ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ @juwanagibigg Channel on Telegram

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

@juwanagibigg


"ይህ ቻናል የጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሲሆን በጅማ ዋና ግቢ ለሚማሩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተማሪዎች በግ/ጉ ሚትላለፉትን መልዕክት፣ት/ቶች፣ስነ ጽሁፎች እና ሌሎችም ለማድረስ የተከፈተ ቻናል ነው።"

ለማንኛውም አስተያየት
👉 @natidula
👉 @MeronW_BAHIRAN
👉 @Mek_J
👉 @AsegidT
👉 @SuraMoD
👉 @Shalule

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ (Amharic)

ይህ ቻናል የጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሲሆን በጅማ ዋና ግቢ ለሚማሩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተማሪዎች በግ/ጉ ሚትላለፉትን መልዕክት፣ት/ቶች፣ስነ ጽሁፎች እና ሌሎችም ለማድረስ የተከፈተ ቻናል ነው። የዚህ አካል ለከባድ ቅርብ ተወካዮችን ያህል በሚገኘው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ በተማሪዎቹ፣ በሚትሉት መልዕክቶች፣ በትቶች፣ በስነ ጽሁፎች፣ በሌሎቹ ቀጥሎች እና ሌሎችም መሳሔዎች የምንገኝ ሲሆን ባጅለት አሰምንቻለው። የቻናልው ይሂዱ፣ ይሰጡ፣ ይማሩ፣ ከታገኙት ንብረትም ይተጉዳሉ ።

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Jan, 10:03


🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎

የተመደቡ ባሶች ስለመጡ ሁላችንም ተቀሳቅሰን እንምጣ

🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎🚎

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Jan, 09:59


❤️እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ ❤️

በሥርዓተ ማኅሌቱ ስትሳተፉ ሚባለውን በዚህ ይከታተሉ😍

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Jan, 05:16


🍂🍂ዛሬ ይጾማል እንዴ? 🍂🍂

🍂🍂🍂 ስንክሳር ዘጥር ፲ እንዲህ ብሎ ያዛል 🍂🍂🍂

🍂 ወለእመ ፡ ኮነ ፡ ዕለተ ፡ በይረሙን ፡ ዘውእቱ ፡ አስተርእዮ ፡ በዕለተ እሁድ አው፡በዕለተ፡ ሰንበተ አይሁድ፡ይጹሙ፡በእለተ ፡ ዓርብ ፡እምቅድሜሁ፡እስከ፡ምሴት፡በከመ ተናገርነ፡ ቅድመ ዳዕሙ ይትዓቀቡ፡እምነ፡በሊዕ፡ጥሉላተ።

🍂 ጥምቀት እሁድ ስለዋለ አስቀድመን አርብ እስከ 12 ሰአት ይጾማል። በዋዜማው ደሞ ቅዳሜ ከቅዳሴ በኃላ ምግብ መመገብ ይቻላል። ግን ጥሉላት አይበሉም።
ለምሳሌ  ሥጋ ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ......

በረከት የምናገኝበት ጾም ያድርግልን !!!



▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
    

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Jan, 19:19


ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ pinned «»

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Jan, 06:20


😍cuuphaa mana kiristaanaa baadiyaatti😍

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Jan, 05:58


😍መልካም የጥምቀት በዓል😍

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Jan, 17:59


🤩ነገ አርብ ነው!🤩
🙏የክርስቲያኖች ሀይል ጸሎት ነው🙏

በጸሎት ኤልያስ  ዝናብም እንዳይዘንብ አደረገ
     📎ከጸሎት ውጪ ሰማይ የሚከፍት ሰማይ የሚዘጋ ምንም ኃይል የለምና

በጸሎት ከፈተና ይወጣል
      📎“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤።” ተብሏልና

በጸሎት መሻታችን ይፈፀማል
        📎ጌታ “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ” ደግሞም “ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”ብሏልና
🙏ብቻ እናንተ ጸሎት ጀምሩ እንጂ!
🙏ብቻ እናንተ የእግዚአብሄርን ስም ጥሩት እንጂ!
🙏ሰው የገለጠውን ቁስላችሁን መድኃኔዓለም ይሸፍነዋል😍
🌿በዕለተ አርብ ማለዳ 12 ሰዓት በጽርሐ ጽዮን እንገናኝ🌿

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Jan, 15:36


😍Faarfannaa Cuuphaa qo'achaa jirtuu?

Qo'annaa Faaruu Cuuphaa kan dhuma bor galgala qabnurratti hirmaadha.

Faaruuwwan Cuupha sagaleedhaaniifi girafiikisiidhaan argachuudhaaf liinkii gara gadii jiru tuqa.

Bor galgala 12:00-1:00 mana Amantaa Hamara noohitti wal haa  argannuu


Faaruuwwan argachuuf
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/JUmaincampus_mezmur_kifel

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Jan, 11:35


ጾመ ገሃድ

ገሃድ ምንድን ነው?

ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ፣ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17)

ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡

በዚህ መሠረት የአሁን የገሃድ ጾም የራሱ አዋጅ አለው

ስንክሳር ዘጥር ፲ እንዲህ ብሎ ያዛል

ወለእመ ፡ ኮነ ፡ ዕለተ ፡ በይረሙን ፡ ዘውእቱ ፡ አስተርእዮ ፡ በዕለተ እሁድ አው፡በዕለተ፡ ሰንበተ አይሁድ፡ይጹሙ፡በእለተ ፡ ዓርብ ፡እምቅድሜሁ፡እስከ፡ምሴት፡በከመ ተናገርነ፡ ቅድመ ዳዕሙ ይትዓቀቡ፡እምነ፡በሊዕ፡ጥሉላተ።

ጥምቀት እሁድ ስለዋለ አስቀድመን አርብ እስከ 12 ሰአት ይጾማል። በዋዜማው ደሞ ቅዳሜ ከቅዳሴ በኃላ ምግብ መመገብ ይቻላል። ግን ጥሉላት አይበሉም።
ለምሳሌ  ሥጋ ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ......

በረከት የምናገኝበት ጾም ያድርግልን!!!

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 19:44


😍በውስተ ጎል
የኪነጥበብ ምሽት

------------------------------------------------------------
📜ጥበብን በጥበብ እናመሰግነው!!
የማይረሳ የጥበብ ምሽት በቤተልሔም ተገኝተን እናሳልፍ!
-------------------------
እሁድ ጥር 4 2017 ምሽት 11:30 ጀምሮ  ሃመረ ኖኅ ቅ/ኪ/ምሕረት ቤ/ክ ቁጥር 1 አዳራሽ እንገናኝ!!
------------------------------------------------------------

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 19:41


ስለዘገየን ይቅርታ በዛሬ ዕለት ከተሳተፉ 48 ተወዳዳሪዎች ከ1-3 የወጡ የዕለቱ ክዋክብት እነዚ ናቸው 🏆
🥇 @Nmhb21 – 6 (19.3 sec)
🥈 @Edmi1212 – 6 (26.3 sec)
🥉 @Abuyemariam1221 – 6 (42.2 sec)

ሁላቹም ስለተሳተፋቹ እናመሰግናለን ዘውትር አርብ ምሽት 2:30 ይጠብቁን
😍ሰናይ ምሽት😍

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 19:16


ስለዚህ የዛሬ ውድድራችን አልቋል
አሸናፊው አሁን ይለቀቃል

🥰እስከዛ ድረስ በyoutube የለቀቅንላችሁን የገና በዓል አከባበር ተከታተሉ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 18:39


https://youtu.be/KLDWzV1QmeM?si=y_VERpcaMGOXFt85

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 18:30


Start this quiz የሚለውን በመጫን ውድድሩን መሳተፍ ይቻላል:: ውድድሩም ልክ 4:00 ሲል ይጠናቀቃል:: መልካም እድል

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 18:28


🎲 Quiz 'የአርብ ጥያቄ'
ኒቆዲምስ ጥያቄና መልስ ይህ በየሳምንቱ አርብ ምሽት3:30 ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ ትምህርትና ሐዋሪያዊ አገልግሎት እየተዘጋጀ የሚቀርብ የጥያቄና መልስ ውድድር ነው በዚህ ውድድር በመሳተፍ መንፈሳዊ እውቀቶን ያሳድጉ!
🖊 6 questions · 45 sec

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 17:59


ውድ የግቢያችን ቤተሰቦች እንደምን አመሻችሁ

👉ሳምንታዊው በትምህርት ክፍል የሚዘጋጀው የጥያቄና መልስ መርሃግብር ልክ 3:30 ላይ ይጀምራል

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Jan, 05:15


😍በውስተ ጎል
የኪነጥበብ ምሽት

------------------------------------------------------------
📜ጥበብን በጥበብ እናመሰግነው!!
የማይረሳ የጥበብ ምሽት በቤተልሔም ተገኝተን እናሳልፍ!
-------------------------
እሁድ ጥር 4 2017 ምሽት 11:30 ጀምሮ ሃመረ ኖኅ ቅ/ኪ/ምሕረት ቤ/ክ ቁጥር 1 አዳራሽ እንገናኝ!!
------------------------------------------------------------

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

09 Jan, 07:17


#የልደታ ጽዋ
ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ
ወሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ

ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ
ሰማያቸውም ፀሐይን አወጣች
።።።።።።።።።ነግሥ።።።።።።።።

በግቢ ጉባኤያችን በጋራ የምንዘክራት የልደታ ጽዋዓ ላይ ይገኙ ዘንድ በእንተ ልደታ ለማርያም ብለን ጠርተንዎታል
።።።።።።።
ቀን-ነገ ሃሙስ ከ11፡30 ጀምሮ በዐውደ ምሕረት
እንዲገኙ ይሁን!!!

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

07 Jan, 06:24


..................................................................
የልደት መርሃ ግብራችን በዚህ መልኩ እየተከበረ ይገኛል!!!
እንዳያመልጦ ላልሰማ እያሰማን ቶሎ እንገኝ😍
...........................................................

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Jan, 20:26


..................................................................

😍ሥርዓተ ቅዳሴ ዘልደት😍
..................................................................

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Jan, 16:32


😍እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ😍

ሥርዓተ ማህሌት ዘልደት

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Jan, 19:31


ፍቁራንን😍😍 እንዴት ቆያችሁን??

እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ነገ ማለትም እሁድ ታህሳስ 27-2017ዓም  የመጨረሻ የልደት መዝሙር ጥናታችን ይሆናል ታዲያ ጥናት ብቻ አደለም ልዩ የዝማሬ ምሽትም ነው እንጂ

ስንመጣ አንድ ጧፍ🕯 እና አንድ ጓደኛችንን 👫👭👬ይዘን እንምጣ🤗

ነገ 12:00
በሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን   አዳራሽ
በጉጉት እንጠብቃኋለን🤗

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

04 Jan, 17:05


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🙏
 
    የ2017ዓ.ም የገና በዓል የስራ ክፍፍል💐

💐💐ከዋዜማው ጀምሮ ቪዲዮመቅረፅ:-        ሚዲያንዑስክፍል 🎞

💐እቃ ማጠብ🍽🥣:-

      👉የዋዜማው ዕለት(ሰኞ)-ናቹራል ባች፣ሙያ እና በጎአድራጎት ክፍል
     👉የበዓል ዕለት (ማክሰኞ) ሜዲካል ባች እና መዝሙር ክፍል

💐💐ሽንኩርት መላጥእና ማስከተፍ 🧅🧄🍴    
            -ሶሻል ባች

💐💐 ውሀ መቅዳት 🫙🚰
       -ትምህርት ክፍል
       -ቋንቋና ልዩፍላጎት ክፍል

💐💐ፅዳት እና ዲኮር 🧹  
      - እቅድ  ክትትል መረጃ ማደራጃ ክፍል
      -ሂሳብ ክፍል

💐💐 ወጥ መስራት 👨‍🍳
       -አባላትጉዳይ
       -የበዓል ኮሚቴ ኣባላት

💐💐መስተንግዶ
      -ከሶስቱም ባች 15ሰው ይመደባል
      -የስራአስፈፃሚ አባላት እና ኢንስፔክተሮች

💐💐ሰሀን መሰብሰብ🍽🥣🍴
      -ልማት ክፍል

      መልካም የልደት በዓል ይሁንልን!!!!

                            እግዚአብሔር ይርዳን 🙏

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Jan, 19:19


🏆የዚህ ሳምንት አሸናፊዎች🏆
🥇 @Natan896 – 10 (1 min 10 sec)

🥈@MeronW_BAHIRAN

🥉@sanenat

ተሳታፊዎች እናመሰግናለን ሽልማታችሁን በውስጥ መስመር እንልካለን
😍ሰናይ ምሽት😍

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Jan, 19:05


የተሰጠው ሰዓት አብቅቷል
ውጤት አሁን ይለቀቃል!!!!!!!!

