🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍ @abuhemewiya Channel on Telegram

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

@abuhemewiya


የጠራ እውቀት ከተቃና አቐምና ተግባር ጋር የተረዘቀ ታድሏል !!

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍ (Amharic)

ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ከአቡ ሀመዊየህ ጋር ይታደጋል። ይህ ገጠር የጠራ እውቀት ከተቃና አቐምና ተግባር ጋር የተረዘቀ ታድሏል! ይህ ቢሆንም ግብር ገለጹ ማለት እንደሆነ ነው። አቡ ሀመዊየህ ለምን እንደተገለጹ ይቆያል? እንደሆነ እናውቃለን! የጌታችን ታሪኩን በትክክለኛ ፈቃድ እንኖራለን። ለመጠበቅ እናሳውቁ ለታሪኩ ስለ ትምህርት እና መኖሪያዎች፣ ከእርስዎ የተከታታቹን መረጃዎችን በማድረግ እንቅስቃሴና መዳብም በማስመረጥ ለታሪኩ የመበት ትምህርት ውጤት ለመስራት ይህን መረጃዎችን ይሰጣል። አቡ ሀመዊየህ ከእንግዳ እንደሆንህ፣ ማመልከት እና ትምህርትን በማስተካከል ወደ ምትችለው እንሂድ! አቡ ሀመዊየህ ከዚህ በኋላ እናሳዋቂ ይሁኑ።

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

11 Jan, 11:50


👉 ሰዎች ወደ አብሬት ለምን ይጓዛሉ ?

