ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጥር 15/2017 ዓ.ም . ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ/ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በሁሉም ዘርፍ ያከናወኗቸውን ተግባራት ማለትም የመማር ማስተማር የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ߹አስተዳደርና ልማት እንዲሁም በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀረቧል።
በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት፣ ም/ፕሬዝዳንቶች፣ የጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች ፣ዲኖች የት/ት ክፍል ሀላፊዎች߹ ስራ አስፈጻሚዎች፣ ቡድን መሪዎች እና አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።
የሩብ ዓመቱ ሪፖርት በዩንቨርሲቲው የስትራተጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በአቶ ልደቱ ግዛው የቀረበ ሲሆን በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ተዳሰዋል ። በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የአንደኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት የተሰጠውን መደማደሚያ መሰረት በማድረገግ ዘርፎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ ምን ያህል እንደተወጡ የጠየቁ ሲሆን የየዘርፉ ሀላፊዎችም በሰራቸው የሚገኙ የስራ ክፍሎችን ሪፖርት ከመገምገማቸውም ባሻገር የመስክ ምልከታ በማደረግ ያገኙትን ጠንካራና ደካማ ጎን ለካውንስሉ አቅርበዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱም የቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ የተሰጡ መደማደምያዎች ተግባራዊ መደረግ በመቻላቸው መደሰታቸውን እና በቀጣይም ይህንን አጠናክሮ መሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ከተሳታፊዎች በተሰጠ አስተያየት ደግሞ የሪፖርት አቀራረቡ እያደገ መምጣቱን ገልጸው ነገር ግን ተሰርተው በሪፖርቱ ያልተካተቱ ተግባራት ተለቅመው መካተት እንዳለባቸው አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች በስፋት ተንስተዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ በቀጣይ ሁሉም ሪፖርቶች ተጨፍልቀው መቅረብ እንደሌለባቸውና ዘርፎች በቁልፍ ተግባር አመልካች /KPI/ መሰረት የየራሳቸውን ሪፖርት ለካውንስሉ ማቅረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ከሀገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት ጋር የፈጸማቸውን የመግባቢያ ስምምነቶች መምህራንና ሌሎች የሚመለከታቸው ተመራማሪዎች ለራሳቸውም ለተቋሙም አቅም መፍጠርና የዩንቨርሲቲውን ከፍታ ለማጎልበት የተፈጠሩ ዕድሎችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ በሰጡት ማደማደሚያ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦችን ያነሱ ሲሆን እነዚህም የመውጫ ፈተናን፣ የምርምር ስራዎች የማህበረሰቡን ህይወት መቀየር አስፈላጊነት ፣ ሀገር በቀል የዶሮ ዝርያ ማሻሻያ ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ተማሪዎችን ማገዝ ለአረጋዊያን ድጋፍ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ያሳሰቡ ሲሆን የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነቶች በትኩረት ሊሰራባቸው ይገባል በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በጋራ እንችላለን!!