Skyline media @skyline7777 Channel on Telegram

Skyline media

@skyline7777


Skyline media (English)

Skyline media is a cutting-edge Telegram channel that provides the latest news and updates in the world of media and entertainment. With a focus on film, television, music, and pop culture, this channel is the go-to destination for all media enthusiasts. Whether you're looking for breaking news about your favorite celebrities, in-depth analysis of the latest blockbusters, or exclusive interviews with industry insiders, Skyline media has you covered

Who is it? Skyline media is a channel created for media enthusiasts who want to stay informed and engaged with the latest trends in the industry. With a team of passionate writers and researchers, the channel delivers high-quality content that is both informative and entertaining

What is it? Skyline media is your one-stop shop for all things media and entertainment. From reviews of the hottest new releases to behind-the-scenes glimpses of your favorite shows, this channel has everything you need to stay up-to-date on the ever-changing world of media. Join the conversation and connect with like-minded individuals who share your passion for all things entertainment by subscribing to Skyline media today!

Skyline media

12 Feb, 01:06


“ በ6 ወራት ለ66 ሺህ 741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” - አማኑኤል ሆስፒታል

አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 ዓ/ም፣ “ በ6 ወራት ለ66,741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚህም 64,256 የተመላላሽ፣ 257 ህፃናት የአዕምሮ፣ 410 ሰዎች የሱስ ህክምና መሰጠቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዩ የኔአለም ገልጸዋል።

እንዲሁም ለ240 የተሃዲሶ፣ ለ921 የአስተኝቶ፣ ለ1,564 ሰዎች ደግሞ የድንገተኛ የህክምና አገልግሎት መሰጠቱን አቶ አብይ አስረድተዋል።

በተመላላሽ፣ በአስተኝቶና በድንገተኛ የህክምና አገልግሎት ከተሰጣቸው ታካሚዎች መካከል 36,300 የጤና መድን ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተመልክቷል።

በተመላላሽና በተኝቶ ህክምና በስድስት ወራት የወንጀልና የፍትሃ ብሔር ተመርማሪ ለሆኑ 413 የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱም ተገልጿል።

“ በሆስፒታሉ አማካኝ አስተኝቶ የቆይታ ጊዜ በ2016 ዓ/ም ከነበረው 36 ቀናት በ2017 ዓ/ም 6 ወራት ወደ 33 ቀናት ማድረስ፣ የአልጋ የመያዝ ምጣኔም በመጀመሪያ 6 ወራት መጨረሻ ላይ 85.2% መፈጸም ተችሏል ” ተብሏል።

ሆስፒታሉ ከ1930 ዓ/ም ጀምሮ በተኝቶ፣ በተመላላሽ፣ በድንገተኛ፣ የጭንቅላት ምርመራ፣ በኤሌክትሪክ ንዝረት፣ በህፃት የአዕምሮ፣ ከህግ ጋር የተያያዙ የአዕምሮ ህክምናና ምርመራ እንዲሁም የነርቭ ህክምናዎችን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ሆስፒታል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Skyline media

04 Feb, 04:36


በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ዝርዝር
1. ዶክተር ዐብይ አሕመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
4. አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኡልፋታ
5. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
6. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ደሳ
7. አቶ ከፍያለው ተፈራ ይግለጡ
8. ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም
9. አቶ አወሉ አብዲ አብዶ
10. አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ
11. ዶክተር ዓለሙ ስሜ ፈይሳ
12. አቶ ሳዳት ነሻ አረባ
13. አቶ ነመራ ቡሊ
14. ኢንጅነር ታከለ ኡማ
15. ዶ.ር ቢቂላ ሁሪሳ
16. ዶ.ር ግርማ አመንቴ
17. ዶ.ር ቶላ በሪሶ
18. ዶ.ር ካሳሁን ጎፌ
19. ወይዘሮ ሎሚ በዶ
20. ወይዘሮ ምስኪ መሀመድ
21. ዶ.ር እዮብ ተካልኝ
22. አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ
23. አቶ አብዱልሀኪም አልይ
24. አቶ ገመቹ ጉርሜሳ ሲርና
25. ዶ.ር መንግስቱ በቀለ ሁሪሳ
26. ዶ.ር ተሾመ አዱኛ
27. አቶ ቲጃኒ ናስር
28. አቶ ሀይሉ ጀልዴ
29. ወይዘሮ መሰረት አሰፋ ጎዳና
30. ኢንጅነር ሌሊሴ ነሜ
31. አቶ እንዳልካቸው ተፈሪ
32. ወይዘሮ ጀሚላ ሲንቢሩ
33. አቶ ከድር ጀዋር
34. ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ሽፈራው
35. አምባሳደር ብርቱካን አያኖ
36. አቶ አለማየሁ እጅጉ
37. ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ ወርቁ
38. ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ
39. ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱራህማን ሃቢብ
40. ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ
41. ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ
42. አቶ ደበሌ ቃበታ
43. አቶ መስፍን መላኩ
44. አቶ ከድር ማሞ
45. ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ቦሩ
46. ዶ/ር ኢ/ር ወርቁ ጋቸና ነገራ
47. አቶ ሲሳይ ቶላ
48. ዶ/ር አብዱልአዚዝ ዳውድ
49. አቶ አህመድ እንድሪስ
50. አቶ አለማየሁ አሰፋ ዲሳሳ
51. ዶ/ር ኢፍራህ ወዚር አብዱላሂ
52. ወ/ሮ ኢክራም ጠሃ
53. አቶ አዱላ ህርባዬ ጎላዴ
54. አቶ ኢብራሂም ከድር ጅማ
55. አቶ መኮንን ባይሳ
56. አቶ አብዱልሰላም ዋሪዮ
57. አቶ ድዳ ጉደታ ዳባላ
58. አቶ ጃርሶ ቦሩ ረሮ
59. አቶ አባቡ ዋቆ ቱራ
60. አቶ ክፈለው አዳሬ
61. አቶ ዋቅጋሪ ነገራ
62. አቶ ደንጌ ቦሩ
63. አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመር
64. አቶ አህመድ ሽዴ መሀመድ
65. ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ኢሳቅ
66. አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህ
67. አቶ አብዱራህማን ኢድ ጣሂር
68. ወ/ሮ ሰሃርላ አብዱላሂ
69. አቶ መሀመድ ኡመር አህመድ
70. አቶ ፈይሰል ረሺድ ኡመር
71. አቶ መሀመድ ፋታህ መሀመድ
72. አቶ አብዱራህማን አህመድ
73. አቶ መሀመድ አደን እስማኤል
74. ወ/ሮ ከድራ በሽር
75. ወ/ሮ ሀሊሞ ሀሰን መሀመድ
76. ወ/ሮ አያን አብዲ መሀመድ
77. አቶ ኢብራሂም ሀሰን አሊ
78. ወ/ሮ ሂቦ አህመድ ኡመር
79. አቶ መሀመድ ናጂ መሀመድ
80. አቶ መሀመድ አደን ጣሂር
81. አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ አህመድ
82. አቶ ጠይብ አህመድ ኑር
83. ዶ/ር አብዱልዋሳ አብዱላሂ በዴ
84. ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲም
85. አቶ አረጋ ከበደ ለጋስ
86. አቶ መላኩ አለበል
87. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
88. አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣው
89. ዶ/ር አብዱ ሁሴን ኢብራሂም
90. ኢ/ር ሀብታሙ ተገኝ ደስታዬ
91. አቶ ዛዲግ አብርሃ ሻረው
92. አቶ አገኘሁ ተሻገር
93. አቶ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ
94. ዶ/ር አህመዲን መሀመድ አህመድ
95. ዶ/ር ድረስ ሳህሉ
96. አቶ ደሳለኝ ጣሰው
97. አቶ ጃንጥራር አባይ ይግዛው
98. ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ አድማሱ
99. አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ መኮንን
100. ዶ/ር ዘሪሁን ፍቅሩ መላኩ
101. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ
102. ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ አለሜ
103. አቶ እንድሪስ አብዱ አህመድ
104. ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ
105. ወ/ሮ ባንቺአምላክ ገ/ማርያም
106. ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ እንየው
107. ዶ/ር ሂሩት ከሳ ወንድም
108. ዶ/ር ደመቀ ቦሩ
109. ዶ/ር ጋሻው አወቀ ትኩዬ
110. ዶ/ር ስቡህ ገበያው ታረቅ
111. አቶ ሲሳይ ዳምጤ
112. ወ/ሮ መስከረም አበበ ወርቅነህ
113. አቶ አሸተ ደምለው ተድላ
114. አቶ አሊ መኮንን አስፋው
115. አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ደሳለ
116. አቶ እድሜአለም አንተነህ
117. አቶ ቻላቸው ዳኛው ከበደ
118. አቶ አህመድ አሊ አባአፍሮ
119. አቶ ጎሹ እንዳለማሁ ወንድማገኝ
120. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ወዳጄነህ
121. ዶ/ር ኢብራሂም ሙሀመድ እንድሪስ
122. አቶ መካሽ አለማየሁ ግዛው
123. አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ አየለ
124. ዶ/ር አማኑኤል ፈረደ አያሌው
125. ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ ማንበግሮት
126. ወ/ሮ አየለች እሸቴ ወ/ሰማያት
127. ዲ/ን ሸጋው ውቤ አዛገ
128. አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው ትኩ
129. ዶ/ር አብርሃም በላይ በርሄ
130. አቶ ታይዜር ገ/ሔር በርሄ
131. ወ/ሮ ያስሚን መሀቢረቢ ሰኢድ
132. አቶ ኦርዲን በድሪ ሀምዶኝ
133. አቶ አሪፍ መሀመድ አዱስ
134. አቶ ካሊድ አልዋን ኢሳቅ
135. አቶ ሙክታር ሳሊህ ኢብራሂም
136. ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም መሀመድ
137. ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ
138. ዶ/ር ጋልዋክ ሮን
139. አቶ አሽኔ አስቲን ቲቶይክ
140. አቶ ቶክ ቾት ቶሃን
141. አቶ ጀሙስ ኞች
142. ወ/ሮ ባንቺአየሁ ድንገታ ነገሪ
143. አቶ አሻድሊ ሀሰን አልአጀብ
144. አቶ ጌታሁን አብዲሳ ሌጮ
145. አቶ ኢሲያቅ አብዱልቃድር ሌጮ
146. ወ/ሮ አስካል አልቦሮ ዲባባ
147. ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ ጉቅ
148. አቶ በባክር ሃሊፋ አብደላ
149. ወ/ሪት ምስኪያ አብደላ ሶሶ
150. ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ጎበና
151. ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ሐጂዙሊ
152. አቶ ደስታ ሌዳሞ
153. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
154. ዶ/ር ፍፁም አሰፋ አደላ
155. አቶ በየነ በራሳ ባላንጎ
156. ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ
157. ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ
158. አቶ አሸናፊ ኤልያስ
159. ወ/ሮ ሀገረፅዮን አበበ
160. አቶ ጥራቱ በየነ
161. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ
162. አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ደቦጭ
163. ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት
164. ሀጂ አወል አርባ ኡንዴ
165. አቶ መሀመድ ሁሴን አሊሳ
166. አቶ መሀመድ አህመድ አሊ
167. ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ አሊ
168. አቶ ወልኦ አይቲሌ
169. አቶ አህመድ መሀመድ ቦዳያ
170. ኢ/ር አይሻ መሀመድ ሙሳ
171. ወ/ሮ አይሻ ያሲን ሀሰን
172. ወ/ሮ ፋጡማ መሀመድ ያሲን
173. አም/ር ሀሰን አብዱልቃድር ባርከት
174. አቶ አብዱ ሙሳ ሁሴን
175. አቶ ኡመር ኑር አርባ
176. ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
177. አቶ ማስረሻ በላቸው ማሞ
178. አቶ ፍቅሬ አማን ጋካ
179. አቶ ነጋ አበራ አጭሶ
180. አቶ በላይ ተሰማ ጅሩ
181. አቶ ፋጂዮ ሳፒ ወትራሻ
182. አቶ አልማው ዘውዴ ግችላ
183. አቶ በየነ በላቸው
184. ወ/ሮ ሄለን ደበበ ወ/ጊዮርጊስ
185. ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ አያኖ
186. ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ገ/ማርያም
187. አቶ ዳዊት ገበየሁ ገሉ
188. አቶ ሀብታሙ ካፍቲን
189. ዶ/ር እንደሻው ጣሰው

