰና

Best kerim

29 Jan, 05:00


#ተፋዑል

ኢማም አሕመድ ለልጃቸው እንዲህ ሲሉ አደራ አሉት፦

« ልጄ ሆይ! መልካምን አስብ (ነይት)፤ መልካም እስካሰብክ ድረስ በመልካም ኹኔታ መኖርህ አይቀርም።»

የማትረሱት የወላጆቻችሁ መልካም ምክር በውስጣችሁ የቀረ አልለ? እርሱን ኑሩት ለልጆቻችሁም አይረሴ መልካም ምክርን ለግሱ!

Best kerim

29 Jan, 03:24


ረቢ ኢግፊር ሊ ወርሃምኒ ወቱብ ዐለይህ (70x)

Best kerim

28 Jan, 20:00


[ አላህ በሚያስተናብራቸው መልካም ነገሮች (ሑስነ ተድቢር) ውስጥ መጨረሻው ተገልጦ እስኪታይ ድረስ እንጂ የማይመሰክር ባርያ ሲያጸይፍ!]

ኢብኑ ዐጣእ (ቁዲሰ ሲረሁ)

እርሱ (አላህ) በሚሰራው ኹሉ አዋቂ ነው፤ በማይገቡንም በሚገቡንም ነገሮች ኹሉ ከርሱ ከጃዮች ነን

Best kerim

28 Jan, 19:39


አል ቁርኣኑል ከሪም ማለት ...

የድምጽ አጠቃቀም ሥርኣት ያስተማረን ነው፦ « ከድምጽህም ዝቅ አድርግ፡፡» ሉቅማን፤19
የአረማመድ ሥርኣትም እንዲሁ « «በአካኼድህም መካከለኛ ኹን፡፡» ሉቅማን፤19 «በምድርም ላይ የተንበጣረረክ ሆነህ፤ አትሂድ፡፡» ኢስራእ፤37
የእይታ ሥርኣት ሊያስተምረን እንዲህ አለ፦ « ዓይኖችህንም ከእነርሱ (ከሰዎቹ) ክፍሎችን በእርሱ ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት፤ ወደ ቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች አትዘርጋ፡፡» ጠሐ፤131 (የሰዎችን ንብረትን በመመኘት መመለከትን ከለከለ።)

አመጋገብ ላይ እንዲህ ገስጾናል ፦ « ብሉም፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ » አዕራፍ፤31

አጠቃላይ ሕይወታችን ላይ ደግሞ « እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡» ሁድ፤112

አማኞች ከዚህ ሙስሐፍ (ቁርኣን) በራቁ ቁጥር በጌታቸው የመተው ዕድላቸው ይሰፋል።

ቁርኣኑ አይተወን፣ አላህ እንዳይተወን

ቲላዋውን፣ መረዳቱን፣ መጠቃቀሙን አይውሰድብና

Best kerim

20 Jan, 07:37


የሥራ ማስታወቂያ!

በ special need ወይም psychology የተመረቀሽና በትምሕርት ቤት ውስጥ ልጆች ላይ ሙያዊ እገዛዎችን ለማድረግ ተነሳሽነት ያለሽ እህት ካለሽ በውስጥ መስመር ብታወሪኝ የሥራ ዕድሎች ምርጫ ይኖሩናል።

Best kerim

17 Jan, 19:18


ከመረጃ በላይ የኾኑ ዕውቀቶች ያስፈልጉናል። መረጃ ከዐቅማችን በላይ ሞልቶ የፈሰሰበት ዘመን ላይ ደርሰናል። የእነ ሸይኽ ጎግል ዘመን አልፎ እነ AI በሚገባ እየኸደሙ ነው። አንድ መስጂድ ከሚሰጡ መረጃዎች በተሻለና በደረጀ መልክ መረጃዎች ከእነዚህ ቦታዎች መገኘታቸውን ማስተባበል አይቻልም። ግና ተፈላጊውን ኢማን የሚያወርሱ ናቸው? የውስጥ ድርቅናን የሚያፋፍሙ አይደሉምን? በደንብ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ስለሰለዋት ብትጠይቀው ይህን የመረጃ ቋጥ ከአንድ ስለ ሰለዋት ብዙ ለማውራት ከሚከብደው ሰባኪ በላይ በተደራጀ መልኩ ያቀርብልሃል። ግና የሰለዋትን ሐይል፣ ተቅዋና ኢማንን ሊያላብስህ አይችልም። የዳዕዋና ዕውቀት ሚናው ደግሞ የሚፈለገው አለማወቅን ለማስገንዘብ፣ ፍራቻን ለማስታጠቅና ኢማንን ለማውረስ ነው። ለዚህ ነው እምነታችሁን የምትወስዱበትን ቦታ ምረጡ የተባለው። በሸሪዓችን የዐሊሞችን ሚና ከፍ ያደረገው ስለ ሸሪዓዊ ሰንሰለት ያለንን ግንዛቤ በደንብ እንድናጤን ነው። ሰለዋት በሉ ብቻ ብለው አልተዉንም አማና የሚያቁት ቀደምት ዐሊሞች እንዴት ማለት እንዳለብንም ጭምረው መንገድን አበጅተው ነው ያለፉት። ለምሳሌ ከ "ተንቢህ አልነአም" የሰለዋት ኪታብ ገጾች ውስጥ እያንዳንዱን ፈስል (ክፍል) ብትገልጥ የሰለዋቶቹ ቁጥሮች ይታወቃሉ። እንደየቦታው ይለያያል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ እስከ መቶ የዘለቁ ሰለዋቶች ታገኛለህ። ለዚህ ነው ቀደምቶቹ በቃላቸው ጭምር የሸመደዱት እንዳሉ የሚነገረው። ሰለዋቱን ሲያደራጁ ከፊቂህና ከሲራ ጋር እንዲሁም ሁለገብ ከሆነ ሸሪዓ መንገድ ጋር መኾኑ ደግሞ እንዴት አድርገው እምነቱን እንዳስጠበቁ ትረዳበታለህ። ስለዚህ የሸሪዓ ዕውቀትን ከ "ነጋዴ" እና ከአላስፈላጊ እምነትን ከሚያደርቁ ሰዎች ለመለየት ሁነኛው መንገድ የሰለዋት መንገድ መኾኑን ደጋግመን መተዋወስ አስፈላጊ ነው።

ይህ ሰለዋት ሸይኽ ለሌለው ሸይኽ ነውና በዘመን መካከል እምነትን ከጥቅምና ከፖለቲካ ከቀየጡ ሰዎች ነጥሎ ለመረዳት ኢማንን ለመጎናጸፍ ልክ እንደዑለሞቹ በዑለሞቹ የሰለዋቱ ኩቱቦች ላይ የሙጥኝ ማለት አስፈላጊ ነው።

አላህ ያግራልና

Best kerim

17 Jan, 16:29


ተሰዉፍ (ኢሕሳን) ታላቁ የደጋጎቹና የዐሪፎቹ መንገድ ነው። ሰዎች በሸሪዓ መንገድ ሊደርሱበት የሚከጅሉት ሩቅ ዓለም ነው። ሰፊው ዐለም ውስጥ ለመዝለቅ አላህን ያወቁ ዑለሞች (ዐሪፎቹ) ልምዶች (ተጅሪባት) ያስፈልገናል። የእነዚህን ደጋግ ሊቃውንቶች መንገድና መስመሮች ፈልጎ መቀጠል ለነፍስ ዕድገት ጠቃሚው መንገድ ነው።

ከኢማም ሐዳድ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ውብ ሥራዎች መካከል አንዱ የኾነውን ይህን ድንቅ ኪታብ ሸይኽ ዐብዱልሓሚድ ( አቡ ሱሀይል ) ከማብራሪያ ጋር አጠናቅሮታል። ይህንና ሌሎች የኢማም ሐዳድ ኪታቦችን ቁጭ ብዬ የመቅራት ጉጉቴን የጨመረው ይሕን ኪታብ በቋንቋችን ለማንበብ ቸኩያለሁ። ይህ መጽሐፍ ተነቦ የሚቀመጥ ሳይኾን በርካታ ውይይቶች የሚያስፈልገው መድረሳዎች ውስጥ ለመምህራንና፣ ለኡስታዞች የነፍስ ዕድገት ለተርቢያ (እነጻ) መሠረት መኾን የሚችል እንደመኾኑ። መጽሐፉ የምርቃ ፕሮግራምም ያስፈልገዋል እላለሁ።

ለወንድሜ ዐብዱልሓሚድ ጀዛከላህ ኸይር ብያለሁ!!

መልካም ምሽት!

Best kerim

16 Jan, 18:08


الرَّحْمَنُ عَلَّمَ القرآن

[አል-ረሕማን፤ ቁርኣንን አስተማረ፡፡] አል–ረሕማን፤01–02

የመካ ሰዎች አልረሕማን ማን ነው? ብለው ሲጠይቁ በመለኮት ሐይል አልሕማንማ ያ የሰውን ልጅ ያስተማረው ነው ተባሉ። አንቀጹም አልረሕማን ቁርኣንን ለሰው ልጅ አስተማረ ብሎ ገለጸ። ከሙፈሲሮቹ ውስጥ በጘዊ ይህን አንቀጽ ሲያብራሩ በጥቅሉ ቁርኣን የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አስተማረ ማለት ነው ይላሉ።

የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መውደድና ማላቅ እርሳቸውን ማወቅ ሁሉን ማወቅ ነው። እርሳቸውን መኖር ቁርኣንን መረዳት ነው። ቁርኣንን ለመረዳት እርሳቸውን ማፍቀርና በእርሳቸው ማለፍ ግድ ኾነ። ሰለዋት ነብያችንን ለማወቅ፣ እርሳቸውን ለማፍቀር፣ የከባበደንን ነገር ለመግለጥ፣ ልባዊ ብርሃንን ለማስከፈት ወሳኝ ነው።

እርሳቸው ላይ ብዙ ሰለዋት ሳናወርድ ለሊቱ አይለፍብን

አላህ ይረዝቀን

Best kerim

16 Jan, 16:48


#የዐቂዳ_ሌቦች_አይደለንም!

ሌቦቹ ገንዘብ ያየዘውን ቦርሳ ሰርቀው ሄዱ። ገንዘቡን ለመውሰድ ቦርሳውን ሲከፍቱ አንድ ጽሑፍ አገኙ እንዲህ ይላል፦ “ ጌታዬ ሆይ! ገንዘቤን አደራ ሰጥቼሃለሁና ከሌቦች ስርቆት ጠብቅልኝ።”
የሌቦቹ መሪ ይህን ጥቅስ ሲያነብ ለባልደረቦቹ ይህን ዕቃ ለባለቤቱ እንዲመለስ አዘዛቸው። በዚህ ተገርመው ምክንያት ጠየቁ።

ዐለቃቸው እንዲህ አላቸው፦ “የገንዘቡ ባለቤት በአላህ ላይ ያለው እምነት እንዳይናወጥ ነው ይህን የምናደርገው! እኛ የገንዘብ እንጂ የዐቂዳ (እምነት) ሌቦች አይደለንም።”

ከሁሉም የባሱና በጣም አደገኛ ሌቦች ማለት እምነትን የሚሰርቁት ናቸው። በዚህ ዘመን ማንነትህን፣ እምነትህን እና ሃይማኖትህን ሊሰርቁብህ የሚፈልጉ ብዙ ሌቦች አሉና ማንነትህ እንዳይሰረቅ ተንጠቀቅ።

ሰው ገንዘብና ንብረቱን ከሚጠብቀው በላይ ዐቂዳውን (ኢማኑን) መጠበቅ አለበት። ይህ ካልሆነ በእምነት ስም እምነት የሚነጥቁት ሐይላትን መቋቋም የሚመጡበትን መንገድ ሊቆጣጠረው አይችልም።

ጌትዬ ሆይ ጠብቀና

ኸሚስ ነው ወደ ሰለዋት ሐድራችን ተመልሰናል

Best kerim

16 Jan, 12:52


ነፍስን ከአላህ ጋር እንደማስታረቅ ያለ ግዙፍ ድል የለም። እየተከናወኑ ባሉ ነገሮች፥ ምንም በማይገቡን ምድራዊ ጉዳዮች ውስጥ እንደዐዋቂና አድራጊ ራስን ከማድከምና በእነዚህ የማይቋጩ ውዥንብሮች ውስጥ ከመኖር የሚሻለው ምንም ባለማወቅ ውስጥ ወደነፍስ ማተኮርና ቀን ከለሊት "ያ አላህ" ማለት ነው። በዋናነት ልትረዳው የምትችለው ትልቁ ዕውቀት ስለነፍስህ ማወቅ ነው፤ እርሱም ከገራ ነው!!

ለእርሱ መኾንን ያስረዳን፤ ከዚህች ዐለም ውጣ ውረድ ከፈተናዎቿና ከዟሊሞቿ ነጃ ይበለን።

ያስረዳን

አልላሁመ ኢግፊር ሊልሙእሚኒነ ወልሙእሚናት!!

Best kerim

15 Jan, 12:46


ሰይዲ ሸምሰ ቲብሪዝ (ቁዲሰ ሲረሁ) እንዲህ ይላሉ፦

«ባሕሩ በቆሻሻው ብዛት አይበላሽም፤ ሙሉ የኾነም በሰዎች የተለያዩ ድርጊታቸው ተጽዕኖ አይደርስበትም። በሰዎች ድርጊት የታመመ ሰው ከእነርሱ ይቅርታ ማድረጉ ሙሉነቱ ሲኾን፤ የታመመው ደግሞ ከአላህ በመጣ ነገር ኾኖ ወድዶት በመቀበሉ ይህ ፍጹም የኾነ ሙሉነቱ ማረጋገጫ ነው።»

አንድ ሰው ይህን ጥልቅ ንግግራቸውን ለመረዳት ከፈለገ ስለነፍሱ ለማወቅ መታገል አለበት፣ ስለነፍሱ ብዙ ለማወቅ የጣረ ሰው ጌታውን ለማወቅ ይታደላል። ይላል "መቃላት ሸምሰዲን ተብሪዚ" የሰኘው መጽሐፍ።

ሰዎች ጌታቸውን ለማወቅ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ዘወትር ዐቅጣጫቸው (ቂብላቸው) ሊኾን የሚገባው ነፍሳቸውን በብርቱ መያዝና መመርመር መቻል ላይ መድረሳቸውን ነው።

ረጀብ 15 ነው፤ የረቡዕ ከሰአት የመጨረሻው የዱዓ ሰአት ነው። (9:45) በተቀሩ ውብ የረጀብ ቀናት ነፍሳችንን የማንበድልበት ነፍሳችንን የምንጠይቅበትን ከሰዎች የተሸሸገ ሥራን እርሱ ይረዝቀና!!

አሚይን

Best kerim

13 Jan, 19:03


ቁርኣን ሐዘንን፣ ድባቴን፣ የማይታወቅ የውስጥ ጉድለትን የሚያባር ተዓምረኛ መጽሐፍ ነው። በዚህ ዓለም ውስጥ ስንኖር በምናውቃቸው ወይም ከቶ በቅጡ በማናቃቸው ብዙ ሰበቦች የተነሳ ድንገተኛ ድብርትና ድባቴዎች ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን። ሰው ነንና ለምን ደበረን? ለምን ሰለቸን ማለት አይቻልም። የዚህች ዐለም አንዷ ባሕሪዋ በነገሮች ጣእምና እርካታ የሚታጣባት መኾኗ ነው። ድካምና መሰለቸት ሲነካን፣ በድንገተኛ ሐዘኖች፣ በማይታወቅ መልኩ በተለያዩ ነገሮች የምንከፋ ጊዜ ወደ ቁርኣንና ሰለዋት ፊታችንን ማዞር አስገራሚ ውስጣዊ ሠላም የምናገኝበት መንገዶች መኾናቸውን ሞክረው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በየዕለቱ በተለይም ከላይ የጠቀስኳቸው ስሜቶች ሲመጡብን ቁርኣንን ለማንበብ መሞከር፣ መልእክቱን ለመረዳት መጣር፣ እንዲሁም በረጅሙ ማዳመጥ ከፍተኛ የኾነ ውስጣዊ መረጋጋትና መልስ የማግኘት ስሜቶችን ያጎናጽፋል። ሰለዋትን እንዲሁ ደጋግሞ በማለት የሰለዋት ሐድራዎችን በድምጽ ማድመጥ ከተለያዩ የስሜት ጫናዎች (stress) ለመቋቋም ምርጡና የተሞከረ መንገድ ነው።

ለምሳሌ ቅርብ ሰአት በአል ሐዲድ ምዕራፍ ውስጥ ቁጥር 22 ላይ ይህን አንቀጽ ሳነብ ነበር « በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡»

ያልተጻፈ ነገር የለም፤ ኹሉም ነገራችን መክቱብ ኾኖ ሲያበቃ የምንጨነቀው ነገር ብዛቱ?!

ይህን መረዳት የምንችለው ከአዕምሮ በላይ የኾነውን ቁርኣን በልብ ዓይን ለማንበብ መንፈሳዊ አረዳድን ለማዳበር ስንለፋ ነው! ችግሮቻችን ወደ አላህ የምናደርገውን ጉዞ እንዳይገቱብን እንጠንቀቅ!!

አላህ ያስረዳና

Best kerim

13 Jan, 11:32


የስራ ማስታወቂያ!

1– በጸሐፊነት የሥራ መደብ መሠረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀት ያላት፣ የተለያዩ ጽሑፎችን ማደራጀት የምትችል፣ የተለያዩ ለሥልጠና እና ሞጁል ሥራዎች ላይ አብራ መሥራት የምትችል፣ ከዐረብኛ እና ኢንግሊዘኛ ቋንቋዎች ጋር ጥሩ ቅርርብ ያላት እህት ካለች በውስጥ መስመር ብትጽፍልኝ ስምምነት ማድረግ እንችላለን።

2– በስፔሻል ኒድ ወይም ሳይኮሎጂ የዲግሪ ምሩቅ ካለሽም ትምሕርት ቤት ውስጥ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ካለሽ እንዲሁ ልታወሩኝ ትችላላችሁ።

Best kerim

12 Jan, 18:59


"ለእምነቴ ትግል ሳደርግ ሰላት እንኳን በቅጡ የምሰግድበት ሰአት አጣሁ። ይገርምሀል ቁርኣን ተቀምጬ ከቀራሁ ቆየሁ፣ ሰለዋት ዚክር የምንላቸው ነገሮችማ ሩቅ ናቸው። ዋናው ነገር ኡመቱ እንዲነቃ መሥራት ነው።"

እንዲህ ዐይነት ስሜት ላይ ስንደርስ አይደለም ለቡድን ለኢስላም ቢኾን ራሱ አደገኛ ሸሕዋ ላይ መኾናችንን ማስታወስ ያስፈልጋል። እዚህ ስሜት ላይ የሌለን ይመስላል? በደንብ ስራችን ሲመረመር ከዚህም የባሰ ነው። ለሊት ሙሉ ስለ መሻኢኾቹ እየተከራከርክ ብታነጋ፣ ከፈርድ ተዘናግተህ፣ ከዊርድህ ካጎደልክ ነፍስህን መልካም እየነፈግካት መኾኑን አትዘንጋ።

ረጀብ ራሕመት የሚወርድበት፣ የረመዳን ስሜትን የምናገኝበት ነው ካልን ምን ያህል የአምልኮ ልምምዶች ውስጥ አለን?! ለማንኛውም ለእምነት የምናደርገው ተጋድሎ ከኢማን ካሸሸን ከመንፈስ ካራቀን ቆም ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።

አላህ ይመልሰን

Best kerim

11 Jan, 14:44


https://www.facebook.com/share/15rKPxeQop/

Best kerim

11 Jan, 06:37


«ያኔ በሰይዳችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መስጂድ ላይ ሐበሾች ሲጨፍሩ (رقص) የነበረው እንዲህ ነበር!!»

ከሰሞኑ በሐገራችን ዐለምአቀፍ ዳዒዎች ለኮንፈረስና ለጥናታዊ ጽሑፎች ምክክር ለማድረግ መግባታቸው ይታወሳል። የመንዙማ ስርኣታችንን ሲያዩ ከላይ የለጠፍኩትን ጥቅስ በግል ድረገጻቸው ላይ ከምስል ጋር አያይዘው አጋርተውታል። ይህ በእውነት ልብን የሚያስፈነጥዝ፣ ሐገራችን በከባበዳት ሰአት ተስፋን የሚያፈነጥቅ ዳግም የሐበሾችን ክብርና መንፈስ ከፍ የሚያደርግ ንግግር ነው። ልክ ጃዕፈር ከሐበሻ መልስ በአላህ መልእክተኛ ንግግር የፈነጠዘውን ያህል ሶሪያዊ ሸይኽ ዶክተር ዐብዱልቃዲር የለጠፉትንም ይህን ጥቅስ ሳይ ዝለል ዝለል ብሎኝ ነበር። ይህ ለእኛ ክብር ነው፣ ይህ ለእኛ ግርማ ነው። ይህ ኮንፈረንስ በተለያየ ሐገር ሲደረግ የነበረና ኮንፈረሱን የመሠረቱት ዶክተር ዐውን ናቸው።

የሐበሾችን ክብርና ታላቅነት ለማሳየት ስትለፉ ለነበራችሁ ሰዎች ይህ ትልቅ ስኬታችን ነው። የሐበሻ ዑለሞች ክብርና ታሪክ አይደለም ለሐገር ለዓለም የሚተርፍ ገጸበረከት ነው።

በደንብ ተደሰቱበት

Best kerim

10 Jan, 09:05


የአሜሪካ ግዛት እንዲህ እሳት ነድዶና ቂያማ መስሎ ዐሥር ሰው ብቻ ነው የሞተው?! እኛ ሐገር እኮ ዐሥር ሰው በማይረባ ምክንያት በየጊዜው ይሞታል። አይ ልዩነት?!

አደጋን መቋቋም የሚያስችል ዝግጅታቸው ይኾን የሚያደነድናቸው?! "ዕድገት" እና "ሥልጣኔ" መንፈስ አልባ ያደርጋል መሰለኝ። ትንሽ ዐቅም ያለን የመሰለን ጊዜ፣ የምንቋቋመው ችግር እንደማይጎዳን እናምናለን። ሠለጠኑ የሚባሉ ሐገራት ችግር እንደማያሰጋቸው በየዕለቱ ተግተው ነው ያደጉት። እንደውም ለቅድመ ጥንቃቄ እንዲህ አድርጉ ሲባሉ ችላ በማለት የሚደርስ አደጋ ነው እንደ ቁጥር የሚመዘገበው። ትልቁ ችግራቸውና ረሐባቸው "መንፈሳዊ ረሐብ" ይመስለኛል። ሁሉን ማድረጋቸው ከመንፈስ ቢያርቃቸውም ቀና መንፈስ ያገኙ ጊዜ ታላቅ ተግባርን እንደሚሰሩ የምናየው እውነት ነው።

ለማንኛውም አሜሪካኖች ትላንት የሚወዱትን የ92 አመቱን ሟች ጂሚ ካርተርን እየሸኙ ነበር። በሌሎች ሐገራት ውድቀት ኢስላም አይነሰርም። ኢስላም የሚነሰረው በአማኞች ጥንካሬና መንፈስ ነው። ድል ማለትም አላህን ማግኘትና ከምድራዊ ፍላጎት ከፍ ማለት መቻል ነው። አላህ የፈለገውን ሥራ ይሰራል፣ ከደጋጎች ውስጥ ክፉዎችን፣ ከክፉዎች ውስጥ ደጋጎችን ይመዛል። እርሱ ምን እንደሚያደርግ ምን አውቀን፣ ባሪያ በእርሱስ ስራ ምን አግብቶት!