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Jan, 18:38


👉ጥያቄና መልሱ 👈
ለ 30 ደቂቃ ሚቆይ
ስለሆነ መሳተፍ ጀምሩ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Jan, 18:35


🎲 Quiz 'ኬሪዎን '
ይህ በየሳምንቱ አርብ ምሽት3:30 ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ ትምህርትና ሐዋሪያዊ አገልግሎት እየተዘጋጀ የሚቀርብ የጥያቄና መልስ ውድድር ነው በዚህ ውድድር በመሳተፍ መንፈሳዊ እውቀቶን ያሳድጉ
🖊 10 questions · 30 sec

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Jan, 18:34


ጥያቄው ሊለቀቅ ነው 3️⃣ 2️⃣ 1⃣

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Jan, 14:41


⭐️ኬሪዎን⭐️

 🎁የጥያቄና መልስ ውድድር 🎁

በtelegram channelችን
    
ዛሬ ምሽት3⃣ :3⃣0 ላይ ይጠብቁን

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Jan, 21:07


📣 📣📣የበረከት ሥራ ጥሪ

ሰላም ተወዳጆች የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁንና ፦

👉 የነዳያንና የአቅመ ደካሞችን ንጽህና መጠበቅ (ልብስ አጠባ🧼 🛁🚿) በተማሪዎች ይሰጣል እርስዎስ ለምን ያመልጦታል?

🗓 አርብ 25/4/2017ዓ/ም
🕒 ከ9:00 ጀምሮ አስከ 12:00
🛁 ቦታ :- ታች ቤት

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Jan, 19:04


🤩ነገ አርብ ነው!🤩
🙏የክርስቲያኖች ሀይል ጸሎት ነው🙏

በጸሎት ኤልያስ  ዝናብም እንዳይዘንብ አደረገ
     📎ከጸሎት ውጪ ሰማይ የሚከፍት ሰማይ የሚዘጋ ምንም ኃይል የለምና

በጸሎት ከፈተና ይወጣል
      📎“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤።” ተብሏልና

በጸሎት መሻታችን ይፈፀማል
        📎ጌታ “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ” ደግሞም “ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”ብሏልና
🙏ብቻ እናንተ ጸሎት ጀምሩ እንጂ!
🙏ብቻ እናንተ የእግዚአብሄርን ስም ጥሩት እንጂ!
🙏ሰው የገለጠውን ቁስላችሁን መድኃኔዓለም ይሸፍነዋል😍
🌿በዕለተ አርብ ማለዳ 12 ሰዓት በጽርሐ ጽዮን እንገናኝ🌿

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Jan, 12:14


"የጌታን ልደት በተወለደባት ቤተልሔም እናክብር ፤በዝማሬም ከመላእክቱ ጋር አንድ እንሁን::"


📌የገና እና የጥምቀት መዝሙር ጥናት

👉ዛሬ ሃሙስ ከ12:00 ጀምሮ በሃመረ ኖኅ ቅ/ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

01 Jan, 21:50


"የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።"
የሉቃስ ወንጌል 2፥7

# ዛሬ በነበረን መርሃግብር ላይ የተጠኑ መዝሙራት

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

18 Nov, 07:53


📽ልዩ የvideo editing ስልጠና በነፃ ግቢ ጉባኤያችን ልትጀምር  መሆኑን እናብስሮ!!!

    🎥ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት የሚችል ማንኛውም የግቢ ጉባኤ አባላት ስልጠናውን መሳተፍ ይችላል
       👉 smart phone ያለው ያላት
      👉ለወደፊት የwifi አማራጭ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል( በጣም አስፈላጊ ግን አይደለም)
       👉ከስልጠናው በኋላ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነ የሆነች
      👉 አዲስ እና ነባር የ media and communication ተማሪዎች ይበረታታሉ!!

🗣ከላይ የተጠቀሱትን የምታሟሉ ታች ባለው Google forms ወይም +251951045021 በመደወል መመዝገብ ይችላል!
      📌ቀን እና ሰዓት :- ቅዳሜ ሕዳር 14 ከ8:30-10:00 ይሰጣል
       📌የስልጠናው ቦታ :-ማዕከል ህንፃ ወይም ከsports cafe (ንግድ ባንክ ካለበት )ዝቅ ብሎ እየተሰራ ያለው ባለ 4 ፎቅ ላይ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfro7KGQbd8Rf9JFveYu7_lEi4F6fSwFt5bPKErHTGJJhkeag/viewform?usp=sf_link

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Nov, 09:41


ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች። ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን ደባለቀች፥ ማዕድዋን አዘጋጀች። ባሪያዎችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች።


📝📝📝📝📝📝የተወደዳቹ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የአደራ ልጆች እደተለመደው ድርሰት በህብረታችን የሳምንቱን ድግስ ደግሳ ትጠብቀናለች መቅረት ፈፅሞ አይታሰብም
ዛሬ(እሁድ) 🧭11:45-1:00
ቦታ 🏘️ታች ቤት

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Nov, 06:55


አዘጋጅ - የቴክኖ ግቢ ጉባኤ
ቦታ- ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
ዋና ግቢ ላላችሁ መጥታችሁ ጉባኤ ሙራድ መርኃግብር መካፈል የፈለጋችሁ እህት ወንድሞቻችን ማደሪያ ቤተ ጽዮናችንን አዘጋጅተናል።

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

17 Nov, 05:23


❖የሕሙማን ጥየቃ 🏨🏨

የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ አምላክ ቢፈቅድ እሁድ (ህዳር 8) የሕሙማን ጥየቃ ሆስፒታል ይኖራል፤ ከበረከቱ ተሳታፊ እንድንሆን ላልሰሙት እያሳወቅን ይሁን !!

መሰብሰቢያ ቦታ: ግሪን ህንጻ
🕢 7:30-7:50L.T እንጠብቆታለን
ሰአት ይከበር !
       
         🙏የነገ ሰው ይበለን 🙏

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 19:56


https://youtu.be/UVO0IKpxDR8

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 04:20


#ኅዳር_7

እንኳን አደረሳችሁ🥰

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት

ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።

ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 05:35


🙎‍♂ እፎ ወአልከ/ኪ?
🙍‍♀ እግዚአብሔር ይሴባሕ🙏

🙎‍♂እፎ ውእቱ እለተከ/ኪ?
🙎እእእእእእ🤔......ሰናይ ውእቱ እለትየ🙏

🙎‍♂👉መንገለ አይቴ ተሐውር/ተሐውሪ?
🙍‍♀-🤔🤔🤔🤔

🙎‍♂👉እንዴ ምነው ይህቺን ብቻ ነው ምታውቀው/ምታውቂው? ለማንኛውም ወዴት እየሔድክ/ሽ ነው? ነው ያልኩት።

🙎-እእእ እንደዛ ነው እንዴ እኔማ ኮርስ ልማር እየሔድኩ ነው::


🙎‍♂ መልካም!👉ለመሆኑ በግቢ ጉባኤያችን ስለሚሰጠው መሠረታዊ የልሳነ ግዕዝና አፋን ኦሮሞ ክህሎት ትምህርት ሰምተሃል/ሻል?
🙍‍♀-ኧረ አልሰማሁም

እንግዲያስ ግቢ ጉባኤያችን ዘወትር ቅዳሜ ከ8-10 ሰዓት የግዕዝና  አፋን ኦሮሞ ክህሎት ትምህርት ታሰጣለች መማር ከፈለክ ከስር ባለው መመዝገብ ትችላለህ/ትችያለሽ።

እርስዎስ እነዚህን ቋንቋዎች መማር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ከስር👇👇 ባለው ሊንክ ይመዝገቡ።


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdIk9VxRtOhJjl_8yQ3zYdJdtHY-JwQO4n5Zw8KF3oRH7KuRQ/viewform?usp=sf_link

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 04:34


🌹አንኳን ለቁስቋም በዓል        በሰላም አደረሳችሁ!🌹

🔔#ደብረ #ቁስቋም🔔
#ደብረ ቁስቋም ማለት ደብረ ምዕራፍ ማለት ነው፤ ከእመቤታችን ክብረ በዓላት መካከል አንዱ በዚህ ስም ይጠራል፤ ለቤተ ክርስቲያን ከሚደረግላት የመዳን ታሪክ ጋር ስለተገናኘ እንጅ ከግብፅ ተራሮች አንዱን መጥራት ስላስፈለገን አይደለም፤ ዛሬ አግዚአብሔር ታላቅ የሆነውን ፍርዱን በምድር ላይ ማድረጉን ለዮሴፍ በሕልም የታየው መላክ አስረድቶታል፤ ‹‹እስመ ሞቱ እለ የሐስስዋ ለነፍሰዝ ሕጻን፤ የዚህን ሕጻን ነፍስ ሊገሏት የሚሷት ሁሉ ሞተዋልና›› ማቴ 2 ፥2ዐ ከዚህ በፊት የተደረገው እንዲህ አልነበረም በልደተ ክርስቶስ ያልተደሰተው ሰይጣን በሔሮድሳውያን አድሮ ስደት የሚገባቸው ግፈኞች አርፈው ተቀምጠው ስደት የማይገኝባት እመ አምላክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ተሰደደች የእግዚአብሔር መላክ የቀኑን ልክ ሳይናገር ‹‹እስክነግርህ ድረስ በዚያ ተቀመጥ›› ብሎ ዮሴፍን ወደ ግብፅ እንዲወርድ አዘዘው፡፡ የመከራ ፉ አይነገርም የእስራኤልን የግብጽ ኑሮ መጀመሪያውን እንጅ መጨረሻውን ከእግዚአብሔር በቀር ማን ያውቀው ነበር፤ የዚህ ዓለምም ጉዞ መጨረሻው በኛ ዘንድ አልተነገረንም
ነገር ግን እግዚአብሔር ማንንም በስደት ምድር አይረሳምና ከሦስት ዓመት ከስድስት ወራት በኋላ ዛሬ ስደተኞችን በምሕረት አሰበ ይህ አርባ ሁለት ወር ለእመቤታችን የስደት ወቅት ይሁን እንጅ ለሔሮድሳውያን ደሞ የንሥሐ ጊዜ ነበር ታዲያ ሔሮድስ ንስሐ ባለመግባቱ ዛሬ ተቀስፎ ሞተ፤ ስደተኛዋእመቤታችን ወደ ናዝሬት ስትመለስ አሳዳጁ ሔሮድስ ከእግዚአብሔር መንግሥት ለዘለዓለም ተሰደደ፤ ሕጻኑንና እናቱን ይዘህ ሽሽ ብሎ ስደቱን የነገረው መላክ ዛሬ ደግሞ ወደ ምድረ እስራኤል ተመለስ ብሎ ነገረው፤ በዚሁ ዕለት ደብረ ቁስቋም ገብተው አድረዋልና ደብረ ምዕራፍ ተብሎ ተተረጎመ፡፡
የምድረ በዳው ጉዞ፣ የበረኃው ስቃይ፣ የግብፅ ዋዕይ፣ የሽፍቶቹ ማንገላታት፣ የሔሮድስ ሰራዊት ከሰባ፣ የሦስት ዓመት ረሀብና ጥም፣ የነኮቲባ ክፉ ወሬ፣ ይሄ ሁሉ መከራ ዛሬ ተጠናቀቀ፤ ማደሪያ የሌላት ዖፍ ብሎ ቅዱስ ዳዊት የዘመረላት ፀዓዳ ዖፍ ድንግል ማርያም ዛሬ ማረፊያ አገኘች ይህችውም ደብረ ቁስቋም ናት፡፡ እንዴት ደስ ይላል ከረጅም የመከራ ወራት በኋላ የተሰማ የምሥራች ነው ደሞ የምሥራቹን ታላቅ የሚያደርገው የሕጻኑን ነፍስ የሚሹት መሞታቸው ነው፡፡ የገደላቸው ሕጻናት ብዙ ናቸው በእናታቸው እቅፍ ላይ እያሉ አንቀው የገደሏቸው አሉ ጡት እየጠቡ ሳሉ ነጥቀው በሰይፍ የቀሏቸው አሉ፤ ተኝተው ሳሉ ከእናቶቻቸው ጀርባ እያወረዱ የጨፈጨፏቸውም ብዙ ናቸው፤ የእናቶቻቸው ልብስ በደም ተነከረ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ ቤተ ልሔምና አካባቢዋ በጩኸት ተሞላች፤ አስቀድሞ በነቢይ እንደተባለ ‹‹ራሔል ስለልጆቿ አለቀሰች በራሔል ልጆች ርስት ላይ የተፈፀመ ጭፍጨፋ ስለሆነና የራሔልም መቃብር በገሊላ አውራጃ ውስጥ ስለነበረ ነው ከአራቱ የእስራኤል ልጆች እናቶች መካከል ራሔልን ለይቶ ይጠራታል፡፡
ሞትን በሰው ልጆች ላይ የፈረደው ንጉሡ ሔሮድስ እሱም በሰማዩ ንጉሥ ሞት ተፈርዶበት መቃብር ወረደ፡፡ እገለዋለሁ ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በኃጢአት የሞተውን ዓለም ለማዳን ኃጢአት ወደ በዛባቸው ሰዎች ሂዶ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ጎበኛቸው፤ ከዚህም በኋላ ወደ ተቀደሰችው ከተማ ለመግባት ያሰበ አይደለም፤ ኃጢአት ወደፀናባት ከተማ ወደ ናዝሬት ተመለሰ።
በእርግጥ የመጨረሻ ድል አይደለምና በክፉው ሔሮድስ ፋንታ ልጁ ነው የነገሠው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ኃጥዕ ሔሮድስን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት ብመለስ ግን አጣሁት ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም›› መዝ 36÷35 የሚለውን የአባቷን መዝሙር እየዘመረች ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡
ደብረ ቁስቋም የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ ነው፡፡ እመቤታችንና አብረዋት የተሰደዱት ሰዎች የምዕመናን ምሳሌዎች ናቸው፤ ምዕመናን የሰማይና የምድር ፈጣሪ ከነእርሱ ጋር እያለ በክፉዎች ምክንያት ይሰደዳሉ፤ እውነትን ይዘው ከሀገር ሀገር ይንገላታሉ፤ በምድረ በዳ ማደሪያ በማጣት፣ በረሀብ በጥምና በእርዛት ይፈተናሉ ነገር ግን ለነፍሳቸው የሚሆን ማረፊያን ፍለጋ እየተጓዙ እንደሆኑ በማሰብ ይፀናሉ፤ በመጨረሻም የጠላታቸውን የዲያብሎስን መሞት ይሰማሉ፤ ለቤተ ክርስቲያን ታላቁ የምሥራች የዲያብሎስ ድል መነሣት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዲያብሎስን በሃይማትና በምግባር ገድላ ራሷን ወደ ማረፊያው ተራራ ወደ ደብረ ጽዮን ታስጠጋለች፡፡ የዛሬው በዓል ቤት አልባ የነበረችው የሰው ልጆች ሕይወት ማረፊያ ያገኘችበት ቀን ነው፤ ስደቱ ቤተ ክርስቲያን በሐሳዊ መሢህ ዘመን የሚደርስባት ስደት መነሻ ነውና የተደረገውም ዕረፍት ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር መንግሥት ለምታገኘው ዕረፍት ማሳያ ነው፡፡ ለዚህ እኮነው መላዕክትም በልጇና በእርሷ ላይ ክንፋቸውን እየጋረዱ ምስጋን ያቀረቡት ቅዱስ ያሬድም ‹‹ዮም ፀለሉ መላዕክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም፤ መላዕክት በልጇና በእርሷ ላይ ክንፋቸውን እየጋረዱ አመሰገኑ›› ብሎ ይናገራል፡፡ መላዕክትን ሳይቀር ያስደሰተ ታላቅ ዕረፍት፡፡
#እግዚአብሔር ዕረፍት በሌለባት ዓለም ውስጥ ስንኖር ዕረፍትን ለሁላንም ያድለን፡፡
🌹መልካም በዓል 🌹
ምንጭ፦የሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ የጡመራ ገጽ!