Skyline media

04 Feb, 04:36


190. ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ፈረንጄ
191. ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
192. አቶ መለሰ አለሙ ህርቦሮ
193. አቶ እርስቱ ይርዳው
194. አቶ ሞገስ ባልቻ ገ/መድህን
195. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ
196. አም/ር ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ
197. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
198. አቶ አንተነህ ፍቃዱ ወ/ሰንበት
199. አቶ ኡስማን ሱሩር ሲራጅ
200. አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
201. ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ
202. አቶ አክሊሉ ታደሰ
203. ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን
204. ወ/ሮ ነጂባ አክመል
205. አቶ ጃፋር በድሩ
206. አቶ ጥላሁን ከበደ ወልዴ
207. ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ዳራ
208. አቶ ታገሰ ጫፎ ዱሎ
209. ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ አቱሞ
210. ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ጦሼ
211. አቶ ገ/መስቀል ጫላ ሞጣሎ
212. አቶ አለማየሁ ባውዲ ሞላ
213. አቶ ንጋቱ ዳንሳ
214. አቶ ኃይለማርያም ተስፋዬ
215. ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ
216. አቶ ብርሃኑ ዘውዴ
217. አቶ ወገኔ ብዙነህ
218. ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ሻሽጎ
219. አቶ አዳማ ቴንጳዬ መንገሻ
220. ኢ/ር አክሊሉ አዳኝ
221. አቶ ዳኜ ሂዶ ዋቆ
222. አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም
223. ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ ሀጢያ
224. ኢ/ር ወንድሙ ሴታ ዳጠሞ
225. አቶ ሰለሞን ሶካ ግኛርታ

Skyline media

03 Feb, 12:28


አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአጠቃላይ 45 አባላት ያለው ሲሆን 10 ሴቶችን አካቷል።

#ኦሮሚያ_ክልል

1. ዶክተር ዐቢይ አህመድ
2. ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
3. ኦቦ አወሉ አብዲ
4. ኦቦ ፍቃዱ ተሰማ
5. አዴ አዳነች አቤቤ
6. አዴ ጫልቱ ሳኒ
7. ኦቦ ሳዳት ነሻ
8. ኦቦ ከፍያለው ተፈራ
9. ዶክተር ተሾመ አዱኛ
10. ዶክተር እዮብ ተካልኝ

#አማራ_ክልል

11. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
12. አቶ መላኩ አለበል
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
14. አቶ አረጋ ከበደ
15. አቶ ይርጋ ሲሳይ
16. ዶክተር አብዱ ሁሴን
17. አቶ ጃንጥራር አባይ
18. ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ

#ሶማሌ_ክልል

19. አቶ አደም ፋራህ
20. አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
21. አቶ አህመድ ሺዴ
22. ወ/ሮ ሃሊማ ዋሽራፍ

#ትግራይ_ክልል

23. ዶክተር አብርሃም በላይ
24. አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር

#ሀረሪ_ክልል

25. አቶ ኦርዲን በድሪ
26. ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም

#አፋር_ክልል

27. ሀጂ አወል አርባ
28. መሀመድ ሁሴን አሊሳ
29. መሀመድ አህመድ አሊ

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ_ክልል

30. ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
31. አቶ ፍቅሬ አማን

#ሲዳማ_ክልል

32. አቶ ደስታ ሌዳሞ
33. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
34. ዶክተር ፍፁም አሰፋ

#ጋምቤላ_ክልል

35. ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ
36. ዶዶክተር ካትሏክ ሩን ናቸው።

#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል

37. አቶ አሻድሊ ሀሰን
38. አቶ ጌታሁን አብዲሳ

#ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል

39. አቶ እንዳሻው ጣሰው
40. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
41. ዶክተር ዴላሞ ዶቶሬ

#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል

42. አቶ ጥላሁን ከበደ
43. ወ/ሮ ⁠ሸዊት ሻንካ
44. ዶክተር ተስፋዬ ቤልጅጌ
45. ዶክተር አበባየሁ ታደሰ

Skyline media

22 Jan, 18:19


https://www.youtube.com/live/AC2qgGIlmbI?si=_dB2az9BLD3eVny_

Skyline media

20 Jan, 16:07


ሊንደን ጆንሰንን ቃለ መሐላውን ያስፈጸሟቸው ሴት ዳኛ ሲሆኑ እስካሁን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ፕሬዝደንትን ቃለ መሐላ ያስፈጸሙ ብቸኛዋ ሴት ዳኛ ናቸው፡፡

ጆንሰን ቃለ መሐላ ላይ ሲፈጽሙ ጎናቸው የቆሙትም ባለቤታቸው በጥይት በተገደሉበት ጊዜ ለብሰውት የነበረውን ያንኑ ልብስ እንደለበሱ ነበር፡፡

ምስሉ ፕሬዝደንቱ በሰው እጅ ለተገደሉበት የአሜሪካ ሕዝብ ተተኪ ፕሬዝደንት መሰየሙን በስተቀር ባልተጠበቀ ምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሥራ እንደሚቀጥል እምነት እንዲያድርበት ያደረገም ነበር፡፡

ታዲያ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሥራ ሁልጊዜ ያለ እንከን ይከናወናል ማለት አይደለም፡፡ በታቀደላቸው ስርዐት መሠረት ያልተከናወኑ ብዙ በዓለ ሲመቶች አሉ፡፡

በሥነ ሥርዓት ያልተከናወኑ በዓለ ሲመቶች የወፍ ምስል

ወደ ጥንት ወደ እ አ እ 1829 ዓም መለስ ብለን የአንድሩው ጃክሰንን በዓለ ታሪክን ብንቃኝ ቃለ መሓላቸውን ከፈጸሙ በኋላ በኋይት በነበረው ድግሥ ላይ የታደሙ ደጋፊዎቻቸው እጃቸውን እየጨበጡ ደስታቸውን ለመግለጽ ጓጉተው ሲረባረቡ አዲሱን ፕሬዝደንት ከግድግዳ ጋር አጣብቀው ሊደፈጥጧቸው ምንም አልቀራቸውም ነበር፡፡ ፕሬዝደንቱ በመስኮት ወጥተው እንዳመለጡ ታሪክ ይናገራል፡፡

በ1865 ደግሞ የፕሬዝደንት አብራሃም ሊንከን ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት አንድሩ ጆንሰን በቃለ መሐላ ሥነ ስርዐታቸው ላይ በስካር መንፈስ ንግግር ማድረጋቸው ተመዝግቧል፡፡ አሟቸው ስለነበረ ለህመም ማስታገሻ እንዲሆናቸው የወሰዱት ዊስኪ ነው ያሰከራቸው የሚል ምክንያት እንደተሰጠላቸው ተጽፏል፡፡

በ1873 ዩሊሰስ ኤስ ግራንት በበዓለ ሲመታቸው ድግስ ላይ "በድግሱ ቦታ ሰማያዊ ወፎች ቢበሩልኝ እንዴት ደስ ባለኝ ብለው ነበር" እና ሐሳባቸው ይሙላ ተብሎ ወፎች ለትዕይንት እንዲበሩ ተደረገ፡፡

ክፋቱ ብርዱ ነበር እና ወፎቹን ክንፋቸውን እያደረቀ እንዳረገፋቸው ይነገራል፡፡ የወፍ ነገር ከተነሳ እ አ አ በ1973ም ሪቻርድ ኒክሰን ርግቦች የበዓለ ሲመታቸው የሰልፍ ትዕይንት በሚያልፍበት መንገድ እንዳይገኙ ለማባረር ኬሚካል አስረጭተው ነበር እና የበዐሉ ታዳሚዎች የዋሽንግተኑ ፔንሲልቬኒያ አቨኑ ጎዳና ላይ መደዳውን ኬሚካሉ የገደላቸውን ርግቦች ሬሳ እንዳይረግጡ እየዘለሉ ያልፉ እንደነበር በፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ታሪክ ተመዝግቧል፡፡

Skyline media

20 Jan, 16:07


የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ

Skyline media

20 Jan, 16:07


የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ
-------

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ በዓለ ሲመት ትልቅ ቀን ነው፡፡ የራሱ የኾነ ወግ እና ሥርዐትም አሉት።

አንዳንዶቹ ከመጀመሪያው ፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ጀምሮ የነበሩ የክፍለ ዘመናት ዕድሜ የጠገቡ ወጎች አና ባሕሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ሁሉም ፕሬዚደንታዊ በዓላተ ሲመት በሚፈለገው ሥርዓት አና ወግ በታቀደው መሠረት ተከናውነዋል ማለት አይደለም፡፡ እሱም ነው አንዳንዶቹን ከሌሎቹ ይበልጥ አይረሴ የሚያደርጋቸው፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1789 ዓ.ም የተከናወነው የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ጆርጅ ዋሽንግተን በዓለ ሲመት
የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ጆርጅ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸውን የፈጸሙት ኒው ዮርክ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡

በወቅቱ ኒውዮርክ የአገሪቱ ጊዜያዊ መዲና ስለነበረች ነው፡፡ አሜሪካዊያን ከዚያ በፊት ፕሬዝዳንት ኖሯቸው ስለማያውቅ የምክር ቤት አባላቱ ሥነ ሥርዐቱ እንዴት ቢከናወን ይሻላል በሚል መክረው እስኪወስኑ ጆርጅ ዋሽንግተን አንድ ሳምንት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡

ከዚያ በኋላ እ አ አ ሚያዚያ 30 ቀን ላይ ፕሬzደንቱ እና ምክትላቸው እንዲሁም የምክር ቤቱ አባላት የHግ መወሰኛው ምክር ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በኋላ በረንዳው ላይ ወጥተው ደጅ ለሚጠባበቀው ታዳሚ እጃቸውን በማውለብለብ ሰላምታ ሰጡ፡፡

በመቀጠል ቃለ መሐላውን የሚያስፈጽሟቸው ዳኛ "በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትነት የተጣለብዎትን ኅላፊነት በታማኝነት ይወጣሉ? ብለው ጠየቋቸው፡፡

ጆርጅ ዋሽንግተን በአዎንታ ቃለ መሐላቸውን ሰጡ፡፡

ይህ ቃለ መሐላ እንዳለ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት ውስጥ የተቀመጠ ነው፡፡ ዳኛው ጆርጅ ዋሽንግተን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ምለው ቃል እንዲገቡ ለማድረግ ነበር ያቀዱት፡፡

ነገር ግን የሚከናወንበት ሰዓት ሲቃረብ ዳኛው መጽሐፍ ቅዱስ እንዳላመጡ ባወቁ ጊዜ በጥድፊያ ሰው ተልኮ ከሌላ ቦታ መጽሐፍ ቅዱስ በውሰት መጥቶ ጆርጅ ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸው ፈጸሙ፡፡

