Abbay TV @abbay_tv Channel on Telegram

Abbay TV

@abbay_tv


Abbay TV 'News & Entertainment"

Abbay TV (English)

Are you looking for a channel that covers both news and entertainment in an engaging and informative way? Look no further than Abbay TV! This Telegram channel, with the username @abbay_tv, is your one-stop destination for all the latest updates on current events, trending topics, and celebrity news. Abbay TV provides a unique blend of news and entertainment content, ensuring that you stay informed and entertained at the same time. From breaking news stories to exclusive interviews with your favorite stars, this channel has it all. Whether you're interested in politics, technology, fashion, or just looking for some light-hearted entertainment, Abbay TV has something for everyone. Who is Abbay TV? Abbay TV is a dynamic and diverse channel that caters to a wide audience of news and entertainment enthusiasts. With a team of experienced journalists and entertainment experts, Abbay TV delivers high-quality content that is both reliable and engaging. Whether you're looking for the latest news updates or want to stay updated on the world of entertainment, Abbay TV has you covered. What is Abbay TV? Abbay TV is a Telegram channel that offers a mix of news and entertainment content, making it a must-follow for anyone looking to stay informed and entertained. With a focus on delivering accurate and timely news coverage, as well as entertaining and engaging entertainment content, Abbay TV is the perfect channel for those who want to stay up-to-date on the latest happenings in the world. Don't miss out on the opportunity to join Abbay TV on Telegram and stay connected with all the news and entertainment updates you need. Follow @abbay_tv today and be part of a community that values both information and entertainment in equal measure!

Abbay TV

30 Jun, 14:08


በኢትዮ ሚዲያ አዋርድ ላይ በምርጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ እጩ ውስጥ የተካተተውን የእርስዎ ምርጫ የሆነውን የአባይ ቴሌቪዥን ጣቢያን ዛሬ ይምረጡ:: እናመሰግናለን!

https://ethio-mediaaward.com/የቲቪ-የቴሌቪዥን-ጣቢያ-እጩዎች/

Abbay TV

07 Feb, 16:21


🏆🎉 አስደሳች ዜና! የለዛ ሽልማት ለ13ኛ ጊዜ ተመልሷል፤ ለዚህ ታላቅ የጥበብ እና የጥበበኞች ልዩ የሽልማት ፕሮግራም ዓባይ ቲቪ ብቸኛ የሚዲያ አጋር መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው።

🌟 🗳 ድምጽዎ አሰጣጥ ሂደት በቅርቡ ይጀምራል የለዛ ሽልማት አሸናፊዎችን ለመወሰን የበኩሎን ለመወጣት ይዘጋጁ !

ዓባይ ቲቪ 'የኢትዮጵያ ምርጥ'

#Abbaytv #LezaAward #VoteNow #SupportTheArts #ExclusiveMediaPartner

@Abbay_Tv

Abbay TV

23 Jan, 14:44


አዲሱን እና ትክክለኛውን ዓባይ ዜና - Abbay News ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👇
https://t.me/AbbayNews ወይም @AbbayNews
ቻናላችንን በመቀላቀል ወቅታዊ፣ተዓማኒ ና ሚዛናዊ ዜናዎችን ይከታተሉ!

ዓባይ ቲቪ 'የኢትዮጵያ ምርጥ'

Abbay TV

17 Jan, 12:11


ከጥር 27 ጀምሮ የድጋሚ የዩኒቨርሲት መውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ተገለጸ ።

በ2016 አጋማሽ ላይ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን በድጋሜ ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 ቀን 2016 እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሐምሌ 2015 የመውጫ ፈተናውን ወስደው ያላለፉ እና በድጋሚ ፈተናውን ለመውሰድ ለሚጠባበቁ ተፈታኞች የፈተናው መርሐ ግብር ከጥር 27 2016 እስከ የካቲት 1 2016 ድረስ ባሉት ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገለጿል።