የኢስላም ጠላቶች የእስልምና ጮራ ከፈነጠቀበት ጊዜ አንስተው ብርሀኑን ለመግታት ከቻሉም ለማጥፋት ብዙ ሞክረዋል ። በተለይ የመጀመሪያው ትውልድ የኢስላምን አድማስ እያሰፋ በነበረበት ጊዜ በዐለም ላይ የነበሩ ሀያላን የሚባሉ ሀገራት ከኢስላሙ ብርሀን ፊት ለመቆም ብዙ ዋጋ ከፍለዋል ። ግን ልፋታቸው ያ ትውልድ ከአላህ ጋር በነበረው ጥብቅ ትስስር ምክንያት መክኖ እንዲቀር አድርጎታል ።
ተስፋ የማይቆርጠው የሸይጣን ሰራዊት አንዱ ሜዳ ላይ ሲሸነፍ ሌላ ሜዳ ፊቱን እያዞረ ከአራሕማን ሰራዊት ጋር ሲፋጠጥ ምኞቱ ከስሞ ቅስሙ ተሰብሮ መመለስ እንጂ ወደ ፊት መቀጠል አልቻለም ። የዚህ አይነቱ ሽንፈት ሚስጢር ሳይገባቸው በማያውቁት ነገር የኪሳራ ካባ ሲደራርቡ ሚስጢሩን ማወቅ አለብን አሉ ።
በዚህም ቆም ብለው ያሳለፉትን በህሊናቸው መስኮት እያማተሩ ሲያዩ ብዙ ሰራዊት በቁጥርም በትጥቅም የማይገናኝ ከጥቂቶች ፊት መቆም እንዲያቅተው ያደረገው በአራሕማን ሰራዊት ልብ ውስጥ የነበረው የኢማን ሀይል መሆኑን አወቁ ።
እየተሸነፉ ያሉት በመሳሪያና በሰራዊት ብዛት እንዳልሆነ ይልቁንም ትንሹ ሰራዊት ከአላህ ጋር ባለው የጠበቀ ትስስር በአላህ እርዳታ መሆኑን ገባቸው ። እያሸነፋቸው ያለው የተውሒድ አቅም እንጂ የሰራዊት አቅም አለመሆኑን አመኑ ።
የዚህን ጊዜ እስትራቴጂ መቀየር አስፈላጊ ሆነ ። ጦርነቱ ከኢማን ጋር ከተውሒድ ጋር ሆነ ለዚህም ሰራዊት መመልመል ጀመሩ ። የአሁኑ መሳሪያ በጀርባ አዝለውት በትከሻ ተሸክመውት የሚሄዱት አይደለም ። ቀላል ሆኖ በጣም አጥፊ መሳሪያ ነው ። በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ያለውን ተውሒድ የሚያጨልም ኢማናቸውን የሚያቀልጥ የሹብሃ መሳሪያ የስሜት መከተል መሳሪያ መታኮስ መሳየፍ የማያስፈልገው በጥቂት ቃላቶች የሚገለፅ ቶሎ ልብ ላይ የሚሰርፅ መሳሪያ መጠቀም ጀመሩ ።
የጦርነቱ ሜዳ ከበረሀ ወደ ሽርክና ቢዳዓ ፋብሪካ ተዛወረ ። ከሙስሊሙ ውስጥ ለዚህ ፋብሪካ ሰራዊት መለመሉ ከበላይ የሚመራው የዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አልየሁድይ ሀላፊነቱ የተወሰነ የኩፍር ማህበር ሆነ ። የሺዓ ፋብሪካ ተከፈተ በወልይ ስም ሙታኖች ይጠቅማሉ ፣ ይሰማሉ ፣ ይረዳሉ ፣ አላህ ስልጣን ሰጥቷቸዋል በሚል አላህን ትቶ እነርሱን መጥራት ተንሰራፋ ። ጎን ለጎን የተለያዩ የቢዳዓ ፋብሪካዎች እየተከፈቱ የሙታን መንፈስ ማምለኩ አድማሱ እያሰፋ ቅርንጫፉ እየበዛ ለዓለም ተዳረሰ ። የሱፍያው እህት ኩባንያ ይህን ሽርክ የማስፋፋቱ ስራ በሰፊው ተያያዘው ።
በዚህም በቀላሉ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ አላህ ያዘነለት ሲቀር ከውስጡ በአላህ ማመን የሚባለውን ማውጣት ቻሉ ። በዚህም አብዛኛውን ሙስሊም ኮፍያ ጥምጣምና ጀለብያ የለበሰ ቆሞ የሚሄድ ውስጡ ባዶ የሆነ እስከሌተን አደረጉት ።
የኢስላም ጠላቶች ሀገራችን ላይ ሙስሊሙን ከኢማኑ ለማራቆት ከከፈትዋቸው የሽርክ ፋብሪካዎች አንዱ አብሬት ያለው ሀድራ ነው ። ቅርንጫፉ ጠቅላይ ቢሮ የሚባለው አ/አ ነው ።
ሰዎች በየአመቱ ወደ አብሬት የሚገርፉት በአላህ ላይ ለማጋራት ውስጣቸውን አላህ ይጠቅማል ከሚለው ኢማን ባዶ አድርገው ያብሬት ሸይኾች ይጠቅማሉ በሚል ቀይረው ለሳቸው ችግራቸውን ለመንገር ነው ።
አው አብሬት የሚሄድ ሙሪድ ኮፍያ ያደረገ ፣ ጀለብያ የለበሰ ፣ ጥምጣም የጠመጠመ ወይም ስሙ ሙሐመድ ፣ አሕመድ ፣ ከማል ፣ ሰፋ ፣ ጀማል የሆነ የሙታን መንፈስ አምላኪ ነው ። ሀድራውን የሚመሩት ጫት ናላቸውን ያዞራቸው ጠንቋዮች ናቸው ። ህዝቡን ቁርኣንና ሐዲስ ሳይሆን ያብሬትዬ የሚሉት ሸይጣን ወሕይ የሚያደርግላቸው ገድል ነው ።
አብዛኛው አብሬትዬ ይመጣሉ በሚል ከሀገሩ የወጣ ነው ። ዱዓእ ሲያደርጉ በሀድራቸው አላህ ያስገባቸው የሚል ነው ። ይህ ተራውን ህዝብ የሚያስተኙበት እንጂ ገስግስ እንደገደላቸው ያውቃሉ ። የራሳቸው ልጆች አንዱ ሌላውን አባታችንን አስገድለዋል በሚል ክስ ላይ ናቸው ። ይህ ከመሆኑ ጋር ወደ አብሬት የሚጎርፈው ህዝብ ችግሩን ለአብሬትዬ ይናገራል ። ዘር ስጡኝ ፣ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ ለማን ተውኝ ይላል ። መከራውን ፣ ችግሩን ፣ ሐዘኑን ፣ ማጣቱን ፣ መጎዳቱን ፣ ፍርሀቱን ለሳቸው ይናገራል ። እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ እጄን ያዙኝ ይላል ።
ኧናገራ ያለውን የአባታቸው ቀብር ( ኧቁባይ ) ሄዶ አፈር ይበላል ። በእንብርክኩ ወደ ቀብሩ ይደርሳል ። ስልኩን አጥፍቶ ጫማውን ከሐረሙ ( ከጊቢ ) ውጪ አስቀምጦ በእንብርክክ ሄዶ ቀብሩ ጋር ስጁድ አድርጎ በጠዋፍ ዞሮ ለአላህ እንጂ የማይገባ አምልኮ ያደርጋል ። ጉዱ በዚህ አይቆምም በየአመቱ የሚሄዱ አንድ ላምስት ተደራጅተው ወደዚህ ቀብር አምልኮ ለመጣራት ተስማምተው ይመጣሉ ።
አሕባሽና ሱፍዮች የዚህ አይነቱን የሽርክና የኩፍር ተግባር በገንዘብ በመርዳት አድማሱ እንዲሰፋና ሙስሊሞች ቀብር አምላኪ እንዲሆኑ ቀንና ለሊት ይሰራሉ ። ይህ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ነው ተብሎ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የቁርኣን አንቀፆች ሲነገራቸው ለከሀዲያን የወረዱ የቁርኣን አንቀፆች ለሙስሊሞች ያደርጋሉ ይላሉ ።
እነዚያ አላህ ሙሽሪክ ያላቸው ከሀዲ ያላቸው ሰዎች ጥቁር ፣ቀይ ፣ ዐረብ ፣ ዐጀም ፣ አጭር ፣ ረዥም ፣ ስለነበሩ ነው ወይስ የሚሰሩት የነበረው ተግባር የኩፍርና የሽርክ ተግባር ስለነበረ ነው ? በእነዚ አባባል ስለ ሶላት ፆምና ዘካ የሚናገሩ አንቀፆች ለእነዛ በዛ ዘመን ለነበሩት ብቻ ነበር አሁን አይሰራባቸውም ማለት ነው ።
ሁሉም በየትኛውም ጉዳይ የመጡ የቁርኣንና የሐዲስ መረጃዎች በየትኛውም ዘመን የትም ቦታ ይሰራሉ ። ሙሽሪኮቹ ሲሰሩት የነበረውን ሺርክ የሚሰራ ሙሽሪክ ይባላል ። ከሀዲያን የሚሰሩትን የኩፍር ተግባር የሚሰራ ካፊር ይባላል ። በግለሰብ ላይ ብይኑን ለመስጠት የሚያስችሉ መስፈርቶች ተሟልተው ከልካዮች ሲወገዱ መረጃው ሲደርስ ያግለሰብ ካፍር ነው ይባላል ። የቁርኣን ህጎች በወረዱበት ምክንያት የተገደቡ አይደሉም ። ቃሉ በያዘው ብይን እስከቂያማ ይሰራሉ ።
በመሆኑም እናትና አባቶቻችንን ከአሕባሽና ሱፍዮች እጅ ለማውጣትና ወደ ተውሒድና ትክክለኛ እስልምና ለማምጣት የምንችለውን ማድረግ ይጠበቅብናል ።