ዋሽንግተን ቃለ መሐላቸውን ከፈጸሙ በኋላ ያዘጋጁትን ንግግር በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት ፊት አነበቡ፡፡

ዊሊያም ማክሌይ የተባሉ ሴኔተር በግል ማስታወሻቸው ላይ ዋሽንግተን ንግግራቸውን ሲያነቡ ተጨናንቀው እጃቸው ይንቀጠቀጥ እንደነበር ማንበብ አስቸግሯቸው እንደነበረም ጽፈዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዚደንት ዋሽንግተን ግር ቢላቸውም ሥነ ሥርዓቱ እጥር ጥፍጥ ያለ እንደነበር አክለዋል፡፡

ቶማስ ጀፈርሰን በ1801 ዓ.ም

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1801 ዓ.ም የሦስተኛው ፕሬዝደንት የቶማስ ጄፈርሰን በዓለ ሲመት ደግሞ ከጆርጅ ዋሽንግተን በዓለ ሲመት ይበልጥ ቀለል ብሎ የተከናወነ ነበር፡፡

ቶማስ ጄፈርሰን ወደ በዓለ ሲመቱ ሥነ ሥርዐታቸው የሄዱት ከሳቸው በፊት እንደነበሩት ሁለቱ ቀደምቶቻቸው በሠረገላ ሳይሆን በእግራቸው ተጉዘው ነው፡፡

የአሜሪካ ምክር ቤት ካፒቶል ሲደርሱ ብዙ ሕዝብ ሲጠብቃቸው ነበር፡፡

ንግግራቸውንም አዘጋጅተው ነበር፡፡ ነገር ግን ድምጻቸው በጣም ድክም ያለ ስለነበረ ንግግራቸውን ሊሰማ የቻለው በጣም ጥቂት ሰው እንደነበር ታሪክ መዝግቦታል፡፡

ቢሆንም ዛሬ ያ የቶማስ ጄፈርሰን የበዓለ ሲመት ንግግር በአሜሪካዊያን ዘንድ በሚገባ ይታወቃል፡፡ በምርጫ ዘመቻው ወቅት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የነበረውን አስቀያሚ ጭቅጭቅ ለማርገብ ያደረጉት ንግግር አድናቆት አትርፏል፡፡

ሆኖም የምርጫው ዘመቻው ጭቅጭቅ የተወው አስከፊ ገጽታ ቀጠለ እና ከጄፈርሰን ጋራ የተፎካከሩት ከሳቸው በፊት የነበሩት ፕሬዚደንት ጆን አዳምስ በጄፈርሰን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ቀሩ፡፡ በዓለ ሲመቱ ነገ ሊሆን በዋዜማው ምሽቱ ላይ ጓዛቸውን ጠቅልለው ከዋይት ሐውስ ወጡ እና ወደቦስተን ተመለሱ፡፡

ዊሊያም ሄንሪ ሃሪሰን በ1841 ዓ.ም

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1841 የዘጠነኛው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሄንሪ ሃሪሰን የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት ታሪክ ሳይወሳ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በዓለ ሲመት ታሪክ ተወሳ ለማለት አይቻልም፡፡ ሲመረጡ የ68 ዓመት ሰው የነበሩት ዊሊያም ሃሪሰን በዘመኑ ከነበሩት ፕሬዝደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ነበሩ፡፡

ታዲያ እንደሚባለው በፕሬዝደንትነት ለማገልገል ጠንካራ መሆናቸውን በጣም ረጅም ንግግር በማድረግ ለማሳየት አስበው ነው ይባላል ኃይለኛ ቅዝቃዜ በነበረበት የበዓለ ሲመታቸው ዕለት ጭንቅላታቸውን በብርድ ቆብ ሳይሸፍኑ ካፖርትም ሳይደርቡ ቆመው ረጅሙን ንግግራቸውን አደረጉ፡፡ ያ በሆነ በወሩ አዲሱ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሃሪሰን ታምመው ሞቱ፡፡

ሥልጣን ላይ ሆነው ሕይወታቸው ያለፈ የመጀመሪያ ፕሬዝደንት ናቸው፡፡ ሐኪማቸው ፕሬዝደንቱን ለሕልፈት የዳረጋቸው የሳምባ ምች ወይም ኒውሞኒያ ነው ብለዋል፡፡፡በተለምዶ ግን ብዙዎች ረጅሙ ንግግራቸው የገደላቸው ፕሬዚደንት ይሏቸዋል፡፡

የሐሪሰን አሟሟት እ አ አ በ2014 ምርምር ተደርጎበት ነበር፡፡ ተመራማሪዎቹ ጄን ሜክሂዩ እና ፊሊፕ ሜክውላክ ሃሪሰን የሞቱት በሳምባ ሕመም ሳይሆን በሌላ ምክንያት ነው ይላሉ፡፡ እነሱ እንደሚሉት ሃሪሰን የታመሙት ከበዓለ ሲመታቸው በኋላ ወዲያውኑ ሳይሆን ቆይተው ከሦስት ሳምንታት በኋላ ነው፡፡ የነበራቸውም የሕመም ስሜት ድካም እና ጭንቀት እንጂ ሳምባቸው ላይ እንዳልነበረ ይናገራሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ በጊዜው ዋሽንግተን ዲሲ ጥሩ የፍሳሽ ማስወገጃ አገልግሎት ስላልነበራት የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ከኋይት ሐውስ በቅርብ ርቀት ሜዳ ላይ ይፈስ ስለነበረ ምናልባት በባክቴሪያ የተበከለ ውሃ ጠጥተው ሳይታመሙ አልቀሩም ሲሉ ተመራማሪዎቹ ድምዳሜአቸውን ኒው ዮርክ ታይምስ ላይ አስነብበዋል፡፡

የ30ኛው ፕሬዚደንት ካልቭን ኩሊጅ በ1923 ዓ.ም

ስለ ፕሬዝደንቶች በዓለ ሲመት ሲወሳ ታዲያ የሁሉም የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት አይረሴ ነው ማለት አይደለም፡፡ የ30ኛው ፕሬዚደንት ካልቭን ኩሊጅ በዓለ ሲመት ቀዝቀዝ ባለ ድባብ ከተከናወኑት ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኩሊጅ እ አ አ በ1923 ነሃሴ ወር ውስጥ ብዙም የሥራ ኃላፊነት ስላልነበረባቸው ቨርሞንት ወደሚኖሩት
ቤተሰቦቻቸው ቤት ለዕረፍት ሄደው ነበር፡፡

አንድ ቀን ሌሊት በተኙበት አባታቸው ይቀሰቅሷቸው እና ቴሌግራም እንደተላከላቸው ይነግሯቸዋል፡፡ ፕሬዚደንቱ ዋረን ሀርዲንግ አርፈዋል የሚል መርዶ የያዘ ቴሌግራም ነበር፡፡ በዚያ ኩሊጅ ፕሬዝደንት ሆኑ፡፡

ኩሊጅ በግል ማስታወሻቸው ላይ ይህንን ባውቅኩ ጊዜ መጀመሪያ ተነስቼ ቆምኩ እና ጸለይኩ፡፡ ከዚያም ከሕገ መንግሥቱ ውስጥ የፕሬዝደንት ቃለ መሐላው ያለበትን አውጥቼ ለአባቴ ያዘው ብዬ ሰጠሁት፡፡ ከዚያም ተመልሼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ብለው እንደጻፉ ተመልክቷል፡፡

ሊንደን ጆንሰን 1963 ዓ.ም

ቀደም ሲል ከተነገረው በተጻራሪ ድንገተኛ ሐዘን የተመላበትን ሊንደን ጆንሰን 36ኛው ፕሬዚደንት ሆነው ቃለ መሓላ የፈጸሙበትን ቀን አይረሴ ነው፡፡ ጆንሰን ቃለ መሃላ የፈጸሙት ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በሰው እጅ በጥይት ከተገደሉ ከአንድ ሰዓት ተኩል በኃላ ነበር፡፡
ጆንሰን በፕሬዝደንታዊው አውሮፕላን ኤር ፎርስ ዋን ውስጥ ቀኝ አጃቸውን ከፍ አድርገው ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ የተነሳው ፎቶግራፍ ታሪኩን ይናገራል፡፡ በስተቀኛቸው ባለቤታቸው በስተግራቸው የሟቹ ፕሬዚደንት ባለቤት ጃኪ ኬኔዲ አጅበዋቸው ይታያሉ፡፡

Skyline media

18 Jan, 21:13


በከባድ ብርድ ምክኒያት የትረምፕ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዐት በቤት ውስጥ እንዲከናወን ተወሰነ
--------

የአሜሪካ ተመራጭ ኘሬዝደንቶች ከቤት ውጭ በሚካሄድ በዓለ ሲመት ስነስርዓት ነበር ቃለ መሃላ የሚፈፅሙት።

አሁን ግን በዋሽንግተን ባለው ከባድ ብርድ ምክንያት የዶናልድ ትራምኘ የቃለ መሃላ ስነስርዓት በምክር ቤቱ ሕንፃ ካፒቶል ሂል እንዲከናወን ተወሰኗል።

ቃለ መሃለው በሚፈፀምበት የፊታችን ሰኞ በዋሽንግተን እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ይኖራል በመባሉ ነው የተመራጩ ፕሬዚደንት ቃለ መሃላ በምክር ቤቱ ውስጥ እንዲከናወን የተወሰነው።

Skyline media

18 Jan, 18:47


የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆኑት የቀድሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጊ የትራምፕን መምጣት ተከትሎ ወደ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

ቲቦር ናጊ የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መወገድ አለበት በሚል የሚታወቁ ሲሆን በቅርቡ የሶሪያው መሪ በሽር አልአሳድን መውደቅ ተከትሎ ኢሳያስም የአሳድ እጣፈንታ ይጠብቀዋል በማለት በማህበራዊ ሚዲያቸው መለጠፋቸው ይታወሳል።

የቀድሞ በ ኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ቲቦር ናጊ እንደ ህዳሴው ግድብ በመሳሰሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ ጎን በመሰለፍ የሚታወቁ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ውዴታም በአደባባይ የሚገልፁ ጉምቱ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሲሆኑ ከወዲሁ ኢሳያስና ግብፅን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ዜና መሆኑ ተዘግቧል ።

Skyline media

18 Jan, 17:04


የአሜሪካው ተመራጭ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሌጋሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በመምራት በበዓለ ስመታቸው እንዲገኙ መጋበዛቸው ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የምታደሙ የአፍሪካ መሪዎችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ስም ዝርዝር በአዘጋጆቹ በኩል ይፋ ተደርጓል።

እንደ ደይሊትራስ ዘገባ ግብዣው በጥር 13 ቀን 2025 ለወጣቱ የናይጄሪያ የንግድ ሥራ መሪ ዶ/ር ኡዞቹክ በተላከ ደብዳቤ “ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕን በማክበር የመድብለ ባህላዊ ጥምረት የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የምረቃ ቦል አስተናጋጅ ኮሚቴን በመወከል እንዲገኙ ስንጋብዝ በታላቅ ክብር ነው ይላል ብሏል።

ይህ ታላቅ ዝግጅት በጥር 20፣ 2025 በዋሽንግተን የሚካሄድ ሲሆን በማዳም ፍራንያ ኢ ካብራል ሩዪዝ መሪነት ከአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት በቀረበው ሀሳብ እንደተገለጸው ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅዖ እና አመራር እውቅና በመስጠት፣ በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ በመገኘታችን ታላቅ ክብር እንሰጣለን ብሏል።

በዚሁም የወቅቱን የአፍሪካ ሌጋሲሲ ኢንስቲትዩት ልዑካንን በዩኤስ ፕሬዝዳንታዊ የትራምፕ በዓለ ስመት ላይ የሚመሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንደሆኑም ዘገባው ጠቅሷል።
WT