እንዲሁም በድጋሜ ለሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የምዝገባ መርሐ ግብሩ ከጥር 8 2016 እስከ ጥር 15 2016 500 ብር በቴሌ ብር በመክፈል ብቻ እንደሚፈጸም አመላክቷል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አክሎም ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ የሚመዘገቡ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚያካሂዱት እና ክፍያ የሚፈጽሙት በትምህርት ተቋማቸው በኩል መኾኑን ጠቁሟል።

ተፈታኞች ተጨማሪ መረጃ እና ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር ወይም በኢሜይል በኩል ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉም አስታውቋል።


@Abbay_Tv

Abbay TV

17 Jan, 08:19


በትግራይ ክልል የከፋ ሁኔታ ባለበት ወቅት የህወሓት አመራር በረዥም ስብሰባ ተጠምዷል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትችት አቀረቡ

የትግራይ ክልልን የሚመራው ህወሓት በረዥም ስብሰባ ላይ በመጠመዱ መንግስታዊ አገልግሎቶች እየተስተጎጎሉ ነው በማለትም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወቅሰዋል፡፡ ሕዳር ወር መግቢያ ላይ የተጀመረው ስብሰባ እስካሁን ያልተጠናቀቀ ሲሆን የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት፣ ነባር የፓርቲው አመራር፣ የትግራይ ወታደራዊ መሪዎች እና ሌሎች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን እስካሁን መቋጫ አላገኘም።

ስለስብሰባው ይዘት ይሁን አጀንዳ በይፋ የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን፤ 'ስትራቴጂካዊ' በተባሉ ጉዳዮች ዙርያ ምክክር እየተደረገ መሆኑ ሲገለፅ ቆይቷል። ይሁንና የዚህ አብዛኛው የትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራር እየተሳተፈበት ያለው ስብሰባ መራዘም፥ በህወሓት ውስጥ ያለ ክፍፍል ማሳያ ነው ብለው በርካቶች የሚገልፁ ሲሆን መንግስታዊ አገልግሎቶች መደናቀፍ እየገጠማቸው መሆኑን በማንሳት ተቃዋሚዎች ትችቶች ሰንረዋል፡፡

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ባይቶና ከፍተኛ አመራር አቶ ኪዳነ አመነ ግልፅነት የጎደለውና ረዥም ባሉት ሰብሰባ ምክንያት መንግስታዊ አገልግሎቶች መደናቀፋቸውን አስረድተዋል፡፡ ሌላው ፖለቲከኛ አቶ ክብሮም ተክላይ የትግራይ ህዝብ በከፋ ችግር ላይ ባለበት አመራሮቹ በግድ የለሽነት ረዥም እና መፍትሔ ይዞ በማይመጣ ስብሰባ ላይ ተጠምደዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

ቅሬታውን በተመለከተ የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊና የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባሉ አቶ ረዳኢ ሐለፎም የትግራይ አመራር ከስራ ይልቅ በስብሰባ ተጠምዷል የሚል ከተለያዩ አካላት የሚሰነዘር አስተያየት እንደማይቀበሉት መግለፃቸውን ዶቼቨለ ዘግቧል፡፡

@Abbay_Tv

Abbay TV

17 Jan, 08:12


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀሰተኛ ደብዳቤ በማዘጋጀት ሰዎችን የማታለል ተግባር ላይ ከተሰማሩ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰበ፡፡


አጭበርባሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ጭነት አገልግሎት (ካርጎ) በኩል ለተለያዩ ግለሰቦች ዕቃ እንደተላከላቸው አስመስሎ በመደወል እና ሐሰተኛ የእቃ ጭነት መለያ ቁጥር በመጠቀም የተላከውን ዕቃ ለመቀበል የሚከፈል በሚል ክፍያ በመጠየቅ እንዲሁም ስራ ፈላጊዎችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመቀጠር ለምዝገባ እና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል ገንዘብ በማስከፈል የማታለል ተግባር ላይ መሰማራታቸውንና ማሕበረሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ ማሳሰቡ ይታወቃል፡፡


