Bonga University @bonga_university_official Channel on Telegram

Bonga University

@bonga_university_official


Together We Can

Bonga University Official Telegram (English)

Are you a current or prospective student of Bonga University? Do you want to stay up-to-date with all the latest news, events, and important announcements from the university? Look no further than the Bonga University Official Telegram channel! This channel, with the username @bonga_university_official, is your go-to source for everything related to Bonga University. From academic updates to extracurricular activities, this channel has got you covered

Bonga University Official Telegram is a community of students, faculty, and staff who are passionate about higher education and dedicated to creating a supportive and inclusive environment for all. Whether you are a freshman trying to navigate campus life or a senior looking for career opportunities, this channel is here to help you every step of the way. By joining this channel, you will have access to timely information, resources, and support that will enhance your university experience

The motto of Bonga University Official Telegram is "Together We Can", reflecting the collaborative spirit of the channel. It emphasizes the importance of unity, teamwork, and collective effort in achieving success, both academically and personally. Through this channel, you can connect with like-minded individuals, seek advice and guidance, and be part of a community that shares your goals and aspirations

Joining Bonga University Official Telegram is not just about staying informed; it is about becoming part of a network of individuals who are committed to excellence and growth. Whether you are looking for study tips, internship opportunities, or simply a place to share your ideas and experiences, this channel is the place for you. So why wait? Join Bonga University Official Telegram today and let's strive for success together!

Bonga University

17 Feb, 06:13


ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው- ቋሚ ኮሚቴዎቹ

(አዲስ አበባ፣ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖልጂ እና የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ገለጹ።

በዩኒቨርሲቲው ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ተቋሙ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ፥ ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በመማር ማስተማር ፣በምርምር እና በማህበረሰብ አግልግሎት እያከናወነ ያለውን ተግባር ለሌች ተቋማት ማካፈል እንዳለበት ተናግረዋል።

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1A2YbADiAZ/

#ከማምረትበላይ
#BeyondProduction

----------------
ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/MoAEthiopia
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/@AgricultureEthiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews
ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia

Bonga University

17 Feb, 06:13


"ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ ምሳሌ የሚሆን ነው" -- ቋሚ ኮሚቴዎቹ
---------------------
(ዜና ፓርላማ) የካቲት 4 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖልጂ እና የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በዩኒቨርሲቲው ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን ተቋሙ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው በምርምር የተደገፈ ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል ።

የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በመማር ማስተማር ፣በምርምር እና በማህበረሰብ አግልግሎት እያከናወነ ያለውን ተግባር ለሌች ተቋማት ማካፈል እንዳለበት ተናግረዋል።

ዩንቨርስቲው በግብርናው ዘርፍ በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ በቅመማ ቅመም፣ በእንሰት ምርት፣በእንሰሳት እርባታ በወተት ላምና ከብት ማድለብ፣በዶሮ፣ በንብ ዕርባታ፣በሀር ምርት እና በሌሎችም ላይ በምግብ ራስን ለመቻል እና የተሻለ ገቢ ለማግኘት እያከናወነ ያለው ስራ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም በጥምር እርሻ በትንሽ መሬት የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ውጤታማ ስራ እየሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ዩንቨርስቲውን በግብርናው ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።

የሸኮ የከብት እና የቦንጋ በግ ዝርያዎችን ጠብቆ ማቆየት እና የማሻሻል ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

የሰው ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖልጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በበኩላቸው ቦንጋ ዩኒቨርስቲ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ እንዲሆን ያስቻለው ጠንካራ አመራርና ሰራተኛውም የቡድን መንፈስ ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል ።

ለተግባር ተኮርና ችግር ፈቺ ለሆኑ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ትኩረት መሰጠቱን በጥንካሬ ያነሱት ሰብሳቢው በመምህራንና በተማሪዎች የሚሰሩ ምርምሮች ወደ ተግባር በመቀየር የአከባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት በማሳደግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በምርምር የተደገፉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው እንዲሁም ተሞክሮውን ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማስፋት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።

ለወጣቶችና ለአርሶ አደሩ ስልጠናዎችን በመስጠት የአመለካከት ለውጥ ማምጣትና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በየደረጃው ካሉ የመንግስት አካላት ጋር በጋራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል ።

