Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን) @almurachurchmembers Channel on Telegram

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

@almurachurchmembers

https://youtube.com/@alamurasdachurch?si=pjUXR_VrdYCln7JH

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን) (Amharic)

ጥያቄ: በአለም አቀፍ እና አስፈላጊ በትምህርት የተለያዩ መንፈሳዊ መረጃዎችን ከማከማች ተከታዮችና መስሪያዎችን ከእናቶች ሚስጥሮች ጋር በማህበረሰብ ለማሳካት የትምህርት ቤተሰብን መጠበቅ አልፈለጉም? አለም ዓርብ የተማሪ ሰዶምና አመት ሲፈጫቸውም የትምህርት ድንበር ላይ መነሳት ይችላል። የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤተሰብ ፣ ናባንዳንድ እና ገለፁ ግን በሀዋሳቸው ያሉት እና ላቀ እጁ። ሁለቱ መንገዶች በመስፈር በዚህ ቤተሰብ መላላጥ፣ ቅዱስ መታሰር፣ ደረጃ፣ መገለጫና ስነ ፋይት፣ ከነሐል፣ ከአካባቢና ከድምፅ በአማርኛ ተናጋሪ ቀላል መረጃዎች ይሁኑ።

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

16 Nov, 16:53

የአላሙራ 7ተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤ/ያን የ2025 G.c ምርጫ ለማካሔድ 7 አባላትን ያቀፈ #አስመራጭ_ኮሚቴን በዛሬው ዕለት ምዕመኑ መርጧል። በዚህም መሰረት:-
አቶ ስንታየሁ ነጋኦ
አቶ ሔኖክ ዱካም
አቶ ማቴዎስ ማርሳ
ወ/ሮ ዘነበች ሻሸጎ
ወ/ሮ አስቴር ዱካሞ
ወጣት ታመነ ተሾሜ
ወጣት አሳምነው ኤልያስ
ከሽማግሌ እስከ ወጣቶች እንደየቅድመ-ተከተላቸው ተመርጠዋል።

👉 አስመራጭ ኮሚቴ ማለት በቤ/ያን ውስጥ ለሚገኙ ከ18 ላለፉ ዘርፎች በ2025 G.C ላይ ዘርፎቹን ወክለው የምሰሩ የቤ/ያን ምዕመናን የምመርጡ ሲሆን፤ የቤተክርስቲያንቱን ምዕመናን፣ ወጣት ሽማግሌውን በተቻላቸው መጠን ሁሉንም የሚያውቁ ናቸው ተብሎ ይታሰባል።

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

14 Nov, 16:08

ሰንበት ቀን የሚኖረውን ምርጫ በተመለከተ...

ውድ ምዕመናን

የጌታ ሰላም በያላችሁበት ይብዛላችሁ

ባለፉት ሰንበታት ከመድረክ እንዳሳወቅናችሁ የፊታችን ቅዳሜ (ህዳር 7/2017 ዓ. ም) ቤተ ክርስቲያናችንን ለሚቀጥለው አንድ አመት የሚያገለግሉ ወገኖችን ምርጫ የሚያከናውኑ የቤ/ክ አባላትን ምርጫ እናከናውናለን ወይም ይህንን ስራ በእኛ ፈንታ ለሚያከናውኑ ብቁ ወገኖች ውክልናችንን እንሰጣቸዋለን።

ከቤተ ክርስቲያን መምሪያ ምዕራፍ 9 (ገፅ 177 ጀምሮ) ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከተፃፈው በጥቂቱ እናጋራችሁ።

"የአገልግሎት ዘርፍ ኃላፊዎች የሚመረጡት ለአንድ ወይም ለሁለት አመት ሲሆን የሚመርጣቸውም አስመራጭ ኮሚቴ ነው። ይህ ኮሚቴ ሪፖርቱን ወደ ቤ/ክ ይዞ ይመጣል። ቤ/ክንም በቀረቡት ስሞች ላይ ድምፅ ትሰጣለች።

"መራጭ ኮሚቴ የቤተ ክርስቲያኗን ፍላጎት ያጠናል። ግለሰቦችም በተለያዩ ዘርፎች ምን ያህል የማገልገል አቅም እንዳላቸው ያጤናል።

"በመራጭ ኮሚቴ አባልነት እንዲያገለግል መመረጥ ያለበት ቋሚ የቤ/ክ አባል ብቻ ነው። ይህም ሰው አመዛዝኖ መፍረድ የሚችልና የቤተ ክርስቲያኗ ደህንነትና ብልፅግና በልቡ ውስጥ ስፍራ ያለው መሆን አለበት።...ይህ ኮሚቴ በጥልቅ ፀሎት ስራውን ይጀምራል።"

በተቻለ መጠን አባላትን የሚያውቅና መክሊታቸውንም የተገነዘበ፤ በከፍተኛ ሁኔታ ምስጢር ጠባቂም መሆን ይኖርበታል።

እንዲህ ያሉ እግዚአብሔር ያያቸውን የሚያዩ እና በእምነትና በመንፈስ ብቻ የተሞሉ ወገኖችን መምረጥ የሚችሉ እነርሱም እንዲሁ የሆኑ አባላትን በዚህ ሰንበት እንመርጣለን።