አላህ ለተበዳዮች መድረስ የሚችል ጌታ ነው። እንዴት? እርሱ ይወቅ ወይም እርሱ ያሳውቀን

Best kerim

10 Jan, 05:51


#የረጀብ_መደድ

ረጀብ ወር የአላህ ራሕመት የሚንቧቧበት ነው። እንደ ቀልድ አንድ ሳምንት አለቀ። ከሚወርደው የራሕመት የበረካ ማዕድ ምን ያህል ተቋድሰን ይኾን። እነዚህ ውድ የሚባሉ ቀናት በጣም ነው የሚሄዱት። መረጃ በማስተላለፍና መረጃ በመሰብሰብ ተጠምደናል። በዚህም የመረጃ ችግር እንደሌለብን ግልጽ ኾኗል። ሐላልና ሐራምን ሰዎች ከሞላ ጎደል አውቀዋል፣ ባይማሩ ራሱ ሕሊናቸው የተከለከለና የተፈቀደን ነገር በግልጹ ይነግራቸዋል። ሌላውኛው ቀመር ደግሞ በኑሮ ሒደት ውስጥ ሁሉም ነገር ሐላል ነው፤ ሐራም ሲቀር። (የሁሉም ነገር መሠረት ሐላል ነውና!) ሐራም የምንላቸው ነገሮች ግልጽ ከመኾናቸው የተነሳ ቆጥረን ኹላ ልንጨርሳቸው አለያ አጠቃለን ልንጨርሳቸው እንችላለን።

የሰው ልጅ በዚህ ልክ እምነቱ ቀልሎ ነገሮች በነጻነት እንዲያከናውን ገርቶለት ሲያበቃ ነፍሲያና ሸይጣን ከዚህ ሐቅ እንዲዘናጋና (ጘፍላ) ውስጥ እንዲገባ ያደርጉታል። የምናያቸው መዘናጋቶች፣ በእምነት ስም የሚሰሩ ደባዎችና ሴራዎች ኹሉ ወደ ሐቅ ዓለም (የሩሕ ዓለም) እንዳንመለስ የሚያደርጉ ማዘናጊያዎች ናቸው። የእምነቱን መሠረታዊ ፍቁድ ነገሮች እንድንጣረስ ያደርጋሉ ይህ ካልሆነ ሐራምን እንድንሰራ ያለማምዳሉ ከዚህ ካለፍን በእምነት ውስጥ በሚፈጠሩ የነፍሲያ ችግሮች ((የዝና፣ ገንዘብ፣ ስሜት) ጣጣዎች ውስጥ እንድንገባ ያደርጉናል።

ከእነዚህ ኹሉ ጣጣዎች በግለሰብ ደረጃ ለመዳን የፈለገ ሰው በሰለዋት ኃይል ባርነትን ይለማመድ። ሰለዋት ከመረጃ በዘለል የማዕሪፋ ዕውቀትን (አላህን የማወቅ) ይከፍታል።

ዕለቱ ጁምዓ ነው። የካህፍን ምዕራፍ በዕለቱ ደግጋሞ ማንበብ አልያ ማዳመጥ ይወደዳል። በምዕራፉ ውስጥ ያሉት ዋና ሁለት ተዋኒያን ሰይድና ሙሳ እና ሰይድና ኸድር ውስጥ ብዙ እንማራለን። ሰይድና ሙሳ ታላቅ ነብይ ናቸው። ሰይድና ኸድር ደግሞ ፍጹም የኾኑ የአላህ ባርያ ናቸው።

ባርያ መኾን ምድር ላይ ካለ ከየትኛውም ማዕረግ በላጭ መኾኑን የምንማርበት ምዕራፍ ነው። ይህንን ደግሞ የመልእክተኞች ኹሉ ቁንጮ የኾኑ ሰይዲ ወቁድወቲ ነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከንግስና ባርነትን መርጠው አሳይተውናል። በማግኘት፣ በመቆጣጠር፣ የሰዎች ላይ የበላይ በመኾን የሚገኝ እረፍት የለም። በዚህ ውስጥም ውስጥን ማዳን ከባድ ነው። በማጣት፣ ባርነትን ለአላህ በማጽደቅ፣ ከእርሱ ጋር በመኾን የሚገኘው ክብር ግን ኃይል ነው።

ረጀብ ነው ኢስቲግፋር እናብዛ፣ ጁምዓ ነው በሰለዋት እንበረታ ካህፍን በማንበብ ከዋሻው ውስጥ ጥቂት ማዕሪፋን ለመውሰድ እንጣር።

ጁምዓ ሙባረክ

Best kerim

08 Jan, 18:14


#ሲድቅ_ማዓ_አላህ

ከአላህ ጋር ያለ ሲድቅ (እውነተኝነት)

አንድ ባሪያ አላህ ዘንድ እውነተኛ ለመኾኑ የሚከተሉት ከዋና ምልክቶች ናቸው ይላሉ።

አንድ የአላህ ባርያ የሚደርስበትን አደጋ እና ለአላህ የሚያደርገውን ትዕዛዛት ኹሉ ፍጡራን ዘንድ መታየቱን በመጥላት መሸሸጉ ከፈጣሪ ጋር እውነተኛ መኾኖኑን አመላካች ነው።

ቀጥለው እንዲህ አሉ፦

አላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ለሰይድና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) በወሕይ (መለኮት) እንዲህ አላቸው፦

« ባርያዬን ስወደው እውነተኛ መኾኑን ለመመልከት ተራራዎች መሸከም የማይችሉትን መከራ አሸክመዋለሁ። በዚህም ታጋሽ ኾኖ ያገኘሁት ጊዜ ወዳጄና አጋሬ አድርጌ ይዘዋለሁ። በገጠመው ነገር ጭንቅ ውስጥ በመግባት ፍጡራኑ መካከል እኔ ላይ ሲያማርር ካገኘሁት ደግሞ እነርሱ ዘንድ ዝቅ አድርጌው ችላ እለዋለሁ።»

ምንጭ ፦ [መጠየቱ ሳሊኪን]
መውላና ዓሪፊ ቢላህ ሸይኽ አሕመድ ጣሂር አልሓሚዲይ (ረዲየላሁ ዓንህ)

አንዳንዴ የሚገጥሙን መከራዎች ከአላህ ዘንድ የመጡ የምንታነጽባቸው መንገዶች ይኾናሉ። ራሳቻችንን ለማወቅ፣ ስለራሳችን እውነተኛ ዕውቀት እንዲኖረን ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል አንዱ በዚህች ዓለም ውስጥ በተለያዩ ነገሮች መፈተናችን ነው። መከራዎችን ማግኘትን መመኘት የለብንም ይኾናል፤ ግና በቀናት መካከል በሚገጥሙን መከራዎች መካከል፣ በሕመሞቻችን ውስጥ ብርሀን እንዳለ ማወቅ ይኖርብናል። ችግሮች ሲነኩን አላህ ጋር የምናወራበት ጥሩ አጋጣሚ መኾኑን አንርሳ። ስላጣናቸው ነገሮች እርሱ ዘንድ ማውራትን ስንለማመድ ከጉዳዩ በላይ አላህ ጋር አብሮነትን በውስጣችን ዘልቆ ይገባል። ሰይድና ያዕቁብ ለአመታት የልጃቸውን መጥፋት ጀምሮ ከአላህ ጋር ሲያወሩ መፍትሔ የከጀሉትም ከርሱ ነበርና በሕምምና ሐዘናቸው ውስጥ ከእርሱ ጋር ማውራትን ከእርሱ ጋር መኖርን አጣጣሙ።

ጌታዬ ሆይ በሚነኩን ችግሮች አንተኑ ብቻ የምናወራ አድርገን

Best kerim

08 Jan, 03:26


ምድር ስበቷ ኃይለኛ ነው። ልክ ከሞቀ ዕንቅልፍ ለመንቃት የሚከብደውን ያህል። የመሬት ስበት በውስጧ ባሉ ነገሮች እንድንወዘፍ የሚያደርግ ነው። በምድር ውስጥ ያሉ የኑሮ ጣጣዎች፣ ውጣ ውረዱ፣ ጭንቀት ሐሳቡ ኹሉ ከስበት ነው። ለዚህ ነው የፈጅር ሰላት ላይ ሙኣዚኑ " አሰላቱ ኸይሩን ሚንነውም" ብሎ የሚጠራን። እውነት ነው ሰላት ከዕንቅልፍ ትበልጣለች። አንድ ሰው በአምልኮ ትክክለኛው ዘውቅ ላይ ከደረሰ ሰዎች ምድር ላይ የሚያስጨንቃቸው ነገር ለእርሱ አያስጨንቀውም። ለኢማን የሚኾንህን ነዳጅ ጨምር ከምድራዊ ስበት ትጠበቃለህ። ይህ ወቅት ለሕይወትህ አስፈላጊው ኃይልህ ነው።

አላህ የፈጅር ወቅትን በረከት አይከልክለን

Best kerim

07 Jan, 16:52


የሰለዋት ኃይል

ሰለዋት በየትኛውም ሁኔታችን ውስጥ ያለ ጠንካራ መሠረታችን ነው። ሰለዋት ዚክር ነው፣ ሰለዋት መድሐኒት ነው፣ ሰለዋት ዱዓም ነው፣ ሰለዋት በአጠቃላይ ነብያዊ ኃያል ድምጽ ነው። ሰለዋት ላይ የተጠመደ ሰው የሚያጣው ልባዊ እርካታ የለም። ሰለዋት የተደበቀ ሐጃን ማውጪያ ስልት ነው። ይህ ነብያዊ ድምጽ ከፍ ሲል በውስጣችን ያለ ተውሒድ ይፋፋል፣ አምልኮዎች ይገራሉ፣ መረዳቶች ይመጣሉ፣ መንፈሳዊ በረከቶች ይሰፋሉ። በተቃራኒው ነብያዊ ድምጽ (ሰለዋት) ሲቀንስና በልኩ ከእኛ ከራቀ የእምነት መረጃዎች ውስጣችን ኢማን ለመዝራት ሩቅ ይኾናል፣ መንፈሳዊ ልምምዶች ትክክለኛ ትርጉማቸውን ያጣሉ፣ የተለያዩ ድምጾች እኛ ልብ ውስጥ ይገዝፋሉ።

ለዚህ ነው በእያንዳንዱ ዚክሮቻችንና ዱዓዎቻችን ውስጥ የዓለሙን ኑር ላይ ሰለዋት የምናወርደው። በየዕለቱ የሰለዋት ዊርዳችንን እናጠናክር፤ መንገዳችን ላይ ለሚገጥመን ብዥታም መፍትሔ የምናገኝበት ነው።

አላህ ይረዝቀን

اللهم صل على محمد عدد الرمل والحصى، في مستقر الأرضين شرقها وغربها وسهلها وجبالها، من يوم خلقت الدنيا إلى يوم القيامة، في كل يوم ألف مرة .

Best kerim

06 Jan, 04:24


ዕለትህን በሹክርና ሰብር (በምስጋና እና ትዕግስት) ጀምረው። አላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) የለገሰህን መልካም ነገር ኹሉ ከሌሎች ጋር ሳታነጻጽር ተደሰትበት፤ በገጠመህ ችግር ዛሬን ደህና ከሆንክ አመሰግን። ነገ "ምን ይፈጠር ይኾን?" የሚለውን ወስዋስ ከአዕምሮህ አስወግድ ዛሬህ ማለት ከቀናት በፊት ነገ የምትለው ነበር። ይህ ዛሬህን አንተ አልፈጠርከውምና ነገህንም ለሚሰራልህ አምላክ እጅህን በመስጠት ልብህን አሳርፍ።

ያ ለጢፍ

Best kerim

06 Jan, 03:40


«ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ»
አልዘልዘላህ፤03

መሬት ስትንቀጠቀጥ፣ ሸክሞችዋን ስታወጣ ሰዎች ተደንቀው ምን ኾነች ይህች መሬት እያሉ እንደሚጠይቁ ቁርኣን ይነግረናል። መሬት ስትርገፈገፍ ከሰማን ሞትና ዕለተ ትንሳኤ እኛ ዘንድ ቅርብ እንደኾነ በመረዳት ለፍጻሜያችን መጨነቅ እንጂ ከሞት የምናመልጥበት ነገር ላይ ከልክ በላይ መጨነቅ አግባብ አይደለም። በየቀኑ የሚሰማውን ንዘረት ከሰማን የሞትን ያህል ማሰብ እንጂ በጥንቃቄ ከሞት የተረፍን ያህል ስለጉዳዩ ዐቅም አልባ ትንተና ውስጥ መግባት አስፈላጊ አይደለም። ይህ ቀልብ የሚያደርቅ ነገር ነውና ሞት ሐቅ መኾኑን አውቆ ለአላህ ሥራን በማቅረብ፣ ልብን ማጽዳት አስፈላጊ ነው።

አላህ መልካም ሥራ ይለግሰን

Best kerim

05 Jan, 19:50


የሐገራችን አንጋፋ የሱፍይ ሊቃውንቶች የኢስላም ታሪክ ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ታላቅ ነው። ታሪካቸውን መጠበቅ የሚቻለው መንገዳቸውን በመቁረጥና መንገዳቸውን በማስተባበል አይደለም። ለዓመታት የሐበሻ ሊቃውንት (ሱፍዮችን) መሳደብ ብሎም አመለካከታቸውን ከእስልምና ያፈነገጠ አካል አድርገው የሚስሉ ሰዎች ንግግሮቻቸው እንደ እምነት ሲያዝ ተመልክተናል።

ዛሬ ላይ በሚድያ ሐይል አንድ ቀደምት የሱፍይን ዑለማ ከእስልምና የወጣ ያህል እንዲታይ የማድረጉን ስራ በሚገባ የሰሩ አፈጮሌዎች "የእምነቱ ሊቃውንት" መስለውም ተሰርተዋል። የቀደሙት መሻኢኾች የስድብና የክህደት ናዳ ሲቀበሉ በዝምታ ከማለፍ ውጭ ለሚሰነዘርባቸው ከባባድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ምላሽ ከመስጠት በመቆጠባቸው የተነሳ ለማሕበረሰባቸው ትዕግስትን አስተምረው አልፈዋል። (እነ ሐጂ ዘይኔ፣ እነ ሸይኽ ራፊዕ፣ እነ ሐጂ ሙሳ ኪኪያን .....)

ሲሰድቧቸው የሚመልሱበት ሐይል ቢኖራቸውም ለሰዳቢያቸው ዱዓ የሚያደርጉ ደጋጎች ነበሩ። ዛሬም ድረስ እነዚህን ዑለማዎችና የያዙትን አመለካከት በሚድያዎቻቸው ሲኮንኑ "ሚዛናዊ" ተብለው ስም ተሰጥቷቸውም ተመልክተናል። ድንገት ከዝምታህ ስትባንና በክህደት መፈራረጅ ልክ አይደለም ብለህ ስታስተምር በራስህን መንገድ ዳዕዋህን ልታስቀጥል ስትጥር እነዚህ የስድብ ባለሙያዎች ብዕሮቻቸውን ያሾሉልሃል።

የደጋግ ቀደምት ዑለሞቹን መንገድ ማስቀጠል ሐገርን፣ ክብርን፣ በረከትን ማስቀጠል ነው። ደካማ አመለካከትን ከማይሞተው ግዙፍ የታሪክና የሰንሰለት ባለቤት ጋር መለካካት ልክ አይደለም። ነገሩ እነዚህ ዑለሞችን መረዳት የሚያስችል ዐቅም ስለሌ ሰዎች ስድብ ይቀናቸዋል ሌላ ኾኖ አይደለም።

የምትጽፍበት ገጽህ መዝገብህ ነው፣ ዑለማ አትስደብ የምታቀውን ለመጻፍ የማታቀውን ነገር አትንካ፣ የማይገቡህ ጉዳዮች ላይ ዘልቀህ ለመጻፍ አትጣር፣ የፖለቲካና ጥቅማዊ ፍላጎትህን በእምነት ውስጥ ለማሳካት አትልፋ!!

አላህ ያስረዳህ

Best kerim

05 Jan, 18:25


ዑለማዎች (ዐሪፎች) ሁሌም የአማኞችን መንፈሳዊ ልዕልና ሞራል ለማሳደግ ይደክማሉ። አላህ ካሳወቃቸው ብዙ ዕውቀቶችም ሳይሰስቱ ብዙ ያካፍላሉ። እውነተኛ ዓሊሞች ለማሕበረሰብ ጥቅም ይቆማሉ እንጂ በሚመሩት ማሕበረሰብ ለመጠቀም አይሰሩም። ኢማም ሐዳድ (ቁዲሰ ሲረሁ) በቅርብ አመታት ያወቅኳቸው እያንዳንዱ ከላማቸው በውስጤ ላይ ሕይወት የሚዘሩልኝ ድንቅ ሸይኽ ናቸው። የትኛውንም መንፈሳዊ ልምላሜ ስትፈልጉ እርሳቸው መልስ አለላችሁ። ዑለማ ቢያልፍም ሐይ መኾኑ የሚገባህ እንዲህ ሲገጥምህ ነው። ወሩ ረጀብ ነው፤ ታላቅ ወር ለመኾኑ በየመስጂዱ ካለው ስብከት አዳምጠን ይኾናል። ታላላቅ የሚባሉ ቀናትን የበለጠ የምትረዳበት መንፈሳዊ ልምምዶችን ካላሳዩህ ዕውቀት ብቻውን ሊጠቅምህ አይችልም። በዚህ ረገድ መልካም ነገርን መጠቆምና ማስተማር የማይደክመውን ሸይኽ ዓዲልን ደጋግሞ ማመስገን ያስፈልጋል።

ይህን ያያዝኩትን የረጀብ ኢስቲግፋር ኪታብ ከሸይኻችን ጋር ዘከርን አላህ ይቀበለን። በመጨረሻ ላይ ያለውንም ዚክር በየምሽቱ ብንለው ተወዳጅ ነው።

አላህ ያስዳና

Best kerim

05 Jan, 15:54


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

04 Jan, 19:43


« ከሰማይም ቁራጭን (በእነርሱ ላይ) ወዳቂ ኾኖ ቢያዩ ኖሮ «ይህ የተደራረበ ደመና ነው» ይሉ ነበር፡፡» አጡር፤44

የመካ ከሐዲያን ዓይነ ደረቆች ነበሩ፤ ማስተባበል ይወዱ ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይዘውት ከመጡት መልእክት ጀምሮ እነርሱ ላይ የሚደርስባቸውን ችግሮች ጨምሮ በሹፈት ይመልሱ ነበር። ስለ አላህ፣ ስለ መላእክት፣ ስለቅጣቱም በዚህ ዘመን አማኝ አይደለሁም ብለው ከሚያነሱት የከረረ በአዕምሮ የታወረን ጥያቄ ያነሱ ነበር። በሐቅ ማስተባበል፣ እውነታን መካድ፣ ያሉ ነገሮችን በደረቁ አዕምሮ መሞገት እንደቁረይሾች፣ እንደ በኒ ኢስራኤሎች የተሟገተም የለም። ከሰማይ የሚላኩ ቅጣቶችን፣ አላህን እንድንፈራውና እንድንጠነቀቅ የሚያደርጉ መልእክቶችን ለመረዳት ሰፊ ልብ፣ ኢማንና የኢማን ብርሃን የነካው አዕምሮ ነው የሚያስፈልገው። በማይስፈልጉ ጉዳዮች አዕምሮን መወጠር የክህደትን ቁልቁለት፣ የእምነትን ድርቀት ነው የሚያወርሰው።

የመካ ከሐዲያን የሰማይ ቁራጭ እነርሱ ላይ ቢወድቅ ይህ ደመና ነው ብሎ ከማሾፍ ወደ ኃላ አይመለሱም። በስንት መንፈሳዊ ነገሮች እንደቀለድን፣ ቁሳዊና የሚታዩ ነገሮችን በውስጣችን እንዳገዘፍን ልብ ማለት ተገቢ ነው።

ምንም እንኳን ቁርኣኑ ለመካ ከሐዲያን ቢኾንም መልእክቱ ለማንም ይሰራልና በአንቀጹ ላይ ቆሞ ራስን መፈተሽን ይወፍቀን።

አላህ ይጠብቀን፣ ያስረዳን

Best kerim

04 Jan, 14:10


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

04 Jan, 12:46


በሕብረት መሥራት፣ በሕብረት አምልኮ ማከናወን በጣም ጥሩና የሚበረታታ ነገር ነው። አላህም እገዛው ያለው በጥሩ ነገር ከሚተባበሩ ሕብረቶች ጋር ነው። በሕብረት ማሰብ ግን መንጋዊነትን ያበረታታል። በተለይም ድርጅታዊና ፖለቲካዊ ነገሮች ላይ በሕብረት የማሰብና በሰዎች አዕምሮ ማውራት ስሜታዊ እንድንኾን ያደርገናል። ኸልዋ (መነጠል) የሚወደድባቸው አጋጣሚዎችም እንዳሉ ማሰብ ደግ ነው።

ከሰዎች ጋር ልቅ በኾኑ ሁኔታዎች መቀላቀል የራስን ማንነትና ክብር ያሳጣል፣ ወደ ጥፋትም ይወስዳል። ሰዎች በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሲኾኑ ለብቻቸውም ኾነ ከሰዎች ጋር ሲቀላቀሉ ሁልጊዜም ከነፍሳቸው ጋር መኾናቸውን መላልሰው ካላረጋገጡ ማንነታቸውን በቀላሉ ሊያጡት ይችላሉ።

አንድ ሰው መኾን የሚችለው ራሱን ነው፣ የሚከተለውን ግለሰብ ወይም ቡድን አይደለም። ራሱን ለመፈተሽ ዕድል የሚኖረው፣ ከመንጋ አስተሳብ መራቁን የሚያረጋግጠው ከራሱ ጋር በጥሞና ማውራት ሲችል ነው። ከየትኛውም ነገር (ወሬና ሐሳብ) ነጠል ብሎ ራስን ማየትና ስለራስ የተሰራውን መልክ ማረም የሁልጊዜም ሥራችን ካልኾነ ይህ በቡድን የመነዳት አባዜ በቀላሉ የሚለቅ አይደለም። ሰዎች ኹሉ ስላወሩለት ጉዳይ የማውራት ግዴታ የለብህም፣ በተነሳው አጀንዳ ኹሉ የመስማማት ግዴታ የለብህም፣ አንተም የራስህ አቋምና ሐሳብ አለህ።

እራሳችንን ለማየት ቁርጠኛ ካልሆንን ሁሌ የሌሎች ድቤ መኾናችን አይቀሬ ነው። ሰዎችን መውደድና ለእነርሱ ድጋፍ ማድረግ አብሮነትን ማሳየት ልክ ቢኾንም ራስን ሲያሳጣ ግን በሽታ ነው።

መልካም ቅዳሜ

Best kerim

04 Jan, 03:52


የዛሬ አመት ረጀብ የኢስራእና ሚዕራጅ ዕለት ሲቃረብ አንድ ጁምዓ ላይ በኒን (ኑር) መስጂድ ለጁምዓ ተከስቼ ነበር። ሙፍቲያችን ስለ ኢስራዕ ወልሚዕራጅ ተዓምረኛ ለሊት አስገራሚ ትንተና የትም ሰምቼው ማላውቀውን ጥልቅ አለም ሲያስቃኙን በጣም ተገርሜ ወጣሁ። በጊዜው አንድ ሸይኼ ጋር ስወያይበት አንድ ጥልቅ ኪታብ ጠቁሙኝና ፈልጌ አገኘሁት ባለ ብዙ ሙጀለድና ትልቅ ተፍሲር ኾኖ አገኘሁት። የኢስራእን ምእራፍ ልመለከት ከፈትኩት ሙሉ ረቂቁን ሳነብ ሙፍቲ የተነተኑትን አገኘሁ። ስለዚህ ኪታብ ሸይኼ ሲያወሩኝ ችሎ የሚተነትነውም ሰው የለም ብለው ነግረውኝ ነበር። ኪታቡንም ለማየት ስሞክር በማዕሪፋ ዒልሞች ተሞልቶ አገኘሁት። ኪታቡ የፋርሶቹን ንጉሶች የኾኑትን እነ ሰይድና ሩሚን ውብ ትንተናዎችና ኩቱቦች ውስጥ ማጣቀሻም ኾነው አየሁ። በፋርስ የተጻፉ ግጥሞችንም ኹላ አካቷል። እጅግ ዕምቅና ኢማን ቀስቃሽ ዕውቀት መለገስ መቻል በጣም ውዱ ነገር ነው። መሰል ዕውቀቶችን ነበር ለ50 አመታትና ከዚያ በላይ ማሕበረሰብን የመገቡት። የተዘወቀ ሰው ያውቃል ይላሉ። አንድ ሰው አወቀ የሚባለው ማንም ሰው አንብቦ ከሚረዳው ጀርባ የሚገኙ ማዕሪፋዎችን (አላህን ማወቅን) ሲሰጠው ነው። በጊዜያችን የመረጃ ዕጥረት የለብንም፣ የአዋቂም እንዲሁ፤ ማዕሪፋን ተሰጥቷቸው ለሰው የሚያሳውቁ ሰዎች እኛ ውስጥ ከሌሉ ኢማን አይገባንም፣ ጀነት አይናፍቀንም፣ ለሞት አንዘጋጅም። ያለንበት ጊዜ ከየትኛውም ትርምስ የምንድነው ውስጣዊ ስክነት ስናገኝ ነው። ወደ ዑለሞች ዘንድ እንጠጋ፣ ወደእነርሱ ይቅርታ እናቅርብ፣ ምንም ያደግን ቢመስለን ከእነርሱና ከዓለማቸው አላዋቂ እንደኾንን እናውጅ!!

ዑለማን ከማስቆጣት፣ ዑለማን ከማሳዘን አላህ ይጠብቀን!

አላህ ያስረዳን

Best kerim

03 Jan, 06:30


ሙሐመዱን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)

እርሳቸውን ማስታወስ ለነፍሳችን ስክነት ነው፣ እርሳቸውን ማመስገን ደግሞ በሕዝቦች ላይ ግድ ተደረገ። ሰይዲ የዚህ ዓለም ጌጥና ደስታችን፣ ሰይዲ የጭንቅንና በደል ኹሉ አስወጋጅ ....

