COUNTRY ACADEMY @countryacademyofficial Channel on Telegram

COUNTRY ACADEMY

@countryacademyofficial


"...... where students come first ......"

COUNTRY ACADEMY (English)

Welcome to COUNTRY ACADEMY, the ultimate destination for all students seeking high-quality education and comprehensive learning resources. As the official Telegram channel for countryacademyofficial, we pride ourselves on putting students first and creating a supportive community that fosters academic excellence. Who is it? COUNTRY ACADEMY is a dedicated channel for students of all ages and backgrounds who are looking to enhance their knowledge and skills in various subjects. Whether you are a high school student preparing for college entrance exams or a professional seeking to improve your expertise, this channel is the perfect platform for you. What is it? COUNTRY ACADEMY offers a wide range of educational content, including study materials, tips and tricks for academic success, live Q&A sessions with experts, and interactive quizzes to test your knowledge. Our team of experienced educators and mentors are committed to providing valuable insights and guidance to help you achieve your academic goals. At COUNTRY ACADEMY, we believe that every student deserves access to high-quality education, regardless of their background or financial status. That's why we strive to make our resources available to everyone, free of charge. Join our channel today and be a part of a supportive community that is dedicated to helping you succeed. So, if you are ready to take your learning to the next level and connect with like-minded individuals who share your passion for education, join COUNTRY ACADEMY today. Remember, at COUNTRY ACADEMY, students always come first!

COUNTRY ACADEMY

18 Dec, 11:24


09/04/2017 ዓ.ም

የታህሳስ ወር መደበኛ ክፍያና የማጠናከሪያ ክፍያ ለምትከፍሉ ወላጆች በሙሉ

የተማሪዎች የታህሳስ ወርሃዊ እንዲሁም የማጠናከሪያ ትምህርት ክፍያ  ነገ ከታህሳስ 10/2017ዓ.ም የወሩ የመጨረሻ የክፍያ ቀን  መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

                   ት/ቤቱ

COUNTRY ACADEMY

12 Dec, 10:42


የ1ኛ ሩብ ዓመት አሸናፊ ክፈሎች ሽልማት!🎉🎉🎉🎉
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

COUNTRY ACADEMY

27 Nov, 14:16


18/03/2017 ዓ.ም

የሁለተኛ ተርም ክፍያ ለምትከፍሉ ወላጆች በሙሉ

የተማሪዎች የሁለተኛ ተርም  ክፍያ  የሚከፈልበት ወቅት ከህዳር 10/2017-ህዳር 19/2017ዓ.ም ሲሆን ነገ ማለትም ህዳር19/2017ዓ.ም የመጨረሻ የክፍያ ቀን በመሆኑ ክፍያዎን በጊዜው እንዲከፍሉ እና ላላስፈላጊ ቅጣት እንዳይዳረጉ በድጋሚ እናሳስባለን።

                   ት/ቤቱ

COUNTRY ACADEMY

19 Nov, 05:45


ማክሰኞ 10/03/2017 ዓ.ም

📌ለሩብ ዓመት (Quarter) ከፋይ ወላጆች!📢📢

የሁለተኛ (2ኛ) ሩብ ዓመት ክፍያ የሚከፈለው ከህዳር 10 እስከ ህዳር 19 ቀን ድረስ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ ወደ ባንክ ሲሄዱ የልጆን መለያ ቁጥር (ID No.) ይዘው መሄድ አይርሱ፡፡

ልዩ ማስታወሻ፡- በአቢሲንያ ባንክ ይከፈሉ የነበሩ ክፍያዎች በሙሉ በአዋሽ ባንክ የሚከፈሉ ይሆናል!

