Golden Age @goldenage2013 Channel on Telegram

Golden Age

@goldenage2013


Explore our channel for inspiring and motivating content, including speeches, videos, photos, and written pieces. Discover book reviews, future plans of rFIR, and join us on a journey of growth.
Youtube channel https://www.youtube.com/@GoldenAgerfir

Golden Age (English)

Welcome to the Golden Age Telegram channel! If you are seeking inspiration and motivation, look no further. Our channel, @goldenage2013, is dedicated to providing you with a wide range of content that will uplift your spirits and fuel your passion for personal growth. From powerful speeches to thought-provoking videos, captivating photos, and insightful written pieces, we have it all.

But that's not all - we also offer book reviews to help you discover your next favorite read, and share the exciting future plans of rFIR, our organization dedicated to fostering personal growth and development in individuals. By joining us on this journey, you will not only be entertained and inspired, but you will also be part of a community that values growth and self-improvement.

Don't miss out on this opportunity to be a part of the Golden Age movement. Join us today and start your journey towards a better and brighter future. And if you're looking for even more content, be sure to check out our Youtube channel at https://www.youtube.com/@GoldenAgerfir. See you there!

Golden Age

01 Nov, 19:14


❤️‍🩹ወንዶች❤️‍🩹

ተርበው እንደበሉት እህል የጣፈጠች ፣ ተጠምተው እንደጠጡት ውሀ የምታረካ የህይወት ምንጭ የሆነች ሚስት አላህ ይስጣቹህ።

❤️ሴቶች❤️

የአይንሽን ቀለም አይቶ ምኞትሽን የሚያውቅ ፣ ከጌታው ምንዳን ከጅሎ አንቺን ለማስደስት የሚጥር ፥ አንቺን የማፍቀር ፀጋ የተሰጠውን ባል ከሪሙ ይለገስሽ።

💫 ላላገቡት እስኪ ላኩላቸው☺️💫



https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

27 Sep, 17:51


ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ እንደበቁ ያስባሉ!
(በ2003 - 2004 ተጽፎ ካልታተመ ጥናታዊ ጽሁፍ የተወሰኑ ማሻሻያዎች ጋር የቀረበ)

📌 ከፍል 2

ሙስሊሙ በጥቂት ነገር ተደስቶ ራሱን ያፅናናል። ጥቂት በመስራት ብዙ ይኮፈሳል። ሌሎች ችግሮችን ቸል ይላል። በከተማ አካባቢ የሚስተዋሉ ዲናዊ እንቅስቃሴዎች እያየ ሃገሪቱን በሞላ በዚያ መልኩ ይመለከታል ምን ያህል በቂ ሥራ እየሰራን ነው? የገጠር አካባቢ ሙስሊሞች ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ናቸው? ምን ያህል ሙስሊም በሚበዛበት አካባቢ በክርስቲያን ሚሽነሪዎች ምን እየተሰራ ነው?

በማህበራዊ፣ በልማት፣ በጤና እና በትምህርት ስም እኛ ራሳችንን ዘንግተን ሙስሊሙ ላይ እየተካሄደ ስላለው የማክፈር ዘመቻ ምን አደረግን? እኛ ስስታም ሆነን የሙስሊሙን እምነት ለማስለወጥ ምን ያህል ገንዘብ እየወጣ ነው? በዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ።