ዩኒቨርስቲው በውጭና በሀገር ውስጥ እያስተማሯቸው ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎች ውጤታማ ጥናትና ምርምሮች እንዲሰሩና ተሞክሮዎችን ወደ ዩኒቨርስቲው እንዲያመጡ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ቢደረግ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል ።

የቋሚ ኮሚቴዎቹ አባላት በበኩላቸው በዩኒቨርስቲው እየተካሄዱ ያሉ ምርምሮች ወደ ችግር ፈቺነት እየተቀየሩ መሆኑን በጥንካሬ አንስተዋል።

በምርምር የተገኙ ውጤቶች ፣የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የህብረተሰብ አግልግሎቶች የሚበረታቱ መሆናቸውን እና ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጴጥሮስ ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) በመማር ማስተማር ፣በምርምር እና በማህበረሰብ አግልግሎት በዩኒቨርስቲው የተከናወኑ ተግባራትን ለቋሚ ኮሚቴዎቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአትክልትና ፍራፍሬ በአካባቢው የአየር ሁኔታ ምክንያት አይበቅሉም የሚለውን ሀሳብ ወደ ጎን በመተው በምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት በሙዝ፣በአናናስ በአቮካዶና በሌሎችም የተሻለ ምርት እና ገቢ እያገኙ መሆኑን ገልጸዋል ።

ዩኒቨርሲቲው 9 የምርምር ትኩረት መስኮች እና 22 እርሻ ላይ የተመሰረቱ የምርምር ስራዎች እንዳሉ ጠቅሰዋል።

በምርምር የተገኙ ውጤቶችን ለአርሶ አደሩና ለአካባቢው ህብረተሰብ የማድረስ ስራዎች በስፋት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ።

(በፋንታዬ ጌታቸው)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/@FDREHOPR
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Bonga University

11 Feb, 06:16


በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እንዲሁም የም/ቤቱ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰሎሞን ላሌ ጉብኝት
ተከናወነ!!
======÷÷÷=================================

ከጉብኝቱ መልስ የቦንጋ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የዩንቨርሲቲውን አጠቃላይ ገጽታ ከየት ተነስቶ አሁን ላይ ምን ላይ ደረሰ የሚለውን አቅርበዋል፡፡ የዩንቨርሲቲውን ስኬቶች ተሞክሮዎች አቅርበዋል፡፡ በተለይ አካባቢው የቡና መገኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የቡና ሳይንስ ት/ት መስክ መከፈቱ ሊጠቀስ ከሚችሉ የዩንቨርሲው መልካም ተሞክሮዎች አንዱ እደሆነ አሳይተዋል፡፡

የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በጉብኝታቸው መደሰታቸውንና ባዩት ነገር መደመማቸውን ገልጸው ዩንቨርሲቲው እንደ እድሜው እንዳልሆነና በርካታ የምርምር ተግባሩ ከዩንቨርሲቲው አልፎ ለሀገር የሚጠቅሙ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ካዩዋቸው የምርምር ፕሮጀክቶች ት/ት መውሰዳቸውን ገልጸው ቦንጋ ዩንቨርሲቲ ከድህነት የምንወጣበትን ብልጭታ አሳይቶናል በማለት የተሰማቸውን ከፍተኛ አድናቆት ሰንዝረዋል፡፡
የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት ሀሳብ ተቋም ሁሌም መሪውን ይመስላል ያሉ ሲሆን በተለይ የቦንጋ ዩንቨርሲቲ አመራር ዋጋ በመክፈልና እራስን መስዋዕት በማድረግ እንደመስራታችሁ ተጨባጭ ለውጥ አምጥታችኋል ብለዋል፡፡ አክለውም ዩንቨርሲቲው የልዩ ተሰጥኦ እና ተውቦ ባለቤት እንደሆነ ጠቅሰው ለዚህ ደግሞ ልዩ ሽልማት ይገባችኋል ብለዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ሰሎሞን ላሌ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በዩንቨርሲቲው የተሻለ ነገር አይተናል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በምርቶቻችሁ ላይ ዕሴት በመጨመር ወደ ማቀነባበር ደረጃ መሻጋገር ብትችሉ ብለዋል፡፡ የዩንቨርሲቲውን ተግባር ተኮር ምርምር ߹ የቡድን መንፈስ ߹ቃል በተግባር መፈጸሙን ፤ ዋጋ ለማረጋጋት እየተደረገ ያለውን ተግባር አድንቀዋል፡፡