እያለ ይቀጥላል

ቡርዳ ሙባረክ

Best kerim

31 Dec, 18:50


የተከበረው የረጀብ ወርን በተመለከተ በዑስታዝ ዓዲል live በመዲንቱል ዑሉም የቴሌግራ ገልፅ ገብተው ይከታተሉ👇

https://t.me/medinetululoom

Best kerim

31 Dec, 18:47


አላህ ብቻ ከሚያቀው ወንጀል፣ ደጋግመን ወደርሱ በመመለስ ውስጥ ፈጽሞ መተው ካቃተን ጥፋት፣ ከዚህ ቀደም አጥፍን አላህ ግን በጥፋቱ ምትክ ጸጋ ስለዋለልን ብዙ ማዕሲያ፣ አሁንም እርሱ ድንበር ላይ እየተላለፍን በተቃራኒው እርሱ በጸጋ ላይ ጸጋን ስላነባበረልን ምሕረት እንለምነዋለን። ጌታችን ሆይ! እያጠፋን ስለምትውልን ጸጋ ኢስቲድራጅ (ለሌላ ታላቅ አደጋ ማመቻቸት) ውስጥ እንዳንገባም በምሕረትህ እንማጸንሐለን።

አስተግፊሩላ ወአቱቡ ኢለይህ

Best kerim

31 Dec, 18:31


Channel photo updated

Best kerim

31 Dec, 18:29


ረጀብ የኢስቲግፋር (ምሕረት መለመኛ) ወር ነው። ሻዕባን የሰለዋት ዓለ ረሱል ወር ነው። ረመዳን ደግሞ የቁርኣን ወር ነው። ከነገ ጀምሮ ለረመዳን የምንሰነቅበት፣ ውስጣችንን የምናጸዳበት ታላቅ መንፈሳዊ ንግድን የምናከናውንበት ወር ነው። በረጀብ የሰራነውን በሻዕባን የምንጠብቅበትና እንክብካቤ የምናደርግበት ወር ነው። ረመዳን የሥራ ውጤት የሚሰበሰብበት ነው። ረመዳን የተለያዩ መንፈሳዊ ተግባራትን የምንለማመድበት ወር አይደለም። የምግብ ዓይነቶችንም በመብላት የምንዝናናበት፣ በኢፍጣር ቢዚ የምንኾንበት ጊዜ አይደለም። የተለያዩ በረመዳን ወቅት የሚጠምዱንን ነገሮች በረጀብ ወር አዘጋጅትን መጨረስ አለብን። ይህን በየቤቱ መወያየት ረመዳንን በተለያዩ ነገሮች የመጠመድን መጤ ቢድዓ ለማስወገድ መስራት ተገቢ ነው።

ዘወትር ከኢሻ በኋላ በዚህ ወር "ረቢ ኢግፊሪሊ ወርሓምኒ ወቱብ ዐለየ ” የሚለውን ዚክር 70 ጊዜ እንበለው!

አላህ የአምልኮና የዚክሮችን በረካ ይለግሰን

Best kerim

31 Dec, 17:41


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

31 Dec, 17:38


አንድ ነገር በመሀል ትዝ አለኝ ...

ያለፈው አመት የተወሰኑ ተማሪዎች የኾኑ ፓርቲ ማዘጋጀት ፈለጉና ቀርቤ አናገርኳቸው። ፍላጎታቸውን በድንብ ስለተረዳሁ በቃ ዋናው መዝናናት ነው የፈለጉት በማለት የተወሰነ ሐሳብ አቀረብኩላቸው። ካቀርብኩላቸው የመዝናኛ ፕሮግራሞች መካከል የመንዙማና ነሺዳ ሐሳብ ነበር። ሙዓዝን ላምጣላችሁና በዛውም እሴታችሁን ሳትለቁ መዝናናት ትችላላችሁ አልኳቸው። የተወሰኑ ሻል ያሉ ልጆች መጡና በጣም ጥሩ ሐሳብ እንዳቀርብኩ በአክብሮት ከገለጹልኝ በኋላ መንዙማ ኺላፍ ይፈጥራል አሉኝ። እንዴት ብዬ ጠየቅኩ? ቢድዓ እንደኾነ በሚገባ ገለጹልኝ። ተማሪዎቹ እኮ በዲጄ የመጨፈር ፕሮግራም ነው ያወጡት፣ ሲቀጥል ምንም አይነት የሰለዋት ፕሮግራምም ኾነ መንፈሳዊ ልምምድ አላዳበሩም። በመውሊድና መንዙማ መሰባሰብን፣ የተለያዩ መንፈሳዊ ልምምዶችን ግን እንዳይቀበሉ ተደርገው ተሰርተዋል።

ብዙ ሰው የጃንዋሪን ዕለት አቀባበል በነጻነት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለመቀባበል አይሳቀቅም። ስለረጀብ ወር ለማውራት ስለሚባሉ ዱዓዎች ለማውራት ግን በቢድዓ ስም እፍረትና መሸማቀቅ ይዞት ይታይል። ታዲያ የዑለማዎችን መንፈሳዊ ልምምዶች ኹሉ በቢድዓና ሺርክ የሚፈርጀው ዕሳቤ አላማው ዛሬም አልተገለጸልህም?!!

ለማንኛውም ወደ ክቡሩ ለይል መመለስ ያስፈልጋል መሰል ሐሳቡ እንዳለ እዚሁ ይኑር

Best kerim

31 Dec, 17:16


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

31 Dec, 12:24


የዛሬን ለሊት እንዲሁ እንደሌላ ቀናት አናሳልፈው። ዱዓዎች፣ ልምናዎችን እናቅርብ። ለቤተሰቡ ሰፋ ሰፋ እናድርግ። ረጀብን በንጹሕ ልብ እንቀበለው። ዑለማዎች በዚህ ለሊት ይህን ዱዓ ይሉ ነበር። ከመግሪብ በኋላ ባሉ መቀማመጦቻችን ውስጥ ዱዓውን ተውሰን ወደአላህ የተማጽኖ ድምጽ እናቅርብ።

አላህ ይወፍቀን

Best kerim

31 Dec, 12:14


ዛሬ ምሽት የምንለው ዱዓ ይህንን ነው። በአላህ ፈቃድ በላይቭ ሥርጭት ምሽት ላይ አስተላልፋለሁ።

Best kerim

31 Dec, 07:30


ነገ ረጀብ አንድ ብሎ ይጀምራል። ዛሬ ምሽት ከመግሪብ ጀምሮ እስከ ፈጅር ድረስ ዱዓ መቅቡል ከተደረገባቸው አምስት ለሊቶች መካከል አንዱ ነው።

እንደተፋዑል ጃንዋሪ 01/2025 ነገ ነው። ረጀብ አንድም ነገ ይጀምራል። በነጮቹ የአመቱ መጀመሪያ ዕለት የሻዕባንና የረመዳን ዋዜማ ወር የኾነውን ረጀብን እንጀምራለን። ወሩን በተለዩ አምልኮዎች ለማጌጥ ኒያችንን ከፍ በማድረግ እንጀምር። ለሊቱ ላይ የሚባሉ ዱዓዎችን በቴሌግራም ቻናሌ ላይ የማጋራ ይኾናል።

መልካም ውሎ

Best kerim

30 Dec, 17:28


የሰዎች ልብ ውስጥ በይበልጥ የገዘፈው ነገር "ጌታ" ለመኾን የቀረበ ነው። ሰዎች ራሳቸውን ለማወቅ ካልታገሉ። የፈለገ ቢማሩ፣ የፈለገ ሐይማኖተኛ ቢኾኑ አንደበታቸውና ገጽታቸው እነርሱን አይገልጽም። ሰዎች በሌሎች ዘንድ የሚፈልጉትን የቅቡልነት ፍላጎት፣ ሌሎችን የመቆጣጠር ስሜት፣ ሁሉንም ነገር ይገባኛል የሚል ነፍሲያ ሐቅ ላይ እንዳሉ በማሳየት ይጋርድባቸዋል። ይህ በነፍሲያ የመታለል አባዜ አላህንም ጭምር መርሳትን ያለማምዳቸዋል።

ሰዎች መስጂዶችን ሞልተው፣ ልዩ አልባሳትን ለብሰው አሸብርቀውና ደምቀው መላእክት መስለው ሲታዩ በክፋት በኩል የሚያልፉም አይመስሉም። ግና ከነጫጭ ጀለቢያዎች ጀርባ ያለውን ሰውን የመጥላት፣ ሰው ላይ የማሴርን፣ ሰው ላይ የመመቅኘትን ወኔ ማን ይኾን ያለበሳቸው?!

ሸይጣን???

መስጂድ ገብተው፣ ሰግደው፣ አንዳንዴም ጾምው፣ ከዚህም አልፎ ዑምራና ሐጅ ተመላልሰው?!

ሸይጣን አይደለም ያስቸገረን በዋናነት ያስቸገረን የገዛ ነፍሲያችን ነው። የአምልኮ ግብ ሳይገባን መስጂዶችን አጨናነቅን፣ በሰለዋትና ዚክር የሚለዝበውን ማንነታችንን በሚድያ ዲን ቀየርን። ለልባችን የሚጠቅሙ ሙረቢዎችን (መምህራንን) ኋላ ቀር ብለን የሚያብረቀርቁ የቲክቶክና የሚድያ ሸይኾችን ተከተልን። ውጪያችን የሚያበራ ውስጣችን የጨለመ ማንነት ወረስን።

ፖለቲከኞች እየተቀደሱ መንፈሳዊ ግለሰቦችን በንቀት ከቦታቸው በውርደት እንዲገፈተሩ ተደረገ። በፍጥነትም የገፈቱ ቀማሽ ኾንን ዛሬ መንፈሳዊነት ርቆናል፣ ኪታብ ብንሰበስብ፣ ዕውቀት ብናከማች ኢጃዛ (ፈቃድ) ከሌለ ዘውቁ ከየት ይመጣል። ዛሬም አልረፈደም በመረጃ ብዛት ያከማቸነው ሐይማኖት በሕይወታችን ውስጥ እንዲሰራ ከፈለግን ለልብ የሚኾነንን ዑለማ እንፈልግ። ፊታችንን ወደ ሰለዋት፣ ዱዓ እና ዚክር እንመልስ። ከልባችን ውስጥ ከገቡ ጣኦቶች ንሰሐ እንግባ።

አላህ ያስረዳን

Best kerim

30 Dec, 17:04


በ special need ወይም Psychology የተመረቅሽ በልጆች ልዩ ፍላጎት ላይ የመሥራት ተነሳሽነት ያለሽ እህት ካለሽ በውስጥ ልታወሪኝ ትችያለሽ።

Best kerim

29 Dec, 18:29


ቲክቶክ የለኝም ምን እንደሚከናወንም አላውቅም። በአደብ መጠቀም ይቻላል ብለው ሊያሳምኑኝ የሚጥሩት ጓዶቼ ሊያስረዱኝ ይጥራሉ። ብዙ ነገር እረዳቸዋለሁ። ቲክቶክ ባለመክፈቴ ግን ምንም ቀርቶብኝ አያውቅም። አንዳንዴ ጥሩ ጥሩ ቀደዳዎችና ቀልዶች እንዳመለጡኝ ይሰማኛል። እነርሱም ተሸራርፈው ፌስቡክ ላይ አያቸዋለሁ። ትዝም የሚለኝ ከሰው ጋር ስቀላቀልና ሲያወሩኝ ነው ትዝ የሚለኝ።

ከሰሞኑ አንድ ፌስቡክ ሪል ላይ አንድ በድ*ቁ*ርናው የምገረምበት ሰው ሞዴል ተደርጎ ቃለመጠይቅ ሲደረግለት አየሁ። ልጁ ጆሮውን ደፍኖ ማይምነቱን ለአመታት በመርጨቱ በሚገርም ኹኔታ ታዋቂና ቢዝነስ ማን ለመኾን እንደታደለ ያወራል። ለአንድ ማስታወቂያ 150 ሺህ ብር እንደሚጠይቅ ኹላ በድፍረት ይናገራል። (ማይምነት ስላለ ማመን እቸገራለሁ። :-D )

አንድ ጊዜ ሠይጣን የኾነ አከባቢ ብርትኳን በነጻ እንደሚከፋፈል ወሬ አስነገረ አሉ። ከዚያም የወሬው ፍጥነትና ድግግሞሽ በዙር ራሱ ጋር ደረሰ። ከሌላ ሰው የራሱን ውሸት ሲሰማ የገዛ የፈጠረውን ውሸት አምኖ ብርትኳኑን ለመውሰድ እንደሌሎች ሮጠ ይባላል።

የውሸት/ ማይምነት ድግግሞሽ በሰዎች ላይ እውነት አድርጎ የማቅረብ አቅሙን ተረዱልኝ። በመሠረቱ የትኛውም የድግግሞሽ ኃይል ዋጋው ከባድ ነው። ዚኪሮችን፣ አውራዶችን በመደጋገምና በማከታተል የምንሰራውም ለዚህ ነው። እና ቲክቶክን ያነሳሁት ለምድር ነው?

የሚድያ ኃይል ጅልነትንና አላዋቂነትን ደጋግሞ በመስበኩ ምን ያህል ሰዎችን እንዳፈራ ብሎም መድረክ ፈጥሮም የመሸለም ወግን በማሕበረሰብ ውስጥ ማስረጹ አስገርሞኛል። መሠረታዊ ዕውቀትን፣ ፍልስፍናንና ጠንካራ ስብዕናን እንዴት እንደሚናድም መመልከቴ እንዲሁ!!

መልካም ምሽት ይሁንልን!

Best kerim

29 Dec, 18:29


"ተቋም ቢኖረን ኖሮ እንዲህ ባልኾንን ነበር" የሚሉ ቁጭቶች በራሳቸው ይታረሙ። ተቋምን እንደ ፈጣሪ አድራጊ ማየት ዋጋ የለውም። እንደ ተቋምና ድርጅት ከታየ ድሮ ድሮ የነበሩ መጅሊሶች በቅጡ ተደራጅተው የነበሩ ተቋም ናቸው።

በስንት መስእዋትነት የተገኘው መጅሊስ በዐቅምና ደረጃ ግዙፍ የሚመስል ነገር ቢታይበትም። ከመዋቅርና ድርጅታዊ ተልዕኮ ግን በልኩ (በሚፈለገው መልክ) የተዋቀረ አይመስለኝም። ሹመት በድንገት የሚሰጥበት፣ የእምነት እሴቶች ከጊዜ ወደጊዜ እየተነኑ የሚሄዱበት፣ የእምነት ዐቅምና ችሎታ፣ መንፈሳዊ ማንነቶች ችላ ተብለው ጩኸት (አክቲቪዚም) እና ፖለቲካ ጮክ ብለው የሚታዩበት ሲኾኑ የሚታይ ነው። እንዲህ መዝረክረክ ሲኖር ደግሞ ግልጽ የኾነ ድርጅታዊ ዓላማን የማይታይባቸው እልፍ ተቋማትን ይፈጥራሉ። ይህ ደግሞ የኾኑ ሰዎችን የግለሰባዊ ፍላጎት ካሟሟላት ውጭ የትልቁን ሙስሊም ፍላጎት ይረዳል ብዬ አላስብም።

ተቋም ተኮር ከኾኑ ጩኸቶች የተሻለው ጥያቄ ለኢስላማዊ እሴቶችና ሞራላዊ ስብእና የሚቆረቆሩ ማንነቶች ስለመመናመን ብንጨነቅ ደግ ነው። ይህ ጭንቀት ዘላቂ የኾነን እምነት በአመራሮች ልብ ውስጥ ይተክላል ብዬ እጠረጥራለሁ።

ያብጀዋ

Best kerim

27 Dec, 18:47


የአላህ ወር ረጀብ ሊገባ ጥቂት ብቻ ቀሩን

“ረጀቡል አሰብ” በመባል ይታወቃል። የአላህ እዝነት በብዛት የሚፈስበት ወር ነው። አብዝተን ምሕረት የምንለምንበት ወር ነው። ለረመዳን ታላቁን ዝግጅት የምንጀምርበት ነው። ከሦስት ቀናት በኃላ ይገባል። ጾሙን፣ መቅራቱን፣ ሰለዋቱን፣ ቂያሙን፣ ሰደቃውን በማድረግ ዝግጅታችንን እንድንጀምር የሚበረታታበት ወር ነው። ዑለሞቹ በዚህ በተከበረ ወር ምሕረት አብዝተን እንድንለምን ይመክሩናል።

አላህ ያድረሰን፣ አምልኮዎችንም ያግራልን

Best kerim

27 Dec, 13:20


« ከባርያ ‎እርዳታና እገዛ ሲቀርብ፤ አላህ ባርያውን ይቀርበዋል። ከባርያ ልፋት እና ትግል ሲጨምር ደግሞ ከአላህ ስኬት (ተውፊቅ) ይከተላል። ከባርያ አደብ የተገኘ ዕለት ከአላህ ክብር ይመጣል።»

አቡል ዓባስ አልአደሚ (ቀደሰላሁ ሲረሁ)

እነዚህ ሱፍዮች ከላማቸው እንዴት ይጣፍጣል። ጥቂት የሆነች ቃላቸው በረከት የተሞላበት ስለኾነ ብዙ መረዳትን ይከፋፍታል። ተስፋና እና ደስታን በልባችን ውስጥ ይዘራል።

የዚህ ከላም ባለቤት በ4ኛው ሒጅሪያ ላይ የነበሩ ከባድ ሰው ነበሩ። በተርታው ጊዜ በየዕለቱ ቁርኣን ያኸትሙ ነበር። በረመዳን ወር ደግሞ በቀንና በለሊት 3 ጊዜ ያኸትሙ ነበር። ይህ ማለት መልእክቱን ከማስተንተን ጋር መኾኑን ልብ ይሏል።

ደጋጎቹን የምንረዳበትን ልብ ይረዝቀን

ባርያ ያድርገን፣ ባርያ ስንኾን እርሱን ማግኝትን ይረዝቀናል።

አላህ ያስረዳና

Best kerim

25 Dec, 18:37


« ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡» አሹዓራእ፤224

የሹዓራእን ምዕራፍ ሳነብ እዚህ አንቀጽ ላይ ቆምሁና ጥቂት አሰብሁ። ቁርኣኑ "ባለቅኔዎች" ያለው ማንን ነው ብዬ ወደ በጘዊ ተፍሲር ዘለቅሁ፤ የመካ ከሐዲያን የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይዘው የመጡን መልእክት (ቁርኣን) ለማስተባበል በተለያየ የቅኔ ችሎታቸው የእርሳቸውን መንገድ ያጣጥላሉ፤ ጛዉን ( አላዋቂ መንጋዎቻቸው) በብዛት ይከተሏቸዋል። ባለቅኔዎቹ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሚሉትን (የአላህ ቃል የኾነውን ቁርኣንን) እነርሱም እንደሚሉ ተከታዮቻቸው ላይ ያመሳስሉባቸዋል።

ከሙፈሲሮቹ መካከል እነዚህ ተከታዮች ሸይጣን እንደኾኑም ይገልጻሉ። ከዚህ የምንረዳው በመንጋ መሐል፣ በጣኦቶች ውስጥ በዋናነት ሰይጣናት ሰርገው እንደሚገቡና በሚገባ እንደሚያጋግሉ ነው። ሀውልቶችና ዛፎችም እንደጣኦት የሚመለኩት በውስጣቸው ሰይጣናት እንዳለ በቁርኣን ስለ ላትና ዑዛ ሲተነተን የምናገኘው እውነት ነው።

መንጋ የሚነዳባቸው ከኢስላም ጋር የሚጻረሩ ነገሮች በሐይማኖት ተመስለው፣ በመልካም ነገር ተቀብተው ቢመጡም ከባለቅኔዎቹና ተከታዮቹ የተለዩ ላይኾን ይችላልና በባለቅኔዎቹ ከመመራት በሰይጣናት ኔትዎርክ ከመጠለፍ አዘውትሮ አላህን መማጸን አስፈላጊ ነው።

አላህ ይጠብቀና፣ ያስረዳንም

Best kerim

25 Dec, 10:41


« የሰው ልጅ ሪዝቁን (ሲሳዩን) ለማምለጥ በነፋስን ፍጥነት ቢጓዝ፤ ሪዝቁ (ሲሳይ) በመብረቅ ፍጥነት ይከተለው ነበር።»

ኢማም ዐለይ ቢን ጣሊብ (ከረመላሁ ወጅሃሁ)

የእኛ የተባለው ሪዝቅ (ሲሳይ) የእኛ ነው። በልኩ መመልከትን ይለግሰን እንበል እንጂ የሚበቃንን ያህል ተለግሶናል እኮ!! ይህ አይበቃኝም ብሎ የመሟገትም ሰውኛ ስሜታችን ጤናማ ነው። ከጤናማ አተያይ ካለፍን ግን ወደ በሽታ ይቀየርና መርካትን፣ ማመስገንን ይነፍገናል። "አይበቃኝም፣ አይመጥነኝም!" ብሎ ከራሳችን ጋር ሙግት ከመጀመራችን በፊት ያለንን የተለገሰንን ጸጋ የመቁጠር፣ በችሎታና ሀይል ያላገኘናቸውን ብዙ ነገሮቻችንን ቆጥሮ የማመስገን ልምዶች አሉን?!

አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ከገጠመን ችግር በላይ ከፍተኛው ጫና የሚያሳድርብን ከሌሎች ሰዎች የሚደርስብን መቋቋም የማንችላቸው ሥነልቡናዊ ጉዳቶች ናቸው። እነዚህ ወስዋሰል ኸናስ ይባላሉ። በሕይወትህ ተመችቶህ አመስገነህ እየኖርህ ይኾናል፣ በምንም ነገር ሳታማርር በደስታ ስሜት ተሞልተህ ሕይወትን እየተጋፋህ ይኾናል። ሰዎችን ዓዛ ማድረጋቸውን በማያቁ መይማን ድንገት ትነካለህ። ኑሮህ ብቁ እንዳልኾነ፣ በቤትህ ደስተኛ እንዳትኾን የሚያደርጉ ቁሳዊ ነገሮችን ያጎሉብህና/ሽና ከዚያም ሰላማዊዉን ቤትህን በግድ ካላናጋሁት እንላለን።

በገንዘብ ሐይል ትዳር ይቃና ይመስል ለገንዘብ ብዙ እንኾናለን፣ በዝና እና በቁስ ሐይል ማንነት ይቀየር ይመስል ብዙ እንለፋለን። ግና በመጨረሻም ሁሉም ሰው የመጀመሪያውን ሕይወቱን ድኽነቱን፣ ችግሩን ሲናፍቅ ታያለህ።

ግና የሚናፍቀው ችግርና ድኽነት የሚያስደስቱ ነገሮች ኾነው ሳይኾን በዚያ ዘመን የነበረውን ውስጣዊ ማንነት ማለታቸው ነው። መስራትና መልፋት በጎ ነገር ነው፣ በቁሳቁሶች መዋብና ማስዋብ ደግ ነገር ነው። እመኑኝ እነዚህ የሚያግዙን የሕይወት ቅመሞች እንጂ በፍጹም ፍጹም ደስታዎችን የሚያመጡ ነገሮች አይደሉም። የዛሬን ሁኔታችንን መቀየር መልካም እርምጃ ነው፣ ግና ነፍስን አስወደዶ፣ አላህን በሚያስረሳ መንገድ መጓዝ ግና ሁሌ በተለያየ መልክ የምንደጋግመው ኪሳራ ነው።

ሰዎች ሆይ! እንረጋጋ ሪዝቃችን አለ። እንዲባርክልን ብቻ አላህን እንለምነው። የምንለፋው አደብ፣ ኢማን፣ የሚባሉ ነገሮችን ለማግኘት ነው። ለፍተን የምናገኘው የሚመስለንም ገንዘብ ዞሮ መልካምን ሰርተን አኺራን ለመሸመት ካልኾነ አይምጣ የሚል የቂን ይኑረን። ሊጎዳን፣ እብሪተኛ ሊያደርገን፣ ሰዎችን ልንበድልበት አይምጣ የሚል የዛሬ ወኔ ከሌለን ዱንያን ለማግኘት የምንሄድበት መንገድ አኺራን እንዳያሳጣን ያስፈራል።

ረቡዕ ከሰአት፤ ሰዓቱ የዱዓ ነው አላህ ያስረዳና

Best kerim

24 Dec, 15:41


#የዘወትር_ማስታወሻ

ሩሓችን ከአካላችን እስካልተነጠለች ድረስ በመጥፎ የምታዘው የነፍሳችን ጠባይ ካላት ባሕርይ መለወጥ አትችልም። በመጥፎ የምታዘን የገዛ ነፍሳችን አደገኛ ጠላታችን ናት። ክፋቷ ኃይለኛ እኛን ብቻ ሳይኾን ዙሪያችንን እንድንጎዳ የምታደርገን ረቂቅ ናት። ዑለማዎች ከሰባ ሸይጣን የበረታች አደገኛ እንደኾነች ይገልጻሉ።

ታዲያ ይህችን ነፍስ አዘውትሮ በመቃወም ከእርሷ ጋር በተጻራሪ መንገዶች ላይ መበርታት ወደ ወቃሽ ነፍስ (ነፍሱ ለዋማ) ማደግ ይመጣል። ይህ ማለት በመጥፎ የምታዘዋ (ነፍሰል አማራህ) ትሞታለች ማለት አይደለም። ልክ እንደ ክረምት እባብ ትመሰላለች ይላሉ። በክረምት መሬት ሰርስሮ በመግባት ይደበቅና ከዚያም በበጋ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ መጉዳቱን ይቀጥላል ።

እኛ የሰው ልጆችም ሁሌም የአላህ አብሮነት በመረዳት ነፍስና ዝንባሌዋን በመታገል ላይ መቆየት በመጥፎ የምታዘንን ነፍስ መቋቋም እንችላለን። ከዚህ የተዘናጋን ጊዜ አላህ ይጠብን እንጂ በዚህች ነፍስ (ነፍሰል አማራ) መርዝ ተነድፈን ወደ ጥሜት እንመራለን።

ስለዚህ እኛ የሰው ልጆች ወደ ቀብር እስክንመጣ ድረስ ከዚህች ነፍስ ጋር የምናደርገው ትግል አይቋረጥም። ይህች ነፍስ እንኳን ያለንን የሌለንን ነገር አሰማምራ ታቀርብልናለች፣ ወደ ውስጣችን ሰይጣን ምሽግ እንዲመሽግ የምታመቻቸውም ይህችው ነፍስ ናት። የዕለት ተዕለት ሕይወት የተራጋጋ እንዳይኾን፣ አመስጋኝ እንዳንኾን፣ ልብ በክፋት እንዲሞላ የምታደርገው፣ አኺራ ከልባችን እንዲርቅ፣ ዱንያ በውስጣችን እንዲነግስ የምታደርገው፣ በውስጣችን በርካታ ጣኦቶችን የምትገነባው እርሷ ናት።

እነዚህን የነፍሲያችንን ጠባዮች ልናውቅ የምንችለው ነፍስን ለማወቅ በሚለፋበት መንገድ ላይ በመገኘት ነው። በአምልኮዎች፣ በአውራዶች፣ በሰለዋት ዚክሮች፣ ነፍስ በቅጡ ለማወቅ የምንጠቀምባቸው መንገዶች ናቸው። በእነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ወደ ኋላ የቀሩ ዐሊሞች፣ ኾኑ ዳዒዎች፣ ሐብታሞች ኾኑ ታዋቂዎች የሚጠለፉት በዚህች ረቂቅ የነፍሲያ ወጥመድ ነው። ነፍሱን ያላወቀ ሰው ደግሞ ጌታውን ሊያውቅ አይችልምና በምንም ነገር ያወቅን ቢመስለን ነፍሳችንን የረሳን ዕለት አላዋቂ መኾናችንን ማስታወስ ደግ ነገር ነው።

አላህ ያስረዳና

Best kerim

24 Dec, 14:40


ከመስጂዶች ውስጥ የገቡ መንፈስና ዕውቀት አልባ ዲስኩሮች ድርቀትን ያስፋፋሉ።

ቅርብ ሰአት አንድ መስጂድ ስገባ አንድ ጎልማሳ እንደጉድ እየፈላ ዲስኩር ሲያደርግ ሰማሁ። ምንድር ይኾን የሚያንተከትከው? ብዬ ትኩረት ሰጥቼ ሳደምጠው ለዑለሞች ዱዓ ማድረግ አለብን ሲል ስሰማው ደስ ብሎኝ ማድመጥ ጀመርሁ። ቀጠለና ያለፉ ዑለሞች ከእኛ እንደሚፈልጉ እንጂ እኛ ከእነርሱ እንደማንፈልግ ሐተታ ያወራ ጀመር፤ ቀጠሎ ቀናትን እየሰየሙ ዱዓና መጅሊስ ብሎ መቀመጥን ክፉኛ መተቸትን ተያያዘው።

ዕውቀትን በልኩ አለመረዳት አደገኛ ድንቁርናን ይፈጥራል። ሁልጊዜም ቢኾን እምነቱን ለመረዳት ካለፉትም ካሉትም ዑለሞች እገዛ ያስፈልገናል። ዑለማዎች የነብያት ወራሾች መኾናቸውን መዘንጋት ወይም አግባብነት ባለው መንገድ አለመረዳት ማሕበረሰብ ላይ እክሎችን ይፈጥራል።

ዱዓና ዚክር፣ ሰለዋትና መንፈሳዊነት ክፉኛ በደረቀበት ጊዜ አይደለም በቀናት ቀርቶ በደቂቃዎች ከፋፍሎ አምልኮን መለማመድ ተወዳጅና የሚበረታታ እንጂ የሚኮነንን ነገር አይደለም። መኮነን ያለበት መስጂድ ተሰባስቦ ፖለቲካ ማቡካት፣ በስመ "ቢድዓ" ሙስሊሙን ከመንፈስ ማራቅና መሰል ረብ የለሽ ነገሮች ናቸው።

ብዙ መስጂዶች ውስጥ ስለአላህ ብዙ እናውራ፣ ከመስጂድ የራቁ ሰዎችን በዚያራ ወደ መስጂድ እንመልስ፣ በተለያዩ የሕብረት ዚክሮችና ሰለዋቶች ኢማንን እንጠብቅ ያሉ ሰዎች ተባረው። በተቃራኒው በዘመናዊነት ስም ከመንፈስ የራቁ፣ ፖለቲካዊ ቁመናዎች ብቻ የተስፋፋባቸው፣ ቁሳዊ ነገሮች ከልካቸው በላይ የሚተዋወቅባቸው እየኾኑ ነው። ሒደቱ በዚህ ከቀጠለ አስፈሪ ደረጃ መድረሱ አይቀሬ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ ከቀናት በፊት አንድ መስጂድ ገብቼ ዐሥር ሰላት ሰገድሁ። ከዚያም በኋላ የዐስር አውራድን ለመቅራት ጀመርሁ መስጂዱ ከገበያ ባልተናነሰ መልኩ ጫጫታው ረበሸኝ፣ ከጎኔ የሚገኙ ሰዎች ኹሉ ስልክ ይዘዋል፣ ዱዓ በሚደረግበት ቅጽበት የ "ሱና" መስጂድ ስለነበር ሁሉም ሰግዶ ሰግዶ ብድግ ብሏል። አንዳንድ ሰባኪዎች ሳይቀር ድምጻቸውን ከፍ እያደረጉ ስለ ዑምራ ቪዛ ዋጋ ያወራሉ :-D ፣ በጣም ተቆጣሁና በቅርብ ርቀት ለሚገኝ አንድ ወጣት በምልክት "ይህ እኮ መስጂድ ነው! አረ ባካችሁ?!" ብዬ በድፍረት ጠቆምኩ በንቀት ስልኩን ማውራቱን ተያያዘ። በጣም ተቆጥቼ ስወጣ ያየኝ አንድ ሰው ላይ ስሜቴን አራግፌ ቀዘቀዝኩ :-D

ሁሌም መስጂዶችን መምራት ያለባቸው የመስጂድ አደብና ክብር በሚያውቁ ሰዎች ነበር። ዛሬ ከላይ እስከታች ሐይማኖተኝነት መስፋፋቱን እንጂ ኢማንና መንፈስ መታደሱን የሚያረጋግጥ ሥርዓት ያለው ነገር የሚገኝባቸው ቦታዎች እጅጉን ተመናምነዋል።

አላህ ይመልሰን
የመስጂድን ክብር የሚያውቁ ሰዎችን ይመልስልን
ኢማን የሚመግቡንን ዑለሞች ወደ መስጂድ ያስገባልን

Best kerim

03 Dec, 06:32


የፍቅር ዋጋ ለልጆች

አንዲት ተማሪ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች አገኘኋት። የሚያለቅሱ ተማሪዎች ሳይ ብዙም መገረም አቁሜያለሁ ባይኾን ቶሎ አዕምሮዬ ላይ የሚመጣው "እንኳን ስሜታቸው አልታፈነ!" ለቅሶኣቸውን አስጨርሼ፣ ሶፍት ሰጥቼ በደንብ እንዲወጣላቸው ካደረግኩ በኋላ ላወራቸው እሞክራለሁ። ይህች የምታነባው ልጅ ምን ሆንሽ? ስል ጠየቅኳት « ሚስተር አንተ አታውቅም እከሊትን እኮ የምወዳት ልክ ነብያችን አቡበክር የሚወዱትን ያህል ነው።» ስትለኝ እኔ ራሱ እምባዬ መጣ። አቤት የፍቅር ዋጋ! ምን ያህል የጓደኝነትን ዋጋ ብትሰጥ ነው ብዬ ቀርቤ በደንብ ጠየቅኳት። ያበሳጫት የምትወዳት ልጅ በሌሎች ዐዳዲስ ጓደኞች መነጠቋ ነበር። ምን አልባትም ለዚህች ልጅ ብቸኛ ወዳጇ የምትወዳት ልጅ ነበረች ብዬ ተጠራጠርኩና። የምትወዳትን ልጅ ማፋለግ ጀመርሁ ክፍሏ ሔጄ አገኘኋትና የጓደኛዋን ትልቅ ፍቅር አስረዳኋትና እባክሽ አትተያት ብዬ ተማጸንኩ ለሌሎች ጓደኞቿም አስረዳሁ። ይህን እንደጨረሰኩ አምርራ ያለቀሰችውን ልጅ መከታተል ጀመርሁ። ለካ ልጅቱ ከወላጆች ጋር ያላት ግንኙነት ልክ አልነበረም። በየቀኑ የሚጨቃጨቁባቸው አድርጊ አታድርጊ ክሶች ፍቅር ከመስጠትና ከመቀበል አርቋቸዋል። (ያሳዝናል!)

መቼ ነው አባትሽ እወድሻለሁ ያለሽ አልኳት? ከባድ ጥያቄ ነበር። እናትሽን አንቺ መቼ ነው እወድሻለሁ ያልሻት ስላት በዝምታ ተዋጠች። የማኣት ምክንያት መደርደር ጀመረች አስቆምኳትና። በቃ ሁሉም ይቅር ልጅ ምንም ሰራ አጠፋ ወላጆቹን መውደድ እኮ አለበት አልኳት። ወላጆችም ቢኾኑ ልጅ ስላጠፋ ወይም ጥሩ ነገር ስለሰራ አይደለም መወደድ ያለበት እኮ?! በቃ የእኛ ልጆች እንደሆኑ እንደተቀበልነው ኹሉ በቀን የሆኑ የፍቅር ቃላቶችን እኮ መለዋወጥ አለብን።

ልጆች በየዕለቱ ከወላጆቻቸው ፍቅርን መቀበል ይሻሉ፣ ከመምሕራንና ከሚመለከታቸው አካላት ኹሉ መፈቀረን ይጠብቃሉ። ሲያድጉ ይህን መጠበቅ እየገቱና እያቆሙ ይሄዳሉ። መጠበቃቸውን በራሳቸው ጊዜ እስኪያቆሙ እንደምንወዳቸው ብንነግራቸው ዋጋውን ያውቁት ይኾን?! ትልቁ ዋጋ ፍቅር አይርባቸውም! በግሌ ልጅ ፍቅር ከሚርበው ምግብ ቢርበው እመርጣለሁ።

እባካችሁ ወላጆች፣ አሳዳጊዎች፣ መምሕራን ከልጆች ጋር በሚኖራችሁ ግንኙነት መልካምን ስታስተምሯቸው፣ ከመጥፎ እንዲርቁ ስታደርጉ በፍቅር ቃላት በአዎንታዊ መልእክት ላይ ትኩረት ማድረጋችሁን አትርሱ። ልጆች ሁሉንም ነገር የሚያቁና የሚረዱ ልዩ ኸልቅ ናቸው። እያደረጉ ሲመጡ ከውስጣቸው ያለውን ብርሃን በሌሎች ክፉ ነገሮች እየተለወጠ ይሄዳልና በጊዜ በልጆች ልብ ውስጥ ፍቅርን በመዝራት ትውልድን ለማዳን የበኩላችንን እንጣር እላለሁ።

ሰላም ውሎ

Best kerim

02 Dec, 15:11


የሸይኽ ዓዲል ቻሌንጆች ዋጋቸው በጣም ከባድ ግና መተግበር የሚችሉ ናቸው። ከሰሞኑ አንድ ደርሳቸው ላይ አንድ ነገር ሲሉ ሰማኋቸው። ንግግሩ ቅሉ ቀለል ያለ ይመስላል፤ ዋጋው ግን አስገራሚ ነው።

ሐሳቡን አሳጥሬ ሳቀርበው ...

የእጅ ስልካችሁን ለመንካት ትዝ ሲላችሁ ለራሳችሁ በዕለቱ መቅራት፣ መዘከር፣ ማንበብ፣ መሥራት ካለባችሁ ነገር ያጎደላችሁትን አስታውሱ። ምንም ካላጓደላችሁ ወይም ሁሉንም ከጨረሳችሁ ስልኩን በተለይም ሶሻል ሚድያ መጠቀም ትችላላችሁ እርሱም በውስጡ የምታስተላልፉት ወይም የምትማሩበት ጠቃሚ ነገር ከመኖሩ ጋር።

ሌላ አንድ ደርሳቸው ላይ ሶሻል ሚድያን ስትጠቀሙ መታጠቢያ/ማረፊያ ቤት ለመግባት በምትጠቀሙበት የጊዜ ልኬት ልክ ይኹን።

ሌላ ደርሳቸው ላይ

አንድ ሷሊህ ሰለፎች/ቀደምቶች ለሊት በሰላት/በቁርኣን አነጉ ሲባል አይገባኝም ነበር። ይኸው በዘመናችን ሰዎች ስልክ ላይ አፍጥጠው ሲያድሩ ሳይ ገባኝ። ሰው በወደደውና በውስጡ ባከበረው ነገር ብዙ ሰአት ማሳለፍ ይችላል።

ልጨምር ... ؟

ከዚህ ሜዳ በቅጡ ለመጠቀም የሚፈልግ የሶሻል ሚድያ ፊቂህ(አረዳድ) ምን እንደሆነ መረዳት የሻ ሰው በሸይኻችን ይጠቀም፣ መድረሳቸው ላይ ይሂድ፣ ሲራቸውን ይከታተል፣ ደርሶቻቸውን ያድምጥ እላለሁ።

መሰል የምክር መንገዶቻቸውን ኹሉ ሞክሬላቸዋለሁ

አላህ ይጠብቃቸው እወዳቸዋለሁ

Best kerim

02 Dec, 13:19


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

01 Dec, 03:31


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

30 Nov, 18:55


ድሮ ድሮ ለኢስላም ስለመሞት ነበር ብዙ የሚወራው፤ ታላላቆች መጀመሪያ በመንገዱ ኑሩበት ብለው መከሩን ። አሁን ደግሞ "በኢስላም ስም መኖር" እና "በእስልምና መንገድ መኖር" እንዳይቀላቀልብን አስረጂ ያስፈልገናል። ይህ ኢስላም አይደለም፣ ይህ ኢስላም ነው የሚለንን አያሳጣን። በዚህ በተቀላቀለበት ጊዜ ለክፉም ለደጉም ለአላህ ብሎ አላህን ከማጣት እርሱ ይፈርጀና!!!

ሰው ለአላህ ብሎ እየለፋ፣ ቁርኣን ከማንበብ ይሸሻል፣ ሰው ለአላህ ብሎ እየደከመ ሰላቱና ዚክሩ ይቀርበታል። ለርሱ ብሎ እያስተማረ አይኖርበትም።

የምናጎድለውን የምናውቅበት ራስን የመረዳት ዐቅም እርሱ ይለግሰና

Best kerim

30 Nov, 16:44


#እውነተኛው_ሐገር

አንድ ቀን ወደ ሰማይ መሰደዳችን አይቀርም፤ ይህች ምድር እንደሁ ለእኛ ሐገር አልሆነችም፣ ወደፊትም አትኾንልንም። ታዲያ ብዙ እየለፋን ያለነው ለምድር ቤት ወይስ ለሰማይ ቤት?!

ሰማይ “የዱዓ፣ የበረከት፣ የመንፈስ ...” ቂብላ (ዐቅጣጫ) ነው። ልክ የሰላት ዐቅጣጫ መካ የኾነውን ያህል። ሰማእ (ሰማይ) ሰፊ ነው፣ እንዲሁ ሰማይ እንበለው እንጂ ምን ጉዱ ታውቆ?! ቁርኣን ሰማያዊ ነው፣ ኢማንም እንዲሁ ከውስጡም የመነጩ ሰማያዊ ሥራዎች (ኢማንያት) ላይ ብዙ ጊዜ ካላሳለፍን ዞሮ ወደ ማንኖርባት ምድር መሳባችን አይቀሬ ነው።

ስለዚህ በዚህ ዓለም ቆይታችን ወደ መጪው ዓለም የሚስበንን፣ ምንዳ ወደምናገኝበት፣ ከአላህና ከነቢ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋር የምንሐድርበት (የምንጣድበት) ነገር እንጂ ምንም የሚያጓጓ ነገር ስለሌለ ምንም ነገር ቢያመልጥህ እነዚህ ኢማንያት (ሰማያዊ ነገሮች) እስካላመለጡህ ድረስ አትቆጭ!

ቁጭት ማለት ከኢማን መንደር መሸሽ ነው!

አላህ ከቁጭት ይጠብቀን፣ ወደ ሰማያዊ ዓለም ይመልሰና

Best kerim

29 Nov, 12:48


https://www.facebook.com/share/v/1AwgYBx1kw/

Best kerim

28 Nov, 18:09


Live stream finished (22 minutes)

Best kerim

28 Nov, 17:46


Live stream started

Best kerim

28 Nov, 17:46


Live stream finished (9 minutes)

Best kerim

28 Nov, 17:37


Live stream started

Best kerim

27 Nov, 17:55


#ስክነት

« የሩሕህን ስክነት ያገኘህበት ቦታ ላይ ቆይ እርሱ ቦታ ማለት ቤትህ ነው።»

መውላና ሸምሰ ቲብሪዝ (ቀደሰላሁ ሲረሁ)

አዕምሮ በብርሐን የተሞላ ክፉና ደግን የምንለይበት ታላቅ የአላህ ሥጦታ ነው። ከወንጀል ሲጠበቅ፣ በልብ ብርሐን (ኢማን) ይታገዛል። አዕምሮ (ዐቅል) በወንጀል ሲጎዳ ብርሃኑ ይጠፋበታል። በአዕምሮ ሚዛን ብዙ ተዓምራት ይሰሩ ይኾናል። ታላቁንና ግዙፉን ዓለም መቃኘት የሚቻለው ግን በልብ መሪነት ነው። የልብ ዓለም ሰፊ ነው። ልብ ከሰማይም ከምድርም ይሰፋል፣ አረ እንደሁም ከዐርሽ ኹሉ ይሰፋል ይላሉ። ልብ ያልመራው፣ በልብ (ሩሕ) ያልተመራ ዐቅል (አዕምሮ) ትርፉ መዘዝ ነው። የእስልምና (ኢማን) ብዙ ዓለሙ ልባዊ ነው። በአፈር በተሰራው ዐቅል (ሎጂክ) ብቻ የምንዳረቀው አይደለም። ይህን መንፈሳዊ (ልባዊ) ዐለም መረዳትም የሚቻለው በኢማን ነው። በርካታ የእስልምና ትዕዛዛትንም መቀበል የሚቻል ከዐቅል ባሻገር በኢማን ነው። ኢልሃምም ለአማኞች የሚመጣው ለልባቸው እንጂ ለዐቅላቸው አይደለም። የጘይብያት፣ የረባኒያው ኹሉ ዐለምን የሚቃኘው በልብ መሪነት እንጂ በዐቅል አይደለም።

የልብህ ዓለም ላይ ስትደርስ፣ የልብህ (ሩሕህ) መንገድ ላይ ስትጓዝ የሚፈለገው ሰኪና ይመጣል። የምትሄድበት መንገድ እርጋታ/ሰኪና ካልለገሰህ የእርጋታህን መንገድ መፈለግ የግድ ነው።

መንገዱ ረጅም ነው፣ አማኝ ደግሞ ሁሌ መንገደኛ ነው

አላህ ያስረዳና

Best kerim

27 Nov, 12:42


ለተጨነቃችሁ ለከባበዳችሁ ሰዎች የምስራች ልንገራችሁ?!

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉን!

« ከጭንቅ መገላገልን ከአላህ መጠባበቅ በላጩ አምልኮ ነው! »
" وأفضل العبادة انتظار الفرج "

የሚያስጨንቁን ነገሮች እንዲወገድልን በመቃረቢያዎች ኹሉ ወደርሱ እየቀረብን ከአላህ ብቻ እንጠበባቅ። አንድም ይህን ከአላህ መጠበቁ አምልኮ ሲኾን ሌላኛ ገጹ የርሱን ውዴታ በማግኘት ወደ ሩሕ ዓለም የመመለስ ዕድል ማለትም ከአላህ ጋር የመቀራረብ ዕድል እናገኛለን።

ወደርሱ የቀረበ ሰው ምን አጣ?!

ለመኖር ከማታጓጓ ዓለም ወጥተን እርሱን ወደምናገኝበት ዓለም ያስገባና!

ያስረዳና

Best kerim

27 Nov, 12:32


https://www.facebook.com/share/p/14jRq2qv4b/

Best kerim

27 Nov, 11:43


በሲቪክስ፣ በጂኦግራፊ፣ ወይም በሒስትሪ የተመረቀ ሰው ሥራ አለ ያናግረኝ። ሴት ብትኾን ይመረጣል።

Best kerim

26 Nov, 17:36


አደረግኩት፣ ፈጸምኩት ሳይኾን አላህ አገራልኝ እንበል። አላህ ችሮታውን የሚያስታውስለትን አመስጋኝ ባርያ ይወዳል። ስናጎድል፣ ሲከብደን፣ ስንደክም ደግሞ አግዘኝ ተረታሁ ማለትን እናዘውትር። ሁሉንም ወደርሱ ማቅረብ ነው። ስሞታ ሰው ዘንድ ሲኾን ነው ከባድ አላህ ዘንድ ሲኾን ወደርሱ መቃረቢያ መንገድ ነው።

አልሐምዱሊላህ

ያግራልና

Best kerim

26 Nov, 08:58


አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ!

የአፍ መፍቻ ቋንቋዋ ዐረብኛ የኾነች ከዐረብ ሐገር የመጣችና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ያጠናቀቀች ሥራ መስራት የምትፈልግ እዚህ መንደር ካለች በውስጥ አድራሻዋን ታስቀምጥልኝ።

አመሰግናለሁ!

Best kerim

26 Nov, 08:00


#የምናይበትን_መነጽር_እናጽዳ

አንድ አንጋፋ ዐሊም አንድን ሸይኽ በኪታባቸው ላይ ኮነኑ ምንድር ነበር ኩነኔው? “የሐዲስ ትራፊክ!” ሲሉ ነበር የኮነኗቸው። ምክንያቱ ደግሞ ሐዲሶቹን እንዳይጠቀሙ በሐዲሶቹ ላይ አቃቂር እያወጡ ሲያችገሯቸው እኮ ነው። ከሺህ ዓመት በፊት ዑለሞቹ የሰሩበትን ሐዲስ አስበው እስቲ እነ ኢማሙ ነወዉይ የተገለገሉበትን ሐዲስ በ19ኛው ክፍለዘመን ማለቂያ ላይ ያለ ሰው ይህን ሐዲስ "ሰሒሕ ያደረገው፣ ደዒፍ አደረገው" ሲባል በእውነት ያስቃል :-D አንዳንዴ እኛም እንዲህ ያደረገናል። ኡስታዝ ይህ ነገር ይፈቀዳል? ሲባል አንጋፋዎቹን ሺህ አመታት የኢስላም ሩሕ ላይ የዘለቁትን ይጠቃቅሱና ኮስተር ብሎ "እንደኔ ይህን መርጫለሁ።" ላ ኢላሀ ኢለላህ! ይህን እኮ ታላላቆቹ ሙሐዲሶች እንኳን አላደረጉትም። ፊቂህ ስትቀራ አላየህም። "ቂል ... ቂል" ተብሎ ይጻፍና "አሰሕ" ተብሎም እንደወረደ ይጻፋል። የሌሎቹን አይጥሉም አይፈርዱም። ሌላ ምሳሌ ልጨምር የኾነ የሥነልቡና ጉዳይ ቢነሳ የውጭ ዩንቨርስቲ ላይ ያሉ ባለሙያዎችን /ፕሮፈሰሮችን አጣቅሰህ፣ ጥናንትን አስቀምጠህ፣ የሐገሪቱን ባለሙያዎች ያሉትንም ታመጣለህ። ምንም የሥነልቡና ዕውቀት በሌለህ ጉዳይ የእነርሱን ጨረፍ ጨረፍ አድርገህ "እኔ የምመርጠው ይህንን ነው" ብትል አያስቅም?!