"የዓለም ዓቀፍ ክርስቲያናዊ ድርጅቶች ህብረት" የሚባለውና ከአንድ ሺህ አራት መቶ (1400) በላይ አባል ድርጅቶችን ያቀፈው የሚሲዮናውያን ድርጅቶች ህብረት በማህበራዊ፣ በልማት፣ በጤና እና በትምህርት ሰበብ በገጠር አካባቢ የሚገኙ ሙስሊሞችን ለማክፈር ትልቅ ዘመቻ ይዟል። ከ1996–2000 (ከአስራ ዘጠኝ ዘጠና ስድስት እስከ ሁለት ሺህ) ዓመት ብቻ 1000,000,000 (አንድ ቢሊዮን) ዶላር ገንዘብ ወደ ሀገር አስገብቷል ።ስንት ሙስሊሞች ከፍረው ይሆን? እኛ የትነን? በካሊፎርኒያ–አሜሪካ መሠረቱን ያደረገው ሳሊቬሽን ጌት ሚኒስትሪ (Salvation Gate Ministry) የሚባለው ድርጅት "የኢስላም እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ (The movement of Islam in Ethiopia)" በሚል በድህረ– ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ በኢትዮጵያ ባለፋት አስርት አመታት ብቻ 20,000 (ሃያ ሺህ) ሙስሊሞችን ወደ ወንጌላዊ ክርስትና ማስገባት እንደተቻለ ይገልጻል። ይህ ሲሆን የኛ ሚና ምን መሆን ነበረበት? መች ይህ ብቻ ሆነና? በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት ያረጋል አይሸሹም በቀረበው ጥሪ "Ethiopian Call" የተሰኘው ዘመቻ በመስከረም 2003 መጀመሩ ይፋ ሆኖ ነበር። የዘመቻውም እቅድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብቻ 1,000(አንድ ሺህ) አብያተ ክርስቲያናት ለማሰራት ነበር። ጥሪው የቀረበለትና በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው "ብለየር ፋውንዴሽን" የተባለው የኘሮቴስታንት ሚስዮናዊ ድርጅት ዓለም አቀፍ ዘመቻ አድርጓል።

በ2005 www.christianpost.com የሚባለው ድህረ ገጽ "ብለየር ፋውንዴሽን በመላ ኢትዮጵያ 800 (ስምንት መቶ) አብያተክርስቲያናትን እያስገነባ እንደሆነ የዳግም ተወለድ ክርስቲያን አባልና የክልሉ ፕሬዝዳንት የሆነው ያረጋል አይሸሹም ሰማ። ፕሬዝዳንት ያረጋል የክርስቶስ ቃል 1000 (አንድ ሺህ) አዳዲስ በሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናት አማካኝነት ወደ ክልሉ እንዲያመጣ ብለየር ፋውንዴሽንን ጋበዘ። ዶ/ር ብለየር በዓለም ላይ የሚገኙትን ወዳጆቻቸውን በጸሎትና በእምነት እንዲሳተፉ ጥሪ አደረጉ ምላሹም አመርቂ ነበር። ብለየር ፋውንዴሽን አሁን በክልሉ 1311 (አንድ ሺህ ሶስት መቶ አስራ አንድ) አዳዲስ አብያተክርስቲያናትን መገንባት ችሏል። የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ያስፋፋሉ።" ሲል ጽፎ ነበር።

ሌላው የክርስቲያን ድህረ–ገጸረ የሆነው www.christiantoday.com በበኩሉ "Since April 2005, deployed Missionaries have reported 24,863 new converts and 446 of the 1,000 church buildings completed or under construction" ማለትም "ከሚያዝያ 2005 ጀምሮ የተሰማሩት ሚሲዮናውያን ሪፖርት እንዳደረጉት 24863 (ሃያ አራት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሶስት) አዲስ እምነቱን (ክርስትናን) የተቀበሉ (ሰዎች) እንዳሉና ከ1000 (አንድ ሺህ ከሚሰሩት) ውስጥ 446 (አራት መቶ አርባ ስድስት) አብያተክርስቲያናትን ሕንጻዎች ግንባታ አልቋል። አልያም በመስራት ላይ ናቸው።" ሲል ጽፎ ነበር።

...
https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

27 Sep, 17:50


ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ እንደበቁ ያስባሉ!