አላህ ይወፍቀን ።

https://t.me/bahruteka

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

10 Jan, 14:30


👉 የነሲሓዎች የአደባባይ ዝቅጠት ለአደባባይ ክስረት

ነሲሓዎች የነበሩበት መንገድ ለዱንያዊ ክብረት እንደማይሆን ሲያውቁ ሸይኻቸው ኢልያስ አሕመድ ህዝቡን አስተኝቶላቸው ከኢኽዋን ጋር ተቀላቅለው መስራት እንዳለባቸው ከወሰኑ በኋላ በ30 የእንቅልፍ ክኒን ወጣቱን አስተኛላቸው ። ቀጥለው የተኛው ህዝብ ሳይነቃ ቶሎ ወደ ሚፈልጉበት ለመድረስ ሩጫ ጀመሩ ። ሩጫቸው ታርጌት ያደረገው የእንጀራ አባቶቻቸው ኢኽዋኖችን ማስደሰት ላይ ነበር ። በዚህም ሸይኻቸው ዶ/ር ጀይላንን ከማወደስ ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን በፍጥነት እየተንደረደረ ነጎደ ።
አደባባይ እየወጣ ከነ ካሚል ሸምሱ ፣ አቡ በከር አሕመድ ፣ ያሲን ኑሩ ፣ ሙሓመድ ሓሚዲን ፣ ሓሚድ ሙሳና ሌሎችም ዋና ዋና መሪዮች ጋር በተለያዩ ፕሮግራሞች አብሮነታቸውን አሳየ ። እሱ መርጂዓቸው ስለሆነ እንጂ እነ አዩብ ደርባቸውም በፊናቸው በተለያዩ መድረኮች አብሮነታቸውን አረጋግጠዋል ። ይህ ሁሉ ሲሆን በ30 የእንቅፍ ክኒን እንዲተኙ የተደረጉ ሙሪዶች አልነቁም ነበር ። ይልቁንም እኛ ስለማናውቅ ነው እንጂ እነርሱ ያለ መስላሓ አይሰሩም የሚል የጋራ ድምፅ ያሰሙ ነበር ።
ኢልያስ አሕመድ 30 የእንቅልፍ ክኒን ሲሰጥ አብዛኛው ወጣት ኢኽዋኖችን ያለእውቀታችን በናንተ ላይ ተናግረን ነበር አሁን ተመልሰናል አውፍ በሉን ብሎ ነበር ። ያኔ የ30 ክኒኖቹ ሚስጢር የገባቸው ሰዎች ውስጣቸው እያረረ ኢኽዋኖች በድል አድራጊነት ስሜት ይጎርሩ ነበር ። መሻኢኾችና የተወሰኑ ወንድሞች ያደረጉት የነሲሓዎችን አካሄድ የማጋለጥ ትግል ብዙ ፍሬ ያፈራ የነበረ ቢሆንም የአሁኑ አይነት ድል ይገኛል ብሎ ያሰበ አልነበረም ።
በሚገርም መልኩ ብዙ ወንድምና እህቶች የነሲሓዎች ሸይኽ ሶሞኑን የሱፍያና ኢኽዋንያ ሚንሀጅ እስፕሪስ ጭማቂ ከሚያንቃርረው ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ጋር የነበረውን ፕሮግራም ካዩ በኋላ አውፍ በሉን ነገሩ በዚህ መልኩ አልመሰለንም ነበር እያሉ ነው ።
ለእነዚህ ወንድምና እህቶች እንዲሁም ለሌሎችም የምንለው መጀመሪያ ምስጋና ሐቅን ላሳወቃችሁ አምላካችን አላህ ይገባው ። ቀጥሎ እኛን በግል በሰድብም ይሁን ስም በማጥፋት ላደረሳችሁት በደል በቅድሜያ እኔ በግሌ አውፍ ብያለሁ መሻኢኾችም ይሁን ሌሎች ወንድሞች ከዚህ የተለየ እይታ ይኖራቸዋል አልልም ። ምክንያቱም ሁላችንም ነብዩን ነውና የምንከተለው ። የአላህ መልእክተኛ አላህ መካን እንዲከፍቱ ድል ሲሰጣቸው እነዚያ መተተኛ ፣ ጠንቋይ ፣ ገጣሚ ፣ እብድ ሲሏቸው የነበሩ የመካ ሹማምንቶች ተሰብስበው ፍርዳቸውን ለመቀበል ሲጠብቋቸው ሂዱ እናንተ ነፃ ናችሁ ነበር ያሉዋቸው ። ነብዩላሂ ዩሱፍም ጉድጓድ ውስጥ የወረወሩዋቸውን ወንድሞቻቸው አላህ ድል ሰጥቶ የበላይ አድርጓቸው አንገታቸውን ደፍተው ይቅርታ ሲጠይቋቸው ሂዱ አላህ ምህረቱን ይስጣቸሁ ነበር ያሉዋቸው ። የሚፈለገው ሐቅን አውቆ ወደ አላህ መመለሱ ነውና የሰዎች ክብር የተነካው በአላህ መንገድ ላይ እስከሆነ ድረስ ከፍታ እንጂ ዝቅታ ስላልሆነ ቦታ አይሰጠውም ። ይልቁንም ይህን ወንጀል ከመስራታችሁ በፊት ከነበራችሁ ደረጃ ይጨምርላችኋል ። ምክንያቱም አላህ ዘንድ አንድ ሰው ወንጀል ሳይሰራ በፊት ከነበረው ደረጃ ወንጀል ሰርቶ ተውበት አድርጎ ሲመለስ ያለው ስለሚበልጥ ።
አሁንም ኢልያስም ሆነ ሌሎች በየቀኑ እየዘቀጡ ማየታችን ለኛ ህመም እንጂ ደስታን አይፈጥርም ። የወንድምና እህቶች መመለስ የሚፈጥረው ደስታ የነሲሓዎች ዝቅጠት ያደበዝዘዋል ። ሙሉ ደስታ የሚሰጠው ሙኻሊፎች ባጠቃላይ ተውበት አድርገው ወደ አላህ መመለሳቸው ነው ። አሁንም ለነሲሓዎች የምንለው በየቀኑ በአደባባይ የምታሳዩት ዝቅጠት ወደ አደባባይ ክስረት እየተቀየረባችሁ ነውና ቆም ብላችሁ አስቡና ተመለሱ ነው ።