በቅርቡም የካናዳ መንግስት የስራ እና የትምህርት እድል እንዳወጣ እና ተቋማችን ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሰው እንደወከለ እንዲሁም መመዝገብ ለሚፈልጉም ሁሉ ክፍያ የሚፈፅሙበት የባንክ አካውንትም አንዳሳወቀ በማስመሰል ደብዳቤ በማዘጋጀት ሰዎችን የማታለል ተግባር ላይ አጭበርባሪዎች መሰማራታቸውን ደርሰንበታል ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማህበራዊ የትስስር ገጽ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡


ስለሆነማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕቃ ለተላከላቸው ደንበኞቹ ዕቃቸው መድረሱን እና ወደ ድርጅቱ በመምጣት አስፈላጊ ሂደቶችን እንዲያስጀምሩ ከማሳወቅ ውጪ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ እንዲከፍሉ በስልክ የማይጠይቅ መሆኑን፣ ለስራ ቅጥር ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የማይጠይቅ እና ከማንኛውም አይነት ኤጀንት ጋር አብሮ የማይሰራ መሆኑን እና ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ የትኛውም ሀገር ሰዎችን የመላክ ስራ ላይ እንዳልተሰማራ ለማሳወቅ እንደሚወድ በመግለጽ ማሕበረሰቡ ይህንን ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

@Abbay_Tv

Abbay TV

17 Jan, 08:11


ሱዳን ከኢጋድ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች::

ከሃገሪቱ ብሔራዊ ጦር ሰራዊት ጋር የተሳሰረው የሱዳን መንግሥት የተፋላሚውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን አዛዥ በጉባኤው እንዲሳተፉ በመጋበዝ ‘የሃገሪቱን ሉላዊነት ጥሷል’ ሲል ከወነጀለው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት - ኢጋድ ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን አስታውቋል።

የሱዳኑ ብሔራዊ ጦር ዘጠኝ ወራት ባስቆጠረው ውጊያ ይዞታውን እያጣ በመጣበት ባሁኑ ወቅት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ጉብኝት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

የዲፕሎማሲ ተቀባይነት ከፍ ለማድረግ የታለመ ነው በተባለ እርምጃ ኢጋድ ከነገ በስቲያ ሃሙስ ኡጋንዳ ላይ በሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ዳጋሎን ጋብዟል። ዳጋሎም ግብዣውን መቀበላቸው አስታውቀዋል።

ይሁንና እርምጃው ለጦር ሰሠራዊቱ ዋና አዛዥ እና ለሃገሪቱ መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ታማኝ የሆኑት የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው ከህብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ይፋ እንዲያደርጉ ምክንያት ሆኗል።

"የሱዳንን ሉዓላዊነት በመጣስ ወደፊት ብርቱ ችግር የሚደቅን አደገኛ ድርጊት ፈጽሟል" ሲሉም ኢጋድን ወንጅለዋል።

ኢጋድ የሱዳን መንግስት ላነሳው ቅሬታና ከድርጅቱ ጋር ግንኙነቴን አቋርጫለሁ በሚል ላወጣው መግለጫ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

ኢጋድ ካሁን ቀደም ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በመሆን በተደጋጋሚ ሁለቱን ተፋላሚ የጦር ጀነራሎች ለማደራደር ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካ መቅረቱ ይታወሳል።

@Abbay_Tv

Abbay TV

16 Jan, 13:40


በመዲናዋ የእሳት አደጋዎች መበራከታቸውን ተከትሎ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአማካኝ በየቀኑ ሁለት የእሳት አደጋዎች እየተከሰቱ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ይሄንን ታሳቢ በማድረግ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

ከሰሞኑ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋዎች እየተከሰቱ መሆናቸው የኮሚሽኑ የህዝብ ግኝኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ በትናንትናው እለት ብቻ በከተማዋ ሁለት የእሳት አደጋዎች መከሰታቸውን ና በዛሬው ዕለት ከረፋዱ 5:10 በየካ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት መነሀሪያ ፊት ለፊት በመኖሪያ ቤት ተጨማሪ ክፍሎች ሰርተዉ የመኝታ ኪራይ አገልግሎት ከሚሰጡ መካከል የአንድ ግለሰብ አራት ክፍሎች በእሳት አደጋ መውደማቸውን ገልጸዋል፡፡

በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ጠቁመው በዚህ አካባቢ በ2015 ዓ.ም በተነሳ የእሳት አደጋ መኝታ ተከራይተዉ የነበሩ ሁለት ወጣቶች ህይዉታቸዉ ማለፉንም አስታውሰዋል፡፡

የአደጋዎቹ መንስኤ እና በኢኮኖሚ ላይ ያደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ንጋቱ፤ ይሄ ብቻ ሳይሆን በጥቅሉ በከተማዋ ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በየቀኑ ሁለት የእሳት አደጋዎች እየተከሰቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህም አሁን ያለው የአየር ጸባይ ሁኔታ ለእሳት አደጋ መከሰት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
መዘናጋት እና ቸልተኝነት ዋጋ ያስከፍላል ያሉት ባለሙያው፤ አሁን ያለንበት ወቅት ለእሳት መከሰት ወይም መባባስ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ስለሆነ ህብረተሰቡ ይሄንን ታሳቢ በማድረግ ከወትሮው የተለየ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

@Abbay_Tv

Abbay TV

16 Jan, 13:39


በኢትዮጵያ ሃዲያ ዞን በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛት ስርጭት መጨመሩን ኢሰመኮ ገለጸ፡፡

በሃዲያ ዞን ግርዛትን ለማስቀረት ተጀምረው የነበሩ የመከላከልና የንቅናቄ ሥራዎች መቀነስ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግርዛት ስርጭት እንዲጨምር አስተዋጾ አድርጓል ሲል (ኢሰመኮ) ገልጿል።

ኮሚሽኑ ታህሳስ 25 2016 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃዲያ ዞን በሻሸጎ፣ ሶሮና ምዕራብ ሶሮ ወረዳዎች በሴቶች ላይ በሚፈጸም ግርዛት ዙሪያ ባከናወነው ምልከታ ተጎጂዎች ለሚያጋጥማቸው የጤና እክል እየተሰጠ ያለው ድጋፍና ክትትል አጥጋቢ አለመሆን ሴቶች ከዘመናዊ ሕክምና ይልቅ ወደ ጎጂ ልማዳዊ አማራጮች እንዲያዘነብሉ ምክንያት እንደሆናቸው ኮሚሽኑ ካጋራው ጽሁፍ አባይ ቴሌቪዥን መመልከት እሏል፡፡

በዚህ ጎጂ ልማድ የሚያልፉ ሴቶች ከጤና እክል ጀምሮ እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት የሚደርስባቸው መሆኑ በክትትሉ ከተለዩ ግኝቶቹ መካከል መሆናቸውን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

የሴትን ልጅ ግርዛት በዞኑ ለማስቆም በተግዳሮትነት ከተነሱት መካከል ድርጊቱ በድብቅ መፈጸሙ፣ ማኅበረሰቡ ሴትን ልጅ የሚገርዙ ግለሰቦችን መደበቁ፣ በአካባቢው በቂና ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት አለመኖሩ የሚመለከታቸው የፍትሕና የአስፈጻሚ አካላት ተቀናጅቶ አለመሥራት እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ሲቪል ማኅበራት ትኩረት ማነስ አበይት ምክንያቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።

ኮሚሽነሩ አክለውም የሚፈጸሙ ጥቃቶች ሴቶች በማኅበረሰቡ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የመሳተፍ ዐቅማቸውን የሚገድብ መሆኑን አስረድተዋል።

ስለሆነም ባለድርሻ አካላት እንደየድርሻቸው ማኅበረሰቡን በማስተማር፣ የወንጀል ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ ለተጎጂዎች አስፈላጊውን የጤና፣ የማኅበረ ሥነ-ልቦና ድጋፎችን በማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