📌 ከፍል 1


እያንዳንዱ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ ያለፈ ታሪኩን በጥሞና ቢፈትሽ ስለመብቱ መጣስ ስለህልውናው መገፋት ከትምህርት ስለመራቁ መደራጀት ስለመነፈጉ ወዘተ በርካታ አሳዛኝና የሚቆጩ እውነታዎች ላይ ሊደርስ ይችላል። ያ ታሪክ ሆኗል። ዛሬ የምንሰራው በታሪክነት ለነገው ትውልድ ይተላለፋል። የነገው ትውልድ ካለንበት ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ምን እንደሰራን ይገመግመናል። ከዚያ የከፋው በአላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ዘንድ ከጥያቄ አለመራቃችን ነው። ይህ ከመሆኑ በፊት ካለፈው ጭቆና አንጻር ምን ያህል ሙስሊሙ ለተሻለ ሁኔታስ እየሰራ ነውን? በንቃትና በትጋት ራሱን እየገመገመ ነው። ሲበዛ የትናንቱን ችግሮች ማውራት በራሱ ጠቃሚ ጎን ቢኖረውም ያ ትምህርት ሆኖን ዛሬን ካልሰራን ጎጂ ይሆናል።

እንደ ሙስሊምነታችን እንዳለን ተጨባጭ ሁኔታ እና በሕገ መንግስቱ ስለተረጋገጠው መብታችን እንዲሁም ለምናልመው ነገ ዛሬን በብልሃት ለመጠቀም ቆርጠን ካልተነሳን የኛ ሁኔታ አስጊ ይሆናል። ለተሻለ ነገ አምርረን የምንታገልበት ወቅት ዛሬ ነው። የኢኮኖሚው፣ የፖለቲካው፣ የማህበራዊው ጥረታችን አልሰምር አልረጋ ብሎ በችግርና ግራ በመጋባት የሚያንከላውሰን አንሶ "አልሰማሁም አላየሁም" እያልን ያለንበትን ተጨባጭ ሁኔታ ውል ብሎ እንዳይታየን በራሳችን ላይ ደንቃራ ሆነናል። ሙስሊሙ እንዲህ ራሱን ጥሎ ስናይ ያልሻረው ቁስላችንን ይቀሰቅስብናል።

የትናንቱ "የእስላም አገሩ መካ የቁራ አገሩ ዋርካ" ጅላጅል ተረትን እያስታወስን ከዚያ አንፃር በተግባር የት ነን? ዛሬን "አለን" እያልን እናሳልፍን። ነገ ግን ህልውናችን ራሱ ሊያልፍ ይችላል። "ከሌላው ተሽለናል" የሚለውን የዋህ ቅኔ በራሳችን ላይ ባንዘርፍ መልካም አይሆንም ትላላችሁ? ዛሬ ደግሞ ምነው? ትሉኝ ይሆናል። በሉ መብታችሁ። ይህን ሁሉ ሀተታ ለምን እንዳበዛሁ ጽሑፋን በጥንቃቄና በጥሞና ሲያነቡ ይረዱኛል። በአላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ፈቃድ ያለንበትን ተጨባጭ ሁኔታ በጥቂቱ ሌሎች ከደረሱበት አንጻር ላስነብባችሁ ጀምሬያለሁ።

...
https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

10 Sep, 15:07


ይህ ዘግናኝ ቪድዮ በሁሉም ቦታ ይሰራጭ። ሁላችሁም በምታገኙት ግሩፕና ገፅ ሁሉ አሰራጩት። ኒቃቢስቲቷ እህታችን ፍትሕ ሳታገኝ፣ አረመኔው ፖሊስ የሚገባውን ቅጣት ሳይቀምስ ዝም አንልም።

||
t.me/MuradTadesse

Golden Age

10 Sep, 08:14


➨ 12ተኛ ክፍሎች ውጤት እንዴት ነበር ?

በመጀመሪያ ለዲግሪ ያለፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ፣ ለሬሚዲያል ያለፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንዲሁም ነጥብ ላልመጣላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ።

ህይወት የራሷ መንገድ አላት ሁላችንም የተፃፈልን ነው የምንኖረው አውቃለሁ ነጥብ ሳይመጣ ሲቀር አንተም ቤተሰብህም ልታዝን ትችላለህ ነገርግን በትምህርት ብቻ አይኖርም ፤ ይህን ማወቅ አለባችሁ ፤ በተለይም በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ ዕድሎች አሉ ወጣት ሆናችሁ ራሳችሁን የምትለውጡበት ስለዚህ እነሱን ነገሮች ተረጋግታችሁ በማሰብ አዲስ ሰው የምትሆኑበትን መንገድ መፈለግ አለባችሁ ። እንጂ ውጤት አልመጣልኝም ብሎ ማልቀስ ፣ ተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ በጭራሽ እንዳትገቡ ተጠንቀቁ ።