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 17:27


የአርብ ጸ ሎ ት ⭐️⭐️⭐️

💠በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።💠                                                            🌹ሁላችንም ተቀሳቅሰን የ አርብ ጸሎትን እናድርስ🌹
  
🙏🏼ጸሎት ዘር ነውና "መከር" አለው
🙏🏼ጸሎት እንባ ነውና "ሳቅ" አለው
🙏🏼ጸሎት ትግል ነውና "ድል"  አለው
🙏🏼ጸሎት ጩኸት ነውና "መልስ" አለው
🙏🏼ጸሎት መተንፈስ ነውና "ሕይወት" አለው
🙏🏼ጸሎት ንግግር ነውና "ማስተዋል" አለው
🙏🏼ጸሎት መራቆት  ነውና "ጸጋ" አለው
https://t.me/JuWanaGibiGG
🏠         በጽርሐ ጽዮን (ታች ቤት)
🕐              ከጠዋቱ 12:15 ።

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

13 Nov, 18:35


https://youtu.be/V4JCjqtKLfA?si=wP12rM_hTSorBorN

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

13 Nov, 18:23


🌿የዝማሬ ጊዜ🌿
ዘውትር ረቡዕ ምሽት 3:30 ላይ ልዮ ልዮ ጣዕመ ዝማሬዎችን በዮቲዮብ ቻናላችን ላይ ያግኙ
  በግቢጉኤያችን ዮቲዮብ ቻናል ላይ ብቻ !!! 

👉ለምታውቁት ሰዎች በመላክ እንድታበረቱን እና በጸሎታችሁ እንድታስቡን እንጠይቃችዋለን።                                     
http://www.youtube.com/@JimmaMainCampusGibiGubae                  
 👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼  👇🏼 ስለ ግቢ ጉቤኤያችንን አገልግሎት የተለያዩ መረጃዎችን ምታገኙባቸው የ telegram channel

የግቢ ጉባኤያችን official telegram channel
፨https://t.me/JuWanaGibiGG
     የተለያዩ መርሃ ግብራት photoዎች
፨https://t.me/juwanagibigubaepics   
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቤተመጽሐፍት አገልግሎት
https://t.me/AGZBM

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

08 Nov, 21:23


💐🌹💐 የልደታ ጽዋዕ 💐🌹💐

ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ
ወሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ

ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ
ሰማያቸውም ፀሐይን አወጣች
።።።።።።።ነግሥ።።።።።።።።።

💐እንኳን ለእመቤታችን ፀሐይን ላወጣችልን ምሥራቃችን እመ መለኮት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ የልደት በዓል አደረሳችሁ😍፤ እያልን የአጠቃላይ የግቢ ጉባዔያችን ጽዋዕ ላይ ይገኙ ዘንድ በእንተ ልደታ ለማርያም ብለን ጠርተንዎታል።

🌹ህዳር 1 (እሁድ)
💐11:45 ጀምሮ
🌹በሐ/ኖ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ አውደ ምሕረት

💐በየባች፣የክፍላትና የጽዋ ግሩፖች ላይ እናጋራ።በአካልም እንቀሳቀስ💐

@JuWanaGibiGG

#share #share #share

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

08 Nov, 19:21


https://youtu.be/tpv_TU3CvoQ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

08 Nov, 15:22


"ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው"
  ኑ ከአባቶቻችንና ከእናቶቻችን ምርቃት እንካፈል

ቦታ:- ግሪን
ሰዓት:- 2:45 ጠዋት
ዕለት፦ ቅዳሜ (30/2/2016 ዓ.ም)

N.B ሰዓት ይከበር!
#ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሞያና በጎ አድራጎት ክፍል

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Nov, 15:47


"አቤት ሲያማምሩ"🤩 አላሉም ? እነኚህን የመሰሉ የተዋቡ ቤተ ክርስቲያናዊ ስርዓታቸውን የጠበቁ ቅዱሳን ስዕላትንስ በእጆ መሳል አልተመኙም? በርግጠኝነት ተመኝተዋል !
ታድያ መጥተው ለምን አይስሉም?
" መሳል አልችልም......."🤔 ሲሉ ሰማው ልበል ?

ግድ የሎትም ኑ "ቅዱሳን ሥዕላትን ለመማር ፍላጎት እንጂ ችሎታ አያስፈልግም "

እርሶ ብቻ ወረቀት እና እርሳስዎን ይዘው ይምጡ!
"እጆን ቀርጾ ማስተካከል የኛ ስራ ነው" እርሶ ብቻ ይምጡ!!!🎨

አነኚያን የተዋቡ ቅዱሳን ሥዕላት በራስዎ እጅ ይስላሉ!!!💡

—ሥዕል በነፃ ማን ይጠላል😋

ዘወትር ቅዳሜ ከ4-6 ሰዓት
💒ቁ.3 አዳራሽ

በጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ መዝሙር እና ኪነ ጥበብ ክፍል በቅዱሳን ሥዕላት ንዑስ ክፍል የተሰናዳ...

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Nov, 04:32


💠💠💠✞✞✞💠💠💠
ርቱዓ ሃይማኖት የጌታችንን ሞት አስመልክቶ ከደረሰው ይህንን ተካፈሉ። ["ርቱዓ ሃይማኖት" ማለት ሃይማኖቱ የቀና፣ የማታወላውል ቀጥተኛ ሃይማኖት ያለው ማለት ነው]
____

+ ጌታዬ ሆይ፡ በመስቀል ላይ ተሰቅለህ መሞትህን ሳስብ አለቅሳለሁ፤ የመስቀልህ ጥላ ሙታንን እንዳስነሳ ሳስብ ደግሞ አደንቃለሁ።

+ መስቀሉ ላይ ራስህን ዘንበል ማድረግህን አስባለሁ፤ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሄደህ፡ የብረት ሰንሰለቶችን ፈትተህ፡ አዳምንና ልጆቹን ወደ ርስታቸው ወደ ገነት በመመለስህ እደሰታለሁ።

+ ነፍስህ ከሥጋህ መለየቷን አስቤ አለቅሳለሁ፤ በቀኝህ ለተሰቀለው ወንበዴ ለ5533 ዓመታት ተዘግታ የነበረች ገንትን በመክፈትህ ደግሞ እደሰታለሁ።

+ በመስቀል ላይ በችንካር መችንከርህን ሳስብ አለቅሳለሁ፤ ፀሐይ በመጨለሟ ደግሞ እደነግጣለሁ።

+ መስቀል ላይ ዕርቃንህን ሳይህ አለቅሳለሁ፤ ቀኑ ጨልሞ ሌሊት መሆኑን ሳስብ ደግሞ አደንቃለሁ።

+ ራስህን እየመቱ “ክርስቶስ ሆይ ትንቢት ተናገር” ማለታቸውን ሳስብ አለቅሳለሁ፤ እልፍ አዕላፍ የሚሆኑ ቅዱሳን መላዕክት፡ “ቅዱስ እግዚአብሔር፡ ቅዱስ ኃያል፡ ቅዱስ ሕያው የማይሞት፤ በዕፀ መስቀል ላይ የተሰቀለ” እያሉ በመስቀልህ ዙሪያ ተነጥፈው ማመስገናቸውን ሳሰላስል ደግሞ ሐሴት አደርጋለሁ።

+ በሰፍነግ ሐሞት እንዳጠጡህ አስቤ አለቅሳለሁ፤ ከጎንህ ደምና ንጹህ ውሃ ወጥቶ፡ መስቀልህ ሥር ያለውን ዓለት ሰንጥቆ የአዳም መቃብር መድረሱን ሳስብ ደግሞ እገረማለሁ።

+ ፊትህ ላይ ምራቃቸውን በመትፋታቸው አለቅሳለሁ፤ ዕውር ሆኖ የተወለደውን፡ በምራቅህ መፈወስህን አስቤ ደግሞ እደሰታለሁ።

+ የብረት ሰንሰለት በአንገትህ ከትተው መጎተታቸውን አስቤ አለቅሳለሁ፤ ሰይጣን ያሰራቸውን በቃልህ መፍታትህን ሳስብ ደግሞ አደንቃለሁ።

+ በጲላጦስ ፊት ታስረህ መቆምህን አስቤ አለቅሳለሁ፤ በባህር ላይ እንደ ደረቅ መሬት መሄድህንና ነፋሳትን መገሰጽህን ሳስብ ደግሞ በእጅጉ እደነቃለሁ፡፡

+ ሊቃነ ካህናቱ እና ሕዝቡ “ስቀለው፡ ስቀለው” እያሉ በመጮሃቸው አለቅሳለሁ፤ ነቢያት ያዩህ ዘንድ እንደተመኙ ሳስብ ደግሞ እገረማለሁ።

+ በሁለት ወንበዴዎች መሃል መሰቀልህን አስቤ አለቅሳለሁ፤ በደብረ ታቦር በሙሴና በኤልያስ ፊት የመለኮትህ ብርሃን ማንጸባረቁንና የመንግሥትህ ግርማ መገለጡን ሳስብ ደግሞ እደሰታለሁ።

+መስቀልህን እስከ ቀራንዮ ድረስ በመሸከምህ አለቅሳለሁ፤ መጻጕዕን “ኃጢአትህ ተትቶልሀል፡ ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ያልከውን አስቤ ደግሞ እደሰታለሁ።

+ ሊቃነ ካህናቱ ሐና እና ቀያፋ “ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሁን” ማለታቸውን ሳስብ አዝናለሁ፤ ለ12 ዓመታት ደም ይፈስሳት የነበረችይቱን ሴት መፈወስህን ሳስብ ግን እደሰታለሁ።

+ ይሁዳ በ30 ብር እንደሸጠህ ሳስብ አለቅሳለሁ፤ ጴጥሮስን ከዓሣ ሆድ ዲናር አውጥቶ ለሄሮድስ መልዕክተኞች ግብር እንዲከፍል ማዘዝህን ሳስብ ደግሞ አደንቃለሁ።

