Seyum Teshome ስዩም ተሾመ @seyum_teshome Channel on Telegram

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

@seyum_teshome


Seyum Teshome ስዩም ተሾመ (Amharic)

ስዩም ተሾመ (Seyum Teshome) በስርዓተ መገናኛ አማርኛ ገጽ የአማርኛ ዜናዎችን እና ቁምነገሮችን እንዴት እንቆይላለን? የSeyum Teshome ስዩም ተሾመ የቴሌግራም ክፍል ነው። በዚህ ቴሌግራም ክፍል የምፅሑႈበት ትንተና ስዩም ተሾመ ስቃያችን ይኖራል በምግብ በደህና መግብᇂያ እና መተዳደሪያ እንዲመሳሰሉ ያግኙናል። ስዩም ተሾመ ገጽ ገጽ የአማርኛ ገጽ የአማርኛ ምሽት እና መልክያ ላሙበት ነው። እያንዳንዱም አማርኛ እና አማርኛ ግን አገርኛ እያንዳንዱም ስለሆነ በመሆኑ እንህናለን። ስዩም ተሾመ ከዚህ ላሉት የጸሁት ሲሆን፣ ዜና የሚያስፈልገው እና በአንድነትመቀመጥ ቴሌግራም የቴሌግራም ግብር አለ። በወንጌል ፖሊስት ላይ ስለ መሪጋም፣ ዜናዉን እና ተጠቃሚውን ከፍተኛ ትምህርት ይቀንሱ።

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

18 Feb, 17:59


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ጋር እያደረጉት ባለው ውይይት፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ተከትሎ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በቤልጅየም እየተካሄደ ያለው 6ኛ የውይይት መድረክ ያለው ለሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው። ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ደግሞ አንድ ቁልፍ ሚስጥር አለ። ይህን ሚስጥር ለመረዳት በቅድሚያ የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነት ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የመጣበትን መንገድ መለስ ብሎ መቃኘት ያስፈልጋል።

ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈፀመ ስድስት (6) ቀናት በኋላ ከአውሮፓ ምክር ቤት (EU Council) አፈትልኮ የወጣ ሰነድ እንደሚያሳየው የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካኖች በባሰ መልኩ የህወሓት ደጋፊዎች ነበሩ። ህወሓት 250ሺህ ጦር ሰራዊት እንዳለውና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይህን ግዙፍ ጦር ፈፅሞ መቋቋም እንደማይችል በግልፅ ይጠቁማል። ከህወሓት ጋር የሚደረገው ጦርነትን ተከትሎ የኦሮሞ ፅንፈኞች አመፅ በማስነሳት ኢትዮጵያን ያፈርሷታል በማለት በሰነዱ ላይ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት እና አባል ሀገራቱ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉትን ግፍና በደሎች ፈፅመዋል፦
• ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ አቋረጠ
• የኢትዮጵያን ምርጫ አልታዘብም ብሏል!
• የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ ልዩ ስብሰባን እንዲያደርግ ጠየቀ
• የአውሮፓ ፓርላማ ማዕቀብ እንዲጣል ጠይቋል
• በG7 ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት ከተመድ እና አሜሪካ ጋር ሆኖ በኢትዮጵያ ላይ ጫና አድርጓል።
• የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እና ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
• በህዳሴው ግድብ ድርድር ዙሪያ ግብፅን ደግፏል
• ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችውን $100 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ሰርዛለች
• ጀርመን በኢትዮጵያ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን አቋርጧል
• የስሎቫኪያ መሪ በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ለተባበሩት መንግስታት ይፋዊ ደብዳቤ ፅፋለች
• ዓለምአቀፉ የገንዘብ ፈንድ (IMF) የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ አልሰጥም በማለት የሀገሪቱ የብድር ተዓማኒነት እንዲያሽቆለቁል አድርጓል

ታዲያ ይሄን ሁሉ ግፍና በደል የፈፀሙት አካላት እንዲህ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ክንፍ ያለ ፍቅር ውስጥ የወደቁበት ሚስጥር ምንድነው?
አንደኛ፦ ህወሓት አከርካሪው ተመትቶ መሸነፉ፣
ሁለተኛ፦ የተሸጠው ሰይጣን (የእስረኞች መፈታት)
👉ለምንና እንዴት የሚለውን ለመረዳት ይሄን ሊንክ ተጭነው ሙሉ ቪዲዮውን ይመልከቱ
https://youtu.be/K0g06DuDyLQ

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

18 Feb, 17:58


የሩሲያ ባሕር ኃይል ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ!