ዩኒቨርስቲ መግባት የስኬት መጨረሻ አይደለም ፤ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ መውጣትም ትልቅ ስኬት አይደለም ፤ ስለዚህ ውጤት የመጣላችሁም ያልመጣላችሁም ተማሪዎች አሁን የህይወታችሁን ትልቁ ውሳኔ የምትወስኑበት ጊዜ ላይ ደርሳችኋል። ምክንያቱም 4,5,6,7 አመታችሁን በትምህርት ማሳለፍ ወይም ደሞ ሌሎች ነገሮች ላይ መስራት ? እሱ የእናንተ ምርጫ ነው።

➨ አስተውሉ ፦

ትምህርት አስፈላጊ አይደለም አላልኩም ፤ ትምህርት ወሳኝነት አለው ፤ ለሀገራችን እድገት የተማረ ሀይል ያስፈልጋል ግን ደሞ ትምህርት ባይሳካም ሌሎች መንገዶች አለላችሁ እሱን መመልከት እና ራሳችሁን ማሻሻል ትችላላችሁ ፤ እንጂ በጭራሽ ተስፋ መቁረጥ ፣ ማዘን ፣ ማልቀስ እና ሌሎች ኔጌቲቭ ስሜት ውስጥ አትግቡ ።

ዋናው አስተሳሰባችሁን ጠንካራ አድርጉ ሌላውን ፈተና ማለፍ ቀላል ነው።

ተግባባን ጀግኖች ! 🔥👍

#ቻናሉን_ለወዳጆቻችሁ_ሼር_በማድረግ_እንዲቀላቀሉ_አድርጓቸው።


https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

07 Sep, 17:59


Jiraattota Magaala Shashemene Gand 05 jirattan hundaaf carraan akkanaa Kuni akka isin hin dabarre!

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

26 Aug, 05:42


" Subscribe, Like, Follow, Share,Join ....Nuuf Godhaa" n tun Sadaqaa Naa buusaa Zamana kanaati" Kadhaan Shariaa keesaatti Jibbamtuudha.
🌿شيخنا أبو صيام بن محمد البدّنّي الهرري " في درس الكافي في البلاغة "

Golden Age

24 Jul, 19:38


የኢትዮጵያ መንግስት ከተባበሩት አረብ ኢምሬት ጋር በመተባበር በቀጣይ 3 አመታት 5ሚሊየን ፕሮግራመሮችን ለማፍራት እቅድ ይዘዋል ::

ይህ ስልጠና ሲጠናቀቅ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት ያገኛሉ::ትምህርቱ የሚሰጠው በኦን ላይን ሲሆን ከርሰዎ የሚሰፈልገው ሞባይል ወይ ላበቶፕ እና ኢንተርኔት ብቻ ነው ::ትምህርቱን በኢንተርኔት ከቤተዎ ሁነው ይማራሉ::

የሚሰጡ ትምህርቶች:-
1.ዌብ ፕሮግራሚንግ
2.ሞባይል ፕሮግራሚንግ
3.ዳታ ሳይንስ
4.AI

ትምህርቱ እድሜ ፆታ አይገድበውም:: ከገጠር እሰከ ከተማ ያሉ ከልጆች እሰከ አዛውንቶች በዚህ እድል መሳተፎ አለባቸው::ምንም አይነት የትምህርት ደረጃ አይጠይቅም :: በማንኛውም ዘርፍ ላይ ብትሆኑ መማር ትችላላችሁ:: በተለይም ወላጆች ሀገራችን ላገኜችው ለዚህ ከፍተኛ እድል ልጆቻችሁን  አሰመዝግቡ ::

