ሳሚኝና ልንቃ
ነግረውሽ እንደሆን…
መጎዳቴን አይተው ህመሜን በዝርዝር
ጤናዬን እንዳጣው ለክፎኝ ያንቺ ፍቅር
የመኖር አኳኋን ውሉ ተዛብቶብኝ
ቀንና ለሊቱ እንደተምታታብኝ
ሰምተሽ እንደሆነ…
አንቺን ካየሁ ወዲህ ሰላም እንደራቀኝ
ፍቅርሽ ውስጤ ገብቶ እንደሚያስጨንቀኝ
ውበትሽ በልቤ ደምቆ እንደተሳለ
የኔ አካል በሀሳብ ካንቺጋ እንደዋለ
ሰምተሽ እንደሆነ…
ብቻ መዋተቴን
እራሴን ማጣቴን
ውሎ አዳር መተከዝ
አለፍ ሲል መፍዘዝ
ለብቻ መፈገግ
ዝም ብሎ መበርገግ
ሆኗልና ግብሬ ሰርክ የማይቀየር
መጥተሽ አንድ በዪኝ ተይ ነገሩ ሳይከር
ባንቺ እንደታመምኩኝ ባንቺው ልዳን በቃ
በውብ ከንፈሮችሽ ሳሚኝና ልንቃ 💋
https://t.me/Binayeeeee
Join our channel
@LovestoryB_Wiz_H
@LovestoryB_Wiz_H