https://t.me/bahruteka

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

09 Jan, 17:55


🍎 ዛሬ ምሽት

ከ3:00 - 4:00

🎙 አቡሐመውያ ሸምሱ ጉልታ ሐፊዘሁለሁ

📚 ተፍሲሩል ፋቲሐቲ ወልሙዓወዘትይኒ ወልኢኽላስ

🕌  አልኢስላሕ ኦንላይን ቂርኣት ፕሮግራም

የኪታቡን pdf ለማግኘት
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/alislaahwomenonlineders/250
                                      
https://t.me/alislaahwomenonlineders

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

03 Jan, 11:18


  ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም
          🏘 በሃሮ ከተማ


👉🏝 ➴➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/9572

🏝 ውድ የሱና ቤተሰቦቻችን የነብያት ውርስ የሆነው የተውሒድ ዳዕዋ በሰሜን ወሎ የነብያት አደራ ተረካቢ በሆኑ መሻኢኾች እያበበና አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ይታወቃል።

አሁን ደግሞ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 27/04/2017 በሀሮ ከተማ የተውሒድን ችግኝ ለመትከል ቀጠሮ ተይዟል። በዚህ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ከሰሜን ወሎ መሻኢኾች በተጨማሪ ሌሎች መሻኢኾችና ኡስታዞች ይካፈላሉ።
    
👉 እነማን ካላችሁ የሚከተሉት ይገኙበታል።
1 🪑🎙 ሸይኽ ዐአብዱልሐሚድ አልለተሚ
         🛖 ከደቡብ ስልጤ ዞን
2 🪑🎙 ሸይኽ ሙባረክ ሑሰይን