የቀበሌና የወረዳ መጅሊሶች፣ የክልል እሰልምና ጉዳዮች፣ የመስጅድ ኢማሞቾ  ሙስሊሙ ማህበረሰብ በንቃት እንዲሳተፍ ቅሰቀሳ ማድረግ አለባችሁ::

ይህን ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት በንቃት መሳተፍ የወደፊቱን የሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ሰለሚኖረው በንቃት እንሳተፍ

ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ:-

https://ethiocoders.et/

Golden Age

19 Jul, 07:04


Paakistaanitti maqaan “Muhammad” akka moggaasa kabajaati fudhatama. Akka nuti “jaal” jannu kana jechuudha, kun aadaa gaarii isaan qabani. Moggaasa kana ammoo dhiiroota 40% oltu qaba. Paakistaanoota wajjiin hojjannu hedduu moggaasni “Muhammad” kannameefii jira. Fakkeenyaaf Kaashif, Faatih, Amiin, Ajmal, Ashraf.. wajjiin hojjataa yoo jiraatte, maqaa kana dura moggaasa Muhammadiitu jiraa beeki. Yoo moggaasa kanaa waliin isaan yaamte itti gammadan.
Muhammad-Kaashif
Muhammad-Faatih
Muhammad-Amiin
Muhammad-Ajmal
Muhammad-Ashraf..

Nagayaafi Rahmanni ergamaa Rabbii Muhammad irratti haa jiraatu.
JirraYaaErgamaaRabbii

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

18 Jul, 07:24


#እስላማዊ 💕    #እውነታዎች 📚

🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
#ጠቅላላ_ዕውቀት ፩ 💞

📝ሚና ከተማ በምስራቃዊ አቅጣጫ ከመካ በ3 ማይሎች ርቀት ላይ የምትገኝ በረሃማ ቦታ ሲትሆን ከሐጅ ስርዓቶች አብዛኛዉ የሚከናወነዉ እዛዉ በረሃማ ቦታ ላይ ነዉ፡፡

📝የመጀመሪያው ኃጢአት (ወንጀል) ኩራት ነው፡፡ እሱም በሰይጣን (ኢብሊስ) ነው የተፈጸመዉ፡፡

📝በፍርድ ቀን የሚጠየቀዉ የመጀመሪያው ጥያቄ ስለ ‹‹ሰላት›› ነዉ፡፡

📝አንዲት ሴት ባለቤቷ ከሞት በኋላ ትዳር ለመመስረት 4 ወራት ከ10 ቀናት መጠበቅ ይኖርባታል፡፡ ከዛ ቡኋላ አዲስ ትዳር መመስረት ትችላለች፡፡

📝ሰዎች በጀነት ውስጥ ምን እንደሚመስሉና ምን እንዳለ ቢያዩ ኑሮ በዚህ ጊዜያዊ ዓለም ውስጥ በምንም ነገር አይደሰቱም ነበር፡፡

📝ከሁሉም የጀነት ዝቅተኛ ደረጃ ዉስጥ የገባ ሰዉ ለብቻዉ አሥር አሥር ሺህ አገልጋዮች ይኖሩታል፡፡

📝አንድ የጀነት ነዋሪ የሆነ ሰው ወደዚህ ዓለም የእጅ አምባሩን አድርጎ ቢመጣ ልክ የፀሐይ ብርሃን ስትወጣ የጨረቃ ብርሃንን እንደሚሸፍነዉ ሁሉ የዚህ የጀነት ሰዉ የእጅ አምባር ደግሞ የፀሐይን ብርሃንን ያጠፋዋል፡፡

📝አሊይ (ረሂመሁሏህ) በኢስላም የመጀመሪያው እስር ቤትን የገነቡ ሰው ናቸው፡፡

📝ዑመር (ረሂመሁሏህ) በኢስላም የመጀመሪያው የሂጅራ ካሌንደር የፃፉ ናቸው፡፡

📝አብዱሏህ ኢብን ዙቤር (ረሂመሁሏህ) የመጀመሪያው በመዲና የተወለደ ሙስሊም ልጅ ነበር፡፡


https://t.me/true1way

Golden Age

14 Jul, 18:43


#Sooma_Aashuraa.