COUNTRY ACADEMY

11 Nov, 14:56


📌📌02/03/2017 ዓ.ም📍

የህዳር ወር መደበኛ ክፍያና የማጠናከሪያ ክፍያ ለምትከፍሉ ወላጆች በሙሉ 📢📢

የተማሪዎች የህዳር ወርሃዊ እንዲሁም የማጠናከሪያ ትምህርት ክፍያ የሚከፈልበት ወቅት ከህዳር 01/2017-ህዳር 10/2017ዓ.ም  መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

     ት/ቤቱ

COUNTRY ACADEMY

18 Oct, 14:17


📌08/02/2017 ዓ.ም

📍ወርሃዊና የማጠናከሪያ ክፍያ ለምትከፍሉ ወላጆች በሙሉ 📢📢

የተማሪዎች የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ እንዲሁም የማጠናከሪያ ትምህርት የሚከፈልበት ወቅት ከጥቅምት 01/2017-ጥቅምት 10/2017ዓ.ም  መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ማሳሰቢያ ፦ክፍያ ሙሉ በሙሉ እየተካሄደ ያለው በአዋሽ ባንክ ሲሆን ለመክፈል ስትጠቀሙበት የነበረ የተማሪ መለያ ቁጥር(ID Number) ያልተቀየረና አሁንም የሚያገለግላችሁ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

  ት/ቤቱ

COUNTRY ACADEMY

17 Oct, 19:13


#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia

COUNTRY ACADEMY

15 Oct, 12:05


ICT Power point Note 👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

COUNTRY ACADEMY

15 Oct, 12:04


CTE Power point Note 👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

COUNTRY ACADEMY

14 Oct, 14:00


የጥቅምት ወር የስነ-ምግባር መገለጫ መርሐችን “የግዜ አጠቃቀም” (Time Management) ሲሆን በቤት ውስጥ ከልጅዎ ጋር እንዲወያዩበት እየጠየቅን በቤት ውስጥ ጥናት እና በስራዎቻቸውም ክትትል እና ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

COUNTRY ACADEMY

14 Oct, 07:58


📌📌04/02/2017 ዓ.ም📌📌

ወርሃዊና የማጠናከሪያ ክፍያ ለምትከፍሉ ወላጆች በሙሉ 📢📢

የተማሪዎች የጥቅምት ወር የት/ቤት ወርሐዊ ክፍያ የሚከፈልበት ወቅት ከጥቅምት 01/2017-ጥቅምት 10/2017ዓ.ም መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፤ እንዲሁም የማጠናከሪያ ትምህርት ክፍያም ከዚህ ወር ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያ የምትከፍሉ ከወርሀዉ ክፍያ ጋር
📍የተርም ከፋዮች የመክፈያ ወቅት ገና በመሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርት ብቻውን የገባላችሁ ስለሆነ መክፈል ያለባችሁ መሆኑን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ ፦ክፍያ ሙሉ በሙሉ እየተካሄደ ያለው በአዋሽ ባንክ ሲሆን ለመክፈል ስትጠቀሙበት የነበረ የተማሪ መለያ ቁጥር(ID Number) ያልተቀየረና አሁንም የሚያገለግላችሁ መሆኑን እየገለፅን ባንክ ላይ ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ጉዳይ በዚህ ስልክ በመደወል የምትፈልጉትን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ 0930519156



                                    ት/ቤቱ

COUNTRY ACADEMY

10 Oct, 12:25


📌30/01/2017ዓ.ም📌

📢በአቢሲኒያ ባንክ ወርሃዊ የት/ቤት ክፍያ ለምትከፍሉ የተማሪ ወላጆች በሙሉ


አቢሲኒያ ባንክ በ2017ዓ.ም አዲስ የት/ቤት የክፍያ ሲስተም ለመጀመር በሂደት ላይ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ እክል ስለገጠመው ወርሃዊ ክፍያ(የሩብ አመት ክፍያን አይመለከትም) በአቢሲኒያ ባንክ ስትፈፅሙ የነበራችሁ ወላጆች በሙሉ የተማሪዎቹን ሙሉ ፋይል ወደ አዋሽ ባንክ ያዞርን ስለሆነ ከነገ ጥቅምት1/2017ዓ.ም ጀምሮ በአዋሽ ባንክ መክፈል ያለባችሁ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።


📌ማሳሰቢያ፦ ለመክፈል ወደባንክ በምትሄዱበት ወቅት ከዚህ ቀደም ከት/ቤቱ የተሰጣችሁ የተማሪ መለያ ቁጥር /CA/2016/__ ብሎ የሚጀምረው ኮድ/ በተጨማሪ እንደ አማራጭ ዛሬ በስልካችሁ ከአዋሽ ባንክ በደረሳችሁ በ33 የሚጀምር 10 ዲጂት የተማሪ መለያ ቁጥርን በመጠቀም መክፈል ትችላላችሁ።

