ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media @infraconmedia Channel on Telegram

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

@infraconmedia


Stay connected and informed with Infracon Media!
Please call 0913104323 or 0979060678 or contact https://t.me/infraconmedia

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media (Amharic)

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media ለሴትና ወንድና አስተኛኝ እና ጠበቁኝን የደረሱትን ድምፅና ማህበረሰብን ያግኙ፡፡ ለተለያዩ መረጃዎችና በዚህ እስቴት ተገኝቷል፡፡ እባኮት አድርገን ከአንዴና ከላብ ጋር የትኛዋል፡፡ እርስዎ ይህን ቻናላችንን ማስተካከል እና ለመመልከት ከእኛ ጋር አገባው፡፡ መልክም። 0979060678 ይደውሉ ወይም በhttps://t.me/infraconmedia አዝማሚው ይግቡ፡፡

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

21 Nov, 14:46


ሞሮኮ የአለማችንን ግዙፉ ስታዲየም እየገነባች ነው
▬▬
ከፖርቱጋል እና ስፔን ጋር በመሆን የ2030 አለም ዋንጫን ከሚያዘጋጁ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሞሮኮ ለውድድሩ ዝግጅቶችን እያደረገች ነው።

በ2028 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሞሮኮ የምትገነባው ይህ የአለማችን ግዙፉን ስታዲየም 115 ሺህ መቀመጫዎች አለው ተብሏል።

ሞሮኮ ለስታዲየሙ ግንባታ 490 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የምታደርግ ሲሆን፣ የ2030ን የአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉት
t.me/infraconmedia

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

21 Nov, 04:47


የኮረንቲ ኤክስፖርት

ኢትዮጵያ ለታንዛኒያ 100 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ለመሸጥ ማቀዷን ብሉምበርግ ዘግቧል። ኾኖም ድርድሩ ሲጠናቀቅ፣ ታንዛኒያ የምትገዛው ኃይል መጠኑ ሊቀየር እንደሚችል ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሃላፊዎች መስማቱን የዜና ምንጩ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ታንዛኒያ መካከል ለዚኹ ኃይል ሽያጭ የሦስትዮሽ ስምምነት ገና ያልተፈረመ ቢኾንም፣ ኬንያ ግን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ ለመኾን ከታንዛኒያ ጋር ስምምነት ተፈራርማለች።

በቴሌግራምም ተከታተሉን
t.me/infraconmedia

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

20 Nov, 01:52


ኢኮሥኮ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን እያስፋፋ ነው
📈📈📈
የኮንክሪት ጣሪያ ማምረቻ ማሽን በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል
📈📈📈
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) ከግንባታ ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች በስፋት ለማምረት እንዲያስችለው ለሀገራችን አዳዲስ የሆኑ የግንባታ ማምረቻ ማሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ ነው።

ኢኮሥኮ ከያዛቸው ዕቅዶች መካከል ሦስት የተለያዩ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማሽኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት የነበረ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ የሆሎው ኮር የተገጣጣሚ ግድግዳና ወለል ማምረቻ የፋብሪካ ማሽን አስገብቶ ተከላውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ሁለተኛው የታየር ሪሳይክሊንግ ማሽን በአራት ኮንቴይነር ተጭኖ የኮርፖሬሽኑ ኢንዱስትሪ መንደር ደርሷል።

ይህ ማሽን ያረጁ የጎማ ግብዓቶችን በመጠቀም የእግረኛ መረማመጃ፣ የልጆች መጫወቻ ንጣፍ እና የመሮጫ ትራኮችን ማምረት ያስችላል።

በቅርቡም በሦስት ሣምንታት ውስጥ የኮንክሪት ጣሪያ ማምረቻ ማሽን የሚገባ መሆኑ ታውቋል።

ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ የሚገኙት ማሽኖች ለግንባታ ግብአቶች የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ከማስቀረታቸውም ባሻገር ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና በጥራት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችሉ ናቸው።

ኢኮሥኮ በተለያዩ የግንባታ ሥራዎች በተለይም በሕንፃና ቤቶች፣ በመንገድና ድልድይ፣ በግድብና መስኖ፣ በአውሮፕላን ማረፊያ እና ሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መንግሥታዊ የልማት ተቋም ነው።

