መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ @spritualbook12 Channel on Telegram

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

@spritualbook12


ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት በተለያየ ዘመን የተጻፉ መጽሐፍት እና ገድላት የሚያገኙበት ነው።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ (Amharic)

የመንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ ቻናል ስለሆነ ወደ ኢትዮጵያ የመጣና የማንኛውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ሊቃውንት ያቀረበው ዘመን ይጠቀምናል። ይህ ቻናል ከተጻፉ መጽሐፍትና ገድላት ለመጻፍ የሚያገኙበት ነው። የቻናሉን እና መጽሐፍያችንን ለማግኘት ይህን ቻናልን በቀላሉ ማስተማር ይኖርበታል። እንደዚህ እኛ የሚጠቀሙት ችግርዎችና መጽሐፍ ማስታወሻዎችን ለማግኘት ከቻናሉ ጋር እንዲያልፍ በማውጣት ምግብ እና ሥራ ለማግኘትን እና በቀላሉ ያግኙ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

09 Feb, 17:57


ጾመ ነነዌ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአጽዋማት ቀኖና መሠረት ሰባት የዐዋጅ ጾም አጽዋማት አሉ። ከሰባቱ አጽዋማት አንዷ በዕለታት ተወሳክና በዓመቱ መጥቅዕ ድምር ውጤት ወይም በመባጃ ሐመር የምትውለዋ ጾመ ነነዌ ናት።

ጾመ ሰብአ ነነዌ (የነነዌ ሰዎች ጾም) የምትጾመው ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ ፴፭ ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም፤ አይወጣም ማለት ነው፡፡ በዚህም ቀመር መሠረት የ፳፻፲፯ ዓ.ም ጾመ ነነዌ የካቲት ሦስት ጀምሮ በአምስት ያበቃል፡፡

ጾመ ነነዌን የጾሙት በነነዌ የሚኖሩ ሰዎች በአምላካችን እግዚአብሔር ትእዛዝ እና በነቢዩ ዮናስ ነጋሪነት ነው፡፡ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት አምላካችም ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ እንዲሄድ አዘዘው፡፡ (ዮናስ. ፬፥፲፩)

እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” ብለው ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑም ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔርን የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ፣ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡

ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ፤ (ዮናስ ፩ እና ፪)፡፡ መጀመሪያ ከተልእኮው ቢያፈገፍግም “ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፦ በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ” እንደተባለው ነቢዩ ዮናስ የኋላ ኋላ ወደ ነነዌ ሄዶ የእግዚአብሔርን መልእክት ዐውጇል። (ዮናስ ፴፫፥፬) በዚያን ጊዜ የነበሩት ሰዎችም እንዲህ አደረጉ፤ “የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ” (ቁጥ.፭) እንዲል፡፡

መጽሐፉ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር እንደማራቸው ይገልጻል፡፡ (ዮናስ ፫) ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አምላካችን ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ (ዮናስ ፬) ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም ለቅጣት የመጣው እሳት እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቅ ዛፎች ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ የእሳቱ ወላፈን ነክቷቸው ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ በንስሐ በጾምና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀው ከጥፋትና መዓት ድነዋል።

እኛንም ካለንበት መከራ፣ ችግርና ሥቃይ እንዲያወጣን፣ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲያኖረን እንደ ነነዌ ሰዎች ንስሐ እንግባ፤ በጸሎት፣ በጾምና በበጎ ምግባር ተወስነን በሃይማኖት እንጽና! 

አምላካችን እግዚአብሔር ቸርነቱን ያብዛልን፤ አሜን!

ከማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ የተወሰደ

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

29 Jan, 04:30


እንኳን ለእመቤታችን ዓመታዊ ክበረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

እንዲሁም በነገው እለት በጅማ ደብረ ኤፍርታ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ይመረቃል እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ይህ ድርብ በዓል ነው ለእኛ ኦርቶዶክሳዊያን

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን

” አስተርእዮ ማርያም “

አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።

ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።

ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ

ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።

ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው ። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።

የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።

ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ከመ ትንሳኤ ወልዳ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።

ሰአሊ ለነ ቅድስት

የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን።
መልካም በዓል

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

20 Jan, 10:40


ቃና ዘገሊላ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጥር ፲፪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በተደረገ ሠርግ ቤት ያደረገውን ተአምር በማሰብ በዓልን ታደርጋለች፡፡ ጌታችን ከጥምቀቱ በኋላ በዶኪማስ ሠርግ ቤተ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታጋብዞ በነበረበት ጊዜ ለእንግዶች ወይን ጠጅ አለቀባቸው፡፡

በዚህም ጊዜ “እናቱ ጌታችን ኢየሱስን የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱም “ አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም” አላት፡፡ እናቱም ለአሳላፊዎቹ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው፡፡ በዚይም እንደ አይሁድ ልማድ የሚያነጹባቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፡፡ ከእነርሱም እያንዳንዱ ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስም “ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው” አላቸው፤ እስከ አፋቸውም እስከ ላይ ሞሉአቸው፡፡ አሁንም ቅዱና ወስደውም ሰጡት፡፡ አሳዳሪውም ያን የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ፤ ከወዴት እንደመጣም አላወቀም፤ የቀዱት አሳላፊዎች ግን የወይን ጠጅ የሆነውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር፡፡ ውኃውን የሞሉ እነርሴ ነበሩና፡፡ አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ “ሰው ሁሉ መልካሙን የወይን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል፤ ከጠገቡ በኋላም ተርታውንም ያመጣል፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስከአሁን አቆየህ” አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም በቃና ዘገሊላ ያደረገው የተአምራት መጀመሪያ ይህ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርትም አመኑበት፡፡ (ዮሐ.፪፥፩-፲፩)

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤ አሜን፡፡

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

18 Jan, 06:39


ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

17 Jan, 11:22


የሥራ ማስታወቂያ አነስ ላለች ምግብ ቤት።

ልምዱ እና ሙያው ያላችሁ እድሉን ተጠቀሙበት ።የሥራ ቦታው አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ።
1) ሼፍ በዛት 1
2) ረዳት ሼፍ ብዛት 1
3)አስተናጋጅ ብዛት 2
4) ባሬስታ ብዛት 2
ለሁሉም የሥራ ቅጥር አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ልምድ ያለው ።
ደሞዝ በስምምነት
ሙያው ያላችሁ በዚህ ቴሌግራም t.me/spritual23 የሙያ ልምዳችሁን ላኩልን ።ወይም በዚህ email [email protected] ብለው ይላኩ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

15 Jan, 00:24


ጥር ፯(7)
አጋእዝት ዓለም ሥላሴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡

የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።እግዚአብሔርም አለ።‹‹ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።››እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ከተማይቱንም መሥራት ተው።ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ።እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። (ዘፍ.፲፩፥፩-፱)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹ኑ እንውረድ›› ባሉት መሠረት ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሦስት መሆናቸው እንረዳለን፤ የስም ሦስትነታቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ የግብር ሦስትነታቸውስ ደግሞ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ የመሆኑ ምሥጢር ነው፤ የአካል ሦስትነታቸው ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ስላላቸው ነው፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመሆኑ የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን? የሚል ጥይቄ የተነሣ እንደሆነ መልሱ‹‹አዎ፤ እንደ ሰው ነው›› ይሆናል፤ ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው፤ የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ በሰማይና በምድር፣ በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ሕያው ባሕርይ ነው፡፡‹‹ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው››እንዲል፤ (ኢሳ.፹፮፥፩-፪) የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ ወዘተ በመሳሰሉት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

13 Jan, 17:09


+ከአእላፋት ማግስት+

Credit: ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው (@yohannes_getachew1)

''ይሄን ስእል እያመለክሽ ነው ሳታገቢ የቆየሽው በጌታ በእየሱስ ስም መንፈስሽን ወጋሁት''

እናቴ ናት በጠዋት እንዲህ የምትለው። አሁንማ ገና እየደረሰ በመሆኑ፥ አእላፋት ዝማሬ ብቻ ሆኗል ወሬው እሱ ይረብሻታል።

ስለ እናቴ ትንሽ ላውራቹህ...

ኤልሳ ትባላለች። ሲበዛ ተጫዋች፥ ረጅም፥ በጣም ቀይ፥ ስትስቅ ጥርሷ የሚያምር፥ በዛ ላይ ዲምፕል ያላት ውብ ናት። አባቴ ደግሞ ሱራፌል ይባላል፤ ዲያቆን ነበር። በእርግጥ እኔ 16 አመቴ እያለ ነው የሞተው። ሰዎች ስለ እርሱ አውርተው አይጠግቡም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፥ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፥ ጸሎተኛ ነበር ፤ መምህሩ ሲቀሩ እርሱ ነበር ጉባኤ ዘርግቶ የሚያስተምረው። ሁሉም ነበር የሚወደው። እኔን ራሱ ውዳሴ ማርያም፥ ዳዊት፥ ቅዳሴ፥ ሰዓታት አስተምሮብኛል። '

'ሰበኔ... ሴት ሆንሽብኝ እንጂ አንቺን ዲያቆን ነበር የማደርግሽ'' የሁል ጊዜ ንግግሩ ነበር።

እናቴ አባቴ በእግዚአብሔር ላይ ያለው መተማመን ይገርማታል። እኔ ልክ 15 አመት ሲሆነኝ አባቴ በጠና ታመመ። የሳንባ ካንሰር ያዘው። ከቤት መውጣት ከበደው፤ ቀኑን ሙሉ የሚያሳልፈው አልጋ ላይ መጽሐፈ መነኮሳትን እያነበበ ነበር። ትንሽ ህመሙ ባስ ሲልበት ደግሞ መጽሐፉን ደረቱ ላይ አድርጎ ለሰአታት መተንፈስ የከብደው ነበር። ከእርሱ ህመም በኋላ ቤታችን ውስጥ ሳቅ የሚባል ጠፋ። እናቴ ቀይ ፊቷን ማድያት ወረሰው።

.......የሆነ ማክሰኞ ቀን ጠዋት ላይ ''ኡኡኡኡኡኡኡኡ'' የሚል ጩኸት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። እናቴ ነበረች። ብርድ ልብሱን ከራሴ ላይ በስርአት ሳላወልቅ ሮጥኩኝ። ኤልሲ አባቴን አቅፋ ፥-

"ጌታዬ ጉድ አታድረገኝ ባክህ ጉድ አታድርገኝ"

"እማ አባቴ ምን ሆነ?" ......እምባዬ ከየት እንደመጣ አላውቅም። ፊቴ ርሷል...

