Awolia School @awoliaschool5 Channel on Telegram

Awolia School

@awoliaschool5


የእወሊያ ትምህርት ቤቶች የቴሌግራም ቻናል እና ግሩፕ ስልክ ቁጥር ነው! 0988489131

Awolia Schools

Channel (ቻናል)
👉 t.me/awoliaschool5
Group (ግሩፕ)
👉 t.me/awoliaschool6

ARDO
Channel (ቻናል)
👉 t.me/ardoeth
Group (ግሩፕ)
👉 t.me/ardoethG

Awolia School (Amharic)

እወሊያ ትምህርት ቤቶች በቴሌግራም ቻናልና ግሩፕ ስልክ አድራጊ ሥራ ላይ ያሳያል። ይህ ቻናል በእወሊያ ቤቶች የተቀላቀሉ ከሆነ ትምህርት መምህርቱን በመጠቀም እና ትምህርት መረጃዎቹን ከእናቴናም መሸነጽ ያለውን ወላጆችን ለመድራት ያድርጉ። Awolia School channel፣ የቴሌግራም ቻናል ሾፍቲን አክብሮ መደምስ እና ከገጹ በኃይሉ የቴሌግራም ቻናል ለመረጃዎች ይሆናል። ስለሆነ የAwolia School channel ይቀርባል።

Awolia School

29 Jan, 14:55


ቀን እሮብ ጥር 21/2017

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ባሉት ክፍት ቦታዎች ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

በፎቶ ላይ የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

መልካም እድል!

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

26 Jan, 12:37


ቀን እሁድ ጥር 18/2017

                   ማስታወቂያ
ለአወሊያ ት/ት ቤቶች ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ

👉 ከነገ ሰኞ ጥር 19/2017 ዓ/ል ጀምሮ በሁሉም አወሊያ ት/ት ቤቶች የመጀመሪያ ሴሚስቴር መጠቃለያ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።

👉 ስለሆነም ተማሪዎችም በጥናታችሁ ላይ በመበርታት ጥሩ ዝግጅት በማድረግ በየትምህርት ቤታችሁ በተቀመጠላችሁ የፈተና ፕሮግራም መሰረት በሰዓቱ ፈተናው ላይ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

👉 ወላጆችን ልጆችን ለፈተናው ዝግጅት እንዲያደርጉ በማድረግ በተቀመጠው የፈተና ፕሮግራም እና ሰዓት መሰረት ወደየ ትምህርት ቤታቸው በግዜ እንድትልኩ እናሳስባለን።


ማሳሰቢያ!
👉 ወርሃዊ የት/ት ቤት የተማሪ ክፍያ ያልከፈሉ ተማሪዎች ከፈተናው በፊት በአዋሽ ባንክ እስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ብቻ እንድትከፍሉ እናሳስባለን።

  
                     አወሊያ ሙስሊም  ት/ት ቤቶች

አወሊያ ቴሌግራም👇
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

19 Jan, 19:26


ቀን ጥር 11-2017 ዓ.ል

📚 ዜና አወሊያ ሙስሊም ት/ት ቤቶች

👉 ለ2 ቀናት (ቅዳሜ እና አሁድ) በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የአወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች የ5 አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ መሰረት ያደረገው ግምገማ፣ ወይይት በዛሬ አለት ተጠናቋል።

👉 ከጋላክሲ ትምህርት ስልጠናና ማማከር አገልግሎት ጋር የሚዘጋጀው እስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ግምገማው የአወሊያ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገበት ሲሆን

👉 አጠቃላይ የእቅድ ዝግጁቱ የደረሰበት ደረጃ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል።

👉 ዶ/ር ጀማል መሀመድ የአ.ዕ.ል.ድ የቦርድ ሰብሳቢ በሁለቱ ቀናት የነበረው ቆይታ ለትምህርት ቤቱ እየተሰራ ያለው ስትራቴጂክ እቅድ ትልቅ ጥቅም እና ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን

👉 የአ.ዕ.ል.ድ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጂ ሰኢድ አስማረ በበኩላቸው የሁለቱ ቀን ቆይታ የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ ግለሰቦች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ስልጠና ለሰጡት ለዶ/ር ጀማል እና ለአቶ አብዱልኳሊቅ ምስጋና አቅርበዋል።
እቅዱን በዋናነት ለሚያዘጋጁት ጋላክሲ ትምህርት ስልጠናና ማማከር አገልግሎት ላቅ ያለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለአወሊያ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር (አልሙኒ) የእቅድ ስራው እንዲሳካ ለሚያደርጉት ጥረት በማመስገን ውይይቱ በዛሬ እለት ተጠናቋል።

👉 አወሊያ ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5

አወሊያ ት/ት ቤት Facebook👇👇👇
👉https://www.facebook.com/Awoliaschool5

Awolia School

17 Jan, 18:03


ቀን ጁምዓ ጥር 9/2017

አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

                   ማስታወቂያ
       ለአወሊያ ማህበረሰብ በሙሉ!

👉 ነገ ቅዳሜ ጥር 10/2017 ዓ/ል መደበኛ ትምህርት እና ስራ በሁሉም አወሊያ ቅርንጫፎች የማይኖር (ዝግ) መሆኑን እያሳወቅን።

👉 ሰኞ ጥር 12/2017 ዓ/ል መደበኛ ትምህርት እና ስራ በሁሉም አወሊያ ቅርንጫፎች ሙሉ ቀን ያለ መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

አወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት


👉 አወሊያ ቴሌግራም
t.me/awoliaschool5

Awolia School

08 Jan, 18:01


ቀን እሮብ ታህሳስ 30/2017

     ዜና አወሊያ ሙስሊም ትምህርት ቤቶች

👉 የአወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ/ል የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት አጠቃላይ የጥያቄና መልስ ውድድር መዝጊያ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ታህሳስ 30/2017 ዓ/ል በአወሊያ ዘመናዊ አዳራሽ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

👉 በአዲሰ አበባ ከተማ በሚገኙት ሁሉም  ቅርንጫፍ የአወሊያ ሙስሊም ት/ቤቶች መካከል በውስጥ ሲካሄድ የነበረው ውድድሩ ማጠቃለያ በትምህርት ዘርፍ አዘጋጅነት ከሁሉም ት/ቤቶች በተውጣጡ ተማሪዎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ማጠቃለያ ውድድር በአወሊያ ዋና ግቢ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

👉 በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱም ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ሀጂ ሰይድ አስማረ   ከ70 አመታት በላይ የከፍታ ታሪክ ያላቸው  አወሊያ ሙስሊም ት/ቤቶች የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎችን የማፍራት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

👉 አያይዘውም የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት  የትምህርት ዘርፍ በያዝነው ዓመት የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅና ብቁ ተወዳዳሪ ዜጎችን ከማፍራት አንፃር የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎች፤ የአቅም ግንባታ ስራዎች፤ የድጋፍና ክትትል ስራዎች እንዲሁም የቅንጅትና የትብብር ስራዎች እየተሠሩ መሆናቸው  የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት እና የስነ ምግባር መሻሻል ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው ለዚህም ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል።

👉 በመጨረሻም የትምህርት ዘርፉ ቅንጅታዊ አሰራሩን አጠናክሮ ተማሪዎች በክፍል ምዘናዎችም ሆነ በከተማ አቀፍ እንዲሁም ሀገር አቀፍ ምዘናዎች ከፍተኛ ውጤት እንዲያመጡ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች እያደረጉት ያለውን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አውስተው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ተማሪዎች ላይ የውድድር የትብብር መንፈስ የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

👉 በጥያቄና መልስ ውድድሩ ከ6ኛ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍሎች 
በሶስቱም የክፍል ደረጃዎች ከ1ኛ እስከ 3ኛ የወጡ ተማሪዎች የሜዳሊያና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