Skyline media

17 Jan, 16:24


የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክቶክ የብሔራዊ ጸጥታ አደጋ በመደቀኑ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ መስጠቱ ተሰማ፡፡
በፍርድ ቤቱ ዛሬ በተካሄደው የቃል ክርክር የቻይናው ባይትዳንስ ንብረት የሆነው ቲክቶክ እንዲታገድ በሙሉ የድምጽ ድጋፍ ማሳለፉን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
በአሜሪካ ከ170 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚ ያለው ቲክቶክ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል ነው እንዲሸጥ ካልሆነም እንዲዘጋ የሚል ክስ የቀረበበት።
ዛሬ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ቲክቶክ ከእሁድ ጀምሮ የሚታገድ ሲሆን እግዱ ተግባራዊ ሲሆን መተግበሪያውን አዳዲስ ተጠቃሚዎች ማውረድ እንደማይችሉ እና ነባር ተጠቃሚዎች ደግሞ ማዘመን (አፕዴት) እንደማችሉ በመረጃው ተገልጿል።
ዶናልድ ትራምፕ የቲክቶክን ጠቀሜታ መገንዘባቸውና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን እንዲያዘገይ ጠይቀው የነበረ ሲሆን ጉዳዩን በድርድር እፈታዋለሁ ማለታቸው ይታወሳል።
የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 9 ዳኞች ያሉት ሲሆን የሀገሪቱን ህገ መንግስት የሚጻረሩ ጉዳዮችን የመስማት፣ ለህግ ትርጓሜ የመስጠት፣ የሲቪል መብቶችን የማስጠበቅ፣ በግዛቶች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን የመፍታት፣ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮች የመምራት ስልጣን አለው፡፡

Skyline media

17 Jan, 16:20


(ቴዲ ሀዋሳ)

የፋሲል ግንብ እድሳት እንዴት ተካሄደ? የመንጣቱ ምክንያት ምንድን ነው?

የጥገና እድሳት እየተከናወለት ያለው ታሪካዊው የፋሲል ግንብ በቅርቡ ይፋ መደረጉን ተከትሎ መወዛገቢያ መሆኑ አልቀረም። ታሪካዊው ሽሯሟ ቀለም ያለው የፋሲል ግንብ ቀለሙ ነጥቶ መታየቱ ለበርካታ መላምት ክፍት እንዲሆን አድርጎታል።

የታሪካዊው ግንብ ቀለም ለዘመናት ከሚታወቅበት ተለውጦ ለምን ነጣ? የሚል ጥያቄ እንዲነሳም ምክንያት ሆኗል።

ለዚህ ምላሽ የሚሰጡት በጥገና እድሳቱ በአማካሪነት እንዲሁም በጥናት የተሳተፉት አንጋፋው አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ የፋሲል ግንብ የተሠራበትን የግንባታ ግብዓት በመጥቀስ ነው።

የፋሲል ግንብ ህንጻ ከመቶ ዓመታት በፊት ሲገነባ በአነስተኛ ድንጋዮች እና በኖራ ሲሆን፣ ለረጅም ዓመታት ዝናብ፣ በፀሐይ እና በተፈጥሯዊ ሂደቶች ውስጥ ሲያልፍ በርካቶች የሚያውቁትን ይሄንን "ሽሯማ" መልክ እንዳመጣ ፋሲል ጊዮርጊስ ይናገራሉ።

አሁን እድሳቱ የተደረገበት ኖራ አዲስ በመሆኑ ቀለሙ ነጣ እንዳለም ያስረዳሉ ይላሉ።

ፋሲል እንደሚገልጹት የእድሳት ሥራው የተከናወነው የፋሲል ግንብ በመጀመሪያ በተገነባበት ማቴሪያል (ቁስ) በዋናነት በኖራ እና በድንጋይ ነው።

"የቅርስ አጠባበቅ ሕግን በተከተለ መልክ ነው የተሠራው" ይላሉ።

"የኖራው አዲስ መሆን ብቻ ይሄንን ነጣ ያለ ቀለም አምጥቷል" የሚሉት አርክቴክቱ ፋሲል የኖራ እና የድንጋይ መልኩ ከተወሰነ ዓመታት በኋላ ወደ ድሮው መልኩ ይመለሳል ይላሉ።

ልዩነቱ አዲስ የመሆን እና የማርጀት ጉዳይ ነው ሲሉም አጽንኦት ይሰጣሉ።

የፋሲል ግንብ መጀመሪያ ሲሠራ ኖራው ለብዙ ወራት ወይም ለዓመታት ተቀብሮ የነበረ ሲሆን፣ አሁንም ሲታደስ መነሻውን ተከትሎ ኖራው ለበርካታ ጊዜያት እንዲቀበር ተደርጎ ጥገናው መካሄዱን ጠቅሰዋል።

ቅርሶች በተፈጥሮ፣ በፀሐይ፣ በዝናብ፣ በአቧራ ምክንያት በዓመታት ቀለማቸው እየተቀየረ የሚሄድ ሲሆን፣ ይሄኛውም ከዓመታት በኋላ የሚታወቀውን ቀለም ይይዛል ይላሉ።

በዓለም አቀፉ የቅርስ ጥገና ሕግ መሠረት ዋነኛው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ በተሠራበት ቁስ (ማቴሪያል) ታድሷል ወይ? የሚለው ነው የሚሉት ፋሲል፤ በተሠራበት ድንጋይ እና ኖራ መልሶ መጠገኑ ዋናው ነገር እንደሆነ አስረድተዋል።

"ይህንንም በትክክል መሥራቱን አረጋግጠናል" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ።

በአንዳንድ ሁኔታዎች የድሮ ቀለሙን ለማምጣት ለመልክ ሲባል ኬሚካል እንደሚቀላቀል የሚጠቅሱት አርክቴክት ፋሲል፤ እነዚህ ግን ኬሚካል ነክ ነገሮች ስለሆኑ ያልታሰበ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

"ቀለሙ እንደ ድሮው ቢመስል እንወድ ነበር፤ ሆኖም ለቀለም ተብለው የሚጨመሩ ነገሮች ያልታሰበ አደጋን በቅርስ ላይ ያመጣሉ" በማለት ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

አክለውም በዓለም የቅርስ አጠባበቅ ደረጃ ዋነኛው ነገር ቅድሚያ የሚሰጠው የመነሻ ሃሳቡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኖራው ትክክለኛ እና አስተማማኝ በመሆኑ የጥንቱ እንደያዘ የጥገና እድሳቱ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

"መነሻውን ሳይለቅ ጥርሳችንን ነክሰን የሠራንበት ነው" ሲሉ የሚናገሩት ፋሲል፣ የቀደመ መልኩ በጊዜ ብዛት ይመጣል ሲሉ የነበረው ገጽታ በጊዜ ሂደት እንደሚመለስ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ታዲያ ይሄ በርካቶች በቀደመ መልኩ (ሽሯሟ) መልክ የሚያውቁት የፋሲል ግንብ መቼ ተመልሶ ይመጣ ይሆን? በሚል ቢቢሲ አርክቴክቱን ጠይቋአዋል።

ዝናብ ሲመታው እና የአየር ሁኔታዎች ሲፈራረቁበት እየተቀየረ ይሄዳል የሚሉት ፋሲል፤ ህንጻው ወደ ቀደመ ቀለሙ ለመመለስም ከሦስት እስከ አራት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ፋሲል እንደሚገልጹት "አንዳንድ ቦታ ላይ በጣም የጠቋቆሩ [የግንቡ አናት ላይ] አካላት ነበሩ" ድንጋዮቹ ወደ ነበሩበት ለመመለስ እስከ አምስት ዓመት ድረስ የሚደርስ ወይም የግንቡ አናት ላይ ያሉትን ጠቆር ያሉትን የቀደመ ገጽታ ለማምጣት ከዚያ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚወስድ ያስረዳሉ።

Skyline media

12 Jan, 01:48


ከሃሰተኛ ምስል ይጠንቀቁ።
የሎስ አንጀለስን አካባቢ ባወደመው ሁለት ትላልቅ ሰደድ እሳት 11 ሰዎች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ባለሥልጣናቱ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጎጂዎችን እንደሚያገኙ ይጠብቃሉ።
በጥቂት አጋጣሚዎች፣ ጓደኞች እና ቤተሰብ ስልክ ላይ ነበሩ እና የሚወዷቸውን የመጨረሻ ደቂቃዎች አንድ ላይ ማሰባሰብ ችለዋል።  አንቶኒ ሚቼል መስመሩ ከመጥፋቱ በፊት "እሳቱ በጓሮው ውስጥ ነው" ብላ ለልጇ ተናግራለች።  ለሌሎች፣ ተስፋ የቆረጡ ጸሎቶች ወይም እንባዎች በፍፁም አይረሱም።

ፖሊስ በመጪዎቹ ቀናት ተጨማሪ ተጎጂዎችን እንደሚያገኝ ይጠብቃል፣ ስድስት ንቁ እሳቶች አሁንም እየተቃጠሉ እና የነፍስ አድን ሰራተኞች ከ10,000 በላይ ህንፃዎችን አመድ እና ፍርስራሽ በማጣራት ላይ ናቸው።  የሎስ አንጀለስ ካውንቲ የህክምና መርማሪ ጽህፈት ቤት “በእሳት ሁኔታዎች እና የደህንነት ስጋቶች” ምክንያት የተወሰኑ አካላትን መለየት ብዙ ሳምንታት ሊወስድ ይችላል።  የእሱ ድረ-ገጽ እንዲህ ይላል፡- “እባክዎ እንዲሁም እንደ የጣት አሻራ እና የእይታ መታወቂያ ያሉ ባህላዊ የመለያ ዘዴዎች ላይገኙ እንደሚችሉ እና እነዚህን ሟቾች ለመለየት ተጨማሪ ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

የሎስ አንጀለስ አውዳሚ ሰደድ
እሳት ሲስፋፋ አንዳንድ ተጎጂዎች የማያቋርጥ እሳቱን ለመመለስ ሲሞክሩ ሞቱ።  ሌሎች አረጋውያን ወይም አካል ጉዳተኞች ከአልጋው ላይ ታፍነው ሞተዋል፣ከሚያቃጥል ሙቀት ማምለጥ አልቻሉም።  አንዳንዶች ሌሎችን ለመርዳት ሲሉ ሞተዋል። ያሳዝናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ ሃሰተኛ ፎቶዎችና ምስሎች እየተሰራጩ ሲሆን እነዚህም ምስሎች ሐሰኛ ናቸው።

Skyline media

11 Jan, 15:14


https://www.tiktok.com/t/ZTYKwc942/

Skyline media

11 Jan, 14:50


የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮዽያ መጡ እላለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

Skyline media

07 Jan, 00:03


https://www.youtube.com/live/ooHBgAhhEio?si=WcrHUkQ2f6r-AxXh

Skyline media

03 Jan, 22:51


ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ቀጣና ብሔራዊ ጥቅሟን እውን ለማድረግ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ትስስር መፍጠር እንደሚገባት የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን ገለፁ።
https://youtu.be/27HWhf9p2ro

Skyline media

31 Dec, 06:28


የኦሮሞ ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ አሳትሞ ያሰራጨውን "አልጸጸትም" የተሰኘ መጽሐፉን PDF ሙሉውን በነጻ አሰራጭቶታል። የማንበብ ፍላጎቱ ላላችሁ ሼር አድርገነዋል። መልካም ንባብ።

Skyline media

30 Dec, 14:03


ሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድን የተከተለ፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ አቋም

https://www.youtube.com/watch?v=7HV25SO462M&ab_channel=EBC

Skyline media

29 Dec, 19:17


የኦሮሞ ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ አሳትሞ ያሰራጨውን "አልጸጸትም" የተሰኘ መጽሐፉን PDF ሙሉውን በነጻ አሰራጭቶታል። የማንበብ ፍላጎቱ ላላችሁ ሼር አድርገነዋል። መልካም ንባብ።

Skyline media

24 Dec, 12:01


#ኢትዮጵያ #ሶማሊያ

ኢትዩጲያ እና ሶማሊያ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ መምከራቸውን አሳወቁ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ስለመወያየታቸው ተሰምቷል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል ተብሏል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር ይገባልም ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጻል፡፡

Skyline media

22 Dec, 11:01


ጀግናው አትሌት ስለሺ ስህን

Skyline media

22 Dec, 10:50


መረጃ‼️

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ስለሺ ስህንን አዲስ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ !

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ትላንት እና ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዷል።

በጉባኤው ከሚጠበቁ ሁነቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀጣዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በአብላጫ ድምፅ አሸንፏል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን በምርጫው 1️⃣1️⃣ ድምፆችን በማግኘት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን ማሸነፉ ታውቋል።

ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት በሚቀጥሉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።

Skyline media

22 Dec, 09:14


የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ እየተከናወነ ነው
*************

በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለፕሬዝደንትነት 6 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ፕሮፋይላቸውም ለጉባኤው ቀርቧል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴው ማብራሪያ እየሰጠ ነው፡፡

1.ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም... ከትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

2.አቶ ያዬህ አዲስ.. ከአማራ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

3.ስለሺ ስህን... ከኦሮሚያ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

4.ሪሳል ኦፒዮ... ከጋምቤላ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

5.አቶ ዱቤ ጅሎ... ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም፤

6. ኮ/ር ግርማ ዳባ... ከደቡብ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ለመሆን እየተወዳደሩ ይገኛል፡፡

በምርጫው ሂደት 27 ድምጽ ሰጪዎች አሉ፡፡

በሃብታሙ ካሴ

Skyline media

21 Dec, 03:50


https://youtu.be/5STdeyAEn2U?si=9AZTBk3EZo4-M5AI

Skyline media

16 Dec, 00:07


በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በህገወጥ ስራዎች ላይ ተሰማርተዋል !
--------

ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መግለጫ የተሰጠ መግለጫ 👇👇

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ የሕግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል የማብራሪያው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደህንነቱንና ጥራቱን የጠበቀ ዘመናዊ፣ ተደራሽ የውጭ ዜጎች አገልግሎት በመዘርጋት የሀገራችን የውጭ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍስት በመጨመር የተጀመሩትን የልማትና የለውጥ ጉዞ በማፋጠን የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ የበኩሉን ሚና ለመወጣት የሚያስችለውን የሪፎርምና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏት ተፈጥራዊና ታሪካዊ የቱሪዝም እምቅ ሀብቶች እና ኢንቨስትመንት ተጠቃሚ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ በሀገር ደረጃ በሚደረግ ጥረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቱሪስት ቪዛ፣ ኮንፈረን ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው የቪዛ ክፍያ ተመን ከ23 በመቶ በላይ እንዲቀንስ መደረጉን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክፍያ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 550/2016 መገንዘብ ይቻላል።

መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው መልካም ጉርብትናና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ካለው ቁርጠኛ አቋም በድንበር አካባቢ ከሚደረጉ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ መፍቀድ በተጨማሪ መግቢያ ቪዛ ሳይጠየቁ በቀን ማህተም (ያለ ቪዛ ከፍያ) ገብተው ለ90 ቀናት እንዲቆዩ መፍቀዱ ይታወቃል።

በተለይ ከኤርትራ (አስመራ ወደ አዲስ ኣበባ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ኤርትራዊያን ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ ማድረጉ በሁለቱም ህዝቦች ያለው ግንኙነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ምን ያህል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ስደተኞች በጥገኝነት እንደሚኖሩ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ፣ ሚዛኑን ባልጠበቀ እና ኃላፊነት በጎደለው አግባብ ተቋማችን ኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውን ሰዎች የተለየ በደል እና አድልዎ እየፈጸመባቸው እንደሆነ፣ ለመውጪያ ቪዛ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ፣ በስደተኝነት የተመዘገቡ ኤርትራዊያን ዲፖርት እየተደረጉ እንደሆነ አድርገው ሲዘግቡ ተስተውሏል።

በርካታ የውጭ ሀገር ሰዎች በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሀገር ውስጥ ሲቆዩ የሚስተዋሉ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ ሀገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ከመሰማራት ጀምሮ በህገወጥ የማዕድን ዝውውር፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በአደገኛ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኮንትሮባንድ፣ በሀሰተኛ ሰንዶች ዝግጅት ወዘተ የመሳሰሉ የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራት ከባድ እና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ሲፈፅሙ መገኘታቸውን ማርጋገጥ ችለናል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባትና በህጋዊ መንገድ ገብተው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እነዚህን አካላት ወደ ህጋዊ መንገድ ለማስገባትና ለመመዝገብ በተደጋጋሚ ጥሪ ማድርጉ የሚታወቅ ቢሆንም ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ስርዓቱ የገቡ ግን በጣም ጥቂት ናቸው።

ስለሆነም የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጉላት አስፈላጊ ነው።

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሐሰተኛ ወይም የተጭበረበረ ማንነት በመያዝ ለውጭ ሀገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ተገኝተዋል።

በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች በሻንጣ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር በርካታ ፍልሰተኞችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።

የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነድና ማንነት በመጠቀም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሲያከናውኑ እና ከህግ ውጭ ሰነዶችን ሲጠቀሙ መገኘታቸው።

ስለዚህ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የሀገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ይታወቃል።

በመሆኑም ህጉ ተፈጻሚ የሚሆነው በሁሉም የሚመለከታቸው የውጭ ሀገር ሰዎች እንጂ በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው። ስለሆነም ለኤርትራዊያን ዜጎች እንደማንኛውም የጎረቤት ሀገር ዜጎች በቀን ማህተም ገብቶ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ (90) ቀናት ቆይቶ ለሚሔድ ሰው ምንም ዓይነት የቪዛ ክፍያ እንደማይጠየቅ ለመግለጽ እንወዳለን።

ከተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ቆይተው የሚጣልባቸው ቅጣት ቢሆንም የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ጨምሮ ለጎረቤት ሀገራት እንዲከፍሉት የሚጠየቀው ክፍያ በእጅጉ (በ200 በመቶ) የቀነሰ ሆኖ እያለ ለኤርትራዊያን የተለየና የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ተደርጎ መዘገቡ ከእውነታ የራቀ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተም ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ጥላ ከለላ መሆን የቆየ ታሪኳና ባህሏ እንደሆነና የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ስደተኞችን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች በጥገኝነት እንድሚገኙ ይታወቃል።

በመሆኑም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከሀገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲከፍል የተረገ ሰው የሌለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

እውነታው ይህን ሆኖ እያለ በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ያለ አግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ መዘገቡ ከእውነት የራቀ ነው።

የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በመጠበቅ ህጋዊ የውጭ ሀገር ሰዎች እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ስራ ላይ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችን እያቀረብን በተለይ ሚደያዎች ሚዛናዊ በመሆን የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ አወንታዊ ሚና እንዲወጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Skyline media

14 Dec, 16:47


ጥቆማ ❗️❗️
እንደወረደ 👇👇👇

አዲስ ነገር መረጃዎች ሠላም ከናንተጋ ይሁን
ኧረ ጅጅጋ 02ቀበሌ ነጋዴዎች በጣም እየተበደልን ነው የቀበሌ አመራሮች አማርኛ ተናጋሪ የሆነ እየመረጡ ቀበሌ እያሠሩ 2000እስከ5000 እያስከፈሉን ነው ክፍያውሰ ደረሠኝ የለውም በአካውንት አደለም የሚገባው በራሳቸው ስልክ ቁጥር ኢ-ብር ነው ሚገባው እና በየ ወሩ አንዴ ግዴታ አረጉት ምክንያት የለውም የነጋዴው ብዛት ከ150በላይ ነው በየመንገዱ ሚዛን ሚሠሩ ህፃናት እንኳን አይምሩም 500እያስከፈሏቸው ነው አማራ የተባለ ብቻ ላይ ነው ይሄን የሚያረጉት ነጋዴው ሠርቶ ለነሱ ነው ሠዉ ለማን እደሚናገር ግራb ገብቶናል እነዚ ሠዎች እንደዚህ  ያረጉት አንዴ አደለም ተደጋጋሚ በየወሩ ነው እነዚ ሠዎች በጣም የተደራጁ ናቸው ገቢያቸው 200ሺ በላይ ነው በየወሩ በምን መጡ ተብሎ ጭንቅ ነው አዘኔታ የላቸው ሴት ጭምር በጥፊ ነው የሚመቱት አማራ ከሆነች ምክንያት መጠየቅ አይቻልም ሀይ ሚላቸው ጠፋ በጣም ተማረናል
እባካችሁ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጠው 🙏🙏

#አዲስ_ነገር_መረጃ

Skyline media

14 Dec, 08:15


የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር …

አዲስ አበባ፣ ታሕሳሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት መነቃቃት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የራሷ ወደብ እንደሌላት ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች አንዳቸው የሌላኛቸውን ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት እና በአፍሪካ ሕብረት ደንቦች ላይ የሰፈሩ ዓለም አቀፍ ሕጎችን ለማክበር ተስማምተዋል።

ይህን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ የሕግ ባለሙያው አንዷለም በእውቀቱ÷ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከሶማሊያ ጋር የተፈራረመችው ስምምነት የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንጻር ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በአፍሪካ የባሕር በር ከሌላቸው ሀገራት ሕዝብ 33 በመቶውን እንደሚሸፍን በተባበሩት መንግሥታት…

https://www.fanabc.com/archives/275233

Skyline media

13 Dec, 10:14


https://www.tiktok.com/t/ZTY94bBhV/

Skyline media

12 Dec, 03:23


በቱርክ ሲደረግ የነበረው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ 
** 

በቱርክ
ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቅቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ግብዣ ዛሬ ምሽት በአንካራ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። 

መሪዎቹ በመግለጫቸውም፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ከፍተኛ አስታዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡  

የኢትዮጵያ የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡
 
ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በበኩላቸው፤ የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡ 

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

Skyline media

11 Dec, 19:35


https://www.tiktok.com/t/ZTYHeqXP3/

Skyline media

03 Dec, 05:49


አንጋፋዋ ሙዚቀኛ አስቴር አወቀ ከሜትሮፖሊታን
ሪል እስቴት ጋር ለመሥራት ተፈራረመች



የሶል ንግስቷ አርቲስት አስቴር አወቀ፣ ከሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት ጋር በጋራ ለመሥራት የተስማማች ሲሆን፤ ስምምነቱ አምባሳደርነትን አያካትትም ተብሏል፡፡፡


ሜትሮፖሊታን ሪል ስቴት፣ ከአንጋፋዋ አቀንቃኝ ጋር የተፈራረመው ስምምነት በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ወደፊት የምታወጣቸውን ሥራዎች እንዲሁም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትሰራቸውን ሙዚቃዎች ማስተዋወቅን ያካትታል፡፡

የአርቲስቷ ማናጀር ወይዘሪት አዳነች ወርቁ እንደገለጹት፤ ድምፃዊጻዊት አስቴር አወቀ ከዛሬ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሜትሮፖሊታን ሪል እስቴት ጋር ሥራዋን ጀምራለች፡፡

Skyline media

30 Nov, 13:06


https://www.youtube.com/live/4v2f5nXM130?si=ncYD3GQGSunwLVvP

Skyline media

27 Nov, 19:21


ጥቆማ ስጡ ተብሏል

በግሩፕ ላይ ሼር አድርጉት

በፎቶው የተያያዙትን ተጠርጣሪዎች ህብረተሰቡ ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጠው የፌደራል ፖሊስ ጠይቋል።

📌ከባንክ እንደተደወለ አስመስለው የተለያዩ ስልኮችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ ሚስጥር ቁጥር በመቀበል በማጭበርበር ከግለሰቦች አካውንት ብር ከሚመዘብሩ ወንጀለኞች ህብረተሰቡ እንዲጠበቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

📌ሕብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የመጭበርበር ወንጀል እራሱን በመጠበቅ ከዚህ በታች በስምና በፎቶ ግራፍ የተገለጹትን ጠርጣሪዎች ሲመለከት ተቋሙ ያበለፀገውን የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ጥቆማና ማስታወቂያ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

Skyline media

14 Nov, 18:36


https://www.youtube.com/live/IUL_kNW5d3U?si=z8FDyhxkvh6okg5J

Skyline media

13 Nov, 13:04


ኤርትራውያን ከኢትዮጵያ ለመውጣት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ገለጹ!