"የልጀነት ፍቅሬ ኧረ ተው" ትላለች።

"እማ አባቴ ምን ሆኗል?!"

"ጉድ አረከኝ! ብቻዬን ለማን ጥለከኝ! ኧረ ያላንተ አይሆንልኝም! ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ"

ጩኸታችንን የሰሙ ጎረቤቶቻችን ቤታችንን ሞሉት። በአንዴ ግማሹ ቲቪ ይሸፍናል፥ ግማሹ ስለ ድንኳን ያወራል......ራሴን ሳትኩ፤ ስነቃ ቀብር ሊሄዱ ህዝብ መጥቷል። ቤቱ ውጪው ግጥም ብሏል። ያ ሁሉ ህዝብ አንድ አባቴን አልሆን አለኝ.....

አባቴ ካረፈ ጊዜ ጀምሮ ቤታችን የማይቀሩ የማይቀሩ 3 ሰዎች ነበሩ። እነዚህ የእናቴ የስራ ባልደረቦች ታዲያ በመጡ ቁጥር ለእናቴ እንፀልይልሽ ብለዋት ነው የሚሄዱት፤ የሆነ ቀን ላይ ከታናናሾቼ ጋር ጸሎት እያደረግን "ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቤት ሃይማኖት ተቀይሯል!" አለችን።

"ወደምን?" አልን

"ጌታን ተቀብለናል! ነገ ትጠመቃላችሁ። አቁሙ አሁን!"

"እንዴ ኤልሲ! እኛ እኮ ልጅ እያለን ተጠምቀናል"

"አንቺ ልጅ! ተናገርኩ በቃ!"

"አልቀይርም! አባቴ ያስተማረኝ ያወረሰኝ ነው፤ አልቀይርም!" አልኩ።

ኤልሲም መልሳ "ነው? ከሆነ ከቤቴ ውጪ! እናንተም እንደዛ ነው?

ታናሽ እህቴም አዎ አለች።

"ውጡ! ችግር እና ረሃብ ሲፈራረቅባችሁ ትመጡ የለ!" አለችን በቁጣ።

ስልኬን አንስቼ ለአያቴ ደወልኩ። አያቴ ብቻዋን የምትኖር፥ በጣም ትልቅ ጊቢ ያላት፥ እሱ ላይ ወደ 20 ምናምን ቤት ሰርታ የምታከራይ ሴት ናት። ስደውል ኑ ኧረ ኑ አለች

......... እናቴ ሃይማኖቷን ቀየረች። ሁሉንም እኛ ክፍል የነበረ ስእለ አድኅኖ አውጥታ አቃጠለች። የአባቴን ግን ከበዳት። የእርሱን ዳዊት፥ የጸሎት መጻሕፍት፥ ሁሉን ነገሩን በአንድ ላይ አድርጋ አንድ ክፍል ውስጥ ቆለፈችበት። እኛም አያታችን ጋር መኖር ቀጠልን።

---------------------------------------------------

እናቴን ሃይማኖቷን ያስቀየሯት ሰዎች Theology እንድትማር አደረጉና ፓስተር ሆነች ።

ዛሬ...

"እሺ ባክሽ... አእላፋት ምናምን እያላችሁ ነው ደግሞ በነጭ ልብስ ጣኦት ልታመልኩ"

"ተይ እንጂ እማዬ... የማይሆን አትናገሪ። ለምን ዛሬ አብረን አንሄድም?"

"ማን? እኔ? ሆሆሆሆሆሆሆሆ... ሥራ አልፈታሁም"

"ምን ችግር አለው? ከደበረሽ ቶሎ እንወጣለን።"

"ቆይይይይይ እሄዳለው። የምሄደው ግን እንዴት ልክ እንዳልሆናችሁ ላሳይሽ ነው!"

ሁላችንም ለባብሰን ወጣን። በጊዜ ነበር የደረስነው፤ ቦሌ መድኃኔዓለም ሞልቷል። እንደምንም ብለን ፊት ተጠጋን። ዲያቆኑ "እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ" ይላል። ቁርጥ የአባቴን ድምፅ! ኤልሲ ደነገጠች። አባቴን ያየችው መስሏት ተንጠራርታ ፈለገችው፤ የለም። የሚፀየውን ጸሎት በግእዝም በአማርኛም ስታየው ቆየች። እምባዋ ይፈስ ጀመር። ጸሎቱ ተጠናቆ ነጫጭ የለበሱ ዘማሪያን መድረኩን ሞሉት። መዝሙር ቀጠለ። ቸሩ ሆይ የሚለው መዝሙር ዘማሪዎቹ መዘመር ጀመሩ። የአባቴ የሚወደው መዝሙር ነበር። የሲቃ ድምጽ አውጥታ አለቀሰች። አሳዘነችኝ ደስም አለኝ። መዝሙሩ አለቀ። በአባቶች ብራኬ ተጠናቀቀ። ኤልሲ ሙሉ ሰአት እያለቀሰች ነበር ።

"ኤልሲዬ በቃ አንቺ ሂጂ፥ እኛ እናስቀድሳለን።"

"ልምጣ?"

"የምርሽን ነው?"

"አዎ ልምጣ"

"ነይ" ድንጋጤዬ ያስታውቃል።

ማህሌቱ አልቆ፥ ቅዳሴው አልቆ፥ ቤት ገባን። እኛ ቤት ከመጣሁ 10 አመት አልፎኝ ነበር። ያው ነው፥ ምንም አልተቀየረም። እናቴ ሮጣ ጸሎት ቤት ገባች። ሁሉ ነገሩ አባቴን አባቴን ይላል። ትልቅ የእመቤታችን ምስለ ስዕል ፊት ወድቃ አለቀሰች።

"ሰበኔ አሁን ገባኝ! ልቤ ተሰብሬ ሲያገኙኝ ዓለም ገደል ስትሆንብኝ አግኝተውኝ ነው! ልጆቼ ይቅር በሉኝ! በጎደለኝ በኩል ሲቆሙ ወዳጆች መሰሉኝ ......"

ተቃቅፈን ተላቀስን። ምን ተረዳሁ መሰላችሁ? እግዚአብሔር ስራው Mysterious ነው። እንዲህ ነው ብለን Define የማይደረግ። ዛሬ ላይ ቤተሰቤ ሙሉ ሆኗል፤ እናቴም ወደ ክርስትና ለመመለስ ትምህርት ለመማር ከመምህሬ ጋር አገናኝቻለሁ። ከ 10 ዓመት ከብዙ ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ። እጆቼን ከፍ አድርጌ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ...

"የእኔን እምባ ያቆምክ እግዚአብሔር... እምባቸውን ለሚያወጡ ድረስ" ብዬ። "ሰላም ለናፈቁ ሁሉ ሰላም ስጥ። አባቴ የደከሙ ልቦችን አሳርፍ፥ ፈገግታን የናፈቁን ሁሉ ሳቅ አጥግብ፥ ለደስታ የተግደረደሩትን ሁሉ አላምዳቸው ...ባለቀሱበት ቦታ እንባቸውን አብስ። ሁሉን ቻይ ሆይ፥ የመዳናቸውን ቀን አታርቅ።"

ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው (Instagram: - @yohannes_getachew1)
ጥር 1 / 2017

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

12 Jan, 09:00


እንኳን ለወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ በዓል አደረሰን ጥር 4 ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት ቀን ነው።

ዮሐንስ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በሕይወትም በኑሮም ጌታ ስለሚመስል (ፍቁረ እግዚእ) ይባለል። ነገረ መለኮትን በበለጠ ከሌሎች አምልቶ አስፍቶ በጥልቀት በማስተማሩ ነባቤ መለኮት (ታዖሎጎስ)ተሰኝቷል። ስለጌታም ባለው ቅናት ባሳየው የኃይል ሥራ በኦኔርጌስ (ወልደ ነጎድጓድም) ተብሏል። ፍጥሞ በምትባል ደሴት በራዕይ መጻእያትን በመግለጡ ባለራዕይ (በግሪክ አቡቀለምሲስ) ይባለል። በዕለተ ዓርብ በመስቀል ሥር ተገኝቶ የጌታን መከራ መስቀል በማየቱ ፊቱ በሀዘን ስለተቋጠረ ቁጽረ ገጽ (ፊቱ በሀዘነ የተቋጠረ) ስምም ተሰቶታል። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የፋሲካን እራት ያዘጋጀ አንካሳን የፈወሰ ታለቅ ሐዋርያ ነው። (ሊቃስ 22፡8) እስከ መስቀል አምላኩን ተከትሎ እመቤታችንን በአደራ የተረከበ ባለአደራ ሐዋርያ ሲሆን ከጰራቅሊጦስ በዓል በኋላ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋራ በኢየሩሳሌም በአንጾኪያ በሎዶቅያ በእስያ ከተሞች በተለይ በኤፌሶን በአሁኑ ቱርክ አስተምሯል። (ዮሐ.19፡26) በወጣትነት ዕድሜው ተጠርቶ በዕለተ ዓርብ የጌታን መከራ እያሰበ ያነባ የነበረ በፍቅር በታማኝነት እስከመጨረሻ ድረስ የጸና ከጌታ ያልተለየ ወንጌላዊ ሲሆን ወንጌልን ጨምሮ 3 መልዕክታትን የጻፈ እንዲሁም በፍጥሞ ደሴት ራዕይ የጻፈ ታላቅ ሐዋርያ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ በንሥር መልክ ይመሰላል። ይህም ንሥር በእግር እንደሚሽከረከራና በክንፍ መጥቆ እንደሚበር ሁሉ ይህ ሐዋርያም እንደሌሎቹ ወንጌላውያን የአብን ልጅ ከሰማየ ሰማያት መውረድ፣ ከድንግል ማርያም መወለድ መከራ መቀበል፣ መሰቀል፣ መሞት፣ ትንሣኤውን እንዲሁም ዕርገቱን ጽፏልና። ንሥር በክንፉ መጥቆ እንዲበር ዮሐንስ ከሌሎቹ ወንጌላውያን ለየት ብሎ አካል ከህልውና ተገልጾለት የቃልን በቅድምና መኖር፣ እንዲሁም የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ጽፏል። ቅዱስ ዮሐንስ በኢየሩሳሌም፣ በአንጾኪያ፣ በሎዶቅያ፣ በእስያ ከተሞች በተለይም በኤፌሶን ወንጌልን አስተምሯል፡፡

ከወንጌላዊው፣ ከሐዋርያው፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ረድኤትና በረከት ይክፈለን አሜን። !!!