         🛖 ከደቡብ ወልቂጤ ከተማ
3 🪑🎙ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል
         🏢 ከኮምቦልቻ ከተማ
4 🪑🎙 ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት
       🏠 ከሰሜን ወሎ ሓራ ከተማ
5 🪑🎙 ሸይክ ሑሰይን ከረም
       🏠 ከሰሜን ወሎ ሓራ ከተማ
6 🪑🎙 ሸይኽ ኢስማኢል ዘይኑ
        🏡 ከደቡብ ወሎ ተንታ ከተማ
7 🪑🎙 ሸይኽ ሑሰይን ዐባስ 
         🏠 ከሰሜን ወሎ ወርቄ
8 🪑🎙 ሸይኽ ሙሐመድ ሲራጅ
          🏡 ከሰሜን ወሎ ሃሮ
9 🪑🎙 ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ
         🏘 ከሰሜን ወሎ ሓራ ከተማ
10 🪑🎙 ኡስታዝ  ሙሐመድ ኑር
         🏢 ከኮምቦልቻ ከተማ
11 🪑🎙 ኡስታዝ ባሕሩ ተካ
          🏫 ከአዲስ አበባ ከተማ
12 🪑🎙 ኡስታዝ አቡበክር ዩሱፍ
         🏞 ከባሕር ዳር ከተማ
13 🪑🎙 ኡስታዝ ዐብዱራሕማን

         🏘 ከሰሜን ወሎ መርሳ ከተማ
14 🪑🎙 ኡስታዝ ኸድር ሐሰን
        🏢 ከወሎ ኮምቦልቻ ከተማ
15 🪑🎙 ኡስታዝ ኑር አዲስ
         🏘 ከሰሜን ወሎ መርሳ ከተማ
16 🪑🎙 ኡስታዝ ሙሐመድ ሰልማን
         🏘 ከሰሜን ወሎ ሓራ ከተማ
17🪑🎙ኡስታዝ ሙሐመድ አሚን
     🏣 ከይፋት ምድር ሸዋሮቢት ከተማ

🏖 በዚህ ፕሮግራም ላይ የሃሮ አልፉርቃን መስጂድን ለማቋቋሚያ የሚሆን ተጨማሪ ፕሮግራም ይኖራል። በመሆኑም የሱና ቤተሰቦች በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ  አሻራችሁን አኑሩ ይላል ጀማዓው።

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል እንዳታስቡ።

አላህ ካለ ፕሮግራሙ የሚጀመረው
    ከጠዋቱ  2 : 30 ይሆናል።
    

🚥 የእሁድ ፕሮግራማችን ከነቤተሰባችን ሃሮ ፉርቃን መስጂድ እናድርግ

♻️ ለበለጠ መረጃ፦
📞☎️  ስልክ ቁጥር 
      📲 +251920474161
      📲 +251929732296
      📲 +251935212614

🎞 t.me/heroselefi

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

01 Jan, 15:49


ልዩ ቆይታ ከሸይኽ ሙባረክ ጋር

ገባ በሉ

https://t.me/medresetulislah

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

27 Dec, 18:01


🛜ሰበር

ዛሬ ምሽት 3:10
በሸይኽ አብዱልሃሚድ አለተሚይ

ከትዳር ህይወት ጋር ተያያዥ የሆኑ ሸሪኣዊ ድንጋጌዎች በዓሊም አንደበት ይዳሰሳሉ::

ሙሐደራ ይኖረናል።

ከደቂቃዎች በኋላ

https://t.me/alislaahwomenonlineders

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

26 Dec, 08:27


🟢የድል ብስራት🟢

የአዲሶቹ ሙመይዓዎች መሪዎች መፍረክረክ በጀመሩ ሰሞን በተደረገ ጀልሳ (ሹራ) ላይ አሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ የቀሩት ቲላዋ:
﴿وَلَقَدۡ سَبَقَتۡ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا ٱلۡمُرۡسَلِینَ ۝إِنَّهُمۡ لَهُمُ ٱلۡمَنصُورُونَ ۝١٧٢ وَإِنَّ جُندَنَا لَهُمُ ٱلۡغَـٰلِبُونَ ۝فَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِینࣲ ۝وَأَبۡصِرۡهُمۡ فَسَوۡفَ یُبۡصِرُونَ ۝ أَفَبِعَذَابِنَا یَسۡتَعۡجِلُونَ ۝ فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمۡ فَسَاۤءَ صَبَاحُ ٱلۡمُنذَرِینَ ۝ وَتَوَلَّ عَنۡهُمۡ حَتَّىٰ حِینࣲ ۝ وَأَبۡصِرۡ فَسَوۡفَ یُبۡصِرُونَ ۝…

(171) በእርግጥም ለመልእክተኞች ባሮቼ (የድል ማረጋገጫ) ቃላችን ፀድቃ አልፋለች።

(172) እነርሱ ናቸው የሚረዱ (አላህ የሚረዳቸው)።

(173) ሰራዊቶቻችንም እኮ በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው።

(174) እስከ ተወሰነው (የቅጣት መምጫ) ጊዜ ድረስም ተዋቸው።

(175): ተመልከታቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያዩታል።

(176): ለቅጣታችን ይጣደፋሉን።

(177): (ቅጣቱ) በመንደራቸውም በወረደ ጊዜ የተስፋራሪዎች (የተዛተባቸው) ንጋት ምንኛ ከፋ !!