ካንትሪ አካዳሚ

COUNTRY ACADEMY

26 Sep, 14:27


ካንትሪ አካዳሚ
         የየወራቱ የስነ-ምግባር መርሆች

                መስከረም
🚦ኃላፊነትን መውሰድ (Responsibility) ፡- በግላችን ለምንወስናቸው ውሳኔዎች ውጤቱ ጥሩም ይሁን መጥፎ ኃላፊነትን ለመውሰድ ፍቃደኛና ዝግጁ መሆን፡፡

               ጥቅምት
የጊዜ አጠቃቀም (Time Management)፡-
ለህይወታችን ጠቃሚ የሆኑ ማንኛውም የምንሠራቸውን ሥራዎች በግብ አስቀምጠን በተሠጠን ሰዓትና ጊዜ በእቅድ የመስራት ብቃት ነው፡፡

               ህዳር
🤝መቻቻል (Tolerance)፡- ሰዎች በሰላም አብረው እንዲኖሩ ሁሉም ተማሪዎች በማህበራዊ ግንኙነታቸው ውስጥ የተለያዬ አመለካከትን እና እምነትን ተቀብሎ የመኖር ጥበብ ነው፡፡

          ታህሳስ
🫸 ሀቀኝነት (Trustworthyness) ፡-  ውጤቱ ምንም ሆነ ምን ያለምንም አድሎአዊ አሰራር እውነትን የመናገር ብቃት እና ድፍረት ነው ፡፡

            ጥር
🧑‍🏫👨‍🏫 በራስ መተማመን (Self-Confidence)፡-
የሆነን ጉዳይ በራስ ብቃት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወን እርግጠኛ መሆን ነው፡፡

                  የካቲት
🇪🇹የሀገር ፍቅር (Patriotism)፡- ውድ ለሆነችው እና መተኪያ ለሌላት ሀገር የሚኖረው ጥልቅ ፍቅር ነው፡፡

           መጋቢት
🧑‍⚖ፍትሐዊነት (Fairness)፡-  ሌሎችን ያለምንም አድሎ በፍትሐዊነት ማገልረገል ፤ መተባበር ፤በጋራ መማር ፤ መስራት እና ማደግ፡፡

              ሚያዚያ
🔑ግልጽነት (Transparency)፡- ምስጢራዊነት በሌለበት ክፍት በሆነ ስርዓት የባለቤትነት መረጃን ሳይሆነ  እምነትን፤ተጠያቂነትን አና ትብብርን የማጎለበት ብቃት ነው፡፡

            ግንቦት
🙏አመስጋኝነት (Gratitude) ፡-  ለተሠጠንን ለሆነልን ነገር ዋጋ መስጠትና ፈጣሪን እንዲሁም ሌሎችን ማመስገን ፡፡

                 ሰኔ
ያለንን ማካፈል (Sharing) ፡- ከተሠጠን ወይም ካለን ነገር በመልካምነት ለሌሎች ማጋራት  ወይም ማካፈል ማለት ነው፡፡

ሲሆኑ  እነዚህ መርሆች በየወሩ የሚጠበቅ ግብ ተቀምጦላቸው ከተማሪዎች ጋር ውይይት የሚደረግባቸው  ፤ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንዲወያዩበት የሚጠበቅ እና ምዘና የሚሰጥባቸው ናቸው፡፡

         ካንትሪ አካዳሚ

COUNTRY ACADEMY

25 Sep, 14:56


COUNTRY ACADEMY pinned «የካንትሪ አካዳሚ ጠቃሚ ሊንኮች 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ልጅዎ የሚማርበትን ክፍል የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ !! Country Academy Important links Grade 8 (8ኛ ክፍል)👇👇👇 @countyryacademygrade8tgchannel Grade 7 (7ኛ ክፍል)👇👇👇 @countryacademygrade7tgchannel Grade 6 (6ኛ ክፍል)👇👇👇 @countryacademygrade6tgchannel…»