በቅርቡ ከሕትመት የወጣውን ታረከ ነገሥት መጽሐፍ ቴሌግራም t.me/spritual23 በመጠቀም መዘዝ ይችላሉ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

10 Jan, 18:39


የኅትመት ብስራት ዜና
ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ለመጀመረያ ጊዜ ገድለ አቡነ ጸጋ ዘአብ ወእምነ እግዚእ ኃረያ ወገድለ አቡነ ታዴዎስ ገድል ታተመ ።

እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ ኀሳቡም ለተጠሩት የልጁን መልክ እንዲመስሉ ወስኖአልና የወሰናቸውንም ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም አጸደቃቸው፤ እነዚኽን ደግሞ አከበራቸው። ሮሜ 8፡28።

በነጻይቱ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ብዙ ቅዱሳን ተወልደው እግዚአብሔርን የተከተሉና ያገለገሉ፤ ቅዱስ ወንጌልን ለዓለም ያስተማሩ፤ ሕዝብን በሕይወት መንገድ የመሩ ብዙ ቅዱሳን ናቸው። ከእነዚኸ መካከልም አባታችን ጸጋ ዘአብና እናታችን ብፅዕት እግዚእ ኀረያ ይገኛሉ።

ካህኑ ጸጋ ዘአብና ብፅዕት እግዚእ ኀረያ በሸዋ ቡልጋ ውስጥ በጽላልሽ አውራጃ በዞረሬ ተወልደው እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡናቸው በማገልገል ምድራዊውን መልአክ ሰማያዊውን ሱራፊ አባ ተክለ ሃይማኖትን ወልደዋል።
በሀሁ መጻሕፍት መደብር ጥቂት ኮፒዎች አስገብተናል
==============================

ሀሁ መጻህፍት መደብር ለረጅም አመታት በቀድሞ ሜክሲኮ መደብሩ እና በስቶር ተቀምጠው የነበሩትን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ መፅሐፎቹን አራት ኪሎ አብርሆት ቤቱመፅሐፍት አጠገብ በሚገኝው መደብሩ በታላቅ የመጻሕፍት ቅናሽ እና የማጣሪያ መሸጥ ጀምራል::

በዚህ የማጣሪያ ሽያጭ ከፍተኛ ቅናሽ የተደረገባቸው መፅሐፎች በተለይ ከታተሙ 2፣ 5፣ 10 ወይም ከዚያ በላይ አመታት የሆናቸው የታላላቆቹ ደራሲያንና የታሪክ ፀሐፊያንንመጻሕፍት በብዛት ይገኛሉ::እንዲሁም

የትምህርት መርጃ መጻህፍት፣
የልብወለድና የታሪክ መጻህፍት፣
መንፈሳዊና አለማዊ መጻህፍት፣
የግጥምና የወግ መጻህፍት፣
የፖለቲካና ኢኮኖሚ መጻህፍት፣
የፍልስፍና እና የስነልቦና መጻህፍት
ከ20—50% ቅናሽ ታገኛላችሁ ።

ያስታውሱ

* አንድ መጽሐፍ ከ50 ብር እስከ 100 ብር ብቻ ባለው ዋጋ መፅሐፍት ይሸጣሉ::
* በቅናሽ የሚሸጡ ከገበያ የጠፉ መፅሐፍትን ያገኛሉ!!!
* አስር መጽሀፍ ለሚገዙ ደንበኞቻችን ደግሞ አንድ መጽሀፍ በነጻ ያበረክታሉ ።

ይህ የቅናሽ የመፅሐፍ ሽያጭ ለተወሰኑ ቀናት ብቻ የሚቆይ ነው:: የዚህ ቅናሽ የመፅሐፍ ሽያጭ እንዳያመልጣችሁ::

#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር

አድራሻ :- አራት ኪሎ አብርሆት ቤቱመፅሐፍት አጠገብ
ስልክ ቁጥር:-
0911006705/0924408461

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

02 Jan, 13:58


    ድንቅ እይታ
ከሀሁ መጽሐፍት መደብር የተወሰደ።
  
መድሎተ ጽድቅ።

መድሎተ ጽድቅ የሚሞግተውን ሐሳብ የፍልስፍና መነሻ በመቆፈር ስለሚነሳ በቅርንጫፍ ከመንጠላጠል ያድነናል፡፡ ለተጨማሪና ዘርፈ ብዙ ንባብ ይጋብዛል፡፡ በአቀራረብ ጥልቀቱ ከሃይማኖት ክበብ ውጪ ያለ ልበ ሰፊ ሰውም ሊያነበው የሚችል ጭብጥና አቀራረብ አለው፡፡ ‹‹የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ አስተምህሮ /እምነትና ሥርዓት/ እንዲህ ነው!›› ብሎ ደንግጎ ለመነሣት የሚፈልግ የሌላ እምነት ወይም ዓለማዊ ጸሐፊ ሊያጣቅሳቸው ከሚገቡ መጻሕፍት ውስጥ የያረጋል አበጋዝ መድሎተ ጽድቅ ተከታታይ መጻሕፍት አስፈላጊ እንደሆኑ ይሰማኛል፡፡ እንደ ተለመደው ያረጋል የያዘውን ርእስ ያደማል፣ አቀራረቡ ኦሪጅናል ነው፣ ለወደፊት ጸሐፍት መነሻና ማጣቀሻ መሆን ይችላል፣ ክርክራዊ አቀራረቡ ፍሰት አለው፡፡ ቃል ይተረጕማል፣ ያራቅቃል፡፡ ዐውድ ይጠብቃል፤ ከጭብጥ አይወጣም፡፡ ለማስረጃዎች ተገቢነት ትኩረት ይሰጣል፤ ማለትም ጥቅስና የታሪክ ማስረጃ ሲያቀርብ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነና አስፈላገነት ያለውን ነው፡፡ ያረጋል አበጋዝ አያመቻምችም! በዓለም ላይ የሚዋልሉ አሁናዊ ሐሳቦችን ለአንባቢ ውሳኔ ክፍት አድርጎ በምንታዌ አይተዋቸውም፡፡ አዙሮ አሽከርክሮ ኦርቶዶክሳዊውን እይታ ግን እንዲህ ነው ይለናል እንጂ፡፡ የያረጋል ቸርነት ለግል ውሳኔ መንገድ በመክፈት ሳይሆን በመጽሐፉ ዋጋ ነው የሚገኝ፡፡ ከይዘቱ፣ ከማጣቀሻው ብዛት፣ ከወሰደው ጊዜ፣ ከኅትመቱ ጥራት፣ ከመጻሕፍቱ ተፈላጊነት፣ ከጸሐፊው ልፋትና ማንነት (ፕሮፋይል) አንጻር በቤተ ክርስቲያን ጸሐፍት ከሚጻፉ መጻሕፍት ውስጥ በርካሽ እያነበብን ያለነው ያረጋል አበጋዝን ይመስለኛል፡፡

📚📚📚

#የሀሁ_መጽሐፍት_መደብር

አድራሻ  ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
              ስ.ቁ  0911006705/0924408461

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

02 Jan, 03:44


በዚህች እለት አቡነ ተክለሃይማኖት ልደታቸው ነው ።

ኢትዮጵያ የብዙ ቅዱሳን ሀገር ነች።ከእነኝህ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንዱ ናቸው።አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእግዚአብሔር ድንቅ ጥበብ፣ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት፤ በኢትዮጵያ ምድር በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ልዩ ስሙ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ፤ አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤›› በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡

አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ ብዙ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንንም አንጸዋል፡፡ ‹ሐዲስ ሐዋርያ› የተባሉትም በዚህ ተልእኳቸው ሲሆን፣ ትርጕሙም ሐዲስ ኪዳንን ወይም ሕገ ወንጌልን እየተዘዋወረ የሚያስተምር ሰባኬ ወንጌል፤ በክርስቶስ ስም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን የሚደርግ የክርስቶስ ተከታይ (ሐዋርያ) ማለት ነው፡፡

አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው፣ በብሕትውና ኖረዋል፡፡በተጨማሪም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፣ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው።

ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን።
መልካም በዓል።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

30 Dec, 13:19


የበዓል ጥቅል

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

28 Dec, 04:00


ለገና በዓል ሀሁ መጽሐፍት መደብር ልዩ የበዓል ሥጦታ አዘጋቷል። ብቅ ብለው ይጎብኙ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

28 Dec, 04:00


https://vm.tiktok.com/ZMkk3mrsf/

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

27 Dec, 18:29


ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረዳቸዋል፡፡ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ በስደት ሲሰደድም ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው፡፡ (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)

ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ›› እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፱)

ቅዱስ ገብርኤል ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤ ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት፤ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል››እንዲል (መዝ.፺፩፥፲፩)፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል››(መዝ.፴፬፥፩)፤ ‹‹በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡››(ዘጸ.፳፫፥፳)