+ መስቀል ላይ ሆነህ “ተጠማሁ” በማለትህ አለቅሳለሁ፤ በቃና ዘገሊላ ውሃን ወደ ወይን ጠጅ መለወጥህን አስቤ አደንቃለሁ።

+ እናትህ ድንግል ማርያም ከዮሐንስ ጋር ሆና የመስቀል ስቃይህንና ሞትህን በማየቷ አለቅሳለሁ፤ መልአኩ ገብርኤል “ካንቺ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም” ያላትን አስቤ ደግሞ እደሰታለሁ።

+ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ለመግነዝህ የሚሆን በፍታ መግዛታቸውን አስቤ አለቅሳለሁ፤ በታቦር ተራራ ላይ ልብስህ በሚያንጸባርቅ መልኩ ነጭ እንደነበር ሳስብ ደግሞ እደሰታለሁ።

+ ሥጋህን ለመቅበር አዲስ መቃብር መፈለጋቸውን ሳስብ አለቅሳለሁ፤ አልአዛርን ከ4 ቀናት በኋላ ከመቃብር አውጥተህ በማስነሳትህ ደግሞ እደሰታለሁ።

+ መራራ ሐሞት እንዳጠጡህ አስቤ አለቅሳለሁ፤ በ5 እንጀራ 5000 ሕዝብ ማጥገብህን ሳስብ ደግሞ እደነቃለሁ።

+ መቃብርህን በታላቅ ድንጋይ መዝጋታቸውን አስቤ አለቅሳለሁ፤ በመሰቀልህ ምክንያት መላዋ ምድር በመናወጿ ደግሞ እገረማለሁ።

+ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንደገነዙህ አስቤ አለቅሳለሁ፤ በልደትህ አህያና ላም በትንፋሻቸው እንዳሟሟቁህ አስታውሼ ደግሞ እደነቃለሁ።

+ በከርሠ መቃብር ማደርህን አስቤ አለቅሳለሁ፤ መስቀል ላይ ሳለህ ጎንህን በጦር የወጋውን ወታደር፡ የታወረችውን አንድ ዓይኑን ከጎንህ በፈሰሰው ደም መፈወስህን እያሰብኩ አደነቃለሁ።

+ የመስቀል ስቃይህን አስቤ በእጅጉ አለቅሳለሁ፤ በቀኝህ የተሰቀለውን ወንበዴ፡ “ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” በማለትህ ደግሞ እደሰታለሁ።

በሊቀ ሊቃውንት ስማኮነ መላክ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

06 Nov, 04:22


#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ

ከቤተ ዮሐንስ አፈወርቅ ቻናል የተወሰደ

እንኳን አደረሳችሁ🙏

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

05 Nov, 16:30


✞ተግባራዊ ክርስትና... ✞   (ጾም፣ጸሎት፣ ምጽዋት ...)

በጾም ቀናት ለነዳያን ቸርነትን ማድረግ ይገባልና፤ የቁርስዎን ዳቦ🍞 ለመሰብሰብ ዘወትር ረቡዕእና አርብ እስከ ጠዋቱ 2:30 ድረስ ቆሎ በር ጋር በጉጉት እንጠብቅዎታለን።

💠ቆሎ በር

የዕለት ጉርስ ለሌላቸው የአቅማችንን እናድርግ🙏

#ጾም_ያለጸሎትና_ያለምጽዋት_የረሃብ_አድማ_ነውና_የቁርሴን_ዳቦ_ለነዳያን!

👉ለእኛ ቀላል ሊመስለን ይችላል፤ ለአንዳንዶች ግን የዕለት ጉርስ ነው።
#ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሞያና በጎ አድራጎት ክፍል

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

03 Nov, 11:05


ለጥበብ አፍቃርያን በሙሉ🤗
እንደምን አላችሁ ድርሰት በሕብረታችን
እንደልማዷ በሰንበት በጥበብ ታሰባስበናለች ታድያ ከርሶ ሚጠበቀው ብዕሮንአንግበው በድግስ ልብሳችን በ ነጠላዎ አምረዉ ደምቀው መገኘት ብቻ ነዉ😌

አደራ!!! ለጥበብ ፍቅሩ ያላችሁ እና መታደም የምትፈልጉ ሁላችሁም አትቅሩብን

📌እሁድ ምሽት 12 ሰዓት

📌 ታች ቤት

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

31 Oct, 12:37


የአርብ ጸ ሎ ት ⭐️⭐️⭐️

💠በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።💠 🌹ሁላችንም ተቀሳቅሰን የአመቱ የመጀመርያውን የ አርብ ጸሎት እናድርስ🌹
  
🙏🏼ጸሎት ዘር ነውና "መከር" አለው
🙏🏼ጸሎት እንባ ነውና "ሳቅ" አለው
🙏🏼ጸሎት ትግል ነውና "ድል"  አለው
🙏🏼ጸሎት ጩኸት ነውና "መልስ" አለው
🙏🏼ጸሎት መተንፈስ ነውና "ሕይወት" አለው
🙏🏼ጸሎት ንግግር ነውና "ማስተዋል" አለው
🙏🏼ጸሎት መራቆት  ነውና "ጸጋ" አለው
https://t.me/JuWanaGibiGG
🏠 በጽርሐ ጽዮን (ታች ቤት)
🕐 ከጠዋቱ 12:15 ።

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

30 Oct, 07:39


ንብ የምትሞተው መቼ ነው?
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“የጥበበኛ ነፍስ መገለጫዋ ይሄ ነውና ሁል ጊዜ የምታመሰግኑ ሁኑ፡፡ ክፉ ደረሰባችሁን? ይህስ እናንተ ከፈቀዳችሁ ክፉ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ አመስግኑ፤ ክፉ የሆነባችሁም መልካም ይሆንላችኋል፡፡ ከተወደደው ኢዮብ ጋር ሆናችሁ “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን” እያላችሁ አመስግኑ /ኢዮብ.1፥21/፡፡

እስኪ ንገሩኝ! ደረሰብኝ የምትሉት ክፉ ነገር ምንድነው? በሽታ ነውን? ታድያ ይሄ እኮ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሥጋችን መዋቲና ለስቃይ የተጋለጠ ነውና፡፡ ሀብት ንብረት ማግኘት አለብኝ የሚል መሻት ነውን? ታድያ ይሄ እኮ ምግኘት የሚቻል ነው፤ ካገኙት በኋላ ግን መልሶ የሚጠፋና በዚህ ዓለም ብቻ የሚቀር ነው፡፡ ከወንድሞች የሚደርስ ሐሜትና የሐሰት ወቀሳ ነውን? ታድያ ተጐጂዎቹ’ኮ የሚያሙንና በሐሰት የሚመሰክሩብን እንጂ እኛው አይደለንም፡፡ “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች” እንዲል ተጐጂዎቹ ይህን ኃጢአት የሚሠሩት እንጂ እኛው አይደለንም /ሕዝ.18፥4/፡፡ ተጐጂው ምንም በደል ሳይኖርበት ክፉ የሚደርስበት ሰው ሳይሆን ክፉ የሚያደርሰው ሰው ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምዉት በሆነ ሰው ልትቈጡ አይገባም፤ ከዚያ ይልቅ ከሞት ይድን ዘንድ ልትጸልዩለት ይገባል፡፡

ንብ መቼ እንደምትሞት አይታችሁ ታውቃላችሁን? የምትሞተው ሌላውን ስትናደፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህች ፍጥረት በወንድሞቻችን ላይ ልንቈጣ እንዳይገባን ያስተምረናል፡፡ እኛው የምንቈጣ (የምንናደፍ) ከሆነ ግን ቀድመን የምንሞተው እኛው ነን፡፡ ስንቈጣቸው የጐዳናቸው ይመስለን ይሆናል፤ ነገር ግን እንደዚያች ንብ ተጐጂዎቹ እኛው ነን፡፡”
@JuWanaGibiGG
@JuWanaGibiGG
@JuWanaGibiGG
ከቤተ ዮሐንስ አፈወርቅ ቻናል የተወሰደ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Oct, 14:16


አጥር ስለፈረሰ ግር እንዳይለን ሰማያዊውን በር ይጠቀሙ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

28 Oct, 17:16


የቅዱስ ገብርኤል ጽዋ

እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ወርሐዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳቹ።

ማክሰኞ 19/2/17 የቅዱስ ገብርኤል ጽዋ በታች ቤት  ሰላሚኖረን ጽዋውን ለመቅመስ ሁላችንም ከጎን ያሉ ጓደኞቻችንን  ቀስቅሰን እንድንገኝ በመላኩ ስም ተጠርታችኋል።

ሰዓት:11:30 መርሐግብሩ ይጀምራል
ቦታ:ታች ቤት(ጽርሐጽዮን)

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Oct, 06:44


📣 እንኳን ደህና መጣችሁ!📣🥰
🌹“... መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ" (ዕብ 10፥25)🌹

በክቡር ደሙ የተዛመድን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ?
ከያለንበት ሰብስቦ በቸርነቱ ብዛት ለዚህች ሰዓት ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን።

በናፍኖት ስትጠብቀን የቆየችው ውዷ ግቢ ጉባኤያችን "ልጆቼ" እንኳን ደህና መጣችሁ ልትለን ለሁለት ቀናት ልዩ ጉባኤ አሰናድታለች።😊
በመርሃ ግብሩም:-
ወቅቱን የዋጁ አጫጭር ጥዑም ሥልጠናዎች
ሥነ ጥበባዊ ሥራዎችና ዝማሬዎች ይጠብቁናል።

🗓 ቀን- 16 እና 17 /2/2017 ዓ.ም
🕙 3:30❗️(ከቅዳሴ በኋላ)
ዕለት: ቅዳሜና እሑድ
📌በጅማ ሐ/ኖ/ቅ/ኪ/ምህረት ቤ/ክ አዳራሽ(ቁ.1)

እናንተም ላልሰሙ ኦርቶዶክሳውያን በማሰማት በሰዓቱ ተገኙ🙏
ክርስቲያን ከመድረሱ ቤተ እግዚአብሔር መገስገሱ😊
የኖኅ መርከብ ክፍት ናት ፈጥነን እንሳፈር!
በሰላም ያድርሰን።

#ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግቢ ጉባኤ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

24 Oct, 18:35


📣 እንኳን ደህና መጣችሁ!📣🥰
🌹“... መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ" (ዕብ 10፥25)🌹

በክቡር ደሙ የተዛመድን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ?
ከያለንበት ሰብስቦ በቸርነቱ ብዛት ለዚህች ሰዓት ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን።

በናፍኖት ስትጠብቀን የቆየችው ውዷ ግቢ ጉባኤያችን "ልጆቼ" እንኳን ደህና መጣችሁ ልትለን ለሁለት ቀናት ልዩ ጉባኤ አሰናድታለች።😊
በመርሃ ግብሩም:-
ወቅቱን የዋጁ አጫጭር ጥዑም ሥልጠናዎች
ሥነ ጥበባዊ ሥራዎችና ዝማሬዎች ይጠብቁናል።

🗓 ቀን- 16 እና 17 /2/2017 ዓ.ም
🕙 3:30❗️(ከቅዳሴ በኋላ)
ዕለት: ቅዳሜና እሑድ
📌በጅማ ሐ/ኖ/ቅ/ኪ/ምህረት ቤ/ክ አዳራሽ(ቁ.1)

እናንተም ላልሰሙ ኦርቶዶክሳውያን በማሰማት በሰዓቱ ተገኙ🙏
ክርስቲያን ከመድረሱ ቤተ እግዚአብሔር መገስገሱ😊
የኖኅ መርከብ ክፍት ናት ፈጥነን እንሳፈር!
በሰላም ያድርሰን።

#ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግቢ ጉባኤ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

24 Oct, 10:21


📣 እንኳን ደህና መጣችሁ!📣🥰
🌹“... መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ" (ዕብ 10፥25)🌹

በክቡር ደሙ የተዛመድን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ?
ከያለንበት ሰብስቦ በቸርነቱ ብዛት ለዚህች ሰዓት ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን።

በናፍኖት ስትጠብቀን የቆየችው ውዷ ግቢ ጉባኤያችን "ልጆቼ" እንኳን ደህና መጣችሁ ልትለን ለሁለት ቀናት ልዩ ጉባኤ አሰናድታለች።😊
በመርሃ ግብሩም:-
ወቅቱን የዋጁ አጫጭር ጥዑም ሥልጠናዎች
ሥነ ጥበባዊ ሥራዎችና ዝማሬዎች ይጠብቁናል።

🗓 ቀን- 16 እና 17 /2/2017 ዓ.ም
🕙 3:30(ከቅዳሴ በኋላ)
ዕለት: ቅዳሜና እሑድ
📌በጅማ ሐ/ኖ/ቅ/ኪ/ምህረት ቤ/ክ አዳራሽ(ቁ.1)