እየኾነ ያለው ይህ ነው። ማንም የማንንም መንገድ መመርመር አይችልም። ይህ እኔ የተከተልኩት መንገድ ነው ልኩ፣ በዚህ መንገድ ካላለፋችሁ እንጂ ምንም አታውቁም ተብሎ አደባባይ አይደሰኮርም። ወደኣላህ መቃረቢያ መንገዱ ምድር ላይ በፈጠው እስትንፋስ ልክ ነው። የእኛ መንገድ ብቻ ነው የተረጋገጠው ማለት አለማወቅን ያወርሳል።

አንድ ልጨምር

ሰይድና ሙሳ አላህን በራሱ መንገድ ለማውራት ወደሚጥር ባርያ ቀርበው የሚያመልክበትን መንገድ ተቹት። ይህ ባርያ አላህን ቢያገኘው "እግሩን አጥቦ ጫማ እንደሚሰፋለት" ያወራ ነበር። በዚህ ንግግር ስለደነገጡ ከዚህ ተግባሩ አስቁመውት ስለሚባለው ነገር አስተማሩት። (በሸሪዓ ሚዛን ልክ ነበሩ)

አዛኙ አላህ ግን ልክ እንዳልሰሩ ምን ከመሰለ አምልኮው እንዳዘናጉት አስታወሳቸው። ምን ለማለት ነው?

እኔ ብቻ ነኝ ሱፍይ አትበል! ተሰዉፍ (ኢህሳን) አላህ ለፈለገው ሰው መርጦ ሊሰጠው ይችላል። እኔ ብቻ ነኝ አምልኮ ውስጥ የሰጠምኩት አንበል! አላህን ብዙ በመጥራት እጽዋትና እንስሳት ሊበልጡን ይችላሉ። የገባህን ነገር ለማስተማር፣ የሰዎችን ስህተት ለማስረዳት ልባቸው ውስጥ ለመግባት አትጣር። ልባቸው ውስጥ ያለውን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው። በአንተ አጠራር የሆነ ስም የምትሰጠው "ሙስሊም" አላህ ጋር የተለየ ስም ሊኖረው ይችላልና አውቃለሁ/እኔ ነኝ የማውቅላችሁ ከማለት "ኢጎ" አላህ ይፈውሰን!

አላህ ያስረዳን

Best kerim

25 Nov, 18:00


ቁርኣን ከመቅራት ስንዘናጋ አንድ የቁርኣን ገጽ ማንበብ ወደ 5000 የሚደርስ ሐሰናት እንደሚያስገኝ፣ አንድ ጁዝ ደግሞ 100 ሺ ሐሰናት አከባቢ እንደሚገኝበት፣ አንድ ጊዜ ማኽተም ደግሞ ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጋ ሐሰናት እንደሚይዝ ማስታወስ አስፈላጊ ነው።

ይህ ቁጥራዊ ስሌት ምንዳ ብሎ በሐዲሱ በመጣበት አግባብ ነው። ምንድነው ቁጥሩ የሚወክለው ሌላ ማዕና ይኖረዋል። እርግጥ ጌታችን አላህ ስንት በምንለው ቁጥር የሚመለክ አይደለም እርሱ የሚመለከው በዘውቅ ነው።

የኢማናችንን ልክ ለማወቅ ከፈገለግን ከቁርኣን ጋር የምንቀመጥበትን፣ በእርሱ ለመሥራት፣ እርሱን ለመረዳት የምንሞክርበትን ቆይታ መመርመር አስፈላጊ ነው። ሁለት ሰፍሐ ቀርተህ ብትተኛ 10 ሺሕ ሐሰናት ማለት ነው። ከሞትን በኋላ አንዲት ሐሰና እንኳን በነፍሳችን መስራት አንችልም የሰዎችን ዱዓ፣ ሰደቃና ሐሰናት እንዲደርሰን እኮ እንማጸናለን?!

ታዲያ ቁርኣንን መረዳት ቢያቅተን፣ ማስተንተን ቢከብደን በቋሚነት ከገጾቹ መካከል ለዕለት መድበን መቅራትን መነፈግ የለብንም። የቁርኣን ዊርዱን የጠበቀ ሰው ዋሪዳም አያጣም።

አላህ ፋሕሙንም፣ ዊርዱንም ይረዝቀና

ያ አላህ

Best kerim

25 Nov, 14:17


የሌሎችን "ሥልጣኔ" ስንጠቀም ዓላማው ሊገባን ይገባል። ለምሳሌ እንደ ሶሻል ሚድያ ያሉ መጠቃቀሚያዎች በዋናነት ስለራሳችን እና ስለ "ኢጎኣችን" አብዝተን እንድንሰራ የሚገፋፋ ቴክኖሎጂ ነው። በዚህም የተከታይ ብዛትና የጥቅም ሽልማቶችም የተዘጋጀበት ወጥመድ ነው። እዚህ መድረክ ላይ የሚመጣ የእምነት ሰው ከዚህ በተቃራኒ መንገድ ላይ ያሉ እሴቶቹን ይዞ እስካልመጣ ድረስ ስለ ታላላቅ የእምነት ጉዳዮች ቢያወራ ራሱ ተከታዩ የሚመለከተውና የሚቀበለው ዝናውን፣ መጠቃቀሚያውን፣ ኪሱን፣ የሚጠቀማቸውን የቴክኖሎጂ ግብኣቶች እንጂ ሌላ ነገርን አይደለም። አንዳንድ ዝነኞች (ታዋቂ የእምነት ሰዎች) በርካታ ተከታዮቻቸውን ይዘው አመታት መዝለቅ እንጂ የሚያወርሷቸው እሴቶች፣ የሚያስለምዷቸው አምልኮዎች፣ የአዝካርና የሰለዋት ልምዶች ከሌሉ ጥቅሙ ለራሳቸው እንጂ ለተከታዮቻቸው አይደለም። ልብ በሉ! በኢማን ውስጥ የሚገኝ ዝና መክበሪያ ሳይኾን ሰዎችን የምናገልግልበት ከባድ አማና ነው። ሰዎች ዘንድ በእምነትህ እየታወቅክ በመጣህ ቁጥር ለእነርሱ ስለምታወርሰው ተግባራዊ ኢማናዊ እሴት መጨነቅህን አትርሳ!

አላህ ያስረዳና

Best kerim

25 Nov, 13:37


ከዐሥር በኃላ የአልዋቂዓህን ምዕራፍ የምናነብበት አፍታ እንውሰድ። የኢማሙ ሻዚሊን "ሒዝብ አልበሕር"ን ብንጨምርበት ደግሞ የበለጠ መልካም ልምድ ይኾንልናል።

ከሰሐቦች መካከል ለልጆቹ ይህን ምዕራፍ በማውረሱ ደሕንነት የሚሰማው ሰሐባ ነበር። መቼስ ሰዎች ስንባል እንደ "ድኽነት" የምንፈራው ነገር የለም! ለዚህ ከቀረቡ መንፈሳዊ መፍትሔዎች መካከል አንዱ ይህን ምዕራፍ ማንበብ ነው። በተከታታይነት ያለማቋረጥ በማድረግ ውስጥ ብዙ መልሶች እናገኛለን። ከድኽነት ውስጥ ዋነኛው አላህ በጻፋቸው ነገሮች ላይ ልብ ወደዶ መቀበል አለመቻሉ ነው።

ይህን ምዕራፍ በመካከለኛ አቀራር 4 ደቂቃ በቂ ነው።

ይረዝቀና!

Best kerim

24 Nov, 18:01


ሸይኽ ሸሪፍ ሑሰይን (አላህ ይጠብቃቸው) በአልዒምራን CMC መድረሳ በቁርኣን ተፍሲር ኢጃዛ ለሰጧቸው ተማሪዎች በተገኙበት ምረቃ ላይ የተሰጣቸው የዕውቅና ሽልማት።

ከዒልማቸው በረከት አላህ ያድለና

Best kerim

24 Nov, 05:37


#በረካን_ውሰዱ

እንቅልፍን ለመተኛት ስናቅድ በሰአቱ ላይ ብናቅድ የተሻለ ውጤታማ ነው። ከፈጅር ሰላት በኋላ ባለው ሰአት ላይ ለመተኛት በፍጹም አናቅድ። ሰአቱ የበረከት ነው። በየትኛውም እንቅስቀሰሴ ውስጥ በረከት የምንሸምትበት ወቅት ነው። ምን አልባት በበሽታ፣ በድካም እና በሌሎች አሳማኝ ምክንያቶች ከሚያርፉ ሰዎች ውጭ ሕጻናትን ሳይቀር ልናለማምዳቸው የሚገባ ጥሩ ልምድ ነው። አንዳንድ ሰዎች ምን ልሰራ ነው የምነሳው? የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። ይህ ስንፍና የወለደው ጥያቄ ነው። ወይም ደግሞ ለሰአቱ ያላቸው ግንዛቤ ደካማ ሆኖ ነው። ሁለቱም መታከም ያለበት በሽታ ነው። ቁርጡ በመኾን ይህን ሰአት ለንባብ፣ ለዚክር፣ ለቁርኣን፣ ለመማር፣ ለስፖርት እና ወዘተ ልንጠቀምበት ይገባል። ምንም ባንሰራ የጸሐይ መውጪያ ሰአቱ ላይ ዎክ በማድረግ አየሩን በመሳብ ውብ የኢማንና የበረከት ንፋስ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ከፈጅር በኋላ እስከ ንጋት በእንቅልፍ ማሳለፍ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) Life style (የሕይወት ዘይቤ) አይደለም። ይህን ጘፍላን (ዝንጉነትን) የሚያወርሰውን ባሕል ለማስወገድ መታገል ወሳኝ ነው።

አላህ ያስረዳና

Best kerim

21 Nov, 19:11


Live stream finished (11 minutes)

Best kerim

21 Nov, 18:59


Live stream started

Best kerim

21 Nov, 18:46


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦

«በጁምዓ ለሊትና በቀኑ ዕለት ሰለዋት ማውረድን አብዙ፥ ሰለዋታችሁ ወደ ይቀርባልና።»

“ሰለዋት አብዙ” ማለት በሰለዋት ተጠመዱ ማለት ነው። "ሰለዋታችሁ ወደ እኔ ይቀርባል" ማለት ደግሞ አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ሰለዋታችሁን ያቀርብልኛል ማለት ነው።

ኡመት ታዲያ በሰለዋት ለመጠመድ፣ ሰለዋትን ለመረዳት ሰንሰለቱን የጠበቁ የዑለሞች እገዛ ያስፈልገዋል። ዑለማእ የአንቢያ ወራሽ ነውና!

ኸይርን ለማካፈል የማይሰስቱት በተሰዉፍ መንገድ ላይ ያለፉት ድንቅ ዐሊሞች/ሱፍዮቹ በርካታ የሰለዋት መድብሎችን አዘጋጅተውልናል።

በግንባር ቀደምነት ከሚታወቁ ምርጥ ዐለም ዐቀፍና ሺ አመታት ካስቆጠሩ የሰለዋት ኪታቦች መካከል ሦስቱን ድንቅ ኪታቦች ናቸውና እንጠቀምባቸው።

የኢማም ቡሰይሪ "ቡርዳ"
የኢማም ጀዙሊይ "ደላኢል ኸይራት"
የኢማም ዐብዱልጀሊል "ተንቢህ አልኣናም"

በሰለዋት ባህር ውስጥ እንድንሰጥም ላገዙን ድንቅ ዐሊሞች ጀዛቸውን ይክፈላቸው!!

በመረጣችሁት ኪታብ ሰለዋቱ ላይ በርቱ እንበርታ! አላህ ወፍቆን ከሦስቱም በረከት የምናገኝበት ለሉትና የጁምዓ ዕለት ያድርግልና!

ምስል፦ መዲነቱል ሙነወራ በምሽት

Best kerim

21 Nov, 14:47


https://t.me/Noor_Musela/4860

Best kerim

21 Nov, 11:18


የዑምራ ፓኬጅ ለምታሳልጡ ኤጀንቶች ነጻ የቢዝነስ ሐሳብ ልቸራችሁ። በየዙሩ ላይ የምትወስዷቸውን ሰዎች የሰለዋት ዚክሮችን አስለምዷቸው። በተለይም በመዲና ግዛት ላይ ደጋግመው የኢማም ቡሰይሪን "ቡርዳን" በውብ ዜማዎች እንዲሉ አስለምዷቸው። ቢዝነሱን በማይበረባ መንፈስ አልባ ፕሮግራም እንዳይደርቅ አግዙት። ካልሆነ ሐይኪንግ ነው የምታደርጉብን!

አላህ ይርዳችሁ!

Best kerim

20 Nov, 12:14


#የረቡዕ_መጅሊስ_ወግ
#አወሊያዎቹ

ይህ ሰአት ዱዓ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅት ነው። ረቡእ በዝሁር እና ዐሥር መካከል ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው በሐዲስ መጥቷል። ከእያንዳንዱ ቀናት ጀርባ በርካታ ምሥጢሮችን የተረዱ ዓሊሞች ቀናቱን ከፋፍለው ዱዓና ሰለዋቶች በማደረግ ዘመን የሚበትነውን ጘፍላ መርታት ችለዋል።

በመጅሊስ ኒያ ሥራ ላይ ላላችሁ፣ እንዲሁም ተመችቷችሁ ዱዓ ለተቀመጣችሁ ሰዎች የሁለት አውሊያዎችን ገጠመኝ ላወጋችሁ ወደድሁ።

በቅርብ ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበሩት ኢማም ሻዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) መዲና ዚያራ በማድረግ ላይ ሳሉ የሰይዲን ዶሪሕ ተበሩክ ሲያደርጉ አንድ ሹርጣ (ፖሊስ) መጥቶ ይህ "ቢድዓ" ነው ብሎ ይከለክላቸዋል። አውሊያ መች የክርክር ናዳ ውስጥ ይገባል። ብዙ ካስረዱት በኋላ እንኳን እርሳቸውን በከበበው ነገር ቀርቶ አንተ እዚህ ኺድማ ላይ ባለኸው እንኳን እባረካለሁ ብለው ሰውነቱን አሻሽተው በረካውን ወሰዱ። :-D (ዝርዝር ጭውውታቸውን ከዚህ ቀደም አጋርቼው ነበር።)

አይ ዑለማ! ልባቸው ሰፊ ነው፣ ከማይረዳቸው ሰው እንኳን መወሰድ ያለበትን ያውቃሉ። ፖሊሱ እምነቱን በተዳረዳው ልክ ነበር ግና ያላየው ዕይታ ነበር እርሱን አስተማሩት ምን አልባትም ልቡን ጠረጉለት

****

አንጋፋዊው ዛሒድ የነበሩት ኢብራሂም ቢን አድሀም (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ጊዜ ወደ ሻም ጉዞ ሲያደርጉ የገጠማቸውን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ በመንገድ ላይ ሳለሁ ውሃ ጠማኝና አንድ ፍየል ጠባቂ እረኛ ስመለከት ተጠጋሁና እንዲህ አልኩት፦ የሚጠጣ ወተት ወይም ውሃ ይኖርሀል?
እንዲህ አለ፦ የትኛው ቢመጣልህ ትወዳለህ?
"ውሃ" ስል መለስኩ። በያዘው ልምጭ መሬቱን ሲወጋው ውሃ መፍለቅ ጀመረ! በጣም ተገረምኩ።
"አትገረም ጠጣ" አለኝ። ውሃውን ጠጣሁት ከበረዶ የቀዘቀዘ ከማር የጣፈጠ ውሃ ነበር። እያየሁት ቆሜ ቀረሁ። ከዚያም ይህ እረኛ እንዲህ አለኝ፦ « ኢብኑ አድሀም አንድ ባርያ አላህን ከታዘዘ ሁሉም ነገር ይታዘዘዋል።»

ምንጭ፦ [ሲየር ኢዕላም አኑበላእ ወሒሊየቱ አልአውሊያ]

አላህ የአውሊያዎችንና የዑለማዎችን ቀድር ያሳውቀና

Best kerim

19 Nov, 18:15


አንዳንድ ሰዎች ጋር ስትደውል ብቻ ወደ ቀና መንገድ ይመልሱሀል። ስርዓት ያስተምሩሃል፣ በዚያው ከእነርሱ መማር ትጀምራለህ። ለምሳሌ፦ ስትደውልላቸው መስጂድ ገብቻለሁ ቆይተው ይደውሉ ይሉሃል። ሰአቱን ስትመለከት የመስጂድ ሰአት ላይመስልህ ይችላል ወይም ከወቅቱ አስቀድመው ገብተውም ይኾናል። በሌላ ወቅት ስትደውል ቁርኣን የማነብበት ሰአት ነው አሁን ይሉሃል፣ በሌላ ወቅት እንዲሁ ስትደውልና ስትላመዳቸው የአውራድ ሰአታቸውንም መለየት ትችላለህ። ቆም ብለህ እኔስ መቼ ነው ለዚክርና አውራድ የተመደበ ሰአት ያለኝ ብለህ ትጠይቃለህ!

በጊዜ ሒደት እነዚህ ሰዎች ማሕበረሰብ ውስጥ ብቻ በመኖራቸው ለማሕበረሰብ መድሐኒት ይኾናሉ። ለውስጥ ስክነት መንገድ ከሚፈልጉልህ እንዲህ ዐይነት ሰዎች ጋር መወዳጀት ራስህን ኾነ ዙሪያህን ማዳን ነው።

ስናያቸው አላህን የሚያስታውሱን ሰዎች ካሉን እናመስግን!

አላህ ያብዛልና

Best kerim

19 Nov, 18:10


ለማስታወሻ ያህል

ፍጡራንን አስመልክቶ የሚያደርጉት ነገር ኹሉ የተጻፈ ነው። የዝህችን ምድር ብርሀን ከማየታችን አስቀድሞ ስለእኛ በመዝገባችን ላይ ተጽፏል። ስለየትኛውም የሚገጥመን ነገር መጨነቅና መጠበብ ትርፉ ነፍስን መጉዳትና ማስጨነቅ እንጂ ሌላ ምንም የለውም። ረጅሙን መንገድ ቀጥል፣ የሚቻለውን ነገር ኹሉ በመፈጸም ላይ ታገል። ነገሮችህን ኹሉ ለእርሱ ብቻ ስጥ። ባሪያ ምን መብት አለው?! ዝም ብሎ አይደል የሚኖረው?!

ለአላህ የሚደረግ ባርነት (ዑቡዲያ) ደግሞ ትክክለኛውን ነጻነት ያወርሳል። ወዳጅ ከወዳጁ ጋር በሚገናኝበት ውድቅት ላይ ተነስቶ አስረዳኝ ብሎ መማጸን፣ ይህን የተወሳሰበ ዐለም ለመረዳት ያግዛል።

አላህ የልብ ንቃት ይለግሰን

Best kerim

19 Nov, 02:43


#የበረካው_ወቅት

አሰላቱ ኸይሩን ሚንነውም

ሰላት ከእንቅልፍ ትበልጣለች

ሲል የፈጅር ሙኣዚኑ

ምላሻችን፦ “ሰደቅተ ወበረርተ” “

ዐሊሞቹ ይህን ሲያብራሩ "ሰደቅት" ማለት አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያሉት ነገር ትክክል ነው። "ወበረርት" የሚለው ደግሞ አንቱ እኛን በማስተማርዎ ሰበብ ከተመረጡት ባርያዎች መካከል እንድንሆን አደረጉን ይህንን ቃል እንድንመልስ ከእንቅልፍ የምትበልጠውን ሰላትም እንድንሰግድ አደረጉን።

አላህ ከዚህ ምርጥ በረከት አይከልክለና!

Best kerim

18 Nov, 10:33


የ10 ደቂቃ በረከት!

ቅርብ ሰአት ዝሁር መስጂድ ልሰግድ ገባሁና። አዝካርና የዝሁር አውራድን ዐስር ደቂቃ ባለሞላ ደቂቃዎች ጨርሼ ልወጣ ስል "ዐሥር ደቂቃ" ለቁርኣን ብጨምር ምን አለበት? ስል ራሴን ጠየቅሁ? የተራራ ያህል ከበደኝ። እንድምንም ታግዬ ጨመርኩ። ከዛስ? ደቂቃዎቹ ጅማሬ ላይ እስከ 3 ደቂቃ ከባድ ነበር። ከዚያ በኋላ ግን መጣፈጥ፣ መረጋጋት፣ መስከን ይጀምራል። ከዚያ ማቋረጥ ኹላ ይከብዳል።

አንዳንዴ ድብርትና ድባቴ ከየት መጡ ሳይባል ውርር ያደርጉናል፣ ዝም ብሎ አልቅስ አልቅስ የሚል ስሜትም ይመጣብናል፣ ዝም ብሎም ይከፋናል ይደብረናል። ሰው አይደለን? ታዲያ ሁሌ እኛ ላይ የሚመጣ ችግር እንዳልኾነ መረዳት አለብን። ይህ እክል ሲመጣብን "ዐስር ደቂቃ" መስጂድ ላይ ቁጭ ብለን ቁርኣንን እንዳለን መረዳት ብንቀራበት። የሚገርም የመሰብሰብ፣ የመርጋትና የማናቀው የደስታ ስሜት እናገኛለን። የ 10 ደቂቃ ርዝማኔ ያለው የቁርኣን ንባብ ለሕይወታችን በረካ ካስገኘ ከቁርኣን ጋር ለመቀራረብ ብንሞክር ምን ዓይነት ኡንስ (ደስታ) እናገኝ ይኾን?!

አላህ ይህን ቁርኣን ማንበቡን፣ መረዳቱን፣ በእርሱ መጠቀሙን፣ በእርሱ መታከምን አይከልክለና

ያ አላህ

Best kerim

18 Nov, 07:01


''ተምሬ የት ልደርስ?'' የሚለው አስተሳሰብ እየሰፋና እየሰረገ መምጣቱ አላሳሰባችሁም?

የምር ከማልጠብቃቸው ሰዎች ሁሉ መስማት ጀምሬአለሁ። ብቸኛው የችግር መፍቻ ቁልፍ ንግድ/ ''business'' እንደሆነ ብቻ እየታሰበ መምጣቱ አሳሳቢ ብቻ ሳይሆን ልክ ያልሆነም ነው። በአንድ ዘርፍ ብቻ ዓለም ልትቆም አትችልም።

በታላላቅ ሃይማኖቶች አስተምህሮ የፈጣሪ ስጦታ የተለያየ እንደሆነ ተነግሮናል። ንግድ ጥበብ ነው። ሁላችንም ነጋዴ ልንሆን አንችልም። ምርጥ ነጋዴ ለመሆን ራሱ ከፈጣሪ የተሰጠህን ጸጋ በትምህርትና በክሂሎት ልታሳድገው/ልታበለጽገው ግድ ነው። እሺ አንተ ነጋዴ ሆንክ፤

- ልጅህን ማስተማር የምትፈልገው የት ነው? መርካቶ ነው?
- ስኳር ሕመምተኛ ሆንክ። የት ልትሔድ ነው?
- ንብረትህን/እድሜህን የሚያሳጣ ችግር ገጠመህ። ጠበቃው ከየት ሊመጣ ነው?
- ልጅህ የመደፈር አደጋ ደረሰባት። ማንን ልትጠራ ነው?
- ሚስትህ ምጥ አፋፋማት፤ ማን ጋ ልትሮጥ ነው?
- ታክስ አናትህ ላይ ቢቆለል ማንን ልታማክር ነው?
- በቅርቡ የሚደረመስ ሕንፃ መሥራት ነው የምትፈልገው?
- ገንዘብህ በአግባቡ ማኔጅ መደረግ የለበትም?
- አዳዲስ ግኝቶችን የሚያመጡልን ተመራማሪዎች አያስፈልጉንም?
.
.
.
ሁላችንም ነጋዴ መሆን አንችልም። ከፈጣሪ የተሰጠንን የተለያየ ጥበብ በትምህርትና ክሂሎት ካዳበርን ባለጸጋነትን የሚከለክለን የለም።

መሠረትን ማናጋት ሁሉንም ሥርዓት ማናጋት ነው። ትምህርት የሁሉም ሥርዓቶች መሠረት ነው። የትምህርት ሥርዓት መበላሸት እና በትምህርት ተስፋ መቁረጥ በሁሉም ሥርዓቶች ላይ ለመቆጣጠር የሚያዳግት የካንሰር ሴል እንደመዝራት ያለ ነው።

በ ዶክተር Hawlet Ahmed የተዘጋጀ ጥሩ ማስታወሻ ነው። ለሌሎች ወገኖቻችሁ አስተላልፉ።

Best kerim

17 Nov, 13:08


Channel photo updated

Best kerim

17 Nov, 04:02


https://www.facebook.com/share/15Y2WVUBiS/

Best kerim

17 Nov, 03:54


https://www.facebook.com/share/p/14WNtDXbMw/

Best kerim

17 Nov, 03:05


የጥዋት አዝካር አብረን እንበል

https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

15 Nov, 16:52


ጥቆማ ለሴቶች!