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብረ በዓሉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን መላእክትን ወርኃዊ እና ዓመታዊ በዓላቸውን በጸሎት እና በምስጋና ታከብራለች፡፡ በተለይም ታኅሣሥ ፲፱ ቀን የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በዓል የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አግብርተ እግዚአብሔር አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከእቶነ እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በግእዝ የተጻፈው መጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ትማልም አሲረነ ሠለስተ እደወ ወደይነ ውስተ እቶነ እሳት ዮምሰ እሬኢ አርባዕተ እደወ እንዘ ያንሶሰዉ ማዕከለ እሳት ፍቱሐኒሆሙ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብሔር ይመስል››፤ ትናንት ሦስት ሰዎች አስረን ከእሳቱ እቶን ጥለን ነበር፤ ዛሬ ግን ዐራት ሆነው ከእሥራታቸው ተፈትተው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ፤ ዐራተኛውም የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል፤ በማለት ይገልጸዋ፡፡ (ወዲያውም ከእቶኑ ሂዶ‹‹ አንትሙ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብድናጎ አግብርተ እግዚአብሔር ንዑ ፃዑ ዝየ፤ ኑ ውጡ›› አላቸው ብር ብር እያሉ ከእሳቱ ውስጥ ወጥተዋል፤ በልብሳቸው ላይም ጥላሸት እንኳን አልተገኘም፤ ናቡከደነጾርም ይህን አይቶ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፤ ንጉሡም አዋጁን በአዋጅ መልሶ ለሕጻናቱ በሹመት ላይ ሹመት በክብር ላይ ክብር ጨምሮላቸዋል)፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት እና ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር፤ አሜን፡፡

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

27 Dec, 18:29


እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

እንኳን ለታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

በዲያቆን ዘአማኑኤል አንተነህ

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለርዳታ የሚደርስ፣ በጨለማ እና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ ‹‹ይወርዳል ይወለዳል›› በማለት በየወገናቸው እና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት ያስፈጸመና የምሥራችን ቃል የተናገር፣ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል ከእፉኝት መርዝ የከፋ በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብሩ

ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሁል ጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ነው፤ በተለይም ስለ ልደተ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋና እና የክብር ሰላምታ ያበሠረ በመሆኑ ‹‹አብሳሬ ትስብእት (መልአከ ብሥራት) መጋቤ ሐዲስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ አምላካቸውን ለማወቅ ‹‹መኑ ፈጠረነ›› እያሉ ሲባዝኑ ሳጥናኤል ‹‹እኔ ፈጠርኳችሁ›› ሲል ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን አምላክ እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንቁም እንጽና፤ ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ (አክሲማሮስ. ገጽ.፴፭) በዚህም አባቶቻችን እንደሚሉት መልአኩን የመጀመሪያው የተዋሕዶ ሰባኪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ መልአክ ነውና፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታ ‹‹ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም፤ድንግል ማርያምን ያበስር ዘንድ የተገባው ሆነ›› እንዲል፤ ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር አድሎታል፤ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክት እና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ካህናት አባቶች እንደሚሉት ስእለት ሰሚ እንዲሁም ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በሀገራችንም ክብረ በዓሉ በቁልቢ ገብርኤል እና በተለያዩ ቦታዎች እጅግ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ይከበራል፡፡

የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደ ምትወደው በድርሳነ ገብርኤል ላይ ተጽፏል፤ ‹‹ርእዩኬ አኃዊነ ዘከመ ታፈቅሮ እግዝእትነ ማርያም ለቅዱስ ገብርኤል እምኲሎሙ መላእክት እስመ አብሠራ ልደተ ወልድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወውእቱ ከመ ያፈቅራ ወይረድኣ በጊዜ ምንዳቤሃ ለነኒ ይርድአነ በጊዜ ምንዳቤነ፣ ወንድሞቻችን ሆይ፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና›› እንዲል፡፡ (ድርሳነ ገብርኤል ዘኅዳር ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፲፫)

ቅዱስ ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእዩ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡›› (ራእ.፲፰፥፩)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ›› እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ (መዝ.፻፫፥፬)

ቅዱስ ገብርኤል ኃያል መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ›› በማለት መስክሯል፡፡ (ራእ.፲፥፩)

ቅዱስ ገብርኤል የመላእክት አለቃ ነው፤ በራማ በሠፈሩት ዐሥሩ የነገድ ሠራዊት ላይ የአርባብ አለቃ ነው፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ‹‹በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት የራማው መልአክ ተብሎ ይጠራል፡፡ (ሄኖክ.፲፥፲፬)

ቅዱስ ገብርኤል ፈጣን መልአክ ነው፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሉት በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ስቅለት ጊዜ በመስቀል ላይ የደረሰበትን መከራ አይቶ አላስችለው ቢል ሰይፍ ወርውሯል፤ ‹‹ዓለምም የሚያልፈው ቅዱስ ገብርኤል የወረወረው ሰይፍ ሲያርፍ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መልኩም ሰይፍ እንደወረወረ ከዚህ በታች በተጻፈው መልኩ እንገነዘባለን ይኸውም፡-

ሰላም ለሰኰናከ ወለመከየድከ ክልኤ

ታሕተ ዐውደ መስቀል ዘቆማ በዕለተ ድልቅልቅ መውዋዔ

ሰይፈ ቁጥዓ ገብርኤል ዘመላኅከ ቅድመ ጉባኤ

አንስትሰ ሶበ ሰምዓ ቃለ ዚኣከ በቋዔ

ኀበ ሐዋርያት ሖራ ይንግራ ትንሣኤ

ትርጉም፡- ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡

በሀገራችን በተለምዶም ‹‹ሚካኤል እንደአየህ ገብርኤል እንዳያይህ›› የሚባል አባባል አለ፤ ይኸውም የመልአኩ ተራዳኢነት እንዳለ ሁኖ ተነግሮ ለማይሰማ አካል ግን መልአኩ ፈጣን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማ እና የምናይ ሲሆን ለምሳሌም ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ቃል ባለመስማቱ (ባለመቀበሉ) ዲዳ ሁኗል፡፡በተጨማሪም በኢ-አማንያንም ዘንድ ሳይቀር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይፈራል፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፩)

ቅዱስ ገብርኤል እና ተራዳኢነቱ

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

26 Dec, 06:56


  የገና ስጦታ 🧧🧧🧧

ለገና ስጦታ ለወዳጅ ዘመድዎ የሚሰጡት የመጽሐፍ በፓኬጅ አዘጋጅተናል።ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መረጠው ለወዳጅዎ መስጠት ይችላሉ።

1ኛ 15 መጽሐፍ
፩ መጽሐፈ አቡሻክር
፪ አሐቲ ድንግል
፫ መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 1እና2
፬ ኵክኀ ሐይማኖት
፭ መድሎተ አሚን
፮ ታሪከ ነገሥት
፯ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
፰ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ
፱ ስንክሳር የመሰከረሙና የመጋቢቱ ሁለቱንም።
፲ የብርሃን እናት
፲፩ ኅብረ ሥርዓት
፲፪ ኦሪት ዘፍጥረት
፲፫ ሕይወተ ወራዙት

2ኛ  12 መጽሐፍ

፩ ኵክኅ ሐይማኖት
፪ መድሎተ አሚን
፫ ምጽዓት ክርስቶስ
፬ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
፭ ታሪከ ነገሥት
፮ መጽሐፍ አቡሻክር
፯ መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 1እና2
፰ ኅብረ ሥርዓት
፱ አሐቲ ድንግል
፲ ሥርዓት ቅዳሴና ምሥጢራዊ ማብራሪያው
፲፩ ኦሪት ዘፍጥረት

3ኛ   10 መጽሐፍ
፩ መዝሙረ ዳዊት ትርጓሜ
፪ ኅብረ ሥርዓት
፫ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
፬ ታሪከ ነገሥት
፭ ሥርዓተ ቅዳሴና ምሥጢራዊ ማብራሪያው
፮ መጽሐፈ ምንኃር
፯ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ
፰ አሐቲ ድንግል
፱ መድሎተ አሚን
፲ ኰኵሐ ሐይማኖት

4ኛ   8 መጽሐፍ
፩ ኰኲሐ ሐይማኖት
፪ መድሎተ አሚን
፫ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
፬ ታሪከ ነገሥት
፭ ስንክሳር የዓመቱ
፮ መድሎተ ጽድቅ 1እና2

5ኛ   5 መጽሐፍ
፩ ሕይወተ ወራዙት
፪ መዋዕያን
፫ መጽሐፈ ምንኃር
፬ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
፭ ታሪከ ነገሥት

6ኛ   3 መጽሐፍ
፩ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምርቱ
፪ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ
፫ ታሪከ ነገስት

እነዚህ መጽሐፍ ለቤተሰብ ለጓደኛ መሰጠት ከፈለኩ በዚህ t.me/spritual23 ቴሌግራም ይዘዙን ያሉበት ቦታ እንልካለን።በየትኛውም ዓለም ያሉ አንባቢያን መጽሐፍትን ቢያዙ እንልካለን ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

18 Nov, 14:30


አጼ ኃይለሥላሴ ቤተክህነት ላይ ስለሰሩት ሥራ እራሳቸው በጻፉት መጽሐፋቸው ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ላይ እንዲህ ይሉናል።

የቤተ ክህነት ሥራ እየተሻሻለና እየታደሰ እንዲሄድ ስለ ማሰባችንና ስለ መጀመራችን።

ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ ነገሥታት ለመንግሥቱ ሥራ ሁሉ አላፊ እንደ መሆናቸው ለቤተ ክህነትም ሥራ አላፊነት አለባቸውና ከሊቃውንቱና መምህራኑ መካከል እየመረጡ በየአድባራቱና በየገዳማቱ ለመሾምና ለመሻር ሥራቸውንም ሁሉ ለመቆጣጠር ሥልጣን አላቸው፡፡