አብዝተን እንፀልይ። አብዝተን እንፀልይ። አስበንም እንምጣ።

ጌታ ይባርካችሁ

*በፅሁፉ ላይ በወንድ ጾታ የተጠቀሱት ለሴቶችም የሚያገለግሉ እንደሆኑ በትህትና እንገልፃለን።

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

12 Nov, 08:12

Job vacancy

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

11 Nov, 04:06

መልዕክት ከስልጠናው አዘጋጅ:-

- ስልጠናው እንደሰልጣኞቹ ንቃት የሚወሰን ሲሆን እንደሁኔታው ከ1 ወር - 3 ወር ሊፈጅ ይችላል፤
- ስልጠናው ለቤ/ያንቱ መመስረት ዋና መሪ በሆኑት በ28ቱ መሰረታዊ እምነቶች ላይ ያተኮረ ነው፤
- ይህን ስልጠና ማንም መሰልጠን ይችላል፣
- የስልጠናው አዘጋጅ አቶ ሳሙኤል ባካሎ ናቸው
- ለሰልጣኞች በሙሉ ማስታወሻ ደብተር ተዘጋጅቷል
- በስልጠናው መጠናቀቂያ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሽልማት ተዘጋጅቷል
- ስልጠናው ለጊዜው እሁድ ክ9;00~12:00 የሚሰጥ ሲሆን እሮብ ደግሞ ከ12-1:30 ይሰጣል፣ በስምምነት ሌላም ቀን ይጨመራል።

እሁድ በነበረው የመጀመሪያ ቀን ስልጠና ላይ እንደመግቢያነት ከላይ በተነሱ ሀሳቦች ላይ የተወያየን ሲሆን እሮብ ምሽት ደግሞ ወደ ትምህርቶቹ ሙሉ በሙሉ ይገባል።

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

11 Nov, 04:05

ስልጠናው እሮብ ምሽት 12:00 ላይ ይቀጥላል።

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

11 Nov, 04:04

የስልጠናው አዘጋጅ አቶ ሳሙኤል ባካሎ

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

11 Nov, 04:03

በመጀመሪያ ቀን ስልጠና ላይ የተገኙ ወጣቶች እና ምዕመናን

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

10 Nov, 11:10

ማስታወቂያ_ለወጣቶች

ዛሬ እሁድ 9:00 ላይ የሚጀምረው ስልጠና እንደተጠበቀ ነው፤ባለፉት 2 ሰንበታት በቁጥር ከ100 የሚያልፉ ወጣቶች በተመዘገቡበትና የ7ተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤ/ያን 28ቱ መሰረታዊ እምነቶች ላይ ያተኮረው ስልጠና ዛሬ ጅማሮውን ያደርጋል፣ ስለዚህ ከ9 ሰዓት በፊት በቤ/ያን እንድንገኝ የስልጠናው አስተባባሪዎች ያሳስባሉ።

👉 11 ሰዓት ላይ በአቶ ዛዛ ጬቡ ቤት የማፅናኝ ፕሮግራም ስለምኖር የፕሮግራሞች መጋጨት እንዳይፈጠር በጊዜ እንገኝ።

📌 ስልጠናው የምደረገው በቤ/ያን ነው።

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

03 Nov, 04:24

ሰላም ቤተሰብ!

ትላንት በሀዋሳ ማረሚያ ተቋም የምትገኝ የሰ/ቀ/አ/ቤ/ክ በይፋ ስራዋን የጀመረች ሲሆን በጌታ ጸጋም የተባረከ ጊዜ በዚህች አጥቢያ ነበረን!

እስካሁን በነበረው ሂደትም በአንድም በሌላም አስተዋጽኦ ያደረጉ ወገኖችን በዚያ የተገኙ ወገኖች አብዝተው ባርከዋል።

በረከቱ ለሁላችሁም ይድረስ!

የሚከተሉትን ፎቶግራፎች በማየት እንድትባረኩ ፣ በቀጣይ እርስዎም ከቤተሰብዎ እንዲሁም ከቤ/ክ አገልጋዮችዎ ጋር ሄደው ወገኖችን የሚጎበኙበትን ፣ የሚያገለግሉበትን ጊዜ ከሚመለከታቸው የቤ/ክ መሪዎች ጋር እንዲያመቻቹ ፣ ጌታ ፈቅዶ ደግሞ ሄደው እስኪጎበኙ ድረስ በዚያ ያለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን የግንባታም ሆነ ሁለንተናዊ አገልግሎት ካሉበት ሆነው እንዲደግፉ በአክብሮት ቤ/ክ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

ተባረኩ!

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

21 Oct, 17:05

ቅዳሜ 3
የውዳሴ ኳየር የ16ተኛ አመት የምስረታ የምስጋና ፕሮግራም (ጥቅምት 2017)

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

21 Oct, 17:00

ቅዳሜ 2
የውዳሴ ኳየር የ16ተኛ አመት የምስረታ የምስጋና ፕሮግራም (ጥቅምት 2017)

Alamura Seventh Day Adventist Church , Hawassa (የሀዋሳ አላሙራ 7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን)

21 Oct, 16:54

ቅዳሜ 1
የውዳሴ ኳየር የ16ተኛ አመት የምስረታ የምስጋና ፕሮግራም (ጥቅምት 2017)