በመማር ማስተማሩ ዘርፍም በመውጫ ፈተናም የተመዘገበው ውጤት የዩንቨርሲቲው የትጋት ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡ አጎራባች ላይ ለሚገኙ ከፍተኛ ት/ት ተቋማትና ከክልል እስከ ቀበሌ ላሉ የግብርና መዋቅሮች ተሞክሮዎችን ማስፋፋት ልምድን ማካፈል ቢቻል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ለተከበሩ የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ቦንጋ ዩንቨርሲቲን በመጎብኘታቸው አመስግነው በቀጣይም ክትትልና እገዛችሁ አይለየን ከናንተ የምንማረው ብዙ አለን በማለት ተማጽኖ በማቅረብ ምክክሩ ተቋጭቷል፡፡
በጋራ እንችላለን!!

Bonga University

09 Feb, 12:49


የፌዴራልና የደቡብ ምዕራብ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አካሄዱ::

በጉብኝቱም የኢፌዴሪ ግብርና ሚ/ር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ : የደ/ምዕ/ኢ/ያ ህዝቦች ክልል ር/መ/ር ከቡር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ: የክልሉ ም/ር/መ/ር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ማስረሻ በላቸው እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ፕ/ት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ መሪነት በዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል:: በመጨረሻም የግብርና ሚ/ሩ ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ ዩኒቨርሲቲው በግብርናው ዘርፍ የሰራቸውን የልማት ሥራዎች በማድነቅ በርቱ ተበራቱ በማለት ምስጋናቸውን አቅርበዋል:: በጋራ እንችላለን!

Bonga University

08 Feb, 10:50


የቦንጋ ዩንቨርሲቲ በመንግስት የኤሌክትሮኑክስ ግዥ/E-GP/ ዙሪያ ለንግዱ ማህበረሰብ ስልጠና ሰጠ::
========የካቲት 01/2017 ዓ.ም.=======
ዩንቨርሲቲው ስልጠናውን ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን መ/ቤት ጋር በመተባበር የሰጠ ሲሆን. . .
መድረኩን የቦንጋ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዎርጊስ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የዕለቱን የክብር እንግዳና የባለስልጣኑን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌን የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ በመጋበዝ ነበር::
የፌደራሉ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርም ክብርት ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ስለ
በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓት ዙሪያ አጠቃላይ የሆነ ማብራሪያ ሰጥተዋል::
በመቀጠል የባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ ባለሞያዎች አቶ አበበ አበሩና አቶ ያፌት መኮንን የስልጠና ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን
ከንግዱ ማህበረሰብ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
በጋራ እንችላለን!!

Bonga University

05 Feb, 13:14


ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከነገ ጥር 26 -30/2017 ዓ.ም. ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅቱን አጠናቀቀ. . .
=======ጥር 25/2017ዓ.ም.======

የዩንቨርሲተው ግብረ -ሀይል ዛሬ ማለዳ ባከናወነው ምልከታ ከነገ ሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ለሚሰጠው ፈተና ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ለማወቅ ችሏል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የመፈተኛ ኮምፒውተሮች በበቂ ሁኔታ የተሰናዱ ሲሆን የመብራትና ሌሎች አገልግሎቶችም በፈተናው ወቅት መቆራረጥ እንዳይኖር ዝግጁ ሆነዋል::
በመጨረሻም የመውጫ ፈተና ግብረ-ሀይል ሰብሳቢ ዶ/ር ያሬድ አያሌው እንደገለጹት ሁሉም የኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እስከፈተናው መጠናቀቅ ድረስ የተሰጠንን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ይህንን ትልቅ ሀገራዊና ተቋማዊ ሀላፊነት መወጣት ይገባናል ብለው የአደራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::
በጋራ እንችላለን!!

Bonga University

28 Jan, 15:35


ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለክረምት ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ገለጻ /Orientation/ ሰጠ፡፡

ጥር 19/2017 ዓ.ም.