ቅዳሜ ጥዋታችሁን ከ 3:30–4:30 CMC የሚገኘው አልዒምራን መስጂድ ከተገኛችሁ በማያጠራጥር ኹኔታ ኢማናችሁ ታድሶ፣ ውስጣችሁ በደስታ ተሞልቶ፣ አስገራሚ ለውጥ የምታገኙበት የሲራ (ሰለዋቶች) በሸይኽ ዓዲል (አላህ ይጠብቃቸው) ተዘጋጅቶላችኋል። ሸይኽ ሲራ አላቸው ከተባለ ምንም ጥያቄና መልስ አያስፈልገውም የትም መገኘት ነው። በሕይወቴ ከተደስትኩባቸው መጃሊሶች ውስጥ የሲራ መጅሊሳቸው በጣም ውብ የሚባለው ነው። ሴቶች በተለይም ነገን እረፍት ያላችሁ መሄድ የምትችሉ ተካፈሉ።

ተርቢያም፣ መንፈስም በመማር ታተርፋላችሁ ኢንሻአላህ

አስተላልፉ!

Best kerim

15 Nov, 08:38


https://youtu.be/qwwKXqFrWn0?si=g0Mw3EwQgc-kQg_P

Best kerim

15 Nov, 08:38


https://www.facebook.com/share/r/1EuMB5Pcgy/

Best kerim

14 Nov, 18:50


ሰለዋት ለኹሉ ችግር መፍትሔ እንደኾነ ካወቅን ሰለዋት የምናወርድበትን መንገድ አብሮ መረዳትም አስፈላጊ ነው። በደፈናው የሚታወቁ ትምሕርቶች መሬት ላይ ወርደው ትክክለኛ አተገባበር የሚያስተምሩ "ሙረቢዎች" ከሌሉት ጥቅሙ አናሳ ነው። ለዚህ ነው የተሰዉፍ ሊቃውንቶች በተለይም የሐበሻ ዑለማዎች ለሰለዋት ትልቅ ትኩረት በመስጠት በመጅሊሳቸው (መቀማመጣቸው) ላይ ኹሉ ሰለዋትን ለተከታዮቻቸው ያለማምዳሉ። እነርሱ ዘንድ የሚቀማመጠው ኹሉ ዐሊም/ፈቂህ ለመኾን እንደማይመጣ ስለገባቸው የሰለዋትና ዚክር ልማድ እንዲኖረው ከአላህ ጋር እንዴት በረጅሙ መቀማመጥ እንደሚቻል አስተማሩ።

ከእኛ በዕውቀት/መረጃ የሚያንሱ ግና በረጃጅም ሁኔታ ከአላህ ጋር መቀማመጥ የቻሉ እናትና አባቶቻችን ይህን ልምድ የወሰዱት ከደጋጎቹ ዑለማዎች ነው። አሁንም ማሕበረሰብ የሚድነው በጥንቱ በረሱሊላህ (ሰላለሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወራሾች በዑለሞቹ መንገድ ነው። ያለፉበትን መንገድ በመመርመር ዕውቀትና መንፈስን አብሮ በማስኬድ ሰለዋትና ዚክር በማጣመር መጓዝ አስፈላጊ ነው።

ለሰለዋት ብለን የምንቀመጥበት ጊዜዎች ይኑሩን፣ ለዱዓና ዚክር መጃሊስ ብለን የምንሰባሰብባቸው የቤተሰብ ሐድራዎች ይኑረን። ልጆቻችንን እና ቤተሰቦችን መጠበቅ የምንችለው በመሰል መጃሊሰ ዚክር፣ በሐለቀተ ተዓሊምና በአምልኮዎች ነው።

አላህ ያግራልን፤ ያስረዳን

ለሰለዋት የተገራ ለይል ያድርግልን

Best kerim

14 Nov, 11:10


#ዑዝላ_ጤንነት_ነው

ዑዝላ ማለት መነጠል፣ መገለል ማለት ነው። በርካታ ፍቺዎች ያሉትን ታላላቆች የሰሩበት ነፍስን ማዳኛ፣ መንፈሳዊነትን ማጎልበቻ መንገድ ነው። የመጨረሻ መጨረሻ ደረጃ የሚባለው ትርጓሜው ከሰዎችና ከክፉ ሐሳቦቻቸው፣ ለዱንያም ለአኺራም ከማይጠቀመው ሐሳባቸው የምንገለልበት መንገድ ነው። ልክ የካህፍ (ዋሻው) ሰዎች ከአምባገነኑ አገዛዝ ራሳቸውን እንዳሸሹት፣ ልክ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) በሒራ ዋሻ ውስጥ እንደተገለሉት።

በዛሬ ዘመን ሚድያዎች በተለያየ ቅርጽ የሰዎች ውስጥ እንዳይረጋጋ ይቆምራሉ። ሆነ ብለው ይህን የሚሰሩ የሚድያ ቅርጾች እንዳሉ ኹሉ የሌሎችን መንፈስ የሚያራግፉም አልሉ።

  ትዳር ከብዶ ዝሙት ከቀለለ፣ ሕይወት አሰልቺ ኾኖ ሞትን ካስመኘ፣ ሓይማኖታዊ ሰበካዎች ሞልተው ኢማን (እምነት) ከጠፋ፣ አስተማሪዎች ከተማሪዎች ጋር ከተመሳሰሉ የሕግ አስከባሪዎችና ጠባቂዎች ዘራፊ ሲኾን ስታይ ከቀውሱና ንትርኩ ራስህን በማግለል፣ ከማይመለከተን ቦታ በመራቅ ነፍስን መታደግ ያስፈልጋል። 

ስታያቸው አላህን ከማያስታውሱህ፣ አብረኻቸው ስትቀማመጥ የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከማያስናፍቁህ ሰዎች፣ ክህሎትን ከማታሳድግባቸው፣ ከማትማርባቸውና ከማትዝናናባቸው ሰዎች መራቅን መለማመድ አስፈላጊ መንፈሳዊ ልምምድ ነው። የምትፈጥርባቸው አዎንታዊ ለውጥ ወይም ትክክለኛ የዐላማ ግንኙነት ከሌለህ አብሮ መዛለቁ ጥቅም የለውም። ይህ ክፋት አይደለም ይህ እውነተኛው መረዳዳት ነው።

ከተለመዱ ስብስቦችህ ውስጥ የኢማን እድገት ከሌለ፣ የአስተሳሰብ ልሕቀት ካልተፈጠረ ምንም አታደርግም መንገድ ለመቀየር ደፋር ኹን። ምንም ዓላማ ከሌለህ አከባቢ ብዙ ሰአት በማባከን ጊዜህን አታጥፋ። ከስበህ (ሰርተህ) ለቤትህ የምታመጣውና ምንዳ የምታገኝበት ቦታ ላይ ኒያን በማስተካከል ከአላስፈላጊ ነገሮች ራስህን ማቀብ ከቻልክ ይህ በራሱ ዑዝላ ነው።

ከማይጠቅሙ የሚድያ አጠቃቀሞች መሸሽ፣ ከአላስፈላጊ ስብስቦች ራስን ማቀብ (ሃይማኖታዊ ቢኾኑም እንኳን) ቅርብ ለኾነው ሞት እንድንዘጋጅ ያግዛል።

ዑዝላ ኒያ ይፈልጋል። ዑዝላ ከሐቅ መሸሽ አይደለም፣ ከመታገል መታቀብ አይደለም፣ አለመጋፈጥም አይደለም። ሀይል ማሰባሰቢያ ነው፣ ዐዲስ መንገዶችን የምንፈልግበት መንገድ ነው፣ የተበላሹ ነገሮችን ከትክክለኛው ነገር የምንለይበት መንገድ ነው። በተለይ ወጣቶች (ተማሪዎች) ስብስቦች የሚያድናቸውን ያህል እራሳቸውን እንዳይመለከቱም ስለሚያደርጋቸው ከበርካታ ጥፋቶች እንዲታደጉ ሲባል የወላጆች ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ ያሻቸዋል። በመገለልና በመሰባሰብ መካከል ያለውንም ልዩነት እንዲረዱ በማስቻል መገለላቸውን ለጥፋት አለማዋላቸውን ማጣራት ያሻዋል።

በመገለል ውስጥ ሊሰሩ ከሚችሉ በርካታ ነገሮች መካከል ዋነኛውም አምልኮኣዊ ተግባራት ናቸው። አካላዊ ጤንነትን ለመጠበቅ፣ አዕምሮኣዊ ደህንነትንም ለመንከባከብ አስፈላጊው መንፈሳዊ ልምምድ ነው። ከሰዎች በምንነጠልበት ጊዜ ከአላህ ጋር ብዙ ለማውጋት ስለሚረዱ ከለመድናቸው ቦታዎች ስንሸሽ ሌሎች ዐዳዲስ ቦታዎች ላይ በዐዲስ ባሕርይ መገኘትም እንችላለን ማለት ነው።

አላህ ያስረዳና

በመቀላቀል ውስጥ ከሚመጣ በላእ ይጠብቀን

Best kerim

14 Nov, 09:28


ልጆች ትምሕርት ቤት መውሰድ ሌላ ራሱን የቻለ ትልቅ ሥራ ነው። በዚህ መሀል ግን የዕለትን ንቃት ይሰሩልሃል፣ የዱንያን ዓላማ እንድታስታውስ ያደርጉሀል። ልጆችህን የማድረስ ኃላፊነት አንተ/አንቺ ጋር ከመጣ አንድም የልጆችን ባሕርያቸውን ለመቅረጽ ምቹ አጋጣሚ ሲኾን፣ ሌላኛው ጥቅሙ ለራስ ነው። የተሻለ ሞራልና ንቃት ላይ እንድንኾን ያስገድዱናል። ልጆች ብርቱና የተሻለ መንፈሳዊ ንቃት ካላዩብን እኛን የመከተልና የማደመጥ ብሎም የመታዘዝ ዝግጁነት አይኖራቸውም። እባካችሁ የራሳችሁንም ኾነ የሌሎችን ልጆች የምታመላለሱ ሰዎች ሆይ ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት የተቻላችሁን ጥረት አበርክቱ።

ልጆችን በትክክል ማነጽ የሚቻለው መንፈሳዊ ማንነታቸው ላይ አሻራ በማሳረፍ ነው። ከውስጣቸው ያለውን መልካም ነገር በመጥፎ እንዳይለወጥ ዘወትር ጥቂት ድጋፍ ከተደረገላቸው በቂ ነው። ልጆች የዘወትር ከባቢያቸውን መልካምና ጤናማ እሳቤዎች ወደውስጣቸው እንዲዘልቅ በማድረግ ባሕርያቸውን መንከባከብ ይቻላል። ከመሳሰሉት ጥረቶች ጋር ዘወትር በሰላቶች መካከል ዱዓም ልናደርግላቸው ይገባል።

አላህ ልጆቻችንን ይባርክልን፤ ለሀገር ለወገን ጠቃሚ ያድርጋቸው!

Best kerim

13 Nov, 18:21


«እኔ በተመረጠው በሙሐመድ ﷺ መንገድ ላይ ያለሁ ብናኝ አቧራ ነኝ።»

ሰይድና ሩሚይ (ቁዲሰ ሲረሁ)

ዐረፎቹ እምነትን ለመረዳት አላህን ለማወቅ ሲሉ በሰይዲ መንገድ ላይ ነፍሳቸውን ለመርታት ትግል አደረጉ። በሰፊው እምነት ውስጥ በመጥፋት ለዘላለም ማብራት ቻሉ። እምነት ራስን (ነፍስያን) የምትገድልበት ሰፊ ቤት ነው። እምነት ራስን (ነፍሲያን) እና ዝንባሌን በመግታት አላህን የምናውቅበት ሱሉክ ነው። እምነት በየዕለቱ ሰዎች ራሳቸውን፣ ክፋታቸውን፣ ወንጀላቸውን የሚረዱበት ዓለም ነው። ሰይዲ ሩሚ (ቁዲሰ ሲረሁ) በአንድ ኪታባቸው ላይ እንዲሁ "አንተ ማለት የወንጀልህ ድግምግሞሽ ውጤት ነህ።" ይለናል። የምንሰራቸው ስህተቶች፣ ወንጀሎቻችን ማለት ሁሌ የውድቀታችን ምልክት አይደሉም። አንዳንዴ መነሻችን፣ ወደ ንሰሐ በራፍ መጠጊያችን ናቸው። በ "እምነት" የተሸፈነ የነፍስያ እስር ቤት ከመግባት በጸጸት የታጀብ ወንጀል ውስጥ መኾን ያድናል። እምነት ውስጥ መጥቶ ነፍሲያን ከማስተዋወቅ ነፍሲያን በእምነት መርህ መግደል ይበረተታል። የአምልኮዎች ግብ የነፍሲያን እብሪት ማስተንፈስ ነው። የአምልኮ ግብ ትህትናን ማላበስ ነው፣ የአምልኮ ግብ ባርነትን ማንገስ ነው። አምልኮ በሰዎች ላይ፣ በሃይማኖቶች ላይ የበላይነትን መቀዳጀት ሳይኾን በየዕለቱ ነፍስያን መታገል መቻል ነው።

አላህ ያስረዳና

መልካም ለሊት

Best kerim

13 Nov, 15:46


ምሕረት ስንለምን (ኢስቲግፋር) ስናደርግ ለአማኞችም ምሕረት እንድንለምን በሐዲሶች ላይ መጥቷል ዑለማዎችም ያበረታታሉ።

ለአማኞች ምሕረት በመለመናችን ሰበብ ኡመት (ሕዝቦች) ላይ የሚደርሰውን ችግር አላህ ሊገፈትርልን ይችላልና።

"አስተግፊሩላሀ ሊልሙእሚኒነ ወልሙእሚናት"

Best kerim

13 Nov, 13:34


አማኞች" ሚን ሐይሱ ላ የሕተሲብ" ይረዘቃሉ!

የትኛውም ሪዝቅ (ሲሳይ) እኛ ባላቀድነው ኹኔታ ሲመጣ ውብ ነው። እኛ አቀድነው በሚመስል ሁኔታ ከሚመጡ ሪዝቆች በላይ ሁሌ በላጩ ባልገመትናቸው ኹኔታ የሚመጡት ናቸው።

ሪዝቅ ሰፊ ነው፤ መረዳቱ፣ ጥንድህን ማግኘቱ፣ ጓደኛ ቤተሰብ ማግኘቱ፣ ስራው፣ ገንዘቡ፣ ጤናው .... ወዘተ እነዚህን ኹሉ ሪዝቆች ስንፈልግ አዕምሮኣችን በሚጠይቀው ልክ ብቻ ሲኾን የውስጥ እርካታን ይነፍጋሉ። የተሰጡን ሪዝቆች፣ የሚለገሱን ጸጋዎች ብንቆጥራቸው ተቆጥረው የሚዘለቁ አይደሉም።

የሰው ልጅ እንደመኾናችን መጠን ሁሌም ለፍተን ስለማግኘት፣ በጥረታችን ስለማደግ እንመኛለን። ግና አላህ ያለምንም ድካምና እንግልት ሪዝቃችንን ከደጃፋችን ያደርግልን ይኾናል። የማየትና የማገናዘብ ነገሩን አይውሰድብን ማለት ነው።

የሰው ልጅ ያለውን እንዳይመለከትና እንዳይረካ አልሞ የሚሰራው ሰይጣን ደግሞ ዋና ሥራው የአላህ ባሪያዎች እንዳያመሰግኑ በማድረግ ነው። በሞላ ሕይወታችን ውስጥ እንከናችንን ለቅሞ ያሳየናል። በምቾታችንም ኾነ በእንግልታችን ጊዜ አመስጋኝነት ከውስጣችን ካልተወገደ ውስጣችን ሰላምን ያገናኛል። ከዚያ ውጭ በተቃራኒው በሁሉም ሕይወት ላይ ማማረርን ካስቀደምን የሕይወት ጥፍጥና እየተወገደ ይመጣል።

በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ያለንን በመውደድ ያጣነውን በመታገስ ከአላህ ጋር ማውጋትን መምረጥ የአንድ ባርያ ማዕረጉ ነው።

ስለሁሉም ሲሳዮችህ አልሐምዱሊላህ

መረዳቱን ይረዝቀና

Best kerim

12 Nov, 18:14


#የኢማን_ኸበር

አነስ (ረዐ) ባስተላለፉ ሐዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦ ጀነት ሦስት ሰዎችን ትናፍቃለች። "ዐሊይን፣ዓማርን እና ሰልማንን" ሓኪም የዘገቡት ሐዲስ ነው። ሌሎችም የሐዲስ ሊቃውንቶች ዘግበውታል።

ወማ አድራከ ዐሊዩን ወዓማሩን ወሰልማን?

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐዲሶችን በልቡና ኾኖ መስማት ውስጥን ያረሰርሳል። ሰለዋት የማብዛት ጥቅሙ ቁርኣኑና ሐዲሱ የያዘውን በርካታ መንፈሳዊ ትርጉም ለመረዳት ስለሚያግዝም ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለባልደረቦቻቸው ወደፊት ስለሚኾነው፣ ነገ ዕለተ ትንሳኤ ስለሚፈጠረውም ነገር እንዲሁም ከመፈጠራቸው በፊት ስለተከናወነውም ነገር ብዙ ብለዋል። አላህ የጊዜና የቦታን ገደብ አንስቶላቸው ብዙ ከአዕምሮ በላይ የኾኑ ኢማናዊ ጉዳዮችን አውግተውላቸዋል። በርካታ መመሪያዎችም የተላለፉት ታዲያ ከምድራዊ ሐሳብ በላይ የኾኑ ናቸው። ሰውኛ ሐሳቦች ኹሉ የመጣል የመነሳት ባህሪ ሲኖራቸው ሰማያዊው የመልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መንገድ ግን ቅዱሱ መንገድ ነው። አማኞች ይህን ቅዱሳዊ መለኮታዊ መንገድ መተገበር ቢሳናቸው ክብሩን መጠበቅና ከየትኛውም ምድራዊ ሐሳብ ጋር እንዳያመሳስሉት ይገደዳሉ። የመመሪያዎቹን ቅዱስነት መውደድና ማክበር በራሱ ከኢማን ነው። ሁሉም ምድራዊ ሐሳቦች በኢማን ኃይል ይስተካከሉ ከሆነ እንጂ ኢማን የየትኛውንም "ዘመናዊ" እሳቤ የሚከጅል አይደለም።

ከላይ የቀረበውን ሐዲስ የኪታብ ንባቤ ላይ ሳገኘው ለሰአታት እንዳስብበት እንዳስብ አደረገኝ፣ የደስታና የቅናት፣ የተስፋና የብርሃን ስሜት በውስጤ አጋባብኝ። የሰይዲ ሐዲሶችና የባልደረቦቻቸው ሕይወት ብቻውን መንፈሳዊና ኢማናዊ ፍንጣቂን የሚለግሱን ሥጦታዎች ናቸው።

አላህ ያስረዳና

Best kerim

11 Nov, 17:45


#እውነተኛው_ከራማ
#ሰው_መኾን

አንድ ዐሪፍ እንዲህ ተጠየቁ

መብረር የሚችለውን ሰውዬ ያውቁታል?

እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ ይህ ብዙ የሚያስገርም ነገር አይደለም ዝንቦችና ነፍሳትም ይበራሉ።

እከሌ የሚባለው ሰው ውሃ ላይ ይራመዳል ምን ይላሉ?

እንዲህ አሉ፦ ይህም እንዲሁ የሚያስገርም አይደለም። አንድ የእንጨት ቅርፊትም ውሃ ላይ መሄድ ይችላል።

ታዲያ ከራማ ምንድር ነው?

እንዲህ ብለው መለሱ፦ የሥነምግባር መርሆችን ሳትጥስ ሰዎች መካከል መሄድ፣ ሰዎችን አለማታለል፣ አለመስረቅ፣ አለማታለል፣ አለማማት፣ ከእምነታቸው አለመጉደል፣ ልባቸውን አለመስበር፣ በጥቅሉ ሰው መኾን መቻል ነው እውነተኛው ከራማ ማለት።

=====================================

🟧 ተሰውፍ ላይ አንድ መርሕ አልለ « ኢስቲቃማ (ጽናት) ከአራባ ከራማ (ተዓምር) ይበልጣል።»

"ሰውነት ይቀድማል" አሉ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር (አላህ ይጠብቃቸውና) ስለ ሰው ልጅ አፈጣጠር ዛቱና ሩሑ፣ ዐቅሉና ልቡ ሰውነቱን ሲያብራሩ ደጋግሜ ብሰማቸው ጥልቁን ትንተናቸውን ጨርሼ አልረዳው። ከባባድ ኪታቦችን በገለጥን ቁጥር ስለሰው ልጆች ባነበብን ቁጥር ንግግሮቻቸው ትዝ ቢሉኝ አወሳዋቸው። የአንድ ጎልማሳ ሰው ዕድሜን ያህል በተፍሲርና ማዕሪፋ ትምህርት የዘለቁት ታላቅ ሰው!

ሰው ያድርገና አላህ

ያስረዳን

Best kerim

11 Nov, 08:13


https://www.facebook.com/share/p/14qc76s6Zd/

Best kerim

10 Nov, 18:40


«اللَّهُمَّ قِني عذابك يوم تبعث عبادك».

«ጌታዬ ሆይ! ባሮችህን በምትቀሰቅስበት ጊዜ ከቅጣትህ ጠብቀኝ።»

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲተኙ በቀኝ ጎናቸው ቀኝ እጃቸውን ከፊታቸው ስር አድርገው ሦስት ጊዜ ይህን ተማጽኖ ያቀርቡ ነበር።

የመኝታ አደብ ላይ ከምንቀራቸው ዱዓዎች መካከል አንዱ ነው።

አላህ ያስረዳን

Best kerim

10 Nov, 17:57


#የምሽት_በረካ

ከመግሪብ ጀምሮ እስከ ኢሻ ሰአት ያለው አጭር ጊዜ ለብዙ የምሽት ዚክሮችና አውራዶች የተሰራ እስኪመስለኝ ድረስ ለመሰል ተግባራት ተባርኮ አገኘዋለሁ። ከዚያ ውጭ ላለ ነገር በምንም መልክ የተረጋጋ ጊዜ ኾኖ አይቼው አላውቅም። ከሰው ጋር በዚህ ሰአት ላውራ ብትል ምንም ያህል ሳታወራ ይመሻል፣ የኾነ ነገር ላንብብ ብትል እንዲሁ፣ መስጂድ መግሪብ ሰግደህ እስከኢሻ ዞር ዞር ልበል ብትል እንኳን ደቂቃ የቆየህ ሳይመስልህ የኢሻ ሰአት ይገባል። ታዲያ ከዚህ ምን ተማርሁ? ከመግሪብ ጀምሮ ያለውን ሰአት ከተቻለ እስከ ኢሻ ድረስ ከዚክርና ቁርኣን አውራድ ውጭ ምንም ነገር ላለመቀላቀል መጣር ነው። ይህን ልምድ ካደረግን በፍጥነት ወደመኝታ የመቅረብ ልምድን እናዳብራለን። ዚክሮቹና ቁርኣኑ በራሱ የእረፍትና የመረጋጋት ሥሜት ስለሚለግስ ጥሩ መኝታ ለማግኘት አንቸገርም።

አላህ ይረዝቀና

Best kerim

10 Nov, 16:02


https://t.me/Noor_Musela/4713

Best kerim

10 Nov, 03:41


የፈጅር ደርስ ጀምሯል https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

09 Nov, 18:27


#ስሙ_መድሐኒት_ነው

«ልክ ሕጻን ልጅ እናቱን እንደሚጠራው እኔም እጠራኻለሁ ጥሪው ለምንም ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን "አላህ.. አላህ ... አላህ" ብሎ ደጋግሞ መጥራትን ስለወደድሁ ነው።»

መውላና ጀላሉዲን አርሩሚይ (ቁዲሰ ሲረሁ)

አላህ ጋር በበቂ ኹኔታ ማውጋት ሳንችል፣ እርሱን ለማወቅ ሳንጥር፣ የዱንያ ሸክምና ስበት ልባችንን ጠፍራ ይዛው ሳለ ባለንበት ኹናቴ እናዝናለን?!

አላህን የምናመልከው እንዲያደርግልን አይደለም፣ አላህ ያዘዘውን መታዘዝ የከለከለውን መከልከል ላይ የቻልነውን የምንጥረው እርሱን ለማስደሰት አይደለም። ቀድሞውኑ ማን በስራው ጀነት ይገባና?

እና ለምን እንለፋለን?