እናንተም ላልሰሙ ኦርቶዶክሳውያን በማሰማት በሰዓቱ ተገኙ🙏
ክርስቲያን ከመድረሱ ቤተ እግዚአብሔር መገስገሱ😊
የኖኅ መርከብ ክፍት ናት ፈጥነን እንሳፈር!
በሰላም ያድርሰን።

#ጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግቢ ጉባኤ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 11:49


++  ኑ  -   አብረን እንሰደድ   ++
                  ❖ ❖
ጌታ ከተወለደ ሁለት ዓመት ሞላው። ንጉሥ አልባዋ ቤተ አይሁድ ንጉሥ ተወለደላት። ትንቢቱ መሥዋዕቱ የዚህን ሕጻን ልደት ፍለጋ የተደረገ ደጅ ጥናት ነበረ። አብርሃም ከሀገሩ የወጣው ከዘመዶቹ የተለየው፤ ይሥሐቅ በአባቱ እጅ የተሠዋው፤ ያዕቆብ በላባ ቤት የበግ እረኛ ሁኖ የተቀጠረው እዚህ ለመድረስ ነበር። ነገር ግን ይህን ሁሉ ልብ ያለው የለም።

ሁለት ዓመት ሲሞላው ሰብአ ሰገል ወርቅ እጣን ከርቤ ገበሩለት። ነገሥታቱ እጅ መንሻ አቅርበው ከተመለሱ በኋላ መልአኩ ገብርኤል መጥቶ ለዮሴፍ "ሔሮድስ ሕጻኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ሕጻኑንና እናቱን ይዘህ ሽሽ" ብሎ ነገረው።

ሰብአ ሰገል ከጌታ ጋር አብረው እንዲሰደዱ ወይም ጌታን ይዘው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አልተፈቀደላቸውም። በሳጥናቸው ወርቅ ይዘው መጥተው ወርቅ የሆነች ሃይማኖት በልባቸው ይዘው ተመለሱ። የነሱን እጅ መንሻ ከተቀበለ በኋላ ሳይውል ሳያድር ተሰደደ።

ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ በቀር አብሮ ለመሰደድ የተፈቀደለት የለም።

ጌታ ባደረበት ለማደር በዋለበት ለመዋል አብሮ መሰደድ ምንኛ መልካም ነው!?
• ዮሴፍ ሆይ በገሊላ ከቀሩ ሰዎች ይልቅ አንተ ብፁዕ ነህ፤ ጌታ ከሌለባት ከተማ ጌታ ያለባት ምድረ በዳ ትበልጣለችና።
• አረጋዊ ሆይ በግብፅ ምድረ በዳ ያገለገልኸው መላእክት በሰማይ የሚያገለግሉትን ነው።
•  ዮሴፍ ሆይ ሕጻኑና እናቱ በተሰደዱበት ምድረ በዳ ከዓለት ላይ ውኃ ፈሰሰ። ሕጻኑን ካሳደደችው ከተማ ግን ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ። የሕጻናቱ ደም በግፍ ሲፈስ ዓይኖችህ እንዳያዩ ሊሠውርህ አብረህ ተሰደድህ።
• አረጋዊ ዮሴፍ ሆይ ኢሳይያስ ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ሁኖ በራዕይ ያየውን ጌታ አንተ በገሊላዊቷ ብላቴና ጀርባ ታዝሎ አየኸው።
• አረጋዊ ሆይ ነቢዩ ዳዊት "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱርም መካከል አገኘነው" ብሎ በመንፈስ የዘመረለትን ሕጻን በግብፅ በረሃ መጓዝ ተስኖት እናቱ እንድታዝለው አንጋጦ እየለመነ ሲያለቅስ ሰማኸው።
✿ ኦ ወዮ እንደ ምን ያለ ድንቅ ነው!?
በአርያም የሚያድር ጌታ በግብፅ ምድረ በዳ አደረ። ከሰው ሁሉ ተመርጠው ከሱ ጋር በምድረ በዳ ያደሩ ሰዎች ምንኛ የታደሉ ናቸው?!  እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በዱር እያደሩ በምድረ በዳ እየኖሩ ከሱ ጋር በልባቸው የሚሰደዱ ቅዱሳን ብዙ ናቸው።
እኛም አብረን እንሰደድ።

ከድንግል ጋር አብረን እናልቅስ።

ኑ! እሾኽ ሲወጋት እንቅፋት ሲመታት ተመልክተን እናንባ።
ኑ! ለልጇ የምታጠጣው እፍኝ ውኃ የቸገራትን ሴት እመቤታችንን እንያት።
ኑ! የልጇን ጫማ ሽፍቶች የወሰዱባትን ሴት ተመልከቷት።
ኑ! መልአኩ ፋኑኤል የመገባትን ብላቴና በግብፅ ከበርቴዎች በር ቆማ ስትለምን ስሟት።
ኑ! የኪሩቤል ክንፍ የሚጋርዳትን እመቤት ግብፃዊቷ ስትመታት ልጇንም ከጇ ነጥቃ ከዓለት ላይ ስትጥልባት ተመልከቱ።
ይህን ግፍ ታዩ ዘንድ ኑ! በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል የተባለው ሊፈጸምባት ልቧ እጅግ አዘነ። ኮቲባ መሬት ላይ የጣለችው ልጇን ለማንሣት ብክንክን ስትል እናያት ዘንድ ኑ! ክርስቲያኖች ሆይ !
"እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅን ትወልጃለሽ ብሎ ያበሠረኝ መልአክ ወዴት አለ" እያለች በግብፅ ጎዳና ወድቃ የምታለቅሰዋን ብላቴና ታረጋጓት ዘንድ ኑ።

ከወደዳችኋትማ አብረናት እንሰደድ። ባለ በገናው ዳዊት፣ ባለ መሰንቆው ዕዝራ ወዴት አሉ? ያዘነች የተከዘች እመቤታችንን ለማጽናናት ይምጡ። በቤተ መቅደስ ያረጋጓት መላእክት ወዴት ሄዱ በግብፅ ቆላ ፀሐይ እንዳያቃጥላት ክንፋቸውን ይዘርጉላት።

➊ አብረን እንሰደድ ፡--
የዮሴፍ በትሮች ሲለመልሙና በግብፅ አሸዋ ላይ ተተክለው ትልቅ ዛፍ ሲሆኑ እናያለን።
አብረን እንሰደድ፦ ሰሎሜ እንዳዘለችው እኛም በዘባነ ልቡናችን በእምነት እናዝለዋለን።
አብረን እንሰደድ፦ እንደ ሔሮድስ ከመቀሰፍ እንድናለን።
አብረን እንሰደድ፦ በመከራው ከተሳተፍነው በክብሩ ሲገለጥ ከእርሱ ጋር እንነግሣለን።
አብረን እንሰደድ፦ በከተማ ከዘገየው ከዮሳ ጋር እንዳይፈረድብን።
አብረን እንሰደድ፦ አብረን እንመለሳለን።

        ( በሊቀ ሊቃወውንት ስምዐ ኮነ መልአክ )

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

15 Oct, 06:34


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

"ተፈሳህኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር" መዝ 122÷1

ውዳሴዋን ልንማር😍
ዳዊቱም ሊደገም🙏
ዜማውንም ልንቀሽረው😊

አብነት ቤታችን ኑ ልጆቼ ትለናለች...

ከረቡዕ ማለትም በ06/2/17

በቁጥር 2 አዳራሽ

ከ10.30-12.00
.
.
.
መቅረት አያዋጣም👆

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

05 Oct, 13:22


ዘመነ ክረምት ቡሩክ ዮም ተፈጸመ፤
በሰላመ እግዚአብሔር መሐሪ ዘእንበለ ንርአይ ሕማመ፤
በእንተ ዝንቱ ነአኲቶ ለዘፈጠረ ዓለመ፤
በእንተ ማርያም ድንግል ዘረሰያ እመ፤
ከመ ያብጽሐነ በኂሩቱ ዓመ ከመ ዮም ዳግመ!

ዝክረ ቅዱሳን - ርቱዓነ ሃይማኖት


"ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘመነ ጽጌ እንግዳ
ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ
ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ
ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ
ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሃሊብ ፀዓዳ" - ማኅሌተ ጽጌ


እንኳን ለምንናፍቃት የጽጌ ዘመን በሰላም አደረሰን። ዘመኑን በሰላም አስፈጽሞ እመቤታችን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ጋር ከስደት ወደ ሀገርዋ ለምትመለስበት ዘመን በሰላም በፍቅር በአንድነት ያድርሰን።🌹

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

02 Oct, 08:00


“ወዳጄ ሆይ!
የትዕቢት መርዝ ተጠራቅሞ አብጦብሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ስለ ወዳጆቹ ሲል አርአያ ገብርን የነሣ ትሑቱ ጌታም ትሕትናን ያስተምርሃል፡፡

የስግብግብነት ትኩሳት አስቸግሮሃልን? ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ደግነትንም ትማራለህ፡፡

የምቀኝነት ብርድ አስቸግሮሃልን? እንኪያስ ወደ ሰማያዊው መዓድ ቅረብ፤ ምህረት ማድረግንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡

ትዕግሥትን የማጣት እከክ ይዞሃልን? እንኪያስ ወደ ቅዱስ ሥጋዉና ክቡር ደሙ ቅረብ፤ ራስን መግዛትንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትህ ልል ዘሊል ብትሆን ይህን መንፈሳዊ መዓድ ተመገብና ብርቱ ትሆናለህ፡፡

ቆሽሸሃልን? እንኪያስ ወደዚሁ መብልና መጠጥ ቅረብ ብዬ እመክርሃለሁ፤ ንጽሕናንም ገንዘብ ታደርጋለህ፡፡”

ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

28 Sep, 16:12


የቅዱስ ገብርኤል ጽዋ

እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ወርሐዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳቹ።

እሑድ 19/1/17 የቅዱስ ገብርኤል ጽዋ በታች ቤት  ሰላሚኖረን ጽዋውን ለመቅመስ ሁላችንም ከጎን ያሉ ጓደኞቻችንን ቀስቅሰን እንድንገኝ በመላኩ ስም ተጠርታችኋል።

ሰዓት:11:30 መርሐግብሩ ይጀምራል
ቦታ:ታች ቤት(ጽርሐጽዮን)

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Sep, 19:05


ሰላም እንዴት አመሻችሁ
     የነገው መርሃግብር ሰዓት ወደ 9:30 ስለተቀየረ ሁላችንም ግቢ ውስጥ ያለን ተማሪዎች ሰዓቱን አክብረን በታች ቤት እንገናኝ::

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

26 Sep, 07:53


ከ medicine ተማሪዎች ውጭ ላላችሁ ተማሪዎች ምዝገባ መራዘሙን እንድታውቁ እናሳስባለን።

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

25 Sep, 16:42


✝️✝️እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ!!!!✝️✝️

☦️የደመራና የመስቀል በዓልን እኛ በግቢ ውስጥ ያለን ተማሪዎች በግቢ ጉባኤ በጋራ ለማክበር እንችል ዘንድ ፦
    📌ነገ ሃሙስ በዕለተ ደመራ 6:30 ላይ  በሐመረኖኅ ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤ/ክ ተገናኝተን ባማሩ ዝማሬዎች ወደ መስቀል አደባባይ(አዌቱ) እንሔዳለን ሁላችንም ተቀሳቅሰን እንገናኝ።
ደመራ ከበራ በኋላ በዝማሬ ታጅበን ወደ ግቢያችን ስለምንመለስ አዌቱ ሆቴል ፊትለፊት እንሰባሰብ።
    📌በተጨማሪም የጌታችንን የመስቀል በዓል አርብ ከቀኑ 10:30 ላይ በታች ቤት በተለያዩ መርሃግብራት እና በዝማሬ እናከብር ዘንድ ሁላችን በሰዓቱ እንገናኝ።
   መልካም የደመራ እና የመስቀል በዓል ይሁንልን