ከጥር 26 – 30 /2017 ዓ.ም. ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ተማሪዎች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ አስፈላጊው ገለጻ በአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር በዶ/ር ያሬድ አያሌው መሪነት የተሰጠ ሲሆን
በመድረኩ ላይ የሬጅስትራር ዋና ዳይሬክተር፣ የኮሌጅ ዲኖች ߹ የኢ-ለርኒግ ዳይሬክተር የተከታታይ ት/ትና ስልጠና አስተባባሪ ተገኝተዋል፡፡
ተማሪዎች ስለሚጠበቁባቸው ተግባራት በተለይ ያላቸውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም የሚሰጡ የቲቶሪያልና የመለማመጃ ፈተናዎችን/Mock exam/ በአግባቡና በወጣላቸው ፕሮግራም መሰረት መጠቀም እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡
የመለያ ስማቸውንና የማለፊያ ቁጥሮቻቸውን በአግባቡ በመመዝገብ መያዝ እንዳለባቸው ከመገለጹም ባሻገር ከት/ት ሚንስትር በተላከው መመሪያ መሰረት ለፈተናው ተገቢውን ግዴታ መወጣት ሌላው በመድረኩ የተነሳ ነጥብ ነው፡፡
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለየ ሁኔታ ይህንን ልዩ የተማሪዎች እገዛ ሲያደርግ ለማህበረሰቡ ከሚሰጠው ድጋፍ አካል አንዱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዚህኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከክረምት ተማሪዎች በተጨማሪ የማታውንና የሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1003 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

በጋራ እንችላለን!

Bonga University

07 Jan, 15:04


ታህሣሥ 29/2017 ዓ/ም

አረጋውያን፣ ተማሪዎችና የጌታ ልደት መታሰቢያ በቦንጋ ዩኒቨርስቲ
===========================

ከዩኒቨርስቲው ተልዕኮ አንዱ የማህበረሰብ አገልግሎት ሲሆን ዩኒቨርስቲው በይፋ ስራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየወሩ ከሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የተለያዩ አይነት ድጋፎችን አስታዋሽ ላጡ አረጋዊያንን እያደረገ መቆየቱ ይታወቃል።

ዛሬም ለአረጋዊያን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በቁጥር 65 ለሚሆኑ የማዕድ ማጋራት አድርገዋል ።

ከቤተሰቦቻቸው በአደራ ለተቀበላቸው መደበኛ ተማሪዎች ልዪ ዝግጅት በማዘጋጀት የተቋሙ አመራሮች በተገኙበት በጋራ አክብረዋል።

በጋራ እንችላለን!

Bonga University

03 Jan, 07:02


ታህሳስ 24/2017 ዓም

1_ ከትናንትና የቀጠለው የመስክ ጉብኝት ተጠናቀቀ!
2_ በ "e-SHE " ቴክኖሎጅ ፋይዳ ላይም ስልጠና ተሰጠ!
=======================

በትናንትናው ዕለት የተጀመረው ይህ ጉብኝት ዩኒቨርሲቲዉ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን በስፋት በዕውቀት ላይ ተመስርቶ በማከናወን ለሀገርና ለወገን የሚጠቅም ስር ነቀል ለውጥ ለማስመዝገብ እየሰራ ያለው ስራ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመመልከት የተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የጉብኝቱን ፋይዳ አስመልክተው በእኩል ደረጃ ሁሉንም ፕሮጀክቶች ተንቀሳቅሰን መመልከታችን በተመሳሳይ መልኩ አቅማችን አሟጠን ለመስራት ያለንን ግብዓቶችና ሀብቶች እንዲሁም የሰው ሀይል እንድናውቅ ያደርገናል፡፡

ስለዚህ የምርምር ፕሮጀክቶች ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመለየትና ለመቅረፍ እንዲሁም ተቋሙ ያለመውን የልሂቀት ጉዞ እውን ለማድረግ በመደጋገፍ በመረዳዳት ለተቋሙ ሰራ ስኬት ሁሉም በተመሳሳይ እውቀት፣ ግንዛቤ በእኩል ደረጃ በመስራት ተቋሙ በ2030 ለመድረስ ያለመውን ራዕይ እውን ለማድረግ የተደረገ ጉብኝት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም በሁሉም ዘርፍ ላይ ያሉንን ሀብቶችና እውቀቶች ሳንሰስት በማፍሰስ ሀገር ከእኛ የምትጠብቀውን ውለታ ልንከፍል ይገባል ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም

የንብ ርባታ ፕሮጀክት ፣

የቻዎቴ ተክል፣

የሙኩና ተክል ፣

የእንስሳት ርባታ፣

የሙዝና የተለያዩ ፕሮጀክቶች፣

ቤተ-መጻህፍት ፣

የተማሪዎች ምግብ ቤትና

የንብረት ክፍል

የተጎበኙ ሲሆን በዚህ ጉብኝት ከታዩ ችግሮች መካከል አንዱ የንብ እርባታ ፕሮጀክት ላይ የአየር ለውጥ ችግር ተጽዕኖ የፈጠረ ቢሆንም በተለይ ንብ በብዛት የሚገኝባቸው አካባቢዎች ላይ በመሄድ ተጨማሪ ጣቢያዎችን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የምርምር ስራዎችን የማሳተምና የተሻሻሉ ዝርያዎችንም የማስፋፋት ሰራ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ ተሳታፊዎችም በተጎበኙ ዘርፎችና ስራ ክፍሎች ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች የሚቀጥሉና የተቋሙ የስራ ባህል መሆናቸውን ገልጸው፡ እንዲሁም በደካማ ጎን የተነሱ ነጥቦች በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው የተቋሙን ራዕይ እውን የሚያደርጉበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሰዓት በኃላ በነበረው የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የስልጠና መድረክ ተከናውነዋል:-

መንግሥት ቀደም ስል የነበረውን የትምህርት አስጣጥ በመፈተሸ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም ተማሪዎች ራሳቸውን ከዘመኑ ቴክኖሎጅ ጋር ማዘመን ግድታቸው በመሆኑ በምንም አይነት ሁኔታ" e-SHE " ቴክኖሎጅ በአግባቡ በመጠቀም ራስን ዝግጁ ማድረግና የሚስጠውን ኮርስ መክታተል እንዳለባቸው ለአድስ ተማሪዎች ስልጠና ቸሰጥቸዋል ። የ ተቋሙ ዲጂታል ላይብረሪ መጠቀም እንዲሁም እገዛ ሲያስፈልጋችሁ ደግሞ የICT ባለሙያዎች እገዛ መጠይቅ ይኖርባቸዋል በማለት መድረኩን ፕረዝዳንቱ በመክፈቻ ንግግራቸው በማሳስብ ያስጀመሩ ስሆን የግንዛበ ማስጨበጫው በባለሙያዎች ተሰጥቱል።

Bonga University

31 Dec, 15:56


ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የዩኒቨርሲቲውን የማሕበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ ለመጀመር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድማሱ ዳምጠው እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በይበልጥ አቅሙን አጠናክሮ በአዲስ መልክ መዋቀሩን በዚሁ ወቅት አቶ አድማሱ አስታውቀዋል፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም አብሮ ለመሥራት ፋናን መምረጡ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው ተቋማቸው የሚሠራቸውን የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማሕበረሰብ አቀፍ ሥራዎች ለማስተዋወቅ ሰፊ አቅም ያለው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ትክክለኛው ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በፍሬው ዓለማየሁ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን

Bonga University

31 Dec, 05:48


የጋራ መግባቢያ ስነድ(MoU) ፊሪማ ሰነ ስርዐት ተከናወነ!!
=========================
ቀደም ሲል ከቡና ጥራት ጋር በተገናኘ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ናሙና በመዉሰድ በሰው ሰራሽ አስተዉሎት የቡናን ደረጃ ልየታ የጀመሩት የFun's Choice Alliance ኩባንያ ልዑካን ከቡና ተመራማሪዎች፣
ከቡና ትምህርት ክፍል መምህራንና ተማሪዎች፣
ከክልልና ከተለያዩ ተቋማት ከመጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና የቡና ባለሀብቶች
ጋር ዛሬ በቀን 21/04/2017 ጧት በካፋ የጫካ ቡና የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበር የቡና ናሙናዎችን ደረጃ የመስጠት ተግባር በሁለት መልክ አከናውነዋል።
በመጀመሪያ በተለመደው አሰራር ማለትም 40% በጥሬው (በአካላዊ ይዘትና እርጥበት መጠን)፣ 60%ን ደግሞ የተወሰደው ናሙና ከተቆላ በኋላ በሚደረጉ የጣዕምና መዓዛ ልየታ ሲሆን ሁሉንም ሂደቶች ከቅምሻ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ለሁሉም ናሙናዎች የተሰጠውን ደረጃ በመመዝገብ ተጠናቋል።
በመቀጠልም በዘመናዊ ማሽን ከላይ የተቀመጡ ሁሉንም የቡና ናሙናዎች አንድ በአንድ በመውሰድ በጣም ባጠረ ጊዜ ደረጃቸው የተለየ ሲሆን በሚያስደንቅ መጣጣም ከ0.1% ያነሰ ልዩነት ተመዝግቧል።
ከሰዓት በኋላም የFun's Choice Alliance ኩባንያ ከሁለት ቀናት በፊት በገባው ቃል መሰረት ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት /Memorandum of understanding/ በመፈራረም በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሯቸው ሥራዎች ላይ በመግባባት ልዑካን ቡድኑ ተሸኝተዋል።
በጋራ እንችላለን

Bonga University

30 Dec, 15:45


https://youtu.be/SloQKzgx5xk

Bonga University

30 Dec, 15:40


የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመመዝገን ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET

Bonga University

03 Dec, 21:55


ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!

Bonga University

21 Nov, 15:35


ሕዳር 12/2017ዓ/ም
ቦንጋ ዩኒቨርስቲ እና ናቡ ኢትዮጵያ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
ስምምነቱ የተፈጥሮ ሀብትን በመንከባከብ የአየር ንብረት ምህዳርን በማስተካከል ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰራዎችን በጋራ ለመስራት ያለመ ነው፡፡
በመድረኩም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ ዩኒቨርሲቲዉ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር ተቋሙን፣ ሀገርን እና አለምን የሚጠቅሙ ተግባራትን ለማከናወን እየሰራ ስሆን ከዚህም መካከል አንዱ ተቋሙ በ2030 በእ.አ.አ በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም በአፍሪካ ካሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንደኛ ለመሆን የሚያደርገውን ጉዞ የሚደግፉ ተግባራትን ማከናወን በመሆኑ የዛሬው ስምምነት በጋራ ተባብረን ከሰራን ራዕያችንን ከማሳካቱም በተጨማሪ ማህበረሰባችን ተጠቃሚ ያደርጋል በማለት ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ እና የናቡ ኢትዮጲያ ኤክስክዩቲቨ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሲሳይ አስፋው ተፈራርመዋል።
በጋራ እንችላለን