የምንሰራውና የምንለፋው አላህ እንዲያዝንልን እንጂ ዝንት ዐለም ብንገዛው እርሱ እኛ ላይ የዋለውን መመለስ የማንችል የርሱ ሎሌዎች ነን። የመጣንበት ዓለም አጭርና ጠፊ ናት። ለዚህች ዓለም ስንኖር እንደዘላለማዊ ኾነን እንኖራለን፤ ለአኺራ ስንሰራ ዛሬ እንደምንሞት አድርገን እንታትራለን። ሥራ ከርሱ እዝነት መከጀያ፣ ሰበብ ማድረሻ ነው። ከስራ መዘናጋት ወንጀል ነው፣ ሥራ ያድነኛል ማለት ማጋራት ነው። ሥራን በተረዘቅነው መንገድ መሥራቱ አምልኮ ነው። አላህ የለገሰንን ነገር ቆጥሮ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይህ ለማድረግ የታደለ ሰው ሌሎችን ከመመልከት ከሌሎች ጋር ከመወዳደር ይቆጠባል። ያመሰግናል፣ ያጣውን እንኳን ለማግኘት ይጠራጠራል።

ደስታ የሚርቀን ያለንን ባለመረዳት፣ በልባችን ውስጥ ጠፊዋን ዐለም አግዝፎ መመለከትና፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለ ፉክክር ነው። ከዚያ ውጭ ለማንም ሰው የራሱ የኾነ የደስታ ሪዝቅ ተሰጥቶታል። አንዳንዶች ደስታን በብዙ ርቀትና ልፋት አገኙት ማለት ሌላውም በዚህ መልክ ማግኘት ግድ ነው ማለት አይደለም።

ለምሳሌ በይቱላሂል ሐረምን ማየት ኢማን ይጨምራል። በሌላ አገላለጽ ደስታ እንበለው። ማየት ያልቻለ ደስታ ተነፈገ? አይደለም! የወላጆቹን ፊት፣ የዑለማ ፊት ቢመለከት እኩል ነው። አልያ የፈጅር ሰላት ሰግዶ ጸሀይ እስክትወጣ ተቀምጦ ሁለት ረከዓ ቢያስከትል ይህን ደስታ ያገኛል። እምነቱ የማለፊያ መንገዱን አብዝቶታል። በሕይወት አለምም ስንኖር ሁላችንም በቀጭኑ መንገድ መተፋፈን የለብንምና ቀና ብለን ሰማዩንም እንመልከት። ሁሉ ነገር ሰፊ ነው፣ ሁሉ ነገር ብርሀን ነው።

ስሙን ደጋግሞ በመጥራት ከርሱ ጋር በማውራት ወደርሱ በመተንፈስ የዕለት ጭንቃችንን እናራግፍ!

ምስሉ ከጽሑፉ ጋር ባይገናኝም፤ የቀደሙ መሻኢኾችን ማስታወሱ በራሱ ራሕመት ስላለው ለጽሑፉ ማጀቢያ ይያያዝልኝ!

አቦ ያስረዳና

ሰላም

Best kerim

09 Nov, 14:09


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

09 Nov, 14:09


#የኒያ_ሐይል

ሠላማዊ ኒያ በልቡ ያለ ሰው በብልሀትና በዐቅል የሚያገኘው ነገር በላይ ስኬታማ ሊያደርገው ይችላል። አላህም እውነተኞችን መልካም ገጠመኝ ይለግሳቸዋል። ሰዎች በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ኒያቸውን/ሐሳባቸውን ለአላህ ሲያደርጉ ተውፊቅ (መልካም ገጠመኝ) ይሰጣሉ።

ሥራዎችን ኹሉ ለአላህ ማጥራት ኢኽላስ ብለን ስንጠራው፤ በየሥራዎቻችን ደጋግመን የሥራችንን ግብ ማደስ ደግሞ ኒያ እንለዋለን። ኒያ በኹሉም ሥራዎቻችን ውስጥ አብሮን ያለ ደጋግመን የምንረሳው ጥልቅ አምልኮ ነው።

ከሰዎች ጋር ስንሰባሰብ፣ ስንማር ስናስተምር፣ ስንበላ ስንጠጣ፣ ቤተሰባዊ ግንኙነት ላይ ወዘተ በኹሉም ጉዳዮች ላይ በየደቂቃው ኒያን ማደስ ያስፈልጋል። ይህን የማደርገው አላህ እንዲወድልኝ ነው፣ ይህን የነየትኩት እንዲህ እንዲመጣ ነው፣ ዛሬ የተገናኘነው በዚያራ ኒያ ነው፣ ዛሬ ይህን የጻፍኩት በማስተማር ኒያ ነው፣ ባል ለሚስት፣ ሚስት ለባል፣ ወላጆች ለልጆች፣ ልጆች ለወላጆች ሲያደርጉ ቆም እያሉ ኒያቸው ውስጥ "ሸይጣንና ነፍሲያ" እንዳይገቡ መከላከል ያስፈልጋል። ለሻይ ቡና ስንቀማመጥ፣ ለመዝናናት ኾነ ለማንኛውም ቅጽበት ኒያና እኛ ከተቆራኘን ከየትኛውም መጥፋት አላህ ሊያድነን ትልቅ ሰበብ ይኾንልናል።

አላህ ኒያችንን ያሳምርልና

Best kerim

09 Nov, 12:36


የምንፈራቸው ነገሮች እየደረሱ ነው ...

እነ ሁሉን ነገር ላውራ በቀደዱት ቦይ ማንም ተነስቶ ዲንን ላስተምር፣ እምነቱን ላቡካ ብሎ የተነሳበት ዘመን ነው። እምነትን ከማንም ሰው መውሰድ እንደማይገባን ደግሞ እስልምናው በሚገባ አስተምሮናል።

አስበው ማንም ሰው ተነስቶ ባስተዋወቀው የእምነት ጉዳይ አንተ ስትሳተፍ?! እነ በረካ፣ ኢማን፣ ዘውቅ የሚባሉ ዋና ነገሮችስ የት ሔዱ?! እነዚህ ቢዝነስ የሚሰሩ ሰዎች ለእነርሱ ሐይኪንግም ዑምራም አንድ ሊኾን ይችላል። ያጣፍጥላቸው (አይመለከተንም ይኾናል ) አብረዋቸው የሚኼዱ ኡስታዞች ግን ከተረዱት እምነቱ ልቅ እንዳልሆነ ሊያስተምሩ ይገባል።

ሁሉም ነገር ፕሮቶኮልና ፕሮፌሽናሊዝም እንዳለው ማወቅም ከአደብ ነው። ክልክል የሌለበት ነገር ወይም ልንሰራው ፈቃድ ያለበት ነገር ኹሉ በዘፈቀደ አይሰራም። የራሱ የኾነ የሚሰራበት አሠራር አደቦች አልሉበት። በተለይም እንደ ሐገርና ባሕል ያሉ ልምዶችንም ማክበሩ ተገቢ ነው።

ስራው ከእምነቱ ጋር በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ የተዛመደ ሰው በሚገባ የእምነቱን መርሆች ለመጠበቅ ዘወትር ሸይኽ ጋር መማከር ይኖርበታል። በተለይም ከአምልኮኣዊ ነገሮች፣ ከመማርና ማስተማር ጋር የተገናኙ ነገሮች ዋና ትኩረታቸው መንፈሳዊነትን ማሳደግና በመንፈሳዊ ማንነት ከፍ ማለት እንጂ ቁሳዊነትን አግዝፎ ማሳየት መኾን እንደሌለበት መገንዘብ ያስፈልጋል።

ከአፋት ይጠብቀን

Best kerim

09 Nov, 03:57


https://t.me/Noor_Musela?livestream

Best kerim

09 Nov, 03:25


#የኢሽራቅ_ድባብ

ቁርኣንን በሚቀሩ፣ የጥዋት ዚክርን በሚዘክሩና እየተማማሩ የጸሐይ መውጣትን በሚጠብቁ የመስጂድ እርግቦች ውስጥ መገኘት ያለውን እርካታ የት ታገኘዋለህ?

የፈጅርን ሰላት በጀምዓ የሰገደ ከዚያም በተለያዩ መልካም ተግባራት ጥቂት ተቀማምጦ ጸሐይ ሲወጣ ሁለት ረከዓ ያስከተለ ሰው። ሐጅና ዑምራ ከማድረግ ጋር የሚስተካከል ምንዳን ይለገሰዋል።

በዚህ ወቅት ጸሐይ የምትወጣው 12:16 አከባቢ ነው።

አላህ አይከልክለና

Best kerim

08 Nov, 12:26


የአንዳንድ ሰዎች ቃላት ልክ እንደ ሰይድና ዩሱፍ ቀሚስ ለአባታቸው እንደኾነው ያህል ዋጋ አላቸው፤ ቃላቸው ሌሎች ላይ ነፍስ ሲዘራ ትመለከታለህ።

ሰይድና ዩሱፍ ቀሚሳቸውን ብቻ ልከው የአባታቸውን ብርሀን ለመመለስ ሰበብ እንደኾኑት ኹሉ በብዙ መልኩ የሚነካንን ችግር ሊጠግንና ሊያሽር የሚችል ሸይኽ ማግኘት ሪዝቅ ነው። የልባችንን ብርሀን የሚጠብቁልንን ሸይኾችን ይጠብቅልን።

ሸይኽም ይለግሰን፣ ጨማምሮም ይስጠና!

اللَّهُمَّ صلِّ على سيدنَا محمد النَّبِي الْأُمِّي الحبيب ، العالي الْقدر، الْعَظِيم الجاه ، وعَلى آله وَصَحبه وَسلم

Best kerim

07 Nov, 18:28


ወደ መኝታ ስንቃረብ እንቅልፋችንን በፈቃዳችን ማምጣት እንኳን የማንችል ደካማ እንደሆንን እንረዳለን፣ ለእኛ የተባለው ዕንቅልፍ እንኳን የሚለገሰን ከሚነላህ ነው።

ስለዚህ

የሩሓችን እና የሪዝቃችን ባለቤት አላህ ብቻ ነውና ነፍሴ ሆይ! አትጨነቂ!!

ባይኾን የምድሩ ማሊክና መሊክ (ባለቤትና ንጉሥ የኾነውን) እርሱን (አላህን) ስለማወቅ ተጨነቂ!!

ልብን ከቂም አጽድቶ የአልሙልክና ሰጀዳህን ምዕራፍ አንብቦ መተኛትን አንርሳ፤ ከአላህ ጋር የቀረውን ሙናጃት ለመጨረስ በጊዜ አርፈን በጊዜ እንነሳ!

ይረዝቀና

Best kerim

07 Nov, 18:14


Live stream finished (12 minutes)

Best kerim

07 Nov, 18:02


Live stream started

Best kerim

07 Nov, 14:37


ሚድያ የሚሰጠውን መረጃ ኹሉ በማመን ዳዕዋ ማድረግ ማሰራጨት ሰው ከሚያድነው በላይ አጥፊ ሊኾን ይችላል። በተለይም ሰዎች ዘንድ የምንናገረውን ነገር መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ስለወንጀልና ወንጀለኛ አብዝቶ ከማውራት ወንጀል ውስጥ ላለመግባት ስለሚያግዙ ነገሮች ማውራቱ የተሻለ ነው። ከሁሉም የተሻለው ከፍ ስላሉ መንፈሶች ማውራት ነው። ማስጠንቀቁ ግድ የሚኾንበት ቦታ ላይ ሲኾን በቀጥታ ጉዳዩ ለማስታወቂያ ግልጋሎት አለመዋሉን ማወቅና መረዳት አለብን። ሰላቢ የኾኑት ሸይጣኒያዎች ነገሮችን በተለያየ መንገድ ማሕበረሰብ እንዲለማመድ በማድረግ የተካኑ መኾኑን አትርሱ። አንዳንድ ለእስልምና ሲጣራ ስማርት የምትሉትን ሰው ሳይቀር አላስፈላጊ ቃላቶችን ተጠቅሞ የእነርሱን አላማ እንዲያስፈጽም ሊያደርጉት ኹሉ ይችላሉ። በተለይም "እከሌ ደፋር ነው ማንንም አይፈራም" የሚባሉ ሰዎች የሚናገሩትን ንግግር ብትመረምሩ በበርካታ መርህ አልባ ንግግሮች የተሞሉ ናቸውና። የምንተቸው ነገር ወንጀል እንኳን ቢኾን ሳናስበው ማስታወቂያ ከመስራት መጠንቀቅ ደግ ነው።

በነፍሲያና ሸይጣን ድብቅ ተንኮል ከመታለል ይጠብቀና

Best kerim

06 Nov, 18:08


ልፋቶቹን ሁሉ ቁርኣንን በመያዝ የታገለ ሰው በሁሉም ጉዳዮቹ ላይ በረከት ይገጥመዋል። ይላሉ አህሉል ቁርኣን። ቁርኣን ለሁሉም እክሎች ደራሽ ሲኾን ነፍሶችን በቀስታ የሚያለዝብ፣ ሕይወትን በበረከት የሚያርስ ታላቅ ስንቅ ነው። ቁርኣን ለዕድሜ ዘመናችን ሰዓታት በረከት ግድ ሲኾን እኛ ግን ለቁርኣን ችለን የምንለግሰው ሰዓት የለንም። የቁርኣን አንቀጾችን በየዕለቱ ለማንበብ በምናደርገው ጥረት አስፈላጊነቱን እየተገነዘብን እንድንሄድም ያግዘናል። ቁርኣንን ለመቅራት ስናስብ፣ ውዱእ ማድረጋችንን፣ ሲዋክ መጠቀማችንን፣ ከመቅራታችን በፊት ዱዓና ኒያ ማስከተላችንን አንዘንጋ። ቁርኣንን አዘውትሮ በአደብ ማንበብ የቁርኣንን ጥቅም ለማግኘት ይረዳናል። ቁርኣን ውስጥ ትልቁ የሚገኘው ነገር መንፈሳዊነት መኾኑንን በመረዳትም ከመቅራት ጎን ለጎን ማዳመጡም ምህረት እንደሚያስገኝ በመረዳት መንፈሳዊነቱን መለማመድ ያስፈልጋል። ቁርኣን አንብበን የምናወራው ሳይኾን ሰጥቶን የምንተገብረው ይበዛልና!

አህሎቹ ከቀመሱት የቁርኣን በረከት ያቃምሰና

Best kerim

06 Nov, 16:14


ከባለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ከልጆች ጋር ብዙ አሳልፋለሁ። በልጆች ዓለም ውስጥ የማሕበረሰብን የሕይወት ዘይቤ ልብ ብዬ እመለከታለሁ። ውሎ አዳራቸውን በሚገባ በመፈተሽ ምን ላይ እንዳሉ እረዳቸዋለሁ፤ ነገም ምን ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ እገምታለሁ። በአጭሩ ምን ለማለት ያህል ነው። የልጆችን መንፈሳዊ ሕይወት በሚገባ መንከባከብ አስፈላጊ ነው። መድረሳ ስለተላኩ፣ ኡስታዝና አስጠኚ ስለተቀጠረላቸው፣ ኪታቦችን ስለቀሩ ... እነርሱ ላይ የተለያየ ወጪ ስላደረግን የሚበቃ እንዳይመስለን። ይህ ሪዓያ (እንክብካቤ) ሲኾን ልጆች የሚያስፈልጋቸው ግን ተርቢያ(እነጻ) ነው። ልጆች አዕምሮዓቸውን የተቆጣጠረው ነገር ማሕበረሰብ ያለበትን ይገልጻልና ከውስጣቸው የገቡትን ራስን ያለመኾን እክሎች በተለያየ መንገድ እየተከታተሉ መንፈሳዊ እነጻዎች የማይለገሳቸው ከሆነ በቅርጽ የሚገለጹ እምነቶች እየሰፉ ይመጣሉና። ልጆች ከወላጆቻቸው በቀጥታ እነጻን የሚያገኙበትን መንገድ መዘርጋት አስፈላጊ ነው።

አላህ ይወፍቀን!

Best kerim

06 Nov, 16:13


#መስጠት

መውላና ጀላሉዲን አርሩሚይ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ስለ መስጠት እንዲህ ይላሉ፦ « የመስጠትን ትርጉም ማወቅ ትፈልጋለህ? ጥልቅ ከሆነው የሕመም ጉዳትህ ውስጥ ለሰዎች ደስታን አሰራጭ።»

ካለህ ላይ ማካፈል ሰውኛ ነው፣ ከተረፈህ ጸጋ ማጋራት ልዩ ሰደቃ ነው። ከውስጥህ በሚመነጭ ስሜት ለሰዎች ደስታ መስራት ግን ከላይ የሚመጣ ከባድ ዋሪዳ (መሰጠት) ነው። ለሰዎች ገንዘብ ኾነ ምንም ነገር ስንሰጣቸው የተመጽዋችነት ስሜት እንዳይሰማቸው አድርገን የሰጠን ቀን ነው፤ በእውኑ የመስጠትን ስሜት በሚገባ የተረዳነው። ይህን ሰደቃ ቢሽዑር (ለሰዎች ስሜት በመጨነቅ የሚለገስ ምጽዋት) ልንለው እንችላለን።

ለሰዎች መለገስ የታደለ ሰው ሲለግስ በተቻለ መጠን የሰጪነትን ኩራት ከላዩ ላይ ለማስወገድ መስራት አለበት። ምክንያቱም የምንሰጠው ስለተረፈን ብቻ ሳይኾን የሰዎችን ስሜትም ለመጠበቅ ነው። በዚህ ስሜት መስጠትን ስንለምድ በምላሹ የምንጠብቀውን ሰውኛ አጸፋዎች በማጣታችን ጉዳት እንዳይነካን ያግዛልና።

አላህ ያስረዳን
ከንጹሕ ስሜታቸው የለገሱንን ወዳጆች ይባርክልን

Best kerim

05 Nov, 17:47


#ከተሪሞቹ_መንደር
#ተርቲብ_ሙነዘም

ከጥበብ መንደር ተሪም የበቀሉ መሻኢኾች በጣም በአጠሩ ቃላት ጥልቅና በረከት አዘል ንግግሮችን ተሰጥተዋል። ተወዳጁ ሸይኽ ሐቢብ ሙሐመድ ሰቃፍ በ "ኢርሱ ነበዊ" የቲቪ ቻናል ላይ የገዛሊይን "ቢዳየቱል ሂዳያ" የተሰኘውን ኪታብ በሚያብራሩበት ፕሮግራማቸው ላይ ከሸይኽ ሐቢብ ዐብዱልቃዲር ሰቃፍ (ራህመቱላህ) የተለገሳቸውን አጭር ምክር እንዲህ ያስታውሱናል።

አንድ ቀን ከመስጂድ ስወጣ አገኙኝና የት ነው የምትሔደው ከዚህ በኋላ ፕሮግራምህ ምንድነው ብለው ሲጠይቁኝ መመለስ አልቻልኩም። "አላውቅም" ስላቸው ተገርመው ፈገግ አልሉ።
ከዚያም እንዲህ አሉኝ ፦ « ልጄ ሆይ የጊዜ በረካ ያለው የምታደርጋቸውን ስራዎች ቀድመህ ማዘጋጀት በመቻል ነው።»

***

አንድ ሰው በሥራውና በውሎው ስኬታማ ነው የሚባለው በዕለቱ እሰራቸዋለሁ ያላቸውን ነገሮች መስራት ሲችልና የተደራጀ ሲኾን ነው።

ከጠዋት ጀምሮ የሚሰራቸውን ነገሮች ቆጥሮ በመጻፍ እያንዳንዱ ያቀደውን ነገር መስራት የቻለ ሰው የዕለቱን በረካ አግኝቷል ማለት ነው። ከዚህ በተቃራኒ ያለምንም ንድፍ መንቀሳቀሱ ግን የበረካን ትርጉም እንዳይረዳ ያደርገዋል። አምልኮዎች ብዙዎቹ መሰል ቁርጠኝነት ይፈልጋሉ፣ ዚክሮች፣ ሰላት፣ ቁርኣን፣ ሰለዋትና የተለያዩ መንፈሳዊ ክንውኖች በራሳቸው ተርቲብና ተንዚም (ቅደም ተከተልና ሥርዓት) ያስፈልጋቸዋል።

በዚህ አጋጣሚ የተባረኩ ዒልሞችን ከዚክርና ከሰለዋት ጋር አጣምራችሁ መታገል ለምትሹ ሰዎች ከላይ የጠቆምኩትን ቻናል ብትከታተሉ ታተርፋላችሁ እላለሁ። ሌሎች ተጨማሪ ጥቆማዎች የምትሹ ልታወሩኝ ትችላላችሁ።

የተባረከ ምሽት ይሁንልን!

Best kerim

04 Nov, 18:11


አንድ ዐሪፍ ቢላህ ተጠየቁ፦ «ጌታዬን ስጣራ በዝምታ ነው? ወይስ ድምጼን በማውጣት?»
እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ « ጌታህን ከፍ ባለ ዝምታህ ጥራው!»

ዝምታ ከድምጽ በላይ ጉልበት አለው፣ ዝምታ ውስጥ ጥልቅ ማሰላሰል አልለ፣ ዝምታ ውስጥ ማሰብና መረጋጋት አልለ፣ በዝምታ ከአላህ ጋር ማውጋት አልለ። ለሊት ዝምታ ይበዛዋል፣ ለሊቱ በቆየ ቁጥር ዝምታውም ይጨምራል። ዝምታው በጨመረበት ውድቅት ለሊት ላይ ባርያም ከወዳጁ ጋር ይገለላል። በዝምታ ለሊት ዝም ባሉ ቃላቶች ወዳጅን ያናግራል።

በጊዜ በዝምታ በማረፍ ጣፋጩን የዝምታ ወቅት የለይልን በረከት ለመውሰድ መነየት ያሰፈልጋል። ለኒያው ያልሰሰተ ሰው ለሥራው ይወፈቃል!

ሰላም

Best kerim

04 Nov, 17:44


በድጋሚ ለማስታወስ!

በመሠረቱ ከተለያዩ ማስታወቂያዎች በላይ ተደጋግሞ መነገር ያለበት መሰል ማስታወሻዎች ናቸው። ዐሊሞቹ ዒልም ከአርባ ጊዜ በላይ ይነገራል እንዲሉ ተከታዩን ማስታወሻ እንካችሁ እላለሁ።

አራት ምርጥ ወቅቶችን ለመጠቀም ሞክሩ ይላሉ ዑለማዎቹ!

① ከፈጅር በፊት ያለው ጥቂት ሰአት

የለይልን ሰላት ለመስገድ፣ ከቁርኣን ገጾች የተወሰነ ለማንበብ፣ ከአላህ ጋር ሙናጃ ለማድረግ፣ የልብን ከወዳጅ ጋር ለማውራት ምቹ የኸልዋ ወቅት ነው።
② ከፈጅር ሰላት በኋላ እስከጸሐይ መውጫ ያለው ጊዜ

ይህ ሰአት በጣም አጭር ሲኾን ጥቅሙ እጅግ የበረታ ነው። በዚህ ሰአት እንቅልፍን ትቶ በመቅራት፣ በመዘከርና በመማማር ማሳለፍ ተወዳጅ ነው።
③ ከዐስር በኋላ ያለው ሰአት

ይህን ሰኣት ዑለሞቹ መንፈሳዊ ወጎች የሚያወጉበት እርምጃዎች በማድረግ፣ ከወዳጅ ጓደኞች ጋር በመገናኘት በመንፈሳዊ ጫወታ የሚዝናኑበት ነው።

④ ከመግሪብ እስከ ዒሻ

አስገዳጅ ነገሮች ካልተፈጠሩ አንድ ሰው መግሪብን መኖሪያ ስፍራው መቅረብ አለበት። በመስጂድ ወይም በቤቱ ይህን ሰአት በዚክርና በቁርኣን ብሎም ለቤተሰቡ ተርቢያ መስጠትን እንደዊርድ ሊይዘው ይገባል።

እነዚህ አራት ወቅቶችን ለመጠቀም ተውፊቅ ያገኘ ሰው ትልቅ ሐብት ተሰጥቶታልና ማመሰገን አለበት። ያልተወፈቀም አላህ ይህን እንዲለግሰው መለመን አለበት።

አላህ ከእነዚህ ወቅቶች በረከት ያድለና

Best kerim

03 Nov, 18:23


ፊርዓውንን መጥላት ብቻ በቂ አይደለም፤ ሙሳንም መኾን ያስፈልጋል። እንደሙሳ ያልኾነ ደግሞ ኸድር አይገጥመውም። በሌላ አገላለጽ የእርኩሱን ሠ*ይጣን ተንኮል የማያውቅና የማይጠየፍ የለም፤ ከሁሉም የተሻለው ግን የእርሱን ሥራ የሚያከሽፉ ሥራዎችን በቋሚነት መተግበርና መንፈሳዊነትን መለማመድ ነው። ስለ እር*ጉሙ ብዙ ከማለት ቀና መንፈስ ላይ መሰንበት ደግ ነው።

ውዱእ አድርጎ፣ ዚክርን ጨርሶ፣ የአልሙልክና ሰጀዳህን ምዕራፍ አንብቦ የመኝታ አደብን ጠብቆ በጊዜ ማረፍን ዊርድ እናድርግ!