👉 በተጨማሪም በትምህርት ተቋም ደረጃ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ከፍተኛ ነጥብ ካስመዘገቡ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል
በ6ኛ ክፍል አወሊያ ፒያሳ፤
በ8ኛ ክፍል አወሊያ ፒያሳ እና አወሊያ ቁጥር 1 አንደኛ ደረጃ አስኮ እንዲሁም
በ10ኛ ክፍል አወሊያ ቁጥር 1 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

👉 የአወሊያ ሙስሊም ት/ቤቶች የ2017 ዓ/ል የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው አጋማሽ አመት አጠቃላይ የጥያቄና መልስ ውድድር መዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ተማሪዎች የተለያየ የተሰጥኦ ችሎታቸውን ያሳዩ ሲሆን በተማሪ ሀምዛ የቀረበው የስማርት ጀልባ የፈጠራ ስራ ፕሮቶታይፕ የታዳሚዎችን ቀልብ የገዛ ድንቅ የፈጠራ ስራ ነበር።

👉 በውድድር መዝጊያ ፕሮግራም ላይ በተማሪዎችና ትምህርት ቤት ማህበረሰቡ  መካከል ከፍተኛ ተነሳሽነትና ተወዳዳሪነት መንፈስ ተስተውሏል።

👉 በቀጣይም እንዲህ አይነት ትምህርታዊ ንቅናቄዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ከቤቱ የቀረበውን አስተያየት ትምህርት ዘርፉ ተቀብሎ እንደሚቀጥሉ ቃል በመግባት የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል።


                      አ.ዕ.ል.ድ ትምህርት ዘርፍ

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

አወሊያ ት/ት ቤት Facebook👇👇👇
👉https://www.facebook.com/Awoliaschool5

Awolia School

07 Jan, 18:03


ቀን ማክሰኞ ታህሳስ 29/2017

አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

                     ማስታወቂያ
ለአወሊያ ት/ት ቤቶች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ

👉 በነገው ዕለት እሮብ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ል በሁሉም አወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት ሙሉ ቀን ያለ መሆኑን እናሳውቃለን።

                     አወሊያ ት/ት ቤቶች

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

03 Jan, 16:16


ቀን ጁምዓ ታህሳስ 25/2017

አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

                     ማስታወቂያ
ለአወሊያ ት/ት ቤቶች ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ

👉 በነገው ዕለት ቅዳሜ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ል በአወሊያ ሙስሊም ሚሲዮን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መካከል ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የጥያቄና መልስ ውድድር ለሌላ ቀን የተላለፈ(የተዘዋወረ) ሲሆን መደበኛ ትምህርት በሁሉም የአወሊያ ትምህርት ቤቶች ነገ ሙሉ ቀን የሚቀጥል(የሚኖር) መሆኑን እያሳወቅን

👉 የጥያቄና መልስ ውድድሩን በቀጣይ በሚገለፅ ቀን የሚካሄድ መሆኑንም ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

                     አወሊያ ት/ት ቤቶች

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

23 Dec, 09:00


ቀን ሰኞ ታህሳስ 14/2017

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

Awolia School

04 Dec, 13:29


ቀን:- እሮብ ህዳር 25/2017 ዓ/ል
Wednesday Dec 4/2024 G.C
           
           ኢናሊላሂ ወኢና ኢሌይሂ ራጅዑን!

👉 በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት በጥበቃ ሠራተኝነት በጡረታ እስከተሽኙበት ቀን ድረስ ለብዙ አመታት ለአወሊያ ያገለገሉት ጋሽ ዳህላን አሊ የአላህ ቀድር ሆኖ ዛሬ እሮብ ህዳር 25/2017 ዓ/ል ወደ ማይቀረው ቤታችን ወደ ሆነው አኼራ ሄደዋል።

👉 አላህ ጀነቱል ፍርደውስ ይወፍቃቸው!
👉 ለቤተሰቦቹም አላህ ሰብሩን ይለግሳቸው!
👉 ለኣላህ ብለን ሁላችንም አውፍ እንበላቸው!