@Abbay_Tv

Abbay TV

16 Jan, 13:33


በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ከሚያጡ ዜጎች መካከል 86 በመቶ የሚሆኑት እግረኞች መሆናቸው ተገለጸ ።

በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ በዓመት ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን ከእነዚህ ዜጎች መካከል 86 በመቶ እግረኞች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አስታውቋል።

በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በቀን አንድ ሰው ሕይወቱን ያጣል የተባለ ሲሆን ከትራፊክ ግጭት ዋና ዋና መንስኤዎች መካከል በፍጥነት ማሽከርከር፣ የደኅንነት ቀበቶ እና የልጆች የደህንነት መቀመጫ አጠቃቀም እንዲሁም ሞተር አሽከርካሪዎች የጭንቅላት መከላከያ ቆብ አለማድረግ እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚዴቅሳ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ በዓመት ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በ2015 ዓ.ም የትራፊክ አደጋ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የሞት አደጋን መቀነሱን ገልጸው፤ በ2015 ዓ.ም 408 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው አጥተዋል:: ይህ ከ2014 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸርም ስምንት በመቶ በትራፊክ የሚደርስ የሞት አደጋ ቀንሷል ብለዋል::

በዚህም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ከትምህርት ቤቶች ጋር በጋራ እየሠራ እንደሚገኝና በተለያዩ ጊዜያቶች ተማሪዎችን በትራፊክ አገልግሎት ላይ እያሠለጠነ እንደሚገኝ ጠቅሷል።

ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከሆኑ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 400 ተማሪዎች የተግባር ሥልጠና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኩልና የንድፈ ሃሳብ ሥልጠና ደግሞ በትራፊክ ማኔጅመንት ባለሙያዎች በኩል አሠልጥኖ በትናንትናው እለት ማስመረቁን ገልጸዋል::

@Abbay_Tv

Abbay TV

16 Jan, 13:32


ዩክሬን የሩስያን ኤ-50 የስለላ አውሮፕላን መታ መጣሏን አስታወቀች::

የዩክሬን የጦር ኃይል አዛዥ ጄኔራል ቫለሪይ ዛሉዥኒ እንዳሉት የአየር ኃይሉ ኤ-50 የተሰኘ በረዥም ርቀት ራዳር የሚቃኝ አውሮፕላን እና አይኤል-22 የተሰኘ የቁጥጥር ማዕከል አውሮፕላንን "አውድመዋል።"

ኤ-50 የተሰኘው ስለላ አውሮፕላን የአየር መከላከያዎችን በመለየት የሩስያ ጄቶች ዒላማዎችን እንዲያጠቁ ያመቻቻል ተብሏል።

የሩስያ ባለስልጣናት ስለ ጥቃቱ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ቢናገሩም ታዋቂ የሆኑ እና ጦርነቱን የሚደግፉ የሩሲያ ተንታኞች የኤ-50 አውሮፕላን መመታት ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚሆን ተናግረዋል ።

የዩክሬን አየር ኃይል ቃል አቀባይ ዩሪ ኢህናት እንዳሉት አይኤል-22 አውሮፕላን ከጥቅም ውጭ እስኪሆን ድረስ ወድሟል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወጣና የአይኤል-22 ነው ተባለ ምስል በጅራቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት አሳይቷል።

ኤ-50ን "ቁልፍ ትዕዛዝ የሚሰጥ፣ ቁጥጥር እና ክትትል የሚያደርግ" ከመሆን ባለፈ ለሩሲያ አውሮፕላኖች እና ለሚሳኤል ስርዓቶች "የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ስለ ዩክሬን አነስተኛ አውሮፕላኖች ኢላማ መረጃዎችን የሚሰጥ" ነው ተብሏል።

@Abbay_Tv

Abbay TV

16 Jan, 13:30


62 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማላዊ መያዛቸው ተገለጸ::

የማላዊ ፖሊስ 62 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በጭነት መኪና ሲጓዙ በራምፊ መያዛቸውን አስታውቋል።