(178): እስከ ተወሰነው (የቅጣት መምጫ) ጊዜ ድረስም ተዋቸው።

(179): ተመልከታቸውም ወደፊትም (የሚደርስባቸውን) ያዩታል።

(180): አሸናፊው ጌታህ  እነርሱ ከሚገልፁት (እንከን ሁሉ) ጥራት ተገባው።

(181): በመልእክተኞችም ላይ ሁሉ ሰላም ሆነ።

(182): ምስጋናም ሁሉ ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ሆነ።


የአሸይክ አሰይዲይ ተፍሲር⤵️
https://t.me/Abuhemewiya/2108

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

26 Dec, 02:21


🔵ውድ ቀናቶች እየደረሱ ነው

ሶስተኛ ዙር ወርሐዊ ፕሮግራማችን ከፊታችን ጁሙዓህ (18/04/2017) ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ይቆያል ኢን ሻእ አላህ

የኪታቦቹ ዝርዝር ለማስታወስ

١. مقدمة في أصول التفسير
የኪታቡ pdf

https://t.me/medresetulislah/6612

٢. الأصول من علم الأصول
የኪታቡ pdf

https://t.me/medresetulislah/6634

٣. مختصر سيرة الرسول ﷺ
የኪታቡ pdf

https://t.me/medresetulislah/6639

٤. بيان فضل علم السلف عل على علم الخلف
የኪታቡ pdf

https://t.me/medresetulislah/6620

٥. بلوغ المرام
የኪታቡ pdf

https://t.me/medresetulislah/6630

٦. متممة آجرومية
የኪታቡ pdf

https://t.me/medresetulislah/6624

المدرس:- 🎙 فضيلة الشيخ أبو عبدالحليم عبدالحميد بن ياسين اللتمي

🕌 በአልኢስላሕ መድረሳ

https://t.me/medresetulislah

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

25 Dec, 11:46


🟢 ገሳጭ ቲላዋ

በአሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሃዲይ አልመድኸሊይ (አላህ ይጠብቃቸው)

ጁመዐህ 09/06/1445


📍በአሸርበትሊይ መስጂድ


የሱረህ አተካሱር መልዕክት በአማረኛ ⤵️
https://t.me/Abuhemewiya/2705

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

25 Dec, 11:04


ተንቢሃት ክፍል-1

በኡስታዝ አቡ ኑዐይም ሱልጣን ሐሰን ሐፊዘሁሏህ

https://t.me/alislaahwomenonlineders

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

24 Dec, 05:21


١. صحيح مسلم

٢. نزهة النظر في توضيح نخبة الفكر في مصطلح أهل الأثر

ዘወትር ከሰኞ እስከ ረቡዕ ከ3:00-5:30

በሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ አስሲልጢ 


     ሰ
            አ
                  ቱ
                        ይቀጥላል።

https://t.me/medresetulislah

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

23 Dec, 08:30


🟢የተምዪዕ በሽታ እንዲህ ይጀምራል

🎤ከአሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚይ ፈትዋ

👉ጥፋት እና ጥፋተኛን እያዩ ኢንካር ከማድረግ ይልቅ ምክንያት መደርደር ::

👉የእነ አህመድ ኣደም እና ያሲን ኑር የተመዪዕ ስልት ነች::

👉የሀገራችን ተመዩዕ በሽታ::

👉ሰለፊይ ዑለማዎች አጥማሚዎችን እንዲህ አጋልጠው ኡማውን  በአላህ ፈቃድ ታድገዋል ::

👉የሙመይዓዎችን ፍልስፍና ትተህ በነቢዩ (ﷺ) ሀዲስ ስራ::
" مَنْ رَأَى مِنْكُمْ مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بِيَدِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسَانِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وَذَلِكَ أَضْعَفُ الْإِيمَانِ ".
أخرجه مسلم في "صحيحه"، كتاب : الإيمان باب النهي عن المنكر من الإيمان (1/ 50) رقم (49).


https://t.me/FATTAWAS

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

23 Dec, 06:59


ተለቀቀ‼️

📌📚📖አዲስ መፅሐፍ 📖📚📌

"አል ኢርሻድ - ወደ ትክክለኛ እምነት መምራትና በማጋራትና በጥመት ባለቤቶች ላይ ምላሽ መስጠት"


الإرشاد إلى صحيح الإعتقاد والرد على أهل الشرك والإلحاد

በሸይኽ ዶክተር/ሷሊሕ ብን አል'ፈውዛን ሐፊዞሁሏህ ተዘጋጅቶ

በአቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አሕመድ ሐፊዞሁሏህ ወደ አማርኛ የተመለሰ

በዚሁ ቻናል በPDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚተላለፍ ይሆናል ተብሎ ቃል በተገባው መሰረት እነሆ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርቧል‼️

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️
አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://t.me/alateriqilhaq