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመሄድ ሲፈልጉ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት እስከ 4ሺህ ዶላር የሚደርስ የተጋነነ ክፍያ እየተጠየቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።የክፍያው ምክንያት ግልፅ እንዳልኾነና ወጥነትም እንደሌለው የተናገሩት ኤርትራውያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የክፍያውን መጠን ዳግም እንዲመለከተው መጠየቃቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል።

የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ፣ እየተጠየቀ ያለው ክፍያ፣ ለመውጫ ቪዛ ሳይሆን፣ በሕገወጥ መንገድ ለቆዩበት ጊዜ የሚወሰን ቅጣት ነው ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡ክፍያው በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃገራት ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተቋሙ የውጭ ዜጎች ምዝገባና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አዳነ ደበበ ገልጸዋል።

አክለውም ክፍያው የውጭ አገር ዜጎቹ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ በጨመረ ቁጥር ክፍያውም እንደሚጨምር ጠቅሰው፤ በህገወጥ መንገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ያሉ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በተቋሙ ተመዝግበው ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ እንዲይዙም አሳስበዋል።
Via_VoA

@Addis_News
@Addis_News

Skyline media

13 Nov, 13:04


ፍራንኮ ቫሉታ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ተባለ

በፍራንኮ ቫሉታ ከውጭ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በመደበኛ የንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ አማካኝነት እንዲገቡ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፍራንኮ ቫሉታ መሰረታዊ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የምርት እጥረት እንዳይከሰት የተወሰነ እገዛ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ፍራንኮ ቫሉታ ባልተገባ መንገድ ለጥቁር ገበያ በመጋለጡ በውጭ ምንዛሬ ላይ ጫና በማሳደር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ትግበራው በመደበኛውና በትይዩ ገበያው መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ተቀራራቢ በማድረጉ የፍራንኮ ቫሉታ እንዲነሳ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም መደረጉን እና በሂደት ላይ ያሉ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲገቡ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም የንግድ ባንኮች ለመረሰታዊ ሸቀጦች የሚሆን በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዳላቸው ጠቅሰው በውሳኔው መሰረትም ከውጭ የሚመጡ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በንግድ ባንኮች የመተማመኛ ሰነድ ብቻ እንዲገቡ መወሰኑንና ይህም ወደ ተግባር መግባቱን አረጋግጠዋል፡፡

መንግስት በመሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ ለግል ባለሀብቶች ፍራንኮ ቫሉታ መፍቀዱ የሚታወስ ነው፡፡

@Addis_News
@Addis_News

Skyline media

08 Nov, 20:15


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
አዲሷ የትራምፕ የጽህፈት ቤት ኃላፊ ማን ናቸው?
ተመራጩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በይፋ ሥልጣን ከመረከባቸው በፊት ሹመኞቻቸውን መምረጥ ጀምረዋል። ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳቸው ኃላፊ የነበሩትን ሱዛን ሳመርል ዋይልስ ጥር ወር ለሚረከቡት ዋይት ሐውስ የጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ መርጠዋቸዋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

Skyline media

08 Nov, 13:28


ገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ምርቶች ላይ ክልከላ ጣለ

አርብ ጥቅምት 29 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዘይትን ጨምሮ ያለውጭ ምንዛሬ ፍቃድ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች ላይ ሚኒስቴሩ ክልከላ እንዳደረገ ነው የገለጸው፡፡

በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያ ዘላቂ በሆነ መንገድ ውጤታማ እንዲሆን ከማስፈለጉ አንጻር ይህን ውሳኔ መወሰን የግድ ሆኖ መገኘቱም ነው የተገለጸው፡፡

በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈጸመባቸው እቃዎችም ከዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ጀምሮ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን የጉምሩክ መስፈርት በማሟላት እቃቸውን ማውጣት እንደሚገባቸው የገለጸው ገንዘብ ሚኒስቴር ይህን እንዲያስፈጽሙም ለጉምሩክ ኮሚሽንና ለብሄራዊ ባንክ ደብዳቤን ልኳል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤው በቀጣይ ዘይትን ጨምሮ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች  በምን አግባብ በአዲስ አሰራር ይቃኛሉ የሚለው ላይ ግን ግልጽ የሆነ ማብራሪያን አላስቀመጠም፡፡

Skyline media

07 Nov, 11:26


ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን እንደያዙ ሊያደርጓቸው የሚችሉት ውሳኔዎች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ለአንድ ቀን ብቻ አምባገነን መሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን ጥር 6 በይፋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ስራ ይጀምራሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/48BHCFH

Skyline media

06 Nov, 12:54


https://www.tiktok.com/t/ZTFcth2WQ/

Skyline media

04 Nov, 20:28


https://www.tiktok.com/t/ZTFvL78wX/

Skyline media

30 Oct, 01:12


ጽንስ ማቋረጥን ትራምፕ ማገዱ በግለሰብ የገላ ነጻነት ላይ መወሰን በመሆኑ ሴቶች ነጻነታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል እኔም ይሄንኑ መብታቸውን በህግ እንዲከበር ህግ አወጣለሁ፤ ፊሪማዬንም አኖርበታለሁ ብለዋል።

የድንበር ማስከበርና የስደተኞች ጉዳይን በሚመለከትም የተጠናከረ የድንበር ጥበቃ ስርዓት እንደሚዘረጉና ህገወጦች ሲያጥሙም ወዲያ እንደሚያባርሩ አረጋግጠዋል። ይሁንና በህጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ ስደተኞች መብታቸውን እንደሚያስከብሩና አሜሪካንን በመገንባት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ንግግራቸውን በመቀጠል ለወጣት አዲስ ቤት ገዥዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቤቶች እንዲገነቡ እንደሚደርጉና የቅድሚያ ክፍያ ድጋፍም እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል።

ትራምፕ በቅስቀሳው አሜሪካውያንን ለመከፋፈል እየጣረ ነው በማለት የከሰሱት እጩ ፕሬዚዳንቷ ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈል ድምጹን ለሀሪስ እንዲሰጣቸውና እርሳቸውን ለሁሉም አሜሪካውያን ያለ ልዩነት እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል ።

የድምጽ መስጠት ሂደቱ እየቀጠለ የሚገኘው የዘንድሮው ምርጫ በቀጣዩ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሲሆን ቀጣይ የሃያሏ ሃገር መሪም ተለይቶ ይታወቃል።
በአንተነህ አብርሃም
ከዋሽንግተን ዲሲ

Skyline media

30 Oct, 01:12


"እኔ ከተመረጥኩ ከምሰራው ዝርዝር ጋር ትራምፕ ከተመረጠ ከጠላቶቹ ዝርዝር ጋር ወደ ፕሬዚዳንት ቢሮ ይገባል" ካማላ ሃሪስ እጩ ፕሬዚዳንት

የዓለማችን ልእለ ኃያሏ አሜሪካ እጩ ተወዳዳሪ ካሚላ ሀሪስ በቀጣዩ ሳምንት በሚጠናቀቀውና የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በመከናወን ላይ በሚገኘው ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ሰንብተዋል።

ይህ ምርጫ በሁለት ፓርቲዎች ወይም በሁለት እጩዎች መካከል የሚካሄድ አይደለም። ምርጫው በአንድነትና ነጻነት እንዲሁም በመከብለዋል።

በቀውስ መካከል የሚደረግ ነው ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ የመዝጊያ ንግግር በዋሽንግተን ዲሲ ፕሬዚዴንሻል ጋርደን ከነጩ ቤተመንግስት ጀርባ አድርገዋል።

ከ40 ሺ በላይ ደጋፊዎች በተገኙበት አደባባይ ባሰሙት የቅስቀሳ ንግግር በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ከፍተኛ ትችት የሰነዘሩት እጩ ፕሬዝዳንቷ ፤ ትራምፕ ከፋፋይና ህዝቦች እርስ በርሳቸው አንዱ ሌላውን እንዲጠራጠር ቀስቅሷል ሲሉ ከሰዋቸዋል።

ትራምፕ በርካታ ክሶች የተከፈቱበትና በፍርድ ቤት በመታየት ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው ያሉት ካሚላ ሃሪስ፤ የፈጸሟቸው ወንጀሎችን ያጣሩ፣ የመረመሩና ለህግ ያቀረቡትን ለመበቀል "ጠላቶች " ያሏቸውን ስም ዝርዝር በእጃቸው መያዛቸውንና ገልጸው ፤ የፕሬዳንቱን ቢሮ አሸንፈው ከወሰዱ ከፍተኛ በቀል ሊያደርሱ እንደሚችሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል ።

እኔ ህገወጥነትን ስከላከልና ለተጎዱት ጥብቅና ስቆም ነበር ያሉት ሀሪስ፤ ከመረጣችሁኝ እዳምጣችኋላሁ፤ መግባባትንም ለመፍጠር በቁርጠኝነት እሰራለሁ። እናንተ ብቻ እድሉን ስጡኝ ሲሉ መራጮችን ተማጽነዋል።

ትራምፕ ቢመረጥ ለሃብታሞቹ ጓደኞቹ ታክስ በመቀነስ በመካከለኛ ገቢ በሚኖሩ ላይ ጫና ያበረታል፤ ካሉ በኋላ በአነሰተኛ ገቢ ለሚተዳደሩት ኑሮን ለመደጎምና የጤናን መድህን ዋስትና ለማረጋገጥ ከልብ እሰራለሁ ብለዋል።

Skyline media

28 Oct, 19:52


ምክር ቤቱ በ2ኛ መደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ያሰሙትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያዳምጣል
************

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።

ስብሰባው የምክር ቤቱን 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ የያጸድቃል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መደበኛ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ የቀረበን የድጋፍ ሞሽን ያዳምጣል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን፣ የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ለመመዝገብ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እና የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።

Skyline media

28 Oct, 19:32


https://p.dw.com/p/4mK8y?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot

Skyline media

28 Oct, 14:32


አትቸኩል ❗️

💍

ሰባኪው አዲስ ተጋቢ ሙሽሮችን ወደ መድረክ ጠርቶ የጋብቻ ስነ ስነርዓታቸውን እያስፈፀመ፦

“ይህንን ጋብቻ የሚቃወም ካለ ወደ መድረክ ይምጣ አለ!”