#Keeyrii_tana_itti_haa_hirmaannuu
Share waliif godhaa Wal yaadachiisaa

👉Ergamaan rabbii (ﷺ) akkana jedhan፦
﴿فَإِذَا كَانَ الْعَامُ الْمُقْبِلُ - إِنْ شَاءَ اللَّهُ - صُمْنَا الْيَوْمَ التَّاسِعَ﴾
" Yoo waggaa dhufu naan gahe fedha rabbiitiin Guyyaa saglaaffaallee ni sooma "
Muslimtuu gabaase

👉Ergamaan rabbii (ﷺ)፦ Hadiisa biraa keessatti akkana jedhan
﴿صيامُ يومِ عاشوراءَ، إنِّي أحتَسِبُ على اللَّهِ أن يُكَفِّرَ السَّنةَ الَّتي قبلَهُ﴾
" Soomni Guyyaa Aashuuraa soomuun dilii waggaa tokko irra namaaf dabruu rabbiin irratti herreega"
Muslimtuu gabaase

Guyyaa bori wiiyxataa (9) fii Kibxata (10) soomuun ajrii guddoo tana haa saamannuu.


https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

14 Jul, 18:42


🌴ዐሹራን መፆም ተወዳጅ ነው

▪️ የዐሹራ ቀን
ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- (የዐሹራን ቀን ፆም መፆም አላህ ያለፈውን አመት(ወንጀል) እንደሚያስምር ተስፋ አደርጋለሁ)።
ሙስሊም ዘግበውታል

የዐሹራ ፆምን ከሱ በፊት ያለውን ቀን አብሮ መፆም ይመከራል ፣ እሱም ከሙሐረም ወር ዘጠነኛው ቀን ነው። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- (አላህ እስከ ቀጣይ አመት ድረስ ካቆየኝ ዘጠነኛውን ቀን እፆማለሁ)።

ሙስሊም ዘግበውታል።

🎈አሹራ
https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

14 Jul, 18:40


🍃 ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ በሐዲስ አል ቁድስ እንዲህ ብሏል፡-
"ባሪያዬም የእኔን ውዴታ እስኪያገኝ ድረስ በፈቃደኝነት(ሱና የሆኑ) አምልኮዎችን በመስራት ወደ እኔ መቅረብን ይቀጥላል።"

💫 የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-
"ሰኞ እና ሀሙስ ስራዎች አላህ ዘንድ ይቀርባሉ፤ እኔም በፆም ላይ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እሻለሁ።"

🍃 ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
" ከረመዳን በኋላ በላጩ ወር የሙሐረም ወር ነው።"
#ሸህሩላሂል ሙሐረም

#1446 ዓ/ሂ
https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

08 Jul, 04:22


ከኢብኑል ቀይም ድንቅ አባባሎች

📋المفاتيح🔑🔑

📋 ቁልፎች 🔑🔑

🔰وقد جعل الله سبحانه لكل مطلوبا مفتاحاً يفتح به

🔰አላህ ለሁሉም ተፈላጊ ነገሮች ሁሉ መክፈቻ ቁልፍ አድርጎለታል~

فجعل مفتاح الصلاة : الطهـــور
የሶላት ቁልፍ = ንጽህና
ومفــتـــاح الحـــج : الإحـــــرام
የሐጅ ቁልፍ = ኢሕራም
ومفــتــــاح البــر : الصــــدق
የመልካም ነገር ቁልፍ = እውነተኝነት
ومفتاح الجـنـــة :  التوحيـــد
የጀነት ቁልፍ= ተውሒድ
ومفتـــاح العلم : حسـن الســــؤال
የእውቀት ማግኛ ቁልፍ = መልካም ጥያቄ
ومفتــــاح النصــر : الظفر والصبــر
የድል ቁልፍ = ትእግስት
ومفتــــاح المزيـــد : الشــكـــر
የጭማሬ ማግኛ ቁልፍ = ምስጋና
ومفتــــاح الولاية : المحبـة والذكــر
የጥበቃን ማግኛ ቁልፍ = ውዴታና ማስታወስ
ومفتــــاح الفــلاح : الـتــقــــوى
የነጻ መውጫ ቁልፍ = ተቅዋ ( አላህን መፍራት)
ومفتــــاح التوفيق : الرغبــة والرهبــة
የስኬት ቁልፍ = ክጃሎትና ፍርሀት
ومفتاح الإجابة : الدعــــاء
የምላሽ ቁልፍ = ተማጽኖ (ዱዓእ)
ومفتـــاح حياة القلب : تدبر القرآن والتضرع بالأسحار
የልብ ህይወት ቁልፍ = ቁርአንን በማስተንተን ማንበብ እና በሰሑር (ንጋት አካባቢ) ለአላህ መተናነስ