አላህ ይግጠመና

Best kerim

03 Nov, 03:26


[በንጋቱም (በብርሀን) በተነፈሰ ጊዜ፤ (እምላለሁ)።] አትተክዊር፤18

ከፈጅር (ሱብሂ) በኋላ የሚነፍስ የብርሀን ንፋስ አልለ። ለሰውነታችንም ኾነ ለውስጠ ልባችን እንዲሁም ለሕይወታችን ወሳኝ ነው። ከፈጅር ጀምሮ ጸሐይ እስኪወጣ ማለትም (11:45–12:10) ገደማ አየሩን መውሰድ፣ መንቀሳቀስ፣ መቅራትና መማማር፣ ወደ ስራ መውጣት በረከትን ያስገኛል። ይህ ለአማኞች ብቻ ሳይኾን ለማንኛውም ሰው የተሰጠ ነው ይላሉ። የፈጅር ሰዎች ለዚህ ማዕረግ የታደሉ ናቸው።

ወፍቀና

Best kerim

02 Nov, 15:00


#ሑስነዘን_ቢላህ

«በአላህ ላይ ያለህ ጥርጣሬ እውነተኛ ቢኾን የከለከለህ ነገር ከለገሰህ ነገር ጋር አንድ እንደሆነ ታውቅ ነበር።»

ኢብን ዓጣእ አስሰከንደሪይ (ቁዲሰ ሲረሁ)

ብዙ ጊዜ አላህን የበለጠ የምንቃረበው ተከልክለናል ብለን ባሰብን ጊዜ ነው። የተለገስንና ጊዜ ያለን እውነተኛ ባሕርይ ይገለጥና ሰዎች ሲመቸን ባሕርያችን የተቀየ ይመስላቸዋል። የጸጋዎች እኛ ላይ መስፋት ያለንን ትክክለኛ ባሕርይ እንደሚገልጥ አይታወሰንም። በተቃራኒው የነገሮች እኛ ላይ መጥበብና መያዝ እንዲሁም መከልከል በርካታ ያሉብንን ነውሮች ከመደበቅ በላይ እኛን (ነፍስን) በሚገባ ይሰራልናል። በደንብ ራሳችን ላይ ለመስራት ከፈለግን በችግራችን ጊዜ በደንብ ራሳችን ላይ እንልፋ ነገ ሲያልፍ አጸያፊ ባሕርያት አብረው ይወድቃሉና።

አንድ ታማኝ ሸይኽ ዘንድ የመጣ የቸገረው ሰው ሪዝቄ ተይዞብኛል የኾነ ዱዓ ያድርጉልኝ አላቸው። እርሳቸው ትንሽ ታገስ ግማሽ አመት ወይም አንድ አመት ከዚያ ያልፋል ይህ አሉት። ሰውዬውም ተጣድፎና ደስ ብሎት ከዚያስ በኋላ አላቸው፦ " ከዚያ በኋላማ ችግርህን በደንብ ትላመደዋለህ።" አሉት ይባላል።

በ "ከራማ" ከችግር ለመላቀቅ ከመሞከር በላይ የሚበልጠው በችግር ጊዜ ነፍሲያን ማረቅ ነው። አቦ የማያልቅበት አላህ ከሁሉም ጸጋ ያቃምሰን፤ ከሚበልጠው መረዳት ይለግሰን!

አሚይንን!

Best kerim

31 Oct, 18:15


Live stream finished (16 minutes)

Best kerim

31 Oct, 17:59


Live stream started

Best kerim

31 Oct, 15:58


#ደማቁ_ለይል

የጁምዓ ለይል በሐገርኛ የኸሚስ አመሻሽ ሲመጣ በአንዴ ከመዲና ሰማይ ስር የተገኘህ ያህል የሚሰማህ ስሜት አልለ። "ሸይኽ የሌለው ሸይኹ ሸይጣን ነው።" ለሚለን ጠንካራው የተሰዉፍ ምልከታ መፍትሔ የሚሰነቅበት ለሊት ነው። ሰለዋት ሸይኽ ላጣ ሰው ሸይኹ ነው እያሉ ሕዝባቸውን የሚያድኑት ዓሪፎቹ በግልም በቡድንም ሕዝብ ሰለዋት ላይ ተጠምዶ ጌታውንም ነብዩንም የሚፈልግበት ውብ መንፈሳዊ ሥርዓታችን ነው።

አላህን ካወቁት ዐሪፎች መካከል የሩሚ የልብ ወዳጅና ሸይኽ ሸምሰ ተብሪዝ (ቁዲሰ ሲረሁ) እንዲህ ይላል፦ « አላህን መፈለግ በሁሉም ልብ ውስጥ የተሳሰረ ነገር ነው። ከአላህ ጋር በቅጽበት መገናኘት አንድ መቶ ከማመር ጋር የሚወዳደር አይደለም።»

ሩሚ በመማር ማስተማር ውስጥ ሊቅ በኾነበት ጊዜ ነበር ተቢሪዝ መጥቶ አላህን ስለማግኘት ጥልቅ ዐለም ግብዣ ያቀረበለት። አየህ አይደለም ስንት የማይረቡ መንገዶች ይቅርና መሰረት ያላቸው ሐይማኖታዊ ተግባራት ራሱ አላህ ጋር ላያዳርሱ ይችላሉ።

ይህን ጊዜ ነው የሸይኽ ያለህ የሚያሰኘው! ሰለዋት ብርሃን ነው፣ ሰለዋት የልብ ስብራትን መጠገኛ ነው፣ ሰለዋት መንገድ የሚያሳይ ሸይኽ ነው

በዱዓችሁ

መልካም የሰለዋት ለሊት

Best kerim

31 Oct, 10:20


ሌላ የሥራ ማስታወቂያ

በጂኦግራፊ፣ ሒስትሪ ወይም ሲቪክስ የተመረቀ/ች የግብረገብ ትምህርት ማስተማር የሚፈልግ/የምትፈልግ ባለሙያ ካለ በውስጥ መስመር ልታነጋግሩኝ ትችላላችሁ።

Best kerim

30 Oct, 18:13


« እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን፤ ለሊቱንም ልባስ አደረግን።» ነበእ፤9–10

መግሪብ ሰአት ጀምሮ ወደ ቤታችን ወይም መስጂድ ላይ እንድንቃረብ ዑለማዎች ይመክሩናል። በተቻለን ዐቅም በማያስፈልግ ሁኔታ እንዳናመሽ ያስጠነቅቁናል። ሲመሽ የወሬዎች ሀይል እንዲቀንስ፣ ለስላሳና መንፈሳዊ ጫወታዎች፣ ዱዓና ዚክር ወይም ቁርኣን ላይ ብናተኩር የበለጠ ጤናማ ዕንቅልፍ እንድንተኛ ይረዳናል። ቀን በዋልንበት ሀይል ማምሸት ለአዕምሮም ጤና ልክ አይደለም። ቀኑን በሥራ የደከመ አዕምሮ ማታም በነገርና በቧልት በሀሜትና በዛዛታ ለሊቱን ማጋመስ የለበትም። ከመግሪብ ጀምሮ ባሉ ውስን ሰአታት በመንፈሳዊ ነገሮች ቀዝቅዞ አኺራን እያስታወሱ ማረፍ ተወዳጅ ነው። የጋሉ አጀንዳዎችን፣ ፖለቲካና ዜና ነገሮችን በተቻለ መጠን ማሳደሩ መልካም ነው።

አላህ ይወፍቀን!

ሰላም

Best kerim

30 Oct, 17:48


ሁሌም ከውስጣችን ሐቂቃ ደስታ እየደረጀ እንዲሔድ ከፈለገን ሁለቱ ነገሮች ላይ ሁሌም ማሻሻያ እንስራ። የመጀመሪያው አላህ ያዘዘውን ሰላት ሁሌም በምርጥ ኢኽላስ ለማከናወን እንጣር፤ ሁለተኛው የዕለታዊ የቁርኣን ዊርድን በጥቂት ገጽ እንኳን ቢኾን ዘውታሪ ለማድረግ እንበራታ። ብዙ ዚክሮችን እንደ ዊርድ ከመያዝ በፊት፣ ብዙ ታላላቅ መንፈሳዊ ልምምዶች ከመመኘት በፊት እነዚህ መሠረታዊ የሚባሉ ዊርዶች ላይ የዘወትር የግል ሁኔታን ማሻሻል ወደ ተሻለ የኢሕሳን ደረጃ ያሳድጋልና በተለይም ከመኝታ በፊት ቁርኣን ስለማንበባችን ራሳችንን መርምረን መተኛት ደጉ ልምዳችን ይኹን!

አላህ ያስረዳን
የተባረከ ለሊት ተመኘሁ

Best kerim

30 Oct, 16:48


#ራስን_ማወቅ

« ለሁሉም ነገር መልስ አለኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ከሰዎች ኹሉ አላዋቂው ነው።»

ሸምሰ ተብሪዝ (ቀደሰላሁ ሲረሁ)

ቀደምቶቻችን ለተማሪዎቻቸው ከዕውቀት በላይ አደብን አብዝተው ያስተምራሉ ምክንያቱም አገኘሁ የምንለው ውስን ዕውቀት ካልተገራ ከሰው ኹሉ የላቅን እንደሆንን እንዲሰማን ያደርገናልና። በየትኛውም ሙያ ኾነ ዕውቀት ላይ ያለን ችሎታ መሰል አጥፊ ዝንባሌን ከማስከተሉ በፊት ቆም ብሎ መመርመር አስፈላጊ ነው። ዑለማኡ ረባኒዮች ዝና እና ክብር ፈልጎ ለሚጠጋቸው ሰው ቅድሚያ የሚያለማምዱት ትህትናን ነው። "አውቃለሁ" ከሚለው ስሜት በላይ "አላውቅምን" የዚክር ያህል እንዲለማመዱም ያግዛሉ።

አስቡት በብዙ ግንኙነቶች ላይ ዛሬ እክል የኾነብን ዋናው ችግር "አውቃለሁ" ባይነት አይደል። ቀደምት ደጋጎች እኮ ኾነ ብለው ወደ ማያውቋቸው ሕዝቦች ውስጥ ይቀላቀላሉ። ከዚያም የሚያቁትን እንደውም የእራሳቸውን ወሬ ሳይቀር ልክ ሰምቶ እንደማያውቅ በማዳመጥ የነፍስያን መንቀልቀል ያስታግሳሉ።

ለማውራት የምንጣደፍውን ያህል ሰዎችን በሙሉ ልብ የማደመጫ ጊዜዎች ቢኖረን ብዙ ዕድገት ይኖረናል። ስለሁሉም ነገር ከቶ ልናውቅ አንችልም። ከማንም ሰው ጋር ስንደማመጥ የምናደምጠው አካል ያለበትን ተጨባጭ ለመረዳት ጥረት ካደረግን ልብን ከማቆሸሽ እልኽ ውስጥ ከመጋባት እንድናለን ይህ እምነት ግቡ ንጹሕን ልብ ለማምጣት እስከሆነ ድረስ የእብሪትን ስሜት በየቀኑ ማረድ ካልቻልን ግቡ ላይ መድረስ አይቻልም። ስለዚህ በቃ የፈለገ ብናውቅ፣ የፈለገ ቢሰለቸን ሰዎችን ጨርሰን እናዳምጥ ከቻልን ደግሞ "አላውቅም" ማለትን እንልመድ!

አላህ ያሳውቀና

Best kerim

30 Oct, 08:48


#ነሲሓ

አንድ ሰው ለሰይዲ በስጧሚ (ቁዲሰ ሲረሁ) «ምከሩኝ?!» ሲል ጠየቃቸው።

ጥልቅ የኾነ ነሲሓ ለገሱት እንዲህ አሉ፦

[ፈጣሪህ አላህ! ከፍራሽ እሰከ ዐርሽ ድረስ የሚልቅ ጸጋን ቢለግስህ፥ “አንተን ነው የምፈልገው” በለው።]

ጸጋ ኹሉ አላህን ካላገናኘ ጎጂ ነው። አላህን የሚያገናኝ ችግር በተቃራኒው ጸጋም ሊኾን ይችላል። በየትኛውም ኹኔታ እርሱን (አላህን) አለመርሳት ላይ መስራትና መልፋት አስፈላጊው የዚህች ዓለም ረጀም ውጣ ውረድ ነው።

በመንገዳችን ውስጥ ለአፍታም ቢኾን እርሱን የሚያስረሳን ጘፍላ እራሱ በጥበቡ ይመልስልና።

ያ አላህ

Best kerim

29 Oct, 19:25


ነፍሴ ሆይ!

የሩሕና የሪዝቅ ባለቤት አላህ ነውና አትጨነቂ!

የሩሕ መምጫም መመለሻም ወደ እርሱ ነው። የሪዝቅ (ዘርፈ ሰፊው ሲሳይ) ብቸኛ ባለቤቱ አላህ ነው። የሰው ልጅ ከተፈጠሩ ነገራት ላይ ተላቆ ወደ ነገሮች ኹሉ ባለቤት ሲሻገር ነው ነጻነቱ እዚህ ምዕራፍ ላይ የደረሱ ኸዋሶች ስሙን ሲጠሩት هو ይሉታል።

يا هو الله
አስረዳን

Best kerim

29 Oct, 14:45


#ዕውቀትን_ከቦታው_ውሰዱ

ዒልም (ዕውቀት) በብዙ መልክ የሚተነተን ሰፊ ጉዳይ ነው። ዑለማዎቻችን ብዙ የዒልም ዓይነቶችን ተንትነው በሕያው ኩቱቦቻቸው ላይ አኑረውልናል። የመረዳት ፈቃዱን ይለግሰን

በዕውቀትና በምርምር የሚሰሩ ደባዎችን መፍታት የሚቻለው በራሱ በዕውቀትና በሥራ እንጂ በጩኸት አይደለም። በጩኸት የሚፈታ ችግር ሁሌ ሌላ ችግርና መዘዝ ይዞ መምጣቱ አይቀሬ ነው። በድንገት የሚገኝ ሙያ በድንገት መጥፋቱ ስለማይቀር ባላችሁበት የሥራ መደብ ላይ ሙያዊ ከበሬታን በመጠበቅ ሥራን ወደዶ በሥራው ለመማር መጣር ያስፈልጋል። ሁሉንም ነገር በመደዴኛ መሄድ ወይም እንደ ነፋሱ መንፈስ ለባህላዊ "ነጋዴ" እንጂ ለባለሙያ የሚሰራ አይደለም። ዓላማህ በየትኛውም መንገድ "ማትረፍ" ከሆነ በመንገድህ መቀጠል ድርሻህ ነው።

ወደ ሕያው የዑለማዎቹ የዒልም አረዳድ ልመለስ "ዒልመ ሰጠር ወሰደር" ሰጠር (ከወረቀትና ከተለመዱ የንባብ ውጤቶች የሚገኘውን ዕውቀት ይወክላል።) ሰደር ያሉት ደግሞ የልብ ዕውቀት ሲኾን ከወረቀት በዘለል ያሉ ዕውቀቶች የሚገኙበት ነው። በኢጃዛ (ፍቃድ) እና በአደብ እንዲሁም በመንፈሳዊ ልምምዶችና ሽልማቶች የሚገኙ ዕውቀቶች ናቸው።

ዕውቀት ምንም ያህል ቢበዛ፣ ምንም ያህል ያሸበረቀ ቢኾን ከትክክለኛ ቦታው ካልተወሰደ ዋጋው ረብ የለሽ ነው። በዘመናችን መንፈሳዊ ክንውኖችና ዕውቀቶች በብዛት በተለያየ ጌጣጌጥ ተሞሽረው የሚተዋወቁትን ያህል የሚሰሩት ሰውም እስከዚህም ኾኗል ቢባል የተጋነነ ገለጻ አይደለም። ስለ እምነትም ኾነ ስለ መገለጫዎች የሚጮኽና የሚቆረቆርም አካል በዝቶ ይታያል። አይደለም በሐገራችን ይቅርና ሩቅ ምስራቅ በሚከሰቱ ነገሮች ልባችን በፍጥነት ሲደማ የሚስተዋል ጉዳይ ነው። ግና ባለን የዕለት ተዕለት ክንዋኔያችን ላይ ተፈላጊ ዕውቀቶች ላይ ስንባክን አይሰተዋልም።

በተለይም የእምነት ትምሕርት ከየትኛውም ዕውቀት አስፈላጊ እንደመኾኑ የምንማርበትን ቦታ መምረጥ ወሳኝ ነው። ከተቻለ ወደ ተግባር ሊቀይሩን የሚችሉ መድረሳዎችን መርጠን ልንማር ተገቢ ነው። ለሕክምና እና ለሌሎች ጉዳዮች አማርጠንና አጣርተን የምንወስነውን ያህል እምነትን ለመማር ስናስብም በሚገባ ማማረጥ አለብን። ምን አልባት ትክክለኛ መምህራንን ካገኘን ተፈላጊውን ዒልም ልናገኝ ይችላልና። ዒልምን መፈለግ ያለው ምንዳ ከፍተኛ መኾኑን እናውቅ ይኾናል። ይህ ከመኾኑ ጋር የት መማር እንዳለብንም ለፍቶ ማግኘት የዚሁ አካል መኾኑነረ መረዳት ተገቢ ነው።

ከመማር ውጭ ተማሪዎችና በተለያየ ስራዎች ላይ የምትገኙም ባለሙያዎች ያላችሁበትን ቦታ በማክበር ጠንካራ ሰራተኛ በመኾን በሙያና በዲሲፕሊን ብዙ ከራማ (ተዓምር ) መስራት እንደምትችሉ በማመን ችግሮችን በራሳችሁ ለመፍታት መጣጣር የዘወትር ምግባራችሁ መኾን አለበት እላለሁ።

አበቃሁ! አላህ ያስረዳና

Best kerim

29 Oct, 08:22


ኬጂ ውስጥ የዐረብኛ ቋንቋ ትምሕርት ማስተማር የምትፈልጉ ልምዱና ዕውቀቱ ያላችሁ እህቶች በውስጥ ልታወሩኝ ትችላላችሁ።

Best kerim

29 Oct, 03:03


የጠዋት እንቅልፍ ይጣፍጣል ግን አይጠገብም የበለጠውን ለማግኘት እንቅልፉን እንቆርጠዋለን። ፈጅር ሰላት ተረዝቀን በጀምዓ ሰግደን ስንመለስ ቶሎ ባለመንቃታችን እንቆጫለን። በመንገዳችን ስንመለስ ከምናገኛቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ቀዝቃዛውና እርጥባማው ጤዛ ነው። ከደቂቃዎች በኋላ ይህ ጤዛ ክው ብሎ ይደርቃል። የዚህች ዐለም (ዱንያ) ትክክለኛ ምሳሌ ማለት ይኽ ክስተት ነው። ስለዚህ ከአላህ ትዕዛዛት ጀርባ ያሉ ምስጢራትን በመፈለግ አምልኮን ማሳመር ወሳኝ ነው።

ሰባሓል ኸይር

Best kerim

28 Oct, 17:52


#በረካ ምን ማለት እንደሆነ በእነዚህ ገጠመኞችህ ውስጥ አስተውል!

በዚህ ወር ውስጥ ለሕክምና ዶክተር ጋር ሳትሄድ ወሩ ካለቀ በረካ (በረከት) ነው። በጥቂት የአመጋገብ ስልት የምትጠግብ ከሆነ ሌላኛው በረካ ነው። ሳትበደር ወሩን ከጨረስከው በረካ ነው። ቤተሰብህና በዙሪያህ ያለው ሰው ሰላም መኾኑ ከበረካ ነው። ስለዚህ ያጣኸውንና ያልደረስክበትን በመፈለግ ሳይኾን ያገኘኸውን፣ የተለገስከውን በመቁጠር ስለሰጠህ በረከት ደጋግሞ ማመስገን ነው የልብህን ሐብት የሚጨምርልህ።

አላህ ለሰዎች በፈለገው መንገድ ይለግሳልና ላንተም የሚለግሰው እርሱ ነው። ለዚህ ነው ዐሪፎቹ (በልብ ሀብት የመጠቁት) ስለ ሪዝቅ ሲጠየቁ ምላሻቸው ጠንካራ የኾነው። ምን አሉ?

« ሪዝቃችን የተጻፈ ነገር ነው። ሪዝቅ ስጠን ብለን ሳይኾን የምንጠይቀው ጌትዬ ሆይ! ሪዝቃችንን ባርክልን ነው የምንለው።»

ብዙ ለመጨመር ወይም ለመሮጥ አለያ ለመጣደፍ አንታገል። የሰዎችን ሐቅ፣ የእምነቱን (የዲን ሐቅ)፣ በዙሪያችን የሚገኙትን ሰዎች ሐቅ ከጠበቅን የምንሰራውን ስራ ሳናጓድል በጽዳት (በኢኽላስ) ካከናወንን እንቅስቃሴን ከአላህ ጋር አስተሳስረን የነገን (የአኺራ ቤት) ካሳመርን በዚህች አጭር ሕይወት ውስጥ በምንከፋንበት ኾነ በምንደሳበት ወቅት ምንዳ እንደምናገኝ ይገባናል።

ስለዚህ እዚህ ላይ ከቆየን ዐሪፍ ቢላህ ሰይዲና ሩሚ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) የሚለንን ወርቃማ ምክር መረዳት ያስችለናል።

« የእምነት (ተደዩን) ዋና ግቡ የሌሎችን ነፍስ ለመቆጣጠር ሳይኾን የራስን ነፍስ ለመግዛት ነው።»

እምነቱን በልባችን ላይ ያኑርልን፤ ያለውንም አረዳድ ይባርክልና

አማን እደሩ

Best kerim

28 Oct, 16:33


https://youtu.be/ZSwVlt-M69s?si=T5wULrAcX5cBLUzm

Best kerim

25 Oct, 18:06


#ተውበት

( إن الله يحب التوابين ويحب المتطهرين )

« አላህ (ከኃጢአት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል።» አልበቀራህ፤222

ሙፈሲሮች ከጠሀራ (ንጽሕና) በፊት ተውበትን (ንሰሐን) የተቀደመበትን መላምት ሲያስቀምጡ በውሃ ከመጥራራት በፊት ከወንጀል ከልብ መመለስ መቅደሙን ለማመላከት ነው ይላሉ። ተውበት ትጥበት ከሚያስፈልገው ቁጥር በላይ አስፈላጊ ነው። ተውበት (ንሰሀ) አሁንም አሁንም በልብ በአንደበት ኾነ በልብ የሚደረግ ታላቅ መማለሻ ነው።

አሁንም አሁንም ደጋግሞ ወደ አላህ ምሕረት መለመን "አስተግፊሩላህ" ማለት ለተውበት ወሳኝ ዚክር ነው። ሁሌም ልብን ወደርሱ የምንመልስበት ተግባር ነው። የውሃ ትጥበቶች፣ ውዱእን ጨምሮ የምንለቃለቅበት ንጽሕናን መጎናጸፊያ ጘፍላን ማስወገጃ መንገዶች ናቸው።

ከተዋቦቹም ከሙተጠሂሮቹም ያድርገና

Best kerim

24 Oct, 18:47


#የዕለትን_መጨረሻ_ማሳመር

ወደ መኝታችን ስንቃረብ ያለን ዕድል ሁለት ነው። አንደኛው ነገ መንቃትን ተስፋ የምንሰንቅበት ነው። ሁለተኛው አለመንቃት እንዳለ የምናስብበትም ነው። ነገን የሚሰጠንም አላህ ነው፤ ለነገም ካልደረስን የምንገናኘው ከእርሱ ጋር ነው። ስለዚህ መኝታችን ትንሹ ሞት ነውና በንጽህና ወደመኝታ መቃረብ ይወደድልናል። ከባባድ ነገሮች በልቦና ውስጥ አለማስቀመጥ፣ ለስላሳ መንፈሳዊ ነገሮች ውስጥ ኾኖ ማረፍ ተወዳጅ ነው። ከቁርኣን ምዕራፎች ውስጥ የሰጀዳንና የአልሙልክን ምዕራፎች አንብበን በጥሩ ዱዓ በጊዜ ለማረፍ እንጣር ከለሊቱ መጨረሻ ጥቂት ሰአት ለሁለት ረከዓ ለመስገድ እንነይትና በዝምታ እንረፍ።

አላህ ያግራልን

Best kerim

24 Oct, 18:15


ከተንቢህ አልአናምን የሰለዋት ኪታብ ላይ ውስን ስንኞችን በቀጥታ ስርጭት ላይ ለማቅረብ ሞክሬ በኔትዎርክ ምክንያት ስለተቆራረጠ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

መልካም የጁምዓ ለሊት

Best kerim

24 Oct, 18:10


Live stream finished (1 minute)

Best kerim

24 Oct, 18:09


Live stream started