Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office @bele2abc Channel on Telegram

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office

@bele2abc


እየተጠነቀቅን እንማራለን።

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office (Amharic)

ቅርፅዎችን ለመግበር ይከታተሉ! ኮልፈ፣ ከራንዮ ከተሐናፈል በተለካዮ ትምህርት ቤቶች፤ የበላ፤ እና የትምህርት ሰራተኞች መተከታተል አለበት። ይህን ኮልፈ ከባባል የተጠናቀቀ ምንጮች፣ መሳሪያዎች እና ልዩ መረጃዎች በእኛ ማድረግ ያሉት አድራጊ ዘገባዎችን በማከተል ከተማውን ለተገናኘች አድርገን በማስጠበቅ የተጠናቀቀ የሰራዊና ጥንቃቄ ነው። ኮልፈ ይህንን ይከታተሉ! ከእኛ ለማግኘት ካስተዳደር ለተጠናቀረው ህፃናት በቀላሉ ኮልፈ ተግባራት ያርጉልን።

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office

18 Jun, 15:12


የ2017 የትምህርት ዘመን የተከለሰ የትምህርት ካላንደር

(ሰኔ11/2016 ዓ.ም)

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office

17 Mar, 10:32


ቀን: 8/7/2016 ዓ.ም

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ሃ/የተ/መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር የተመሰረተበትን ፭ኛ ዓመት በዓል በኤግዚቢሽን ማዕከል አከበረ።

በክብረ በዓሉ ላይ የመኪናውን ዋጋ 25 % ቆጥበው ላጠናቀቁ 90 መምህራን እና የህብረቱ ዓባላት የመኪና ቁልፍ አስረክቧል።

@mars@abc

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office

14 Mar, 03:27


መምህር ቴዎድሮስ ብርሃኔ ይፈልጋችኋል

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office

25 Feb, 14:09


ቀን :17/6/2016 ዓ.ም

ጤግሮስ ትሬዲንግ ከፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስ/ማኅበር ጋር በመሆን በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሆቴል የአባልነት መስፈርታቸውን ላሟሉ እና ቁጠባቸውን ለአጠናቀቁ የተወሰኑ መምህራን የመጀመሪያ ዙር ዘመናዊ የኤሌትሪክ መኪኖች ብድር የመስጠት ዝግጅት እና የፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርአገብር አካሄዷል።

ጤግሮስ ትሬዲንግ "የእውቀት ባለቤት ውለታ እንመልስ" በሚል መሪ ቃል ለሀገር ባለውለታ ለሆኑ መምህራን ቁጠባና ብድርን መሰረት ያደረገ "ደራሽ" የተሰኘ የመኪና ግዥ ፕሮጀክት በመቅረፅ እና በማስተባበር ላለፉት ዓመታት ቁጠባን በማበረታታትና ብድር በመስጠት ማኅበረሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአካባቢ ልማት ላይ የድርሻውን በመወጣት ላለፉት ተከታታይ ዓመታት የሰርተፊኬት እና የዋንጫ ተሸላሚ ከሆነው ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ስ/ማኅበር ጋር በመሆን የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የአባልነት መስፈርት አሟልተው ለሚገኙ እና በጤግሮስ ትሬዲንግ የደራሽ የመኪና ብድር ፕሮጀክት ለታቀፉ አባላት የመኪና ግዥ ብድር አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ዛሬ በኢትዮጲያ ሆቴል እንደተገለጸው ይህ የደራሽ የመኪና ብድር ፕሮጀክት ቅድመ ቁጠባ 25% ለቆጠቡ መምህራን በ10 አመት የሚከፈል ብድር ነው።


በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የበላይነህ ክንዴ ጄነራል ትሬዲንግ ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ለመምህራኑ የመኪኖቹን ቁልፍ ሰጥተዋል

በተጨማሪም በነገው ዕለት የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ስራ እንደሚጀምር ባለሀብቱ በመድረኩ ላይ ገልጸዋል።

#mars@abc

Kolfe Keraniyo Sub-City Education Office

28 Sep, 18:56


የኮልፌ ፪ኛ ደረጃ መምህር የሆነው ወንድማችን መምህር ቴዎድሮስ ብርሃኔ የጭንቅላት ነርቭ መሰንጠቅ ህመም ደርሶባቸው ወደ ውጭ ሃገር ሄደው እንዲታከሙ ተወስኖላቸዋል። ከህመማቸው ድነው ወደ ስራቸው ለመመለስ የእኛን የስራ ባልደረቦቻቸውን ዕርዳታ እየተጠባበቁ ስለሆነ በምንችለው ድጋፋችንን በማድረግ እንድረስላቸው።

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው።

#mars@abc