ነገር ግን የመንግሥቱ ሥራ እየበዛ ከሄድና በዙሪያቸውም ካሉት አረማውያን ጋራ በየጊዜው ጦርነት ከማድረጋቸው የተነሣ የቤተ ክህነትን ሥራ ( በሙሉ ለመቆጣጠር ጊዜ አልነበራቸውም ነበርና በቤተ ክህነት ወገን በስሕተት እየገባ ልማድ ሆኖ የቀረና የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓት የሚያጎድል ብዙ ነገር ነበር፤

አሁን ግን ሕገ መንግሥት አቁመን ለሚኒስቴር ቤቱ ሁሉ ደንብ ሰጥተን ሚኒስትሮች ለየሥራቸው ሁሉ አላፊ ሆነው እንዲሰሩ ስለ አደረግን ከመንግሥት ሥራ በሚተርፈው ጊዜያችን ከሊቃውንቱና ከመምህራኑ ጋር እየተገናኘን የቤተ ከህነቱን ሥራ ጥቂት በጥቂት እየተሻሻለ እንዲሄድ አደረግን፡፡ ይኸውም ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡

፩ኛ፡ - የኢትዮጵያ ሕዘብ ትልቁም ትንሹም ወንዱም ሴቱም ክርስቲያንነቱ ጸንቶ የሚኖር ስለ መሆኑ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ በየትልልቁ በዓላት ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄደ ቅዳሴ ይሰማል፡፡ የሚችልም ሥጋ ወደሙ ይቀበላል። ነገር ግን ቅዳሴው ሕዝቡ ሁሉ በማያውቁት በግእዝ ቋንቋ ስለ ነበረ ብዙዎቹ የዜማውን ድምጥ ከመስማት በቀር ምስጢሩን የሚያስረዳ ቃል ሳይሰሙ ወደየቤታቸው ይመለሱ ነበር፡፡ አሁን ግን ጸሎተ ቅዳሴው በአማርኛ ቋንቋ እንዲተረጎምና እንዲታተም አድርገን በቤተ ክርስቲያኑ ስለ ሕዝቡ መላውን እንኳን ባይሆን ዋና ዋናውን ቃል በቋንቋው ሲነበብ መስማት ጀምሯል። ወንጌልና ሐዋርያት መለክትም በአማርኛ ቋንቋ እንዲነበብላቸው ተደረገ።

፪ኛ : በትልቁ አድባራትና ገዳማት የሚኖሩት አለቃው ከካህናቱና ከገበዙ አበ ማኅበሩ ከመነኮሳቱና ከአርድእቱ ጋራ ስለ ኑሮአቸው በየጊዜው በመካከላቸው የሚነሳውን ሁከት ለማስቀረት ስንል ሊቃውንቱንና መምህራኑን እየሰበሰብን  የቀድሞውን የየአድባራቱንና የየገዳማቱን የኑሮ ልማድና ደንብ እያስመጣን  እየተሻሻለ አዲስ ደንብ እንዲቆም በመደረጉ ትልቅ ጥቅም ተገኝቶበታል ።ተሻሽለው የቆሙትም አዲሶቹ ደንቦች በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በኢየሩሳሌምና በሌሎችም ገዳማት ሁሉ ይገኛሉ፡፡

፫ኛ ባገራችን በኢትዮጵያ በቀድሞ ዘመን የተክሊል ጋብቻ ለመኖሩ መጽሐፈ ተክሊል በየአድባራቱ መገኘቱ ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ግራኝ አሕመድ የሚባለው በተነሳበት ዘመን ወይም ዮዲት የምትባለው ከፈላሾች ወገን የሆነች ነግሳ  ክርስቲያንን ባጠፋችበት ዘመን ይሁን አልታወቀም እንጂ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እየጎደለ ስለ ሄደ በሕዝቡ ይቅርና በካህናቱም ቢሆን በተክሊል መጋባት በጣም አልሰፋም ነበር፡፡ ዳሩ ግን ከቤተ ክህነትናከሕዝቡም ወገን ብዙዎቹ ከሚስቶቻቸው ጋራ ሥጋ ወደሙ እየተቀበሉ ጋብቻቸውን አጽንተው ይኖሩ ነበር።

አሁን ግን ሊቃውንቱና መምሀራኑ የተክሊል ጋብቻን አጠንክረው እንዲሰብኩ አድርገን የተክሊል ጋብቻ የተለመደ ሆኗል፡፡

፬ኛ፡ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ባንዳንድ አውራጃ ሰው ሲሞት ዘመዶቹ አንዳንዶቹ ጠጉራቸውን እየቆረጡ ደረታቸውን እየመቱ እየጮሁ ያለቅሱ ነበር። አሁን ግን ሰው ሲሞት ዘመዱ ለኀዘኑ ምልክት በልብሱ ጫፍ ጥቁር ምልክት ከማድረግ በቀር ጠጉር መቁረጡን ደረት መምታቱን ከል መልበሱን እንዲተው በቤተ ክርስቲያኑ እየዞራችሁ ስብኩ ብለን ለመምህራኑ ትእዛዝ ስለ ሰጠንና መምህራኑም በትጋት ስለ ሰበኩ ስለ ሞተው ሰው ተስፋ እስከ መቁረጥ ማዘን እየተቃለለ ሄዷል።
እየተቃለለ ሄዷል፡፡

፭ኛ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅና ሃይማኖትዋ እንዳይናወጥ የተሰጣትም ሕግ እንዲጸና ለማድረግ አላፊነት እንዳለብን ስለ ተረዳነው የሳምንቱ አንድ ቀን ሊቃውንቱና መምህራኑ ወደ እኛ እየቀረቡ የቤተ ክርስቲያን ችግር ሁሉ በቃላቸው እንዲያመለክቱ ስለፈቀድንላቸው የቤተ ክርስቲያን ችግር እየተቃለለ ሄዷል።

ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ገጽ 135-137
ይህን መጽሐፍ ከ55ዓመት በኋላ  በድጋሚ እንዲታተም ለለፋው ለጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ክብር ይግባው።

ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጽሐፍት መደብር
አድራሻ አራት ኪሎ አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ጎን።
☎️☎️☎️🤳 0911006705
                    0924408461

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

15 Nov, 00:53


በዓለ ደብረ ቁስቋም

እንኳን አደረሰን።

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡

ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡
ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

መልካም በዓል ይሁንልን ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

14 Nov, 17:05


ምሥጢር ነው ብዬ ብነግረው ምሥጢር ነው ብሎ ነገረው ።

ለማንም እንዳትናገር!

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የአንድን ዲዳና ደንቆሮ አንደበት ‘ተከፈት’ ብሎ በአምላካዊ ኃይሉ ከፈተ፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ ግን ‘ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት’’ (ማር 7:36)
‘አትንገር ብዬ ብነግረው አትንገር ብሎ ነገረው’ ይሏል እንግዲህ ይኼንን ነው፡፡

የመልካም ሰውነት አንዱ መለኪያ ምሥጢር ጠባቂነት ነው፡፡ እውነተኛ ባልንጀርነትም ምሥጢርን መስማት ሳይሆን የሰሙትን ጠብቆ መያዝ ነው፡፡ ይህ የሚሆንላቸው ሰዎች በማኅበረሰቡ ዘንድ ይከበራሉ በፈጣሪም ዘንድ ዋጋቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በምድርም ቢሆን ለከፍተኛ ሓላፊነት የሚታጩትና ከፍ ያለ ክብር የሚሰጣቸው ሰዎች በማሰቃያ ሥፍራ ሳይቀር እየተንገላቱ ምሥጢር የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፡፡

አንዳንድ ሰው ግን የሰማውን ምሥጢር ለሌላ ሰው ለማዝረክረክ ማሰቃያ አያስፈልገውም፡፡ አትንገር የተባለውን እስኪናገር ድረስ ሆዱን ይቆርጠዋል፡፡ እግሩን እሾህ የወጋው ሰው እስኪነቀልለት ድረስ እንደሚንገበገብ ይህ ዓይነት ዓመል የተጠናወተውም ሰው ምሥጢሩን ለሌላ ሰው እስኪያሰማ ድረስ ይንቆራጠጣል፡፡ ‘ቀሊል ሰው’ ይለዋል ጠቢቡ ሲራክ

ምሥጢር ጠባቂነት ለወታደር የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡፡ በኮድ ማውራት ግድ የሆነውም ለዚህ ነው፡፡ ለሐኪም የሙያ ቃል ኪዳን ነው፡፡ ለጠበቃ የጥብቅና ፈቃድን ላለማጣት የሚጠበቅ ሕግ ነው፡፡ ለካህናት የንስሓ ልጆችን የመጠበቅ ሰማያዊ ቃልኪዳን ነው፡፡ ዓለም የምትናወጸው በዚህ መርሕ ኖረው ምሥጢር በማይጠብቁ ሰዎች ነው ማለት ይቀልላል፡፡

ጌታችን ያደረገው ፈውስ ቢሆንም ማስታወቂያ ሥሩልኝ ግን አላለም:: እንዳይናገሩ አዝዛቸው:: ከዚህም የምንማረው ብዙ ነው:: የሰውን መልካም ነገርም ቢሆን ምሥጢር መጠበቅ የግድ ነው፡፡ ለዚያ ሰው ሥራ እንቅፋት ላለመሆን ሲባል ዝም ማለት እርዳታ ነው:: የሰውን ኃጢአትና ነውር መደበቅ ደግሞ "ከባቴ አበሳ" (በደልን ሸፋኝ) አስብሎ በፈጣሪ ክብር ያስገኛል::

ሙሴን ወደ ስደት የዳረገው ምሥጢር መቋጠር የማይችል እስራኤላዊ ነበር፡፡ ሙሴ ለእርሱ አግዞ ግብጻዊውን ገድሎ ቢቀብርና ነጻ ቢያወጣው ‘አመስጋኝ አማሳኝ’ /አመስጋኝ አጥፊ/ እንዲሉ ሔዶ ወሬውን ነዛው፡፡ ወሬው በአጭር ጊዜ ተዳርሶ እስከ ፈር ኦን እልፍኝ ደረሰ፡፡ በአንድ መቋጠር በማይችል ወንፊት ሰው ምክኛት ሙሴ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ የዱር ስደተኛ ሆነ፡፡