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

22 Dec, 18:52


አንተ ሙወሂድ ሆይ!! አንቺ የተውሂድ ባለቤት ሆይ ልብ በሉ!! ዒባዳ ዒባዳ ሊባል ሚችለው ተውሂድ ሲታከልበት ብቻ ነው‼️

በቃ ሰለፊይ ስትሆን እንዲህ ነው:: የትኛውም ርዕስ ላይ ተውሂድን ችላ ልትለው አትችልም‼️


ሰለፊያ ማለትም ነብያቶችንና ተከታዮቻቸውን መንገድ መከተል ነው።


ለመከታተል  👇👇
https://t.me/EUSaCochannel?livestream

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
t.me/EUSaCochannel

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

22 Dec, 18:19


🌐  አሁን  

💎ተጀመረ

📚 صفة صلاة النبي صلى الله عَلَيْهِ وَآلِهِ وَسَلَّم
📚የነቢዩ (ﷺ) ሰላት አሰጋገድ



🎤 በአቡ ሀመዊያህ ሸምሱ
ጉልታ(ሀፊዘሁሏህ)




📖  የኪታቡ pdf 👇👇
t.me/EUSaCochannel/176

╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 

ለመከታተል  👇👇
https://t.me/EUSaCochannel?livestream

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
t.me/EUSaCochannel

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

21 Dec, 04:37


👆👆👆
🔈
#ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ፡፡

🔶
በአዲስ አበባ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተደረገ ሙሐደራ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

20 Dec, 14:47


👉 የከሰሩ ነሲሓዎች ክስረት

አል ሂዳያ በሚል በጉራጌ ዞን የሚንቀሳቀሱት የድሮዎቹ ሙመዪዓዎች የአሁኖቹ ኢኽዋኖች ባለፈው ሳምንት ጉንችሬ ማዞሪያ ዑመር መስጂድ ላይ ነጭ ነጩን እንቅጭ እንቅጩን በማስቀመጥ የተደረገው ዳዕዋ የቁም ቅዠት ውስጥ ከቷቸው እነሞር ላይ ዳዕዋ ብሎ ማስተዋወቅ በኪሳራ ላይ ኪሳራ እየጨመረብን እንጂ እየጠቀመን አይደለም ። ስለዚህ ወጣት ሽማግሌ አዛውንት ጎልማሳው እንዲሁም ወንድና ሴቱንም የምናገኘው በጁሙዓ ስለሆነ ለዘብተኛ ዳዒዮችን እየጋበዝን ህዝቡን መያዝ እንችላለን የሚል እስትራቴጂ ነድፈው ይህንንም በዛሬው ጁሙዓ ተግባራዊ አድርገውታል ። ዳዒዮቻቸው እነባሕሩ የማለት ሞራሉ ስለሌላቸው የሙስሊሞቹን አንድነት የሚበታትኑ ሰዎች አሉ ተጠንቀቁ በሚል ተሕዚር መለማመድ ጀምረዋል ።
ለነሲሓዎችና ሙሪዶቻቸው እንዲሁም ዱዓቶቻቸው ማለት የምንፈልገው ድሮም በሐቅ ሰዎች ላይ ተሕዚር ተለማመዱና ከባጢል ሰዎች ለማድረግ መግቢያ ይሆናችኋል ብለናል ። ነገር ግን አሁንም ማረጋገጥ የምንፈልገው አው እኛ በቀብር አምላኪና አላህን በሚያመልክ መካከል አንድነት የለም ነው የምንለው ።
አንድ ለመሆን ቀብር አምላኪ ሆኖ በሽርክ ወይም አላህን አምላኪ ሆኖ በተውሒድ ነው መሆን የሚቻለው እንላለን ። ቀብር አምላኪና አላህን አምላኪ አንድ ማድረግ ከባድ ወንጀል ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል : –

« أَفَنَجْعَلُ الْمُسْلِمِينَ كَالْمُجْرِمِينَ »
القلم ( 35 )
" ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን ?"

« مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ »
القلم ( 36 )
" ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ ፡፡

ሙስሊም ማለት አላህን የሚያመልክ ነው ። ቀብርን ፣ ወልይን ፣ ቀንን ፣ ቆሌን ፣ አድባርን ፣ ሸይኽን …… ወዘተ የሚያመልክ ሙስሊም አይደለም ። ስለዚህ አንድ ሊሆኑ አይችሉም ። አንድ ለማድረግ ቀብር አምላኪዮች ተውበት አድርገው ሊመለሱ ይገባል ። ቀብር ማምለክ ፣ ወልይ ማምለክ ፣ ሸይኽ ማምለክ ወይም እነዚህን አካላት እርዱኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ አክብሩኝ ፣ አሽሩኝ ፣ ሞሽሩኝ ፣ ዘር ስጡኝ ፣ ከጭንቅ አውጡኝ ማለት ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ መሆኑን መንገር ይገባል እንላለን ።
አላማቸው የማንም ቁስል ሳይነካ ህዝብ መሰብሰብና በዲን መነገድ ያደረጉ ነሲሓዎች የሚልኩዋቸው ዳዒ ተብዬዎች ይህ ያሳምማቸዋል ያስቆጣቸዋል ። በዚህ መልኩ ዳዕዋ የሚያደርጉትን በታታኝ ይሉዋቸዋል ። በመሆኑም በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያላችሁ የሱና ሰዎች ባጠቃላይ እነሞር ላይ ያላችሁ በተለይ እነዚህን ሆድ አምላኪ ተላላኪዮች አሳፍራችሁ ልትመልሱና ኪሳራቸውን ልታስቀጥሉ ይገባል ። በቁጭታችሁ ሙቱ እንጂ የተውሒዱ ዳዕዋ ያብባል የናንተ ማንነት ለህዝቡ ይነገራል እንላቸዋለን ።