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

19 Nov, 16:23


1.9 ቢሊዮን ብር ይፈጃል

የመካነ ኢየሱስ/እስቴ - ስማዳ መንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው
▬▬▬
ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ እየገነባው ነው
🔸📈📈📈🔸📈📈📈🔸
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን'ን ከደቡብ ወሎ ዞን ጋር የሚያገናኘው የመካነ ኢየሱስ/እስቴ - ስማዳ መንገድ ግንባታ በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

50.4 ኪ/ሜ የሚሸፍነው የመንገድ ፕሮጀክቱ፣ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።

አሁን ላይ የ47 ኪሎሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ተሠርቷል። በቀሪው የፕሮጀክቱ ክፍል ማለትም ወገዳ ከተማ ላይ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውኃ ማፋሰሻ፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ። በተጨማሪም የአምስት ድልድዮች ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።

የመንገድ ግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም አሁን ላይ 90.9 በመቶ የደረሰ ሲኾን፣ ቀሪ ሥራዎችን በዚህ ዓመት ለማጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል።

በፕሮጀክቱ የከተማ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለፕሮጀክቱ መቋረጥ ምክንያት የነበረ ቢኾንም፤ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከየአካባቢው የመስተዳድር አካላት ጋር ባደረገው ጥረት ግንባታውን ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል።

ግንባታውን ዓለም አቀፉ 'ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ' እያከናወነ ይገኛል። ለግንባታው የሚውለው 1.9 ቢሊዮን ብር የሚሸፈነው በፌደራል መንግሥት ነው።

'ፕሮሚናንት ኢንጅነሪንግ ሶሉሽንስ' ግንባታውን የመቆጣጠርና የማማከር ሥራ እየሠራ ይገኛል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀድሞ ከእስቴ ወደ ስማዳ ለመጓዝ ይወስድ የነበረውን 3 ሰዓት የጉዞ ጊዜ በግማሽ ያሳጥረዋል። (ERA)

ኢንፍራኮን ሚዲያ - Infracon Media

19 Nov, 10:16


ADD | Grand Techno Fiber
📈📈📈📈📈📈📈📈📈
በሀገራችን ላለፉት 20 ዓመታት ከ87 አይነት በላይ የፋይበር ግላስ ምርቶችን በግንባር ቀደምትነት በማምረት የሚታወቀው ግራንድ ቴክኖ ፋይበር ጥራታቸው የተጠበቀ የተለያዩ የፋይበር ግላስ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን በማቅረብ ሙሉ በሙሉ የደንበኞችን ፍላጎት በማሟላት ላይ ይገኛል።

📈ግራንድ ቴክኖ ፋይበር በአሁን ወቅት ለደንበኞቹ እየሠራ ከሚገኘው ምርቶች ውስጥ በዋናነት ጠባብ ቦታ ላላቸው የመኖሪያና የንግድ ቤቶች እንደ ቦታው አቀማመጥና እንደ ደንበኛው ፍላጎት በመሬት ውስጥ የሚቀበሩ በፋይበር ግላስ የተሠሩ የውሃ ማጠራቀሚያ (ሴፕቲንክ ታንከር) እየገነባ የመፍትሔ ሥራዎችን በመተግበር ላይ ይገኛል።

📈ፋይበር ግላስ የተለያዩ ዓይነት ጫናዎችን እና ሙቀት የመቋቋም ብቃቱ ከፍተኛ ስለሆነ፣ በመሬት ውስጥ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ለመሥራት ተመራጭ ሆኗል፡፡

📈 ይህን ሥራ በኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ እና ሌሎች ጠባብ ግቢ ባላቸው ቦታዎች ላይ መሥራት ይቻላል፡፡

📈እርስዎ ቤትዎን ይገንቡ! የፋይበሩን ሥራ ለግራንድ ቴክኖ ፋይበር ይተዉት!!!

💥 ለተሟላ የፋይበር ግላስ ምርቶች ግራንድ ቴክኖ ፋይበር አለልዎት!!!

💥 ለበለጠ መረጃ 0940516393 ወይም 0948969696 ይደውሉ

💢ግራንድ ቴክኖ ፋይበር💢
▬ ለህሊናችን እንሠራለን ▬