Bonga University

13 Nov, 12:36


ከዚህ ስብሰባ በኋላ ዩኒቨርስቲዎችን የምንመራበት አመለካከት Fundamentally መቀየር አለበት።
ክቡር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
የአርባ ሰባቱም የመንግስት ዩኒቨርስቲ ቦርድ አመራሮችና ፕረዚዳንቶች በተገኙበት መድረክ ላይ ክቡር አቶ ኮራና ዶክተር ሰለሞን የዩኒቨርስቲዎች አሁናዊ ገፅታ ምን እንደሚመስልና ከሪፎርም አንፃር ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎ ክቡር ሚኒስትር አደራና አቅጣጫ ሰጥተው ሰብሰባው ተጠናቋል።
በስብሰባው የተገኙ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ የሚከተለውን ሀሳብ በመድረኩ አንስተዋል።
ነጥቦቹም፣
1. *ጥራት* - የትምህርት ጥራትን ጉዳይ በዘለቀታዊ መንገድ ለመፍታት የ ማህበረሰብ ኣገልግሎት ስራችንን ማዕከል ያደረገ የከፍተኛ ትምህርትና የመደበኛ ትምህርት ቅንጅት ትኩረት ቢደርግ፣
2. *የሪፎርም ምስሰዎች* - 6ቱ ምሶሶዎች ውጤታማ መሆን የሚችሉት ለዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በ ጥልቀት ስናስጨብጣቸው ስለሆነ በተለይ የመምህራንና የቴክኒክ ሰራተኞች የክብር ስራ ተከታታይ የልማት እና የአቅም ግንባታ ስራዎች ትኩረት እንደሚያስፈልግ፣
3. *መረጃ* - የከፍተኛ ትምህርት የመረጃ ስርዓት በልዩ ትኩረት ተነባቢ የሆነ ተቋማዊ ቋት በየዩኒቨርስቲው ተደራጅቶ በሀገር (MoE) ደረጀ የሚሰበሰብ ሆኖ ቢመራ፣
4. *ስነምህዳር* - የከፍተኛ ትምህርት ስነምህዳር ጉዳይ ሊይዛቸው የሚገቡ ተግባራት ተለይተው (በተለይም ደጋፊ ከባቢያዊ ሁኔታ ከመፍጠር አኳያ ከአካባቢ የመንግስት መዋቅር ጋር የሚሰሩ ስራዎች) መለኪያም ተበጅቶላቸው ቢመሩና፣
5. *የሚለካ የቦርድ ተግባር* - የቦርድ ተግባርና ሃላፊነት በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ በተመለከተው መሠረት ለሁሉም ዩኒቨርስቲ ሊሆን በሚችል መልኩ minimum የጋራ format ኖሮን በሚለካ መንገድ እንድንመራ MoE ቢረዳን የሚሉ ናቸው።
ስብሰባው እጅግ ገንቢ ሀሳቦች የተነሱበት መሆኑንና በቀረበው ግምገማ መሠረት ዩኒቨርስቲያችን በቦርድ፣ በከፍተኛ አመራር፣ በአመራር፣ በመምህራን፣ እና በተማሪዎች ደረጃ ትኩረት ማድረግ የሚገቡን ጉዳዮች ለይተን ወደ እቅድ ቀይረን እንምራ በማለት አመራር ና አቅጣጫ ለዩኒቨርስቲው ቦርድ አባላት ክቡር ፕሮፌሰር አፈወርቅ እንደሰጡ በቦታው የተገኙ የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት መረጃውን ለዩኒቨርስቲው አስተላልፈዋል።
በጋራ እንችላለን!
መልካም ቀን

Bonga University

10 Nov, 14:50


በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕ/ት የተመራው ልዑካን ቡድን በጌሻ ወረዳ ያሉትን የምርምር ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ገመገመ::
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕ/ት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ ከቀን 30/02-02/03/2017 ዓ/ም ድረስ በጌሻ ወረዳ በአበታ: ኑትቅቲ እና ተገሎ ቀበሌ የሚገኙትን የእንሰት: ቡና: አፕል: ሙኩና ምርምር ፕሮጀክት: ለሰርቶ ማሳያነት የተዘራውን የስንዴ ማሣ እና በመማር ማስተማሩ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ የሚሰጠውን የትም/ት ሂደትና ሁለተኛ ደረጃና መሠናዶ ት/ቤቶችን ለማብቃት የተሠሩ ስራዎችንና የተገኘውን ውጤት በመመልከት በቀጣይ መሠራት ባለባቸው ተግባራት ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መክረዋል::
በጋራ እንችላለን!!