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

19 Sep, 14:42


#ጼዴንያ_ማርያም



በግብፅ ጼዴንያ በምትባል ሀገር ስሟ ማርታ የምትባል አምላክን የምትፈራ
የከበረች የተመረጠች ሴት " ሠው አለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢነዳ ምን
ይጠቅመዋል" ማቴ ፲፮፥፮ የሚለውን ቃል አስባ የአባቶቻችንን የነ
አብርሐምን የነሎጥን ፍኖት ተከትላ ሠፋፊ አዳራሾችን አሠርታ እንግዶችን
እያስተናገደች ስለ ነገረ እግዚአብሔር ስለ ነገረ ሃይማኖት ትጠይቅ
ትረዳም ነበር።
ከእለታት በአንዱ ቀን ስለ ነገረ እግዚአብሔር ስትጠይቅ በኢየሩሣሌም
የእመቤታችንን ሥዕል የሚስሉ ሠዎች እንዳሉ በሥዕሏም የለመኑት ነገር
ሁሉ እንዲፈፀም ተረዳች። እሷም እመቤታችንን አብዝታ ትወድ ስለነበር
ከእንግዶቿ ብዙ ወርቅ ሠጥታ የሚገዛላት ሠው እንዳለ ጠየቀች።
ከእንግዶቹም አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ለእመቤታችን
ካላት ፅኑ ፍቅር ልቡ ተነክቶ " እኔ እሔዳለሁ በራሴም ገንዘብ ገዝቼ
ካመጣሁልሽ በኋላ ትከፍዪኛለሽ" አላት ይህንንም ከሠማች በኋላ እጅግ
ደስ አላት።
መነኩሴው አባ ቴዎድሮስም ኢየሩሣሌም ደርሠው ገዳማትን ተሣልመው
ስርዓት አምልኳቸውን ከፈፀሙ በኋላ ማርታ የአማፀነቻቸውን ያማረች
የከበረች የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው በክብር ሸፍነው በደረታቸው
አቅፈው ወደ ሃገረ ጼዴንያ ለመጓዝ በረሃውን ማቋረጥ ጀመሩ።
በበረሃውም አንበሣ አባ ቴዎድሮስን ሊገድላቸው እየጮኸ መጣ
መነኩሴውም ፈርተው ሲንቀጠቀጡ በደረታቸው የታቀፏት ሥዕል ታላቅ
ድምፅ አውጥታ አንበሣውን አባረረችላቸው መነኩሴውም የሥዕሏን ኃይል
እያደነቁ ጉዟቸውን ቀጠሉ።
በበረሃውም የሥዕሏን ድንቅ ተአምር እያደነቁ ሲጓዙ መዝረፍና መግደል
የለመዱ የበረሃ ሽፍቶች አጊንተው መነኩሴውን ከበቧቸው ሥዕሏም
ለሁለተኛ ግዜ አፍ አውጥታ እንደ መብረቅ ባለ ድምፅ ጮሃ ሽፍቶቹን
አባረረችላቸው።
እነዚህን ሁሉት ድንቅ ተአምር ያዩ አባ ቴዎድሮስ "ከአውሬና ከሽፍታ
ያዳነችኝን ሥዕል ወደ ሃገሬ ነው የምወስዳት" ብለው አስበው መርከብ
ለመሣፈር ወደ ወደቡ አቀኑ ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ የምትጓዘውን መርከብ
ተሣፍረው ጉዟቸውን ቀጠሉ በባህሩ መሀከል ሲደርሱ ማዕበል ተነሣና
መርከቧን አቅጣጫዋን ቀይራ ወደ ጼዴንያ አቅጣጫ ገፋት ፈቃደ
እግዚአብሔር ነውና በመጨረሻም መርከቧ ጼዴንያ ሃገር ደረሠች።
አባ ቴዎድሮስም መርከቧ ወደ ጼዴንያ እንደመጣች ባዩ ግዜ "ግዜው ራቅ
ብሏል ሥዕሏን ግዛልኝ ያለችኝ ማርታ ብዙ እንግዶች ቤቷ ስለሚስተናገዱ
አታውቀኝም" ብለው ወደ እንግዳ ተቀባዩአ ማርታ ቤት አቀኑ።
በዚያም ተስተናግደው ውለው አድረው ጠዋት ከእንግዶች ጋር ተቀላቅለው
ሊወጡ ሲሉ በሩ ለሌሎች እንግዶች ክፍት ሆኖ ሲያስወጣና ሲያስገባ
ለእሣቸው ግን ዝግ ሆኖ መውጣት ተሣናቸው ለረጅም ግዜ እየተዘዋወሩ
ማርታ ተመለከተቻቸው " አባቴ የታመሙ ይመስለኛል ዛሬን አርፈው ነገ
ይሄዳሉ" አለቻቸው መነኩሴውም አድረው በነጋታው ሊወጡ ሲሞክሩ በሩ
ለሁለተኛም ለሦስተኛም ግዜ መውጣት ተሣናቸው።
ማርታም ተገርማ አባ ቴዎድሮስን "አባቴ እንደ በሽተኛ ሣይተኙ እንደ ጤነኛ
ሣይሄዱ ሦስት ቀን ሆኖት በእርሶ ላይ ይህ የማየው ነገር ምንድነው ብላ
ጠየቀቻቸው።
መነኩሴውም የእግዚአብሔር ፈቃድ ለማርታ እንደሆነ ተረድተው "እኔ ወደ
ኢየሩሣሌም ስሄድ ሥዕለ ድንግል ማርያምን እንድገዛልሽ የላክሽኝ ነኝ"
ብለው ሥዕሏ ከመሞት ስላዳነችን ወደ ሃገሬ ልወስዳት ነበር
እግዚአብሔር አልፈቀደም ሦስተኛ ተአምር መርከቡን ገፍታ ወደ ሃገርሽ
አመጣችኝ ብለው ተአምረኛዋን ሥዕለ አድኅኖ ከደረታቸው ሥራ
አውጥተው ሰጧት ማርታም ሥዕሏን ባየች ግዜ እጅግ ድስ ብሏት
ለሥዕሏም ሠግዳ እልል እያለች አመሠገነች።
የሥዕል ቤት አሠርታ በዚያም አኖረቻት ቀንና ሌሊት ሻማ እያበራችላት
በፀሎትና በስግደት ትተጋ ነበር።
ከሥዕሏም ወዝና እንባ እየወጣ በግልፅ ይታያል። የተቀበትና የዳሱሱ ሁሉ
ካለባቸው ከማናቸውም ደዌ ይፈወሣሉ። ይህቺ ቅድስት ሥዕለ አድህኖ
ከማርታ ቤት ለረጅም ግዜ ኖራለች።
ይህቺ ቅዱስ ሉቃስ የሣላት ሥዕለ አድኅኖ እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያም ድንቅ ተአምር ያደረገችበትን በማሠብ በሃገራችን በአዲስ አበባ
ዙሩያ ልዬ ዞን ቡራዩ ከተማ በ፲፱፶፭ ዓ.ም ቤተክርስቲያን ታንፆ ቅዳሴ ቤቱ
በየአመቱ መስከረም ፲/10 ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ይህ በዓል
ከእመቤታችን ከ፴፫ቱ በዓላት አንደኛው እመቤታችን በሥዕል ድንቅ ተአምር
ያደረገችበት "የሥዕል በዓል" በመባል ይከበራል።
የእግዚአብሔር ቸርነት
የእመቤታችን አማላጅነት
የቅዱሳን በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

10 Sep, 13:16


🌼እንኳን በሰላም ለዘመነ ማቴዎስ አደረሳችሁ🌼 🌼🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት🌼🌼🌼🌼 ልዩ የበዓል ዝግጅት በጽርሐ ጽዮን ዕረቡ መስከረም ፩ ታች ቤት አይቀርም እንደ ሁል ጊዜው ግቢ ጉባኤ ያችን ❗️🌚የ ዘመናትን አምላክ🌝 እናመስግን ትላለች በእለቱ ሁሉ ሙሉ ሆኖ ይጠብቃችኆል🌼🌼 join and share these links for photos📸📸 https://t.me/juwanagibigubaepics, ..to get info📞📞📞📞📞 @JuWanaGibiGG . subscribe and share our youtube channel https://youtu.be/F3RNJWK3Jjg?si=Bz8yUJO7ITdRu8FV

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

07 Sep, 08:50


ሐዋርያት ሆይ በእግዚአብሔር ፊት እስከምትቆሙ እጠብቃችሁ ዘንድ ከእኔ ርዳታን ሹ። የዚህ የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ ሩፋኤል ተአምራቶቹ ብዙ ናቸው ስለእኛ ይማልድ ዘንድ የበዓሉን መታሰቢያ ልናደርግ ይገባናል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_መልከጼዴቅ

በዚህችም ቀን ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ የመልከጼዴቅ መታሰቢያው ነው። መልከጼዴቅም ዐሥራ አምስት ዓመት በሆነው ጊዜ ከአዳም ሥጋ ጋር እንዲልከውና በምድር መካከል እንዲያኖረው እግዚአብሔር ኖኅን አዘዘው እርሷም ቀራንዮ ናት። የዓለም መድኃኒት ክርስቶስም መጥቶ በዚያ እንደሚሠዋ አዳምንም ከልጆቹ ሁሉ ጋር እንደሚያድነው አመለከተው።

ከዚህም በኋላ በአባቱ በኖኅ ትእዛዝ ሤም መልከጼዴቅን በሥውር ወሰደው የእግዚብሔርም መልአክ እየመራቸው ሔደው ወደ ቀራንዮ ተራራም አደረሳቸው መልከጼዴቅም ክህነትን ተሾመ። ዐሥራ ሁለት ደንጊያዎችንም ወስዶ መሠዊያ ሠራ ከሰማይ የወረደለትንም ኅብስትና ወይን መሠዊያ በሠራቸው ደንጊያዎች ላይ መሥዋዕትን አሳረገ።

ምግቡንም መላእክት ያመጡለታል ልብሱም ዳባ ነው በአባታችን አዳም ሥጋ ዘንድ ሲያገለግል ኖረ። አብርሃምም ከጦርነት ነገሥታትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ኅብስትንና ወይንን አቀረበለት አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው እርሱ ካህንም ንጉሥም ሁኖ ተሹሟልና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አፄ_ዘርዓ_ያዕቆብ_ጻድቁ

በዚህችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው ዘርዐ ያዕቆብ አረፈ። ዘርዐ ያዕቆብ ብሎ ስሙን መልአክ ነው ያወጣለት፡፡ ሲወለድም ብርሃን ቤቱን ሞለቶት ታይቷል፡፡ ግማደ መስቀሉን ከአባቱ ከዐፄ ዳዊት ተረክቦ በማስመጣት በግሸን አስቀምጦታል፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የጻድቁን የደብረ ቢዘኑን የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ከጠጣችው በኃላ የእምነቷን ጽናትና ጥልቀት አይተው ጻድቁ ባደረባቸው መንፈስ ቅዱስ ትንቢትን በመናገር "ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል" ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለሀገራችንም ሆነ ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ውለታ ውለዋል፡፡ ጣዖት አምልኮን ከሃገራችን ለማጥፋት ብዙ ሺህ ካህናትን አሰልጥነው በመላ አገራችን አሰማርተዋል፡፡ የኑፋቄ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉባኤያትን አዘጋጅተዋል፡፡ ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሰው ለአገልግሎት አብቅተዋል፡፡ ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥተው አስተርጉመዋል፡፡ ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለቅዱስ መስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርገዋል፡፡ እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ከመውደዳቸው የተነሳ ዛሬም ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸው ብዙ ሥርዓቶችም በሊቃውንት እንዲሠሩ አድርገው ሌሎች ብዙ በጐ ተግባራትንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሰራጵዮን_ዘሰንዱን

በዚህችም ቀን ሰንዱን ከሚባል አገር ቅዱስ ሰራጵዮን አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ትርጓሜያቸውንም ተማረ የዚህንም ዓለም ገንዘብ ሁሉ ትቶ ወደ አረሚ አገር ሔደ ራሱንም በሃያ ብር ሸጦ ማገልገል ጀመረ የሽያጩንም ዋጋ ጠበቀው። እንጀራ ሳይበላ ውኃ ሳይጠጣ ከስሕተታቸው ይመልሳቸው ዘንድ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት በሆነ በክርስቶስ አሳመናቸው ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተማራቸው ከዚህም በኋላ ስለርሳቸው ራሱን ባሪያ አድርጎ እንደሸጠ እንጂ እርሱ ባሪያ እንዳልሆነ ነገራቸው ሽያጩንም ለድኆች እንዲሰጡት ሰጣቸው።

ከዚህም በኋላ መንካያውያን ወደሚባሉ ሕዝቦች ሒዶ ለነርሱም ራሱን ሸጠ የክብር ባለቤት ወደሆነ ክርስቶስ እምነት እስከመለሳቸው ድረስ ተገዛላቸው። ከዚህም በኋላ ደግሞ ወደ ሮሜ አገር ሒዶ በሰላም እስከ አረፈ ድረስ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩና በቅዱሳኑ አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጳጉሜንና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ እና #ከገድላት_አንደበት)

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

07 Sep, 08:50


#ጳጒሜን_3

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጳጒሜን ሦስት በዚህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት #ርኅወተ_ሰማይ ትባላለች፣
የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ #ቅዱስ_ሩፋኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ #የካህኑ_መልከጼዴቅ መታሰቢያው ነው፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ መልካም ስም አጠራር ያለው #ቅዱስ_ዘርዐ_ያዕቆብ አረፈ፣ ሰንዱን ከሚባል አገር #ቅዱስ_ሰራጵዮን አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ርኅወተ_ሰማይ

ጳጒሜን ሦስት በዚህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች ርኅወተ ሰማይ (ሰማይ የሚከፈትባት) ቀን ትባላለች።

አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት አንድም ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ።

እመቤታችን ድንግል ማርያም ለአጼ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ፣ የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት፣ ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል። በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል።

ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል። ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሩፋኤል_ሊቀ_መላእክት

በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የሩፋኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው። ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት ነው።

ይህም እንዲህ ነው ሀብታም ሴት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ መጥታ ሳለ ከእርሷ ጋርም ብዙ ሰው ነበረ። ከባሏም የወረሰችው ብዙ ገንዘብ አላት በሊቀ ጳጳሳቱ ቤት አንጻር ያለውን ኮረብታ አስቆፈረችው በጥቅምት ወር ዐሥራ ስምንት ቀን እንደጻፍን የወርቅ መዝገብ ተገለጠ።

በዚያም ወርቅ ብዙዎች አብያተ ክርስቲያናትን አነፀ ከእርሳቸውም አንዲቱ የመላእክት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ ሩፋኤል በስሙ የታነፀች ይህች ናት። ሥራዋንም በፈጸመ ጊዜ እንደዛሬው በዚች ቀን አከበራት።

ብዙ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጸች ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና። የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ ያን ጊዜ ይህ የከበረ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ።

ይቺም ቤተ ክርስቲያን እስላሞች እስከተነሡበት ዘመን ኖረች ከዚህም በኋላ ሁለተኛ ያ አንበሪ ተናወጸ ደሴቲቱም በላይዋ ከሚኖሩ ብዙ ሕዝብ ጋራ ሠጠመች።

#ዳግመኛም የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ ጻድቅ ለሆነ ንጉሥ አኖሬዎስ ተናገረ። እንዲህም አለው ንጉሥ ሆይ እኛ ወዳንተ ልንመጣ በመርከብ እንደተሳፈርን ዕወቅ በጒዞ ላይ ሳለንም በቀዳሚት ሰንበት ቀን በደሴት ውስጥ ታናሽ ቤተ ክርስቲያን አየን ወደ ወደቡም ደርሰን በዕለተ እሑድ ሥጋውን ደሙን እንቀበል ዘንድ ወደርሷ ሔድን።

ለዚያች ቤተ ክርስቲያንም በጐኗ ታናሽ ገዳም አገኘን በውስጧም ወንድሞች መነኰሳት አሉ በክብር ባለቤት ጌታችንም ፈቃድ ወደ ርሳቸው ደረስን ። መነኰሳቱንም በቀደሙ አባቶች ዘመን የተጻፈ አሮጌ መጽሐፍ በእናንተ ዘንድ እንዳለ እጽናናበት ዘንድ እርሱን ሰጡኝ አልኳቸው።
እንዲህም ብለው መለሱልኝ እኛ ትርጓሜያቸውን የማናውቀው መጻሕፍቶች በዕቃ ቤት አሉ። እኔም አያቸው ዘንድ ወደዚህ አምጡልኝ አልኳቸው። በአመጡአቸውም ጊዜ መረመርኳቸው ጌታችንም በደቀ መዛሙርቱ ፊት ያደረጋቸውን ኃይሎችና ድንቆች ተአምራቶችን ስለ ሰማይና ምድርም ጥንተ ተፈጥሮ አገኘሁ።

ሁለተኛም ስመረምር ስለ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሹመትና መዐርግ አባቶቻችን ንጹሐን ሐዋርያት የጻፉትን አገኘሁ ይኸውም ጌታችን በደብረ ዘይት ከእሳቸው ጋራ እያለ የመለኮቱን ምሥጢር በገለጠላቸው ጊዜ። ሐዋርያትም እንዲህ ብለው እንደለመኑት ጌታችንና ፈጣሪያችን ሆይ የከበረ የሩፋኤልን ክብሩን ታስረዳን ዘንድ እንለምንሃለን በየትኛው ዕለት በየትኛው ወር ሾምከው።

ከባልንጀሮቹ የመላእክት አለቆችም ትክክል ነውን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ዘንድ በዓለም ውስጥ ስለርሱ እንድናስተምር እርሱም በመከራቸው ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ በአማላጅነቱም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኙ ዘንድ።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዘዘና ከሦስተኛው ሰማይ ሦስቱ የመላእክት አለቆች ሚካኤል፣ ገብርኤልና ሩፋኤል መጡ በታላቅ ደስታም ለክብር ባለቤት ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰገዱ። ጌታችንም ሩፋኤልን እንዲህ አለው የክብርህን ገናናነት የባልንጀሮችህንም ልዕልናቸውን እንዲያውቁ ለሐዋርያት ንገራቸው።

ያን ጊዜም ለጌታችን ሰገደ ይነግራቸውም ዘንድ ጀመረ እንዲህም አላቸው ደገኛው የመላእክት አለቃ ሚካኤል ለሁሉም መላእክት አለቃቸው ነው ስሙም ይቅር ባይ ይባላል።

ሁለተኛም የመላእክት አለቃ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ አገልጋይም ጌታም የሆነ የዓለሙ ሁሉ እመቤት የሆነች አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሠራት ነው። የእኔም ስሜ ሩፋኤል ነው ይህም ደስ የሚያሰኝ ቸር መሐሪ ቅን የዋህ ማለት ነው እኔም ኃጢአተኞችን በእግዚአብሔር ዘንድ አልከሳቸውም ከኃጢአታቸው በንስሓ እስኪመለሱ ስለ ቅንነቴ በእነርሱ ላይ እታገሣለሁ እንጂ።

በሃያ ሦስቱ የመላእክት ነገድ ሠራዊት ላይ እግዚአብሔር የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ እግዚአብሔር አብን ይቅር ባይ ልጁን አጽናኝና አዳኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስን እናመሰግነው ዘንድ።

በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሺህ ዓመት ተድላ ደስታ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የክብር ጽዋን በሚሰጣቸው ጊዜ ለቅዱሳኖቹ በጎ ነገርን እንድሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ። ደግሞም በዚች ቀን ከዕፀ ሕይወት ዐጽቅ ወስጄ ለተመረጡ ክርስቲያኖች በእጄ እንድሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ።

የሰማያት መዛግብትም ከእጄ በታች ተጠብቀው የሚኖሩ እኔ ሩፋኤል ነኝ። እኔም እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እከፍታቸዋለሁ እዘጋቸዋለሁም።

በምድር ሰው ለባልንጀራው ስለ ስሜ በጎ ነገር ቢያደርግ እኔ በመከራው በችግሩ ረዳዋለሁ ወይም የሹመቴን ነገር የሚጽፍ ወይም ከቅዱሳን ጋራ ስሜን የሚያስብ ወይም በስሜ ለቊርባን የሚሆነውን የሚሰጥ ወይም በበዓሌ ቀን ምጽዋትን የሚሰጥ ይኸውም እግዚአብሔር በሊቃነ መላእክት ክብር የሾመኝና ያከበረኝ ጳጕሚን ሦስት ቀን ነው። ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እስከማስገባው በብርሃን ሠረገላ እኔ እሸከመዋለሁ በምድር ላይ ከቶ እንደርሱ ያለ የማይገኝ መዐዛው እጅግ ጣፋጭ በሆነ ሽቱ ነፍሶቻቸው እርሱን በማሽተት ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ።

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

01 Sep, 17:31


Join and invite

https://t.me/gibigubayat_mirukan_hibret?livestream=eb9dabf9536a5f402e

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Aug, 18:35


ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ pinned «https://youtu.be/F3RNJWK3Jjg?si=Bz8yUJO7ITdRu8FV»

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Aug, 17:31


https://youtu.be/F3RNJWK3Jjg?si=Bz8yUJO7ITdRu8FV

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Aug, 17:30


https://youtu.be/B20KnJP1Ahw?si=kLMLKrlWjjugci5K

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Aug, 14:49


✤✤✤ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ✤✤✤
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ ሀገሯ #ሸዋ_ቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌየ ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ወላጆቿ ከአባተቷ ቅዱስ ደረሳኒ ከእናቷ ከቅድስት ዕሌኒ በግንቦት 12 ቀን ተወለደች፡፡ እነርሱም ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ከወለዱ በኋላ በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በማስተማር ስላሳደጓት ከልጅነቷ ጀምራ በሥነ ምግባር፣ በሃይማኖት የታነጸች በመልኳም እጅግ ውብና ያማረች ሆነች፡፡ ባደገችም ጊዜ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ የንጉሥ ባለሟል ለሆነ ስሙ ሠምረ ጊዮርጊስ ለተባለ ደግ ሰው በሕግ አጋቧት፡፡ ከሕግ ባሏ ከሠምረ ጊዮርጊስም ዐሥራ ሁለት ልጆችን ወለደች፡፡ ከእነዚህም መካከል አስሩ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ፡፡
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዐፄ #ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት የነበረች ኢትዮጵያዊት ጻድቅ ስለነበረች ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ገብረ መስቀል በትዳሯ፣ በሥነ ምግሯና በሃይማኖቷ በሁለመናዋ የተመሰገነች መሆኗን ዝናዋን ስለሰማ ‹‹#በጸሎትሽ አስቢኝ›› በማለት ከአገልጋዮቹ ውስጥ እርሷን እንዲያገለግሏት፣ 174 አገልጋዮቸን ላከላት፡፡ ብዙ ፈረስና በቅሎ እንዲሁም ለነገሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማም ላከላት፡፡ ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ‹‹ለዓላማዬ እንቅፋትና ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል እንደዚሁም ወርቁ ጌጡ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ነገር ግን እነዚህን አገልጋዮች ምን አደርጋቸዋለው?›› እያለች ወደ እግዚአብሔር አመለከተች፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ #ሚካኤል ፊቱ እንደ ፀሐይ እያበራ ሦስት ኅብስት በእጁ ይዞ መጥቶ ‹‹የእግዚአብሔር ባለሟል ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! እነሆ ይህን #ኅብስት ተመገቢ እግዚአብሔር በቸርነቱ ብዛት ሰጥቶሻል›› አላት፡፡ እርሷም ፈጣሪዋን አመስግና ኅብስቱን ከመልአኩ እጅ ተቀብላ ተመገበች፣ መዓዛ ጣዕሙም ሰውነቷን አለመለመው፡፡ በዚህም የተነሳ እስከ ሦስት ቀን እህል ሳትበላ ውኃ ሳትጠጣ ቆየች ኃይለ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቷ አድሮባታልና፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡- ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት፡፡ ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ ቢያሥነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት (ስዕለት) አደረገች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን ከሞት አሥነሳለት፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ‹‹ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን ካመሰገነች በኋላ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ሕፃን ልጅዋንም ይዛ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደች፡፡ ስትሄድም በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግሯ ከመንገዱ ብዛት ከእንቅፋቱም የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሟ መሬት ለመሬት እየፈሰሰ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰችና አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡ ይዛው የተሰደደችውን ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ ሲያለቅስ ከመነኮሳቱ አንዲቷ ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር ብላ ወደ በአዓቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፡፡ ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በ 3 ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ብፁዓን ገባ፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅዱስ ሚካኤል ካለችበት በዓት አውጥቶ በክንፉ ተሸክሞ ከጣና ደሴት አደረሳት፡፡ ከዚያም ሰውነቷ ተበሳስቶ የባሕር ዓሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደ ተተከለ ዓምድ ሆና ሳትወጣ ባሕሩ ውስጥ ዐሥራ ሁለት ዓመት ቆማ ስትጸልይ ኖረች፡፡ ከዐሥራ ሁለት ዓመት በኋላም ጌታችን ተገልጦላት #ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ከዚህ በኋላ ሕይወቷን በሙሉ በታላቅ ተጋድሎ ስታሳልፍ ጌታችንም ከቅድስት እናቱ ጋር ሆኖ በየጊዜው ይጎበኛት ነበር፡፡ ቅዱስ ሚካኤልንም የሁልጊዜ ጠባቂዋ አድጎ ሰጥቷታል፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ብሔረ ብፁዓን እየሄደች ከዚያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ጋር እስከ ሰባት ቀን ድረስ ስትነጋገር ትቆይ ነበር፡፡
#ሄኖክና #ኤልያስ ወዳሉበት ወደ ብሔረ ሕያዋንም እየሄደች ትመለስ ነበር፡፡
✤✣✤
ከዕለታት አንድ ቀን በጣና ማዶ መዕቀበ እግዚእ የሚባል አንድ ሰው ነበረና መልአከ ጽልመት ወደ እርሱ ዘንድ መጥቶ ‹‹ፈጣሪውን ክደህ ይህን ዕፅ በሰውነትህ ብትቀብር ሞትና እርጅና አያገኝህም›› አለው፡፡ እርሱም ለዚህ ክፉ ሀሳቡ ፈቃደኝነቱን ስለገለጠለት መልአከ ጽልመት በሰውነቱ ውስጥ ዕፁን ቀብሮለት ሄደ፡፡ መዕቀበ እግዚእም ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጥቶ ‹‹ሰላም እልሻለው በጸሎትሽም ተማጽኛለሁ፣ የፈጠረኝን እግዚአብሔርን እስከ መካድ ደርሼ ብዙ ኃጢአት ሰርቻለውና›› አላት፡፡ ቅድስት እናታችንም በዚያን ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደችና ስለዚህ ሰው በፍጹም ኀዘን በመሆን ወደ ፈጣሪዋ አመለከተች፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን መጥቶ ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! ለዚህ ሰው ምሕረት አይገባውም፣ የምገድል የማድን የምቀስፍ ይቅር የምል አምላክ እኔ እያለሁ ፈጣሪውን ክዶ በሰይጣን ምክር ተማምኖአልና›› አላት፡፡ በዚህ ጊዜ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጌታችንን እግሩ ሥር ተደፍታ ‹‹አንተ መዓትህ የራቀ ምህረትህ የበዛ ፈጣሪ ሆይ! ማርልኝ ሁሉ ይቻልሃልና…›› ስትል አጥብቃ ለመነችው፡፡ ሁሉን የፈጠረ ጌታችንም ‹‹ስለ አንቺ ፍቅር ምሬልሻለው›› አላት፡፡ ከዚህ በኋላ ማዕቀበ እግዚእን ጠርታ ‹‹ኃጢአትህን ይቅር ብሎሃል›› አለችው፡፡ ከዚህ በኋላ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የተቀበረውን ዕፅ ሰውነቱን ፍቃ ስታወጣለት ደሙ እንደ ቦይ ውኃ ወረደ፤ በዚያው ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ከማኅበረ ሰማዕታት ጋር አንድ ሆነች፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ #ስድስት ክንፎችን ሰጥቷታል፡፡ በበዓለ ጥምቀት ወቅት ሙሴ፣ ኤልያስና መጥመወቁ ዮሐንስ ጌታ የተጠመቀበትን የዮርዳኖስን ውኃ አምጥተው ሙሴ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ቀኝ እጇን፣ ኤልያስ ግራ እጇን ይዘዋት ዮሐንስ ውኃውን በራሷዋ ላይ አፍስሶ አጥምቀዋታል፡፡ ከጌታችን ጥምቀት በኋላ እንደዚህ ዓይነት መንገድ የተጠመቀ ማንም የለም፡፡ እነርሱም ጓንጉት በምትባል ገዳም ውስጥ የገዳም አስተዳዳሪ እንደምትሆንና እጅግ ብዙ ተከታዮች እንደሚኖሯት ትንቢት ነግረዋት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፡፡
የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ምልጃና ጸሎት አይለየን🙏