#Ethiopia : የሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል ልዑክ የሁለቱን አገራት የዘለቀ ትብብር መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ፡፡ሁለቱ ሀገራት ለረጅም አመታት የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያላቸው ሲሆን፤ የጉብኝቱ ዓላማም የትብብሩ አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የልዑኩ መሪና በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን ተልዕኮ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያዊያን የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባሕር ኃይል ኢንዲኖራትና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ ዐቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሩሲያ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የዛሬ ሦስት ዓመት መቋቋሙን ገልፀው በተማረ የሰው ኃይል ለማደራጀት እየተሰራ ስለመሆኑ ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡

"ከሌሎች አገራት የባሕር ኃይሎች አደረጃጀት እና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልምድ በመውሰድ፤ የተሰጠንን አገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ተሰርቶና በመከላከያ ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷል"ም ብለዋል፡፡

ኮሞዶሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከባሕር ኃይሏ ማግኘት የምትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌደሬሽን ባሕር ኃይል ጋር በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

18 Feb, 17:58


በአፍሪካ እና አውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው ሀሳቦች ተቀባይነት አግኝተዋል- አምባሳደር ሂሩት ዘመነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው የአፍሪካ እና አውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው በርካታ ሀሳቦች ተቀባይነት ማግኘታቸውን በቤልጂየም፣ ሉክሰንበርግና በአውሮፓ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለጹ። አምባሳደሯ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በጋራ ጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ያነሳቻቸው የትብብርና…

https://www.fanabc.com/በአፍሪካ-እና-አውሮፓ-ህብረት-የጋራ-ጉባኤ/

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

18 Feb, 17:56


ይህ ድንቅ "An Animated History Of Poverty" የተሰኘ የBBC4 ዶክመንተሪ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚስተዋለው ስር የሰደደ ድህነት ዋና መንስኤው በተለያዩ ሀገራት/ቡድኖች ቁጥጥር ስር የሚገኘው የሃብት ክምችት እንደሆነ ይገልጻል። የከፋ ድህነት መንስኤው ኢኮኖሚያዊ ሃብትና ንብረት በጥቂት አካላት ቁጥጥር ስር በመውደቁ ምክንያት እንደሆነ ጥንታዊ ታሪኮችን እና የሥነ ምጣኔ ምሁራንን እያጣቀሰ መሳጭ በሆነ መልኩ ያቀርባል። ሙሉ ቪዲዮውን በጥሞና ብትመለከቱ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ዕውቀት ታገኙበታላችሁ።

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

17 Feb, 19:38


ከወንድሜ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሁለትዮሽ ግንኙነት እና አኅጉራዊ ጉዳዮች ላይ ስለ ነበረን ፍሬያማ ውይይት ምስጋናዬ ይድረስ። በአገሮቻችን መካከል ያለው የዳበረ ግንኙነት ለቀጣይ ትብብር ጠንካራ መሰረትን የጣለ ነው።

Thank you, my brother President Emmanuel Macron, for a fruitful conversation about bilateral relations and continental issues. The long-standing relationship between our countries provides a solid foundation for future collaboration.

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

17 Feb, 19:37


በአፍሪካ ኅብረት እና የአውሮፓ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተሳትፎ በፎቶ

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

17 Feb, 19:37


#የኔታ_ትንታኔ #ቅምሻ #ኦሮማራ #ኢትዮጵያ
ሙሉ ፕሮግራሙን ለመመልከት ይሄን ሊንክ ይጫኑ⤵️
https://youtu.be/Pc1cvibnmCw
አዲሱን ቻናላችንን
#Subscribe ⤵️ #Share⤵️ #Follow⤵️
https://youtube.com/channel/UCqSaopvYkuENnzU8__ei2gA

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

17 Feb, 19:36


U.S. Defense Secretary Lloyd Austin, attending a NATO meeting in Brussels, told reporters that the reports of shelling are “certainly troubling” and that the United States is still gathering details. “But you know we’ve said for some time that the Russians might do something like this in order to justify a military conflict, so we’ll be watching this very closely.”

In Moscow, the Russian government ordered the expulsion of the U.S. Embassy’s second-ranking diplomat, Deputy Chief of Mission Bart Gorman, the State Department confirmed Thursday. No reason was immediately given for the expulsion of Gorman, whom a department spokesperson described in a statement as “a key member of the Embassy’s senior leadership team.” The statement called the move “unprovoked” and “an escalatory step” and said the United States is “considering our response.”

https://www.washingtonpost.com/world/2022/02/17/ukraine-russia-putin-nato-munich/

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

17 Feb, 19:36


ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ሁነው ተሾሙ
*************
አማራ ክልል መንግስት ክልሉ የገጠውን የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ በክልሉ ያሉ የፀጥታ መዋቅሩ ጉድለቶችን እና ጥንካሬዎችን በዝርዝር ግምገማ ሲያካሂድ መቆየቱን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ አስታውቋል። በመሆኑም ክልሉ የገጠመውን የህልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የህዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ አድርጓል።
ስለሆነም፦
1- የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር የፀጥታ አማካሪ

2- የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ሁነው ተሹመዋል!
Via Ethiopian Broadcasting Corporation

Seyum Teshome ስዩም ተሾመ

17 Feb, 14:14


ከክሪስታሊና ጆርጂየቫ ጋር ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ ተቋም ጋር ያላትን ትብብር ስለ ማጠናከር እና የለውጡን ሂደት በቀጣይነት ስለ መደገፍ ተወያይተናል።

Grateful for the discussion with Kristalina Georgieva on forging strengthened partnership with IMF as Ethiopia resumes reforms she fought hard to maintain despite adversities.