ጌታችን በዚህች ምድር ሲመላለስ ተአምራቱን እንዳይናገሩ ያደርግ የነበረው ተአምራቱ ቢነገሩ የሚጎዱ ሆነው አልነበረም፡፡ በአንድ ወገን መከራ ከፊቱ አስቀምጦ ክብርን መፈላለግ እንደማይገባ ሲያስተምረን ሲሆን በሌላ በኩል ግን ከጊዜው በፊት መከራን ሊያደርሱበት እንዳይነሳሱና የመጣበትን ዓላማ ቅድሚያ መፈጸም እንደሚገባው ሲያስረዳ ነበር፡፡

ምሥጢር መጠበቅ በጎ ዕቅድንም ይጨምራል፡፡ ያለ ጊዜው የወጣ በጎ ዜናም ሆነ ዕቅድ በአፍ ይቀራል፡፡ ሳይሠራ ፈተና ይበዛበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳይሠሩ ቀድሞ ‘እሠራለሁ’’ ብሎ ነጋሪት መጎሰም ለጠላት ማንቂያ ደወል ነው፡፡ አበው ‘የሰይጣን ጆሮ አይስማ’ የሚሉት ለሰይጣን ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ነገር ሳይሠራ ተወርቶ ይዳረሳል፡፡ ክፋቱ በጣም ያወራከው ነገር የሰራኸው የሚመስልህ ነገር ነው፡፡ ብዙ ካወራህ በኋላ ያወራኸውን ከሰራኸው ለመለየት መቸገርህ አይቀርም፡፡ ዝም ብሎ መሥራትን የመሰለ ደግሞ ምንም ነገር የለም፡፡ ችግሩ ‘አሣ ሳትይዝ አሣ እጠብሳለሁ አትበል’ እንደሚባለው ከሥራ ማኒፌስቶው መቅደም የለበትም::

አንዳንዴ ደግሞ "በምሥጢር እየሥራ" መሆኑን የሚያወራም ሰው አለ:: ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው አሁን የማላስታውሰው ጽሑፍ ላይ በድሮ ዘመን ደረታቸው ላይ "የምሥጢር ፖሊስ" የሚል ጽሑፍ የተለጠፈባቸው ሰላዮች ነበሩ ይባላል:: ምሥጢሩም እንዳይቀር ጉራውም እንዳይቀር ነው ነገሩ:: እንዲህ ያለ ነገር ስንት ሥራ አበላሽቶአል መሰላችሁ?!

ዝም ማለት የቻለ ተቋም ወይም ግለሰብ ባይሠራ እንኳን ዝምታው ግርማ ይሆነዋል፡፡ ‘ሬሳ የሚፈራው ለምንድር ነው? ቢሉ ዝም ስለሚል’’ ይባላል፡፡ ዝም የሚል ወገን ባይሠራ እንኳን ‘ዝም ያለው ምን እየሠራ ነው?’’ ያሰኛል፡፡ መረዳት ከቻልን ውስጥ ውስጡን የልባቸውን እየሠሩ ፣ በፈለጉት ቦታ የፈለጉትን እያስቀመጡ ፣ ንብረት እያፈሩ ፣ እየተደራጁ ጸጥ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ላይ ላዩን ደግሞ እያወሩ ምንም የማይሠሩ ዓለምን ሞልተዋታል፡፡

ሥጋትንህንም ሁሉ መደበቅ አንድ ብልህነት ነው፡፡ አንዱን ሰውዬ ዘራፊዎች አግኝተው ቅጥቅጥ አደረጉት ይባላል፡፡ ኪሱን ሲፈትሹ ግን ያገኙት አምስት ብር ብቻ ነው፡፡ ብስጭት ብለው ‘’አንተ ለ አምስት ብር ብለህ ልትሞት ነበር እንዴ?’’ ሲሉት ‘አይ እኔማ ካልሲዬ ውስጥ የደበቅኩትን አምስት መቶ ብር ትወስዱብኛላችሁ ብዬ ፈርቼ ነው’ ብሎ አረፈው፡፡

በዚህ ዘመን አንደበትን ያለመሰብሰብ ችግር እንደዚህ ሰውዬ እየጎዳንም ነው፡፡ እንዲህ ሊያደርጉ ነው ፣ እንዲህ ሊሠሩ ነው ወዘተ በሚል ጥቆማ ተበረታትተው ብዙ ክፉ የሠሩና የሚሠሩ ዘራፊዎች አሉ፡፡ አንዳንዴም እንደ ባለ አምስት መቶ ብሩ ሰውዬ ያላሰቡትን ያሳሰብናቸው ቀማኞች አሉ፡፡ የማይተዋወቁትን ሰዎች ሳናውቅ አብረን ሰድበን አንድ ያደረግናቸው ፣ የማይታወቁትን ሰዎች በነቀፋ ጀግና ያደረግናቸው ብዙ ናቸው፡፡
የዚህ ዘመን መሻገሪያ ወርቃማ ሕግ አንደበትን መቆጠብ ፤ የቻለ ድምጽ አጥፍቶ በጎ መሥራት ፣ ያልቻለም የሚሠሩ ሥራዎችን በአንዳንድ ነጋሪቶች አለማደናቀፍ ነው፡፡

‘ኢየሱስም ያዩትን እንዳይናገሩ አዘዛቸው’’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

08 Nov, 08:08


የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ አቡነ ሚናስ ማኅበር የገዳሙን ማኅተም አስመስሎ በማሠራት ገንዘብ የሚቀበሉ ሰዎች መኖራቸውን ገለጸ፡፡

የገዳሙ አበምኔት መምህር ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም የገዳሙ መነኮሳት ነን የሚሉት የውሸት ማኅተም በማሠራት፣ ያለ ማኅበሩ እውቅና ተወክለናል በሚል ከምእመናን ገንዘብ እየተቀበሉ ነው ሲሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

የገዳሙ ጸሎተ ምሕላ አሳራጊ አባ ገብረ ሥላሴ ተበጀ በበኩላቸው የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ አቡነ ሚናስ ማኅበር ለሦስት ጊዜያት ጠፍቶ እንደገና በእግዚአብሔር ፍቃድና በአባቶቻችን ጽናት ተመልሶ የቀና ገዳም ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከ40 ያላነሱ ዝጉኃን ባሕታውያንና ከ80 በላይ አረጋውያን የሚጦሩበት ለጊዜው በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው ይህ ገዳም ባለፉት ጊዜያት በርካታ ፈተናዎችን ያስተናገደ ገዳም ነው ያሉት ደግሞ የገዳሙ ረእድ አባ ኃይለ መስቀል ወልደ ሳሙኤል ናቸው፡፡

ገዳሙ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሀገረ ስብከት አስተዳደር ውጭ እንደነበር የጠቀሱት አባ ኃይለ መስቀል ወልደ ሳሙኤል በገዳሙ ስም ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎችን ለማስቆምና ለባለድርሻ አካላት ለማሳወቅ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም አቅመ ደካማ አረጋውያን ከሱባኤ ሲወጡ እንጀራ የሚቀምሱበት ማይለበጣ የሚባለው የገዳሙ ክፍል ባሳለፍነው ዓመት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ገደሉ ተንዶ ከስድስት በላይ የደካሞች መኖርያ ቤት መፍረሱ የተገለጸ ሲሆን የፈረሱትን ቤቶች መልሶ ለማሠራት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚየስፈልግ እና የተናደዉን ገደል ተፋሰሱን ለማስቀየር ከፍተኛ ወጭ ስለሚጠይቅ ገዳማውያኑን በፈተና ውስጥ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማርያም የሚባሉ ራሳቸውን የዋልድባ ገዳም ተወካይ አድርገው በተለያዩ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉና በተለይም በውጭው ዓለም ከምእመናን ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰው መሆናቸውን በመረዳት ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የገዳሙን ትክክለኛ ማኅተም በማረጋገጥና የገዳሙን አካውንት ብቻ እንዲጠቀሙ አበምኔቱ አሳስበዋል፡፡

አሁን ላይም ይህንን እና ሌሎች ጉዳዮችን ለመፍታት እንዲሁም መነኮሳት ነን በማለት የገዳሙን ገንዘብ ያለአግባብ የሚጠቀሙትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ሂደት መጀመሩን አባቶች ተናግረዋል፡፡

የገዳሙ አካውንት፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000018796779-ጎንደር ዐቢይ ቅርንጫፍ
1000064118742-አዲአርቃይ ቅርንጫፍ
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ነው።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

07 Nov, 05:14


ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው እጅግ አስገራሚው የአቡነ ይምዓታ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ!
ጥቅምት 28 ቀን በዓመታዊ የዕረፍታቸው በዓል ታስበው የሚውሉት አቡነ ይምዓታ ይህንን ተራራ በተአምራት በፈረስ እንደወጡት ገድላቸውን ጠቅሰው የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ከአገልጋዮቻቸው አንደኛው ለፈረሱ ራት ሳር ሳይሰጠው በውሸት "ለፈረሱ ሳር ሰጥቼዋለሁ" ብሎ አቡነ ይምዓታን ይዋሻቸዋል፡፡ እርሳቸውም የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበርና "...ውሻ እንጂ የሰው ልጅ በሐሰት አይጮህም" ብለው ሐሰትን ስለመናገሩ ገሠጹት፣ ወዲያውም በተአምራት ከአንገቱ በላይ የውሻ መልክ ያለው ሆነ፡፡

የአቡነ ይምዓታ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ትግራይ ገርዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ እርሱም ቢሆን በገዳሙ አባቶች እገዛና ድጋፍ ነው፡፡
ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም በ6ኛው መ/ክ/ዘመን የተሣሉ እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡

ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ ‹‹በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል›› በማለት ይገልጻል፡፡

ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑትና የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ የተከናወነላቸው የአቡነ ይምዓታ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
✞ ✞ ✞

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

06 Nov, 11:55


ጥቅምት ፳፯(27) የመድኃኒታችን የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

“ሁሉን የያዘውን ያዙት፣ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፣ የሕያው አምላክን ልጅ አሠሩት፣ በቁጣ ጎተቱት፣ በፍቅር ተከተላቸው፣ በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት። ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፣ ኃጢኣትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፣ በመኳንንት በሚፈርደው በእርሱ ፈረዱበት!”

ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

02 Nov, 06:56


የዕለተ ቅዳሜ የመጽሐፍ ጥቆማ
የመጽሐፉ ርዕስ፦ መጽሐፈ ወግሪስ
የገጽ ብዛት ፦ 109
ተሪጓሚ ፦ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ(የመጻሕፍት ብሉያትና ሐዲሳት መምህር )።

"ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ትሑት ሁን፤ ባለጸጋ ትሆን ዘንድ ድኻ ሁን፤ ትጠግብ ዘንድ ረኃብን ውደዳት:: ጤነኛ ትሆን ዘንድ የመብል ሸክምን አቅልል፤ ትከብር ዘንድ ተዋረድ፤ ደስ ይልህ ዘንድ አልቅስ፤ ትኖር ዘንድ ሙት፤ ትበራ ዘንድ ትጋ፡፡ ትድን ዘንድ በማስተዋል ጸልይ፡፡ ኃጢኣትህን ይቅር ይልህ ዘንድ አብዝተህ ጹም:: ታገኝ ዘንድ ፈልግ፤ ታተርፍ ዘንድ ለመነገድ ተፋጠን፡፡ ስጥ ይሰጡሃል፤ ባዕለ ጸጋ ትሆን ዘንድ በብርሃናውያን መንገድ ትመላለስ ዘንድ መስቀልህን ተሸከም፤ ሥጋህን ጥላት ነፍስህን አንጻት፡፡"

ከመጽሐፈ ወግሪስ የተወሰደ

መልካም እለተ ሰንበት

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

01 Nov, 04:32


እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን” ማለት ነው። ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን
ያሰማራል። መ.ሄኖክ 6፥2 ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን
የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል።

መልካም ቀን ይሁንልን ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

30 Oct, 07:40


የበረሃዋ ኮከብ ቅድስት ጣማፍ ኄራኒ።

በቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ

በነገ ዕለት ጥቅምት ፳፩ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. በቅብጥ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ መርቆሬዎስ ገዳም እመምኔት የነበረችው እማሆይ ኄራኒ በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ ይደረጋል፡፡  ኄራኒ ማለት ሰላም፣ ፈቅር ማለት ነው፡፡ እናት ኄራኒ በእመ ምኔትነት በምታስተዳድረው የቅዱስ መርቆሬዎስ ገዳም ታላላቅ መንፈሳዊ ተግባራትን አከናውናለች፡፡

እናታችን ቅድስት እማሆይ ሄራኒ ዘወትር "ጌታ ሆይ ሰማዕት መኾን እፈልጋለኹ፡፡" በማለት በጸሎት ትጠይቅ ነበር።  " በገዳም ውስጥ እኅቶቼ ተጣልተው ማየት አልፈልግም፤ የኀሳብ ፈተና የማልችለው ፈተና ነው።" በማለት በሕመም መሰቃየትን መርጣለች፡፡ በዚኽም የተነሣ እማሆይ ሄራኒ እጅግ በጣም ከባድ ሕመሞችን ታማ ለ 27 ጊዜያት ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል፤   እነዚህ ሕመሞች ግን ለርሷ የደስታ ምንጮች ነበሩ። ሰማዕትነትን የሚሹ ሰማያዊውን ርስት መንግሥተ ሰማያትን ያገኛሉ፡፡ ቅዱሳን ደዌ እንዳይለያቸው አጥብቀው ይጸልዩ ነበር፤ ደዌ ስላልተለያቸውም ለአምላካቸውም  ልባዊ ምስጋና ያቀርቡ ነበር፡፡
እማሆይ ሄራኒ ሃያ አምስት ዓመታት በደዌ ውስጥ ኹና ፍፁም ክርስቲያናዊ ተጋድሎ ፈጽማለች፣ በጸሎቷና በምልጃዋ ብዙዎችን ከደዌያቸው ፈውሳለች፡፡ በትሕትናዋ፣ በንጽሕናዋ፣ በጸሎቷና በቅድስናዋ ለብዙዎች አርአያ ኾናለች፡፡ ከግኁሣን አበው ጋር በነበራት ከፍተኛ ቅርበት ታላላቅ መንፈሳዊ ምሥጢራት ተገልጠውላታል፣ ከግሑሳን ጋር በአንድነት በመጸለይ ታላቅ በረከትንና ክብርን አግኝታለች፡፡ እማሆይ ኄራኒ በአጸደ ሥጋ በነበረችበት ጊዜ አኹንም በአጸደ ነፍስ ኾና የብዙዎችን ችግር የቃለለች፣ ጭንቀታቸውን ያስወገደች፣ በንስሐ እንዲመለሱ ያስተማረች፣ በዘመናችን በምድረ ቅብጥ ገዳማዊ ሕይወትን ያጠናከረች ቅድስት ናት፡፡
እናት ኄራኒ ከሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስለነበራት በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዋና በሚያጋጥማት ፈተና ውስጥ ኹሉ ከአጠገቧ በመኾን በርካታ አስደናቂ ተአምራትን በማድረግ ይራዳት ነበር፡፡ በሕክምና ተስፋ ያጡ በርካታ ሕሙማን፣ በተለያየ ፈተና የተጨነቁ ሰዎች፣ ልጅ በማጣት የተፈተኑ ባለትዳሮች ኹሉ በቅድስት ኄራኒ ጸሎትና አማላጅነት የልቡናቸውን መሻት አግኝተዋል፡፡ በእርሷ አማካኝነት የታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ድንቅ ተአምርና ተራዳኢነት በስፋት እንዲታወቅ አድርጋለች፡፡ በሕይወተ ሥጋ በነበረችበት ዘመን የሰማዕቱን ቅዱስ መርቆሬዎስን ሦስት በዓላት ( ኅዳር ፳፭ ቀን ሰኔ ፱ ቀንና ሐምሌ ፳፭ ቀን) በየዓመቱ በታላቅ ዝግጅት ታክብረው ነበር፡፡ ከሥጋ ዕረፍቷ በኋላም ለብዙዎች በሕልም ተገልጣ በጸሎቷ ረድታቸዋለች፡፡
ማክሰኞ ጥቅምት ፳፩ ቀን ከቀኑ ፲፪ ሰዓት ቀን የቅድስት ኄራኒ ነፍስ ከሥጋዋ ተለይታ በቅብጥ በቅዱስ መርቆሬዎስ ገዳም ሥጋዋ አርፏል፡፡
የቅድስት ኄራኒና የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎትና በረከት ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትኹን፡፡ አሜን፡፡

የአባቶቻችን ጥርጥር የሌለባት የቀናች ሃይማኖታቸው፣ ድል የማትነሣ ተጋድሏቸው የመንግሥቱ ወራሽ እንድንኾን ያብቃን፡፡ አሜን፡፡

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

27 Oct, 03:54


ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ።

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን፣ ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤ ደቀ መዝሙሩም ሆነ፤ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤ አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲)

በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከል የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንግልን ሰብኳል፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡ የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህውን ማኅበረ እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት እየጠፋች ወንጌል ደግሞ እየሰፋች ሄደች፡፡ (የሐዋ.፮፥፬)

ቅዱስ እስጢፋኖስም የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ያደረበትና ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ታምራትን የሚያደርግ ሰው ስለነበር በዚያን ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡበት፤ ከእርሱ ጋርም ክርክር ገጠሙ፤ ነገር ግን ሊያሸንፉት አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበታልና በፈጣሪ ኃይል አሸነፋቸው፡፡

ከዚህም በኋላ በሐሰት ምስክር ‹‹ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› በማለት ወነጀሉት፤ እርሱ ግን ስለ እውነት መሰከረ እንጂ በጀ አላላቸውም፤ ሊቀ ካህናቱም በጠየቁት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላኩ መሰከረ፤ በመጨረሻም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ፡፡ አባቶቻችሁ ከነቢያት ያሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፡፡ በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም፡፡›› በዚህም ተበሳጭተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ በዚህም ምስክሩን ፈጽሞ የሰማዕታት አክሊልን በጥር ፩ ቀን ተቀዳጅቷል፤ በዚህም ቀዳሜ ሰማዕታት ይባላል፡፡(የሐዋ. ፯፥፶፩-፶፫)

አይሁድ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለማጥፋት ቀንተው ሲገድሉት ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ክርስትናን ለማጥፋት እነርሱን ሰበብ አድርጎ ለሞቱም ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ክርስትናን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስገድላል፤ ያስጨፈጭፋል፤ እንዲሁም ያሳድዳል፡፡ በየጊዜውም በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨፈጨፉት ሕፃናት፣ አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች ምንም በማያውቁት ምክንያት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ነው፡፡ እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡ ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!

የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡፡

ከማኅበረ ቅዱሳን ድኅረገጽ የተወሰደ

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

24 Oct, 03:12


እንኳን ለአቡነ አረጋዊ ፣ገብረ ክርስቶስ እንዲሁም ሐዋርያው ፊሊጶስ ዓመታዊ ክበረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።

ጥቅምት 14 ጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ የእረፍቱ መታሰቢያ ቀን ነው። በዚሁም ቀን ታላቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የተሰወረበት ዕለት ነው እንዲሁም ሐዋርያው ፊሊጾስ ያረፈበት የመታሰቢያ ዕለት ነው።

የቅዱሳኑ የአባታችን አቡነ አረጋዊ፡ የጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ እንዲሁም የሐዋርያው ፊሊጶስ በረከታቸው ረድኤታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን ፡፡
መልካም በዓል ይሁንልን ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

22 Oct, 03:13


እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ ።
በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪)።
    ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን ‹‹ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ›› ብሎናል፡፡ (ማቴ.፲፰፥፲) እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.፲፫፥፮-፱) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.፴፫፥፪) እርሱ ‹‹ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው›› መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን፤ አሜን፡፡

መልካም ቀን

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

19 Oct, 04:18


ታላቁ ቅርሳችን ቅዱስ ላሊበላ እና የኢትዮጵያ ሥልጣኔ በታሪከ ነገሥት መጽሐፍ።

"ኢትዮጵያ የሚገርሙ እና የሚያስደምሙ ታሪካዊ እሴቶች ያላት ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ አደባባይ ገንና እንድትታይ ካደረጓት ሁለግብ ሀብቶቿ በግንባር ቀደምነት የላስታ የሮሐ አድባራት ይጠቀሳሉ፡፡ ላሊበላ መንፈሳዊነት ከዓለማዊነት ፍንትው ብሎ ተለይቶ ረቆ የሚታይበት መካነ መንፈስ ነው፡፡

በዚያ ዘመን ከኢትዮጵያ አልፎ በሌላው ዓለም ያልነበረው እና አቻ የሌለው የላሊበላ ዘመን ታሪክ ድንቅ ሥራ ብዙ ሊባልለት የሚችል ቢኾንም ብዙ እንዳይባልለት አንዳች አፍአዊም ኾነ ውስጣዊ ተፅዕኖ የነበረበት ይመስላል፡፡ ያ ዘመን በተለይ አውሮጳ 1500-1000ዓ ም ከዚያም ባለፈ የጨለማ ዘመን በሚሉት ኹኔታ ቢገኙም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እና ኢትዮጵያ ግን ከሀገራዊ አንድነቱ ባሻገር ድንቅ የኪነ ሕንፃ ባለቤት ነበሩ:: ይህን ዐይነት ሥራ አይደለም አፍሪካ 1500 እና 400 ዓመታት በኋላ ዘመነ ዳግም ልደት/ renaissance ተብሎ የተነሣው ምድረ አውሮጳም ማሳየት የቻለ አይመስልም፡፡ ዛሬም ቢኾን፡፡

የዘመነ ላሊበላ ሥልጣኔን ስንመለከተው ሀይማኖታዊ ብቻ አይደለም:: አጠቃላይ የኾነ የማንነት ሥልጣኔም ጭምር እንጅ፡፡ እንደውም ከአክሱም ድቀት በኋላ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ክብር የተመለሰበት ጅማሮ ነው የቅዱስ ላሊበላ ዘመን። ምንም እንኳን ዓለም ዐቀፉ ኹኔታ ተስማሚ ባይኾንም ነገሥተ ላስታ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ግብጽን ጨምሮ ከአህጉረ ባሕረ ሜድትራንያን ጋር ግንኙነት ነበራቸው፡፡ እራሳቸውንም በማኅበራዊው እና ሥልጣኔው ተወዳዳሪ ማድረጋቸውን ገድላቱም ኾነ ታሪክ ነገሥቱ ይጠቁማሉ፡፡"

ታሪከ ነገሥት ገጽ146_148

ይህ መጽሐፍ ከገበያ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም ዳግም ለሕትመት በቅቷል ።ከገበያ መልሶ ሳይጠፋ ወደ መጽሐፍት መደርደሪያችሁ ታስገቡት ዘንድ ምክሬ ነው።

ዋና አከፋፋይ ሀሁ መጽሐፍት መደብር ።

አድራሻ አራት ኪሎ አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ጎን
ስ.ቁ 0911006705
0924408461

ይህ በፌስቡክ መንደር መገኛችን ነው።
https://www.facebook.com/groups/325620972980210/

በቅርቡ ከሕትመት የወጣውን ታረከ ነገሥት መጽሐፍ ቴሌግራም t.me/spritual23 በመጠቀም መዘዝ ይችላሉ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

18 Oct, 11:34


የመጽሐፍ ጥቆማ:- ታሪከ ነገሥት
ጽሐፊ መምህር ደሴ ቀለብ
የገጽ ብዛት 563
የሸፈን ዋጋው :-860
ይዘት ከሚኒልክ 1ኛ እስከ ሚኒልክ 2 የነገሥታትን ታሪክ የያዘ ።

ሐይቅ እስጢፋኖስ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ሐይቅ እስጢፋኖስ ።
ሐይቅ እስጢፋኖስ በጥንቱ መልክዐ ምድር የአምሐራና የአንጎት መገናኝ ላይ የነበረ ገዳም ነው።አመሠራረቱ ከአቡነ ኢየሱስ ሞዓ መምጣት 300 ዓመታት ቀድሞ ነው።

ሐይቅ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን የተሠራው በ842 ዓ.ም.ነው።ሐይቅ እስጢፋኖስ በቅዱሳት መጻሕፍት፣የጽሕፈት ትምህርትና በማኅበራዊ የምንኩና ሕይወትና በተግባረ ዕድ የተደራጀ ነበር።

በሐይቅ እስጢፋኖስ ከጋሳጫ፣ከሳይንት፣ከበጌምድርና ከሸዋ በሚመጡ ተማሪዎች ከ800 በላይ መነኮሳት በትምህርተ ሀይማኖት ሰልጥነው፣በንቡረ ዕድነትማዕረግ ተመርቀው በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተሰማርተዋል።ለምሳሌ፦አቡነ ኂሩት አምላክ ዘጣና ቂርቆስ እስጢፋኖስ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ፣አቡነ ጸሎተ ሚካኤል ዘደብረ ጎል፣አቡነ አሮን ፣አባ ሠረቀ ብርሃን፣አባ ዘኢየሱስ፣የደብረ ሊባኖስ ገዳም መስራች አቡነ ተክለሃይማኖት ይጠቀሳሉ።
" አባ ኢየሱስ ሞዐ የተመሠረተዉ እና በመካከለኛዉ ዘመን የሀገራችን የመጀመሪያዉ” ዩኒቨርሲቲ ተብሎ የሚታወቀዉ የሐይቅ ገዳም ለባህል እና ታሪክ መጠበቅ ታላቅ ባለውለታ ነዉ። ገዳሙ እና አካባቢዉ በተለይም የሰሎሞናውያኑ እና የታላላቅ አበው የዕውቀት ምንጭ ሆኖ አገልግሏል:: አቡነ ተክለ ሀይማኖት እና ይኩኖ አምላክም የተማሩት በዚሁ ገዳም ሲኾን በኋላ ተመልሰዉ ቢመጡም በመጀመሪያዉ የቆይታ ዘመናቸዉ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሐይቅ ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም/ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዘጠኝ/ዐሥር ዓመት ተቀምጠዋል።

በዚያም መጻሕፍትን የቤተ ክርስቲያን ታሪክን እና የገዳም ሥርዐት ዕውቀትን እንዳሰፉ ፕሮፌስር ታደሰ ታምራት ገልጸዋል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እና ይኩኖ አምላክን ያስተማሩት የአባ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም/ ዩኒቨርሲቲ ቤተ ትምህርት ሐይቅ ብዙ ሊቃውንትን ያስገኘ ገዳም ሲሆን በኋላ ዘመንም አባ ጊዮርጊስን የመሰሉ አባት ተገኝተወብታል፡፡ እንደ ሌሎች አባቶች ኹሉ አቡነ ተክለ ሀይማኖትም የራሳቸዉን ገዳም ደብረ አስቦን መሥርተዋል፡፡"

ታሪከ ነገሥት ገጽ 152

ይህ መጽሐፍ ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም ሁልጊዜ የጠፉና የጥንት መጽሐፍትን በማሳተምና በማከፋፈል ለአንባቢያን በማቅርብ የሚታወቀው ሀሁ መጽሐፍት መደብር ጥቂት ኮፒዮችን አሳትሞ ይዞልን ቀርቧል ። መጽሐፉ በዋናነት በሀሁ መጽሐፍት መደብር ቢከፉፈልም በሁሉም መጽሐፍት ቤቶች ያገኙታል።

ሀሁ_መጽሐፍት_መደብር
አድራሻ ቁ.1 አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
2 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ
ስ.ቁ 0911006705/0924408461

ይህ በፌስቡክ መንደር መገኛችን ነው።
https://www.facebook.com/groups/325620972980210/

በቅርብ ለሕትመት የበቃውን ታረከ ነገሥት መጽሐፍና ሌሎችንም መጽሐፍ ለማዘዝ ይህን ቴሌግራም t.me/spritual23 በመጠቀም ማዘዝ ይችላሉ። በየትኛውም ዓለም ያሉ አንባቢያን መጽሐፍትን ቢያዙ እንልካለን ።

መንፈሳዊ መጽሐፍትን ፍለጋ/ኃሠሣ መጽሐፍተ ዘግዕዝ

14 Oct, 16:50


እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ምድረ_ከብድ_አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ _ገዳም

ምድረ ከብድ  ደቡብ ውስጥ ጎራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ነው የሚገኘው፡፡ ምድረ ከብድ ትርጉሙ ከባድ ስፍራ፣ ጽኑ ቦታ፣ ከፍ ያለ በረከት የሚገኝበት ማለት እንደሆነ የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡

ከአዲስ አበባ 122 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከጢያ ትክል ድንጋዮች አቅራቢያ የሚገኘው ምድረ ከብድ በንጉሥ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት  በራሳቸው በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተመሰረተ ገዳም ነው፡፡ ጻድቁ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ ኖረው ያረፉትም በዚሁ ገዳም ነው፡፡

በግራኝ  ጦርነት የቃጠሎ ጉዳት ደርሶበት ነበር፡፡ የሸዋው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ናቸው በድጋሜ ያሰሩት፡፡ አሁን የምናየውን ህንጻ ቤተክርስቲያን በሳር ክዳን ያሰሩት ፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ሲሆኑ ወደ ቆርቆሮ ክዳን እንዲቀየር ያደረጉት ደግሞ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ናቸው፡፡

ቦታቸው ለመርገጥ ያብቃን አሜን።

1,537

subscribers

1,656

photos

15

videos