ومفتـــاح الرزق : السعي مع الاستغفار والتقوى
የሲሳይ ቁልፍ = አላህን ማርታ መጠየቅ (ኢስቲግፋር) እና አላህን መፍራት ከእንቅስቃሴ ጋር

ومفتـــاح العــز : طاعــة الله
የልቅና ቁልፍ = አላህን መታዘዝ
ومفتاح كل شر : حب الدنيا وطول الأمل .
የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ቁልፍ = ዱንያን መውደድና ለመኖር ረዥም ተስፋ ማድረግ

🔖المرجع
📘حادي الأرواح ص : 100
🔖 ምንጭ
📘 ሓዲል አርዋሕ ገጽ 100

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

28 Jun, 07:12


አደራ አደራ አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም እንዲደርሳቸው #ሼር አድርጉት

ነብያችን ሰለሏህ አለይሂ ወሰለም አንድ ቀን ለዒድ ሶላት ሲወጡ ልጆች ሰፈር ላይ ሲጫወቱ ነበር።

አንድ ልጅ ተገንጥሎ ያለቅሳል ረሱልም ጠጋ ብለው ሄደው ጠየቁት "ምን ያስለቅስሀል? ከልጆች ጋር ለምን አትጫወትም?" ልጁም ነብያችን መሆናቸውን አላወቀም ነበር፣

"አባቴ ከረሱል ሱለሏህ አለይሂ ወሰለም ጋር
ፊሰቢሊላህ ወጥቶ ሸሂድ ሆነ ፣ እናቴም ሌላ ባል አግብታ ባሏ አባረረኝ፣ ምግብ መጠጥ ልብስም ቤትም የለኝ፣ እነዚህን ልጆች ሳይ አባት ያላቸው ናቸው። እና አባቴን አስታወስኩ" አላቸው።

ረሱልም ( ሰለሏህ ዐለይሂ ወሰለም) እጁን ይዘው "በቃ እኔ አባትህ፣ አኢሻ እናትህ ፣ ዓሊይ አጎትህ፣ ሀሰንና ሁሴን ወንድሞችህ ፣ ፋጢማ እህትህ እንዲሆኑልህ አትሻም?" ሲሉ ያኔ አወቃቸው። "እንዴት አልፈልግም ያረሱለሏህ!?" አላቸው።

ይዘውት ቤት ሄደው ፣ ጥሩልብስ አልብሰው ፣ አብልተው አጠጥተው ሽቶ ቀቡት። ደስተኛ ሁኖ ወጣ ልጆች "ቅድም እያለቀስክ ነበር አሁን ምን አገኘህ? ደስተኛ ሆነሃል" አሉት

ልጁም "እርቦኝ ነበር ጠገብኩ ፣ ራቁት ነበርኩ ለበስኩ፣ የቲም ነበርኩ ረሱለሏህ አባቴ ፣ አኢሻ እናቴ ፣ ዓሊይ አጎቴ ፣ ሀሰንና ሁሴን ወንድሞቼ፣ ፋጢማ እህቴ ሆነው እንዴት አልደሰትም!?" አለ።

ልጆቹም "ምን አልባት አባቶቻችን ፊሰቢሊላህ ሸሂድ ሆነው በነበር እንደሱ እንሆን ነበር!" አሉ

ረሱል ( ሱለሏህ አለይሂ ወሰለም ) ወደ አኼራ የሄዱ ጊዜ ልጁ አፈር ወደላዩ እየበተነ አለቀሰ። "አሁን ነው የቲም የሆንኩት" ሲል ....አቡበክር (ረድየሏሁ አንሀ ሰሙት ፣ሄ ደው እቅፍ አደረጉት።

እውነትም የእዝነት ነብይ!!