በዚህ ጊዜ አንድ የ 3 ዓመት ህፃን ልጅ ያቀፈች እርጉዝ ሴት ከአዳራሹ መጨረሻ ወንበር ተነስታ በእርጋታ ወደፊት መጓዝ ጀመረች። ሙሽሪትም ያች ህፃን የያዘች እርጉዝ ሴት ወደፊት ስትመጣ ስታይ ሙሽራውን፦

“ ወራዳ ልክስክስ በሚስትህ ላይ ነው ልታገባኝ የነበረው?” አለችና በጥፊ መታው በጎን ያለውን በር ከፍታ እየሮጠች እና እተራገመች ሄደች። አብዛኛው ታዳሚ በተፈጠረው ክስተት ተገርሞ እያጉረመረመ እና እርስበርስ እያወራ በሚቀርበው በር እየወጣ ሄደ። ያች ህፃን የያዘች ሴት ፊት ወንበር ላይ ስትደርስ ከአንዱ ወንበር ላይ ቁጭ አለች። ሰባኪውም ግራ ተጋብቶ፦

“ምነው ችግር አለ እህቴ?” ሲል በታላቅ ትህትና ጠየቃት!

ሴትዮዋም “ኧረ ምንም ችግር የለም ጌታዬ! ትንሽ የመስማት ችግር ስላለበኝ በደንብ እንዲሰማኝ ከፊት ልቀመጥ ብዬ ነው አባቴ!” ስትል መለሰችላቸው!...

የነገሮችን ፍፃሜ በደምብ ሳናጣራ በመሰለኝና በደሳለኝ (Rule of thumb) ቸኩለን በግምት ድምዳሜ ላይ ከመድረስ እንቆጠብ። ማስተዋል አለመቻላችን እና መቸኮላችን ብዙ ነገር ያሳጣናል።

© Author፡ Unknown

[ሸጋ ቀን ተመኘሁላችሁ 🙏]

Skyline media

26 Oct, 16:35


https://www.youtube.com/live/P5RJHRpHjYA?si=XVQ7iF813hqmpyeq

Skyline media

23 Oct, 03:24


የኤርትራ ጦር ሰራዊት አባላት የባህር ሃይል አባላትን ጨምሮ ሶማሊያ መግባታቸውን ራዲዮ ኤርና ዘግቧል።

በሶማሊያ ከ300 በላይ የኤርትራ ወታደሮች ተሰማርተዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ3,000 በላይ የሶማሊያ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥ ስልጠና እየወሰዱ ነው።

ፎቶ፡ ራድዮ ኤርና

Skyline media

23 Oct, 03:20


https://www.facebook.com/share/v/vBWtbBxBum2K4EWh/

Skyline media

21 Oct, 09:43


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መተግበር ለኢትዮጵያ ምን ያስገኛል?
የናይል ተፋሰስ አገራት ለሚያስተሳስራቸው የዓለም ረጅሙ ወንዝ፤ የትብብር እና አጠቃቀም ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ሂደት የጀመሩት ከ27 ዓመት በፊት እ.አ.አ በ1997 ነበር። ሦስት አስር ዓመታት ገደማን የፈጀው ስምምነት የማርቀቅ፣ የድርድር እና የማፅደቅ ሂደት ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. የመጨረሻውን ደረጃ አጠናቅቆ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል። ኢትዮጵያ ለዓመታት ስትጥርበት የነበረው የዚህ ስምምነት ተግባራዊ መሆን ምን ጥቅም ያስገኝላታል?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

Skyline media

18 Oct, 17:10


https://www.youtube.com/live/sc7Bw7pdhrM?si=ncslK8hRzPj7Xo3u

Skyline media

18 Oct, 09:36


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ለሦስት ከፍተኛ ኃላፊነቶች ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል፡፡

በቅርቡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው በተሰየሙት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ቦታ የተተኩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የፍትሕ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰላማዊት ካሳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

Skyline media

18 Oct, 02:18


ከቡና ወጪ ንግድ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
*************

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ወደ ውጭ ከተላከ ቡና 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በሩብ ዓመቱ 115 ሺህ 851 ቶን በላይ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወደ ውጭ በመላክ 522 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ መገኘቱን ባለሥልጣኑ ገልጿል።

ከተገኘው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው የቡና ምርት መሆኑም ተጠቁሟል።

በተጠቀሰው ጊዜ 115 ሺህ 174 ነጥብ 75 ቶን ቡና በመላክ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱም ነው የተገለጸው።

በ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር የዚህ ዓመቱ በመጠን 69 በመቶ እና በገቢ የ46 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Skyline media

17 Oct, 17:29


#ኢትዮጵያ  #ሶማሌላንድ

የኢትዮጵያ መንግሥት ራስ ገዟ ሶማሌላንድ አዲስ አበባ ላይ ኢምባሲ እንድትገነባ በነጻ ቦታ ሰጥቷል።

የሶማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢሳ ካይድ፣ ለግዛቲቷ በተሰጣት ቦታ ላይ ትናንት የኢምባሲውን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

መንግሥት ለኢምባሲ መገንቢያ ቦታ መስጠቱቱ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ያለውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናክረው የግዛቲቷ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልጧል።

Skyline media

17 Oct, 17:15


የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ ያስፈልጋል - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን


የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተር ጄኔራሉ በአዲስ አበባ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ “በአፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር” የተመለከተ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

ባቀረቡት ገለፃም "ዓለም በአሁኑ ወቅት አንዱ ሌላውን ጥሎ የሚያልፍበት የበይ እና ተበይ አውድ ውስጥ ይገኛል" ብለዋል፡፡

የዓለም ነባራዊ ሁኔታ የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ ቀርፆ ወደ ተግባር መግባትን የግድ እንደሚልም ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዓለም አቀፋዊ አውድ ውስጥ አፍሪካ አንድነቷን ካላጠናከረች ልክ እንደ በፊቱ የሌሎች የመጫወቻ ሜዳ የመሆን ዕጣ እንደሚገጥማትም አንስተዋል፡፡

Skyline media

17 Oct, 15:12


አዳኒ ኢትዮጵያ በሽግግር ወቅት ላይ ነች እና ጊዜ ሰጡኝ ብሏል።

"ጊዜ ሰጥተነዋል፣ ኢትዮጵያ በሽግግር ወቅት ላይ ነበረች፣ የሥርዓት ለውጥ ተካሂዶ አዲስ አገዛዝ መጣ።ስለዚህ ይህ ግምገማ ከቀደምቶቹ ውስጥ አንዱ ቢሆንም በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ወደሚገኝበት ወሳኝ ወቅት አልፏል። እኛን የሚነኩ ሁኔታዎች ናቸው ስለዚህ ዓይኖቻችንን የምንከፍትበት ደረጃ ላይ ነን ሲሉ የአዳኒ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

በዚህ አመት መስከረም ወር ላይ ከኢትዮጵያ ወታደራዊ አዛዥ ብርሃኑ ጁላ ለቀረበለት መግለጫ ኦብነግ ምላሽ ሰጥቷል።

በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት የአዛዡን መግለጫ ለማብራራት እና ለማብራራት እየጠበቀ መሆኑን ተናግራለች።

በወቅቱ ለቢቢሲ ያነጋገራቸው የኦብነግ ቃል አቀባይ ጉዳዩ አስገራሚ መሆኑን ተናግሮ ሊቀበለው አልቻለም።

አብዱልቃድር ሀሰን ሂርሞጌ (አዳኒ) ኦብነግ ያንን አባባል እንደ ቅስቀሳ እንደሚቆጥረው ጠቁመዋል።

"ለእኛ እንግዳ እና አዲስ ነገር ነው የዛፎቹ እግር እየተረገጠ የኢትዮጵያ ሃይሎች ጠላት ሆነው ከኋላችን እንዳሉ ተጠቁሟል።

የኦብነግ መግለጫ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ብርሃኑ ጁላ የተሰጠ መግለጫን ተከትሎ ነው።

Skyline media

17 Oct, 15:10


የእነዚህ ድንጋጌዎች ውጤት ምንድን ነው?

"በሰላም አብረን እንድንኖር እና በአጠቃላይ ለስድስት አመታት ለሰላም ስንታገል የቆየው ብቸኛው ነገር ስለ ሰራዊቱ የተፃፉት ፅሁፎች አልተተገበሩም ፣ የተጎዱትን ህዝቦች መልሶ የማቋቋም ፅሁፎች። ጦርነቶቹ አልተተገበሩም፣ ውይይቱ ሊቀጥል የሚገባቸው ኮሚቴዎች ለችግሩ መሰረት እና ከየት እንደመጣ መፍትሄ የማፈላለጉ ሂደት ትንሽ ተጀምሯል እና አልቀጠለም ብለዋል አብዲቃድር ሀሰን

Skyline media

17 Oct, 15:08


እ.ኤ.አ. በ2018 ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት በፓርቲዎቹ መካከል የረዥም ጊዜ ጦርነት ያስቆመውን ኦብነግ በድጋሚ እየገመገመ ነው ብሏል። ድርጅቱ ከ6 አመት በፊት የተስማሙባቸው አንዳንድ ድንጋጌዎች ተግባራዊ እንዳልሆኑ ገልጿል።

በኢትዮጵያ እና በኦብነግ መካከል የተደረገው ስምምነት ምን ነበር?

ለቢቢሲ ልዩ ቃለ ምልልስ የሰጡት የኦብነግ ቃል አቀባይ አብዲቃድር ሀሰን ሂርሞጌ (ነጭ) እንደተናገሩት ስምምነቱ የኦብነግ አላማ የህዝቡና በጦርነት የሚፈልገው መሬት ሰላም እንዲፈልግ ነው ብለዋል።

"በተጨማሪም በሶማሌና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ችግር ወይም "በኦጋዴንያ የሚኖሩ የሶማሌ ህዝቦች" ችግር ከግጭቱ መንስዔ ተነስቶ መፍትሄ ፈልጎ ለአካባቢው፣ ለፌዴራል እና ለኦብነግ ኮሚቴዎች የችግሩን ምንጭ በማጣራት መላክ እንዳለበት ጠቁመዋል። ቆይ አንዴ።"

"በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖቻችን ወደ ሶማሊያ፣ኬንያ እና ጅቡቲ እና ሌሎች ሀገራት ጎረቤት ሀገራት እንዲመለሱ እና እንዲሰፍሩ እና የኦጋዴን ነፃ አውጪ ሰራዊት በድርጅቱ ውስጥ እንዲገባ" የኦብነግ ቃል አቀባይ አብዲቃድር ሀሰን ተናግረዋል። ሂርሞጌ (ነጭ)።

Skyline media

16 Oct, 17:27


የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከተፋሰሱ ሀገራት ጋር ለ13 ዓመታት ውይይትና ድርድር የተደረገበት ነው፡- ኢንጅነር ተፈራ በየነ
****

በቅርቡ ወደ ተፈፃሚነት የገባው የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ለ13 ዓመታት በሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ውይይትና ድርድር የተደረገበት መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አማካሪ ኢንጅነር ተፈራ በየነ ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ እንዲረቅ እና ድርድር እንዲደረግበት ከዚህ ቀደም በነበሩ ትብብሮች አባል ባትሆንም በታዛቢነት በነበራት ተሳትፎ ያነሳችው ሃሳብ መሆኑን ኢንጅነሩ ይገልፃሉ፡፡