https://t.me/bahruteka

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

20 Dec, 05:28


↪️ የሸይኻችን ሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ አለተሚይ ሀፊዘሁላህ ደርሶችን የምትከታተሉ የነበራችሁ እንዲሁም መከታተል የምትፈልጉ ደርስ ሰኞ እለት ተጀምሯል። ስለዚህ ደርሳ እንዳያመልጣችሁ ቶሎ ቶሎ ወደ መድረሳ ግቡ።

📙 አዲስ የተጀመሩ እና እየተቀሩ ያሉ ኪታቦች

* ፉቱሀቱል ቀዩሚያ (አዲስ ተጀመረ)
* ቡሉጉል መራም (አዲስ ተጀመረ)
* ሸርሁ ዐቂደቲ ሰፋሪኒያህ (ነባር)
* ሙኽተሰሩ ሰዋዒቂል ሙርሰላህ (አዲስ ተጀመረ)
* ሲያነቱ ሰለፊይ (ነባር)
* ተፍሲር ቁርአን (ነባር)
* ሱነኑ አቢ ዳውድ (ነባር)
* ሱነኑ ቲርሚዚይ (ነባር)
* ሶሒሁል ቡኻሪ (ነባር)

ስለዚህ እነዚህን ኪታቦች በማዘጋጀት ወደ መድረሳው ገባታችሁ ከሸይኽ ዕውቀት መቅሰም ትችላላችሁ።

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

19 Dec, 12:35


🟢ስለ ሀሰን አቱራቢ ምን ይላሉ?

🎤ከአሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚይ ፈትዋ

👉ስለሙብተዲዕ ጥፋት ሲነገር ድሮ የነበረበት ጠንከራ ማንነቱ ከአሁኑ ውድቀቱ አንፃር ቢጠቀስ ::
👉ሀሰን አቱራቢ በዐቂዳው ሙልሂድ ነው::
👉የሀገራችን ኢኽዋኖች ከሚከተሏቸው መሪዎቻቸው መካከል አንዱ ነው::

👉ሰለፊይ ዑለማዎች አጥማሚዎችን እንዲህ አጋልጠው ኡማውን በአላህ ፈቃድ ታድገዋል ::

https://t.me/FATTAWAS

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

16 Dec, 19:27


🟡ሀቅ እና ወርቅ

ከሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ወርቃማ ንግግሮች

قال ابن تيمية
《…فَالْحَقُّ كَالذَّهَبِ ‌الْخَالِصِ، كُلَّمَا امْتُحِنَ ازْدَادَ جَوْدَةً، وَالْبَاطِلُ كَالْمَغْشُوشِ الْمُضِيءِ، إِذَا امْتُحِنَ ظَهَرَ فَسَادُهُ.》

አላህ የወደዳት
ወርቃማዋ እውነት
ስትፈተን በሳት
ዝቃጩን አራግፋ
ኮረፉን አረፋ
ጨለማውን ገፋ
ጠላት አሸንፋ
በተሻለ ሴራ
አስመሳይ ሲጣራ
ጥራቷን ጨምራ
እዩ ስታበራ
ሀቅን እንደወርቁ
ልባሞች እወቁ
ከባጢልም ራቁ

https://t.me/Abuhemewiya

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

16 Dec, 19:05


ሰ ለ ፍ ዮ ች

https://t.me/AbuImranAselefy/9509

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

15 Dec, 18:00


ዘወትር ቅዳሜ፣ እሑድ፣ ሰኞ እና ማክሰኞ ከፈጅር ሶላት  በኋላ የሚሰጠው

📚 ሪያዱ አስሷሊሒን ሚን ከላሚ ሰዪዲል ሙርሰሊን

✏️ የኪታቡ አዘጋጅ:- የኢማም አንነወዊይ

በሰአት የሚቀጥል ይሆናል።

🎙 ትምህርቱ የሚሰጠው  በአቡ ሐመዊያህ ሸምሱ ጉልታ (ሐፊዘሁላህ)



🕌 
አልኢስላሕ መድረሳ


አልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ። https://t.me/medresetulislah

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)

15 Dec, 11:22


አሁን በኡስታዝ አቡ ኡበይዳ


በጉራግኛ ቋንቋ




https://t.me/medresetulislah

11,487

subscribers

267

photos

35

videos