"በጃሂሊያ (ብሄርተኝነት) ጥሪ የተጣራ እርሱ በእንብርክክ ጀሃነም የሚገባ ነው ፤ ቢፆምና ሙስሊም ነኝ ብሎ ቢሞግት እንኳን።

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

26 Jun, 09:27


بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ جَاعِلِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلًا أُو۟لِىٓ أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَۚ يَزِيدُ فِى ٱلْخَلْقِ مَا يَشَآءُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ (١)

“Faaruun hundi kan Rabbii uumaa samiifi dachii ta’e, kan maleykotas ergamtoota abbootii kooluuwwan lama lamaa, sadi sadiifi afur afurii taasiseef haa ta’u Uumama keessattis waan fedhe ni dabala Dhugumatti, Rabbiin waan hunda irratti danda’aadha”

مَّا يَفْتَحِ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ مِن رَّحْمَةٍ فَلَا مُمْسِكَ لَهَاۖ وَمَا يُمْسِكْ فَلَا مُرْسِلَ لَهُۥ مِنۢ بَعْدِهِۦۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ (٢)

“Rahmata irraa wanta Rabbiin namaaf bane wanti ishee dhorgu tokkoyyuu hin jiru Wanta Inni dhorges Isa boodaan wanti ishee gadi dhiisu (ergu) hin jiru Innis injifataa, ogeessa”

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱذْكُرُوا۟ نِعْمَتَ ٱللَّهِ عَلَيْكُمْۚ هَلْ مِنْ خَٰلِقٍ غَيْرُ ٱللَّهِ يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ (٣)

“Yaa namootaa! Ni’imaa Allaah of irratti yaadadhaa Sila Rabbiin ala uumaan biraa kan samiifi dachii irraa soorata isiniif kennu ni jiraa? Isa malee gabbaramaan haqaa hin jiru Kanaafuu akkamitti isa (irraa) garagaltu?”

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

25 Jun, 18:23


ከቤተሰብ የሚጀምር ህመም
መቼም አያልቅም!

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

15 Jun, 19:42


Maatiin Golden Age hunduu Eid Mubarak.


Baga geessan!!
تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال

መላው የGolden Age ቤተሰብ ኢድ ሙባረክ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።


እንኳን ደስ አላችሁ።

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

15 Jun, 03:51


#Sadarkaa_guyyaan_ARAFAA_qabdu

◀️  قال رسول الله - صلى الله عليه وسلم -: « ما من يوم أكثر من أن يعتق الله فيه عبدا من النار من يوم عرفة » . رواه مسلم.

▶️  Ergamaan rabbii (saw) akkana jedhan 《 guyyaa arafaa caala guyyaan rabbiin irra hedduu gabricha isaa ibidda irraa bilosoomsuu waan taane 》

◀️   سئل رسول الله - صلى الله عليه وسلم - عن صوم يوم عرفة، قال: « يكفر السنة الماضية والباقية »  رواه مسلم

▶️  Ergamaan rabbii (saw) sooma guyyaa arafaa irraa gaafatamee akkana jedhe 《 Dilii waggaa dabarteetiifii tan waggaa dhuftuu maara 》
Join and share
👇👇👇👇
https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

14 Jun, 17:57


🛑 የአረፋ ቀን ፆም!

ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

🛑 የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 ነው።

⚫️ ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።

⚫️ ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል። ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።

⚫️ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።

⚫️በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣

1/ ቀኑን መጾም

2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር

3/ ዱዓእ ማብዛት

⚫️ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

🛑 የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ነው።

https://t.me/GoldenAge2013

Golden Age

14 Jun, 14:49


ነገን መጾም አንርሳ!!

https://t.me/GoldenAge2013