👉 ጽ/ቤታቸንም በቀድሞ የስራ ባልደረባችን ሞት ጥልቅ ሀዘኑን እየገለፀ ለቤተሰቦቹም ሆነ ለመላው የጽ/ቤቱ መምህራን እና ሠራተኞች መፅናናትን ይመኛል።

                                አ/ዕ/ል/ድ

አወሊያ ቴሌግራም👇👇👇
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

22 Nov, 17:45


ቀን ጁምዓ ህዳር 13/2017

                   ማስታወቂያ
ለአወሊያ ት/ት ቤቶች ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ

👉 ከፊታችን ሰኞ ህዳር 16/2017 ዓ/ል ጀምሮ በሁሉም አወሊያ ት/ት ቤቶች የመጀመሪያ ሴሚስቴር አጋማሽ (ሚድ) ፈተና መሰጠት ይጀምራል።

👉 ስለሆነም ተማሪዎችም በጥናታችሁ ላይ በመበርታት ጥሩ ዝግጅት በማድረግ በየትምህርት ቤታችሁ በተቀመጠላችሁ የፈተና ፕሮግራም መሰረት በሰዓቱ ፈተናው ላይ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

👉 ወላጆችን ልጆችን ለፈተናው ዝግጅት እንዲያደርጉ በማድረግ በተቀመጠው የፈተና ፕሮግራም እና ሰዓት መሰረት ወደየ ትምህርት ቤታቸው በግዜ እንድትልኩ እናሳስባለን።


ማሳሰቢያ!
👉 ወርሃዊ የት/ት ቤት የተማሪ ክፍያ ያልከፈሉ ተማሪዎች ከፈተናው በፊት በአዋሽ ባንክ እስኩል ማኔጅመንት ሲስተም ብቻ እንድትከፍሉ እናሳስባለን።

  
                        አወሊያ ሙስሊም ት/ት ቤቶች

አወሊያ ቴሌግራም👇
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

02 Nov, 18:20


ቀን ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017

ማሻአላህ

👉 በዛሬው እለት በአወሊያ ቁ.1 አንደኛ አና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት(አስኮ ቅርንጫፍ) በ2016 ዓ/ል በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ላይ በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል ለተዘዋወሩ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ሽልማቱንም የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመተባበር አዘጋጅተዋል።

👉 በአመቱም የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችም የእውቅና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን

👉 በተጨማሪም ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡት ተማሪዎች የአንድ አመት ነፃ የትምህርት እድል በአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት ተሰጥቷዋቸዋል።


አወሊያ ቴሌግራም👇
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

01 Nov, 13:30


ቀን ጁምዓ ጥቅምት 22/2017

                       ማስታወቂያ
     ለአወሊያ ቁ.1 ት/ት ቤቶች ወላጆች በሙሉ!

የአወሊያ ቁ.1 ት/ት ቤቶች ዋናው ግቢ ወላጆች የፊታችን እሁድ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ል በተማሪ ወላጅ ተወካዮች(ወተመህ) እና በትምህርት ቤቱ አስተዳደር አማካኝነት የተጠራ ስብሰባ (ምክክር) ስላለ ሁሉም የአወሊያ ቁ.1 ት/ት ቤቶች ወላጆች በአወሊያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እንድትገኙ ስንል እናሳውቃለን።

አወሊያ ቴሌግራም
👉 t.me/awoliaschool5

Awolia School

23 Oct, 16:18


ቀን እሮብ ጥቅምት 13/2017 ዓ/ል

ማሻአላህ

👉 በዛሬ እለት በአወሊያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የ2016 ዓ/ል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋም (ዩኒቨርሲቲ) በቀጥታ ላለፉ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና ሰርተፊኬት ከቀድሞ የአወሊያ ተማሪዎች ማህበር (አልሙኒ) እና ከአ.ዕ.ል.ድ ተበርክቶላቸዋል።

👉 በዚሁ ስነስርዓት ላይ ለዚህ ውጤት መምጣት ከፍተኛ ድርሻ ለነበራቸው መምህራን እና ሠራተኞች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።


አወሊያ ቴሌግራም👇
👉 t.me/awoliaschool5

3,432

subscribers

2,673

photos

41

videos