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Aug, 14:48


ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።

አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳ በአባታችን ተክለሃይማኖት ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ)

ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ

29 Aug, 14:48


#ጻድቁ_አቡነ_ተክለሃይማኖት - #ነሐሴ_24

ነሐሴ ሃያ አራት በዚህችም ቀን ታላቅ የከበረ ሐዲስ ሐዋርያ የትሩፋትም መምህር የሆነ አባታችን ተክለሃይማኖት አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ጸጋ ዘአብ የእናቱ ስም እግዚእ ኀረያ ነው እሊህም ቅዱሳን ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ብርሃንን ላበሩ ካህናት ከወገኖቻቸው የሆኑ ናቸው። እግዚእ ኀረያም መካን ስለሆነች ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እያዘኑ ሲጸልዩ ኖሩ።

በዚህም ነገር እያሉ የዳሞት ገዥ ሞተለሚን ሰይጣን አነሣሣው የሸዋን አውራጃዎች እስከ ጅማ እስከ ገዛ ድረስ። የሀገር መኳንንቶችም በየተራቸው ሚስቶቻቸውን ይሰጡታል። ከማረከውም ደምግባት ያላቸውን ሴቶች ያገኘ እንደሆነ ቁባቶች ያደርጋቸዋል።

በዚያም ወራት ወደ ጽላልሽ ደርሶ ብዙ ክርስቲያኖችን ገደለ ከእርሳቸውም የሚበዙትን ማረከ ጸጋ ዘአብም ከግድያ ፍርሃት የተነሳ ሸሸ አንድ ወታደርም ተከተለው እርሱም ወደ ባሕር ተወርውሮ ገባ በእግዚአብሔርም ፈቃድ በባሕሩ ውስጥ ተሸሸገ።

ሚስቱን እግዚእ ኀረያንም ወታደሮቹ ማረኳት ወደ ሞተለሚም አደረሷት ባያትም ጊዜ ውበቷንና ላህይዋን አደነቀ በልቡም እጅግ ደስ ብሎት ብዙ ሽልማትን ጌጥን ሰጥቷት በሽልማትና በጌጥ ሁሉ ሸለማት አስጌጣትም የጋብቻ ሥርዓትንም ማዘጋጀት ጀመረ ለሠርጉም እንዲሰበሰቡ ወደመኳንንቶቹ ሁሉ ላከ።

እግዚእ ኀረያም ይህን በሰማች ጊዜ ከአረማዊ ጋር አንድ ከመሆን ያድናት ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር ጸሎትን አደረገች። ያን ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በብርሃናዊ ክንፉ ተሸክሞ ከዳሞት አገር ወደ ምድረ ዞራሬ አድርሶ ወዲያውኑ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በሴቶች መቆሚያ አቆማት። ባሏ ጸጋ ዘአብም ከማዕጠንት ጋራ በወጣ ጊዜ እንደተሸለመች ቁማ አያት አድንቆ በልቡ ይቺ ሴት ምንድን ናት ወደዚህስ ማን አመጣት አለ።

የማዕጠንቱንም ሥራ ጨርሶ ወጣ በጠየቃትና በመረመራት ጊዜ እርሷ ሚስቱ እግዙእ ኀረያ እንደሆነች አገኛት እርሷም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እግዚአብሔር ያደረገላትን ነገረችው።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ በአንዲት ሌሊት ተገለጠላቸው የዜናው መሰማት በዓለሙ ሁሉ የሚደርስ የተባረከ ልጅ ይወልዱ ዘንድ እንዳላቸው ነገራቸው አበሠራቸው።

ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ይህ ቅዱሱ ተፀንሶ በታኀሣሦ ወር በሃያ አራት ተወለደ በጸጋ ዘአብና በእግዚእ ኀረያ ቤታቸው ታላቅ ደስታ ሆነ ከዘመዶቻቸውና ከጐረቤቶቻቸው ጋራ ደስ አላቸው።

ለክርስትና ጥምቀትም በአስገቡት ጊዜ ፍሥሓ ጽዮን ብለው ሰየሙት። ሕፃኑም አደገ ድንቅ ተአምራትንም እያደረገ ዕውቀትንና ኃይልንም ተመልቶ በመነፈስ ቅዱስ ጸና።

ከዚህም በሗላ ዲቁና ይሾመው ዘንድ አባ ጌርሎስ ወደ ተባለ ጳጳስ ወሰዱት በዚያንም ዘመን በዛጔ መንግሥት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚን ነበር። ወደ ጳጳሱም በአደረሱት ጊዜ ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል ብሎ ትንቢት ተናገረለት። የዲቁና ሹመትንም ተቀብሎ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።

ጐልማሳ በሆነ ጊዜ አራዊትን ሊያድን ወደ ዱር ሔደ። ቀትር ሲሆንም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልኩ የሚያምር ጐልማሳ አምሳል በቅዱስ ሚካኤል ክነፍ ላይ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ወዳጄ አትፍራ እንግዲህ የኃጢአተኞችን ነፍስ ወደ ሕይወት የምታጠምድ ትሆናለህ እንጂ አራዊትን የምታድን አትሆንም ስምህም ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንደ ኤርምያስና እንደ አጥማቂው ዮሐንስ እኔ ከእናትህ ማኀፀን መርጬ አከብሬሃለሁና እነሆ በሽተኞችን ትፈውስ ዘንድ ሙታንንም ታሥነሣ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠሁህ ርኩሳን አጋንንትንም ከሁሉ ቦታ ታሳድዳቸዋለህ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ገንዘብን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች በተነ ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ለሰው ምን ይጠቅመዋል እያለ ቤቱን እንደ ተከፈተ ትቶ ምርኩዙን ይዞ በሌሊት ወጣ።

ከዚህም በኋላ ወደ ጳጳስ ሔዶ የቅስና ሹመት ተቀብሎ ለሸዋ አገር ሁሉ ወንጌልን መስበክ ጀመረ። ዐሥራ ሁለት ሽህ ሦስት መቶ ነፍስ ያህል አጠመቀ ለጣፆት የሚሠውበትን ሁሉ ሻረ በውስጡ የሚኖሩ አጋንንት እስከሸሹ ድረስ ዐፀዶቻቸውን ሁሉ ቆረጠ።

ሁለተኛም ወደ ዳሞት ምድር ሔዶ ብዙ ሟርተኞችንና አስማተኞችን ጠንቋዮችን አሳመነ ከሀዲ ሞተለሚም ብዙ ወራት ተቃወመው በጉማሬ ማጥመጃ ውስጥ በመጨመር ብዙ ጊዜ ወደ ገደል ወረወረው እርሱ ግን በደኀና ይመለሳል ደግሞ ሊወጋው ጦር ወረወረ ጦሩም ተመልሶ እጁን ወግቶ ተጠመጠመበት በተሠቃየም ጊዜ አባታችንን ለመነው እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳምኖ አዳነው የተጠመጠመበትንም ጦር ፈታለት ቀናውን መንገድ የሚያጣምሙ ሟርተኞችንም አጠፋቸው።

ከዚህም በኋላ በክብር ባለቤት ጌታችን ስም ያደረገውን ድንቅ ተአምራቱን አይተው የአገር ሰዎች ሁሉም ከንጉሣቸው ጋራ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠርቶላቸው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት አስተማራቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው ከዚህም ሁሉ ጋራ በጾም በጸሎት በስግደት ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ ተጠምዶ ይጋደል ነበር።

ዜናውንም ሰምተው ወደርሱ የሚመጡትን የነፍሳቸውን ድኀነት ያስተምራቸዋል የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስን በማመን ያጸናቸዋል።

ከዚህ በኋላ በኤልያስ ሠረገላ ተቀምጦ ወደ አምሐራ ሀገር ሔደ በገድል ተጸምዶ ወደሚኖር መነኰስ ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል በአንዲት ቀን ደርሶ በዚያ እንደባሪያ ሲያገለግል ኖረ በአንድነት የሚኖሩ መነኰሳትንም ያገለግላቸው ነበር የሞተውንም እስከማንሳት ድረስ ከደዌያቸው ይፈውሳቸው ነበር።

በዚያም ዐሥራ ሁለት ዓመት ከሆነው በሗላ ሐይቅ በሚባል ቦታ ወደሚኖር ወደ ኢየሱስ ሞዓ የእግዚአብሔር መልአክ እንዳዘዘው ሔዶ ከእርሱም የምንኲስና ልብስ ቀሚስና ቅናትን ተቀበለ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሔዶ ለአቡነ አረጋዊ አራተኛ ከሆነ ከአባ ዮሐኒ ዘንድ ቆብንና አስኬማን ተቀበለ። ሁለተኛም ወደ ኢየሩሳሌም ሒዶ ከከበሩ ቦታዎችና ከሊቀ ጳጳሳቱ ቡራኬን ተቀበለ።

በዚያም ወደ ሸዋ ምድር ተመልሶ የአባቱ ወንድም ልጅ የሆነ አባ ዜና ማርቆስን አገኘው በወግዳ በረሀም በአንድነት ኖሩ ከዚያም ግራርያ ወደ ሚባል አገር ሒዶ በኮረብታ መካከል ዋሻ አዘጋጅቶ ተቀመጠ በቀንም በሌሊትም ከዚያ አይወጣም ነበረ ከጥቂት ቅጠልም በቀር እህልን አይቀምስም መጠጡም ጥቂት ውኃ ነው።

ብዙ ወንዶችና ሴቶች ወደርሱ መጥተው መነኲሳቶች ሆኑ በአንድ ቤት ውስጥ በአንድ መኝታ ላይ ተኝተው ያድራሉ እርስበርሳቸውም አይተዋወቁም እነርሱም እንደ ሕፃናት ናቸው በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜም በአንድነት ይቆማሉ በዘመኑ ሰይጣን ሰለ ታሠረ ወንዱ ሴቷን ሴት እነደሆነች አያውቅም እንዲሁም ሴቷ ወንዱን ወንድ እንደሆነ አታውቅም።

በዚህም በኋላ መጠጊያ ሠርቶ በፊቱ በሗላው በቀኙ በግራው የተሳሉ ፍላጻዎችን ተከለ ይህንም ማድረጉ በመደገፍና በመተኛት እንዳያርፍ ነው በዚያም እግሩ ከቅልጥሙ እስቲሰበር ሰባት ዓመት ቆመ። በዚያም ወራት ምንም የዕንጨት ፍሬ ወይም ቅጠል ሳይቀምስ ውኃም ሳይጠጣ ኖረ።...