ስደተኞቹን በጭነት መኪና ይዞ ሲጓዝ የነበረው ሹፌር ተሽከርካሪውን እና ስደተኞቹን ትቶ መሄዱ ሲገለፅ የጭነት መኪናው ሲፈተሽ ምንም አይነት የጉዞ ሰነድ የሌላቸው 62 ኢትዮጵያውያን መያዛቸው ተገልጿል።

ስደተኞቹ በአሁኑ ወቅት በራምፊ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ተያያዥ ወንጀሎች ምን ያህል ተሳትፎ እንዳላቸው ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ሌሎች መዳረሻዎች ሲጓዙ የሚያዙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በተደጋጋሚ ይነገራል።

@Abbay_Tv

Abbay TV

14 Jan, 06:26


#ዜና_ዕረፍት

አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋዉ መሸሻ ከዚህ አለም በሞት ተለየ‼️

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ እና መሪ የነበረዉ ጋዜጠኛ አስፋዉ መሸሻ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ በዛሬው እለት ተሰምቷል።

ጋዜጠኛዉ ለወራት በህመም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ህክምናዉንም በአሜሪካ ሲከታተል እንደነበር ይታወሳል።

ዓባይ ቲቪ በጋዜጠኛዉ ህልፈት የተሰማዉን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

@Abbay_Tv

Abbay TV

13 Jan, 18:02


ሰከላ በዚህ ሳምንት ክ አንጋፋው አርቲስት ዘላለም ይታገሱ ጋር!
በዓባይ አገልግል እሁድ ከምሽቱ 1፡00 ጀምሮ
ቆይታችሁ ከዓባይ ቴሌቪዥን ጋር ይሁን !!

Follow us on:
YouTube: https://bit.ly/abbay_tv
Tik-Tok: https://bit.ly/Abbaytv
Instagram: https://bit.ly/abbayTv
Telegram: https://t.me/Abbay_Tv

ዓባይ ቲቪ 'የኢትዮጵያ ምርጥ'

#ዓባይቲቪ #AbbayTv #Sekela #Thisweek

@Abbay_Tv

Abbay TV

13 Jan, 17:31


ቲክቶከሮቹ በማን ይቀነስ
በዓባይ አገልግል እሁድ ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ
ቆይታችሁ ከዓባይ ቴሌቪዥን ጋር ይሁን !!

Follow us on:
YouTube: https://bit.ly/abbay_tv
Tik-Tok: https://bit.ly/Abbaytv
Instagram: https://bit.ly/abbayTv
Telegram: https://t.me/Abbay_Tv

ዓባይ ቲቪ 'የኢትዮጵያ ምርጥ'

#ዓባይቲቪ #AbbayTv #Manyikenes #Thisweek

@Abbay_Tv

Abbay TV

13 Jan, 17:15


Friday 90's በጉራማይሌ
በዓባይ አገልግል ከ11፡00 ጀምሮ
ቆይታችሁ ከዓባይ ቴሌቪዥን ጋር ይሁን !!

Follow us on:
YouTube: https://bit.ly/abbay_tv
Tik-Tok: https://bit.ly/Abbaytv
Instagram: https://bit.ly/abbayTv
Telegram: https://t.me/Abbay_Tv

ዓባይ ቲቪ 'የኢትዮጵያ ምርጥ'

#ዓባይቲቪ #AbbayTv #Guramayle #Thisweek

@Abbay_Tv

Abbay TV

13 Jan, 16:45


ስለ መሰንቆ ህዝቡ ምን አለ?
በ ዓባይ አገልግል እሁድ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ
ቆይታችሁ ከዓባይ ቴሌቪዥን ጋር ይሁን !!

Follow us on:
YouTube: https://bit.ly/abbay_tv
Tik-Tok: https://bit.ly/Abbaytv
Instagram: https://bit.ly/abbayTv
Telegram: https://t.me/Abbay_Tv

ዓባይ ቲቪ 'የኢትዮጵያ ምርጥ'

#ዓባይቲቪ #AbbayTv #mesenko #Thisweek

@Abbay_Tv