Bonga University

08 Nov, 17:53


የ2017የመጀመሪያ 1ኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተካሄደ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ/ም በአንደኛ ሩብ ዓመት በሁሉም ዘርፍ ያከናወናቸውን ተግባራት ጥቅል ሪፖርት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት፣ ም/ፕሬዝዳንቶች፣ የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የቀረበዉን ሪፖርት ያደመጡ ሲሆን ውይይቱንም በመምራት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመድረኩም ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሰው ሀይል እጥረት ሲሆን ይህንንም ለመቅረፍ አንዳንድ ኮሌጆች ላይ በገበያ ላይ ያልተገኙትን በዝውውር ማምጣት የተቻለ ሲሆን በአስተዳደር ሰራተኞች በኩል ያለውን ችግር ለመቅረፍ በትናንሽ መደቦች ላይ በኮንትራት የማሟላትና እንዲሁም ተመሳሳይ መደብና ደሞዝ ያላቸውን በዝውውር ለማሟላት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የተቋሙ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ እንደሚከተለው አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን፣
_ መማር ማስተማር በተመለከተ የመውጫ ፈተና ዝግጅት ከአሁኑ መጀመር አለበት፡፡
_ በላብራቶሪና በቤተ-መጻህፍት ላይ በየሳምንቱ ክትትትል እየተደረገ ችግሮች መቀረፍ አለባቸው፡፡
_ የምርምር ፕሮጀክቶችን ለህትመት ከማብቃት ጋር ያለው ሁኔታ ትኩረት ይሻል፡፡
_ የአካዳሚክ እውቀትን እንዴት ወደ ገቢ ማመንጫ መቀየር እንዳለብን መሰራት አለብን፡፡
_ ምርምሮቻችን አከባቢያችንን ሀገራችንን ችግር የምቀርፍና የሚያበለጽግ መሆን አለበት።
_ መምህራኖችን የምናሰለጥነው በትኩረት አቅጣጫችን መሰረት ያሉ ሲሆን እንዲሁም
በአስተዳደርና ልማት ዘርፍ በኩል
_ የንብረት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ይሻል፡፡
_ ንብረት በሁለት መንገድ ህይወት ያላቸውና የሌላቸው ተብሎ ተመዝግቦ ተይዞ በየጊዜው ክትትል መደረግ አለበት፡፡
_ የግቢው ንፅህናን በተመለከተ ዘወትር ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል
_ የውስጥ ገቢን ከማመንጨት አንጻር ቡና፣ ቅመማቅመም፣ የጅም ዋጋ ወዘተ በደንብ መሰራት አለባቸው ያሉ ሲሆን፣
በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በኩል
_ ህብረብሄራዊነትን የሚያጎለብቱ ጽሁፎችና መዝሙሮች በየጊዜው ተደራሽ መደረግ አለባቸው በማለት ገልጸዋል፡፡
በስተመጨረሻም በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በጋራ እንችላለን!!!

Bonga University

04 Nov, 15:05


በ World University Ranking for Innovation(WURI) ያገኘነውን ደረጃና ምክንያቱን እንድናስረዳ፣ ልምድ እንድንካፍልና እኛም የሌሎችን ልምድ እንድንካፈል በተደረገልን ጥሪ መሰረት የዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት ቀርበው ያስረዱና ከበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር MoU የተፈራረሙ ሲሆን አብዛኞቹ መጥተው ልጎበኙን ቃል ገብተዋል።
በጋራ እንችላለን!

Bonga University

26 Oct, 16:43


በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የልማት የስራዎች አንዱ በሆነዉ የሻይ ቅጠል ምርት መልካም ውጤት እያስመዘገበ መሆኑንና የሻይ ቅጠል ምርታማነትን ለማሳደግ በምርምርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
በጋራ እንችላለን!

Bonga University

17 Oct, 11:19


Dear brothers and sisters

no need to put any suffix, infix or prefix on coffee .
Just "coffee science" Please.
We endorsed it at Senate meeting some 3 or 4 years a go!

Bonga University

11 Oct, 05:57


ለትምህርት ፈላጊዎች
◈◈◈◈
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መርሀ ግብሮች እና ትምህርት መስኮች በግል ለመማር ማመልከት የሚትችሉ መሆኑን ዩኒቨረሲቲው ገልጿል!!
◈◈◈◈
በጋራ እንችላለን!

Bonga University

05 Oct, 16:13


Bonga University Holds Curricula Validation Workshop
Today (October 5, 2024),
Bonga University held an external curriculum validation workshop for a PhD program in Coffee Science and an MSc program in Climate Change and Food Security.
The draft curricula, which were internally validated last week, have now been externally validated after a thorough examination of the needs assessment, the programs' rationale, and their alignment with the university's thematic areas.
With the external validation of these curricula, Bonga University has become one of the few universities in the world—and the first in the academic history of Ethiopia—to offer a PhD program in Coffee Science and an MSc in Climate Change and Food Security.
In his opening speech, Dr. Kelelew Addisu, the Vice President for Academic, Research, Community Service, and Technology Transfer, indicated that teaching Coffee Science and conducting research at a PhD level in the birthplace of coffee is indeed a proud moment.
Together we can!!

Bonga University

03 Oct, 18:02


ክቡር ሚኒስትር!
ስለሰጡን ዕውቅና ከልብ እናመሰግናለን!
በጋራ እንችላለን!!
Yes
Together we can!
we thank you so much!
we will do more!!!