እ.ኤ.አ በ1997 ተቀባይት ያገኘውን ጥያቄዋን ተከትሎ የተጀመረው የትብብር ማዕቀፍ ከመቅረፅ እና መደራደር ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን ማለፉን ተናግረዋል፡፡
በቀዳሚነት ከተፋሰሱ ሀገራት 3 አባላት ያሉት ፓናል ተቋቁሞ ድንበር ተሻጋሪ ውኃዎችን የሚጋሩ ሀገራትን በመመልከት እና ያሉ ሃሳቦችን በመገምገም ዛሬ ላይ መድረሱን አንስተዋል፡፡

በድርድር ልዑካን አማካኝነት የነበሩ የልዩነት አንቀፆች እየጠበቡ መምጣታቸውን ኢንጅነሩ ይጠቅሳሉ፡፡

ይህን ተከትሎ የውኃ ካውንስሉ እ.ኤ.አ በ2005 ያቀረበውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ በሚንስትሮች ደረጃ እ.ኤ.አ ከ2006 እስከ 2010 ድርድር መደረጉን ያስረዳሉ፡፡

በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ኢትዮጵያ ድርድሩን ስትመራ የቆየች ሲሆን፣ስምምነት ላልተደረሰባቸው ነጥቦች አማራጭ የረቂቅ ሰነዶችን በማቅረብ እና ንግግር በማድረግ ለጋራ ተጠቃሚነት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየችበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ስምምነቱን ተከትሎ የሀገራቱን የሕግ ባለሙያዎች ያካተተ የናይል የትብብር ማዕቀፍ ኮሚሽን በሕግ መቋቋሙን ገልፀዋል፡፡

በዚህም በሚኖር የሽግግር ጊዜ በናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ በኩል የተደረጉ ስምምነቶች እና ስራዎችን ጨምሮ ለኮሚቴው የማስተላለፍ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ ሥምምነትን ከተፋሰሱ ሀገራት ስድስቱ ፈርመው በፓርላማዎቻቸው ማጽደቃቸውን ተከትሎ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ተፈጻሚነት ገብቷል። ይህም ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት የባለቤትነት መብትን የሰጠ ሆኗል።

ስምምነቱን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ እና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያስጠብቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በአፎሚያ ክበበው

Skyline media

16 Oct, 10:11


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መተግበር ለኢትዮጵያ ምን ያስገኛል?
የናይል ተፋሰስ አገራት ለሚያስተሳስራቸው የዓለም ረጅሙ ወንዝ፤ የትብብር እና አጠቃቀም ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ሂደት የጀመሩት ከ27 ዓመት በፊት እ.አ.አ በ1997 ነበር። ሦስት አስር ዓመታት ገደማን የፈጀው ስምምነት የማርቀቅ፣ የድርድር እና የማፅደቅ ሂደት ባለፈው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 3/2017 ዓ.ም. የመጨረሻውን ደረጃ አጠናቅቆ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል። ኢትዮጵያ ለዓመታት ስትጥርበት የነበረው የዚህ ስምምነት ተግባራዊ መሆን ምን ጥቅም ያስገኝላታል?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

Skyline media

13 Oct, 12:15


ከተባበርን ጠንካራ ቀጣና መፍጠር እንችላለን - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተባበርን እና ከተደጋገፍን ሁላችንም በጋራ በመልማት ጠንካራ ቀጣና መፍጠር እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት ገብቷል፡፡

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በናይል ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተደረገው የማዕቀፍ ስምምነት ወደ ተፈጻሚነት መግባት ለጋራ ብልጽግናችን የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል፡፡

በናይል ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተደረገው የማዕቀፍ ስምምነት (ሲ ኤፍ ኤ) ወደ ተፈጻሚነት መግባት የአባይ ወንዝ ውኃን በፍትሐዊነትና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የተሄደበትን ረጅም ጉዞ የቋጨ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ ወደ ተፈጻሚነት የገባበት የዛሬው ቀንም ለተፋሰሱ ሀገራት ታሪካዊ መሆኑን ገልጸው÷ እውነተኛ ትብብርን ለማጎልበት በጋራ ለምናደርገው ጥረት መሰረት ነው ብለዋል፡፡

የማዕቀፍ ስምምነትቱ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱ እንደ ናይል ወንዝ ተጠቃሚ ሀገራት ያለንን ትስስር ያጠናክርልናል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም የጋራ ሃብታችን የሆነው የናይል ወንዝ ለሁላችንም ጥቅም እንዲውል ያስቻለ ነው ብለዋል።

ይህ የማዕቀፍ ስምምነት እውን እንዲሆን ላስቻሉ አካላትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል ስምምነቱን ያልፈረሙ አካላት እንዲፈርሙ ጥሪ አቅርበው÷ ከተባበርን እና ከተደጋገፍን ሁላችንም በጋራ በመልማት ጠንካራ ቀጣና መፍጠር እንችላለን ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

Skyline media

13 Oct, 12:04


በተጨማሪም ስምምነቱ ለሁሉም የናይል ተፋሰስ ሀገሮች ሕጋዊ መብት ዕውቅና እንደሚሰጥ ገልጸው÷ ሁላችንንም ለውኃው ፍትሐዊ ክፍፍልና ለዘላቂ አጠቃቀም ተገዥ ያደርገናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
እያንዳንዱ ሀገር የሌላውን መብት ሳይጋፋ በጋራ የሚያድግበትና የሚበለጽግበት የሁሉንም መጻኢ ተስፋ እንደሚወክልም አመላክተዋል፡፡
ዘላቂ ልማት የትብብር ስምምነቱ ማዕከል ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ የናይልን የውኃ ሀብት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶችም እንዲሆን አድርገን መጠቀም የሚያስችል ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ስምምነቱ ናይልንና ከባቢውን እንድንጠብቀው፣ ውኃውን የወደፊቱን ተጠቃሚ በማይጎዳ መልኩ እንድንጠቀም ያስገድደናል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
ሁሉም የተፋሰሱ ሀገሮች ስምምነቱን  እንዲቀላቀሉትና መርሆዎቹን በታማኝነት እንዲፈጽሙ ጥሪ ያቀረቡት ሚኒስትሩ÷ የናይል ወንዝ የተስፋ ምንጭ የሚሆንበትን፣ ተግዳሮቶችን በጋራ የምናቃልልበትና ለራሳችንና ለመጪው ትውልድ የተሻለ  ዓለም የምንፈጥርበትን መጻኢ ጊዜ ለመገንባት በጋራ እንሥራ ብለዋል፡፡
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በትብብር ጉዟቸው ላደረጉት አስተዋጽኦ አመሥግነው÷ ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ በምናደርገው ጉዞም አጋርነታቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

Skyline media

13 Oct, 12:04


የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሐብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ስምምነቱ ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን አስመልክተው የናይል የትበብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈጻሚነት ማብሰሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም÷ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ከዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ  ወደ ተፈጻሚነት መግባቱን አስታውቀዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የዛሬው ቀን በናይል ተፋሰስ ታሪክ ልዩ መሆኑን አንስተው÷ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ የተፋሰሱ ሀገራት መንግሥታትና ሕዝቦች ለዚህ ታሪካዊ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ለዚህ ስምምነት ከጥንስሱ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በተለያየ መንገድ አስተዋጽዖ ላበረከቱ  ኢትዮጵያውያንም ሚኒስትሩ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የናይል የትብብር ስምምነት ተፈጻሚ መሆን የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽንን መመስረት እንደሚስችል ጠቅሰው÷ ኮሚሽኑ ለሁሉም ተጠቃሚነት የናይል ወንዝን የማስተዳደርና የመጠበቅ ኃላፊነት ይወስዳል፤  የትብብሩም የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ የሕግ ማዕቀፍ፣ የናይልን ወንዝ ለሁላችንም ጥቅም ለማዋል የጋራ ቁርጠኝነታችን ምስክር እንዲሁም የውኃ ሀብቱን በእኩልነትና ፍትሐዊነት የመጠቀም መብት ማረጋገጫ የሚሆን ስምምነት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የናይል የውኃ አጠቃቀምን በተመለከተ የነበረውን  ኢ-ፍትሐዊነት ያስተካክላል፤ የሁሉንም የናይል ሀገሮች የጋራ ሀብት ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

Skyline media

10 Oct, 17:16


https://www.youtube.com/live/fCDUw5B_3Rk?si=jeNa1tCesOkIxbhR

Skyline media

09 Oct, 17:54


ወ/ሪት ሰሎሜ ታደሰ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቃባይ እያሉ ስለ ኤርትራ ወደቦች የሰጡት ምላሽ

Skyline media

08 Oct, 22:08


የአዲስ አበባ የሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስድስቱ ኮሪደሮች እና ሁለቱ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደሮች የትኞቹ ናቸው?
***

• 
ካዛንቺስ፣ መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ፣ ቸርችል፣ አራት ኪሎ፣ እስጢፋኖስ


•   ሳውዝጌት፣ መገናኛ ፣ ሃያሁለት፣ መስቀል አደባባይ


•  ሲኤምሲ፣ ሰሚት ጎሮ፣ ቦሌ አየር ማረፊያ ቪአይፒ ተርሚናል፣ አዲስ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚብሽን ማዕከል

•  ሳር ቤት፣ ካርል አደባባይ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አቦ ማዞሪያ፣ ላፍቶ አደባባይ፣ ሃና ፉሪ ኮሪደር


•  አንበሳ ጋራዥ፣ ጃክሮስ ጎሮ

•  አራት ኪሎ፣ ሽሮ ሜዳ እንጦጦ ማርያም፣ ጉለሌ እጸዋት ማዕከል


•  የቀበና ወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት

•  እንጦጦ፣ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ኮሪደር ልማት


   በአጠቃላይ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት 2817 ሄክታር የቦታ ስፋት ሲኖረው 132 ኪሎሜትር ርዝመትን የሚሸፍን ነው።

Skyline media

06 Oct, 18:07


በአዲስ አበባ ከተማ በበርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ተሰምቷል።

ከምሽት 2 ሰዓት በኃላ በርካታ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ነበር።

ህፃዎች ላይ የነበሩ ሰዎችም በደንብ ንዝረቱ የተሰማቸው ሲሆን በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉ ነዋሪዎች ከስጋት አንጻር ወደ መሬት ወርደው ተሰባስበው ነው የሚገኙት።

ከአዲስ አበባ ውጭም በሌሎች ከተማዎች / ቦታዎች መሰል ሁኔታ እንደነበር ከቤተሰቦቻችን በሚላኩ መልዕክቶች ተረድተናል።

Skyline media

03 Oct, 05:43


#አማራ

መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ኦፕሬሽን መጀመሩን
የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኮለኔል ጌትነት አዳነ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በርካታ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተዋል።
የክልሉ ሰላም ሙሉ ለሙሉ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እስኪመለስ ድረስ መከላከያ ሰራዊት ከክልሉ እንደማይወጣ ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በፋኖ ሀይሎች እና በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች መካከል ከአንድ አመት በላይ ውጊያ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።

በዚህም ጉዳዩ እስካሁን በድርድር ይፈታል በሚል ብዙ ጥረት እንደተደረገ ገልፀው መከላከያ ሰራዊት ከዚህ በኋላ አይታገስም፣እርምጃ ወደ መውሰድ ገብቷል ብለዋል።

በዚህም ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ ከፋኖ ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ በርካታ ሰዎች እና አመራሮች መታሰራቸውን ገልፀዋል። ኦፕሬሽኑ ይቀጥላል ብለዋል።

በተመረጡ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ከትናንት በስተያ ጀምሮ የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይሎች ከነገ ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ትዕዛዝ እያስተላለፉ ይገኛሉ።